Monday, July 18, 2011

ስሙ ከብዶት ሞተ

ኃይለ ገብርኤል (ከአራት ኪሎ)
የጥቁር ህዝቦች ሁሉ መመኪያ እና መኩሪያ የሆነውና በትውልድ ለትውልድ ቅብብሎሽ በደማቅ አሻራነቱ ዛሬም የሚወሳው ታላቁ ታሪካችን ሀገራችን ባህር ተሻግሮና ድንበር ጥሶ በመጣው የጣልያን ጦር ላይ ያስመዘገበችው ድል ነው። በወቅቱ ለጣሊያኖች ሽንፈት ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የጀግንነት ኩራት ከነበሩት የጦር መሪዎች መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሹ አሉላ አባ ነጋ ናቸው። አንድ ጣልያናዊ ዜጋ በአጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ጀግኖች የደረሰባቸውን ሽንፈት በተለይ ደግሞ የጦር መሪው የአሉላ አባ ነጋን አንፀባራቂ ገድል ከመጻሕፍት ካነበበ በኋላ አንዳች የሀፍረት ስሜት ይወረዋል። ይህንን ስሜት ለማስወገድም በውስጡ የበቀል ስሜት ይፈጠርበታል። ከዚያም ቁጭቱን ለመወጣት የሚያስችሉትን አማራጮች ሲያወጣ እና ሲያወርድ ከቆየ በኋላ ዓላማዬን ያሳካልኛል ያለውን አማራጭ መረጠ። ከዚያም በቤቱ የሚያሳድገውን ውሻ “አሉላ” ብሎ ስም ያወጣለታል።
ይህንን ውሻ ባለቤቱ ከስራ ሲመጣ ሁል ጊዜ ያጫውተዋል ስሙንም ለሰሚ እስኪሰለች ድረስ በየአጋጠሚው ሁሉ ሲጠራው ያመሻል። ለውሻው ያወጣለትን ስም በሰፈሩም በመስሪያ ቤቱም ያለው ሰው ሁሉ እንዲያውቅለት እና “እሰይ አበጀህ የኛ ልጅ” እንዲባል ለሁሉም ይናገራል። አሉላ እንዲህ እና እንዲያ አደረገ፣ አሉላ ዘለለ፣ አሉላ ተገለበጠ . . .ሰውየው የሚታወቅባቸው የዘወትር ዜማዎቹ ናቸው።


አንድ ቀን የውሻው ባለቤት ከስራ ሲመለስ ጠዋት በሰላም ትቶት የሄደውን ውሻ ሞቶ ያገኘዋል። በሁኔታው በጣም ይበሳጭና ውሻውን ለሚያውቀው ሁሉ “አሉላ” ሞተ እያለ አያረዳ በሁኔታውም በጣም ማዘኑን ይገልፅ ሰለ አሟሟቱም ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ያብራራላቸው ያዘ። የሰሙትም እንደዚህ ሆኖ ይሆናል እንደዚያ አጋጥሞት ይሆናል እያሉ የየራሳቸውን መላምት ማስቀመጥ ቀጠሉ። በመስሪያ ቤቱ ውስጥ አብራው የምትሰራ እና የውሻውን ስም ከሰማችበት ሰዓት ጀምሮ ቆሽቷ ሲያር የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊት ውሻውን ለሞት ሊያበቁት ከሚችሉት ምክንያቶች መካከል አስተያየቷን እንድትናገር ዕድሉ ይሰጣትና ምን ትናገር ይሆን ብለው ሲጠብቋት በውሻው ሞት አንጀቷ ቅቤ የጠጣው እህቴም እንደሌሎቹ ምክንያቱን ለመናገር ምንም ጣራ ጣራ ማየት፣ ምንም ፀጉር ማሻሸት ሳያስፈልጋት በፍጥነት እና ባጭር ቋንቋ ውሻው የሞተው ስሙ ከብዶት ነው አለቻቸው። 


ስም ህይወት ያለቸውንና የሌላቸውንም ፍጥረታት አንዱን ካንዱ ለመለየት የምንጠቀምበት የመግባብያ መሳሪያ ነው። የሌሎቹን ፍጥረታት ትተን የሰው ልጅን ብቻ እንኳን ብንመለከት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ለማከናወን የተለያዩ ስሞችን ያወጣል ይሰይማል። የአንዳንድ ሰዎችን መጠሪያ ስም ብናይ ሦስት እና ከዚያም በላይ ሰሞች ያሏቸው ሊያጋጥሙን ይችላሉ። አንድ ሰው የቤት ስም፣ የት/ቤት ስም እና የክርስትና ስም ሊኖረው ይችላል። አንዳንድ ጊዜም የሰውዬውን ተክለ ሰውነት በመመልከት ለምሳሌ ወፍራሙን ሰው “ቀጮ”፣ አጭሩን “አስራት” እንዲሁም የግለሰቡን አመለካከትና አስተሳሰብም ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ልዩ ስሞች ሊወጡለት ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪም ግለሰቡ እንደተሰማራበት የሙያ ዓይነት የብቃት መለኪያ የሆኑ የተለያዩ የማዕረግ ስሞችም ሊሰጡት ይችላሉ። እነዚህ የማዕረግ ስሞች እና የግለሰቦቹ ምግባር ሲሰማሙም ላይስማሙም ይችላሉ። ማዕረጋቱ በግብር የተገለጡ እንደሆነ ያሰደስታል ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ያሳፍራል ያዋርዳልም።


