Monday, July 4, 2011

መኪና ያባለጋቸው


ከጓደኛዬ ጋር እያወራን በቤት መኪና እንጓዛለን፡፡ አዚህቺው አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ እኛ በወሬያችን በጣም ስለተመሰጥን ጓደኛዬ ለካስ በቀስታ ነበር የሚነዳው፡፡ ከኋላችን ያለው መኪና ጥሩንባ ሲነፋ አልሰማ ነውም፡፡ በመጨረሻ ከኋላ ወደ ጎናችን መጣና መስተዋቱን ዝቅ አድርጎ «እናትክን እንደዚህ ላድርጋት» ብሎ ተሳደበ፡፡ ከስድቡ ይልቅ የደነገጥኩት የተሳደበውን ሰውዬ ሳየው ነበር፡፡ እንተዋወቃለን፡፡ አገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው ትልልቅ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ በየሚዲያው በቀን አንድ ጊዜ አታጡትም፡፡
ሲያየኝ ከመደንገጡ የተነሣ እንደ ጉም በንኖ እንደጢስ ተንኖ ነው ከአካባቢያችን የጠፋው፡፡ ለብዙ ሰዓታት ያህል ድንጋጤዬ ሊያባራ አልቻለም ነበር፡፡ እኔ ሳውቀው በጣም ጨዋ፣ ሰው አክባሪ እና ሲናገር የተረጋጋ ነበር፡፡ ክፉ ቃል ከአፉ ሲወጣ ገጥሞኝ አያውቅም ነበር፡፡ ዛሬ ምን ነካው
እርግጠኛ ነኝ ይህ ወዳጄ መኪና ካባለጋቸው ሰዎች አንዱ ነው፡፡ ሞባይል ውሸትን መኪና ስድብን አምጥቶብናል፡፡ ቴሌ ከሞባይል ሲም ካርድ ጋር የሃያ አምስት ብር ካርድ ነው ወይስ የሃያ አምስት ብር ውሸት ነው አብሮ የሚያድለው? ያሰኛልኮ፡፡ አሁን አሁንማ የት ነው ያለህው? በሚለው ጉዳይ ላይ መተማመን አልተቻለም፡፡ ምክንያቱም አያሌ ቃላት በሞባይል የተነሣ ትርጉም ቀይረዋልና፡፡
«መጣሁ» ማለት «ለመምጣት እያሰብኩ ነው»
«ደረስኩ´ ማለት «እየተነሣሁ ነው»
«እዚህ ነኝ» ማለት «እዚያ ነኝ»
«ከታክሲ ወረድኩ» ማለት «እየተሣፈርኩ ነው»
«ከቢሮ ወጣሁ» ማለት «ኮምፒውተር ልዘጋ ነው»
«በር ላይ ደረስኩ» ማለት «ከኛ ቤት በር ልወጣ ነው» ማለት እየሆኑ ነው፡፡
ሞባይል ታድያ ብቻውን አይደለም፡፡ መኪና የሚባል ወዳጅም አለው፡፡ ያኛው በውሸት ይኼኛው በስድብ ከተማዋን እያጨናነቋት ነው፡፡
«ጅብ የነካው ሥጋ ይበላል ወይ)»ብሎ ቢጠይቀው
«ሲርብ ነው ሳይርብ» አለው አሉ፡፡
«ሳይርብ ነው እንጂ ሲርብማ እንኳን ጅብ የነካው ሥጋ ራሱ ጅቡስ ቢሆን ይበላ የለም ወይ» ብሎ መለሰለት ይባላል፡፡
አሁንም «እገሌ ጨዋ ነው ወይ ሲሏችሁ «መኪና ሲይዝ ነው ሳይዝ» ብላችሁ ካልጠየቃችሁ ጉድ ትሆናላችሁ፡፡ እግረኛ ጨዋዎችን መኪና እያባለጋቸው ተቸግረናልና፡፡
እንዴው ለመሆኑ ግን መኪና ለመጓዝ ነው ለመቅደም የተገዛው? ለምን ከማታውቁት ሰው ጋር ትሽቀዳ ደማላችሁ? ሽልማት የለው፣ ሬከርድ አይሠበር፤ ምን አለፋችሁ? አንዳንዶችማ ሰውን ማስደንበር፣ ከፊት ያለን አሽከርካሪ ማጨናነቅ የዕውቀት መለኪያ ይመስላቸዋል፡፡ በተለይ ከጎን ያለውን መኪና የምትነዳው ሴት ከሆነች ነጅው የቅርጽም የይዘትም ለውጥ ያደርጋል፡፡
