Thursday, June 23, 2011

እኛ ክፍል ውስጥ (ክፍል ሁለት)


አሁንም አምስተኛ «» ነው ያለነው፡፡ ዛሬ ክፍላችን በሁለት ተከፍሎ ኳስ ይጫወታል፡፡ ሃያ ሁለት ተማሪዎች ተመርጠዋል፡፡ «» እና «» ቡድን ተብለውም ተሰይመዋል፡፡ አዳነ ተማቹ «» ቡድን አምበል ሲሆን ዕንግዳ ደግሞ «» ቡድን አምበል ሆኗል፡፡ ዓለሙ ደግሞ ጮርናቄውን አስቀምጦ ለዳኝነት ተሰልፏል፡፡ የቀረነው ሠላሳ ስምንት ልጆች ደግሞ ደጋፊዎች ሆነናል፡፡
አጥናፉ ተንታኙ እንደለመደው መተንተን ጀምሯል፡፡ «ቢያንስ እዚህ ክፍል ውስጥ እንኳን የተመልካቹ እና የተጫዋቹ ቁጥር ቢቀያየር ምናለ» አለ አጥናፉ፡፡
«አንተ ደግሞ ከፊፋ ልብለጥ ትላለህ» አለው ዓለሙ፡፡
«የግድ ሁሉም ነገር ከውጭ መገልበጥ አለበት እንዴ፤ ለራሳችን ራሳችን መሥራት እንችላለን» አለ አጥናፉ፡፡
ድንገት አንድ ጭብጨባ ተሰማ፡፡ ሁሉም ዘወር ሲሉ አሰግድ ነበር የሚያጨበጭበው፡፡ «አሁን ለማን ነው ያጨበጨብከው? ለእኔ ነው ለእርሱ አለና ዓለሙ አፈጠጠበት፡
«ለሁለታችሁም» አለ አሰግድ
«ምን ስላልን ነው ለሁለታችንም የምታጨበጭበው» ዓለሙ ሊገጨው ደረሰ
«ላላችሁት ነገር ሁሉ ጭብጨባ ይገባዋል» አሰግድ በመላ ፊቱ ሳቀ፡፡
«አሁን ምን ይሁን ልትል ነው?» ዓለሙ ወደ አጥናፉ ዞረ፡፡ ሌሎቻችን ሊቧቀሱ ነው ብለን ማን ያሸንፋል በሚለው ላይ መከራከር ጀመርን፡፡ ቤቲ «አጥናፉ መተንተን እንጂ መማታት አይችልም» ብላ ተከራከረች፡፡ ሠናይት ደግሞ «አጥናፉ በአፉ ብቻ ሳይሆን በቡጢም ሊተነትን እንደሚችል» አስረዳች፡፡ አጥናፉ ግን ትንታኔውን ቀጠለ፡፡
«የዚህች ሀገር ችግር ከተጫዋቹ ይልቅ ተመልካቹ እየበዛ ነው፡፡ ለውጥ ማምጣት የሚቻለውኮ በተጨዋችነት እንጂ በተመልካችነት አይደለም፡፡ በዚህ በኩል ስጠው፣ በዚህ አቀብለው፣ እገሌ መውጣት ነበረበት፣ እገሌ ማግባት ነበረበት እያሉ ሃሳብ በመስጠት ለውጥ አይመጣም፡፡ ገብቶ በመጫወት እንጂ፡፡ ምን መሆን እንዳለበት ሃሳብ የሚሰጡ ሞልተዋል፤ መሆን ያለበትን ገብተው የሚያደርጉ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ምናለ እኛ ክፍል እንኳን ሠላሳ ስምንት ሰው ተጫውቶ ሃያ ሁለት ሰው ቢመለከት?
«ዋንጫ እንዲመጣ እንፈልጋለን፡፡ እኛ ታግለን ዋንጫውን ማምጣት ግን አንፈልግም፡፡ ሌሎች ታግለው ዋንጫውን ሲያመጡ ለመደሰት ነው የተዘጋጀነው፡፡ ዋንጫው ካልመጣ ደግሞ እንደኛ የሚበሳጭ የለም፡፡ ለምን? ለምን ራሳችን ታግለን ራሳችን ዋንጫ ማምጣት አንለምድም? ለምን ይኼ ከኛ ክፍል አይጀመርም?»
አጥናፉ የተናገረው ነገር ለዓለሙ አልገባውም፡፡ «አሁን ትደግፋለህ ወይስ አትደግፍም? ግልጽ አድርግ ሐተታ አታብዛ» አለው፡፡
