Monday, June 27, 2011

ጨዋው ማነው?


ይኼውላችሁ እዚህ እኛ መሥሪያ ቤት ውስጥ በዓመቱ መጨረሻ ምስጉን የሆነውን ጨዋ ሠራተኛ ለመምረጥ ኮሚቴ ተቋቋመላችሁ፡፡ የኮሚቴው ዓላማ እንዴው በዓመቱ ውስጥ እጅግ ጨዋ የሆነው የመሥሪያ ቤታችን ሰው ማነው? የሚለውን በሠራተኞች ድምፅ ማስመረጥ ነው፡፡
ኮሚቴያችን አንድ የሃሳብ መስጫ ሳጥን መግቢያው በር አጠገብ ሰቀለና «በአንድ ሳምንት ውስጥ እጅግ ጨዋ ነው የምትሉትን ሰው ምረጡ» ብሎ ማስታወቂያ አወጣ፡፡ ለያንዳንዱ ሠራተኛም አንድ የመምረጫ ካርድ ተሰጠው፡፡ ይኼን ሰሞን ካፍቴርያም፣ ቢሮ ውስጥም፣ መንገድ ላይም ሌላ ወሬ የለም፡፡ ወሬው ሁሉ ማን ጨዋ ሠራተኛ ሆኖ ሊመረጥ እንደሚችል የሚደረግ ክርክር እና ውይይት ነው፡፡
እንዲያውም «ምርጫው ከተጀመረ በኋላ ጨዋ መሆን የጀመሩ አሉ» እየተባለም ይታማል፡፡ «ይኼን ሰሞን እዚህ መሥሪያ ቤት የመጣ ባለ ጉዳይ፣ እንኳን ጉዳዩ ሊንዛዛ በአጭሩ ከማለቁ የተነሣ ሊደነግጥ ሁሉ ይችላል» ብለው ያሙት ደግሞ ራሳቸው ባለ ጉዳዮች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
በሳምንቱ መጨረሻ የምርጫ ሳጥኑ ሲከፈት አንድ የተጠበቀና አንድ አስቂኝ ውጤት ተገኘላችሁ፡፡ አብዛኛው ሰው ተሾመን መምረጡ ማንም አልገረመውም፡፡ ድምፁ የማይሰማ፣ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል፣ ከትንሽ ከትልቁ ጋር ተግባብቶ የሚኖር፣ ቅሬታ እና እሮሮ የማያውቅ ነው እየተባለ ሰው ሁሉ ከዓይን ያውጣህ ሲለው ነው የኖረው - ተሾመን፡፡ ሠራተኛው ሁሉ እርሱ ሊመረጥ እንደሚችል ገምቷል፡፡ እንዲያውም ይህ ውድድር የተካኼደው እርሱን ለመሸለም ሲባል ነው ያሉም አሉ፡፡
ሰውን ሁሉ የገረመውና ያሳቀው ግን የአየለ ነዝናዛው መጠቆም ነው፡፡ አንዳንዶቹ አየለ ነዝናዛው፣ ሌሎቹ አየለ ኦዲተር፣ የቀሩት ደግሞ አየለ ቢፒአር፣ የመጨረሻዎቹም አየለ ፈላስፋው እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡
«አሁን አየለ ነዝናዛውን የሚጠቁም ጤነኛ ይባላል፡፡ ራሱ አየለ ራሱን አይጠቁምም፡፡ እርሱ እቴ ከመጨ ቃጨቅ እና ከመዳረቅ ውጭ ምን ያውቃል፡፡ ይህ ለምን አልሆነም፣ ለምን ተደረገ ማለት ብቻ ነው፡፡ ይህ ለምን ዘገየ፣ ለምን ተበላሸ፣ ይህ ዕቃ ባከነ ዕቃ ተበላሸ እያለ ያልተቀጠረ ኦዲተር ሆነብንኮ፡፡ አየለ እንዴው ከማን አለቃ ጋር ተስማምቶ ይኖር ይሆን?
«ይኼው የርሱ ታናናሾች እየተሾሙ፣ እየተሸለሙ መዓርግ በመዓርግ ሲሆኑ እርሱ እዚህቺው ወንበር ላይ አሥር ዓመት የፈጋው በጠባዩ አይደል እንዴ? እርሱ ለባለ ጉዳይ እንጂ ለሠራተኛ ግድ የለው፡፡ ማን ይሆን አየለን የጠቆመ? ሰይጣን መሆን አለበት» ያልተባለ የለም መቼም ይህን ሰሞን፡፡
ኮሚቴው ራሱ የአየለ መጠቆም ገርሞታል፡፡ በርግጥ አየለን የጠቆሙት ሃያ አምስት ሰዎች አይሞሉም፤ ቢሆንስ ግን መጠቆሙስ፡፡ ከሠራተኛው ዘጠና በመቶ የሚሆነው ተሾመን የጠቆመ በመሆኑ ኮሚቴውም ድምፁን ሰብስቦ «የዓመቱ ጨዋ ሠራተኛ ተሾመ ነው» ብሎ ለማወጅ እየተዘጋጀ እያለ ከኮሚቴው አባላት አንድ ሰው የተለየ ሃሳብ አቀረበ፡፡
