አሁን ያለነው እኛ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ይህ ክፍላችን አምስተኛ ቢ ይባላል፡፡ ስድሳ ተማሪዎች እዚህች ክፍል ውስጥ ተቀምጠናል፡፡ በጠዋቱ ክፍል ውስጥ ገብተን ስም ጠሪ መምህራችንን እየጠበቅን እንገኛለን፡፡ ዛሬ ለክፍላችን የተለየ ቀን ነው፡፡ የክፍላችንን አለቃ እንመርጣለን፡፡
ሰልፍ ላይ ብዙዎቻችን ማን አለቃ መሆን እንዳለበት ስናወራ ነበር፡፡
አንዳንዶቻችን አዳነ ተማቹ አለቃ መሆን እንዳለበት አስበናል፡፡ አዳነ ተማቹ የሚታወቀው ያገኘውን ሁሉ በመማታት ነው፡፡ ለእርሱ የሁሉም ነገር መፍትሔ ዱላ ነው፡፡ እርሱ መጣ ከተባለ ሁላችንም አንገታችንን ነው የምንደፋው፡፡ በተለይ ሴቶቹ በጣም ነው የሚፈሩት እና የሚጠሉት፡፡ አዳነ ተማቹ አለቃ መሆን አለበት የተባለበት ምክንያት ሁለት ነው፡፡ አንዳንዶቻችን አዳነ ተማቹ የክፍላችን አለቃ ከሆነ በክፍል ውስጥ ረባሽ ተማሪ አይኖርም፡፡ እየገጨ ጸጥ ያደርገዋል ብለን አስበናል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ አዳነ ተማቹ አለቃ ካልሆነ እርሱን ማን አለቃ ሆኖ ጸጥ ያሰኘዋል? ብለው ይጠይቃሉ፡
የአዳነ ተማቹን አለቃነት የማይደግፉት ደግሞ አዳነ ተማቹ አለቃ ያስፈልገዋል እንጂ አለቃ መሆን አይችልም ይላሉ፡፡ እኛ በክፍላችን ውስጥ መማር እና መደሰት እንጂ መፍራት እና መንቀጥቀጥ አንፈልግም ይላሉ፡፡
ሌሎቹ ተማሪዎች ደግሞ ዓይናለም አለቃ መሆን አለባት ይላሉ፡፡ በርግጥ ይህንን አስተያየት ብዙዎቻችን አልተቀበልነውም ነበር፡፡ ሴት እንዴት አለቃ ይሆናል፡፡ እንዲያውም ዕፀገነት ሴት አለቃ መሆን የለባትም ብላ ተከራክራለች፡ «ሲረብሹ መማታት አትችልም፤ ታለቅሳለች» ነበር ያለቺው፡፡
ዕንግዳ መሆን አለበት ብለው አስተያየት የሰጡም ነበሩ፡፡ እንግዳ ሁሉንም ነገር በመቃወም የሚታወቅ ልጅ ነው፡፡ ክፍል ጥረጉ ሲባል ይቃወማል፤ አትክልት አጠጡ ሲባል ይቃወማል፤ ተሰለፉ ሲባል ይቃወማል፤ አንዳንድ ጊዜ መምህሩ የለም ውጡና ተጫወቱ ሲባልም ይቃወማል፡፡ ስለዚህ አለቃችንን እየተቃወመ ከሚያስቸግረን ለምን ራሱን አለቃ አናደርገውም ያሉ ልጆች ነበሩ፡፡
