Thursday, June 30, 2011

መንፈስ ነን ወይስ ቁስ?


ታች ክፍል እያለሁ የተማርኩት ትምህርት ሰሞኑን ትዝ አለኝ፡፡ ስለ ቁስ አካል ሳይንስ ያስተማረን ትምህርት፡፡ ቁስ ማለት ክብደት ያለው እና ቦታ የሚይዝ ነገር ነው የሚለው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከፍ ካልኩ በኋላ የተማርኩትን ሌላ ነገር አብሮ አስታውሶኛል፡፡ «መንፈስ»፡፡ «መንፈስ የማይጨበጥ እና የማይዳሰስ፣ ክብደት የሌለው እና ቦታ የማይዝ ህልው ነው» የሚለው፡፡
አሁን እኛ ቁስ ነን ወይስ መንፈስ? እዚህች እንወዳታለን በምንላት ሀገር፣ ስሟ ሲጠራ ደማችን በሚሞቅላት፣ ነፍሳችን በምትግልላት ሀገር እኛ ቦታችን የት ነው? ልክ ነው እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሀገሬም ኢትዮጵያ ናት፡፡ ኢትዮጵያም የኔ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጭ የምለው፣ የምተኛው፣ የምኖረው፣ የማርፈው፣ የት ላይ ነው? ወይስ ቦታ አልባ መንፈስ ነኝ? አሁን አሁንኮ ሁለት ዓይነት ኢትዮጵያውያን እየታዩ ነው፡፡ መናፍስት ኢትዮጵያውያን እና ቁስ ኢትዮጵያውያን፡፡
እዚህ ሀገር መንፈስ መሆን ቀላል ነው፡፡ መንከራተት ነዋ፡፡ ቁስ መሆን ግን ከባድ ነው፡፡ ቁስ ደግሞ ቦታ ይይዛል፡ እዚህ ሀገር ደግሞ ከባዱ ነገር ቦታ ማግኘት ነው፡፡ የመሬት ዋጋ የነፍስ ዋጋ ሊሆን ምንም ባልቀረው እንደ አዲስ አበባ ባለ ከተማ ድኻ ምን ቦታ ይኖረዋል? መኖርያ አለን የሚሉት ዘመዶቼ እንኳን በቴሌቭዥን ኃይለኛ ክላሲካል ሲሰሙ መደንገጥ ጀምረዋል አሉ፡፡ ደግሞ ምን ዐዋጅ ሊወጣ ነው? እያሉ፡፡
ቴሌቭዥን የሌላቸውም አንድ ወፍራም ትከሻ ያለው ባለ መኪና ሁለት ጊዜ መንደሩን ከዞረው ምጥ ከመጣባት ሴት በላይ ወገባቸውን ያንቁታል፡፡ ይኼ ሰው ያለ ነገር ሁለት ጊዜ መንደራችንን አልዞረውም፤ ይህንን ቦታ በሊዝ ሊገዛው መሆን አለበት፤ የት ይሆን ደግሞ የምንሄደው? ይላሉ፡፡
አንዳንዶቹ ደግሞ መሥፈሪያ ሲያጡ ከከተማ ወጣ ያለ ሜዳ ይፈልጉና ጎጆ ይቀልሳሉ፡፡ ቤት ሲሠሩ የሚናገራቸው የለም፡፡ «አንድ ቤት ሕገ ወጥ ግንባታ የሚባለው ባልተፈቀደ መሬት ላይ ሲገነባ አይደለም፡፡ ከተገነባ አሥር ዓመት ሲሞላው ነው? የሚለው ሕግ ሲወጣ የት ነበርን ግን? አንዳንዱ ቤትኮ ሲሠራ ዝም ተብሎ ተሠርቶ ሲያልቅ ነው አፍርሱ የሚባለው፡፡
ለነገሩ ረስቼው ነው እንጂ ይሄኮ የእነርሱ ብቻ ችግር አይደለም፡፡ አንድ ጊዜ በሠፈራችን አስፓልት ሲሠራ መቆፈሪያ እና አካፋ የያዙ ሰዎች እየመጡ መንገድ ዳር ይቆማሉ አሉ፡፡ መንገድ ሠራተኞቹ ነገሩ ሲደጋገምባቸው ጠየቁዋቸው፡፡
«ሥራ ፈትታችሁ ለምን ትቆማላችሁ አሏቸው፡፡
«የስልክ ኬብል ልንቀብር ነው» አሉ መቆፈርያ እና አካፋ የያዙት፡፡
«ታድያ አሁን መንገዱ ሳይሠራ በፊት ለምን አትቀብሩም» መለሱ መንገድ ሠሪዎቹ፡፡
«አይ፣ መንገዱን ቆፍራችሁ ቅበሩ ተባልን እንጂ ቀድማችሁ ቅበሩ አልተባልንም» አሉ ቆፋሪዎቹ፡፡
የተሠራውን አፍርሰን ካልሆነ ከተሠራው ጋር ተጣጥመን መሥራት አንችልም እንዴ? ያሉ መንደርተኞን ነበሩ፡፡
ሌሎቹ ዘመዶቼ ደግሞ በየባላባቱ ቤት ተከራይተው ይኖራሉ፡፡ በከተሞች ውስጥ ቤት አከራዮች ጥቂቶች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ባላባቶች ናቸው፡፡ ከተከራዩ ጋር የአከራይ እና ተከራይ ግንኙነት አይደለም ያላቸው፤ የባላባት እና የጭሰኛ ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ልብስ መቼ እና ምን ያህል መታጠብ እንዳለበት፤ ስንት እንጀራ መጋገር እንዳለበት፤ ስንት ሰው ቤት ውስጥ ማደር እንዳለበት፤ ልጆች ማታ ማታ እስከ ስንት ሰዓት ማጥናት እንዳለባቸው፤ ስንት ቁጥር አምፖል ማብራት እንዳለባችሁ፣ ስንት መውለድ እንዳለባችሁ፣ ወልዳችሁ ስንት የአራስ ጠያቂዎች ሊጠይቋችሁ እንደሚገባ የሚወስኑት ባላባት አከራዮች ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀማችሁን የሚወስኑላችሁ እነርሱ ናቸው፡፡ እኛማ መናፍስት ነን፡፡
አንድ መንፈስ የሆነ ጓደኛዬ የገጠመውን ላውጋችሁማ፡፡
ይኼ ጓደኛዬ ቤት ተከራየላችሁ፡፡ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ፡፡ ያከራዩት ሴትዮ አስቂኝ፣ አሳዛኝ፣ አስገራሚ እና አስቀያሚ ናቸው፡፡ አንድ ቀን ማታ መጸዳጃ ቤት ሊገባ ሲል የሴት እና የወንድ የመሰለ «ስፕሪስ ድምፅ» ሰምቶ ቀና ሲል ልቡ ሰተት ብላ ነበር፡፡ ጠባቂ መልአኩ ነው ያተረፈው፡፡ ሴትዮዋ በቃ ያላቸው ነገር ግንባር ብቻ ነው፡፡ ዓይናቸው እና አፍንጫቸው የት እንደ ደረሰ አይታወቅም፡፡ ጓደኞቹ «አንዱ ተከራይ ወስዶባቸው ነው» እያሉ ይተርታሉ፡፡ በዚያ ጨለማ ዓይናቸው ቀይ፣ ጥርሳቸው ነጭ፣ ፊታቸው ጥቁር ሆኖ ሲታይ የግብጽ ባንዴራ የተውለበለበ ይመስላል፡፡