«የአየለ ነዝናዛው እና የአየለ ፈላስፋው መጠቆም በራሱ አንድ ነገር ይነግረናል፡፡ አነስተኛም ቢሆን ይህንን ሰው የሚያደነቅ ሠራተኛ በመሥሪያ ቤታችን አለ ማለት ነው፡፡ አየለ ድምፅ ገዝቶ ነው እንዳንል እርሱ እንዲህ የሚያደርግ ሰው አይደለም፡፡ ታድያ ሃያ አምስት ሰው እንዴት እርሱን ጠቆመ? ለምን ከሁለቱም ሰዎች ደጋፊዎች ሁለት ሁለት ሰዎች ጋብዘን አናከራክርም? የአነስተኞችም ቢሆንኮ ድምጻቸው መሰማት አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ እውነትን በድምጽ ብልጫ መወሰን ከባድ ይሆናልና፡፡ በኋላ ሰምተነው ቢሆን ብለን ከምንቆጭ ለምን ቀድመን አንሰማቸውም፡፡»
ይህ የኮሚቴው አባል ሃሳብ ብዙዎቹን የኮሚቴ አባላት አስማማቸው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም መላው ሠራተኛ በተገኘበት ክርክሩ መደረግ አለበት ብለው ያቀረቡት ሃሳብ ነገሩን ይበልጥ አሳመረው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች ጉዳዩን ደገፉትና አንድ ከሰዓት ውይይቱ ተደረገ፡፡
በአዳራሹ ውስጥ ሠራተኛው ግጥም ብሎ ሞላ፡፡ አራት ሰዎች ደግሞ መድረክ ላይ ወጡ፡፡ አየለን ደግፈው የሚከራከሩት ሰዎች ወደ መድረክ ሲወጡ አዳራሹን የሞላ ሳቅ ነበር የተቀበላቸው፡፡ አንዳን ዶችም ዓይናቸውን በጨው አጥበው ለአየለ ነዝናዛው ለመከራከር መውጣታቸው አስገርሟቸዋል፡፡
መጀመርያ ተሾመን የሚደግፉት ተናጋሪዎች መድረኩን ተቀበሉ፡፡
«በዚህ መሥሪያ ቤት ተሾመን የሚስተካከል ጨዋ ሰው የለም» አለ የመጀመርያው ተከራካሪ፡፡ «ድምፁ አይሰማም፤ የታዘዘውን ሁሉ እሺ ብሎ ይቀበላል፤ የአለቃውን ትእዛዝ ያከብራል፤ መመርያ ያከብራል፤ ከጥበቃ እስከ ኃላፊዎች ድረስ እርሱን የማያደንቅ የለም፡፡ በጠዋት ሰዓት አክብሮ ይገባል፤ ማታም ሰዓት አክብሮ ይወጣል፡፡ ሌላ ሠራተኛ ሥራውን ቢያዘገይበት በትእግሥት ይጠብቃል እንጂ እንደ አየለ አይቆጣም፡፡ ደመወዙን እንኳን ሲያዘገዩበት አንድም ቀን አማርሮ አያውቅም፡፡
«የጥበቃ ሠራተኞች እንኳን አንድ ነገር ይላሉ ተሾመን የሚፈልጉ ሰዎች ሲመጡ እርሱ ወጥቶ ያነጋራቸዋል እንጂ ሰዎች ወደ ቢሮው አይገቡም፡፡ እኛም ለመፈተሽ፣ ቢሮ ለማሳየት፣ መረጃ ለመስጠት አያደክመንም ብለው ያመሰግኑታል፡፡ ታድያ ተሾመ ያልተሸለመ ማን ሊሸለም ነው ብሎ ሲቀመጥ ሠራተኛው ሁሉ አዳራሹን በጭብጨባ ቦታውን ሊያስለቅቀው ነበር፡፡
አብዛኛው ሰው እየሳቀበት ለአየለ የሚከራከረው ሰው ተነሣ፡፡
«አየለ ለምን ይከራከራል? የመከራከር ሱስ ስላለበት ይመስላችኋል? አይደለም፡፡ ማንኛውንም ነገር በምክ ንያት ለመቀበል ስለሚፈልግ ነው፡፡ እስኪ እዚህ መካከላችን ያሉት የኢንስፔክሽን ሰዎች በእውነት ስለ እውነት ይናገሩ፡፡ ባለፉት ዓመታት ሥራውን ጥንቅቅ አድርጎ በሥርዓት በመሥራት አየለን የሚስተካከለው አለ አለና ወደ ኢንስፔክተሩ ዞረ፡፡