አሰግድ መሆን አለበት አለች ስመኝ፡፡ ሁላችንም ሳቅን፡፡ እርሷም የቀልዴን ነው ብላለች በኋላ፡፡ አሁን አሰግድ ይሁን ቢባል ማን ይስማማል? ራሱም አይስማማም፡፡ አሰግድኮ ማጨብጨብ ብቻ ነው የሚችለው፡፡ በቀደም ለት ስድሳ አራት ሲካፈል ለአራት ስንት ነው? ብሎ መምህራችን ጠየቀንና አሰለፈች «ሁለት» አለች፡፡ አሰግድ አጨበጨበ፡፡ መምህራችን ተበሳጩና «አንተ ደግሞ ሲገባህም ሳይገባህም ነው እንዴ የምታጨበጭበው» አሉትና አሳቁበት፡፡ አንድ ቀን ዩኒት ሊደራችን እየተናደዱ መጥተው እኛ ክፍል ገቡ፡፡ ሁላችንም ፈርተን ጸጥ አልን፡፡ «ክፍል ቶሎ ግቡ ስትባሉ ለምን አትገቡም?» ብለው ማንም ያልመለሰውን ጥያቄ ጠየቁን፡፡ ሁላችንም ሊገርፉን ነው ብለን ፈራን፡፡ አሰግድ ሆዬ አጨበጨበ፡፡
ዩኒት ሊደራችን «ማነው ያጨበጨበው» አሉ፡፡ አለንጋቸውን እንደያዙ፡፡
«እኔ ነኝ» አለ አሰግድ፡፡
«ለምንድን ነው ያጨበጨብከው?» አሉ አለንጋውን እያወዛወዙ፡፡
«በሃሳብዎ ተደስቼ፡፡» መምህሩ አፋቸውን በእጃቸው ይዘው እየሳቁ ከክፍል ወጡ፡፡ እኛ ግን ከዱላ ስላስጣለን ያን ቀን አመስግነነዋል፡፡
ሁሉንም የሚያስማማ አለቃ ሊገኝ አልቻለም፡፡ የክፍሉ ልጆች «አይሞቅሽ አይበርድሺ» የሚሏትን ትኅትናንም የጠቆሙ ነበሩ፡፡ ኤፍሬም ግን ተናድዶ «ምን እርሷ አይሞቃት አይበርዳት፡፡ ስንገረፍም ዝም ነው፤ ስንሸለምም ዝም ነው፡፡ ባለፈው የኛ ክፍል በሲ ክፍል ሲሸነፍ ሁላችን ስናለቅስ እርሷ ዝም አለች፡፡ ዲ ክፍልን ስናሸንፍም እኛ እየጨፈርን እርሷ ዝም አለች፡፡ ምን ብለን ነው አሁን እርሷን የምንመርጣት» ብሎ ሲከራከር ነበር፡፡
አንድ የቀረን አጥናፉ ተንታኙ ነው፡፡ አጥናፉ ተንታኙ በእድሜ ከሁላችንም ይበልጣል፡፡ ሁልጊዜ መጨረሻ ነው የሚሰለፈው፡፡ በችግር ምክንያት ዘግይቶ ትምህርት እንደ ጀመረ አንድ ቀን አውርቶናል፡፡ አንድ ነገር ሲሆን እርሱ ለምን ይህ እንደሆነ ታውቃላችሁ? ይልና ይተነትናል፡፡ ልጆቹ በዚህ ምክንያት አጥናፉ ተንታኙ አሉት፡፡ አንዳንዴ ከባድ ነገር ያመጣና እርሱ እና መምህሮቻችን ይከራከራሉ፡፡
ቤተ ልሔም ግን «አጥናፉ ተንታኙ ከተመረጠ እኔ ክፍል እቀይራለሁ» አለች፡፡ «እርሱ እያንዳንዱን ነገር ሲተነትን ልባችን ይደክማል» ብላ አሳቀችን፡፡ «በቀደም ዩኒት ሊደሩ ገርፈውኝ እያለቀስኩ ስመጣ አጥናፉ ተንታኙ አየኝና ለምን እንደተመታሽ ታውቂ ያለሽ? ብሎ ይተነትንልኛል፡፡ ለራሴ አሞኛል እርሱ...»
ታድያ ማን ይሁን?