እንደ ደነገጠ መብራት አብርቶ መጸዳጃ ቤት ገባ፡፡ ቁጭ ብሎ ገና ሳይደላደል መብራቱ ጠፋ፡፡
«ኧረ ሰው አለ» አለ ምናልባት ሰው የሌለ መስሏቸው የቤቱ ልጆች አጥፈተውት እንዳይሆን ብሎ፡፡
«ዐውቄያለሁ» አሉት አከራይዋ በስፕሪስ ድምፃቸው፡፡
«ታድያ ያብሩልኛ» ይላል ጓደኛዬ እንደ ተቀመጠ፡፡
«አይ ቀዳዳውን ካዩ በኋላ መብራት ምን ያደርጋል» ብለውት ዕርፍ፡፡
እንዲህ ሆነን የምንኖር፤ እዚህ ነው የሚባል ቦታ የሌለን፡፡ የአንስታይንን ቲዎሪ ከማሻሻል ይልቅ ቀበሌ ሄደን መታወቂያ ለማውጣት «አድራሻ» ስንባል መመለስ የሚጨንቀን፤ ከአንዱ መንደር ወደ አንዱ መንደር ስንዘዋወር እድሜያችን ያለቀ ሰዎች፤ ቁስ ነን ወይስ መንፈስ?
እኛማ መንፈስ ነን፡፡ ማደርያ የሌለን፡፡ መንፈስኮ ነው የራሱ ማደርያ የሌለው፡፡ በሌላው ላይ አድሮ የሚኖር፡፡ በአንድ ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀገረ ይሁዳ እየተዘዋወረ ሲያስተምር ብዙ አጋንንት ያደሩበት ሰው አገኘ፡፡ አጋንንቱን ውጡ ሲላቸው የት እንሂድ? አሉት፡፡ መንፈስ ናቸውና የራሳቸው ቦታ የላቸውም፡፡ እናም ማደርያ ይሻሉ፡፡ በአካባቢው አያሌ ዐሳማዎች ነበሩና ወደ እነዚያ እንዲገቡ ለመኑት፡፡ ግቡ ብሎም ፈቀደላቸው፡፡ እነርሱ ወደ ዐሳማዎች፤ ዐሳማዎችም ወደ ባሕሩ ገቡ፡፡ የመናፍስት ኑሮ እንዲህ ነውና፡፡
ታድያ እኛ ባላባት አከራዮቻችን በፈለጉ ጊዜ የሚያስወጡን፤ ማደርያ ፍለጋ ስንንከራተት የምንኖር፤ ቁስ ነን ወይስ መንፈስ? እኛስ ብንሆን የሠራነው ቤት በሊዝ ተሽጧል፤ ለኢቭስተር ተሰጥቷል፣ ለሌላ ተግባር ይፈለጋል፤ ማስተር ፕላኑ ተሻሽሏል፤ የከተማዋ አስተዳደር ወስኗል ተብለን እየተነሣን ስንሠፍር የምንኖር ዜጎች መንፈስ ነን ወይስ ቁስ?
በከተሞቻችን ቁሶች ጥቂት ናቸው፡፡ ይኼ መንገድ ላይ የሚያድረው እርሱኮ መንፈስ ነው፡፡ የራሱ የሆነ የሚይዘው ቦታ የት አለውና ቁስ ይሆናል፡፡ ይኼ ሦስተኛ ክፍል «ሰው የሚያስፈልጉት ሦስት መሠረታዊ ፍላጎቶች» ተብላችሁ የተማራችሁትን እርሱት፡፡ «ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ» የሚለውን ሕልም ዘንጉት፡፡ በአማርኛ «ጎዳና ተዳዳሪ» ማለትኮ መንፈስ ማለት ነው፡፡ ዛሬ ፒያሳ፣ ነገ መርካቶ ከነገ ወዲያ ካዛንቺስ የሚያድር መንፈስ፡፡
በርግጥ የታደሉ አንዳንዶች ኮንዶሚኒየም ቤት ደርሷቸው ከመንፈስነት ወደ ቁስነት ለመሸጋገር በቅተዋል፡፡ ወደፊት ትከሻ ሰፊ ኢንቨስተር ሠፈራቸውን እንዳያይባቸው እየተማፀኑ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ አገር ለቅቀው ወጡና መንፈስነትን ትተው ቁስ ሆነዋል አሉ፡፡ ባንክ አበድሯቸው፤ መንግሥትም አግዟቸው ቦታ ኖራቸው አሉ፡፡ የሚያሳዝነው እነርሱ መንፈስ ሆነው ማደርያ እያጡ ሲንከራተቱ የነበረበትን ሕይወት ረስተው እዚህ ሲመለሱ ቁስ የነበርነውን ሰዎች መንፈስ እያደረጉ ማስቸገራቸው ነው፡፡
መቼም ባህላችን ደግ ነው፡፡ እንደ ምዕራባውያን ብንሆን ኖሮ በዚህች ሀገር የሚኖሩት መናፍስት ቁጥር ዛሬ ያለነውን ሦስት እጥፍ በሆኑ ነበር፡፡ አይ ባህላችን ደጉ፤ የአርባ ዓመትም የሠላሳ ዓመትም ልጅ ከወላጆቹ ጋር ያለ ሃሳብ ይኖራል፡፡ እነዚህኮ ውቃቤ ነበር መባል ያለባቸው፡፡ ውቃቤ ቤተኛ መንፈስ አይደል፡፡ ቤተኛ መናፍስት ሆነው ከቤተሰባቸው ጋር ይኖራሉ፡፡ ደግሞ ያኮርፋሉ፤ ይቆጣሉ፤ እናት አባቶ ቻቸውን ያንቆራጥጣሉ፤ መናፍስት አይደሉ፤ ተለማመኑኝ ይላሉ፡፡ ቁስ ለመሆንማ በምን ዐቅማቸው፡፡
«እንዲያውም ብዙዎቻችን ከመንፈስነት ወደ ቁስነት የምንቀየረው ከሞትን በኋላ ነው፡፡ በተለይ በኛ ባህል እና አሠራር ሰው በቁሙ ያላገኘውን ቦታ ሲሞት ያገኘዋል፡፡ ያቺን ሦስት ክንድ ከስንዝር መሬት ሲሞት የሚያጣት የለም፡፡» ብሎ አንዱ ጓደኛዬ ሲናገር ሌላው ተቃወመው፡፡ «ሙታንምኮ መናፍስት ሆነዋል፡፡ እስኪ በየቤተ ክርስቲያናቱ ሂድ፡፡ ከስንት ዓመታት በፊት የተቀበሩት ሙታን አስከሬናቸው እየተነሣ ከመቃብር ወደ ፉካ፤ ከፉካ ወደ ጋራ ጉድጓድ እየዞሩኮ ነው፤ የሙታን መናፍስት ማለት እነዚህ ናቸው፡፡ አባትህ የት ተቀበረ? እናትህስ? ወንድምህስ? መልስ መስጠት አትችልምኮ፡፡ መናፍስት ምን ቦታ አላቸው ብለህ ነው» ብሎ ተነተነው፡፡
በፊት በፊት የፒያሳ ልጅ፣ የየካ ልጅ፣ የላፍቶ ልጅ፣ የሽሮ ሜዳ ልጅ፣ የባህር ዳር ልጅ፣ የጎንደር ልጅ፣ የመቀሌ ልጅ፣ የሐረር ልጅ፣ የድሬዳዋ ልጅ፣ የነቀምቴ ልጅ፣ የጋምቤላ ልጅ፣ የአሶሳ ልጅ፣ የአዋሳ ልጅ፣ የዲላ ልጅ፣ ይባል ነበር፡፡ ያኔ ብዙ ሰው ቁስ በነበረበት ዘመን፡፡ አንድ ቦታ ተወልዶ አንድ ቦታ በሚታደግበት ጊዜ፡፡
ዛሬ አይቻልም፡፡ ፒያሳ ተጋብተው፣ ሽሮ ሜዳ አርግዘው፣ ላፍቶ ይወልዱታል፣ የካ ክርስትና ተነሥቶ፣ የመጀመርያ የልደት በዓሉን ሐረር፣ ሁለተኛውን መቀሌ፣ ሦስተኛውን አዋሳ ያከብራል፡፡ አንደኛ ደረጃ ዲላ፣ መካከለኛ አዲስ አበባ፣ ከፍተኛውን ፍቼ፣ ኮሌጅ ጅጅጋ ይማራል፡፡ ታድያ ይኼ የምን ልጅ ነው? የምንም፤ መንፈስ ነዋ ቦታ የለውም፡፡