ወዲያው ኢንስፔክተሩ ተነሡና «ባለፉት ዓመታት ባደረግናቸው ምርመራዎች ሥራውን በጊዜ፣ በጥራት እና በሕግ መሠረት በመሥራት አየለን የሚስተካከል ሠራተኛ በመሥሪያ ቤታችን የለም» አሉ፡፡
የአየለ ተከራካሪ አመስግኖ ቀጠለ፡፡ ከዚያም ሁለተኛው የአየለ ተከራካሪ ተነሣ፡፡     
«ታድያ ሥራውን በጥራት፣ በጊዜ ገደብ እና በሕግ መሠረት ከሚሠራ ሠራተኛ በላይ ጨዋ ከየት ይገኛል፡፡ አየለ የሚከራከረውኮ እርሱ በጊዜው ሥራውን ይሠራና ወደርሱ ጉዳዮቹን ማሳለፍ ያለባቸው ሰዎች ስለሚዘገዩ ነው፡፡ ይኼ አየለን ያናድደዋል፡፡ እዚህ የተቀመጥነው ልናወራ፣ ቡና ልንጠጣ፣ ዘመዶ ቻችንን ልናጫውት አይደለም፤ ሥራችንን ብቻ ልንሠራ ነው ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡
«ለመሆኑ መመርያ ማክበር ማለት የተባለውን ሁሉ ያለምንም ሁኔታ አሜን ብሎ መቀበል ነው? ይህኮ መሥሪያ ቤት እንጂ ወታደር ቤት አይደለም፡፡ ለምን ይህ ሆነ? ይህ ያልሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? ይህ ቢሆን አይሻልም ነበር ወይ? ብሎ መጠየቅ መጨቃጨቅ ነው? አንድ ምሳሌ ላንሣ በስብሰባ መመርያ ሲተላለፍ እንደ አየለ ከመከራከር ይልቅ እሺ ብለው የሚቀበሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኋላ ግን ሥራው ሲገመገም እነዚህ ሰዎች «አልገባንም ነበር፣ በደንብ አልተረዳነውም፣ ያኔ ሲነገር በደንብ አልሰማ ሁትም፣ ግር አለኝ» ይላሉ፡፡ ታድያ እንደነዚህ ሰዎች ዝም ማለት እንዴት ጨዋነት ይሆናል?
አየለኮ ያልገባውን ይጠይቃል፤ ያልተስማማበትን ይከራከራል፤ ይሆናል ያለውንም ሃሳብ ይሰጣል፤ ከዚያም ሥራውን በተሻለ ሁኔታ ይሠራል፡፡ ለኛ ጨዋ ማለት ይኼ ነው፡፡ እርግጥ ብዙ ኃላፊዎች የማይከራ ከራቸውን፣ ሰጥ ለጥ ብሎ የሚገዛላቸውን፣ የሚሽቆጠቆጥላቸውን ሠራተኛ ይወድዳሉ፤ ፍርሃት ግን ጨዋነት አይደለም፡፡ ፍርሃት ከነጻነት ማጣት እና ካለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡ ሌሊት ሌሊት በጨለማ ስንሄድ ለምን እንፈራለን? አካባቢውን ማየት ስለማንችል ነው፡፡ ማየት ካልቻልን አናውቀውም ማለት ነው፡፡ ቀን በዚያ ቦታ ስንሄድ ግን አንፈራም፡፡ ፍርሃት ካለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡ የሚፈራቸው ሠራተኛ ማለት የማያውቃቸው ሠራተኛ ማለት ነው፡፡
«አንድ ሠራተኛኮ ተልዕኮው፣ አሠራሩ፣ ግቡ እና ሕጉ ሊገባው፤ ገብቶትም ውጤታማ ነው በሚለው መልኩ ሊሠራው ይገባል እንጂ እሺ ስላለ ብቻ ተቀብሏል ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዱ ለመገላገል ሲል እሺ ይላልኮ፡፡
«እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ከማይከራከረው ከተሾመ እና ከሚከራከረው ከአየለ በዚህ መሥሪያ ቤት ለውጥ ያመጣ ማነው? የደመወዝ፣ የመዋጮ፣ የዕድገት፣ የሠራተኛ ጥቅማ ጥቅም በበላዮቻችን ሲቀርብ አየለ ባይከራከር ኖሮ ምን እንሆን ነበር? ሌሎቻችንማ ውስጥ ለውስጥ ከማማት በቀር አንዳች አንናርምኮ፡፡ ልዩነቱ አየለ ይሟገታል፣ እኛ እናማለን፡፡ ለመሆኑ ብዙ ጊዜ አየለ ሲናገር አንጀታችንን አላራሰውም ወይ?