በመግቢያችን ላይ የተመለከትነው ጣልያናዊ ለውሻው ያወጣለት ስም የውሻውን ታማኝነትና ጀግንነት ለመናገር ፈልጎ አልነበረም፤ እሱና መላው የሃገሩ ዜጎች በታሪካቸው መቼም በማይረሱትና መላው ዓለም በሚያውቀው በኢትዮጵያውያን አይበገሬነት የደረሰባቸውን መራራ ሽንፈት ለማቃለል አስቦ እንጂ። በአሁኑ ወቅትም ያልተገባንን እና ያልተፈቀደልንን ስም የያዝን እና ጭብጥ ለማትሞላ ምግባራችን የሰማይ ስባሪ የሚያክል ስም ተሸክመን ያለ እፍረት ባደባባይ ስንታይ የምንውል እጅግ ብዙ ሰዎች እኮ አለን። ስማችን እኛን ሳይገልፀን እኛም ስማችንን ሳንመስለው በሰውም በፈጣሪም ዘንድ የተጠላ እና የተናቀ ስራን እየሰራን እንደ ውሻው ስማችን በቁማችን የገደለን። 


በአለማዊውም በመንፈሳዊውም ህይወታችን በተለያዩ መስፈርቶች አማካኝነት እንደየብቃታችን እና ቅድስናችን በአንድ ቃል፣ በሁለት ቃላት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በዓረፍተነገር የሚገለፁ የማዕረግ ስሞች ይሰጡናል። በየትምህርት ቤቱ ከጀማሪ መምህር እስከ መሪ መምህር፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከረዳት ምሩቅ እስከ ሙሉ ፕሮፌሰር፣ በፖሊስና በመከላለያ ሰራዊት ከምክትል አስር አለቃ እስከ ጀነራል፣ በቤተ ክህነትም ከዲያቆን እስከ ፓትርያርክ ያሉት ማዕረጋት ለዚህ አስረጅ ናቸው።


ከዚህም በተጨማሪ ብዙ የማዕረግ ሰንሰለት ያልወጣላቸው ወይም የሌላቸው የስራ አይነቶችም አሉ እንደ ጋዜጠኛ (የትናንቱም የዛሬውም ያው ጋዜጠኛ እንጂ አስር አለቃ ጋዜጠኛ፣ ሃምሳ አለቃ ጋዜጠኛ አይባልም)፣ ደራሲ፣ አርቲስት፣ ሰዓሊ፣አትሌት፣ ፀሐፊ ወዘተ.። ይህም ማለት ምንም እንኳን አብዛኞቹ የማዕረግ ስሞች ህግ እና ስርዓት ተቀረፆላቸውና መስፈርት ወጥቶላቸው የተቀመጠ ቢሆንም አንዳንዶች ግን ጀማሪውን ከአንጋፋው የማይለዩ የአምናውንም የዘንድሮውንም ሁሉንም በደምሳሳው በአንድ የሚጠሩም አሉን ማለት ነው።


የማዕረግ ስሙ በባሌም ይገኝ በቦሌ ዋናው ነገር የትኞቹ ወይም እነማን ናቸው ስራቸውን አክብረውና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህግና ስርኣትን አክብረው ሌት ተቀን የሚያከናውኑትን መልካም ስራ ስማቸው የገለጠላቸው? ወይም ስማቸውና ግብራቸው ሰምና ወረቅ የሆነላቸው? እነማንስ ናቸው ድካምና ስልቹነት፣የስነ-ምግባር ብልሹነትና ራስ ወዳድነት ጎጆ ሰርቶባቸው በሰማይም በምድርም የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ህግ እና ስርዓት እየጣሱ ለሚሰሩት በሰውም በፈጣሪም  ዘንድ ለተጠላ ተግባራቸው ስማቸው መሸፈኛ ካባ የሆናቸው እና እንደዚያ ገበሬ እህሉን ገና ሳይወቃ በክምር ላይ እያለ በብድር የጨረሰውና ክምሩንም ተመልክቶ “አንቺ ክምር ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል” እንዳለው ያሉ የሚመስላቸው ነገር ግን ባዶ የሆኑና ስማቸው ከብዷቸው በቁማቸው የሞቱ?


በተለይ ዛሬ ዛሬ በመንፈሳዊው ዓለም የምንመለከተውና የምንታዘበው ነገር በቃላት ስብስብ በተሰራ ዓረፍተ ነገር ተገልፆ በአራት ነጥብ የሚዘጋ አይደለም። የሐዋርያትን ፈለግ ተከትላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሐዋርያዊ አገልግሎት ያመች ዘንድ እንደ ብቃታቸው መንፈሳዊ ሰዎችን በተለያዩ ማዕረጋት ትሾማለች። አስራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሏቸው የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም። ወንድሞች ሆይ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤ እኛ ግን ለፀሎትና ህዝቡን ለማገልገል እንተጋለን። ይህም ቃል ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኛቸው(የሐ. ስራ 6፡2-6)። 


በዚህም መሰረት ከመንፈሳውያን መካከል በመልካም የተመሰከረላቸውን፣ መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን እና ለአገልግሎት ፈቃደኛ የሆኑትን መንፈሳውያን ለእያንዳንዱ ማዕረግ ተስማሚውን መንፈሳዊ መስፈርት አዘጋጅታ ከዲያቆን እስከ ፓትርያርክ ድረስ ትሾማለች። የዲያቆናትን መሾሚያ እንኳን ከሆኑት መካከል የተወሰኑትን ብናይ ንጹሐን የሆኑ፣ ሕዋሳታቸውን የሰበሰቡ፣ ላንዱ አንድ ላንዱ አንድ ጧት እንድ ማታ አንድ እያሉ ነገር የማይለዋውጡ፣ መጠጥ የማያበዙ፣ ኃላፊውን ገንዘብ የማይወዱ፣ ከክህደት ከኑፋቄ ንጹህ በሆነ ልቡና የሃይማኖታቸውን ትምህርት አጽንተው የያዙ መሆን እንዳለባቸው ቃለ ዓዋዲው ያስቀምጣል።