ይኼ መኪና ስንቶቹን ትዕግሥተኞች ትዕግሥት አልባ አድርጓቸዋል መሰላችሁ፡፡ ሲሄዱ ሲሄዱ ሲሄዱ ሲሄዱ በሚለው ተረት እንዳላደጉ እንደ ሄሊኮፕተር በርረው፣ እንደ ጄት ፈጥነው፣ ካልሄዱ የነዱ የማይመስላቸው ነጅዎች እየበዙ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እንዲህ የሚቸኩሉት የሚያስቸኩል ነገር ኖሯቸው አይደለም፡፡ ካልቸኮሉ የነዱ ስለማይመስላቸው እንጂ፡፡
እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ በሥራ መውጫ እና መግቢያ ሰዓት መንገዱ ሲጨናነቅ እንደ ልማዳቸው መፍጠን ያቅታቸውና ሱሳቸውን ለማስታገስ መሪውን ሲገፉት ታያላችሁ፡፡ ጎማቸው ነው እንጂ ስሜታቸው በርሯል፡፡ መሪ ይገፋሉ፣ ማርሽ ይቀያይራሉ፣ ነዳጅ ይሰጣሉ፣ በበእግራቸው ፍሪሲዮን አሥር ጊዜ ይረግጣሉ፡፡
መኪናውን ትራፊኩ አልለቀው ሲላቸው እጃቸውን በመስኮት አውጥተው ከፊት መስተዋቱ በፊት ያስቀድሙታል፡፡ እጅ ብቻውን ይሄድ ይመስል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ካላረካቸው ደግሞ የተቀመጡበትን ወንበር ወደፊት በማስጠጋት ቢያንስ ለአንድ ሚሊ ሜትር ያህል ወደፊት ለመንፏቀቅ ይሞክራሉ፡፡
ሌሎቹን ደግሞ መኪና ትዕግሥታቸውን አስጨርሶ ተሳዳቢ አደረጋቸው፡፡ መኪና ላይ አራት ዓይነት ስድቦች መጥተዋል፡፡ ጨዋነታቸው ፈጽሞ ያልለቀቃቸው የመጀመርያዎቹ በውስጣቸው ነው የሚሳደቡት፡፡ አንገታቸውን ይነቀንቃሉ፣ መሪ በቡጢ ይመታሉ፣ በጫማቸው ወለል ይረግጣሉ፣ ዓይናቸውን ያጉረጠርጣሉ፡፡ አልሰማናቸውም እንጂ ውስጣቸው ባለጌ ነው፡፡ ሙልጭ እያደረገ ይሳደባል፡፡
የጨዋነትን ድንበር መሻገር የጀመሩት ሁለተኛዎቹ ደግሞ እዚያው መኪናቸው ውስጥ አፍ አውጥተው ይሳደባሉ፡፡ ልዩነቱ በመስኮት ብቅ አይሉም፡፡ መኪናዋ ራሷ የስድብ ሱስ የያዛት ይመስል ተናድደው ካልተሳደቡ አሥር ጊዜ ሞተር ይጠፋባቸዋል፡፡
የባሰባቸው ወደ ሦስተኛው ደረጃ ይተላለፋሉ፡፡ በአፋቸው የተሳደቡትን በድምፃቸው ማስተጋባት ሲያቅታቸው በክላክስ ይሳደባሉ፡፡ አንባርቆባችሁ ከአጠገባችሁ የጠፋ መኪና የለም? ከኋላችሁ ሆኖስ መብረቃዊ ጥሩንባ ያጮኸባችሁን ታስታውሳላችሁ? ያኮ «የስድቡ ሳውንድ ትራክ» ማለት ነው፡፡ ወይንም «ስድብ በክላሲካል»፡፡ ትርጉሙን አልነግራችሁም፡፡
ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል እና መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ቤተ ክህነት ግቢ ይገናኛሉ አሉ፡፡ ከዚያ መጋቤ ምሥጢር ይህንን የቤተ ክህነት አሠራር ከግራ ከቀኝ ይተቸዋል፡፡ ሊቀ ካህናትም ይሰማሉ፡፡ በመጨረሻ ሊቀ ካህናት «በል ልሂድ ወልደ ሩፋኤል ለምን ተናገረ ሳይሆን ክንፈ ገብርኤል ለምን ሰማ ነው የምባለው» አሉ ይባላል፡፡ እኔም ከተረጎምኩላችሁ እንዲሁ ነው፡፡
ከዚህ የከፉት አራተኞቹ ናቸው፡፡ ያናደዳቸውን ባለ መኪና በሰድብ ካላጥረገረጉት ከነፍሳቸው ሂሳብ የተቀነሰ የሚመስላቸው፡፡ ከዚያ ልብስ እና ከዚያ መኪና የወጣ የማይመስል ስድብ የሚሳደቡ፡፡ መንገድ ቢያጡ ነዳጅ አቃጥለው አደባባይ ዞረው በመመለስ አጥረግርገው የሚመለሱ፡፡ አንዳንዴኮ እዚህ መኪና ውስጥ የሀብታም መቃብር ነው ያለው እንዴ? ያሰኛችኋል፡፡
የሀብታም መቃብር ውጩ በቀለም እና በዕብነ በረድ አጊጦ ውስጡ ግን ሬሳ ነው፡፡ እነዚህም ሰዎች የያዙትን መኪና፣ የለበሱትን ልብስ፣ ለመኪናቸው ያለበሱትን ጌጥ አይታችሁ ካፋቸው የሚወጣውን ስድብ ስትስሙ እነርሱ ራሳቸው ከስድብ የተሠሩ እንጂ ስድብ ከአፋቸው የወጣ አይመስላችሁም፡፡
የሚገርማችሁኮ አመል ሆኖባቸው ሰው ብቻ አይደለም የሚሳደቡት፡፡ የምታቃጥል ፀሐይ፣ የሚዘንበ ዝናብ፣ የተቋተ ጎርፍ፣ የወደቀ ዛፍ፣ የተበላሸ የትራፊክ መብራት፣ የምታቋርጥ አህያ፣ ዘላ የገባች ፍየል፣ የተቆፈረ ጉድጓድ፣ የተከመረ ድንጋይ፣ ያዘመመ የስልክ እንጨት፣ የተተከለ ድንኳን፣ የተሰጣ እህል አይቀራቸውም፡፡ የመኪናቸውን መስኮት ዝቅ አድርገው ያጥረገርጉታል፡፡ ስድብን እንደ ትንፋሽ ከአፋቸው ከመውጣቱ የተነሣ ሞተሯ ሲጠፋ፣ ጎማዋ ሲተነፍስ፣ መስተዋቷ ሲበላሽ፣ የመስተዋት መጥረጊያው አልሠራ ሲል የገዛ መኪናቸውንም ቢሆን ከማቅመስ አይመለሱም፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም የሚሰድቡት ሰው ይርቅባቸውና ባለመሳደባቸው እርር ኩምትር ሲሉ አያቸ ዋለሁ፡፡ እና ምናለ እናንተ ፖስተር እና ስቲከር የምታመርቱ ድርጅቶች ምርጥ ምርጥ ስድቦችን አትማችሁ ብታከፋፍሉ፡፡ ያዋጣችሁ ነብርኮ፡፡ እነዚህ ሰዎችም ቀረብ ያሉትን በምላሳቸው የራቁባቸውን ደግሞ ፖስተሩን አውጥተው በማሳየት የልባቸው ይደርስላቸው ነበር፡፡
ስቲከሩንም ቢሆን በመኪናቸው ፊት እና ጀርባ በመለጠፍ «ታምሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ» በሚለው ብሂል መሠረት «ከሆነ በኋላ ከመሳደብ አስቀድሞ በመስደብ ነገሩን እንዳይሆን´ ያደርጉት ነበረ፡፡ የመኪና ፋብሪካዎችስ ብትሆኑ እነዚህን እንደ ሙዚቃ የሚክሸነሸኑ ክላክሶች ከምታመርቱ ለእነዚህ ሰዎች በጥሩንባው ምትክ ስድብ የሚያወጣ ክላክስ ብትገጥሙላቸው ምናለ፡፡ ኧረ ተባበሯቸው፡፡
በአንድ መንደር የነበረ አንድ ሹም እንደ ተሾመ የቀየውን ሕዝብ ይሰበስባል፡፡ ሰውዬው ሥልጣኑን ከጨዋነት በፊት ነበርና ያገኘው መንግሥትንም፣ ካህናትንም፣ ሕዝቡንም፣ አሽከሮቹንም፣ ሚስቱንም፣ ዳኞቹንም፣ እያነሳ ይሳደባል፡፡
በኋላ ታድያ እስኪ ምን ትላላችሁ? ብሎ ሽማግሌዎቹን ሲጠይቃቸው አንድ አረጋዊ ተነሡና ጌታዬ «ወይ ከሹመቱ ወይ ከስድቡ አንዱን ቢተውት ምናለ አሉት አሉ፡፡ አሁንም እነዚህ ባለ መኪኖች ወይ መኪናውን ወይ ስድቡን ቢተውት ምን ይላቸዋል?

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው
 

23 comments:

 1. Daniel ;girum Eyita new.Long live to you.mariam abizta Tibarkih Lela min Elalehu!!!

  ReplyDelete
 2. In Finland Pedestrians are given high priority, its so wonderful culture that they don't compete with pedestrians - just opposit to Ethiopian drivers.

  ReplyDelete
 3. Thank you, Daniel. We're learning a lot from your views.

  When I was a college student, I had not any contact with drivers. I have been working in a governmental organization since 2007. I always hear unwanted words from the drivers. I have asked myself why most of the drivers have the same behaviour. The secret is "Mekinaw".

  ReplyDelete
 4. ይገርማል! ብዙወቻችን በምንታወቅበት ቦታ ጭዋ በማንታወቅበት ቦታ ደግሞ የለየልን ባለጌወች ሁነን እንገኛለን፡፡

  AA from Addis Ababa

  ReplyDelete
 5. ጥሩ ነገር አንስተሃል
  በአንድ መንደር የነበረ አንድ ሹም እንደ ተሾመ የቀየውን ሕዝብ ይሰበስባል፡፡ ሰውዬው ሥልጣኑን ከጨዋነት በፊት ነበርና ያገኘው መንግሥትንም፣ ካህናትንም፣ ሕዝቡንም፣ አሽከሮቹንም፣ ሚስቱንም፣ ዳኞቹንም፣ እያነሳ ይሳደባል፡፡

  ReplyDelete
 6. SELAM D Daniel tiru meliket new! endezeh aynet ezi America yetelemede neger new!ename yetesadebekubet giza bezu new.Lalemesadeb emokralehu!!

  ReplyDelete
 7. ልክ እንደዚሁ ትልቅ የማስታወቂያ ድርጅት ያላቸው ሰው ናቸው በተለቪዢን መስኮት ሁል ጊዜ እርሳቸው ባይቀርቡ የማስታወቂያ ሥራቸው ከድምጻቸው ጋር ይቀርባል:: ቢሔራዊ አካባቢ በሰላም ሀገር "ዘብራ" ሲሻገር የተሳደቡኝ ተመሳሳይ ስድብ ሁሌ አይረሳኝም::

  እርሱስ ይሁን እንደው መድረክ ላይ ሲወጡ "የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ ሆኖልኝ: ዕድሜውን ያርዝምልኝ፡ ምስጋናዬ ልክ የለውም...ወዘተ" ለምን ይሄ ሁሉ ውሸት ይንቆረቆራል? ነው ወይስ የኢትዮጵያ ህዝብ እግረኛውን አይጨምርም? አለበለዚያ ሁለት ዓይነት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አሉ ማለት ነው: የተለቪዢንና የገሃዱ ዓለም ኢትዮጵያዊያን::

  ReplyDelete
 8. That is why a lot of Ethiopians are driving in America's highways by taking down their windows and out their arms. When you get used to something, it is very hard to quit it.

  By the way, those kinds of people are the one who commit accidents and consequently being in jail or live short period of time. The more being disrespectful, the fastest we call our deaths.

  What I don't understand always is that the chance of meeting each other on the highway driving is almost zero. So, why being disrespectful for people, whom we don't know?

  We have hotline numbers to notify the police, if we see somebody driving recklessly. Insulting doesn't change anything. If we want the reckless driver to learn his/her lesson report him/her for the police instead of insulting a person who we don't even know.

  ReplyDelete
 9. በተለይ ከጎን ያለውን መኪና የምትነዳው ሴት ከሆነች ነጅው የቅርጽም የይዘትም ለውጥ ያደርጋል፡፡this is about me.

  ReplyDelete
 10. Dear Daniel,

  When I went through with your article last week, I was amazed that I have the same observation.