ይህንን ሲናገር የተወሰነ ሰው አጨበጨበ፡፡
ለመሆኑ ተሾመ ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር የሚግባባው በመሥራት ነው ባለ መሥራት? ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ ይባላል፡፡ ከተኛበት የማይቀሰቅሰውን የማይወድ ማን አለ? የአየለ ችግርኮ እርሱም ተነሥቶ የተኙትን ሁሉ ስለሚቀሰቅስ ነው፡፡
«አየለኮ ማንኛውንም ጉዳይ በአሥር ደቂቃ ውስጥ እጨርሳለሁ ብሎ በራሱ ላይ መመርያ አውጥቶ በቢሮው ላይ የለጠፈ ነው፡፡ እኛ ግን ምን አልነው «ማን ፈቀደልህ? መመርያ ማውጣት የማናጅመንቱ ኃላፊነት ነው፡፡ አየለ የማናጅመንቱን ሥልጣን ተሻማ» ብለን ከሰስነው፡፡ ማስጠንቀቂያም ተሰጠው፡፡ ሰው በራሱ ላይ መመርያ ቢያወጣ ምናለበት? መመስገን እንጂ መቀጣት ነበረበት? ብዙ ሠራተኛኮ «ጉዳዬን ከቻልኩ በአንድ ሳምንት፣ ካልቻልኩም ከዚያ በላይ እጨርሳለሁ» ብሎ መመርያ አውጥቷል፡፡ ግን አልለጠፈውም፡፡ ታድያ ማን ተቀጣ? ማንም፡፡ አየለ ግን ከታዘዘው በላይ በመሥራቱ መመርያ ጣሰ ተባለ፡፡
አሁን ለኛ ጨዋ ማለት ከታዘዘው በላይ የሚሠራ ሳይሆን በዝምታው ውስጥ የታዘዘውን የማይሠራ ሠራተኛ ነው ማለት ነው? ይህንን እኔ ጨዋ ሳይሆን በደበበ ሰይፉ ቋንቋ «ጥሬ ጨዋ» ነው የምለው፡፡ ጨዋነቱ ከጥሬነቱ የሚመነጭ ማለት ነው፡፡
«ለመሆኑ አየለን ለምን ኦዲተር አልነው? አስተሳሰባችን ስለተለያየ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ያለ አለቃ መሥራት አንችልም ብቻ ሳይሆን ከአለቃ ውጭ ሌላ እንዲጠይቀንም አንፈልግም፡፡ የሥራ ባልደረቦቻችን፣ ደንበኞቻችን፣ የበታቾቻችን ስለ ሥራችን ሊጠይቁን አይችሉም ብለን እናምናለን፡፡ አየለ ደግሞ ይህንን አያምንም፡፡ ደንበኞቹ፣ ጓደኞቹ፣ የበታቾቹ ቢጠይቁት፣ ቢቆጣጠሩት ደስ ይለዋል፡፡ ለዚህ ነው ለደንበኞቹ ሲያብራራ የሚውለው፡፡ መመርያ ነው መመርያ ነው፣ ሕግ ነው ሕግ ነው አይልም አየለ፡፡ መረዳት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ያስረዳል፡፡
አየለ ሥራ ሲጓተትበት፣ ቀልጦ ሲቀርበት ለምን? ሥራህ አይደለም ወይ? ሳትጨርስ ለምን ወጣህ ይላል፡፡ ይህንን ሲለን ኦዲተር እንለዋለን፡፡ ለአየለ የመሥሪያ ቤቱ ሥራ ሁሉ ይመለከተኛል ብሎ ያምናል፡፡ ለብዙዎቻችን ደግሞ ከቢሯችን ውጭ ማሰብ አንችልም፡፡ እኔ ምን ቸገረኝ? አለቃው አይደለሁ፤ ዋናው የራሴን መሥራቴ ነው፤ እኔ የለሁበትም ስለምንል የመሥሪያ ቤቱ ሌላው ሥራ ጥንቅር ቢል ግድ የለንም፡፡ ታድያ እኛ ነን ጨዋ ወይስ አየለ?
«ጥሬ ጨው ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች
  መደቆስ መሰለቅ ገና የሚቀራቸው
  እኔ የለሁበትም ዘወትር ቋንቋቸው» አለ ደበበ፡፡