እንግዲህ ዲያቆን ከሚለው የማዕረግ ስም ጀረባ ከላይ የጠቀስናቸውና ሌሎችም ተጨማሪ መንፈሳዊ ኃላፊነቶች መኖራቸው ግልጽ ነው። ስለዚህ ዲያቆን እገሌ ተብለው የሚጠሩና በአገልግሎታቸው ስፋትና መጠን የተመሰገኑ፣ ትኅትናን ከቅንነት በማስተባበራቸው ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ፣ ስለለበሱት ስጋ ሳይሆን ስለ መንፈሳዊ ኃላፊነታቸው የሚገዳቸው ባጠቃላይ ሃይማኖትን ከምግባር በማስተባበር ትክክለኛውን መንፈሳዊ ሕይወት የሚኖሩ ወንድሞች ስማቸው ከግብራቸው ድርና ማግ የሆነላቸው ናቸው። እንደነዚህ ያሉትን ወንድሞች በቀላሉ ማግኘት ዛሬ ዛሬ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። በተቃራኒው ደግሞ ሲጀመር ገና እራሳቸው መንፈሳውያን ሳይሆኑ መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ የገቡ፣ አገባባቸውም መንፈሳዊውን ህይወት ለስጋዊ ህይወት ማሳለጫነት ለመጠቀም እንጂ መንፈሳዊ ዋጋ ለማግኘት ያልሆነ፣ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴአቸው የስነ-ምግባር ብልሹነት የሚሰተዋልባቸው አሉ። እንደነዚህ ያሉት ወንድሞች ከራሳቸውም አልፈው ዲቁናን ያስነቅፋሉ። ስሙን ይጠሩበት እንጂ ስሙ በፍፁም እነርሱን አይገልጻቸውም። ዲቁናን እንደ ጭምብል ይጠቀሙበታል፣ ዲቁናን ይገለገሉበታል እንጂ ዲቁናን አያገለግሉበትም። ለእንደእነዚህ ያሉ ወንድሞች ጊዜው የአገልግሎት ሳይሆን የአገልጋዮች ነው። በመሆኑም እንደእነዚህ ያሉቱ ዲያቆን የሚለው ስማቸው ከብዷቸው በቁማቸው የሞቱ ናቸው። 


ቀደም ባሉት ጊዜያት መንፈሳዊ ዝማሬን የሚያሰሙን ዘማርያን እኅቶችና ወንድሞች ቁጥራቸው አናሳ ይሁን እንጂ መዝሙራቱ ልዩ ነበሩ። መዝሙራቱ ነገረ ሃይማኖትን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክን፣ የቅዱሳንን ተጋድሎና ክብርን፣ ትውፊትን፣ የክርስትና ስነ-ምግባርን በረቀቁ እና ስሜትን በሚነኩ ምርጥ ቃላት አማካኝነት በቀላሉ በሰማዕያን ልቡና ታትሞ እንዲቀመጥ የማድረግ መንፈሳዊ ኃይል ያላቸው ናቸው። የመዝሙራቱ ግጥም እና ዜማም አገልግሎቱ ለቤተክርስቲያን ነውና የቤተ ክርስቲያንን ድንበር ያላፈረሰ እና ከሌሎችም ልዩነቱን የጠበቀ ነው። ዛሬ ዛሬ ግን ዘማርያኑ በዙ መዝሙራቱም እንዲሁ። 


የዘማርያኑም ሆነ የመዝሙራቱ መብዛት በራሱ ችግር የለውም። የዘማርያኑ መብዛት ግን በዝማሬው አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ነፍሳት በመጨመር ፋንታ ስጋዊ እና ደማዊ የሆነ ውድድር እና ፉክክር በመካከላቸው እንዲፈጠር አደረገ። በዚህ ውድድር ሳቢያም መዝሙራቱ ህግ መር ከመሆን ወደ ገበያ መርነት ተሸጋገሩ። የመዝሙራቱ ልጓም ህገ ቤተክርስቲያን መሆኑ ቀረና ገንዘብ ሆነ። ከዚህ ጋር ተያይዞ መዝሙሩ በሚዘመርበት ወቅት የአለባበስና የእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል እንቅስቃሴ የራሱ ስርዓት አለው። ይሁን እንጂ በአንዳንድ “ዘማሪያን” ዘንድ የሚዘወተረው እና የምንመለከተው ግን በዕውቀትም ይሁን ያለዕውቀት ከስርዓት የወጣ ነው።


መዝሙር ሰው ለልዑል እግዚአብሔር ስላደረገለት ነገር ምስጋና የሚሰዋበት፣ ስለተቸገረበት ጉዳይ ልመና የሚያቀርብበት፣ ስለ በደሉ ደግሞ ይቅርታንና ምሕረትን የሚጠይቅበት የአገልግሎት አይነት ነው። በመሆኑም ለሰው ልጅ ሁሉ ከልዑል እግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው። እዚህ ላይ ሁሉም ሰው መዘመር ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። በማያሻማ መልኩ መልሱ አዎ ነው። ነገር ግን መዝሙር በመንፈስ ከፈጣሪያችን ጋር የምንገናኝበት በመሆኑ ዘማሪው በመጀመሪያ ደረጃ መንፈሳዊ መሆን ይጠበቅበታል። የዘማሪው መንፈሳዊነት ምን ዓይነት መዝሙር መዘመር ኦንደሚገባው፣ መዝሙሩን ለማዘጋጀት የሚያሰፈልጉት ጥንቃቄዎች የትኞቹ እነደሆኑ፣ መዝሙሩን በሚዘምርበት ወቅት ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮች የትኞቹ እነደሆኑ እንዲለይ ያስችለዋል። ነገር ግን መዝሙርን አንድ ሰው እራሱን(ለግሉ) ከፈጣሪው ጋር ለማገናኘት መዘመር እና በመዝሙር አማካኝነት ሌሎች ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ ማድረግ በእጅጉ ይለያያሉ። ሁለተኛው ዓይነት የመዝሙር አጠቃቀም በመዝሙር የማገልገል ፀጋን ይፈልጋል፤ ያለዚህ የፀጋ ስጦታ ማገልገል ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።