ሰልፉ ተጀመረ፡፡ ሰልፉም አለቀ፡፡ እኛም ክፍል ገባን፡፡
ክርክሩ እንደ ቀጠለ ስም ጠሪ መምህራችን መጡ፡፡
«ዛሬ አለቃ ለዚህ ክፍል ይሾማል» አሉ ስም ጠሪው፡፡ አጥናፉ ተንታኙ እጁን አወጣ፡፡ ቤተ ልሔም ደግሞ «አሁን ምኑ ይተነተናል» አለች፡፡
«የክፍሉን አለቃ እኛ እንመርጣለን ወይስ እርስዎ ይሾማሉ» አለ አጥናፉ፡፡ አንዳንዶች እህ እህ አሉ፡፡
«ያው ነው፡፡ ጊዜውን ለማሳጠር ያህል ግን እኔ እሾማለሁ» አሉ ስም ጠሪው ስማችን የተጻፈበትን ክላሴር ዴስኩ ላይ እያደረጉ፡፡
«ለምን እኛ አንመርጥም» አለ አጥናፉ፡፡
«እናንተ ምኑን ታውቁታላችሁ፡፡ ገናኮ ልጆች ናችሁ» አሉ ስም ጠሪው እየሳቁ፡፡
«ዛሬ እጅ አውጥተን ይሆነናል የምንለውን መምረጥ ካልቻልን ስለ ምርጫ እንዴት ሊገባን ይችላል፡፡ ትክክለኛ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መጀመር ያለበትኮ ከክፍላችን ነው፡፡ ዛሬ ያልለመድነውን ነገ ከየት እናመጣዋለን» አለ አጥናፉ፡፡
«አጥናፉ ፖለቲካ መታ» አለና እኛ ዴስክ ላይ የነበርነውን ልጆች አስናቀ አሳቀን፡፡ አስናቀ እጁን አውጥቶ ምንም ሃሳብ አይሰጥም፡፡ ሰው ከተናገረ በኋላ ግን ተደብቆ ይፎትታል፡፡
«አንተ ደግሞ ጀመርክ፡፡ ልጆቹን ለምን ተንኮል ታስተምራቸዋለህ» ስም ጠሪያችን ተቆጡ፡፡
አጥናፉ መቼም ከያዘ አይለቅም፡፡ «ይኼኮ ተንኮል አይደለም፡፡ መጀመርያ እኔ አለቃ እሆናለሁ የሚል ልጅ ካለ ይናገር፤ ከሌለ እኛ እንጠቁም፤ የተጠቆሙት ደግሞ ቢመረጡ ለክፍሉ ምን ምን እንደሚያደርጉ ይንገሩን፤ ከዚያ ድምፅ ይሰጥ፡፡ እንዲያውምኮ አስመራጭ ኮሚቴ ኖሮ፡፡ የድምጽ መስጫ ሳጥን ሠርተን፡፡ ካርድ አዘጋጅተን፡፡ በግልጽነት ምርጫ ለምን አናደርግም፡፡ ሐቀኛ አስመራጭ፣ ሐቀኛ መራጭ ማፍራት ከዚሁ መጀመር አለበት፡፡»
አንዳንዱ ነገር ገብቶናል፡፡ አንዳንዱ ነገር ግን ግልጽ አልሆነልንም፡፡ እጃቸውን ከዴስኩ በታች አድርገው ያጨበጨቡ ልጆችም ነበሩ፡፡
«አንተ በቃ ያለ መረበሽ ምንም ነገር አታውቅም፡፡ እድሜህን በየሜዳው ፈጅተህ መጥተህ አሁን በመማርያ ጊዜህ ትረብሻለህ» አሉና ስም ጠሪ መምህሩ ተቆጡት፡፡ ከዚያም «ይህንን እስክንጨርስ ውጭ ውጣ» ብለው አስወጡት፡፡ አንዳንዶች ከንፈራቸውን መጠጡለት፡፡ ግን እውነቱን ነውኮ ለምን አንመርጥም? እያሉ የሚጠይቁም ነበሩ፡፡ ማንም ግን እርሱን ደግፎም ሆነ ተቃውሞ በግልጽ ለመናገር እጅ ያወጣ አልነበረም፡፡ ውስጥ ለውስጥ ግን ተንሾካሾክን፡፡
«አሁን ትንታኔ ሳይሆን አለቃ ነው የምንፈልገው፡፡ ይህ ክፍል ረባሽ ክፍል ሆኗል፡፡ ባፈው ጊዜ የስፖርት መምህር ቀረብን ብላችሁ ተሰልፋችሁ ዳይሬክተሩ ጋ ሄዳችሁ፡፡ አያስተምረንም፣ ይቀራል፣ ይቀየርልን አላችሁ፡፡ ይህ ብልግና ነው፡፡ ከናንተ አይጠበቅም፡፡ መምህሩ ከቀረ አርፋችሁ ክፍል ውስጥ አትቀመጡም፡፡ ስለዚህ ጸጥታ ማስከበር የሚችል ሰው ያስፈልገናል፡፡ የሚፈራ፤ የሚከበር» አሉ ስም ጠሪያችን፡፡
ከዚያም «ዓለሙ» አሉና ተጣሩ፡፡
ዓለሙ «አቤት» ብሎ ተነሣ፡፡