አሁን ተሾመ ጨዋ ነው ተባለ፡፡ በሩን ዘግቶ ወደ እርሱም የሚመጣ የለ እርሱም አይሄድ፤ ሥራው ቢሠራ ወይንም ባይሠራ ግድ የለውም፤ ለአለቆቹ ተሽቆጥቁጦ የታዘዛቸው ይመስላቸዋል፤ ሥራውን ግን አይሠራውም፡፡ እርሱ ድክመቱን በፈገግታው፣ ስንፍናውንም በትኅትናው ደብቆ ይኖራል፡፡ ተሾመኮ ሰላምተኛ የሆነው ጨዋ ስለሆነ አይደለም ጊዜ ስለተረፈው ነው፡፡ ሰውዬውን፣ ባለቤቱን፣ ልጆቹን፣ ከብቱን፣ ዶሮውን፣ ሠፈሩን ሁሉ ሲጠይቅ የሚውለው ጊዜ ተርፎት ነው፡፡ አየለማ ጊዜ የለውም፡፡ ለእርሱ ሰላምታ ማለት ጉዳይን ፈጽሞ፣ የታዘዘውን ሠርቶ፣ ውጤት አምጥቶ ደንበኛን ማስደሰት ነው፡፡
ተሾመ በጊዜ ይገባል፡፡ ልክ ነው፡፡ ግን በጊዜ ገብቶ ምን እንደሚሠራ ያየው አለ? እስኪ ግቡና የተከመ ሩትን ፋይሎች እዩ፤ እስኪ ግቡና በኮምፒውተሩ ላይ የተጫኑትን ጌሞች እዩ፤ እስኪ ግቡና ስልክ ለስንት ሰዓት እንደሚያወራ ስሙት፤ እስኪ ግቡና በቀን ስንት ሻሂ እና ቡና እንደሚጠጣ እዩ፤ እና ጨዋ ማለት ይሄ ነው? ዋናውኮ ስንት ሰዓት ገባ? ሳይሆን ለስንት ሰዓት ያህል ሥራውን ሠራ? የሚለው ነው፡፡
ሰው ካልሠራ ዝምተኛ ይሆናል፡፡ በእሥራኤል ሙት ባሕር የሚባል ባሕር አለ፡፡ ጸጥ ያለ፡፡ ምንመ ዓይነት ንቅናቄ የሌለው፡፡ ውኃው ከዐለቱ ጋር ሲጋጭ የማይተይበት፡፡ ለምን? ቢባል በውስጡ ምንም ዓይነት ሕይወት የለማ? ስለዚህ ጸጥ ያለ ነው፡፡ ሕይወት ያለውማ ይጠይቃል፣ ይከራከራል፣ ያስረዳል፣ ይረዳል፣ እንዴት? ለምን? መቼ? ይላል፡፡ ተሾመኮ ሕይወት የለውም፡፡ ጉዳይ የለውምና በምን ጉዳይ ይጋጫል፡፡ ጉዳይ የለውምና በምን ጉዳይ ይከራከራል፡፡ ጉዳይ የለውምና ለየትኛው ጉዳይ ያማርራል፤ ታድያ ጨዋ ማለት ሕይወት የሌለው፤ ሃሳብ የሌለው፣ ጉዳይ የሌለው ነው ማለት ነው?
«ወገኖቼ እኛ አሁን ጨዋ ማነው? የሚለውን ከመምረጣችን በፊት ጨዋነት ምንድን ነው? በሚለው ላይ መስማማት ነው ያለብን፡፡ ጨዋነት መከራከር፣ የተሻለ ሃሳብ ማቅረብ፣ መሞከር፣ መፍጠር፣ መንቃት፣ መጠየቅ፣ ሥራን አክብሮ መሥራት፣ የተሻለ የሥራ ከባቢ መፍጠር፣ ለምን ብሎ መጠየቅ? ይመለከተኛል ብሎ ማሰብ፣ እኔ የለሁበትም ሳይሆን እኔም አለሁበት ብሎ ማመን፤ ሌሎች ሰዎችንም ከተኙበት መቀስቀስ ማለት መሆን አለበት፡፡
«ትርጉሙን ስላበላሸነው ልጆቻችን አካባቢያቸውን ከማወቅ ይልቅ አርፈው እንዲቀመጡ፤ ከመሞከር ይልቅ እጃቸውን አጣጥፈው እንዲፈሩ፤ ከመፍጠን ይልቅ ዘገምተኛ እንዲሆኑ፤ ከመጠየቅ ይልቅ ዝም እንዲሉ፤ ከመከራከር ይልቅ ሁሉን አሜን ብለው እንዲቀበሉ፤ የራሳቸውን ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ የሌላውን ብቻ እንዲጋቱ፤ ሃሳባቸውን ከመግለጥ ይልቅ ሃሳብ አልባ ሆነው በዝምታ እንዲቀመጡ፤ ከመናገር ይልቅ እንዲያልጎመጉሙ፤ አደረግናቸው፡፡ ጨዋነት ግን ይኼ አይደለም፡፡ ይኼ ጥሬ ጨዋነት ነው»
ሲቀመጥ ሁሉም ቆመው አጨበጨቡለት፡፡ አያሌ እጆችም ጭራሮ መስለው ወደ ላይ ወጡ፡፡ ጨዋ ማነው? በሚለው ላይ እንደገና ድምጽ መሰጠት እንዳለበትም ሁሉም ሃሳብ ሰጡ፡፡ ከተሾመ በቀር፡፡