«ቁጭ እላለሁ፡፡»
«ዝም ብሎ ቁጭ ማለትማ አይቻልም፤ የስፖርት ፔሬድኮ ነው»
«የቤት ሥራዬን እሠራለኋ»
«አትችልም፤በስፖርት ቤሬድ የቤት ሥራ መሥራት ክልክል ነው»
«ማን ነው የከለከለው?»
«እኔ መከልከሉን እንጂ ከልካዩንየተከለከለበትን ምክንያት የማወቅ ግዴታ የለብኝም» አለው ዓለሙ
«ለምን?»
«አንተ ከኛ በፊት ተወልደህ ከኛ ኋላ የቀረኸው ለምን? እያልክ ስለምትጠይቅ ነው፡፡ ወይ «» ወይም «» መደገፍ አለብህ» አለውና ጥሎት ሄደ፡፡
አሰግድ አጨበጨበ፡፡
ጨዋታው ተጀመረ፡፡ «» ቡድን ልጆች በደንብ ይጫወታሉ፡፡ ጎል ኪፐራቸውም አሪፍ ነው፡፡ አቤት አሸናፊ ኳሷን ሲለጋት፡፡ ትንሽ እንደ ተጫወቱ፡፡ እስክንድር የመታት ኳስ ጎል ሆነች፡፡ «» ቡድኖች ጨፍረው ሳይጨርሱ ዓለሙ ጎሉን ሻረባቸው፡፡ እሳት ልሰው እሳት ጎርሰው መጡ፡፡
«እንዴት የጸዳች ጎል ትሽራለህ» ብለው አፋጠጡት፡፡
«ቢሽረው ምናለበት?» አለች ሰላማዊት
«እንዴት ቢሽረው ምናለበት ትያለሽ፣ በዓይኔ በብሌኑ ያየሁትን ጎል ይሽረዋል»
«እሱ ደግሞ አለመግባቷን አይቷላ»
«እና እርሱ ትክክል እኛ ስሕተት የሆንነው ምን ስለሆነ ነው አሏት «» ቡድን ልጆች፡፡
«እርሱ አለቃ እናንተ ተማሪዎች ናችኋ? አለቃ ደግሞ ሁልጊዜም ትክክል ነው» ሰላማዊት አፈጠጠች፡፡
«እኔኮ የሳይንስ መምህራችን ባስተማሩን መሠረት ትናንት ካሮት በልቻለሁ» አለ ምንተስኖት፡፡
«በደንብ ለማየትኮ ካሮት አይደለም የሚያስፈልገው» አለ አሰግድ
«ታድያ ምንድን ነው» ምንተስኖት አፋጠጠው፡፡
«አለቃ መሆን ነዋ»
«አያችሁ እናንተ ቡድን ውስጥ ያሉ ተጫዋቾች ብዙ ጮርናቄ አይገዙም፤ እኔ ደግሞ ደንበኞቼን ማስቀየም አልችልም» አላቸው እየሳቀ፡፡
«እና ጎልና ጮርናቄ ምን አገናኘው አሸናፊ ጠየቀ፡፡
«ዋናውኮ ጎል ማግባት አይደለም፤ ጮርናቄ መግዛት ነው፡፡» ዓለሙ ሳቀ፡፡
«ያገባነውን ኳስማ ልትሽረው አትችልም» አለች ሚጠጢዋ ሰሎሞን
«ሚጠጢዬ ዋናውኮ አንቺ ማግባትሽ ሳይሆን እኔ ማጽደቄ ነው» አለው ዓለሙ እያሾፈ፡፡
«ገንዘቡን የሰጠ ቅኝቱን ይወስናል ማለት ይኼ ነው» ብሎ አጥናፉ ተነተነው፡፡
«ምን?» አለች ቤቲ ተረት እና ምሳሌ ጻፉ ሲባል እንዲሞላላት ቶሎ ብላ አጥናፉ የተናገረውን ደብተሯ ላይ ዓለሙ ሳያያት ጻፈቺው፡፡
«አዝማሪ ቤት ታውቃላችሁ ልጆች» አለ አጥናፉ፡፡ «እናውቃለን፣ እናውቃለን፣ እናውቃለን፣» ብዙዎች ከበቡት፡፡
«እኛ ሠፈር አዝማሪ ቤት ነፍ ነው» አለቺ አሰለፈች፡፡
«አዝማሪ ቤት ውስጥ ምን መዘፈን እንዳለበት የሚወስነው አዝማሪው አይደለም»
«ታድያ ማነው? እስክስታ መቺዋ ሴትዮ መሆን አለባት፣ እርሱ እየዘፈነ እንዴት እርሷ ትወስናለች» አለ መዳፉን በቡጢ እየመታ አዳነ ተማቹ፡፡
«ምን መዘፈን እንዳለበት የሚወስነው ገንዘብ ለአዝማሪው የሚሰጠው ሰው ነው፡፡ ያንተ ግጥም መቻል፣ ዜማ መቻል ምንም ዋጋ የለውም፤ ዋናው ገንዘብ መስጠትህ ነው ÝÝ አንተ ማነህ? አይደለም ዋናው ጥያቄ ስንት ትሰጣለህ? ነው»
ቤቲ አልገባትም፡፡ «እኔኮ ሌላ ተረትና ምሳሌ የሚነግረን መስሎኝ ነበር» አለቺና ተመልሳ ዛፉ ሥር ቁጭ አለች፡፡ ዓለሙ በቁጣ ፊሽካ ሲነፋ ሁሉም ተጨዋቾች ቦታቸውን እንደገና ያዙ፡፡
አሰግድ አጨበጨበ፡፡ ከዚያም «የሀ ቡድን መቀጣት አለበት» አለ፡፡
«ለምን?» አሉና የቡድኑ ልጆች ክንዳቸው ላይ ያለውን ሸሚዝ እና ሹራብ እየሰበሰቡ ተጠጉት፡፡
«እንዴት አለቃችንን እንዲህ ደፍራችሁ ትናገሩታላችሁ፡፡ እርሱኮ አለቃ ነው»
«ቢሆንስ» አለች ሰሎሞን ሚጢጢ
«ቢሆንስ ማለት አትችልምÝÝ አለቃን ወደላይ መናገር ምን ማለት ነው? ውኃ ወደ ላይ አይፈስም ይባላልኮ» አሰግድ ምራቁን በፍርሃት እየዋጠ ተናገረ፡፡ ዓለሙ ደስ አለው፡፡ አሰግድ የተናገረው እርሱ ያላሰበውን ነገር ነው፡፡ «» ቡድን ልጆች ትንሽ ተንበረከኩ፡፡ እነርሱ ሲንበረከኩ ብዙ ልጆች «ምን አጨቃጨቃቸው አርፈው ዓለሙ የሚላቸውን አይሰሙም፡፡» ይሉ ነበር፡፡
ሠናይት ደግሞ «በቀደም ሰልፍ ላይ የተባለውን እረስተውታል፡፡ ዩኒት ሊደራችን መጨቃጨቅ፣ ማንጓጠጥ፣መከራከር ብልግና ነው፡፡ አለቆቻችሁ እና መምህሮቻችሁ የሚሏችሁ ሁሉ እሺ ብሎ መቀበል ብቻ ነው» ብለዋልኮ፡፡
ጨዋታው እንደተጀመረ ዓለሙ ወደኛ መጣና እኔን እና አሸብርን «ጨዋታውን ተከታተሉና ለሚኒ ሚዲያ ዜና ትሠራላችሁ» አለን፡፡ ደስ ብሎን ደብተር እና ስክርቢቶ አወጣንና መጻፍ ጀመርን፡፡
ጨዋታው ሲያልቅ ተማሪዎቹ በተሰበሰቡበት ዜናውን አሸናፊ አነበበው፡፡
« አምስተኛ ተማሪዎች መካከል የተደረገው የእግር ኳስ ውድድር «» ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ» ይላል ርእሱ፡፡
«ይኼ ዜና መሆን አይችልም» አለ ዓለሙ በቁጣ
«ለምን?» አለ አሸናፊ
«ርእሱ መቀየር አለበት» አለች ቤቲ
«ምን ተብሎ?» አላት አሸናፊ
«በአምስተኛ ተማሪዎች መካከል የተደረገው የእግር ኳስ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ» ነው መባል ያለበት» አሰግድ ለራሱም አጨበጨበ፡፡
«እንዴት የኳስ ውድድር ተደርጎ ስንት ለስንት እንዳለቀ ሳይገለጽ ዜና ይጻፋል» አሸናፊ ሽንጡን ገትሮ ተከራከረ፡፡
«እስኪ ሬዲዮ ስማ፤ እስኪ ቲቪ ተመልከት ስብሰባው በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ፤ ጉባኤው ልዩ ልዩ ውሳኔ አሳለፈ፤ የዓመቱ የትምህርት ሥራ አበረታች ነበር ተባለ፤ ዕድገታችን ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው ነው ይባላል እንጂ ስንት? የሚለው ሲነገር ሰምተህ ታውቃለህ?» ቤቲ ሞገተቺው፡፡
«እርሱማ እውነትሺን ነው» አለ አሸናፊ ቀዝቀዝ ብሎ፡፡
ቤቲ ፊቷ ፈካ «እና አንተ ከሬዲዮ እና ከቲቪ ትበልጣለህ?»
«አይበልጥም፣ አይበልጥም» ብዙዎች ደገፏት፡፡
ቀጠለ ዜናውን ማንበብ
«የመጀመርያውን ግብ ያስገቡት የሀ ቡድን ነበሩ፡፡ ነገር ግን ዳኛው ዓለሙ ጮርናቄ ባለመግዛታቸው ሽሮባቸዋል» ዓለሙ እሳት ላሰ እሳት ጎረሰ፡፡
«እንደዚህ ተብሎ ዜና ይጻፋል?»
«ይኼ እውነት አይደለም?» አለ አሸናፊ፡፡
«እውነት ሁሉ ዜና ይጻፋል፤ አጠይመው አጠይመህ ጻፈው»
«ምን ብዬ ነው የማጠይመው?» አለ አሸናፊ ቋንቋው ራሱ አልገባው ብሎ፡፡
«የመጀመርያውን ጎል የሀ ቡድን ቢያገቡም ነገር ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ተሽሮባቸዋል ብለህ ነዋ»
«አንዳንድ ማለት ምን ማለት ነው?»
«በቃ አንዳንድ ነዋ»
«ማን ሻረው? ለምን ተሻረ? ቢባልስ»
«አንተ ደግሞ የአማርኛ መምህራችንን ይመስል አርፍተ ነገሩ ሁሉ ባለቤት ያስፈልገዋል እንዴ» ቤቲ ነበረች፡፡
«ሰው አትንካ፣ ዝም ብለህ ድርጊቱን ጻፍ» አሸናፊ ግ ራ ገባው
ቀጠለ ማንበብ፡፡
«ጨዋታው በሀ ቡድን የጨዋታ የበላይነት እና በለ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቋል፡፡»
አሁን ሃያ ሁለቱም ተጨዋቾች አሸናፊን ሊበሉት መጡ፡፡
«ይኼ እኛን ለማሳጣት ነው፣ ማንን ልታስበላ ነው፣ የማንም መጨዋቻ ሊያደርገን ነው እንዴ½ ዜናው ሚዛናዊነት ይጎደለዋል፣ ወደ አንዱ ቡድን ያደላ ነው» ሁሉም ጮኹ፡፡
«ቀይረው ቀይረው ዜናውን፤ እዚቹ ቀይረው፤ አፍንጫህን ሳልልልህ ቀይረው» አለ አዳነ ተማቹ ቡጢውን አዘጋጅቶ፡፡
«ምን ብዬ ልቀይረው» አለ አሸናፊ ጨንቆት፡፡
«ሁለቱ ቡድኖች በሚገባ ተጫውተው በደማቅ ሁኔታ አለቀ፡፡ ጨዋታው ወደፊትም ቀጣይነት ይኖረዋል ብለህ ጨርሰው»
«እንዲህ ከሆነኮ ዜናው ምንም አይናገርም» አሸናፊ አዘነ፡፡ ከጻፈው ዜና ውስጥ ያልታረመው የጸሐፊዎቹ ስም ብቻ ነው፡፡
«አየህ አሸናፊ ዜና ማለት አሁን ያሻሻልከው ነው፤ ምንም የማይናገር፤ አንዳች ነገር የሚናገሩትን ዜናዎችማ አንሰማቸውም አናያቸውም፣ ስለዚህ የትኞቹን አርአያ አድርገህ ትጽፋቸዋለህ፤ የሚያሳዝነው ቀደምቶቻችንን ከነስሕተታቸው እንድንቀዳ የተፈረደብን መሆናችን ነው» አለና አጥናፉ ተንታኙ ወደ ክፍል አመራ፡፡

24 comments:

 1. ጉደኛው አጥኔ በቃ አንዴ ተንታኝ የሚል ስም አሸክመውት የሚችለውንም የማይችለውንም ይተነትናል አይደለም? ... አጥንዬ አንዳንዴ አልችልም ... አላውቅም ይባላል እኮ። ... በየጨዋታ መድረኩ እንዲህ ወጌሻውንም ፣ የቡድን መሪውንም ፣ ጨዋታውን ሊዘግብ የሄደውን ጋዜጠኛ ሳይቀር ገብታችሁ ብትጫወቱ የሚሉ ስንት ፈላስፋ ተንታኝ አጥናፉዎች አሉ መሰሏችሁ ...

  ReplyDelete
 2. ይህቺ ናት ኢትዮጵያዊነት

  አንዳንዶቹ ታዳሚዎች የጡመራውን መድረክ የልጅ ጨዋታ እያስመሰሉት ነው፡፡ ስድብና፣ ከፍ ዝቅ ማድረግን የተያያዙት ይመስለኛል፡፡ አንድ ሳንቲም የተለያየ ገጽታ እንዳለው እንኳን ለመረዳት የሚችሉ በማይመስል መልኩ አንድ ግለሰብ ፊትና ኋላ፣ ግራ ቀኝ፣ ውስጥና ውጪ ወዘተ ... የሌለው ባለአንድ ገጽ (unidimensional) አድርገው ይስሉታል፡፡ ሎሎቹ ደግሞ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥንቅጥ በአርጩሜ ልክ የማስገባት ያህል ቀለል አድርገው የጽሑፉን መልእክት ወደጎን በመተው በስሜታዊነት ሲወናጨፉ ይስተዋላል፡፡ በተለይ አንድ ታዳሚ የታሪክ መፋለስ እንዳለ በሚያስመስል መልኩ ከየት አመጣኸው ዓይነት ተጠየቃዊ አስተያየት ካቀረበ በኋላ ከታሪክ አዋቂዎች ጋር ለማገናኘት እንደሚተባበር ገልጿል፡፡

  ይህ የጡመራ መድረክ ሃሳባቸውን በጽሑፉ የሚያቀርቡ ታዳሚዎች ብቻ ተደርጎ ከተወሰደ ስህተቱ ከራስ አልፎ በስሚ ስሚ የሚታደሙትንም ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ነው፡፡ የዚህ ጡመራ ታዳሚዎች ከ1,000,000 በላይ ናቸው፡፡

  በዚህ ቁጥር ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንቶችና የገዢው ፓርቲ ቁልፍ ሰዎች ሳይቀሩ በተዋረድ የመድረኩ ቅርብ መሆናቸው ሊጠረጠር አይገባም፡፡ አስረጂዬ "አዲስ ነገር" ሳምንታዊ ጋዜጣ ናት፡፡ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብአዴን የፖለቲካ መሪዎች በሁለተኛ ወገን ጋዜጣውን በማስገዛት ማታ ቤታቸውን ቆልፈው በድብቅ ያነቡ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይናገሩ ነበር፡፡

  ከዚህ አንጻር የአስተያየት ሰጪዎቹ ቁጥር ኢምንት ነው፥ ግን ደግሞ አስተያየታቸው ጠቃሚ ነው፡፡ ጥልቀት ያለው ተጨማሪ ሃሳብ ከማካፈል አንስቶ ነገሩን ባለጡመራው ካቀረበበት እይታ ወጣ ባለ መልኩ አስፍተን እንድናይ የሚያደርጉ አቀራረቦች ለማየት ችያለሁና፡፡ በአንጻሩ የቀጨጩ፣ ግለሰብ ተኮር የሆኑ፣ ስድብ እንደ ሚኪያቶ አረፋ አንደበታቸው ላይ የሚኩረፈረፍባቸው ታዳሚዎችንም ለማየት አስችሎናል ባይ ነኝ፡፡

  እነዚህ ኩርፍርፍ ማኪያቶዎች ስክነት የሚባል መንፈስ ስላልፈጠረላቸው በደመነፍሰ ተነስተው የኢትዮጵያ ተቆርቋሪ፣ የወያኔ ቀንደኛ ተቃዋሚ መስለው ይታያሉ፡፡ እነዚህ ሰለሞኔዎች ናቸው ለእኔ፡፡ ጥቅም ሲቀር ወይም ሲገኝ ማረኝ ብለው ወያኔ እግር ስር የሚገኙት (ቁረጠው ፍለጠው በዘፈነበት ዛሬ ደግሞ ይምራን ያለውን አርቲስት ልብ ይሏል)፡፡ የምርጫ ሕግ እያለን፥ በምርጫ ሥነ ምግባር ሕግ ካልተገዛን፥ ብለው ለመሸወድ ገብተው ተሸውደው የቀሩት፣ አንፈርምም ያሉትን ጸረ ሕዝብ ብለው ከኢሕአዴግ ጋር አብረው ያሳጡትም እንደ እኔ ወገናቸው ከሰለሞኔዎች ነው፡፡ በምርጫው ወቅት ሕዝቡ ድምጹን ለእነሱ ነፍጎ አንፈርምም ላሉት መስጠቱ ሲታይም የሕዝብ አሸናፊነት ከመረጋገጡም በላይ ከሕዝብ ጋር የቆመውንም በውል አሳይቷል፡፡

  የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልዕልናና ብልጽግና ብቻ ለማዋል መጀመሪያ ለራስና ለራስ ብቻ ቃል መግባት ነው፡፡ በአደባባይ መለፈፍ ብቻውን ጠቃሚ ነው ብዬ አልወስድም፤ ቢሆንማ ኖሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምስት ዓመት በፊት ሦስት ጊዜ ይበላ ነበር፡፡ የሥራ አጡ ቁጥር ተገልብጦ የሰው ኃይል እጥረት ይገጥመን ነበር፣ ባድመ በቴሌቪዥን ሳይሆን በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ውሣኔ የእኛ ትሆን ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡

  ታዲያ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማን ይምራው በየትኛው መንገድ ብዬ ስጠይቅ የሚከተሉት መልሶች በኅሊናዬ ይመጣሉ፣

  1. በጭፍን ጥላቻ እንደ ማሽላ የማይስቁ፣ ገንዘብና መሞዳሞድ ትውስ የማይላቸው፤ ኢትዮጵያን ሲስሉ ከቤተሰባቸውና ከቤተሰዎቻቸው በዘለለ በአራቱም አቅጣጫ ዘር፣ሃይማኖት፣ጾታ ሳይገድባቸው ኢትዮጵያ የአማራ፣የኦሮሞ፣የትግሬ፣የሲዳማ፣የሶማሌ፣ የአፋር፣ የወላይታ፣ የጉራጌ፣ የአደሬ፣ የኩናማ የ80ዎቹ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሆኗን ተገንዝበው የሚታገሉ፡፡
  2. ቂምና በቀልን በይደር ይዘው ነገ ለመግረፍና ለማሳደድ፣ አሰፍስፈው የማይጠብቁ፣፤ እንደ ማንዴላ የኢትዮጵያ ቁስል የሚሽረው በይቅርታና በብሔራዊ እርቅ በይቅር ለእግዚአብሔር ነው ብለው ኢትዮጵያን የማትበታተን፣ የማትበጣጠስ የሰሜኑ ደቡብ፣ የምሥራቁ ምዕራብ ወይም እንዲህና እንዲያ በነጻት እየተንፈላሰሰ የሚኖርባት በአንድ ጠንካራ መቀነት የታሰረች አገር አድርገው ለመገንባት የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ትግል ስትራቴጂ ነድፈው የሚንቀሳቀሱ፡፡

  ሜሪላንድ አሜሪካ

  ReplyDelete
 3. ታዳሚዎች ሆይ፣

  ጽሑፉ በመሠረታዊነት የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ትዝታን ለማስኮምኮም አልቀረበም፡፡ ተረት ተረቱን ተዉትና ይህ ጽሑፍ እኛ ክፍል የተባለችውን ኢትዮጵያን የሚገልጽ ነው? በእውነትም እኛ ክፍል ውስጥ ሥርዓት የሚመስል ግን ደግሞ ጉልበትና ማስፈራራት ነው ሕጋችን? እኛ ክፍል ውስጥ ከአለቃው ውጪ ሌሎቻችን ለሕግና ለሥርዓት እንገዛለን? ክፍላችን ለዲሲፒሊን የሚገዛ፣ በሞራል የታነጸ፣ ሃሳብ በነጻነት የሚፈልቅበት ደግሞም የሚንሸራሸርበት ክፍል ነው? የእኛን ክፍል የሚመራት የሃሳብ(የእውቀት)ልዕልና ነው ወይስ ድርቅና የሚለውን እየጠየቅን እውነት እንድንመሰክር፣ ያለንን እንድናካፍል፣ የተንሻፈፈውን እንድናቃና ነው፡፡

  ታዲያ ተረት ተረትን ምን አመጣው? ባለቤቱ ተረት ተረት ብሎ አቅርቦልናል፡፡ ተረቱ ወቅታዊውን የአገራችንን ሁኔታ ይመለከታል? መልስ እንስጥ፡፡ ያለበለዚያ ያኔ አንደኛ ደረጃ ... እያልን ልጅነቴን አንጫወት፡፡

  ከሜሪላንድ አሜሪካ

  ReplyDelete
 4. የሚያሳዝነው ቀደምቶቻችንን ከነስሕተታቸው እንድንቀዳ የተፈረደብን መሆናችን ነው

  ReplyDelete
 5. «እንዲህ ከሆነኮ ዜናው ምንም አይናገርም» አሸናፊ አዘነ፡፡

  ReplyDelete
 6. Dear Daniel,

  The continued article have followed inductive analysis. It went from detail to general assumptions. I appreciate your perspective and analysis capacity that teach your audience by giving simple stories and convey reality in life.

  ReplyDelete
 7. ልክ ልኬን ነገረኝ
  ያውቅበታል እሱ እውነታን ለማቅረብ፤
  በሚገባን ብሂል ቀምሮ ማስነበብ።
  የተጓዝንበትን የደመነፍስ መንገድ፤
  አንዱ ሁለት ሆኖ ለየብቻ ሲያረግድ፤
  ለምታልፈው አለም እንዲያ ሲተራረድ፤
  ከራስ ጋር ሲግጥም በቡድን ተባድኖ፤
  አካሉን አውድሞ ሲዘፍ በፋኖ፤
  አይቼ ማደጌን ሆኘ በጉረኖ፤
  ልክ ልኬን ነገረኝ በክፍል ሸሙኖ።
  የዘመኑም ቢሆን ፋኖ የወለደው፤
  ይኸው ተቀምጧል ዛሩ እንደተጋባው።
  የሚገጥማቸውን መድቦ ጨርሷል፤
  እንድንለያቸው ስምም ሰጧቸዋል።
  ፊሽካውንም ነፍቷል፤
  መመሪያም ተላልፏል፤
  ታሪክን ለመድገም ሁሉም ይሯሯጣል።
  መግጠሙስ ባልከፋ፤
  መሪን ለመለየት ስለሚሆን ተስፋ።
  ግና ችግራችን እኛ እምንፈልገው፤
  ለመግጠም ያሰብነው በድሮው ሜዳ ነው።
  ያ በእየ ሰፈሩ ኳስ የገጠምንበት፤
  ጋሬጣና ድንጋይ የተነጠፈበት፤
  የገባ ተጨዋች የሚላላጥበት፤
  እርግፍ አርገን ትተን አስበን ወደፊት፤
  ምነው ባዲስ ሜዳ ቢሆን ምን አለበት?
  ተጨዋች ሳይደማ አይታም ሳይሰጋ፤
  መሪያችን ለመምረጥ ምነው ብንከፍል ዋጋ?

  ዲን ዳንኤል፡ በጣም አመሰግናለሁ።
  ከጀርመን

  ReplyDelete
 8. I am always read ur articles and I feel great and also feel anger ... I want ask question for everyone read Daniel's view ...pls we have to be practical person ... I was started to be person ...

  ReplyDelete
 9. dani it is very interesting . i think it will be continue.....

  ReplyDelete
 10. hmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmm

  ReplyDelete
 11. dn leul
  LET GOD BLESS U DN!
  DON'T FORGET TO CONCENTRATE ON SPIRITUAL ISSUES.

  ReplyDelete
 12. this and some other stories happened in ur class,country.SO WHAT????.................. PLS
  leave such stories for beiwketu or some other authors. what we need from u is a soul food. tell us about forefathers.i am afraid we are losing u.

  ReplyDelete
 13. I go through the article...I really like it. Actually the message is not to remind the elementary class life. It has a very huge message to all Ethiopian. We can see the different behavior of human beings. And we can learn a lot of things from each one of the actors. The overall message is to in for that we should focus on the practical part rather than talking. We can not build a country of our dream theoretically (Just by talking).It should be through carrying out our part as soon as possible. We should not wait someone to do for us. Change can start from oneself not from others.

  THANK YOU D/n DANI...GOD BLESS YOU

  ReplyDelete
 14. «ዋናውኮ ጎል ማግባት አይደለም፤ ጮርናቄ መግዛት ነው፡፡»
  Thanks Dani

  ReplyDelete
 15. Thanks D/n.Daniel, Continue,but do not forget spiritual writing for ever,please give more emphasis for Spiritual.

  ReplyDelete
 16. ዲ/ን ዳንኤል በምሳሌ የምትፅፋቸው ነገሮች ለሚገባው ሰው ታላቅ መልዕክት የሚያስተላልፉና የሚገርሙ ናቸው። ሌላው አስተያየት የምንሰጥ ሰዎች ብዙ ጊዜ ስታዘብ ዳንኤል የፃፈውን መልሰን Post እናደርጋለን ወይም ምንም ትርጉም የሌለው መልዕክት እናስተላልፋለን። ለምን? ይቅርታ! እኔ እንደስህተት ያየውትን ሳልናገር ማለፍ ስለማችልና የናንተንም የሰውንም ጊዜ ያባከናችሁ ስለመሰለኝ ነው። እባካችሁ መፃፍ ያቃተን ሰዎች ጥሩ አንባቢ ብቻ እንሁን።

  የእግዝአብሔር ሰላም አይለየን!! አሜን።
  የኖኅ መርከብ ከአ.አ

  ReplyDelete
 17. This is the real.... In our contry..... Ethiopia...

  ReplyDelete
 18. ዘነበ ወላ የተባሉ ፀህፊ ልጅነት በሚባል መፅሀፋቸው የልጅነት ዘመን ትዝታቸውን በሚጥም ቋንቋ አቅርበውልን ነበር፣ በዚህ ፁኁፉቸው የክፍላቸው አለቃ የነበረው ልጅ ሌሎቹን ህፃናትን በኩረኩም ያጎናቸው የነበረው ከቤታችው ካመጡት ቆሎና ዳቦ አላካፍልም ስለሚሉት እልቅናውን ተገን በማድረግ ቂሙን ለመወጣት እነደሆነ ሸጋ በሆነ አገላለፅ ተርከውልናል፣ የዛሬው የወንድማችን የዲያቆን ዳንኤል ወግም ከሞላ ጎደል የሚያሳየን ሀቅ ቢኖር በዛ በየኔታ ት/ቤት ተጀምሮ እሰከሽምግልና የዘለቀው የአለቅነት መንፈስ ዛሬም ድረስ ጉዱ ቢመዘዝ ቢመዘዝ አላልቅ ብሎ ይህው ፍዳ አበሳችንን እንቆጥራለን፡፡