  Because of my nature of the Job I travel a lot. I have seen Mumbai, Nairobi, Kampala, and others who have a serious and highly complicated traffic jam in the world. And yet, I have never seen a place like Ethiopia where people are not tolerating a simple traffic jam in a rush time. It is a common practice that almost all drivers are competing even to be one car ahead. Above all, most of us are driving even with wrong direction.

  If someone driving a 4WD or a new car he/she doesn't like to see others in front of them. They pretend like the road is only for them. They assume everybody should leave the road to them.

  It is not unique that Ethiopians are also misbehaved when they are deriving while raining. They don't care for others. It is a common practice that they bath someone on the street with a dirty water.

  Moreover putting horn, insulting which one can not tolerate, and recklessness are the common character of the drivers in Ethiopia. From this perspective I analyze that we have had a hidden naughty characteristic.

  It is vivid that "The Fear of Lord is the Beginning of wisdom." So, how can we honor God by despising his own creature with his image. For me, this article inspire us to reconsider our bad characteristics.

  This article is striking our heart and mind to cheek how we are behaving beyond our cultural norms and values. Thus we should reconsider ourselves to remain as humble as possible.

  ReplyDelete
 11. Dear Daniel,

  When I went through with your article last week, I was amazed that I have the same observation.

  Because of my nature of the Job I travel a lot. I have seen Mumbai, Nairobi, Kampala, and others who have a serious and highly complicated traffic jam in the world. And yet, I have never seen a place like Ethiopia where people are not tolerating a simple traffic jam in a rush time. It is a common practice that almost all drivers are competing even to be one car ahead. Above all, most of us are driving even with wrong direction.

  If someone driving a 4WD or a new car he/she doesn't like to see others in front of them. They pretend like the road is only for them. They assume everybody should leave the road to them.

  It is not unique that Ethiopians are also misbehaved when they are deriving while raining. They don't care for others. It is a common practice that they bath someone on the street with a dirty water.

  Moreover putting horn, insulting which one can not tolerate, and recklessness are the common character of the drivers in Ethiopia. From this perspective I analyze that we have had a hidden naughty characteristic.

  It is vivid that "The Fear of Lord is the Beginning of wisdom." So, how can we honor God by despising his own creature with his image. For me, this article inspire us to reconsider our bad characteristics.

  This article is striking our heart and mind to cheek how we are behaving beyond our cultural norms and values. Thus we should reconsider ourselves to remain as humble as possible.

  ReplyDelete
 12. የእኛ የእግረኞችም ችግር ነው፡፡ ባለመኪናዎቹ የሚሳደቡት ባለመኪናዎችን ብቻ ሳይኖን እግረኞችንም ጭምር ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መንገድ አቋርጠን ስንሻገር፡፡ እነሱ በእግራቸው ተጉዘው የሚያውቁ አይመስሉም፡፡

  ReplyDelete
 13. Yihe hulu Mekani yelelachew were new....kkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 14. አንዳንዱ ሹፌር የብልግናው ጣራ ለእግረኛ ዜብራ እራሱ እንስሣው ቢቆም አይቆምም አይደለም ቀርቶ ለተሰመረ መስመር:: ምን ይሻለን ይሆን!

  ReplyDelete
 15. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel,
  But I want to mention something which i noticed only by living in America for so long. Ethiopians are way better than some American drivers. As we all know it is called road rage in America where some drivers shoot other drivers just because they cut infront of them. These people get so irritated when a driver behind or on the side pass and get in front of them. Thats the reason why they kill a lot of innocent drivers. So far, we have not seen something this bad in Ethiopia. I hope it doesn't start happening soon since the drivers are getting so impatient.

  ReplyDelete
 16. ዲያቆን ምትኩ አበራ ከአ.አ.July 8, 2011 at 10:35 AM

  ዳኒ ይህንን ጽሑፍ ሳነብ በቅርቡ አንድ ባለ ሀብት የነገሩኝ ትዝ አለኝ።ሰውየው ከውጭ መጥተው ነው ኢትዮጵያ ውስጥ “ኢንቨስት“የሚያደርጉት ጫንጮ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ትልቅ ሆቴል አላቸው።በዚህ ጽሁፍ የተጠቀሱትን መኪና ያባለጋቸውን ሰዎች በተመለከተ ሲናገሩ በጣም ተማረው ቢሆንም ለራሳቸው መፍትሄ ያሉትን እየተጠቀሙ ነው መኪና ስነዳ የላሉ ሰውየው።መኪና ስነዳ ሦስት ነገሮች እይዛለው ሽጉጥ፣አጭር ዱላና ጉማሬ ለምን ስላቸው መኪና ያባለገው አፉን ሲከፍት መኪናዬን አቁሜ እወርድና በዱላው አቀምሰዋለው የዘመኑ ሰው ነኝ ለሚለው ደግሞ ሽጉጤን ይዤ እወርድለታለው አሉኝ አለንጋውስ ስላቸው አለንጋዋ በየመንገዱ እናትን አዝማች አድርጎ ለሚሳደበው ባለጌ ነው ነበር ያሉኝ።ያጋጠመዎት ክፉ ነገር ይኖር ይሆን ስላቸው ሁሉም እኮ ሽነታም ነው ጉልበቱ ምላሱ ላይ ነው ዱላዬን መዥረጥ አድርጌ ከመኪናዬ ስወርድ ሩጫውን የሚያስነካው የመኪና ባለጌ ነው የሚበዛው ነበር ያሉኝ…………………..

  ReplyDelete
 17. Yewesten new yetenagerkew. Betam amesegenalehu.

  Egn egeregnoch eko nen yabalegenachew. Hegu legna kedemya eyeseten ,menged komewe seyasalefun eyamesegenen ena eji eyenesan eko balegu. Bahelachen ante tebes anchi tebeshe, ante kedem anchi kedemi neber le balemekenochu gen "hule ene lekedem" new mesel behilu. Lebona yestachew, lela men yebalal.

  ReplyDelete
 18. I will read/show this to all my staff members! either they are members of insulting group or offended many times or otherwise.

  ReplyDelete
 19. this realy intersting danie thank you for your message

  ReplyDelete
 20. yegna hager ye ashkerkariwoch neger yehone mela yasfeligewal. beteley kilakisin betemelekete. ine ahun yalehubet hager(Norway) kilaks dimts kesemahu yehone kefitegna adega liders mehon alebet . yalebelezya gn le igregna kidmiya silemisetu, tetebabkewu sileminedu ina keminim belay yesewun selam merebeshn atibikewu silemiferu kilalks fetsmo ayasemum. betekaraniwu igna hager andegna abzagnawun gize yesewun sihtet menager sileminiwed yihon inja lemifeterwu iyandandu sihtet kilaks yideregal , irasun inde astemary ina kechy adirgo kilaks kaladeregena weto kaltesadebe mehed maychil ashkerkarin mengedu yikuterewu. huletegna sewu lemetirat ina selam lemalet hulu kilaks yideregal, yihegnawu demo silelelawu hibreteseb gilawy selam kalemechenek yemeta yimeslegnal . yihegnawu indiawum ethiopiawiyan sewu akbari nen milewun neger tirgum yasatabignal. yemechereshawu demo leserg ina leye girigiru yeminefawu kilaks newu igzer yasayachihu and sewu lagebawu lelawu kilaks mesmatu min tirgum alewu. inde ine iko mushirochu mefeterachewun lalak chilalehu gin yesergachewu let klaks argewu inen yirebishugnal ine inde gileseb yalemerebesh mebt alegn inesu demo betekaraniwu yemerebesh mebt yelachewum gin bemalakewu mikniyat sirebesh igegnalehu betam askign meselegn yihegnawu demo.....

  ReplyDelete
 21. ውድ ዳንዔል፤
  ድንቅ እይታ ነው! በቅርቡ በሥራ ተለይታኝ ከዋለች ባለቤቴ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን በተቻለ ፍጥነት በእግረኛ ማቋረጫ ስንሻገር አንድ ሾፌር/ባለመኪና በመኪናው መስኮት አንገቱን አውጥቶ ምን አለኝ መሰላችሁ «ምን አለበት ቤት ብታቅፋት!» የሚገርመው ያፍ አመል ሆኖ እንጅ መቼ አቀፍኳት?
  መልካም እይታን አምላካችን ያድለን!

  ReplyDelete
 22. I am from Atlanta from Mehaber Kidusan thank you kale Hiwot yasemah deacon Daniel long live God,saint Mary have given you,serv you!I want see you I've been harry! until gubae.

  ReplyDelete
 23. Thank you brother

  ReplyDelete