44 comments:

 1. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel.
  I feel so sad for my people. I live in America, I have my own house unless i wanted to sell it or stop the mortgage, nobody can take it away from me. Even if they do, they will give me exactly what my house costs. But in our own country Ethiopia, people are forced to leave from their house which can be sold for 2million birr, and are give 400,000 birr instead. I'm afraid that we would become like kenya very soon. My sister used to tell me that the Indians in Nirobi are very rich and too many. Most of the kenians are hired by and work for the Indians. In their own country. what a crime. we have to do something about it. Atlanta.

  ReplyDelete
 2. ኡ ኡ ኡ ኡ ... ቢሮ ውስጥ ለብቻዬ ስስቅ "ምነው ምን ያስቅሃል?" አሉኝ ከጎኔ ያሉት የሃገሬ የሐበሻ ልጆች:: መንፈስ ነው የሚያስቀኝ አልኳቸውና ይህንን ጽሁፍ አስነበብኳቸው::ያንተ ጽሁፍ ሁልጊዜ እኛ ቢሮ መወያያችን ነች:: ልክ ሃገር ቤት ያለን ያህል ነው የሚሰማን:: መቼስ "ማሽላ ሆዷ እያረረ..." ይባል የሌ?

  ስንቱን አስታወስኩ መሰለህ ውይ ውይ ውይ... በተለይ 12ኛ ክፍል ስማር ጋሽ አበበ ያስደነገጡኝን ቁሳዊው አካሌ ቢረሳ መንፈሴ ግን ፈጽሞ አይረሳም:: ምን እንዳደረጉኝ ታውቃላችሁ? ሰርቪስ ቤታቸውን ከጓሮ ተከራይተን ነበር የምንኖረው፤ ከምሸቱ 5:30 አካባቢ ነው እያጠናሁ ሳለሁ በመሃል መጸዳጃ ቤት ለመሄድ ተነስቼ በር ከፍቼ ስወጣ ልክ በር ላይ በጣ...ም ረጅም ሰው ቁሟል አቤት አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ ተውኝ! እንደው ብቻ ሳላውቀው:
  "ማነህ?" አልኩ፤
  "ማንስ ቢሆን ምን አገባህ ቤቱኮ ባለቤት አለው" አሉኝ፤
  ወዲያው ጋሽ አበበ እንደሆኑ ሲገባኝ... እንዴ ጋሽ አበበ ከመቼ ወዲህ እንደዚህ ረሰሙ አልኩ በውስጤ::

  "ምነው ምን ሆኑ?" ስላቸው
  "ምን አባክ አገባህ? ወዴት ነው የምትሄደው? አርፈህ አታጠናም?"
  ብቻ መጠየቅ እንጂ መመለስ ድሮም ስላልፈጠረባቸው ባልደነቅም የዛሬው ግራ አጋብቶኛል:: ለነገሩ የመብራቱን ቆጣሪ የሚያጠፉበት 6:00 ሰዓትም ስለደረሰ ከዚህ በኋላ ብዙም ማጥናት አልችልም:: በንዴት ውስጥ ሆኜ ብቻ የሞት የሞቴን በድፍረት

  "ኧረ እኔ የወጣሁት ሽንትቤት ለመሄድ ነው፤ እርስዎስ ቢሆኑ ለምንድነው እንደዚህ የሚያስደነግጡኝ?" ስል
  "እንዲህ ነችና አበበ የባሻው ልጅ!" አሉና የያዙትን ወጋግራ መሳይ ዱላ መዘዝ አድርገው ሲያሳዩኝ፤ እየለቀቀኝ የነበረው ድንጋጤ ተመልሶ ሲወረኝ ለካንስ የክፍሌን በር ገርበብ አድርጌ ነበር ቅድሙኑ:: ወደ ኋላ ደገፍ ስል ተነሸራትቼ ወደውስጥ ወደቅሁ:: ከዛ ተኝቶ የነበረው ጓደኛዬ ደንግጦ ብድግ አለና መብራቱን ሲያበራ ቶሎ ብቻ "በሩን ዝጋ በሩን ዝጋ... ጋሽ አበበ ናቸው አልኩት" ብቻ እሱም ግራ በመጋባት በሩን ከዘጋ በኋላ "ምን ሆኑ ደግሞ? አንተስ ለምን ከፈትክ?" ሲለኝ: እሳቸው ከውጪ ቆመው ሲያዳምጡ ኖሮ "አርፋችሁ ተኙ ሽንትቤቱም እየሞላ ተቸገርኩ፡ የመብራቱንም ቆጣሪ አልቻልኩም" ሲሉን ውይ የሳቅነው ሳቅ:: የሚገርመው ነገር ደግሞ ቅድም መጥቶ የነበረው ሽንቴ መጥፋቱ... አይ ጋሽ አበበ::

  ReplyDelete
 3. የ“ፍትህ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “አቦይ ስብሀትን በጨረፍታ” የሚል ታዛቢ ጽሑፍ አትሟል፡፡ ጋዜጠኛው እኒህን አወዛጋቢ የህወሓት ጭንቅላት ይነካካቸዋል፤ ይተቻቸዋል፡፡ ሰውየው የሚናገሩትን ስለማወቃቸውም ይጠራጠራል፡፡ አሁን አቦይ ጡረታ ወጥተዋል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ መድረኮች አይጠፉም፡፡