አንድ ሰው ድምፁ ስለቀጠነ ወይም ስለተስረቀረቀ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ካሴት፣ ሲዲ እንዲሁም ቪሲዲ ለማዘጋጀት የሚያስችል ገንዘብ ስላገኘ ብቻ ዘማሪ ይሆናል ማለት አይደለም። መዝሙር እግዚአብሔርን የምናገለግልበት መንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ ስጋችንን ለማስደሰት ትርፍ የምናገኝበት ቢዝነስ አይደለም። በመዝሙር ለማገልገል ደግሞ መቅደም ያለበትን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት ጠንቅቆ ማወቅን ይፈልጋል። ለማወቅ ደግሞ ቁጭ ብሎ ከአባቶች እግር ስር መማርን ይጠይቃል። ይህንን ሳያደርጉ እንደው ብድግ ብሎ ግጥሙን እገሌ ፃፈው ዜማውን ደግሞ አኔ ደረስኩተ ካሉ በኋላ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት ጠብቆ የወጣ መዝሙር” የሚል ጽሑፍ ለጥፎ ለገበያ የሚያቀርብ “ዘማሪ” የዘማሪነትን ክብር ያጎደፈ እና ፀጋ እግዚአብሔርን በምስር ወጥ የለወጠ በመሆኑ “ዘማሪ” የሚለው ስም ከብዶት በቁሙ የሞተ ነው።


 ቸር ያሰማን።

42 comments:

 1. ከአናቱ የተቀመጠዉ ሰዉ ከራሱ ክብር ይልቅ ሃይማኖቱን የሚያስከብር የሚያከብር እግዚአብሔርን የሚፈራ ቢሆን ማንኛዉም አገልጋይ በስርዓቱና በደንቡ ይጓዝ ነበር:: እንዲያከብሩም ማድረግ ይችል ነበረ::
  ዉሻ በቀደደዉ________ ሆነና
  የመሪዎችን ሥርዓት አልባ መሆን የተረዱ አጋጣመዉን ተጠቅመዉ ፍላጎታቸዉን አሳክተዋል:: ከመስመር ዉጭ ለሆኑ ዘማሪዎችም ሆኑ ሃይማኖት መሪዎች እግዚአብሔር መንፈሳዊ ልቦናቸዉን ይክፈትላቸዉ ይክፈትልን :: ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ያበርታህ ይጠብቅህ::

  ReplyDelete
 2. አልቀናል። አልቆልናል። አልቆብናል። እሱ ከመንበሩ ምረቱን ይላክልን።

  ReplyDelete
 3. Well said Dani! Egziabher yetebekeh!

  ReplyDelete
 4. ይመቻል።ደስ አለኝ። thanks for all education u r giving us for free. Dear have u noticed that the Ethiopians r changing their names to foreign names which is an identical crisis. if u see students learning in colleges even changing their names before graduation and those who didnot change it getting shame of it.i think all names r equal only to represent the people and nothing else. if u go to cooleges and kg u will get many people with one new name. please write about it befor we loose our names by identity crisis.

  ReplyDelete
 5. Selam Dn. Dani

  ይህንን ሳያደርጉ እንደው ብድግ ብሎ ግጥሙን እገሌ ፃፈው ዜማውን ደግሞ አኔ ደረስኩተ ካሉ በኋላ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት ጠብቆ የወጣ መዝሙር” የሚል ጽሑፍ ለጥፎ ለገበያ የሚያቀርብ “ዘማሪ” የዘማሪነትን ክብር ያጎደፈ እና ፀጋ እግዚአብሔርን በምስር ወጥ የለወጠ በመሆኑ “ዘማሪ” የሚለው ስም ከብዶት በቁሙ የሞተ ነው።
  Thanks you are 1000% right

  God be with you and your family

  ReplyDelete
 6. tilik kumneger ansetehale.egiziabher yibarkih.lenegeru min enesu bicha legnam sim meletef, mesqel limadachin honoal.wosen yelenim

  ReplyDelete
 7. all views are from 'ABOVE', so pls bo ezin yisimae, webo ayin yeriey!!!

  ReplyDelete
 8. ስማቸው እየከበዳቸው የሚሞቱት ያሳዝናሉ። የቤተክርስቲያንን ክብር፣ ሃይማኖቷንና ሥርዓትዋን እንዲያስጠብቁ የተሾሙ ጳጳሳት አይደሉም እንዴ ዲቁናውን የሚያድሉት? በዲቁናቸው ሳይታመኑ ቅስና እየሾሙ፣ ሊቀ ትጉኃን፣ መጋቢ ሃይማኖት፣ መጋቢ ሐዲስ እያሉ ካለ አቅማቸው ስም እያሸከሙ የሚገድሏቸውስ እነሱ አይደሉምን? ለሟቾቹም ለገዳዮቹም ልቡና ይስጥልን።

  ReplyDelete
 9. ውድ ወገኖቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን !!!