«አንተ የዚህ ክፍል አለቃ ሆነሃል፡፡ ማንም ልጅ እንዳይረብሽ፤ የሚረብሹትን ስማቸውን ጻፍ፤ ሁሉንም ጸጥ አሰኛቸው» ዓለሙ ፊቱ ሁሉ ጥርስ ሆነ፡፡ ያ ሁሉ ክርክራችን ከንቱ ሆነና ማንም ያለሰበው ዓለሙ አለቃችን ሆነ፡፡ ዓለሙ ጮርናቄ እያመጣ ክፍላችን ውስጥ ይሸጥ የነበረ ልጅ ነው፡፡ እርሱ ከተመረጠ በኋላ ሁላችንም ጮርናቄ እየገዛን መብላት አዘወተርን፡፡
እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ክፍላችን ውስጥ ጸጥታ ሆነ፡፡ ማንም አያወራም፡፡
ክፍላችንም በትምህርት ቤቱ የጠባይ ተሸላሚ ሆነ፡፡
ይሄ ነገር "እኛ ሀገር ውስጥ " ብለህ ጽፈኸው ቢሆን ኖሮ እስከ መጨረሻው ማንበቤን እንጃ ... የምናውቀው የምናየው ነውና።
ReplyDeleteደስ የሚል መዕልክት ነው:: "እርሱ ከተመረጠ በኋላ ሁላችንም ጮርናቄ እየገዛን መብላት አዘወተርን" የዚህ የጮርናቄ ነገር ግን አልተገለጠልኝም::እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ያስባት
ReplyDeleteዲን ዳንኤል በጣም ደስ የሚል አዝናኝ መጣጥፍ ነው። የረሳሁትን የልጂነቴን ትውስታ ነው የነገርከኝ። ካንተ ገና ብዙ የህይወት ምግብ እንጠብቃለንና ድንግል ማርያም ከጎንህ ትሁን። በ ኢቢኤስ የጀመርከውንም ቃለ እግዚአብሄር አጠናክረህ ቀጥልበት። ብዙዎቻችን ከ እረኛችን ርቀናልና ትመልሰን ዘንድ ተመርጠሀል።
ReplyDeleteDani: to tell u frankly this is not as the previous ones....
ReplyDeleteDani I like the way you presented our childhood memory, it just reminds me my days at elementary schools in Ethiopia. For comparison purpose I will present what I experienced in in the other part of the world. The place is in one of the big universities in US. There are 120 students in my professional class, we need a class president who can represent us. one week before the election day the student dean of the college sent a memo asking anyone who is interested to be a class president to submit their credentials and on election day the candidates stand in front of the class and debated for a while and at the end we voted on who should be our class president.
ReplyDeleteSo can we say that classrooms are reflections of the real life in each country?
Ayimetinim Dani,
ReplyDeletenice one Dn Daniel!!!
ReplyDeletethe real reflection of what is going on in our land these days
ReplyDeleteአጥናፉዎች እኮ ነበሩን ነገር ግን ብዙ ስም ጠሪዎች እና አጨብጫቢ ተማሪዎች በዛን!