27 comments:

 1. ጨዋ ማነው? በሚለው ላይ እንደገና ድምጽ መሰጠት እንዳለበትም ሁሉም ሃሳብ ሰጡ፡፡ ከተሾመ በቀር፡፡

  ReplyDelete
 2. አዎ እንደዚህ ያለ ነገር ብዙ አለ

  ReplyDelete
 3. It made me to see myself. I am one of those /chewa/ but my mind tells me ....

  Thanks once again to see myself.

  ReplyDelete
 4. Dear Daniel,

  What a nice article is this? It tells us how we perceive people when we are leaving together. At this point of time, I want to recall the late Haddis Alemayehu's wonderful book entitled "FIKER ESKE MEQABIR". I hope you may recall "GUDU KASSA" who criticized every wrong thought within FITAWRARI MESHESHA's family and the then Feudal society. To me, GUDU KASSA were born beyond his time. To sum up I would like to put forward something, by any measurement "Well done is better than well said."

  ReplyDelete
 5. ሰው ካልሠራ ዝምተኛ ይሆናል፡፡ በእሥራኤል ሙት ባሕር የሚባል ባሕር አለ፡፡ ጸጥ ያለ፡፡ ምንመ ዓይነት ንቅናቄ የሌለው፡፡ ውኃው ከዐለቱ ጋር ሲጋጭ የማይተይበት፡፡ ለምን? ቢባል በውስጡ ምንም ዓይነት ሕይወት የለማ? ስለዚህ ጸጥ ያለ ነው፡፡ ሕይወት ያለውማ ይጠይቃል፣ ይከራከራል፣ ያስረዳል፣ ይረዳል፣ እንዴት? ለምን? መቼ? ይላል፡፡

  ReplyDelete
 6. ሰው ካልሠራ ዝምተኛ ይሆናል፡፡ በእሥራኤል ሙት ባሕር የሚባል ባሕር አለ፡፡ ጸጥ ያለ፡፡ ምንመ ዓይነት ንቅናቄ የሌለው፡፡ ውኃው ከዐለቱ ጋር ሲጋጭ የማይተይበት፡፡ ለምን? ቢባል በውስጡ ምንም ዓይነት ሕይወት የለማ? ስለዚህ ጸጥ ያለ ነው፡፡ ሕይወት ያለውማ ይጠይቃል፣ ይከራከራል፣ ያስረዳል፣ ይረዳል፣ እንዴት? ለምን? መቼ? ይላል፡፡

  ReplyDelete
 7. ተሼ በእርግጥም “ ጨዋ” ነው ያመነበትን የገባውን በሚሰማው መልኩ እሚገልጽ “እብድ” ፡ “ የመኖር ሂሳብ ያልገባው” አለያም “ ጨዋ ያላሳደገው” ተብሎ በሚፈረጅበት አለምና ማህበረሰብ ውስጥ.

  አየለ” እብድ” ነው! እውነት ሳይሆን የማይስማማ “ መስማማት” አስማምቶት በሚኖር እኛነት ውስጥ. ግናማ የት እንደበቀለ ባላውቅም ከኛነታችን ልያስታርቁን ፡ እምነትን ሊያስተምሩን፡ እልፍ ሊያደርጉን ከተፈጠሩት ጥቂቶች ከጥቂቶችም ኢምንቶች ፡ ስውነት ከገባቸው ሰዎች የኛነት ግን “ እብዶች “ አንዱ ነው. እነ አየለ የመጠራታቸው ሚስጥር የገባቸው ፡ “ በሃሳባችውና በተግባራችው የህይወት ክቡር ዓላማና ሰዋዊ ክብራቸው ከምንም በላይ የሆነባቸው ናቸውና እሚኖሩት በገባችው ዓለም እሚሰሩት በተረዱት እውነታ ልክ ነውና ምንም ብንላችው እነሱም ግራ አይገባቸው እኔውም አይገርመኝም.

  እነ አየለ እንኩዓንስ በሰው ዘንድ “If God loves history what is your history? ” እንዲሉ በሰማያዊው አምላክ እንኩአን ቢጠየቁ እንደ ሰው ተፈጥረው እንደ ሰው የሚኖሩ ከሚባሉት ናችውና እነርሱን እነርሱን እንዲያበዛልን እኛንም የነርሱን መረዳት እንዲሰጠን እንጸልይ?

  ዳኒ ቃለ-ህይወት ያሰማልን

  ፍቅር-ዓለም ከጆበርግ

  ReplyDelete
 8. It is good for us. I like it...

  ReplyDelete
 9. ደሳለኝ ወንድሙJune 27, 2011 at 4:51 PM

  በጣም ዎድጀዋለሁ፡፡ ለማለት የፈለከው ነገር ተረድቶኛል፡፡ ከጭቅጭቁ ቀነስ አድርጎ ለማለት የሚፈልገውን ነገር ባግባቡ እስከተናገረ ድረስ የለውጥ ሰው በመሆኑ ሊበረታታና ሊሸለም የሚገባው አየለ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ ሥሜታቸውን ፊት ለፊት ከሚነግሩን ሰዎች ይልቅ እያበላሸን ዝም የሚሉንን ሰዎች እንመርጣለን፡፡ ይህም ፈጽሞ ተገቢ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ያየለ ጸባይ ደጋፊዎቹ እንደመሰከሩለት አይነት ከሆነ እንደሱ አይነት ሰዎች ጥፋት እየተሰራ ዝም ለማለት የማይሆነላቸውን ያህል የሚያበረታታ ስራ ሲሰራ ካገኙት አለቃቸውንም ቢሆን ለየት ባለ ሁኔታ ለማበረታታት የሚደፍር ቅንና የዋህ ልብ እንዳላቸው ልብ እንበል፡፡ ቃለ ህይዎት ያሰማልን ዳንየ፡፡ ያገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን፤ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 10. Thank you Dn Dani
  I like the message behind.We need to change our attitude towards what we call "chewa" and "Neznaza". One source of the problem is that the Boss or Manager wants to secure his post for a long time. To secure the post he wants to have staffs who are silent and accept whatever they told to do so. Then after sometimes the boss consider himself as the life of the company-no one replace him, the staffs and the position will not exist without him.This is the mentality we develop in most place of our country-Kebele/wereda, subcities, government organizations, private firms, NGOs etc.

  ReplyDelete
 11. "አንዳንድ ጊዜ እውነትን በድምጽ ብልጫ መወሰን ከባድ ይሆናልና......"
  I like that!