  እንደዚህ ስር የሰደዱና የቤተክርስቲያናችንን መሰረት ለመናድ የሚነሱ አእላፍ የጠላትን ደባዎች እንዲህ በፈረጠመ ቋንቋ መቃወም በስጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚያመጣው ፈተና ቀላል እንደማይሆን ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ እንደዚህ አይነት አገልግሎቶችን ለማግኘት ሁላችንም ተግተን መፀለይ ይጠበቅብናል፡፡

  ለኔ እንደ ምዕመን እጅግ የሚገርመኝና መልስ ያጣውለት ነገር ቢኖር የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ፈርጀ ብዙ ፋተና ነው፡፡ ይገርማል…. ምን ማለት እንደምችል አላውቅም ….

  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ፡፡

  ReplyDelete
 10. አይ አንች ቅድስት ቤተክርስቲያን !!! ዝምምምም…………..

  ReplyDelete
 11. ጽሁፉ ወቅታዊና ትክከለኛ ነው። እኛ በቤተ-ክርስቲያናችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ጉዳይ አንጀታችንን ከማሳረሩም በላይ አሁን አሁን ማን ላይ እምነት እንደምንጥል ግራ ገብቶናል። ምክነያቱም ዛሬ አለ ያልነው ሰው ነገ ለርካሽ ጥቅምና ለሥጋዊ ህይወት ይጠፋል። አስመሳዩም በዝቷል። ከሁሉ ደግሞ የሚደንቀው የታወቁትን አስመሳዮች እንኳን ሃይ ባይ መጥፋቱ ነው። አገልጋዮቹም እርስ በርስ አየተዋወቁ ምን አገባኝ ይሁን፤ ምን እንደሆነ አይታወቅም አብረው ይቀድሳሉ፣ አብረው ማህሌት ይቆማል፣ በአጠቃላይ አብረው ያገለግላሉ። አሁን መዕመናኑ እግዚአብሔር ዝም እንደማይል ቢያውቅም ስለ ሃይማኖቱ ትዕግስቱ ስላለቀ ወደ ሌላ እርምጃ እየሔደ ነው። ይህንንም ዳኒ አንተ ከማወቅህም በላይ በአንድ ወቅት በከሃዲ ዘማርያንና በሰባኪያን ላይ የተወሰደውን የወጣቶች እርምጃ በአይንህ ተመልክተህ በሰዐቱ ከተጋበዙት ሰባኪያን አንዱ በመሆንህ "ሃይማኖት የሌለው ሰው በምድርም በሰማይም መቅሰፍት አያጣውም።" በማለት ታላቅ መልዕክት አስተላልፈሃል። እውነት ነው።

  እግዚአብሔር ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደደሩትን ልቦና ይስጣቸው።
  የኖኀ መርከብ ከ.አ.አ.

  ReplyDelete
 12. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  አስተያየት አለኝ
  በቤተክርስቲያን የኛ ያልሆነ እንግዳ የሆነ (አዲስ)ትምህርት እያስተማሩ “መጋቤ ሐዲስ” የተባሉትስ ስማቸዉ አይከብዳቸዉ ይሆን? ስማቸዉ ማስተካከያ ተደርጎለት “መጋቤ አዲስ” ሊሆን ይገባዋል እላለሁ።
  G From MN,USA

  ReplyDelete
 13. ene hule yemigermegn neger yih new= yeabune pawlosin sim lemetrat yemikatelew gize, yemiyizew bota....ena bezih sim yemisraw sira????? enemegabe ADDISN ema tewachew.

  ReplyDelete
 14. It is a good idea! The only solution for the problem is to pray, the PEOPLE of the ethiopia , EOTC let us see ourselves as the "MEMNAN" OF THE PAST , ARE WE LEADING OUR LIFE AS OF BEFORE? Pls let us remember our fathers , mothers ,elders . As we all know there was no time the church with out problem , but it was solved b/c our mothers , fathers was praying , and God help them to solve the problem why not in our time? Is the GOD of that time is different from the GOD in our time? NO! We can not be as before to get raid of the problem .

  ReplyDelete
 15. ወቅታዊ እና ትክክል ነዉ ግን አሁንም ብዙ ይቀራል ማታ አለማዊ ቤት ቆይተዉ ጠዋት ቤ/ክ አገልገጋይ የሚሆኑ ሰዉን ሳይሆን እ/ር የሚያታልሉ ብዙ አሉ። አምላክን ማን በንጽህ ልቦና ይለምነዉ? የሁሉም ሰዉ ሴጣን በተበተበዉ የዓለም ንዋይ ተጠምዷል ድንግል ማርያም፣ ቅዱሳኖች በልመናቸዉ አይለዩን እንጂ ዓለም የ1 ደቂቃ እድሜ ሊኖራት አይገባም ነበር የሁላችንን ልቦና በንፅህ ልቦና አምላክን እንድንለምን የሱ ፍቃድ ይሁንልን። አሁን እንደዚህ አይነት በተደጋጋሚ አዉጣልን ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 16. This is really interesting.

  There was a King whose name was John. He was in a field to see his soldiers. He got a soldier who was not happy in the field. The King asked him why he wasn't happy. The soldier replied, "I am afraid of the enemy." The King asked his name. "May name is John", said the soldier. Finally, the King shouted, "Simen mels weym atbkeh tekus."