  “ሰውየው ሕዝብን የሚያስከፋ ከመሪ የማይጠበቅ ነገር ይዘባርቃሉ፤ ጡረታ ሲወጡ ይተውታል የሚል ቅን ግምት ነበረኝ ግን…” ሲል ይቀጥላል ጋዜጠኛ ተመስገን፡፡ በግንቦት ወር አቦይ ብሔራዊ ትያትር በፕ/ር ጌታቸው ሀይሌ “ደቂቀ እስጢፋኖስ” መጽሐፍ ዙርያ ውይይት ተካሄዶ ነበር፡፡ ለውይይት ይረዳ ዘንድ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የመነሻ ሐሳብ አቀረቡ፡፡ በዘርአያእቆብ ዘመን መንግሥትና ሃይማኖት የተደበላለቁበት ዘመን እንደሆነ ጠቅሰው እንኳን ያን ጊዜ ቀርቶ አሁንም ፖለቲካና ሃይማኖት አልተነጣጠሉም፤ የተቋጠረ፣ ያልተፈታ ነጠላ አለ” ሲሉ ተናገሩ፡፡ አቦይ ስብሀት እምር ብለው ተነሱ፡፡ ማይክም ጨበጡ፡፡ እናም የፕሮፌሰሩን መደምደሚያ አጥብቀው ተቃወሙ፡፡ “…ፕ/ር ያልተፈታ ነጠላ ብለው ነገሩን ወደ ፖለቲካ ለማዞር የሞከሩት ስህተት ነው፡፡ ዋናው ጥገኛ የሆኑት እነርሱ ናቸው (የኦርቶዶክስ እምነት ጳጳሳትን ማለታቸው ነው) እላያችን ላይ የተጣበቁት እነሱ ናቸው፡፡ እኔ ከመካከላቸው አንዱ ነጻነታችንን እንፈልጋለን የሚል ጳጳስ ካለ እሸልመዋለሁ፤ እመኑኝ ሁሉም የማይረቡ ናቸው፡፡” አሉ፡፡

  ፕ/ር መስፍን ደግሞ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- “አምነሀለሁ፤ ስብሀት ትክክል ነህ፡፡ አንዳቸውም አይረቡም፤ ነገር ግን ቤተ ክህነት ሰው እንዳታፈራ አድርጋችሁ ከሠራችሁ በኋላ የሚሸለመው ከየት ይመጣል? እስኪ ንገረኝ ስብሀት፤ እነዚህን ሰብስቦ ያመጣቸው ማን ነው? እናንተ አይደላችሁም? አንተ አንዱ አይደለህም እንዴ ከያሉበት ለቃቅመህ ያመጣሃቸው!”

  ReplyDelete
 4. yegaremal machakakenachen

  ReplyDelete
 5. It is tough to live and settle in Ethioipa. I do not know who is free to get the place he/she rented from government or private owners or bought,got from government will have a secured feeling about the property he/she has.Let alone our property even we are living in insecure environment.

  Our problems are vast and wide with many burdens.

  We are becoming nomads.

  Let us start to change something daily which doesn't cost us.

  Today's assignment
  Treat all the people we met with smile.I promise.

  ReplyDelete
 6. Hi Dn. Dany! I real appreciate ur view of our being spirit! In reality as we r baptized, we are spirit! God bless you. reciate ur view of our being spirit! In reality as we r baptized, we are spirit! God bless you.

  ReplyDelete
 7. Dn Daniel! Thank you
  I'm always dreaming to have my own house in my country. But I could not find one. It is due to the various laws of the country. No one has the confidence to say something about the country's Land administration law. The law emanates from the person who hold the position.

  ReplyDelete
 8. I like it Dn. Daniel. Let's hope that some day we will be changed to matter. GOD bless Ethiopia & Ethiopian.

  ReplyDelete
 9. I'm sad when I read this article. In my view the main source of the land problem is the government itself. The land owner ship problem was raised in 1966E.C. revolution, but unfortunately it was not resolved , then in 1991 we had the same opportunity to resolve this issue, but unfortunately the guys in power have the same ideology as their predecessors. I do not know when the next government change will be, but I have a hope when our generation come to power, land will be privatized, can be sold and own by individuals not government, then hopefully we can mitigate the current problem.

  ReplyDelete
 10. እኔ እምለው አዲስ አባዎች አዲስ አበባ የሐገሪቱ ካፒታል ሲቲ አይደለም እንዴ? ትንሽቱ ኢትዮጽያ እያላቺሁ ታወሩስ የለ እንዴ? እስኪ ወደ ክፊለሀገር ወጣ ብላችሁ የሰውን ፊቅር፣ ተመልከቱ አከራይ ለተከራይ ያለውን መውደድና እንክብካቤ ቃኙ። ለመሆኑ እግር የጣለው መንገደኛ አሳድሩኝ ቢላችሁ ታስጠጉታላቺሁ? የት አለ አንድነታችሁ፤ የት አለ ለሰው ያላችሁ ፍቅር፡ ስለምን ሁሌ ስለችግር ታወራላችሁ፡ ስለምን የአዲስ አበባ እና የክፊለሀገር የኑሮ ሁኔታ የሰማይና የምድር ያህል ልዩንት ያለው መስሎ ይታያችሁል?ያለቻችሁን አጭር እድሜ ሳትጨናነቁ መኖርን ለምን አትማሩም። አናት ቤት አከራዮችስ ስለምን ነገ ጥላችሁት ስለምትህዱት ቤት ታስባላችሁ ለምን ይሆን የሰው ፍቅርን ገንዘባችሁ የማታደርጉት፤ በእውነት አፈርኩባችሁ እናንተ እኮ ለክፍለሀገር ህዝብ ምሳሌ መሆን ነበረባችሁ። ለነገሩ አሁንም የናንተን ምሳሌ አደርገው ነጋዴዎቻችንና ቤት አከራዮቻችን ሰልጥነውልናል። ለማንኛውም እግዚአብሄር ኢትዮጽያን ያኑርልን!!

  ReplyDelete
 11. thank you Dn. Daniel! i read my own life. i'm a lecturer. i'm now in my early 30s. i was born in oromia, learned in amhara, serving in tigrai, now living in addis. i have experienced living in Nekemt, Gondar, Mekelle and now in addis. but living in addis is really a bad thing i have been experiencing. those you have said 'balabats'(owners of the houses) are so illiterate, merseless, greedy....i have no word to express them. the work of 'kebeles', 'delalas',...is very annoying. sorry to see them in Ethiopia. i am seeing forward to leave addis. it is difficult to think of getting married and leading a peaceful life with such environment. all you have wrote is correct.

  ReplyDelete
 12. thak you dani. let the CADRES have their own places(not a place)and houses. non cadres are not citizens of ethiopia and no right to have their own houses. if they have to have, they should....... God may reverse it one day!

  ReplyDelete
 13. በጣም የሚገርመው ነገር ተከራይ የነበርን ሰወች ጊዜ ሰጦን አከራይ ስንሆን ከአከራዮቻችን የከፋ በደል አድራሾች መሆናችን ነው፡፡

  AA from Addis Ababa

  ReplyDelete
 14. ጥሩ ምልከታ ነው ዲ/ን ዳንኢል:: ኑርልን:: የተረዱህ ግን ጥቂቶች ይመስላሉ:: ፓለቲካ ሳይሆን ፓለቲካ ያመጣው ችግራችንና እውነታ ነው:: ክፍለ ሃገርስ ቢሆን? ስለየትኛው ክ/ሃገር እንደተወራ እንጃ እንጅ የተለየ ሁኒታ የለም ካዲሳባው:: ለምን ይዋሻል? ቦታና ቢት ያላቸውም ቢሆኑ እኮ ምንም መተማመኛ የላቸውም ስለነገ:: በጥቅሉ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ነው ማለት ይቀላል:: አሳዛኝ ትውልድ ሆንን:: እግዚአብሂር ይጠብቅህ ይርዳህ:: አሚን::

  ReplyDelete
 15. eyasaqe yemiastemir tsihuf- abet Ethio tele neger
  «ሥራ ፈትታችሁ ለምን ትቆማላችሁ?» አሏቸው፡፡
  «የስልክ ኬብል ልንቀብር ነው» አሉ መቆፈርያ እና አካፋ የያዙት፡፡
  «ታድያ አሁን መንገዱ ሳይሠራ በፊት ለምን አትቀብሩም» መለሱ መንገድ ሠሪዎቹ፡፡
  «አይ፣ መንገዱን ቆፍራችሁ ቅበሩ ተባልን እንጂ ቀድማችሁ ቅበሩ አልተባልንም» አሉ ቆፋሪዎቹ፡፡
  የተሠራውን አፍርሰን ካልሆነ ከተሠራው ጋር ተጣጥመን መሥራት አንችልም እንዴ? ያሉ መንደርተኞን ነበሩ፡፡

  betam hulgize neber yemigermegn lekas mengedu sayisera meqiber ke denb wichi honobachew new.