  በእኛ ቤት እልቅና ውርስ ነው፣ አለቃ ፈላጭ ቆራጭ ነው፣ ወደደውን ያኖራል፣ ያለወደደውን ደግሞ የአይንህ ቀለም አላማረኝም ብሎ እንኳ ሊያጠፋው እንደሚችል መብት እንዳለው አምኖ የተቀበለ ነው፣ እልቅና ርስት… እልቅና ጉልት ነው በእኛ ሰፈር… ማን ወንድ ነው፣ ማን ጀግና ነው አለቃነታችንና የአለቅነታችን ዘመን የሚወስነው… እንግዲህ የሚበዛው ታሪካችን ያለፈው ከጓዳ እሰከ ማጀት፣ ከየኔታ ት/ቤት እሰከ ትላልቆቹ የትምህርት ተቋማት፣ ከወረዳ/ ቀበሌ እሰከ ትላልቆቹ የፖለቲካና የፍትህ ተቋማት አለቅነታቸው ይግባኝ በሌለው አለቆች ፈላጭ ቆራጭነት ስር ነው…

  ምህረት፣ እርቅ፣ ፍቅርና ይቅር የመባባል መንፈስ ፈፅሞ የተለየው የአለቆቻችን ልብና የእልቅናቸው ዘመን መቼ ይሆን እንደ ማንዴላ በአለቅነቴ ዘመን ለህዝቤ ይሻላል፣ ይጠቅማል የሚለውን ለመስራት ሞክሬአለሁ፣ አሁን ግን ሀገሬንና ህዝቤን ሊጠቅምና ሊያገለግል የሚችል ሌላ አለቃ ያሰፈልገናል በሚል ትሁትና ቅን መንፈስ ስልጣኑን በሰላም የሚስረክብ አለቃ በታሪካችን ለማየት የምንታደለው… አለቃ/መሪ የፍቅርና የይቅርታ ልብ ሊኖረው ይገባል፣ እነደእነዚህ አይነቶቹ አለቆች/መሪዎች ይፈጠሩ ዘንድ ሁላችንም በየመሰኩና ባለንበት ቦታ ሃላፊነት አለብን፡፡
  ስላም! ሻሎም!
  ፍቅር ነኝ- ከሀገረ ማዲባ (ኔልሰን ማንዴላ)

  ReplyDelete
 19. ወገኖቼ አስኪ ግን ይህች ክፍላችን የእኛ ቤተ ክርስትያን አየይደለችም ብላችሁ ታስባላችሁ? እስኪ አለቃዎቿን እዩአቸው ፡፡ እኛም ደግሞ 38ንቱ ተመልካቾች አይይደለንም ትላላችሁ ?

  ዲ. ዳኒ እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡ ለእኛም ባለንበት ሁሉ ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ ባለን ሁሉ ምን ማድረግ እንዳለብን አስኪ አንዲሁ ጠቆም አድርገን፡፡

  Tesfahun Oute ነኝ ,ከ Chandler, Arizona

  ReplyDelete
 20. የአገሬ ጋዘጠኞች አንጀቴን በሉት(እነ ኢቲቪ) !!! “«እንዲህ ከሆነኮ ዜናው ምንም አይናገርም» አሸናፊ አዘነ፡፡ ከጻፈው ዜና ውስጥ ያልታረመው የጸሐፊዎቹ ስም ብቻ ነው፡፡”

  ReplyDelete
 21. Sara Adera
  ለውጥ ማምጣት የሚቻለውኮ በተጨዋችነት እንጂ በተመልካችነት አይደለም፡፡
  «ዋናውኮ ጎል ማግባት አይደለም፤ ጮርናቄ መግዛት ነው፡፡»
  እጅህን ይባርከው!
  እንግዲህ ልቦና ይስጠን ለእነ ጥቅም አሳዳጆችም እሱ ፈጣሪ አምላክ መልካሙን መንገድ ይምራቸው::
  ሁላችንንም እሱ ይቅር ይበለን!!!

  ReplyDelete
 22. Dn, Dany... negerna menged ket yale kehone siyanebutm sisemutm ayitmim. Danishu eyitawochih hulu and neger lay bicha MUCHICHICHICH...... yemilu balemehonachew kemastemarm yaznanalu kemaznanatm demoooo... BEQA Dany.

  ReplyDelete