  ReplyDelete
 12. በጣም እጅግ በጣም ወደድኩት እግዚአብሔር ይስጥልኝ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር አድሎሃል አንተም እየተጠቀምክበት ነው:: በመንገድህ እመብርሃን ትቁምልህ:: እድሜ ለአንተ እነ ተሾመ ማንነታቸውን አወቁ:: ... እነ ተሾመ አንገት ደፍተው ምንም ሳይሰሩ አይናቸውን አቅለስልሰው ሲመሰገኑ
  ... እነ አየለ ግን ትክክለኛውን በመጠየቃቸው ያ ሁሉ ስም ሲወጣላቸው ቢኖርም በበኩሌ ረጅም እድሜ ለነ አየለ!!!!!!!!!!
  Sara Adera

  ReplyDelete
 13. ዲ/ን ዳንኤል የመስሪያቤቱን እንቆቅልሽ ፍንትው ባለ መነጽርህ ተመልክተህልኛል። በተለይ እኛ ኢትዮጽያውያን እገሌ ስንት ሳት ገባ ስንት ሳት ወጣ የሚለውን የሞኞች አስተሳሰብ እንጂ ሐላፊነቱን ምን ያህል እየተወጣ ነው የሚለውን ነገር ከግምት ውሰጥ አናስገባም። ይህ ደግሞ የአብዛኞቹ ስራአስኪያጆቻችንም ጭምር ትልቁ ድክመት ነው።
  ከዛም ባለፈ እስኪ ሁላችንም ከዚህ ቁም ነገር አዘል ታሪክ ተንስተን እራሳችንን እንመዝን ተሾመ ነን ወይስ አየለ?

  ReplyDelete
 14. ዳኒ የዛሬው ጽሁፍህ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ምን ልትመስል እንደምትችል ያሳየኝ ነው፡፡ በእውነት አደጋ ላይ ነን፡፡ አለቃን እንደ ሳይጣን የምንፈራ፣ አለቆችም እንደ እግዚአብሔር መከበር የሚፈልጉ፣ ሁሉም በተዋረድ አጨብጫቢ እና አጐብጓቢ ፣ ሥራ የምንሠራው መስራት ስላለብን ሳይሆን አለቃ ስለሚጠይቀን ብቻ………… ኡኡኡኡኡኡ!!!!!

  ReplyDelete
 15. "When guns speaks, death settles disputes". Analogically speaking, we should speak loudly like Ayele so that we can bury the hatchet on time. Otherwise, we'll ended up being like Teshome--a smoldering fire which might have been erupted at any point in time! Hats-off Author!

  Tena Tabia Folk (Kebele 03)
  Bahirdar

  ReplyDelete
 16. ለብዙ አመታት ከራሴም መሰል ወንድሞችና እህቶች ጋር ስወያይበት የነበረ ጉጋይ ስለሆነ ጥሩ
  አስተያየት ነው ዝም ያለ ሰው ብቻ በእኔ አባባል የሚቅለሰለስ ብቻ ጥሩ ነ ውማለት አይቻልምና
  ብዙ ተናጋሪም እንዲሁ እስቲ በሁሉም ቦታ ዝምታው ሆነተናጋሪው በ በቅንነት ቢሆን ሁላቱም አስፋላጊ ናቸው

  ReplyDelete
 17. Thank you dear, Dn. Daniel!Keep it up!!!

  ReplyDelete
 18. ene teshe yihin anbibew min bilew yihon? mechem yihen anbibew kaltelewetu meche endemilewetu enja.Ene ayele demo bezih sirachew gefitew bizu endenesu aynetochin mefter endalebachew salasasib alalfim. d/n Daniel kale hiwot yasemalin
  mengiste semaatin yawirisilin
  Amen

  ReplyDelete
 19. ኤልሮኢ ዘኢሉባቦርJune 30, 2011 at 12:02 PM

  በጣም ጥሩ መልዕክት ነው
  ምክንያቱም በኢትዮጵያ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ትልቅ ናቸው የሚባሉት ተቀዋማት ሳይቀሩ የዚህ ችግር ተጠቂዎች ናቸው፡፡አመክንዮ ማቅረብ ብዙ ነገር ያሳጣል ሰው የሚገሙት በስራቸው ሳይሆን የሰውን በጎ ስራ አበላሽተው በማቅረብ ነው፡፡
  በዲ.ን ዳንኤል የሚቀርቡት ጽሁፎች ለሚያስተውል ሰው አንዱ ብቻ በቂ ይመስለኛል አሁን ትውልዱን ለመታዘብ እንደቻልኩት ምን ያህል እንዳነበበና ፀሐፊዎችን ለማድነቅ ሲሆን ራስን ለመለወጥ ግን ብዙም አይታይም ሰለዚህ ሁላችንም ብናስብበትና በምንሰማው በምናነበው መለወጥ ብንችል የሚወጡት መልክቶች ግባቸውን ይመታሉ የሚል ዕምነት አለኝ
  ለፀሓፊው ረጅም የአገልግሎት ዘመን ከጤና ጋር ከነቤተሰቡ አምላክ ይስጠው

  ReplyDelete
 20. It is good views for everybody who are lazy nowadays because this time is suppose to be reproductive and be self confidence time. So i support the way Ayele do. Thank you! Dani i like your article so much. God bless you.

