Friday, July 8, 2011

ለቤተ መጻሕፍትዎ


ጳውሎስ ኞኞ፡- አጤ ሚኒሊክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች

አዘጋጅ- ጳውሎስ ኞኞ
አሳታሚ- አስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት፣
አታሚ- ርኈቦት አታሚዎች
ዋጋ፡- 120 ብር
ገጽ- 622
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ጉልሕ ሥፍራ ያላቸው ዐፄ ምኒሊክ የተጻጻፏቸውን ደብዳቤዎች ጳውሎስ ኞኞ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ 1978 ዓም በፊት፡፡ በዚሁ ዓመት መጽሐፉ ይታተም ዘንድ ለመነጋገር ጳውሎስ ለኩራዝ አሳታሚ ሰጠው፡፡ በኋላ ሲጠይቅ «የበላይ አካል ወሰደው» ተባለ፡፡ የበላዩ አካል ማነው? ብሎ ቢጠይቅ ግን መልስ ሰጭ አላገኘም፡፡
ይኼ 2245 የዐፄ ምኒሊክ ደብዳቤዎችን የያዘው መጽሐፍ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በአስቴር አሳታሚ ድርጅት አሳታሚነት ሰሞኑን ታትሟል፡፡
በዘመኑ የነበረውን የውስጥ ግንኙነት፣ የመኳንንት እና የመሳፍንት ሁኔታ፣ የመንግሥትን አሠራር፣ የመሪዎችን አስተሳሰብ፣ የሕዝቡን እና የኑሮውን ሁኔታ እና ሌሎችንም በደብዳቤዎቹ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያን ነገር በኢትዮጵያኛ ከጻፉልን ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው፡፡ ብዙዎቹ ምሁራን ለጆርናሎች እና ለወርክሾፖች እንጂ ለሕዝብ የሚሆን ትሩፋት የላቸውም፡፡ ጳውሎስ ኞኞ ግን እኛ የምናነባቸውን ብዙ ሥራዎች አትርፎልናል፡፡ እኔ እንዲያውም በዘመናዊ ታሪካችን ውስጥ ጳውሎስ ኞኞን ያህል ለሕዝብ የሚሆን ሁሉን አቀፍ ዕውቀት ሰጭ ሥራዎች የሠራ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፡፡
የጳውሎስ ሥራዎችን ከልጅነታችን ጀምሮ አንብበናቸዋል፡፡ አስደናቂ ታሪኮችን ብዙዎቻችን ታች ክፍሎች ሆነን ነው ያነበብናቸው፡፡ ከከበደ ሚካኤል እና ከጳውሎስ ኞኞ በቀር ለታችኛው ክፍል ተማሪዎች የሚሆን ቁም ነገር ያለው ሥራ የሠራ ሰው በዚህች ሀገር አለ?
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተካተቱት ደብዳቤዎች መካከል እጅግ ወሳኙ ደብዳቤ ራሱ ጳውሎስ ኞኞ ለጓድ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ (ነፍሳቸውን ይማርና) የጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ በወቅቱ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲካ ቢሮ ተለዋጭ አባል፣ የሀገር እና ሕዝብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስትር ለነበሩት ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ጳውሎስ የምሬት ደብዳቤ ጽፏል፡፡
በዚህ ደብዳቤው ጳውሎስ ለሀገሬ ልሥራ ባለ የሚደርስበትን እና የደረሰበትን መከራ ዘርዝሮታል፡፡ በየዘመናቱ ያሉ ደራስያን ያጋጠማቸውን እና የሚያጋጥማቸውን መከራ ነው በደብዳቤው ውስጥ የምናየው፡፡ ጳውሎስ መጽሐፎቹ ይወሰዱበታል፣ ማን ወሰዳቸው? ሲል የበላይ አካል ይባላል፡፡ ይህ የበላይ አካል ግን አይታወቅም፡፡ የሰበሰብካቸውን ማስረጃዎች በአስቸኳይ አስረክብ ይባላል፡፡ ማን አለ? ሲል የበላይ አካል ይባላል፡፡
በዚህ ምክንያት ካሁን አሁን ያለኝን ሁሉ ማስረጃ ይህ ማነነቱ ያልታወቀ የበላይ አካል ይወስድብኝ ይሆን? በሚል ሰቀቀን ውስጥ መግባቱን ይገልጣል፡፡ «የኢትዮጵያን ሕዝብ እና መንግሥት አልበደልኩምና ከሀገር እንድወጣ ይፈቀድልኝ» ብሎ አመለከተ፡፡
በዚህ ማመልከቻው ለመሣፈርያ የሚሆን ገንዘብ ለመለመን እንዲፈቀድለት፣ ከሀገር እንዲወጣ እንዲፈ ቀድለት፣ ከሀገር ሲወጣም ዶክመንቶቹን ይዞ እንዲሄድ እንዲፈቀድለት ለምኗል፡፡
የጳውሎስ ደብዳቤ መልስ ሳያገኝ የደርግ ዘመን አለፈ፣ ደብዳቤው የተሰጣቸው ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ታሠሩ፤ በኋላም ራሱ ጳውሎስ ኞኞ አረፈ፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ ግን መጽሐፉ እጃችን ገባ፡፡ ምስጋና ለቤተሰቦቹ እና ለአሳታሚዎቹ፡፡
እኔ ግን ሁለት ነገሮች ነገር ቅር አሉኝ፡፡ ምነው ለመጽሐፉ የደከመው፣ ደክሞም ያዘጋጀው፣ አዘጋጅቶም ሲታተም ሳያይ ያለፈው የጳውሎስ ኞኞ ታሪክ ሲሆን በመግቢያ፣ ካልሆነም በጀርባ ሽፋኑ ሳይጠቀስ ቀረ፡፡ ሥራው ያለ ሠሪው ምንድንነው?
ቢያንስ በቀጣይ ይታተማል የተባለው መጽሐፍ ሲታተም ስለ ጳውሎስ ኞኞ አጭር ታሪክ መካተት አለበት፡፡
 በሌላ በኩል ደግሞ ዐፄ ምኒሊክ ደብዳቤ የጻፉበትን ቋንቋ አሁን ባለው አስተሳሰብ ለማረም መሞከር ስሕተት ይመስለኛል፡፡ አንደኛ በዘመኑ ስላለው አስተሳሰብ ማወቅ የሚቻለው በቃላቱ ነው፡፡ አስተሳሰበ በዋናነት የሚገለጠው በቋንቋ ነውና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ዐፄ ምኒሊክ ስንጽፍ በራሳችን ቋንቋ እንጻፍ እንጂ እንዴት ዐፄ ምኒሊክን በእኛ ዘመን ቋንቋ እናስጽፋቸዋለን?
የአሳታሚዎቹ ችግር ይገባኛል፡፡ ግን ችግሩን ካልተጋፈጥነው ለሁለት ዘመናት የተከማቸውን የኢትዮጵያ ዶክመንት አርመን እንዴት እንዘልቀዋለን? እኛ የሞቱ አባቶቻችንን ቋንቋ መረዳት አለብን እንጂ እንዴት የሞቱ ሰዎች የኛን ቋንቋ ተረዱ እንዴት ይባላሉ
በዚህ ሃሳብ ምክንያት ብዙዎቹ ደብዳቤዎች ምኒሊክ ሳያውቁ «መታረማቸውን» ጳውሎስ ኞኞ ካሰባሰባቸው መካከልም ሁለቱ ደብዳቤዎች መቅረታቸው የችግሩን ሥር መስደድ ያሳያል ፡፡
መልካም ንባብ፡

25 comments:

 1. To whom it may concern

  Oh my God , I can't wait to get the book.
  We need to listen our fathers history, it keeps it alive if it doesn't change the words. It is a kind of live history.By the way what do you think if we videotape priest's ,known persons, and other people's voices and pictures who contribute to our country.
  I promise to start it.

  ReplyDelete
 2. Thank you D/Daniel; I hope this book will give a clear picture of the thoughts and level of understandings reflected during that time. It will tell us the real and significant contributions of Atse Minilik II to the modernization of our country-Ethiopia. Today the present regime is doing day and night to shadow these contributions of the King.....
  anyways thank you D/Dani .. and the time will come that the ture history can be spoken to the generation ....

  ReplyDelete
 3. ዲን ዳኒ: እኔ የሚገርመኝ ያንተና የይስማዕከ የብዕር ኃይል ነው:: ማንም የማንበብ ዝንባሌ የሌለው ሰው በግድ እንዲያነብ ይገፋፋል አቀራረባችሁ:: በዚህ በጣም የሚበረታታ አቀራረብ ስላላችሁ በርቱ እላለሁ:: ሌላው ደግሞ በጣም የሚገርመኝ ነገር ራማቶሓራ በሚለው መጽሓፉ ላይ እንደዚሁ ጸሓፊዎችን ሸንቆጥ የሚያደርግ አቀራረብ ተጠቅሟል ይስማዕከ፤ ቃል በቃል ባላስታውሰውም መልዕክቱ ወቅቱን ጠብቆ የማይጽፍ ደራሲ ለሙያው ተገዥ እንዳልሆነና ድርሰቱ በኋላ ዘግይቶ "በወቅቱ ያለውን መንግስት ፈርቼ ነው" ብሎ ቢያቀርብ የማይጠቅም መሆኑን ያትታል:: እናም ከአቀራረብህ እንደምረዳው የያኔው የጳውሎስ ኞኞ ትጋት ከዛሬው ከይስማዕከ ትችት ያመለጠ ይመስለኛል::

  በዚሁ አጋጣሚ ግን እንደዚሁ የአንዳንድ መጻሕፍትን አቀራረብ ጨምቀህ ብታቀርብ የማንበብ ፍላጎታችንን ከመጨመርህ ባሻገር ለባለመጻህፍቶቹም ጥሩ ማስታወቂያ ሠራህ ማለት ነው አስበዋ 1ሚሊየን አንባቢን ባተረፈ "ብሎግ" ላይ አንድ መጽሐፍ ቀረበ ማለትኮ ቀላል አይደለም:: ያንተንም ማሕበራዊ ነክ መጻሕፍት እዚህ ላይ በታስተዋውቀን ጥሩ አማራጮች ናቸው:: ቸር እንሰንብት "ቺርስ"

  ReplyDelete
  Replies
  1. Man .... ye yismaeke fiction ketemecheh u r in trouble ... beunet new yemilih ... except some conversation all the main ideas r damn ... have u seen the davinchi code? off course all the idea of yismaeke is derived from it .... but the code braking is not like "sebatenyaw sininy sostenyaw kal" bla bla ... it needs deep mathematics like phi with all its seasonings .... as we see the davinchi code ... all in all this bloody dertogeda is damn childish!!!!

   Delete
 4. D Daniel Tiru eyeta new tks!D Daniel please ..
  adis neger enfelgalen [KEMENFESAWI ALEM] kemilew
  amedihe laye Fetari yetebikehe DANY!!
  DANIEL KE MARRY-LAND!

  ReplyDelete
 5. Tesfa Z Gofa/AddisJuly 9, 2011 at 9:55 AM

  Tesfa Z gofa/Addis
  What a nice summary and comment.I like it and keep it up. By the way, is it possible to edit History? Choice of words and style by themselves speak a lot.Therefore, it is better to forward the document as it is and let the readers and historians comment on it.Let us have the original.

  ReplyDelete
 6. To whom it may concern

  we Ethiopian want to hear and read the real situations of our country were, and we want know the real letters which were written by Atse Minilik II. God bless Ethipia.
  Daniel Keep it up

  ReplyDelete
 7. I am addicted to your articles-it has all entities: from'earth' to the 'sky. Kepp it up Dan!!

  ReplyDelete
 8. "እኛ የሞቱ አባቶቻችንን ቋንቋ መረዳት አለብን እንጂ እንዴት የሞቱ ሰዎች የኛን ቋንቋ ተረዱ እንዴት ይባላሉ?" well said....