  ReplyDelete
 17. መዝሙር እግዚአብሔርን የምናገለግልበት መንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ ስጋችንን ለማስደሰት ትርፍ የምናገኝበት ቢዝነስ አይደለም። እውነት ነው::
  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ፡፡
  ማንነታቸውን ለመደበቅ በቅናት እና በተለያየ የጥቅም ማጣት የተነሳ በማይገባቸው ሰዎች ላይ የራሳቸውን ስም ለማከናነብ የሚጥሩትንም የድንግል ማርያም ልጅ በሩቁ ይያዝልን አሜን::
  Sara Adera

  ReplyDelete
 18. እንደነዚህ ያሉት ወንድሞች ከራሳቸውም አልፈው ዲቁናን ያስነቅፋሉ። ስሙን ይጠሩበት እንጂ ስሙ በፍፁም እነርሱን አይገልጻቸውም። ዲቁናን እንደ ጭምብል ይጠቀሙበታል፣ ዲቁናን ይገለገሉበታል እንጂ ዲቁናን አያገለግሉበትም። ለእንደእነዚህ ያሉ ወንድሞች ጊዜው የአገልግሎት ሳይሆን የአገልጋዮች ነው። በመሆኑም እንደእነዚህ ያሉቱ ዲያቆን የሚለው ስማቸው ከብዷቸው በቁማቸው የሞቱ ናቸው።
  Well said! Thank you.

  ReplyDelete
 19. ጥሩ ምልከታ ነው።

  ReplyDelete
 20. Haile Gebrie ke 4 Kilo...Kale Hiwoten yasemalen.
  I appreciate the view presented. It sometimes irritates to observe worldly things in our church. As an Orthodox Tewahedo Christian, it should be shame to buy such irrelevant CDs.
  ወገኖቼ የዘፈን ሲዲ ገዝቶ ማዳመጥ ይበጃል:: እሱ አንድያዉን የለየለት ጉዳይ ነው:: በእግዚያብሔር ስም አመካኝቶ መዝፈን ግን መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው:: እንዴው ስንሰማው ይታወቀን...ኡምዚቃው ነው ወይስ መልእክቱ ነው ለቦናችንን የሰበረው?

  ስም የለሽ ከፊንላንድ

  ReplyDelete
 21. Dear Haile Gebreal

  Thank you very much for weel written articel. Dear blog followers, please read first the author, and say thank you for him. For this article the writer was Haile Gebreal.

  Thanks

  ReplyDelete
 22. lebona yestilin enji min enelalen

  ReplyDelete
 23. menkos mot sehon yemot sew degemo yemayegeba sem bemestet yegelal

  ReplyDelete
 24. Dear Haile Gebreal,

  Thanks to your intervention. It touches my inside of in. Thus, one should analyze and consider the image of him or her. To my observation people are pretending as if they are so nice, intellectual, and honest but they are not. Hence, we should work hard to identify the fox from the sheep.

  ReplyDelete
 25. Qale hiwoten yasemalen !!! zweter weseten erfet yeminesaw teyake neber zemari tebeyewochum yehen anebebew ersachewn yemiteyekubet yemielewtubet yaderegelachew

  wendm Dani tegawen yabezaleh ende ante yalewn asteway EGZIABHER yabezalen Amen !!

  ReplyDelete
 26. መፍትሔው አንድ ብቻ ነው። የቤተክርስቲያንን ስርዓት አክብሮ የሚያስከብር አባት/ፓትርያርክ/ እንዲሾም ሁሉም የበኩሉን ማድረግ ብቻ!ይህን ደግሞ እንደሰው ከምእመኑ የሚጠበቀውን ማድረግና ውሳኔውን ከእግዚአብሔር መጠበቅ። ከሰው የሚጠበቀው የቤተክርስቲያንን ስርዓት አክሮ የማያስከብረውን አለመቀበል፣ ስሙን አለመጥራት እና ወደ እግዚአብሔር መጸለይ። ስሙን አለመጥራት ያልኩበት ምክንያት ቅን መሪ ስጠን እያልን ስንጸልይ ከህገወጡ ጋር በክፉ ስራው መተባበር የለብንምና ነው። አለበለዚያ ጸሎታችን እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ይሆንብናል፤ለፈጣሪም ያስቸግራል።

  ReplyDelete
 27. Thanks for the idea that u brought. Lebonawene yesetine.

  ReplyDelete
 28. ዛሬ ለሚታየው የመዝሙር ከስርአት መውጣት አንዱና ዋናው ተጠያቂ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ብዙ የቤተክርስቲያንን ስርአት የጠበቁ ዘማርያንንና መዝሙራትን ማፍራት ሲቻል የማኅበሩ አባላት በግል መዝሙር ማውጣት አይችሉም በሚል የማኅህበሩ ደካማ ደንብ ምክንያትና ይህንንም ለማሻሻል ርምጃ ባለውሰድ ትልቅ ክፍተት ተፈጥሮ ያለስርአት የሚዘፍኑ ‘ዘማርያን’ ነን ባዮች የአግልግሎቱን መስክ እንዲቆጣጠሩ ያደረገው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩና በቀላሉ በማጥናት ሊዘመሩ የሚችሉ የተዘጋጁ መዝሙራት በቤተክርስቲያን እያሉ እንደ ፈጠራ ስራ የራስን ግጥምና ዜማ እያቀናበሩ ‘መዘመር’ አዲስ የቤተክርስቲያን ባህል ነው። ለመሆኑ መዝሙር ሰው ደስ ሲለው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግንበት የሚዘመር እንጂ ሰው የራሱን ስሜት ማስደሰቻ ወይንም የሌሎችን ሰዎች ስሜት ለማርካት የሚዘመር ነው ወይ? ማንም ደስ ያለው ቢኖር ይዘምር አለ ቅዱስ ዳዊት። በምን ደስ ያለው? በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ! ለማን ይዘምር? ለእግዚአብሔር። ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የሚያስደስት የመላእክትን መዝሙር አዘጋጅታ እያለ የአግቦ፣የቁርሾ፤የሆድ መባስ፤የአሽሙር፣ ያልሆኑትን ያልኖሩበትን በጌታ ምክንያት ተገፋሁ፣የመከራ ጎርፍ ቢወርድብን ምናምን…. እየተባለ እንዲቀለድ ከላይ ካሉት የቤተክርስቲያኗ ጠባቂዎች ባላነሰ በዚህ ዘርፍ ማኅበረ ቅዱሳን በግትር አቋሙ ምክንያት ይህ ጥፋት እየሆነ ነው።