ReplyDeletenice view Dani
Dani I enjoyed your piece. Please write piece of this sort on "Model and Icon persons" respect to religion. There is pervasive problem of following persons in bad or good ways. Thus if you write peice of this ilks people may not recant their belief due to the mere fact that their model follow other religion. I hope St Paul is the Icon and I expect you will bring these sort amply.
ReplyDeleteኦ.ኦ.ኦ... ዳኒ እውነት ዛሬ ደግሞ ወደ አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት ወሰድከኝ፡፡ የቤት ጠረጋው፤ ዛፍ መትከሉ፤ አትክልት ማጠጣቱ ...... ደስ ይላል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ከ25 ዓመት በፊት የአንደኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ የሆነውን ነገር ሁሉ ግልፅ አለልኝ፡፡ በጣም የገረመኝ ያኔ የማስታውሰውን ያህል ሌሎችን አላሰታውሳቸውም፡፡
ReplyDeleteበነገራችን ላይ የአጥናፉን ንግግር ወድጄዋለሁ
""«ዛሬ እጅ አውጥተን ይሆነናል የምንለውን መምረጥ ካልቻልን ስለ ምርጫ እንዴት ሊገባን ይችላል፡፡ ትክክለኛ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መጀመር ያለበትኮ ከክፍላችን ነው፡፡ ዛሬ ያልለመድነውን ነገ ከየት እናመጣዋለን» አለ አጥናፉ፡፡ ""
ለቆይታ እንደ እነዚህ እያዝናኑ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ዕይታዎችህን አትርሳቸው፡፡
TESFAHUN OUTE ነኝ ከ CHANDLER, ARIZONA
Hi Dn. Dani yageligilot zemenihin yaberkitilih yigermihal 20 amet wede hula new yewesedikegn. tizita yetimihirt bet tizita betam des yilal eyazinana timihirt yisetal.
ReplyDeleteአቦ ስድስተኛ ክፍል እያለን በቀለ የሚባል አለቃችንን አስታወስከኝ ፡፡ በጥፊ የሚመታን በራሳችን እጅ ነበር .. እጅህን አላላ.. . . ይልና .. እጃችንን ስናላላ በራሳችን እጅ የራሳችንን ፊት ያጮልልን ነበር ፡፡ አሁን ከ20 ዓመት በኋላ ትዝ አስባልከኝ፡፡
ReplyDeleteአቦ አሁን ባገኝው ምን እንደምለው እኔ ነበር የማውቀው
ዳኒ እናመሰግናለን
Dn Daniel be EBS laye Yejemerkewen program ebakhen kenun ena seatun betegelselegn Egzihabhere Yeagelgelote gizhen yebarkleh.
ReplyDeleteMelat
I enjoy it so much B/c I was there before some years ago and u r so good in expression of the childrens idea and their language that is exactly how we used to talk, i read it as kid and laugh like one. I am so proud of u....... Egziabiher Yetebikeh
ReplyDeleteካነበብኩት ሁሉ ይኄ ምርጥ ነው በርካታ መጽሓፍት የሚያጽፉ ቁም ነገሮች ታጭቀውበታል ይህ ጽሁፍ በምርጫው እንዳይሳተፍ ለተባረረው ለአጥናፉ ቢሰጠው እንዴት ሰምና ወርቁን ብትንትን አርጎ ያወጣው ነበር!!! በጣም ፋፍተው ከወጡት ጭብጦች ውስጥ ልጥቀስ (ዓለሙ ጮርናቄ እያመጣ ክፍላችን ውስጥ ይሸጥ የነበረ ልጅ ነው፡፡ እርሱ ከተመረጠ በኋላ ሁላችንም ጮርናቄ እየገዛን መብላት አዘወተርን፡፡ እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ክፍላችን ውስጥ ጸጥታ ሆነ፡፡ ማንም አያወራም፡፡ ክፍላችንም በትምህርት ቤቱ የጠባይ ተሸላሚ ሆነ፡፡)
ReplyDeleteዳንኤል በርታ
ሰይፉ ከኦስሎ
ሰላም ዲን ዳንኤል፡-
ReplyDeleteየጻፍኸው ነገር እጅግ ሁለንተናን ይነካል። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ አይነት መልዕክት አለው። አምላክ እንዲህ አይነት ሰዎችን አብዝቶና አትረፍርፎ ይሰጠን ከማለት ውጭ ሌላ የምጨምረው የለኝም። ዘልቆ ገብ የሆነው እይታህ አይለየን።
ከሀገረ ጀርመን
Dear Daniel,
ReplyDeleteThis article gives an insight to our normal and realistic life. When I was in an elementary school particularly at grade one, we have a class leader "ALEQA". He was senior at age wise than us. I do remember how treated us. Finally, at the end of the year we passed to the grade two and our leader failed. When the new year begun and when we joined grade two, that guy didn't accept our grade two student status. Thus, he forced most of us to remain at grade 1 and the director involved on the issue to free us and to joined grade two. In line with this, your article inculcate how someone in power behave.
Nigusie DzARC
ReplyDeleteThank you Dn.Dani
but we didn't get such chance at least to forward our feeling to wards our church's elector and/or candidate rather they are simply assigned specially this day based on personal interest rather than candidate's quality of education
The analogy was strikingly awesome and yet painful when we delve deep in to it. It's a mere reflection of the status-quo vividly described in a rather satirical fashion. After all, that is the golden side of Literature. The Author catapulted me back in to my elementary life at "ATSE TSERTSE DINGLE ELEMENTARY" back in Bahirdar. Not surprisingly, he fast forwarded me through time and metaphorically showed me the incumbent's current stand as well...The yawning governance gap if you will. HATS-OFF to the writer!
ReplyDeleteTena Tabia Folk (Kebele 03)
Bahirdar
አዙሮ ነገረኝ
ReplyDeleteየመከነብኝን የራሴን ፍላጎት፤
መሪዬን ለመምረጥ እንዴት እንዳስቀሩት፤
ይኸው ተረከልኝ የሹመቱን ሂደት፤
የተከወነውን በኛ ትምህርት ቤት።
ባአስተማሪው ጫና አለቃ ተሹሞ፤
ስንቱን መና አስቀረው በዱላ ኮርኩሞ።
ያሁኑም አለቃ የቅጅ መሆኑን፤
አዙሮ ነገረኝ አስታዉሶ ታሪኩን።
ትዛዙን አክብሬ እያደርሁ ከወለል፤
ግዛ የሚለኝን ሸምቼ ያለውል፤
ዛሬም እኖራለሁ በሰፊዋ ክፍል።
ዲን ዳንኤል ድንቅ ለሆነው መጣጥፍህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ!
ከሀገረ ጀርመን
በጣም ደስ ይላል የልጅነት ትዝታ አራተኛ ክፍል እያለን ለፈተና መፈተኛ አንዳንድ የደብተር ሉክ ካልሰጠነው በረባሽ ስማችንን እየጻፈ በከንቱ የሚያስገርፈን የክፍል አለቃ ነበረን እድሜው ትልቅ ስለሆነ ብቻ የተመረጠ እስከአሁን ድረስ አልሳውም ዳኒ እግዚአብሄር የበለጠውን ያድልህ
ReplyDeleteyes its በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ አይነት መልዕክት አለው። it is like a book called "who stole my cheese".thxs Dani
ReplyDeleteውይ አሁንስ ያለቀብህ ይመስላል ፡፡ አያንጽም ብዙም አያዝናናም፡፡ አንተን የሚመጥን ጽሁፍ አይደለም፡፡
ReplyDeleteዳኒ በእውነት የክፍሉ ጸጥታ እና የጮርናቄው ነገር በፍጹም ሊገባች አልቻለም፡፡ “እርሱ ከተመረጠ በኋላ ሁላችንም ጮርናቄ እየገዛን መብላት አዘወተርን፡፡ እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ክፍላችን ውስጥ ጸጥታ ሆነ፡፡ ማንም አያወራም፡፡”
ReplyDeleteAhii! Aleka gin Chornake iyameta timirt bet yemishet mehon alneberebetim. Probably today...alekoch chornake eyeshetu yihon??
ReplyDelete"«ዛሬ እጅ አውጥተን ይሆነናል የምንለውን መምረጥ ካልቻልን ስለ ምርጫ እንዴት ሊገባን ይችላል፡፡ ትክክለኛ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መጀመር ያለበትኮ ከክፍላችን ነው፡፡ ዛሬ ያልለመድነውን ነገ ከየት እናመጣዋለን» አለ አጥናፉ፡፡ "
ReplyDeleteDany it the face of ETHIOPIAN ELECTION the others know about you any time and select for you the others always.
Really it is the starting of Ethiopian Parliament in regime of Emperor Haile selasie and continue in Derg SHENGO and NOW ADAYS in EPRDF when this type of election stop and we select our favorite representative .......................................
"GOD SELECT THE EFDR HOSE OF REPRESENTATIVES".
Hi Dani,
ReplyDeleteMany of your readers may not understand the'chornake' stuff at the end of your article.So I though I should do some explaing. The classroom enviroment is a symbolic setting that represents various government or non-government, social or religious institutions and even country. Adane Temachu is sybolic of dictator personalities,Atnafu is a genuine freedom fighter..a Trotsky...if you dont mind.Engda is a blind and cynical opposer or personality while Asegid is an equally bling and conformist supporter. The other characters all represent the lack of commitment, laziness selfishness and phonniness of the mass.Finally Aemu comes with his Chornake.
Alemu represents a 'cunning dictator' who manages his peoplethrough corrupt politics and economics.If you want to be excluded from the list of 'rebash' students which Adane has the full power to write, you have to buy his Chornake. If you don't do this, not only would he report you but won't sell you 'Chornake' especially on loan. Chornake, a food, represents our basic need. In order to get that we have to be silent. There are Alemu's in our working place, there are Alemu's in even the church and the Edir. With few best quality 'chornake's' which only satiate our biological appetite, we have to accept their unsavoy 'Chornakes':low sallary,orders,call for meetings,mass work campaigns, demonstrations,poor condominium with unfair pricetags,etc and nowadays oil,sugar, and flour.
yechornaqewn neger yemiyabraraln kal pls
ReplyDeleteThis is the target what going on in our country today. we wish dimocracy based on the path of Atnafu; and a people when they have abilities stand to participate on Alemus' business.
ReplyDelete“እርሱ ከተመረጠ በኋላ ሁላችንም ጮርናቄ እየገዛን መብላት አዘወተርን፡፡ እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ክፍላችን ውስጥ ጸጥታ ሆነ፡፡ ማንም አያወራም፡፡”
ReplyDeleteግልጽና ግልጽ ነገር ኪ.ኪ.ኪ .የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል ፡፡
እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡
selam leenanete yihun dani tebarek bro ebakachehu wegenoch le ehetachen << Erbika> betena seletamemech be hospital selmetegegn betselot asbuat ke Germen new
ReplyDeleteHello Diacon Daniel, isn't this site ... "your view"...? why can't you sometimes write some explanations when a lot of people are at lose about something you posted? you know its like what ever we (your viewers)write is falling on deaf ears, it can be frestrating at times...
ReplyDeleteበጣም ይገርማል!!!!
ReplyDeleteአምስተኛ እና ስድስተኛ ክፍል ባለሁበት ጊዜ አንድ ይመስገን መለስ የሚባል አልቃ ነበረን:: ሁል ጊዜም በመማታት ይታወቃል::አንዴ አንዱን ትልቅ ተማሪ "ለምቦጭ" እያል ፊት ፊቱን የጠፋውን አስታውስክኝ::
በጣም አስትማሪ ነው!!!!!!!!
Good Story Dn. Daniel it's the reflection of our real life!!!
ReplyDeletewhat happened to you? betam yewerede new .................
ReplyDeletealekebeh ende?
ReplyDeletebetam astemry new!Thank u Dn .Daniel
ReplyDelete