  Thanks Dani

  ReplyDelete
 9. ይህ መፅሀፍ ግን አዲስ ነው?
  በተለያዩ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ሲጠቀስ የሰማሁት ስለመሰለኝ ነው

  ReplyDelete
 10. ዳኒ የአሳታሚዎችን ፍርሃት መረዳትህ ግሩም ነው፡፡ ግን ግን በ17 ዓመት እልህ አስጨራሽ ትግል የተገኘ የመጻፍና የመናገር መብት እያለ መፍራት ብሎ ነገር ምን አመጣው? አሁንም እንደነ ጳውሎስ ኞኞ ዘመን ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ የፈሰሰውን የፕሬስ ነጻነት የማያምን ትውልድ አለ እንዴ? ነው የጳውሎስ ኞኞ ዘመን ‹የበላይ አካል› ፍርሃት አሁንም አለ ልበል? ቢኖር ነው እንጂ ባኖርማ ኖሮ እምዬ ምኒልክ የጻፉትን ደብዳቤ (ምኒልክ እንደተናገሩት) ተብሎ እንደወረደ ለማሳተም እንቸገር ነበር? መቸም መልዕክቱን ምኒልክ በተናገሩበት ዐውድ ለመረዳት አስጋሪ ሆኖ አይደለም፡፡
  የሰዎችን አስከ ወዲያኛው ድረስ መለያየት የሚያሳይ አንድየቆየ የቋንቋ አጠቃቀም ወይም አባባል ላንሳ፡፡ ‹ከአሁን በኋላ አንተና እኔ እስላምና አማራ ነን› የሚል ነው፡፡ አባባሉ በአሁን ጊዜ ምን አልባት በአማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች የአማራ ብሔርነት የላቸውም የሚል ትርጉም ሊሰጠው ይችላል፡፡ ይህችን ነጠላ ትርጓሜም ይዞ መብታችን ተረግጧል የሚል ሙግት ሊከሰት ይችላል፡፡ በምኒልክ ዘመን የቋንቋ ይትብሃል ግን አማራ የሚለው ቃል ክርስትናን እንዲወክል ተደርጎ ገብቷል፡፡ ስለዚህ ትርጉሙ ‹የአንተና እኔ ጉዳይ መቸም ቢሆን በእምነት እንደማይገናኙት እንደ እስላምና እና እንደ ክርስትና እምነት ተከታዮች ሆነናል› የሚል ፍቺ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም በዚያን ዘመን የተጻፈን ጽሁፍ በዘመኑ ቋንቋ ዐውድ(context) መሰረት መረዳት እየተቻለ የአድሃሪ ኃይሎች ቋንቋ ነውና አብዮት አብዮት በሚሸት ተራማጅ ቋንቋ እንቀይረው፣ የኪራይ ሰብሳቢዎች አስተሳሰብ አለበትና ፈጣን ልማትንና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብን በሚሰብኩ ቃላት እንቀይረው ማለት በእኔ እምነት ከሞኝነት ያለፈ ጅልነት ይመስለኛል፡፡
  እናም ዳኒ ትዝብትህ ትዝበቴ ነው፡፡ ኅሊናን እንደወጠረ የሚያልቀው የፊውታራሪ ተክለ ሐዋሪያት ግለ ታሪክም የዚሁ አይነት የቋንቋ እርማት ችግር ገጥሞት አይቼ አዝኛለሁ፡፡ በአሁኑ የእድገት መነጽር የአለፈ ዘመን ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ አስተዳደር፣ ዕድገት፣ ስለጣኔ.㗹㜎㜎እየተመለከቱ ስህተት ነበር፣አጥፍተዋል፣ ተጠያቂ ናቸው እያሉ የመተቸት አባዜ፣ እንዲያው ይህ ጠባብነታችን፣ መቸ ይሆን የሚለቀን? የአሁኑንና ያለፈውን ማመዛዘን የማይችል ‹የበላይ አካል› እስካለ ድረስ

  ReplyDelete
 11. I like your comments.
  Thank you

  ReplyDelete
 12. Ere Dani yante ayn eko yenen yeteshefene ayn eyekefete hulun yasayegnal, endew yelibh birhan, yemastewalih, ye bierih neger... betemesito sibo bebotaw hogne ayne endiyay yaregegnal, wey gud.............. bel tebarek, yihes kelay kalteseteh kante endet yihonal! bel, yabzalih, ejig melkam alih.

