Saturday, July 16, 2011

አንድ ነገር አለ


ዓርብ ዕለት ማታ ነው ለቅዳሜ አጥቢያ፣ ድሬዳዋ እምብርት ላይ ቆመን፡፡ ከአንድ የምሽት ፕሮግራም ተመልሰን ከኛ ከሚለዩ ወንድሞች ጋር እያወራን፡፡ ከኛ ራቅ ብሎ አንድ ወጣት ዘና ኮራ ብሎ ይሄዳል፡፡ ሌሎች ወጣቶች ደግሞ ከርሱ በግምት ሃምሳ ሜትር ርቀው ከኋላው ይከተሉታል፡፡
«ግን ነፍሱ ምን አግኝቶ ነው በዚህ ሰዓት እንዲህ የሚጀነነው» አለ አንዱ፡፡
«ምናቅለታለሁ» ሌላው መለሰ
«አንድ ነገርማ ሳይኖረው እንዲህ አይሆንም»
«እርሱማ ያለ አንድ ነገር እንዲህ በማታ ይጀነናል»
«አዎ አንድ ነገር ይኖረዋል፡፡»
ወጣቶቹ ወጣቱን በዚያ ማታ ስለ ጀነነው ነገር ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ግን «በአንድ ነገር» ተስማሙ «አንድ ነገር ሳይኖረው አይቀርም» ብለው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ወደ ዝርዝር ቢገቡ ኖሮ አይስማሙም ነበር፡፡ በምሥጢራዊው ጥቅለላ ግን ተስማሙ «አንድ ነገር አለ» በሚለው፡፡
«አንድ ነገር አለ» በማኅበረሰባችን ውስጥ የቆየ የሽንፈት መደበቂያ ሥውር መንገድ ነው፡፡
«እንዲህ ያደከምሽኝ እግሬ እስከሚነቃ
አንዳች ነገር አለሽ ሌሊት የሚወቃ»  ይል የለ ሥነ ቃላችንስ፡፡
ተንትኖ፣ ዘርዝሮ፣ ፈትሾ፣ እስከ መጨረሻው ሄዶ፣ መጋረጃውን ገላልጦ፣ ቆፍሮ፣ ሰባብሮ ውስጡን ከማየት፣ በውስጡ ባለው ነገር ላይም ከመከራከር ይልቅ እንዴው በደፈናው «አንድ ነገር ቢኖር ነው» እያሉ መስማማት፡፡
እገሌ እንዴት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሆነ፣ አንድ ነገር ቢኖር ነው
እገሌ እንዴት ባለ ሥልጣን ሆነ፣ አንድ ነገር ቢኖር ነው
እገሌ እንዴት መናኝ ሆነ፣ አንድ ነገር ቢኖረው ነው፡፡
የእገሌ ልጆች ጎበዙ፣ አንዳች ነገር አጠጥቷቸው ነው
«አንድ ነገር» ከየት መጣ?
በንጉሡ ዘመን የነበሩ ሰዎች ሲያወሩ በተደጋጋሚ የምሰማው ነገር አለ፡፡ «ንጉሡ እንዴው ድንገት ከች ሲሉ፣ አቤት ግርማ ሞገሳቸው፤ ቁመታቸው አጭር ነው፣ ሰውነታቸው ቀጠን ያለ ነው፣ ፊታቸው ላይ ግን አንዳች ነገር አለ፣ እንዴው ስታዩዋቸው ስገዱ ስገዱ የሚያሰኝ አንድ ነገር አለ» ነገር ምንድን ነው? የሚነግራችሁ የለም፡፡ ብቻ አንዳች ነገር አላቸው፡፡
ከተገለጠ ነገር ይልቅ ያልተገለጠ ነገር በማኅበረሰባችን ውስጥ ከበሬታም ዋጋም ያገኛል፡፡ በላዩ ላይ አወ ሳሰዱ፣ አመራረቱ፣ ይዘቱ እና አገልግሎቱ የሚያበቃበት ጊዜ ከተነገረው ዘመናዊ መድኃኒት ይልቅ «በእኩለ ሌሊት፣ ዶሮ ሳይጮኽ፣ ሰው ሳያይ፣ በጋቢ ተሸፋፍኖ፣ በነጭ እንጀራ ውስጥ፣ ፊትን ወደ ምዕራብ አዙሮ» የሚወሰደው የአበሻ መድኃኒት ልዩ ክብር አለው፡፡ ለምን ቢባል ከተገለጠ ነገር ይልቅ የተሸፋፈነ ነገር ክብርም ዋጋም አለውና፡፡ ዐዋቂው ይህንን ሁሉ ያሉት አንድ ነገር ቢኖራቸው አይደል?

37 comments:

 1. yes I accepted Ur View anyways Thanks.

  ReplyDelete
 2. አንተ ራስህ ይህን ላመፃፍ የተነሳሳህው አንድ ነገር ቢኖር ነው:: ብዬ አሰብኩ ዳኒ ልቀልድ እስቲ

  ReplyDelete
 3. yaa, but you write it because there is something you wish others to look. why don't you say it out.

  ReplyDelete
 4. Thanks for the observation on Dire street. I think this is a nice idea for us to talk about.

  As Ethiopian, I heard a lot of such phrases and some proverbs, which seem don't make sense, but they do to me. They are phrases for people to explain a lot of things with one saying, two birds with stone kind of deal.

  Most languages use the same. Phrases might say several topics or ideas. Take our politicians talks, they don't tell you an explicit answer for some issues. That is where we, the people, learn to use such kind of sayings, just to be safe rather than dead sure.

  I do believe that it is better to use such phrases than generalization and/or being hundred percent sure of something, which we aren't, and eventually judging people wrongly. To avoid judging the book by the cover rather than the core value of the idea inside it.

  ReplyDelete
 5. የኢትዮጵያ አይዶል ዳኞችም እንደ ኢህአዴግ ለታዳጊ ክልል ተወዳዳሪዎች የተለየ ድጋፍ የሚያረጉት አንድ ነገር ስለ አለ ነው::

  ReplyDelete
 6. ድንቅ ብለሃል ዳኒ! አካፋን አካፋ ፤ ዶማንም ዶማ ብሎ መጥራት ወንጀል ሆኖ በሚወሰድበት እንዲያውም እንዲያውም አንድን ነገር እንዳለ ባለመግለጥ “ ጨዋ፣ አዋቂ ያሳደገው …“ እሚል ስያሜ በሚሰጥበት ማህበረሰብ ውስጥ ያን “ አንድ ነገር” ማን ይግለጠው ብለህ ነው ? ለነገሩማ ዘዬአችንም እሚለው “ ዝርዝር ኪስ ይቀዳል” አይደል ? እናማ ለምን? እንዴት? ወዴት? በሎ መጠየቅ መቁረጥን ይጠይቃልና እስቲ ፈጣሪ ልብ ይስጠን.

  ፍቅር-ዓለም ከጆበርግ

  ReplyDelete
 7. የኢትዮጵያ አይዶል ዳኞችም እንደ ኢህአዴግ ለታዳጊ ክልል ተወዳዳሪዎች የተለየ ድጋፍ የሚያረጉት አንድ ነገር ስለ አለ ነው::

  ReplyDelete
 8. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel
  Even in English, they say there must be one thing. I think it is a human nature and our universal language. GOD BLESS!!! Atlanta
  By the way, when are you coming to Atlanta

  ReplyDelete
 9. Great as usuall!!!!

  ReplyDelete
 10. ማህበረሰባችን ´´አንድ ነገር አለ´´ በሚል ፈሊጥ ተስማምቶ የመቀመጡ ምንጩ ከምን ይሆን? ጥርጣሬ?ፍርሃት?የበታችነት?ንቀት?ወይስ ምን ይሆን? በዚህ እሳቤስ ተግባብተን የተቀመጥንበት ከመቼ ጀምሮ ይሆን? ይህን ከመሰሉ አመለካከቶች ለመውጣት ምን ማድረግ ይኖርብናል? ይህን አመለካከት ለመቀየር ሐላፊነቱ የማን ይሆን? ብቻ ይኸኛው ጽሑፍህ መመለስ ወደማልችላቸው ጥያቄዎች ውስጥ እንድዘፈቅ አደረገኝ። የአእምሮ ጅምላስቲክ ውስጥ መክተት ትችልበታለህ። ተሳክቶልሃል። እንደዚህ ያሉና እንደ ´´አልበር እንዳሞራ-- ´´ አይነት አመለካከቶቻችን ከህዝባችን ለማውጣት ነቅሶ አውጪ ጸሐፊዎችን አምላክ አያሳጣን።
  በርታ

  ReplyDelete
 11. D/n Dani selam lante yhun.
  ከተገለጠ ነገር ይልቅ ያልተገለጠ ነገር በማኅበረሰባችን ውስጥ ከበሬታም ዋጋም ያገኛል፡፡ በላዩ ላይ አወ ሳሰዱ፣ አመራረቱ፣ ይዘቱ እና አገልግሎቱ የሚያበቃበት ጊዜ ከተነገረው ዘመናዊ መድኃኒት ይልቅ «በእኩለ ሌሊት፣ ዶሮ ሳይጮኽ፣ ሰው ሳያይ፣ በጋቢ ተሸፋፍኖ፣ በነጭ እንጀራ ውስጥ፣ ፊትን ወደ ምዕራብ አዙሮ» የሚወሰደው የአበሻ መድኃኒት ልዩ ክብር አለው፡፡ ለምን ቢባል ከተገለጠ ነገር ይልቅ የተሸፋፈነ ነገር ክብርም ዋጋም አለውና፡፡ ዐዋቂው ይህንን ሁሉ ያሉት አንድ ነገር ቢኖራቸው አይደል? እንዴ! ዳንኤል አንድ ነገርማ አለ.
  Hailemeskel Z Maputo.

  ReplyDelete
 12. Thank you D/n Dani
  "There is One thing--Anid neger ale". Where is that? Is it in our mind? hand? where?????????
  I believe in seeing things from different angles-360 degree.But it should not be something confusing.
  This saying is ("There is One thing--Anid neger ale")killing our church, organizations and the country as a whole. Rather than searching the real thing, we all prefer to say there is one thing. But the surprise thing is that nobody knows the one thing. Therefore please everybody don't tell us there is one thing rather tell us what that one thing is.Let us say "Akafan akafa malet enlimed...with good manner and the way to teach others to develop the way we want --say it clearly---
  Change starts from oneself not from others.
  Thank you

  ReplyDelete
 13. Dear Daniel,

  Yes indeed I agree with your view, we are binding with the unknown fact. We are always agree as if there is something behind the curtail which is not known very well.

  "አንድ ነገር አለ» በማኅበረሰባችን ውስጥ የቆየ የሽንፈት መደበቂያ ሥውር መንገድ ነው፡፡ "

  ReplyDelete
 14. of course ale anid negerma ante rasih indet yihenin blog tikeftaleh anid neger binor new inji

  ReplyDelete
 15. I apperciate your views always.dani are our path finder. we shoulid get rid of this bad trend from our daily life. belive or not phycologically we(ethiopians) lost our confidence because of this.we have a lot of similar weakness and we need to search the others.I begun today what about u???

  ReplyDelete
 16. Thank you very much Dn Danile kibret for your bright ideas.

  ReplyDelete
 17. ልክ ብለሀል ዳኒ! ግን እኮ እኛ ብቻ ነን እንዴ አንድ ነገር አለ የምንለው? ተጠበቡ ተመራመሩ የምንላቸው ሳይንቲስቶችም እኮ የስነ ፍጥረት ሁነት ጥልቅና ምጡቅ ቢሆንባቸው በደምሳሳው አንድ ሐይል(supernatural power)አለ ነው ያሉት። በርግጥ ቅንነት በተሞላ መንገድ የሰውን ማንነት ብንፈትሽ መልካም ነው ነገር ግን አነድ አንዴ ድርጊት በቂ ይሆናል እኮ። እንዴት ቢባል አንድን ሰው ከሚያደርገው ወይም ከሚሰራው ካልሆነም ከሁኔታው ተነስተን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እናነበዋለንና።

  ReplyDelete
 18. yes ye ethiopian idol sewochen yamahachew lije
  Ande-Neger selaleh new...Ena gen betam new yemadenkachew!!

  ReplyDelete
 19. yes Aba Sereke Mahiberekidusan yemiyasadedubet meknyat ande neger ale!!

  ReplyDelete
 20. DANY kemenfesawi alem yemilew amedihen yeresahibet miknyat ande neger binor new!

  ReplyDelete
 21. Great views!! God bless you more and more!!!
  Danile from Marry Land

  ReplyDelete
 22. አንተ እራስህ ያለ አንድ ነገር እንዲህ አይነት ምልከታ አይኖርህም ነበር ፡፡
  አይ አንድነገር !!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 23. ከተገለጠ ነገር ይልቅ ያልተገለጠ ነገር በማኅበረሰባችን ውስጥ ከበሬታም ዋጋም ያገኛል፡፡

  ReplyDelete
 24. Discuss it briefly .
  " ande neger ale ende minew "
  GOD BLESS ETIOPIA !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 25. yihen saneb aned neger tiz bilogn saqehu.

  ReplyDelete
 26. ከተገለጠ ነገር ይልቅ ያልተገለጠ ነገር በማኅበረሰባችን ውስጥ ከበሬታም ዋጋም ያገኛል፡፡ በላዩ ላይ አወ ሳሰዱ፣ አመራረቱ፣ ይዘቱ እና አገልግሎቱ የሚያበቃበት ጊዜ ከተነገረው ዘመናዊ መድኃኒት ይልቅ «በእኩለ ሌሊት፣ ዶሮ ሳይጮኽ፣ ሰው ሳያይ፣ በጋቢ ተሸፋፍኖ፣ በነጭ እንጀራ ውስጥ፣ ፊትን ወደ ምዕራብ አዙሮ» የሚወሰደው የአበሻ መድኃኒት ልዩ ክብር አለው፡፡ ለምን ቢባል ከተገለጠ ነገር ይልቅ የተሸፋፈነ ነገር ክብርም ዋጋም አለውና፡፡ ዐዋቂው ይህንን ሁሉ ያሉት አንድ ነገር ቢኖራቸው አይደል?

  ReplyDelete
 27. Ante Rasih And Neger Kemsehal Mesel endih Yetmitisifew... Bicha Kale Hiwot Yasemah

  ReplyDelete
 28. እውነት ብለሀል ዳኒ፡አንዳንዴ ግን አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንደሚባል በማይመለከተንና በማያገባን የሰዎች ጉዳይ እየገባን እውነታውን ስናውቅ ምነው ሳለውቅ በቀረብኝ ኖሮ የምንል አለንና፡፡ እኛን በማይመለከቱንና በማያገባን ጉዳይ ላይ አንድ ነገር አለ /እኔን አይመለከተኝም/ብሎ በደናው ማለፉ ሳይሻል አይቀርም እላለሁ፡፡
  አዜብ ዘሚኒሶታ

  ReplyDelete
 29. I do believe that we afraid to demystify that "Ande Neger" partly because we haven't had raised in a more transparent family and partly because we haven't had a benign governor/leader. In effect, we ended up wrapping ourselves in a rather subjective opinion and keep on understanding things in our own little world as a tortoise in it's own shell. Moral of the story: We have to unveil the subjectivity veil and we have to try to discern issues in more objective pattern!

  Ye Tena Tabia folk (Kebele 03)
  Bahirdar

  ReplyDelete
 30. አንተስ ያለአንድ ነገር ይህን ጻፍክ? አንድ ነገር ቢኖር ነው እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 31. ሰላም ላንተ ይሁን ዲ/ን ዳንኤል፡፡
  ስነ-ቃላችንስ ሾላ በድፍኑ አይደል እንዴ እሚለው ታዲያ ውስጡን ከፍተን ብናየው ትሉ ሊኖር ነው ትሉ ካለ ደግሞ መብላታችንን ልንተወወው ነው፡፡ ስለዚህ በልተን እንታመም/ሳናውቀው እንጠቀም/ ይመስላል የህብረተሰባችን አመለካከት፡፡
  ቃለ ህይወትን ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፡፡

  ReplyDelete
 32. እንደምን ዋልክ ዳኒ!
  አንዲት ተለዋጭ ቃል መምጣቷን መዘንጋት የለብህም። «የማታውቀው/ቂው ነገር አለ» የምትለዋን። ብዙ ሰዎች እኔን ጨምሮ ለሽንፈታችን መሸፈኛ የምንጠቀምባት መሆኗ አይደል?
  * ምን አለበት እሺ ብትይ? «የማታውቀው ነገር አለ»
  * ምን አለበት ብትግባቡ? «የማታውቀው ነገር አለ»
  * ምን አለበት... «የማታውቀው ነገር አለ»

  አዎ ብዙ እንድናውቅ የማይፈለግ ግን በእርግጥ የሌለ ነገር አለ።
  አምላካችን ልብ ይስጠን!

  ReplyDelete
 33. great! I is good to know the implications of such phrases

  ReplyDelete
 34. One thing i know and admire is that the Amharic language has a deep structure and is rich with idioms that can be used to express a variety of issues with beautiful live phrases.

  ReplyDelete
 35. thank you .
  i like the view and ways of expression it can be understood in many ways

  ReplyDelete
 36. እንዴ………….. አንድ ነገርማ ሣይኖር እንዴት ሆኖ
  የሆነ ነገርማ አለ!!
  ይሄ ነገር እንዴት ነው ከውስጣችን የተወዳጀው
  የሆነ ነገርማ አለ!!!! ጉድእኮ ነው!!!!
  AmanAb Hawassa

  ReplyDelete