  Lemimeleketew hulu! Ebakachihu lehagerachihum asibu le denbina le sireat bicha ayidelem. Tenegageruna mengedu teserto sayalq cabil qiberulin.
  Lemanignawim lib yisten.

  Ye kirayun neger tewut andandoch hulet sost bota kus yihonalu - hulet sost bet yakerayalu enesu be qebele bet(bedehaw menoria) tenqebarew yinoralu menafistun eyanqeteqetu yinoralu. Wey kiray le mehonu yedelala waga yawetaw man new. Delalochis menafist nachew kus.

  ReplyDelete
 16. እኔ ሁሌ ግራ የሚገባኝ ሰው ከሰፈሩ አስነስተው ሌላ ሰፈር ያሰፍሩታል ሌላው ሰፈር ሌላ ደካማ ሰፈር ይመሰረታል ምኑላይ ነው ለውጡ?

  ReplyDelete
 17. To solve all these mess, we need one person who can lead the great Ethiopia in 21 centurey. Unless, we leave and die just with our tears. Let us find a person who can lead us... a person who has fear of God.... a person who affection for his own people....a person who always think about his people...if we pray and fight the current rebles we can get that person....

  ReplyDelete
 18. ይኸውልህ ዛሬ በተደረገው የሊዝ ጨረታ ለ 1ካ.ሜ. 10,000 ብር ባስገባም ሌሎች እስከ 26,000 ብር በመስጠታቸው ተሸነፍኩ። ይህን ምን ትለዋለህ እንዴትስ ነው በዚህ ዓይነት ከመንፈስነት ወጥተን ቁስ መሆን የምንችለው። ለመቃብራችን እንኳን እኮ ቦታ ማግኘታችንን እንጃ..

  ReplyDelete
 19. ከሀያ ዓመት በፊት ከእናቴ ጋር በፖለቲካ ዙርያ ተከራክረን ነበረ፡፡የክርክሩ ርእስ ሰላም ከወጣ በኋላ ድሃ ያልፍለታል ቤት ያገኛል ወዘተ ነበረ፡፡እናቴ ይህ መንፈስ የሆነ ሃሳብ በሙሉ ልብ ልታሳምን ብትሞክርም ምንም እንኳ የ 10 ዓመት የነበርኩ ቢሆንም ይህ መንፈስ የሆነ ሐሳብ አላቂ እንዳልሆነና በኋላም ሀብታምና አፈቀላጤ እንደሚያልፍለትና ደሃ ቤት እንደሚያጣ ስነግራት ከቤቴ ውጣ ስትለኝ እየወጣሁ እያለሁ እየተፈላበት የነበረው ጀበና አንስታ ጀርባዮን መታችኝ ጀበናውም ሳይሰበርና ቡናውን ሳይፈርስ ቀረ፡፡ እናም ድሮ ድሃ የመሬት ይዞታ ሲሰጠው ግማሽዋን ሽጦ ከመንፈስነት የምታድን ቍስነትን ይምስታስጀምር ቤት ይሰራ ነበር፡፡ አሁን ግን የ ቁሶች ድርብርብ እድል ሆነ መሬት በሊዝ ይሸጣል ቁሶችም እስከ 10 ቤቶች መያዝ ጀምረዋል አረ ስንቱን ይነገራል፡፡ ኮንደሚኒየምም እኮ የሃብታሞች እየሆነ ነው፡፡እኔም የ 33 ዓመት ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ይሀውልህ ባለ ክንፎች መንፈስ ሆነናል አንዴ አዲግራት አንዴ አክሱም አንዴ ባህር ዳር አንዴ መቀሌ ሌላም አዲሰ አበበባ አሁንም መቀሌ 7 ዓመት ትዳር በክራይ ቤት!እንግዲህ አምላከ እስራኤል ያውቃል የመሪዎቻችን ልቦና ያራራ መንፈሶች ለሆንም ቁስነት ሎሆን ያብቃን አሜን !!!!!!!

  ReplyDelete
 20. menawe yaakerrayene cheger alafekawe

  ReplyDelete
 21. Gun Some time times Solution ?????????????

  ReplyDelete
 22. Please use also PDF like Dejselam When you post please

  ReplyDelete
 23. menawe yatakarayane chegere becha yakaraies?

  ReplyDelete
 24. ዓይናቸው ቀይ፣ ጥርሳቸው ነጭ፣ ፊታቸው ጥቁር ሆኖ ሲታይ የግብጽ ባንዴራ የተውለበለበ ይመስላል... በጣም አሳቀኝ

  ReplyDelete
 25. ወደው አይስቁ! አረ ሁለተኛ ላይ አስተያየት የሰጠኸው ወልዴ የተባልከው ወንድሜ በጣም ነው ያሳቅኸኝ::: ጋሽ አበበ በህይወት ካሉ ለምን አሁን አትጠይቃቸውም ለምን እንደዛ ያረጉ እንደነበር? ነገሩ ቢያሳዝንም በሰአቱ ባንተ ላይ የደረሰው ነገር ግን በጣም አስቆኛል::Anyway, thank you for making me laugh

  መኮንን

  ReplyDelete
 26. ለመኮንን:

  ጋሽ አበበ ባልሳሳት አሁንም አሉ፤ ኧረ ተወኝ ከዚያ ደግሞ መሮኝ ወጥቼ እነ እትዬ ሙሉ ቤት ገባሁ: እሳቸው እውነት ለመናገር ባይውልዱኝም እናቴ ነበሩ ማለት እችላለሁ:: ግን የእሳቸው ውሻ ደግሞ ለሁለት ወራት ያህል ስቃዬን ነበር ያሳየችኝ ቂቂቂ... ማታ ማታ እራቴን ስበላ ከእራቴ ላይ ቆርሼ ድርሻዋን ካልሰጠኋት ጠዋት መውጫ የለኝም:: በኋላ ግን በጣም ተስማማን እንደውም ሰው ሲመጣ እኔ ማስታረቅ ጀመርኩ:: ብቻ ምን አለፋህ ጋሽ አበበም እትዬ ሙሉም ውሻቸውም ለዛሬ እኔነቴ አስተዋጽኦ አድርገዋል::

  በነገራችን ላይ የአንዳንዶቹ አስተያየት በስደት እንድጸና እያደረገኝ ነው:: አንድ ካሬ 26Killo ብር ከሆነ ምን ልንሆን ነው ጎበዝ? ነጮቹ "ዛፍ ላይ ነው የምትኖሩት" ያሉን እውነት ልሆን ነው እንዴ?

  ReplyDelete
 27. It is not just for fun, I am deeply worried about the situation in my country. I have got three brothers and our father and mother both passed away almost 20 years ago. We are inherited more than 1000 acer compound with a big house in the middle. We have promised to them not to sell and to rent for thired hand. It is now on the brick like you said, the neghbours telling us the rich man is hanging around every day. My father put three "ye-weyyira" trees in memory of his three children and it grew up with big care. We consider those trees like he and our mother live with us for ever. Look what kind of crime is going to commited on us? They are going to take not only their pure property and they want to sell our souls too.