  ReplyDelete
 21. የሚገርም ጽሁፍ ነዉ፡፡ ዲ. ዳንኤል ይህን ጽሁፍ ያነበብኩት እኔ የምሰራበት መስሪያ ቤት ዉስጥ ይሄን የሚመስል ምርጫ ከተደረገ ከ2 ወይም 3 ቀናት በኋላ ነዉ፡፡ ለነገሩ አካሄዱ እንጅ ዉጤቱ አይመሳሰልም፡፡ ረሳሁት ባክህ ለካስ የአየለም ዉጤት ሊቀየር ነዉ! ጓደኞቼ ጠቁመዉኝ አነበብኩት፡፡ ለነገሩ ቀናት ሊያልፉ ይችል ነበር እንጅ አንተ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን ሳላነብ አልቀርም፡፡

  ጽሁፉን ስጨርስ በሳቅ መድከም ጀመርኩ፡፡ ብዙ ጊዜ ሳላባክንም የፌስ ቡክ ገጼ ላይ ፖስት አደረግኩት፡፡ በነገራችን ላይ የጽሁፉን ባለቤት በግልጽ ጠቅሼ ነዉ ፖስት ያደረግኩት፡፡ ነገር ግን ያን ጽሁፍ ካነበቡ የስራ ጓደኞቼ አብዛኞቹ እኛ ስብሰባ ላይ የነበረ ሰዉ የጻፈዉ ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ጊዜ አልወሰደባቸዉም፡፡

  እኛ ክፍል ዉስጥ በሚል የጻፍከዉን ጽሁፍም ከፌስ ቡክ ገጼ ላይ ፖስት ላደርገዉ አሰብኩና ይህን ባደርግ ባልደረቦቼ የጽሁፉ ባለቤት እኔ መሆኔን ከመጠራጠር አልፈዉ የየዋህነት እርግጠኝነት ዉስጥ እንዳይገቡ ስለፈለግሁ ሀሳቡን ትቼዋለሁ፡፡


  ጽሁፍህ ምን ያክል የብዙ መስሪያ ቤቶችን ጉዳይ የሚነካ መሆኑን የኔ ገጠመኝ በሚገባ የሚያስረዳ ይመስለኛል፡፡


  እግዚአብሄር ዓይኖችህን ያብዛልህ!  እኔ ነኝ ከጎንደር

  ReplyDelete
 22. ጨዋ ማለት በቤተክርስቲያን ባዶ፣ እውቀት የሌለው
  አባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል
  ክአትላንታ

  ReplyDelete
 23. ተሼ ምን ያድርግ የሚገመገመው፣ ደመወዝ የሚጨመርለት፣ ዕድገት የሚሰጠው በቅን ሥራው ሳይሆን በፖለቲከኞቹ ዘንድ በሚያሳየው ዓመል ነው፡፡ ታዲያ ተሼ ምን አጠፋ? የሚፈልጉትን ሰጥቶ የሚሹትን መውሰድ (ሰጥቶ የመቀበል መርሕ) ያለ የነበረ ወደፊትም የተሼን አለቆች ዓይነት ማውራት እንጂ መሥራት የማይሆንላቸው፣ ማቆላመጥ እንጂ ማሰብ የተሳናቸው ሰዎች ዕልቅና በሚያገኙባት ሀገር ውስጥ የሚኖር ነገር ነው፡፡ እንዲያውም በቻርለስ ዳርዊን ሐልዮት ከተመለከት ነው the best way to survive in these days of austerity ሆኖ ይገኛል፡፡

  ReplyDelete
 24. Ewenetem Endegena mercha yekahed

  ReplyDelete
 25. ዳኒ ቃለ-ህይወት ያሰማልን!!!


  Hailemeskel Z Maputo

  ReplyDelete
 26. ሁሉም ሰው የሚሰማውን ህሊናው የሚነግረውን እውነቱን ነገር ከመናገር ይልቅ ሰዎች ምን ይሉኛል፣ ሰዎች አሳዝን ይሆን እያለ መጥፎን እንደ በጎ፣ ክፋትን እንደ ደግነት፣እውነትን ከመናገር ይልቅ የበላይ ኃላፊ በመፍራት ብቻ ሁሉም የተዘዝከውን ሳታምንበት መሰራት የህልና እስረኛ ከመሆንአልፎ የሃገር ና የወገን ኝፋት የሚያመጣ ነውና ሁላችን በተለያየ መስሪያቤት የሚንሰራ የመንግስት ይሁን የግል መስሪያቤቶች አለቆች ዝም ከሚል ይልቅ ለሚታዙት ሥራ የሚቃወም ሰው ብትወዱ ይጠቅማችኋል። ይህ ሲል ግን ሳይገባው መስራት የማይፈልግ ወይም የማይሰማማበት ከሆነ መቃወሙ አግባብ ነው። የተሰጠውን ሥራ ሁሉ ካለ ምንም ማቅማማት እሺ ብሎ የሚቀበል ነገር ግን በተግባር የማይሰራው ሰንቱ!! ዲ/ን ዳኒ በረታ ሳይጋቡ መጋባት ግራ መጋባት እንሚባለው ነው። በርታ ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete