Tuesday, June 7, 2011

የምስጋና እና የይቅርታ ሰሞን


የምስጋና ቀን የሚለው ጽሑፍ ከወጣ በኋላ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ብዙ አንባብያን በስልክ እና በኢሜይል ሃሳባቸውን ልከውልኛል፡፡ በጽሑፉም ላይ አስተያያት ሰጥተዋል፡፡

አንዳንድ አንባብያን ይህ ነገር ከንቱ ውዳሴን እንዳያባብስ ያሠጋል ብለዋል፡፡ ሥጋታቸው አይከፋም፡፡ ከንቱ ውዳሴ ማለት ግን አንድን ሰው «እግዜር ይስጥልኝ» በማለት የሚመጣ አይደለም፡፡ ሰውን ያለ ዐቅሙ እና ያለ ሥራው እየደጋገሙ በማመስገን የሚመጣ እንጂ፡፡

በሌላም በኩል ደግሞ ነገሮችን ሁሉ በጻድቃን ዓይን ማየት ያለብን አይመስለኝም፡፡ እነርሱማ እንዲያውም መመስገን አያበረታታቸውም፡፡ ይህንን ደረጃ አልፈውታልና፡፡ አሁን እየተነጋገርን ያለነው ስለ እኔ እና ስለናንተ ነው፡፡ እኛ አይደለንም ወይ «እጄ ዐመድ አፋሽ ሆነ» የምንለው፡፡ «በልቶ ካጅ፣ ምስጋና ቢስ፣ የበላበትን ወጭት ሰባሪ፣» እያልን የምናማርረው እኛ አይደለንም ወይ፡፡

አንዳንድ ወገኖቼ ሰው መልካም መሥራት ያለበት ለመመስገን ሳይሆን ለጽድቅ ብሎ ነው ብለዋል፡፡ ልክ ነው፡፡ ሲሠሩ መመስገን እና ለመመስገን ብሎ መሥራት ግን ይለያያሉ፡፡ በሌላም በኩል ለፈጣሪ ብለው እና ጽድቅን ብቻ አስበው የሚሠሩ ወገኖቼን ይህ ጽሑፍ አይመለከታቸውም፡፡ የእነርሱ ደረጃ የተለየ ነው፡፡ የሚመለከተው እኔን መሰሎቹን ደካሞች ነውና፡፡

እንደ እኔ በማኅበረሰባችን ላይ ከንቱ ውዳሴ ካመጣው ጉዳት ይልቅ ለበጎ ሠሪዎች ዋጋ አለመስጠታችን ያመጣው ጉዳት የሚብስ ይመስለኛል፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድ ሰው መጥቶ «መመጽወት እፈልጋለሁ ከንቱ ውዳሴም እፈልጋለሁ አለው፡፡ ዮሐንስ አፈ ወርቅም «ሳትመጸውት ብትቀር አንተም ነዳያንም ትጎዳላችሁ፤ ለከንቱ ውዳሴ ተብሎ ሳትመጸውት ከምትቀር እየመጸወትክ በነዳያኑ ጸሎት ከዚህ ፆር ብትድን ይሻላል» አለው ይባላል፡፡

አባቶቻችንኮ «ወድሶ ለሰብእ በዘኢኮነ ድልወ» ይላሉ፡፡ ሰውን ባልሆነው ነገር እንኳን አመስግነው ማለት ነው፡፡ ሳልሠራ ይህን ያህል ምስጋና ያገኘሁ ባደርገውማ ምን አገኝ ነበር ብሎ ይበልጥ እንዲተጋ ይላሉ፡፡

እናም እንደ እኔ እንደ እኔ አያሌ ሰዎች በጎ ሠርተው በጎ መሥራቸውን እኛም፣ እነርሱም ሳናውቀው እያለፉ ነው፡፡ የበጎ ነገር አርአያም እያጣን ነው፡፡ እነዚያ በጎ አድራጊዎችም ያመጡትን ለውጥ ስለማያውቁት በበጎ ሥራቸው አይበረቱበትም፡፡ አሁን ለምሳሌ መምህሮቻችን ተማሪዎቻቸው ምን ላይ እንዳሉ፣ እነርሱ ባስተማሩት ትምህርት ምን ሀገራዊ ለውጥ እንደመጣ ቢያውቁ አይበረታቱም ትላላችሁ?

አንድ ወዳጄ ደግሞ ከመቀሌ ደውሎ «ይህ ቀን የምስጋና እና የይቅርታ ቀን» ቢሆን ብሎኛል፡፡ የሚደንቅ ማለፊያ ሃሳብ ነው፡፡ በዚሁ ቀን የምናመሰግናቸውን ማመስገን ይቅር ልንላቸው፣ ወይንም ይቅርታ ልንጠይቃቸው የሚገቡትንም ይቅር ማለት ወይንም ይቅርታ መጠየቅ መልካም ሃሳብ ነው፡፡

የኮሙኒኬሽን ባለሞያዎች የአንድን ማኅበረሰብ ማኅበራዊ ጤና ለመጠበቅ ሁለት ቃላት ይበቃሉ «አመሰግናለሁ/እግዜር ይስጥልኝ» እና «ይቅርታ» ይላሉ፡፡ The Two Most Powerful Words  ይሏቸዋል፡፡


አንዳንድ ወዳጆቼ «ይህንን ነገር በየጊዜው እናድርገው እንጂ ምን የተለየ ቀን ያስፈልገዋል» ብለዋል፡፡ መልካም ለተቻለው፡፡ የክርስቶስን ትንሣኤ በፋሲካ ቀን እንድናስበው ማድረግ ሌላ ቀን አናስበው ማለት አይደለም፡፡ የሰው አአምሮ ግን ማስታወሻ ያስፈልገዋልና ነው የተለየ ቀን የተወሰነለት፡፡

እናም እስካሁን በመጡት ሃሳቦች በጳጉሜ ወር የሚለው የብዙዎች ሃሳብ እየሆነ ነው፡፡ እስኪ የጳጉሜን ወር ለዚህ እንጠቀምባት፡፡ አምስት ወይንም ስድስት ቀን ናት፡፡ በእነዚህ ቀናት ልናመሰግናቸው የሚገቡንን ሰዎች እና አካላት እናመስግናቸው፡፡ ስልክ ደውለን፣ ደብዳቤ ጽፈን፣ በአካል ተገኝተን፣ ከተቻለም የማስታወሻ ስጦታ አዘጋጅተን እንላክላቸው ወይንም እንስጣቸው፡፡

ይቅር ልንላቸው የሚገቡንንም ይቅር እንበል፤ ይቅርታ መጠየቅ ያለብንንም ይቅርታ እንጠይቅ፡፡ ጳጉሜን የዓመቱ መዝጊያ ናትና ዓመቱን በምስጋና እና በይቅርታ ብንዘጋው ምናለ፡፡ መንግሥታትም በዚህ ጊዜ ነው ለእሥረኞች ይቅርታ የሚያደርጉት፡፡

እስኪ ከዘንድሮ እንጀምር፡፡

39 comments:

 1. ቅዱስ ሐሳብ ነው፡፡ አብዛኞቻችን በቀል እንጂ ይቅርታ ጀግንነት አይመስለንም፡፡ አንድ ሐሳብ ልጠቁምህ-ቀን ሆኖ በብዙ ሰው ዘንድ ከመከበሩ በፊት የይቅርታ የመወያያ ሐሳቦችን ፖስት አርግ እና open the door for discussion. This way u can make things as subtle as they can get; and will eventually arrive @ a purpose.

  ReplyDelete
 2. ግሩም ሃሳብ፡፡ እግዜር ይስጥልን!!!

  ወርሃ ጳጉሜን
  የምስጋና እና የይቅርታ ሰሞን
  ሃሳቡን ያስፈጽመን
  አሜን!!!

  ReplyDelete
 3. Right view at the righp time.

  ReplyDelete
 4. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በረድኤት ይጠብቅልን፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
  ሁልጊዜ በጎ በጎውን መመኘት እና ማድረግ መቸም ቢሆን ማንንም ጎድቶ አያውቅም፤ ሁሉንም ግን ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ በጎ ማድረግን ከይቅርታና ከምስጋና ጋር ብንጀምረው እጅግ ማትረፊያ ነው፡፡ ኧረ እግዚአብሔር ትንሣኤ ኅሊና ወልቡናን አድሎ የይቅርታና የምስጋና ሰዎች ያድርገን!!!!!!
  መጣዓለም አማረ፡ ኮምቦልቻ ደ/ወሎ

  ReplyDelete
 5. ዲን. ዳንኤል በጣም ጥሩ ጊዜ ነው የተመረጠው! እንግዲህ ጥሩ የይቅርታ መንገዶችን እናገኝ ዘንድ እንዲሁም ጥሩ የመልካም ሥራ ማበረታቻዎችን መልካም ለዋሉልን እናደርግ ዘንድ ቀኖቹንም በአግባቡ እንጠቀምባቸው ዘንድ ስለ ይቅርታ እና ስለ መልካም ሥራ ምስጋና አቀራረብ እና ጥቅም እንዲሁም የመወያያ ርዕሶችን ብታዘጋጅ መልካም ነው!
  ይቅርታ አድራጊውም ሆነ ይቅርታ ጠያቂው እንዲሁም በጐ ሥራ የተደረገለትም ሆነ ምስጋና ተቀባዩ በልባቸው ለዚህ ተግባር ልባቸው የቀና ይሆን ዘንድ በፌስቡክ ወይም በዚህ በብሎግህ የድርጊት መርሃግብር አዘጋጅተህ ሰው በያለበት ይህንን ተግባር በመፈጸም ወርሃ ጳጉሜን እንዲያሳልፍ ብታደርግ ጥሩ ነው!

  ReplyDelete
 6. It is a wonderful idea I will do it this year. thank you Daniel

  ReplyDelete
 7. ይሄ የኔም ሀሳብ ነው። ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 8. "እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም። መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።"ማር4:38 መምህር ሆይ የወቅቱ የቤተክርስቲያን ፈተና አይገድህምን?

  ReplyDelete
 9. Germ Asab Betely Le Ethiopianoch Betam asfelagi Yimeslengal.

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንኤል እጅግ በጣም ጥሩ ሃሳብ ነው ያነሳኻው የጳጉሜን ሳምንት በይቅርታና በምስጋና ማሳለፍ ከምንም በላይ የሰውን አእምሮ እና አስተሳሰብ ወደ መልካምነት ይመልሰዋል:: ሰው አዲስ ዓመት ለመከበል ብሎ የሚበላና የሚጠጣ ነገር እንዲሁም የሚለብሰው ላይ ሲረባረብ የሚታይበት ብዙሃኑ ራሱን የሚጎዳበት ሰሞን ሆኖ የሚታይበት ነውና አንዳንድ አባቶች ይህን ሳምንት በጾምና ፀሎት በማሳለፍ ይጠቀሙበታልና ሙሉ ያሳለፈውን የጳጉሜን ሳምንት በይቅርታና በምስጋና ማሳለፉ ብሎም ቀን ወስኖ መጠቀሙ መልካምና ይበል የሚያሰኝ ነውና በዚሁ ይቀጥል::

  ReplyDelete
 11. ዳኒ እግዚአብሔር ያበርታህ፡፡ አወ የበደሉንን ይቅር እንበል፣ ያደረጉልንንም እናመስግን፡፡ ጳጉሜ ደግሞ የእኛ የኢትዮጵያዊያን ልዩ ናት፡፡

  ReplyDelete
 12. danie that is a good aydu
  iya

  ReplyDelete
 13. This is excellent which will bring very good things in our life let alone for Ethiopia but for the world.
  We should take good things from other culture like hard work,systematic work ,thanks giving day ,mother day,father day ,family day and so many.Technology is advancing due to sharing from one profession to other,learning of each other's culture.
  We celebrate bad(sin) doing day without setting most of our day. I think we need to set pagme for thanks giving and apology day.And those who believe on the idea start it."To finish a job ,start it".

  Do we hate educational materials prepared by foreign countries. No, so let us learn good.

  As we plan for our life including spiritual let us plan for good habits.

  some people in the world plan for doing bad and it is easy for us to copy this bad ,if we are going to learn ,learn the good.

  sharing is happiness,variety is a spice of life.

  ReplyDelete
 14. sile kentu wudase

  If people are feeling kentu wudase while most people
  in the world are suffering from this world problem like poverty,hatred,lose of hope,lose of love,economy,disease.It will be funny to say kentu wudase at this time.It seems personal respect then serying GOD our, FATHERS were scarified even for bad. We have to scarify our kentu wudase for the innocent christians,if thought word of God could do more than us.We are blocking their way.But all depends on our gift.
  To avoid the fear of kentu wudase- remind yourself

  1.I need to do for the people of the world
  2. Why many professors ,scientists who created new think discontinue their work?

  3.we are just pipes-God is working,as long as we are with God ,He will work.

  4. We have to know our capacity, what ever we feel will not give us kentu wudase,there are many to do.

  5. Read what our fathers did, it will be reference

  6.Know the problem of our church(individuals, group,the building)and compare with the effect of kentu wudase on one person.

  7.Think of your family- we are doing every possible effort for our family, but do not feel any kentu wudase. This is our responsibility and obligation. Feel spritual thing is same, we are family with GOD.

  sharing is happiness,variety is a spice of life.

  ReplyDelete
 15. ቆንጆ ህሳብ ነው ይሁን ብለናል

  ReplyDelete
 16. ውድ ወንድሜ እረጅም እድሜ ይስጥልኝ። አያቴ ስታሳድገኝ ሁሌ ከህሌናዬ የማይጠፋና የማስታውሰው ቃል አለ፡አምላኬ ይህን አይንሳኝ። እኔም እንደ እርሷ ይህን ማለፊያ የሆነውን መዐድ እግዚአብሔር አሳይቶ አያንሳኝ። ከልብ ተቀምረው የሚወጡ መልዕክቶችህ የዘወትር ምግብ ሆነውኛልና። ለራሴ ቃል ገብቻለሁ--ለዛሬ ማንነቴ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉልኝን ሰዎች ለማመስገን። ትናንት ሁለተኛ ደረጃ ስማር የትምህርት ቤት ደብተር የሚገዛልኝ ከተወለድሁበት አካባቢ የሚሰራ አንድ የዲፕሎማ ምሩቅ ነበር። ዛሬ ግን እኔ በውጭ አገር የፒ.ኤች.ዲ. ትምህርቴን እከታተላለሁ። እኔ ውለታ ቢሱ ይህን ሰው አይደለም መርዳት ጠይቄው አላውቅም!
  ወንድሜ አመሰግንሃለሁ። ወደ ማንነቴ ተመልሼ የመጣሁበትን እንዳስብ አድርገኸኛልና! እግዚአብሔር አሁንም ከክፉ ይጠብቅህ።
  ወንድምህ

  ReplyDelete
 17. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በረድኤት ይጠብቅልን፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 18. betam yemidegef hasab new dani EGZIABHER yechemerbet mechem yemelkam neger telat aytefamena AMELAK bertat yesten AMEN. MEKLIT BESUFEKAD NEGNE.

  ReplyDelete
 19. I like this nobel idea.

  ReplyDelete
 20. Dear Daniel,

  One can not deny there are people who are selfless. I knew many people who assist others without considering a return, even if the powerful words such as "thank you". Thus, I believe that gratitude could not forced people to do something for the sake of it. Actually, gratitude and forgiveness are the pillar of Christianity too.

  ReplyDelete
 21. For your information in a small research I made a year ago on sale of Post cards statistics shows that Sorry Cards are hardly sold but among others Thank you, Birthday and Holiday greetings, and congratulations cards are sold the last one being the highest.

  Couldn't that imply that our people do not say sorry . But for me I have already concluded that We Habesha people don't say sorry. Please help if you can disproof this.

  ReplyDelete
 22. ዳኒ ግሩም ሀሳብ ነው፡፡ አሮጌውን አመት በምስጋና እና በይቅርታ ፈፅመን፣ አዲሱን አመት ያመሰገነም እረክቶ ይቅር ያለም ይቅር የተባለም ተደስቶ በመልካም መንፈስ ይቀበላል፡፡

  ያድርሰን ያርግልን

  ማሂ

  ReplyDelete
 23. Thanks I will try every years Know start today.
  urs.

  ReplyDelete
 24. Danie,I heard news that the Australians have there own special day named as Sorry day which celebrate annually to redress the past injustice. We Ethiopians needs this things very badly. We should appreciate peoples for their good performance.In my part, I feel that there are so many respected peoples behind my educational success.It belongs to be a warm gratitude and appreciative gift or letter to them. It is a good perspective Danie. Haileyesus, from Debre Markos University.

  ReplyDelete
 25. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
  ለያዥ ለገላጋይ የሚያስቸግረውን የይቅርታ ልማዳችንን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ማስቀረት ከቻልን እጅግ መልካም ነው፡፡
  ሰው ላደረገልን ነገር ‹‹እግዚአብሔር ይስጥልኝ›› ማለት ተገቢ ነውና ይህንን ባህል የሚያዳብር ይልቁንም ደግሞ ያለፉ ትውስታዎቻችንን እያሰብን እግዚአብሔርንም እንድናመሰግን የሚገፋፋ ስለሆነ ሀሳቡ የሚደገፍ ነው፡፡
  በተረፍ ማስታወሱን ግን እንዳትረሳ፡፡

  ReplyDelete
 26. 1. Puagme every year.
  2. Day 29&30 every
  monz.
  3. Sunday every week.
  4. At night every day.