  ReplyDelete
 29. ቸር ያሰማን።

  ReplyDelete
 30. ዉባለ መለሰJuly 20, 2011 at 12:18 PM

  ኧረ ስንቱ ሠው ነው “ዘማሪ” ነኝ እያለ ገበያ ላይ የሚወጣ ቤት ይቁጠረው፡፡ዓመታዊ በዓላት ሲመጡ እኮ ትዝ የሚለኝ “አሪፍ” መዝሙር ነው ግዙ እያሉ የሚሉት ነገር ነው፡፡ስንቱ ምዕመን ጆሮ መስማት የሚፈልገውን ሳይሆን የማይፈልገውን የሚሰማው በድምጽማጉያ የሚለፉት ትንሽ እንኳን ድምጹን እንቀንሰው አይሉም ምክንያቱም ለእነሱ ቢዝነሳቸው ስለሆነ፡፡ “ቤቴን የጸሎት ቤት ሳይሆን የ------ ቤት አደረጋችሁት” አምላካችን እንዳለው:: ስንቱ የመዝሙር ካሴት ነው sansured ተደርጎ የወጣው ፡፡ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው!

  ReplyDelete
 31. በርግጥ ስማችን የገደለን ብዙዎች አለን በነፃ የተሰጠንን የህይወት ቃል ባገኘነው መልካም ስም ተጠቅመን የምንሸቅጥ ግን ህሊናችን ምን እየፈረደብን ይሆን መማር ከቻልን እግዚአብሔር በትዕግስት እያስተማረን ነውና እንፀፀት

  ገብረማርያም
  ከአአ

  ReplyDelete
 32. It is possible, to learn from now( it is time to learn)

  ReplyDelete
 33. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  ግን ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው ማን ይሆን???

  ReplyDelete
 34. ጆሮ ያለው ይስማ!!!ማስተዋልን ለሁላችን ያድለን።

  ReplyDelete
 35. ዲያቆን ዳንኤል,እግዚአብሔር ፀጋ እና በረከቱን ጨምሮ ያድልህ. በምታነሳቸው ወቅታዊ እና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ.ጽሁፍህን መከታተል ከጀመርኩኝ አመት ሁኖኛል እናም ለቤተክርስቲያን ያለህ ተቆርቃርነትህ በጣም እቀናለሁ.ቡዙ ነገሮችን ልክ ያልሆኑ ሲከናወኑ አያለሁ ነገረ ግን እኔ ማነኝ? እኔ የእዉቀት ረሃብተኛ ነኝ እንጂ መገሰጽ የማልችል ትንሽ ፍጡር መሆኔ አምናለሁ.ጊዜ ካለህ ለመረዳት ከምፈልገው ነገር 1. መምህር ግርማ ማንነት እና እሳቸውን እንደ አንድ አባት መቀበል አለብን ወይ? 2. በየትኛው ሲኖድዮስ የምትመራ ቤተክርስትያን ነው መከተል ያለብን? የሰው አገር ስደተኛ ነኝ በዚህ ባለሁበት አገር ህዝቡ ከተከፋፈለ ቆይቶዋል አሁን ደግሞ በማንም አንመራም ብለው የነበሩትም አንድ ቤተክርስቲያን አሁን በአሜሪካ ነው የምንመራው ብለዎ አሉ እናም ህዝቡ ለሁለት ተከፈለ. አንተስ ምን ትላለህ በዚህ ጉዳይ ላይ? እግዛብሔር ይስጥልኝ አመሰግናለሁ.

  ReplyDelete
 36. ኃይለ ገብርኤል (ሌላኛዉ ዳኒ) ቃለ ህይዎት፡፡ ያሰማልን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ዝክረ ያሬድ የመዝሙር አዉደ ርዕይ ማህበረ ቅዱሳን አዘጋጅቶ ነበር፡፡ እኔም የማየት ዕድሉ ገጥሞኝ አይቸዋለሁ፡፡ ስለዚህ በተነሳዉ ጉዳይ ላይ ትንሽ ማለት ፈለግሁ፡፡
  1. የገጠመንን ነገር በዕዉቀት አስደግፎ መደገፍ ወይም መቃወም፤ ለምሳሌ የአንዳንድ ዘማሪያን መዝሙር ቀጥታ ብር ላይ ያተኮረ ነዉ ስለዚህ ከመናፍቃን የድሮ ካሴቶችም ቢሆን የመዝሙር ግጥም ገልብጦ ዜማዉን ኦርቶዶክሳዊ አስመስሎ ወይም የኦርቶዶክስ ታፔላ ለጥፎ ገቢ መሰብሰብ (ምሳሌ፡ “ካልበረከኝ አልለቅህም”) ስለዚህ መርምሩ፤ ለምን በሉ፤
  2. በኦርቶዶክሳዊ ሐይማኖት ጉዳይ የሰዉ ቲፎዞ መሆንና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ስርዓት ቀናተኛ መሆን በጣም ይለያየሉ፡፡ “እኔ የእኔ ለእኔ” ምናምን የሚል መዝሙር ገጣሚዎችም ሆኑ ዘማርያን በእነ ይልማ በነኪነጥበብ መዝሙሮች ነፍሳችን ወደ ሰማይ ስትከንፍ፤ በናንተ “እኔ የእኔ ለእኔ” መዝሙሮች ደግሞ “እኔ ለካ ደሃ ነኝ፤ በምድር ካልደላኝ የሰማዩ ምን ያደርጋል …” እንድንል የሚገፋፋ ይመስላል፡፡ ክሊፖቹስ ቢሆኑ “በስጋ ደልቶን፤ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን መጽሃፍ ቅዱስ ስናነብ ጥሩ ምግብ በማዕድ ሞልቶ ስንመገብ … ወዘተ” ነዉ አካሄዱ፡፡ እኛ ደግሞ ስጋዉያን ስለሆንን መንፈሳዊዉ ስራ በምድራዊ ታፔላ ሲወራ ደስ ይለናል፡፡
  3. አንድ ወዳጄ ከመናገር ይልቅ መጻፍ የበለጠ ዕዉቀት ይጠይቃል ይላል፡፡ ከላይ ያሉት ብጹኣን አባቶች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና የመሳሰሉት አንድ ጥሩ የሆነ ሲስተም/አካሄድ መፍጠርና ያንን ማስጠበቅ ቀላል ይመስለኛል፡፡ ከዛ በኃላ ብዙ እንድትጽፉልን እንፈልጋለን፡፡ ግን መጀመሪያ የተቀመጣችሁበት መቀመጫ የሚፈልግባችሁን ስራ በተገቢዉ ለቤተክርስቲያኒቱ ስሩላት፡፡
  4. ዝም ብሎ ዳር (boundary) የሌለዉ ስብከት/መዝሙር ለማዘጋጀት የምትተጉ አካላት ቆም ብላችሁ አስቡበት፡፡ ከሆድና ከታዋቂነት ይልቅ ሐይማኖት ይበልጣልና:: “ሆዳቸዉ አምላካቸዉ፤ ክብራቸዉ በነዉራቸዉ” እንዳይሆንባችሁ!!!!! አመሰግናለሁ! ታናሽ ወንድማችሁ፡፡

  ReplyDelete
 37. እዽግ አስተማሪ ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ይልክ ይሄን ሳነብ ምን ትዝ አለኝ መሰለክ ለምን የክርስትና ስማችንን እንደገና ለአለማዊውም ስማችን መጠቀም እንደማንዸምር። አሁን የሚጠቀሙት እንደፋራ እየተቆጠሩ እንደሆነና የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ደግሞ ከአለማዊ ስም ወደ እራሳቸው አየቀየሩ እንደሆነ አስባለሁኝ። ስለዚህ አቀም የወሰደ ንባብ አላየሁኝም። ሊኖር እንደሚችል አስባለሁኝ። ከሌለ ግን ዳኒ ብታስነብበን መልካም ነው እላለሁኝ።

  ReplyDelete
 38. ኃይለ ገብርኤልን (ከአራት ኪሎ) እግዚአብሔር ይስጥልን፣ እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡ ዲያቆን ዳንኤልንም እንደዚህ አይነት እድል ስለፈጠረልን እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡ እንደ እኔ ግን መፍትሔው አሁንም የቤተክርስቲያናችንን ትምህትርት ደግሞ ደጋግሞ ከአባቶች ስር ቁጭ ብሎ መማር ነው፡፡ ካወቅን አንሳሳትም፡፡ ኃይለ ገብርኤልን (ከአራት ኪሎ) እግዚአብሔር ይስጥልን፣ እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡ ዲያቆን ዳንኤልንም እንደዚህ አይነት እድል ስለፈጠረልን እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡ እንደ እኔ ግን መፍትሔው አሁንም የቤተክርስቲያናችንን ትምህትርት ደግሞ ደጋግሞ ከአባቶች ስር ቁጭ ብሎ መማር ነው፡፡ ካወቅን አንሳሳትም፡፡

  ReplyDelete
 39. ለሁሉም ልቡና ይስጥ። ችግሩ ካልፈለጉስ?

  ReplyDelete
 40. በመዝሙር ለማገልገል ደግሞ መቅደም ያለበትን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት ጠንቅቆ ማወቅን ይፈልጋል። ለማወቅ ደግሞ ቁጭ ብሎ ከአባቶች እግር ስር መማርን ይጠይቃል። ይህንን ሳያደርጉ እንደው ብድግ ብሎ ግጥሙን እገሌ ፃፈው ዜማውን ደግሞ አኔ ደረስኩተ ካሉ በኋላ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት ጠብቆ የወጣ መዝሙር” የሚል ጽሑፍ ለጥፎ ለገበያ የሚያቀርብ “ዘማሪ” የዘማሪነትን ክብር ያጎደፈ እና ፀጋ እግዚአብሔርን በምስር ወጥ የለወጠ በመሆኑ “ዘማሪ” የሚለው ስም ከብዶት በቁሙ የሞተ ነው።
  that is true

  ReplyDelete
 41. Ere enante enedih atekawomu Lehulum egziabeher eko ferdun yisetal. Ebakachihu andachin andachinin lemem mekonenu asfelege? Beka hulum sew Yismamagnal yalewun Mezemur yemadamet mebet eko alew. le Betekrestian eko egeziabeher Ale. Esiki Hulachinim lelawun kemekonenachin befit rasachinen eney? Eski manew Be Geta fit nitsu, Kidus? Ere yibekan. Menalbat eko legna Hatiategna meslo yetayen sew be Geta fit eko kebir linorew yichilal. Egziabeher Endegna eko aydelem Yemiferdew. Beka hulunem Le Egziabeher Seteten benetewus.

  ReplyDelete