  ReplyDelete
 28. bandweqt aleqachin sle addis abeba lmatawi edget ena yedehawoch etafanta siteyequ "...dehana festal gizew siders erasu yberal..." alu ybalal

  menfesawinet ende yemoral zqtet betayebet bezih zemen sew wendmun lesantim sebara "menfes" biadergew minun ygermal... degmo tnsh qoyten bebalebetochachinm enwawal yhonal

  ReplyDelete
 29. ዳኒ አሁን ላልቅስ ፣ ስቅስቅ ብዬ ላልቅስ፡፡ ተኖረና ተሞተ አሉ…… እንግድህ እኛ መንፈሶችም ኖረዋል ተብሎ ይሙቱም እንባላለን፡፡ መቸ ኖርን እና ነው የምንሞተው? በእውነት ዳኒ ጽሁፍህን እያነበብኩ አለቀስኩ፡፡ የተሰማኝን ሀዘን ሊረዳ የሚችለው ችግሩን የሚያውቀው ብቻ ነው፡፡ በጣም ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት አይሰማኝም፡፡ ሁለተኛ ዜጋ እንደሆንኩ ነው የማስብ፡፡
  ቂቂቂቂ……. እንባና ሳቅ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ይህችው ኢትዮጵያ ለመንፈስም ሆነ ለቁስ የምትጥለው ግዴታ እኩል ነው፡፡ እንዲያውም ለኛ ለመንፈሶቹማ እንከ ሞት ድረስ መስዋዕት እንድንሆላት ትጠይቀናለች፡፡ “ አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ”፡፡ ቂቂቂ … ኡኡኡኡኡኡ…….. ቂቂቂ
  አይ ኢትዮጵያ !!! እነኛ ከመንፈስ ተወልደው ዳር ድንበርሽን ለማስከበር የተሰለፋት ከርታታ ልጆችሽ፣ አካላሽ ከሚቆረስ እኔ ልሙትልሽ …. ድንግልናሽ ከሚረክስ የእኔ ደም ይፍሰስልሽ…..
  ቂቂቂ……… ሳር እስቃለሁ አሉ እማማ እንትና….. ቁሶቹ እንዲኖሩ መንፈሶቹ ይሰው!!!
  መቸ ነው ኢትዮጵያ ????

  ReplyDelete
 30. ዳኒ

  አሁን ተነግሮ የማያልቅ ብሶት ቀሰቀስክ ::የአከራይና ተከራይን ጉዳይ ሳስብ መቸም እማማ ኢትዮጵያ የሚያልፍላት አይመስለኝም ::በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ ባለቤቶች ፈሪሃ እግዚአብሄር አያውቁ : መንግስትም ህግ የለው:: ወገን ተሰቃየን'ኮ .... በቤት ክራይ መኖር ከጀመርኩ 6 አመት ሆነኝ: 6 አምት ሙሉ እግዚአብሄርንም መጭውን ጊዜም የማይፈሩ 3 ባለቤቶችን ተሸከምኩ::ኧረ ለማን አቤት ልብል ??
  ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ

  ReplyDelete
 31. yemigerim eyita new Dn.Dani...Egziabhar hulachininim yasiben

  ReplyDelete
 32. ዛሬ ያ አይቻልም፡፡ ፒያሳ ተጋብተው፣ ሽሮ ሜዳ አርግዘው፣ ላፍቶ ይወልዱታል፣ የካ ክርስትና ተነሥቶ፣ የመጀመርያ የልደት በዓሉን ሐረር፣ ሁለተኛውን መቀሌ፣ ሦስተኛውን አዋሳ ያከብራል፡፡ አንደኛ ደረጃ ዲላ፣ መካከለኛ አዲስ አበባ፣ ከፍተኛውን ፍቼ፣ ኮሌጅ ጅጅጋ ይማራል፡፡ ታድያ ይኼ የምን ልጅ ነው? የምንም፤ መንፈስ ነዋ ቦታ የለውም፡፡ yigermal ewnet ewnet yigrmal

  ReplyDelete
 33. “የመሬት ፖሊሲ የሚቀየረው በኢህአዲግ መቃብር ላይ ነው፡፡”ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ

  ኢትዮጵያውያን በታሪክ እንዳሁን ወቅት ባለ አሳፋሪና አሳዛኝ ሁኔታ የሰብዓዊነት ነፃነታችንን ክብራችንና ፍቅራችንን ያጣንበትና ግራ የተጋባንበት ወቅት እንዳሁን ያለ አይመስለኝም፡፡ምናልባት ይህንን ስል ጥቂት ቁስ-አካል የሆኑ ሰዎችን ለማስደሰትና ለመጥቀም ሲባል አንዳንድ ለአይን የሚማርኩ ብልጭልጭ ነገሮች ወይንም ቁስ-አካሎች እዚህም አዚያም ጣል ጣል ብለው በመናፍስትነት የተመሰሉትን ጭምር አይን በሚማርክ ሁኔታ አይታዩም ለማለት አይደለም፡፡ለማለት የፈለግሁት ከምጊዜውም በላይ በአርአያ ስላሴ ከተፈጠረው ክቡር ሰው ይልቅ ቁስ-አካልና ገንዘብ የበለጠ የተከበሩበት የታሪክ አጋጣሚ እንደሆነ ነው፡፡በእርግጥ በፀሀፊው አባባል ቁስ-አካል የተባሉት ጥቂቶችም ይሁኑ መንፈስ የተባሉት ብዙሀኑ ምስኪኖች እንደ ጤናማ ክቡር ሰብዓዊ ፍጡር ማሰብና መኖር ካልቻሉ ሁለቱም ሙታኖች ናቸውና ብዙም ያን ያህል ልዩነት ያላቸው አይመስለኝም፡፡የሰው ልጅ እርስ በእርሱ በግለሰብ ደረጃ የተለያየ ቢመስልም ነገር ግን በተፈጥሮና በመለኮታዊ እይታ ሲታይ ግን ሁሉም እርስ በእርሱ እንደ ድር የተሳሳረ አንድ ስብስብ ወይንም ማህበረሰብ ነው፡፡ያንዱ ግለሰብ ወይንም ማህበረሰብ ውድቀት/እድገት፣ክብር/ውርደት፣ ጤንነት/ደዌ፣ፍቅር/ጥላቻ፣ሰላም/ሁከት፣ ነፃነት/ባርነት ወዘተ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሂደት እንደዚሁ የሌላው ግለሰብ ወይንም ማህበረሰብ ተመሳሳይ ክስተት መንስኤ እንደሚሆን እርግጥ ነው፡፡በኒውተን የተፈጥሮ ህግ መሰረት For every action force there is an equivalent reaction force ወይንም ሰው የዘራውን መልሶ ያንኑ በምላሹ ያጭዳል እንደሚባለው ነገሮች በስተመጨረሻ እራሳቸውን በተለያየ መልክና መንገድ በረቀቀ ሁኔታ የየራሳቸውን ሂሳብ ያወራርዱና Equilibrium ይሆኑ ዘንዳ ግድ ነው፡፡ስለዚህም በመንፈስ የተመሰሉት ከውጪ ሲታዩ የተጎሳቆሉትና የተራቡት እኛ እንደምናስበው ያን ያህልም የተጎሳቆሉና የተራቡ አይደሉም እንዲሁም በቁስ-አካል የተመሰሉት ከውጪ ሲታዩ የደላቸውና የጠገቡትም ያን ያህል እኛ እንደምናስበው የደላቸውና የጠገቡ አይደሉም፡፡
  ተፈጥሮና ህይወት እራሷን በራሷ በረቀቀ መንገድ የምታካክስበትና የምትጠግንበት መንገድና መላ ያን ያህል አታጣምና፡፡በእርግጥ ቅዱስ መፅሀፍም የሚራቡ ብፁአን ናቸው ይጠግባሉና የሚለውን እያስተወስን በዚህ እኛም እንፅናናለን እንጂ፡፡አሁን ስልጣን ላይ ያሉትና ከዚህ በፊት ቤተስብ በቅጡ እንኳን አስተዳድረው የማያውቁት ሀይሎች ስልጣንን በሀይል ተቆናጠው እኛን ማስተዳዳር የጀመሩት አንዳንዶቹ ቀጥታ ቤተ-መንግስት ገብተው ነው አንዳንዶቹም ያማረ ቪላ ቤት ውስጥ ገብተው ነው፡፡አብዛኞቹ በወሳኝነት ከፍተኛ አመራርና ስልጣን ላይ ያሉት ሀይሎች ትዳር ይዘው ልጅ ወልደው ቤተሰብ የመሰረቱት በዚህ አይነት የተደላደለ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ነው፡፡ስለዚህም ሌላው አብዛኛው ምስኪኑ ኢትዮጵያዊ አባወራ ወይንም እማወራ ቤተሰቡን በማስተዳዳር ሂደት ውስጥ በተለምዶ ያለፈበትንና የሚገጥመውን እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ ሁኔታ እነሱ ጭራሽ ወይንም በቅጡ አልቀመሱትም፡፡ስለዚህም ስለተራው ዜጋቸውና ህዝብ ችግርና ሰቆቃ ለማዳመጥ ለመረዳትና ይህም ችግሩ ያን ያህል ተሰምቷቸው መፍትሄ ሊሰጡት ያን ያህል አይፈልጉም ወይንም የሞራል ብቃትና ልበ-ቀናነት የላቸውም፡፡ወይንም በሌላ በኩል ቢያንስ እነሱም የመጡበትን ችግርና የህብረተሰብ ክፍል ለጊዜው ቢሆን እረስተውታል ማለት ነው፡፡
  ዛሬ ብዙሀኑ ምስኪን ኢትዮጵያውያን ዜጎች በተኩላዎች እንደተከበቡ በጎች ወይንም አውራ በሌለው ንብ ወይንም ቤተሰቦቻቸውን በኤድስ ወይንም በሌላ ምክንያት በለጋ እድሜያቸው በሞት የተነጠቁና ክፉኛ የተጎሳቆሉና ሰብሳቢ ዘመድ ያጡ የሚንከራተቱ ምስኪን ህፃናትን እንመስላለን፡፡ስለዚህም በእርግጥ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ላለን ምስኪን ዜጎችና ህዝቦች ህይወት በራሱ ለሰጋችን ወይንም ለቁስነታችን ስለማይመች ይህንን እጅግ ፈታኝ የመከራ ወቅት በመነፈስነት ማሳለፋችን አስፈላጊና ጠቃሚ አይደለምን?

  እግዚአብሄር በመለኮታዊ ሀይሉ ኢትዮጵያን የተበተኑ ምስኪን ልጆቿን በፍቅርና በአክብሮት እንባቸውን አብሶና አፅናንቶ በፍቅርና በክብር የሚሰበስብና የሚያስተዳድር ልበ ቀናና አስተዋይ መሪዎች ይስጣት፡፡
  እግዚአብሄር ይስጥልኝ
  ከአድናቆትና ምስጋና ጋር፡፡

  ReplyDelete
 34. ዳኒ ይህን አንተ የምትለውን ችግር ገዢዎቻችን ቢያውቁ ምንኛ በጠቀመን ነበር፡፡ በአንድ ወቅት አንድ “ትልቅ” ባለሥልጣን በሚዲያ ቀርበው “ደመወዜ ስድስት ሺህ ብር ብቻ ነው፡፡” አሉ፡፡ (እኔም ቁርጥ እንደእናንተ ድሀ ነኝ ማለታቸው መሰለኝ፡፡) እውነት እውነት እልሃለሁ እኚህ ሰው ድህነትን ወይ ረስተውታል ፤ አልያም የድህነት (አያውቁትም ላለማለት፡፡)
  እርሳቸው ምን ቸገራቸውi ለቤት ኪራይ አይከፍሉ፤ ለቀለብ አይከፍሉ፤ መብራት አይመጣባቸው፤ ውኃ ኪሳቸው ላይ አይቆጥርባቸው፤ ቴሌ ያለፈቃዳቸው ከስልካቸው ላይ ለአባይ መዋጮ አያስገብራቸው፤ ምናልባትም ለልጆቻቸው ትምህርት ቤትም አይከፍሉ፡፡ አከራይ ኣያስጨንቃቸው፡፡ ልጆቻቸው ተርበው አያለቅሱ፤ ባዶ ሆዳቸው ላይ ብርድ ገብቶ ሲያንሰፈስፋቸው አላዩ፡፡ በክረምት “ቤቴን ቀለም ልቀባው ስለሆነ ቤት ፈልጊ፡፡” የሚላቸው የለ፡፡ እርሳቸው ምን አለባቸው የዘይት ዋጋን መናር፣ የስኳርን መጥፋት፣ መቶ ብር ምንም ሊገዛ እንዳቃተው የሚያውቁት በስታቲስቲክስ ነው፡፡ ማታ ገብተው የሚያዩት ቴሌቪዥን የሚናገረው የኛን የድሆቹን በአከራይ ግልምጫና በጠኔ መሸማቀቅ ሳይሆን በጥጋብና በቁንጣን መድረሻ ማጣታችንን ነው፡፡ ታዲያ እንዴት ብለው ይረዱን?
  ችግር ደግሞ ሲረሳ እንዴት “ደስ” ይላል መሰለህ፡፡ ሰው ራበኝ ሲልህ ረኀቡን ለማስታገስ ዳቦ ከመስጠት ቀድሞ አንተ ያኔ በረኀብህ ጊዜ ምን ዓይነት ስሜት እንደተሰማህ ለማስታወስ ትሞክራለህ፡፡ ከዚያ ከረኃብ እንዴት እንደወጣህ ለረኀብተኛው የጀግንነት ተጋድሎህን ትተርክለታለህi ወይም ሰሞኑን አንድ የፈረንጅ ሼፍ ዱባይ ላይ ሲያሽሞነሙነው በአረብ ሳት የተመለከትኸውን ቆንጆ ምግብ በደመወዝህ “ስድስት ሺህ ብርነት” የተነሣ ከቴሌቪዥኑ ላይ አውጥተህ መብላት እንዳልቻልህ ትነግረዋለህ፡፡ ይህን ሁሉ የምትተርክለት ረኀቡ “ስለሚገባህ” ነውi “እናቱ የሞተችበትና እናቱ ገበያ የኼደችበት እኩል ያለቅሳሉ፡፡” አሉ አበው ሲተርቱ፡፡
  የአከራዮች ኢሰብአዊ ትእዛዝ ተስፋ ያስቆረጣት አንዲት እኅቴ “ተከራይ ማለት እኮ ሰው አይደለም! የአከራይ ታሕታይ እስትንፋስ ማለት ነው- ውጣ! ሲባል ብንን… ቡንን… ብሎ የሚጠፋ፡፡” የተሳሳተች አይመስለኝም፡፡ እኔ እዚህ ንግግር ውስጥ የሰማሁት ቀቢጼተስፋ እጅግ ያስደነግጠኛል፡፡ የአንድ መንግሥት አለባት ተብሎ የምትታሰብ ሀገር ግብር እየከፈለች የምትኖር ዜጋ ራሷን ከሰው ተራ ካወጣችው መንግሥቱስ የሰዎች መንግሥት ይሆናል ብላችሁ ነው? እንጃ!

  ReplyDelete
 35. ዳኒ አንድ የገጠመኝን የቤት አከራይ ህግ ላውጋ፡፡ ዘመዴ እዚያ ቤት ውስጥ ለመከራየት ህጉን ካሟሉ ጥቂት ተከራዮች መካከል አንዷ ነበረች፡፡ እዚህያ ጊቢ ለመከራየት ሱሪ የምትታጠቅ ሴት አትችልም፣ እሷን ብሎ የምመጣ ሴትም ሱሪ አይፈቀድላትም፣ አንድ እንግዳ ለማምጣትም ሆነ ለማሳደር ከመምጣቱ ከሁለት ቀን በፊት ማሳወቅ አለባት፣ የሚቆይበትንም ቀን ማሳወቅ አለባት፣ ከዚያ ካለፈ ይባረራል፡፡ ይህ የጊቢው ፅኑ ህግ ነው፡፡ አንድ ቀን የሚያድር እንግዳ አምሽቶ ሲመጣ ለመቀብ የግቢውን በር ከፍታ ትወጣለች ሰዎቹን ለመቀበል በቆመችበት 5 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ የጊቢው በር ከውስጥ ይቆለፋል፤ እንግዶቹን ተቀብላ በር ብታንኳኳ የውስጥ በኩል የጊቢው ባለአባት ቆመው ከቻልሽ ከፍተሽ ግቢ እንጂ በር አትቆርቁሪ በማለት በቁጣ ተናግረው ጥለዋቸው ይገባሉ፡፡ በመጨረሻ 3 ሰዓት የቆሙ ከምሽቱ 5 ሰዓት አሁን ተቀጥተሻልና ለሌላ ጊዜ ግን የግቢው ህግ ብትጥሺ ትባረሪያለሺ ተብላ የተቀረቀረው በር ተከፍቶላቸው ገቡ፡፡ በቁስ የምተዳደር መንፈስ ይልሀል ይህ ነው፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 36. ኤልሮኢ ዘኢሉባቦርJuly 7, 2011 at 12:19 PM

  ብዙዎች ብዙ ብለዋል ነገር ግን ለዚህ በቀናነት ለሚሄድ ህዝብ መፍትሔው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው ምክንያቱም ብዙ ተከድኖ ይብሰሎች ሞልተዋል፡፡አሁን ባለ ሁኔታ እስቲ ታዘቡ እያንዳንዳቸው ሕንጻዎች ከጥቂቶች በቀር የተገነቡት በግፍ በተንኮል በተሰበሰበ በንፁሃን ደም ነው ፡፡ ልክ እንደ ግብፅ ፒራሚዶች፡፡
  እግዚአብሔር ያስበን ሁላችንንም በዳንም ተበዳዩንም

  ReplyDelete
 37. «እንዲያውም ብዙዎቻችን ከመንፈስነት ወደ ቁስነት የምንቀየረው ከሞትን በኋላ ነው፡፡ በተለይ በኛ ባህል እና አሠራር ሰው በቁሙ ያላገኘውን ቦታ ሲሞት ያገኘዋል፡፡ ያቺን ሦስት ክንድ ከስንዝር መሬት ሲሞት የሚያጣት የለም፡፡» ብሎ አንዱ ጓደኛዬ ሲናገር ሌላው ተቃወመው፡፡ «ሙታንምኮ መናፍስት ሆነዋል፡፡ እስኪ በየቤተ ክርስቲያናቱ ሂድ፡፡ ከስንት ዓመታት በፊት የተቀበሩት ሙታን አስከሬናቸው እየተነሣ ከመቃብር ወደ ፉካ፤ ከፉካ ወደ ጋራ ጉድጓድ እየዞሩኮ ነው፤ የሙታን መናፍስት ማለት እነዚህ ናቸው፡፡ አባትህ የት ተቀበረ? እናትህስ? ወንድምህስ? መልስ መስጠት አትችልምኮ፡፡ መናፍስት ምን ቦታ አላቸው ብለህ ነው» ብሎ ተነተነው፡፡
  Hailemeskel Z Maputo

  ReplyDelete
 38. ወይ ጉድ እንዴት አምላክ አውጥቶኛል፡፡ እናቴ ነብሷን ይማረው እና በሕይወት የለችም፡፡ የእሷ አምላክ እረድቶኝ ሌላ እናት ሰጠኝ፡ አከራዬን፡፡ ማንም ሰው እኔ ካልነገርኩት ከምታሳየኝ ወደር የሌለው ፍቅር ባዳ ናት አይልም ክፉ አይንካት አምላክ ይጠብቃት፡፡ የሀገሬ ነገር ግን በታም ያሳዝናል፣ ያስቆጫል፡ ያስለቅሳል፡፡ ይህ አንዱ ችግር ሲሆን ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያላት ሀገር ሆናለች፡፡ የቅዱሳኑ አምላክ ይራዳን እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 39. Daniel, thanks for raising this burning issue, keep up the good work.

  I agree with akerayoch every where being rude.Not just in Addis but in every major city most of them are like this. Ewunetim lemin yiwashal...

  I think there should be some legal means to oblige them to respect people who rent their rooms. I also believe that a significant improvement will be achieved if people who rent a room in a compound pay their own(or the weighted average) expenses like water,electricity, toilet cleaning, etc... As every one knows, these are the main reasons for the owners to complain. Most people who rent a house choose to pay more for such small expenses, over losing their freedom every day and of course they will try to minimize usage for their own sake.

  Such a scheme should be adopted in Ethiopia, as it is done in many other countries.Without this, the average worker/student/family leader who can't buy their own house soon enough are left alone leading a life filled with discomfort for many years, coming from greedy home owners who want to save little more money by counting them as subjects whom they can do whatever they want to.

  @T/D: You said "betam hulgize neber yemigermegn lekas mengedu sayisera meqiber ke denb wichi honobachew new."

  (though it is out of subject it is worth commenting on)
  Your attitude about Tele's digging stems from a lack of even a little knowledge of how a new network should be built.It doesn't require expertise,just common sense would suffice. Digging to bury cables is the most important, yet time consuming step in installing a new network and this is the normal scheme used in every other world.Everyone, including you, believes that Ethiopia needs communication facilities and if it has to be done they have to do it some how. In ethiopia when the roads were built there were no cables and they had to put them there now...They will have taken another easier option if there was any. Why do we have to count that as a destruction? Those people are trying to do something better for the poor people of Ethiopia (at least in this case)...Lemin yialeagebab enankuashishachewalen?

  ReplyDelete
 40. I AM AFRAID AS THERE ARE MANY BAD TRUTH IN OUR COUNTRY WITH THIS SHAMELESS GOVERNMENT.

  THANK YOU Dn.Dani

  ReplyDelete
 41. Hi Dan, want not wast not to get land, house, injera, love, absulote thinking...etc in ethiopia what do u think to stop those thinks. Thank you.

  ReplyDelete