  ReplyDelete
 13. this article reminds me of the event in jijiga university that culminated in removal of an important Amharic book used for reference in literature and language department upon complaint presented by students with out consulting even the instructors.the problem was only a single word that described a section of the society as 'galla'.how can we change history like Russian leader Joseph Stalin unless we take a lesson and correct it?our current leader only changed the name and letting them speak in their own language but the degree of repression and looting is of the worst in the history of Ethiopia......

  ReplyDelete
 14. Dani we miss you, where are you we need to read your blog at least every other day

  ReplyDelete
 15. i have been waiting for ur response on ur controversial article -'kekursho wedesiret". we need more explanation on that issue .i understand u have the right to have ur own position regarding ay event but his one is sensitive and ur conclusion is full of confusion and deception while the matter is clear for a layman .

  ReplyDelete
 16. ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎJuly 14, 2011 at 11:17 AM

  ዲ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተ ይሁን
  መቼም የመጽሐፉ ጥቅም አንድ ሁለት ተብሎ የሚዘረዘር አይደለም። በተረትና በቀልድ መልክ የሰማነውን ያለፈ ዘመን ታሪካችንን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መነጽር ነውና ብዙዎቻችን እንምንወደውና እንምንጠቀምበት አምናለሁ። ከዚህ ባሻገርም ባጭሩ ለማስቀመጥ የሞከርከውን ትዝብት እኔም አጋራሃለሁ። ትዝብትህ መጽሐፉን የሚያነበው ሰው በመጽሓፉ ውስጥ ያሉትን ታሪኮች እንዴት መገንዘብ እንዳለበት፣ ታሪክ ጸሀፊዎችም ለሚጽፉት ጽሑፍ ሊያደርጉት የሚገባውን ጥንቃቄ እንዲሁም አታሚዎችና አሳታሚዎችም በመጽሐፍ ሕትመት ወቅት ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ ነገር እንዳለ እጥር ምጥን ባለ ቋንቋ ነው ያስቀመጥከው።
  ቸር ያሰማን።

  ReplyDelete
 17. D.daniel how r r u ok? tefah mekrhe nafkonal menfesawy sheta yalachew kerstnachen eytften balebet bahunu wekte yematena memher yasfelgal ena mekren astnanan gesten selam une egzabher ytebkeh yabertahe. tenchwa temarhe.

  ReplyDelete
 18. D.daniel endmnhe bedhna new ytefahew? selkdemut, seltenute abatochachen lemn atngrenem be haymanot yematena new ahun yemasflgen ena asebebet wendmachen be senat komen sel haymanotchen endnsera yerdanal ena egzabeher yrdahe. tanch yemarhe.

  ReplyDelete
 19. To all and Orthodox people
  new website

  http://www.melakuezezew.info/

  ReplyDelete
 20. ዲ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተ ይሁን.
  የጳውሎስ ሥራዎችን ከልጅነታችን ጀምሮ አንብበናቸዋል፡፡ አስደናቂ ታሪኮችን ብዙዎቻችን ታች ክፍሎች ሆነን ነው ያነበብናቸው፡፡ ከከበደ ሚካኤል እና ከጳውሎስ ኞኞ በቀር ለታችኛው ክፍል ተማሪዎች የሚሆን ቁም ነገር ያለው ሥራ የሠራ ሰው በዚህች ሀገር አለ?
  thanks a lot D/n Dani.be blessed!!!
  Hailemeskel Z Maputo.

  ReplyDelete
 21. Thanks Dani,
  I agree with what you stated about the "correction" of the words and ideas made on the content of the book.I also share what led the publishers end up like this.But what ADDIS ABABA UNIVERSITY PRESS used to publish the WORKS OF NEGADRAS GEBRE HIWOT BAYKEDAGN is a good example how to deal with such problems. A.A.U. Press forwarded the whole content and words as they were written by NEGADRAS himself, nearly 100 years ago.But the press gave us explanation on some words and ideas of the book that may not be clear to the present generation using foot notes,that is a great bridge between the two generations to link each other.One of the book was published in 1953 by the son of Negadras "being corrected",but AAU Press recorrected it back now .I appreciate this move.
  I suggest the publishers of Paulos Gnogno's works to use this way out,to help us share the exact essence of the then feelings . Thanks all.

  ReplyDelete
 22. ዳኒ፤ ግሩም እይታ ነው ። በርታ !

  ReplyDelete