  ReplyDelete
 27. ዘሐመረኖህJune 8, 2011 at 2:58 PM

  ድንቅ ሃሳብ ነው ሰዎች ላደረጉልን መልካም ስራ ማመስገናችን ተገቢ ነው እነሱን ከማበረታታት አልፎ ለሌሎች አርአያ ይሆናል ብዙ ጥቅም አለው ሆኖም እርስ በእርሳችን ስንመሰጋገን በመሃል እግዚአብሔርን ማመስገናችንን እንዳንረሳ በዚህ ቀን በቅድሚያ እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገር ሁሉ እናመስግን በርግጥ ፍጥረት ሁሉ ዓመቱን ሙሉ ፈጣሪን ለማመስገን ስለተፈጠረ በዚህም ቀን ማመስገን ይጠበቅበታል ይቅርታ መጠየቁም ሆነ ይቅርታ ማድረጉ ተገቢና መንፈሳዊም ነው ሆኖም በቀን ውስጥ ሰባ ጊዜ ሰባት ይቅርታ ማድረግ እንደሚገባንና በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ ኤፌ 4 27 ስለታዘዝን ዓመት ጠብቀን ብቻ ሳይሆን ምንጊዜም ይቅርታ ማድረግና ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባን እንዳንዘነጋ ሆኖ በዚህም ቀን ይቅርታ መጠየቅም ሆነ ይቅርታ ማድረግን ብንፈጽም መልካም ነው

  ReplyDelete
 28. Dn.Dani ejig betam tiru hasab new mechem eskahun begna bahil yetlmedew sewun selseraw sera bekumu mamsgen sayhon sele seraw menkef new aleyam ya sew kezh alem kalefe bewala yelele chmamro weym ya sew asebot yemayawukewun neger endh neber endh serto..... malet new ena ahun yehe yemisgana ke ejig tiru hasab new .Lewegenu bego negern yaderg ersu manew ?enamsgenew yele yele metshafu.

  ReplyDelete
 29. I love the idea and God may open our heart to do it. Okay now Dn. Daniel Kibret you know what your part is follow up and take a survay just to know how many people use it and also you have to encourage people until they adobpt it.
  God be with forever.

  ReplyDelete
 30. እጅግ የሚደነቅ ሃሳብ ነው ብዙሃኑ ጰግሜ ለአዲሱ ዘመን መቀበያ የጾምና የጸሎት ጊዜ ያደርጋታል። በዚያውም መልካም ነገር የሰሩልንና የምናመሰግንበት እኛ ድግሞ ከልብ ይቅርታ የምናደርግበት ከጾምና ከጸሎት ጋር ቢሆን እጅግ የተቀደሰ ሀሳብ ነው።

  ReplyDelete
 31. ግሩም ሃሳብ

  ReplyDelete
 32. Hi Daniel,for whom is the day of thanks? brothers, sisters, mothers, fathers, uncle, friends...??????


  the Dire Dawa

  ReplyDelete
 33. please Dani, say something about the current situation of our CHURCH.

  ReplyDelete
 34. ዳኒ፡ ጥሩ ሃሳብ ነው ያነሳኸው፡፡
  በቅርቡ ከእህቴ ጋር ስናስበው ነበር ይህንን ዓይነት ሃሳብ፡፡ የምስጋና ቀን ይኑረን ስትለኝ እኔ ደግሞ የምንወቃቀስበት ይኑር አልኩ፡፡ እርስ በርሳችን ቤተሰቡ በሙሉ ስላደረግነው መልካም ነገር ብቻ ሳይሆን ስላጠፋነው ነገር እና መድገም ስለሌለብን ጥፋቶች፡፡ አንዳችን በአንዳችን ላይ አይተን ሳንናገር ስለተላለፍነው ነገር በሚል፡፡
  ለማንኛውም ሃሳቡ ከመቼውም በላይ ተስማምቶኛልና አንተንም እግዚአብሔር በአገልግሎት ያበርታህ፡፡
  እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 35. Demmellash /Adea berga EthJune 11, 2011 at 2:48 PM

  It is more memorable if it will be held a week annually as u have said /Phagumen/ thank u

  ReplyDelete
 36. ዲ ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ::እኔ ግን ይቅርታ ስንተየቅም ሆነ ስንመሰገን በከንቱ እንዳንኮፈስ እፈራለሁ::(በቀረብኝ እንዳንል)ያልለመደብን ባህል ስለሆነ ትንሽ ምክር ብታክልበት እላለሁ::
  በረከተ እግዚአብሄር አይለይህ::

  ReplyDelete
 37. let us practice this kind of ideas individually as well.

  ReplyDelete
 38. ዲ/ን ዳንኤል አመሰግናለሁ። ከመቀሌ የደወልኩት እኔ ነበረኩና ሐሳቤን ተቀብለሀ የምሥጋና ብቻ ሳይሆን 'የምሥጋና እና የይቅርታ ቀን'ተብሎ መሰየሙ ደስ ብሎኛል።

  ReplyDelete
 39. አንድ ሰው መጥቶ «መመጽወት እፈልጋለሁ ከንቱ ውዳሴም እፈልጋለሁ አለው፡፡ ዮሐንስ አፈ ወርቅም «ሳትመጸውት ብትቀር አንተም ነዳያንም ትጎዳላችሁ፤ ለከንቱ ውዳሴ ተብሎ ሳትመጸውት ከምትቀር እየመጸወትክ በነዳያኑ ጸሎት ከዚህ ፆር ብትድን ይሻላል» አለው ይባላል፡፡

  ዲያቆን ዳንኤል፡ ለአንተ ወደላይ መንገሩ ቢከብደኝም ከላይ ከተቀመጠው ጽሑፍህ እንደተረዳሁት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዚህ መልእክቱ ያስተላለፈው ውዳሴ ከንቱ አይጠቅምም፡፡ ነገር ግን ጠላት ይህን ምክንያት አድርጎ ምጽዋቱን እንዳያስቀር አንተም መስጠቱን ቀጥል፡፡ እነርሱም ውዳሴ ከንቱ እንዲቀርልህ ይጸልዩልህ ነው፡፡ እናም ያለቦታው የተጠቀሰ ነውና ቢስተካከል፡፡ ሌላው ደግሞ በብዙ ጽሑፎችህ ላይ እንዳየሁት የቤተክርስቲያንን ትምህርት ከማኀበራዊ ሳይንስ ጋር እየቀላቀልክ ታቀርባለህ፡፡ ብዙ ሰው ደግሞ አንተን የሚያውቀው በቤተክርስቲያን መምህርነትህ ስለሆነ የአንተ ቃል እንደቤተክርስቲያን ድምጽ ተወስዶ ለብዙዎች የመሰናክል ድንጋይ ሊሆን ይችላልና ከጸሎት ጋር ጥንቃቄ ብታደርግበት፡፡ ከቻልክ ደግሞ በደጅ ጥናትም ሆነ በትምህርት ከአንተ የቀደሙ አባቶች ጋር ቀርበህ ምክር ብትወስድ ሕዝቡንም ሕይወትህንም ታተርፋለህ፡፡ በመጨረሻም ልልህ የምወደው ይቅርታ ጥሩ ነው፡፡ ምስጋናም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሲደረግ ኢትዮጵያዊ ትውፊቱን በማይጋፋ መልኩ ሲሆን የበለጠ ጥሩ ነውና ይህንንም አስብበት፡፡ አንተም የውዳሴ ከንቱ ሰለባ ሆነህ ከመንገድ እንዳትቀር ሁሌም የምትመሰክርላት ሃይማኖት ጠበቃ የሆኑት ቅዱሳን እንዲቆሙልህ ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡ በተረፈ መጀመሪያ መቀመጫዬን እንደተባለው ወቅቱ የቤተክርስቲያን ፈተና በአደባባይ ወጥቶ ያፈጠጠበት ጊዜ ነውና ምስጋናውም ይቅርታውም እንደተጠበቀ ሆኖ እግዚአብሔር የምሕረቱ ፊቱን መልሶ የቤተክርስቲያናችንን ክብር እንዲገልጽ ሁላችንም በአንድ ሃሳብ ወደፈጣሪያችን ብናመለክት ወደቅዱሳን ብንማልድ የበለጠ ይጠቅመናል፡፡ የቅዱሳን አምላክ ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete