Tuesday, June 14, 2011

ትኩስ ድንች


አንድ ጊዜ ብዙ ሰዎች ምግብ ለመቀበል ቆመው ይጠብቁ ነበር፡፡ ሰልፉ ሁለት እና ሦስት መቶ ሰዎችን ሳያካትት አልቀረም፡፡ ምግብ አዳይዋ በትልቅ ጎላ ሚታደለውን ነገር ለሁለት ወጣቶች አሸክመው መጡ፡፡ ሰልፈኛው ሁሉም ተቁነጠነጠ፡፡
ምግብ አዳይዋ ጎላውን ከፈቱና ጭልፋቸውን ወደ ውስጥ ላኩት፡፡ የመጀመርያው ተሰላፊ ምራቁን ዋጠ፡፡ በትልቁ ጭልፋ አንድ ትልቅ የተቀቀለ ድንች አወጡ፡፡ የመጀመርያው ተሰላፊ የእጁን መዳፎች አፍተለተለ፡፡ ሴትዮዋ ጭልፋውን ገፋ አደረጉለት፡፡ በሁለት እጆቹ መዳፎች ያንን ዱባ የሚያህል ትኩስ የሚያልበው ድንች ተቀበለ፡፡
ጮኸ ሰልፈኛው፡፡ አቃጠለው፡፡ እፉፉፉፉ እያለ ወደ ኋላው ዞረና ለቀጣዩ ሰው ሰጠው፡፡ ከዚያም እፎይ አለ፡፡ ሁለተኛውም ሰው እንደተቀበለ መዳፎቹን ትኩሳቱ ላጠው፡፡ ፊቱ በርበሬ መሰለና ዘወር ብሎ ለሦስተኛው ሰልፈኛ አቀበለው፡፡ መጀመርያ ተደስቶ የነበረው ሦስተኛው ሰልፈኛ የድንቹን እሳት ሲቀምስ ጊዜ ዓይኑ እንባ አቀረረና እርሱም በተራው ለአራተኛው አስተላልፎ እፎይ አለ፡፡
እንዲህ ሰልፈኛው ሁሉ እየተቀባበለ፤ ድንቹን ለማብረድ አንዱም ሰው ሳይጥር፤ ሁሉም ለሌላው እያቀበለ ድንቹ ሄደ፡፡ ሄዶ ሄዶም ከመጀመርያው ሰልፈኛ እንደገና ደረሰ፡፡
የድንቹን ትኩሳት ለማብረድ የመጀመርያው ሰልፈኛ ጥረት አድርጎ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ በመጠኑ ችግሩን ይቀንሰው ነበር፡፡ ነገር ግን እንዳለ ምንም ነገር ሳያደርግ ነው ለቀጣዩ ሰው ያስተላለፈው፡፡ የርሱ ዓላማ ችግሩን ከእርሱ ማሸሽ እንጂ ለችግሩ መፈታት አስተዋጽዖ ማድረግ አልነበረም፡፡ ቃጠሎውን ከመቀነስ ወይንም ከማጥፋት ይልቅ የሚቃጠልለት ሌላ ሰው ፍለጋ ነበር ወደ ኋላ የዞረው፡፡
ሁሉም ሰልፈኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ሌላ በእነርሱ ምትክ የሚቃጠልና ችግሩን ከእነርሱ ላይ የሚወስድላቸው ሰው ነበር የሚፈልጉት፡፡ ማንም ችግሩን መፍታት አለብን፤ እንችላለንም ብሎ ድንቹን ወደ ውኃ ወስጥ ለመክተት፤ በልበሱ ይዞ ለማብረድ ወይን ሌላ አንዳች መፍትሔ ለመስጠት አልጣረም፡፡
ይህ የትኩስ ድንች አስተሳሰብ ይባላል፡፡
እስኪ የተሳተፋችሁባቸውን ስብሰባዎች አስታውሱ፡፡ በዚያ ስብሰባ መጨረሻ አንዳች ነገር የሚከውን ኮሚቴ ይቋቋም ይባላል፡፡ ያን ጊዜ ተሰብሳቢው ሁሉ እጁን ያወጣል፡፡ እጁ የሚያወጣው እኔ እሠራለሁ ለማለት አይደለም፡፡ አንድ ሌላ ድንቹን የሚወስድ ሰው ለመምረጥ ነው፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም ያንን ሰው የምንጠቁመው ይሠራዋል ይችለዋል ብለን ሳይሆን ድንቹን ከኛ ወደ ሌላ ለማስተላለፍ ስንል ብቻ ነው፡፡
ይህ መሆኑን የምናውቀው ደግሞ የመረጥናቸው ሰዎች ተራራ ይውጡ ገደል ይውረዱ የሚጠይቃቸው ቀርቶ የሚያስባቸው ባለመኖሩ ነው፡፡ ኮሚቴው መቋቋሙን እንኳን የሚያስታውስ አይገኝም፡፡ የሰጠናቸው ኃላፊነት እንዲሳካ ምንም አስተዋጽዖ አናደርግም፡፡ በመጨረሻው ቀን ግን ለወቀሳ እንሰባሰባለን፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ገንዘብ ከእኛው እንዲያሰባስቡ እኛው ሰዎችን እንመርጥና እየተመረጡት ሰዎች ገንዘቡን ለመሰብሰብ ሲመጡ ግን እኛው ለመስጠት እናስቸግራለን፡፡ የማንሰጣቸው ከሆነ ለምን ሰብስቡ ብለን መረጥናቸው? ያን ጊዜ የመረጥናቸው ገንዘቡን እንዲሰበስቡ ሳይሆን ትኩሱን ድንች ከኛ ወደነ እርሱ ለማዞር ነበር ማለት ነው፡፡
በየቢሮው ውሳኔ ለመወሰን የተቸገርነውኮ በትኩስ ድንች አስተሳሰብ ምክንያት ነው፡፡ ወሳኝ ተደርገው በየቢሮው የሚቀመጡ አካላት ትልቁ ጥያቄያቸው ችግሩ እንዴት ይፈታል? አይደለም፡፡ አንድ ነገር ቢሆን ማን ይጠየቃል? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው መፍትሔ ደብዳቤውን እየመሩ ማሻገር ብቻ ነው፡፡ እንደ ትኩሱ ድንች፡፡
አንዳንድ በስብሰባ የሚወሰኑ ነገሮችን ስታዩኮ አሁን ለዚህ ኃላፊው አንሶ ነው ይህ ሁሉ ሰው የሚሰበሰበው? ትላላችሁ፡፡ ዋናው ምክንያት የትኩሱ ድንች ጥያቄ ነው፡፡ ትኩሱን ድንች ብቻውን ከሚይዘው የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች ሁሉ በመቃጠሉ እንዲተባበሩት ለማድረግ፡፡ እነ እገሌም አሉበት፤ እነ እገሌም ነበሩበት ለማለት፡፡
አንድ ጊዜ በእኛ ሠፈር የሚያልፍ ትልቅ የውኃ ማስተላለፊያ ፈነዳ እና ስንት ወጭ የወጣበት ንጹሕ ውኃ ሠፈሩን አጥለቀለቀው፡፡ አንድ ኅሊና ያለው ሰው አይቶ ማለፍ ከበደውና መሣርያውን አምጥቶ በጭቃው ውስጥ እየተንቦራጨቀ ሠራው፡፡ ውኃው ቆመ፡፡ የመንግሥት ወጭም ዳነ፡፡ ሠፈሩም ከውኃ እጥረት ተላቀቀ፡፡
ከስንት ቀናት በኋላ ሰው መከሰሱን ሰማሁ፡፡ ምነው መሸለም ሲገባው? ብዬ ስጠይቅ «አይ ለውኃ እና ፍሳሽ ማመልከት ነበረበት እንጂ መሥራት አልነበረበትም» ተብሎ ነው አሉ፡፡ አይ የትኩስ ድንች አስተሳሰብ፡፡ ይህ ሰው «ሕግ» ጥሷል ቢባል እንኳን መጀመርያ የሠራበት ምክንያት፣ ያኘው የግል ጥቅም ካለ፣ ያደረገው አስተዋጽዖ እና ያዳነው የመንግሥት እና የሕዝብ ገንዘብ፣ እንዲሁም የፈታው ችግር መታየት አልነበረበትም፡፡
ይህ «ማመልከቻ» የሚባለው አሠራር ራሱ የትኩስ ድንች አስተሳሰብ ውጤት ሳይሆን አይቀርም፡፡ በቀላሉ የሚፈታውን ችግር ሁሉ ለሚመለከተው አካል ማመልከት እንደ ትልቅ ተግባር ይቆጠራል፡፡ ለምን አታመለክትም? ነው ሰው ሁሉ የሚለው፡፡ አጥሩ ሲፈርስ ሙያውን ተጠቅሞ መሥራት የሚችለው ሁሉ ለሚመለከተው አካል በማመልከት ግዴታውን የተወጣ ይመስለዋል፡፡ ችግሩን ፈትቼዋለሁ ወይ? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡፡ ችግሩን አስተላልፌዋለሁ ወይ? የሚል እንጂ፡፡
የትኩስ ድንች አስተሳሰብ «የሆኑ ሰዎች» የሚባሉ የማይታወቁ አካላትን ፈጥሯል፡፡ ይህንን ነገር መሥራት ያለባቸው፤ ይህንን ችግር መፍታት ያለባቸው፣ ቢሮውን ማስተካከል ያለባቸው፣ ለኢትዮጵያ መታገል ያለባቸው፣ የየቤተ እምነቱን ችግር መፍታት ያለባቸው፣ የኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ያለባቸው፣ መብታችንን ማስጠበቅ ያለባቸው፣ ለነጻነታችን መሞት ያለባቸው፣ የትምህርትን ጥራት ማምጣት ያለባቸው፣ «የሆኑ ሰዎች» አሉ፡፡
እኛ አይደለንም፤ እኛንም አይመለከተንም፤ እኛ አንችልም፤ እኛም አይፈቀድልንም፡፡ ነገር ግን የሚችሉ፣ የሚፈቀድላቸው፣ የሚመለከታቸውም «የሆኑ ሰዎች» አሉ፡፡ የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲ ያውም ተምኔት ሆነዋል፡፡
በመካከለኛው የሀገራችን የታሪክ ዘመን የተፈጠረው መመሰቃቀል ብዙውን ሰው ተስፋ አስቆርጦት ነበር፡፡ ችግሩ መቼ ይቃለላል? ማንስ ያቃልለዋል? ለሚሉት ጥያቄዎች መልሱን ማግኘት ከባድ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህ የተነሣ አንዳች መፍትሔ ያለው፣ ሁሉን የሚችል አንድ ሰው አለ ተባለ፡፡ ቴዎድሮስ የሚባል፡፡ በየመጻሕፍቱ ይህ ችግር ቴዎድሮስ የተባለ ንጉሥ ሲነግሥ ይስተካከላል፡፡ የአንድ ላም ወተት፣ አንድ ዘለላ እሸት አገር ይመግባል ተባለ፡፡
ቴዎድሮስን ለማምጣት ወይንም ራስን ቴዎድሮስ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ «አንዳች የሆነ» ቴዎድሮስ የተባለ ትኩሱን ድንች የምናቀብለው ሰው ይመጣል፣ እስከዚያ ዝም ብላችሁ ጠብቁ ተባለ፡፡ ሁሉም በየዘመኑ ትኩሱን ድንች ለማያውቀው ለቴዎድሮስ እያቀበለ አለፈ፡፡ ማንም ድንቹን ለማብረድ መጣር አልፈለገም፡፡ ይሄው ቴዎድሮስም ሳይመጣ፣ ምስቅልቅሉም ሳይለቅቀን እዚህ ደረስን፡፡ ትኩሱ ድንችም እየተሸጋገረ እኛ ዘንድ ደረሰ፡፡
ይህ እና ሲፈጸም እገሌ ለምን ዝም አለ? ይህ ነገር ሲደረግ እነ እገሌ የት ነበሩ? ይህኮ የነ እገሌ ሥራ ነው፡፡ እነ እገሌ ይህንን ቢያደርጉ መልካም ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እነ እገሌ ምን ይላሉ? ትኩሱ ድንች ይሄዳል፣ ይሄዳል፣ ይሄዳል፡፡ የሚያበርደው ግን የለም፡፡
አንዳንዴም ድንቹ ወደ ፊት እና ወደ ላይ ብቻ አይደለም የሚተላለፈው፡፡ ወደ ኋላም ይሄዳል፡፡ አሁን ለተፈጠረው ችግር ወይንም ፈተና ተጠያቂዎቹን ፍለጋ ወደ ኋላ ብቻ የመጓዝ አባዜ አለ፡፡ ከኛ በፊት ለነበረው ትውልድ ትኩሱን ድንች ማቀበል፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ፣ ይህ ቢደረግ ኖሮ፣ ቢፈጸም ኖሮ እያሉ አያትን እየወቀሱ እና እየኮነኑ ዐጽማቸው ድንቹን እንዲሸከም ለማድረግ እየሞከርን ነው፡፡
በየጉባኤያቱ፣ ዐውደ ጥናቱ፣ ሴሚናሩ እና መግለጫዎቹ ለችግሩ እኛ ምን መፍትሔ እንሰጣለን? ብሎ ከመወያየት ይልቅ ለአባቶቻችን ዐጽም ትኩሱን ድንች ለማሸከም ጥረት ሲደረግባቸው ይታያል፡፡ ግን ድንቹን አላበረደውም፡፡
ድንቹ ከልጅ ወደ አያት ብቻ አይደለም፡፡ የየዘመናቱ አንዳንድ አያቶችም ቢሆኑ ትኩሱን ድንች ሁሉ ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ ነው የሚፈልጉት፡፡ «የስምንተኛውን ትውልድ» መውቀስ እና ተጠያቂ ማድረግ የችግሩ ሁሉ መፍቻ ይመስላቸዋል፡፡ ትኩሱን ድንች ለማብረድ የበኩላቸውን ከማድረግ ይልቅ ለትውልዱ አስረክበው በሰላም ማረፍ ይሻሉ፡፡
ትኩሱ ድንች ከዘመን ወደ ዘመን ብቻ አይደለም፡፡ ከብሔር ወደ ብሔር ከብሔረሰብም ወደ ብሔረሰብ ይጓዛል፡፡ እንዳንዱ ብሔረሰብ ዛሬ በእጁ ያጋጠመውን ትኩስ ድንች ለሌላው ብሔረሰብ አስረክቦ መገላገል ይፈልጋል፡፡ በየስብሰባውም ሌላውን ብሔረሰብ በመውቀስ እና በመክሰስ ድንቹን በተግባር ሳይሆን በኅሊናው ያበርደዋል፡፡
ድንቹን መቀባበሉ ሁላችንም ይልጠን ይሆናል እንጂ አያበርደውም፡፡ ከኛ ወደ ሌላው ስናስተላልፈው እኛን ባለማቃጠሉ የበረደ ቢመስለንም ሌላውን ግን በማቃጠል ላይ ነው፡፡ ለዚህም ነው ተመልሶ ሳይበርድ እኛ የሚደርሰው፡፡

46 comments:

 1. the best article!!! gin.....sirat metebekin tewu eyalk new? besirat mehiedu makabedna tikusun dinch masalef kehoneko hulum neger sirat alba lihon new memher!!! geta yirdah

  ReplyDelete
 2. ድንቹን መቀባበሉ ሁላችንም ይልጠን ይሆናል እንጂ አያበርደውም

  From Awassa

  ReplyDelete
 3. its wonderful........yahunum tewled degnechun lekedmow meleso bemestet sebebegha honual....THANKS DANI.

  ReplyDelete
 4. You are right, Dn Daniel. However educated we are, however greatly posted we may be, however better we think we do things than others, we still expect someone else to solve our problems.

  Your writing reminded me of a saying: Being born an eagle doesn't do any thing if the eagle is brought up among the ducks.

  What is our difference, then, from any layman if we push difficulties to others and if we pull benefits from them to us?

  Are we, being born eagles, still living among the ducks?

  ReplyDelete
 5. ድንቹን መቀባበሉ ሁላችንም ይልጠን ይሆናል እንጂ አያበርደውም፡፡

  ReplyDelete
 6. That is right; this opinion was addressed at the following youtube link as well:

  http://www.youtube.com/watch?v=6-jAZfXevRY

  ReplyDelete
 7. It is a good explanation! Thanks for this but I see a comedy or drama......that I do not remember the owner which is entitled "ትኩስ ድንች" with the same concept. So please site as initial reference if you watch or hear it.

  ReplyDelete
 8. egziabher yistilin betam enameseginalen!
  Tsega
  Bahir Dar

  ReplyDelete
 9. Dn. Daniel, Thank you. It remembered me this comedy.

  http://www.youtube.com/watch?v=6-jAZfXevRY

  ReplyDelete
 10. እ ን ዲ ያ ው መ ላ ማ ለ ት እ ኛ ኢ ት ዮ ጵ ያ ው ያ ኖ ች ያ ቅ ተ ን ይ ሆ ን ወ ይ? እ ን ዴ ት ስ ል ን ደ ፍ ረ ው እ ን ች ላ ለ ን? አ ስ ተ ያ የ ት ህ ብ ዙ አ ስ ተ ም ሮ ኛ ል ። ይ ህ ን ያ ነ በ ቡ ት ሁ ሉ በ አ እ ም ሮ አ ቸ ው ው ስ ጥ እ ን ዲ ያ ብ ላ ሉ ት በ መ ድ ሃ ኒ ዓ ለ ም እ ማ ለ ዳ ለ ሁ ። ቃ ለ ሕ ይ ወ ት ያ ሰ ማ ል ኝ

  መ አ
  ከ ሃገረ ማርያም

  ReplyDelete
 11. Amazing view !!! keep it up, may go bless you.

  ReplyDelete
 12. ..........I like the way, how you present. It is a wondering observation.

  thanks and i will not be "Dinech Akebayi" i will be "Dinech Aberaje" Thanks, Enewnegn Yared, AA

  ReplyDelete
 13. Wow. That is exactly what is going on everywhere. I will try to do my best to be part of solution maker. Amlak Yibarkih.

  ReplyDelete
 14. ርብቃ ከጀርመንJune 14, 2011 at 7:04 PM

  ድንቅ ብለሀል ዲያቆን ዳንኤል ሁላችንም መፍትሄውን ሳይሆን ችግሩን ብቻ እያናፈስን ተቸግረናል ጽሁፍህ ጥሩተግጻጽ ሆኖን ድንቹንወደሌላሰው መጣል(ከመግፋት) እንድታቀብና በየተቀመጥንበት የሃላፊነት ወንበርላይ የሚገባንን ስራ ሰርተን ለሀገራችንም ሆነለወገናችን ትኩሱን ድንች ላለማቀበል የበቃንያርገን!

  ReplyDelete
 15. ዛሬ ዛሬ ሁሉም ሰው ከላይ የሚመጣለትን ትዕዛዝ ያለምንም ማመዛዘን ማብላላት እና መረዳት እንዳለ ለማውረድ ይሞክራል እንጂ በተሰጠው አዕምሮ የነገሩን ጥቅም እና ጉዳት ለመረዳት አይሞክርም። በመሆኑም ጉዳዩን በተሻለ ሁኔታ አዳብሮ ለተጠቃሚው ማድረስ የሚታሰብ አይደለም። ስለዚህም ነው ከቀበሌዎቻችን አስተዳደሮች የምንሰማቸው ቃላቶች እና ዐረፍተ ነገሮች ሳይቀሩ ማታ በቴሌቪዥን በፓርላማ ላይ ሲተላለፉ የሰማናቸው ሆነው የምናገኛቸው።

  በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ በኢትዮጵያና በኤርትራ የድንበር ጉዳይ ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ስለጉዳዩ ሲያብራሩ የፍርድ ሂደት አፈጻጸሙ ሰጥቶ በመቀበል ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ገለጹ።ታዲያ በቀበሌያችን ስብሰባ ላይ አንዱ ነዋሪ እኛ ባድመን ከሰጠን የምንቀበለው ምንድነው? ብለው ቢጠይቁ የቀበሌው ሊቀመንበር የሰጠው መልስ ሰጥቶ መቀበል ማለት ሰጥቶ መቀበል ማለት ነው ሌላ ታሪክ የለውም ብሎ መለሰለት። አንዳንዴም ትኩስ ድንቹ የመጨረሻው ተዋረድ ላይ የወድቅ እና ወደ ላይ መመለሻ የለውም እኛስ ለማን እንስጠው ነው ያለው ከሜዲያኑ?

  ReplyDelete
 16. Dear Dany,

  It is interesting narration. We should start to act responsibly.

  ReplyDelete
 17. ßetam ßetam ßetam Ejig Adregei Ameseginalehu Dani.
  Ante Liji Gin Atimotim ßeka Yehone Hayl Ale ßewustih.
  Edmeh Yirzemilin, lela minim yemilew yelegnim!
  AGE

  ReplyDelete
 18. WEy Eyita... Dani I like this...

  ReplyDelete
 19. we need to awake,
  I agree if this"tikus dinich" theory is practiced for good things like appreciating those people who do best and learn from them,pass on it to the next generation,individuals,family,friends etc.-encourage people who works and try to be with them.

  on the other hand do not try to pass a problem to
  non existent-"ekele" ,we need to try it first,then pass it on to those people who could thinking carefully. Do not pass it just to get rid of the problem.

  By the way whatever good or bad we do, it will bounce to us again so be careful on throwing bad stones up higher but throw light ball on people.

  About election whenever we elect, I think we are promising to help those people.Do not leave them in the alone.Endurance.

  And also,we need to think teamwork and put your feet in the other shoes-say to yourself what would I do if I were him/her/them.

  I think all the above works to the moral of people too.
  Sharing

  ReplyDelete
 20. ዲ ዳኒ አስተዋይ አእምሮውን የሰጠህ ጌታ ዪመስገን::ለእኛም አስተዋይ አእምሮ ያድለን::የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን::

  ReplyDelete
 21. It is the true and it happens at most of us. thank you dn.danel for giving thislesson. we need to carry and perform our responsibility where we are appointed. then we will get mental satisfaction as well as praise.

  ReplyDelete
 22. that is v good view D Danny;may God help us to focus on our problem & solve it, instead of share it to another person.

  ReplyDelete
 23. typical behavior of our system

  ReplyDelete
 24. Dani..egizer yistilign. Tkikil bilehal....tikus dinich bikebabelut waga yelewum....endet enabiridewu bilo masebna erimija mewused kehulacinim yitebekital.

  ReplyDelete
 25. it is amazing wow God bless you

  ReplyDelete
 26. well done keep it up dani
  we should promise for our selves not do this vicious circle process flow.can BPR solve this?

  ReplyDelete
 27. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲን ዳንኤል
  ይህ ነገር አሁን ለአገልግልሎት ባለህበት ቦታ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብየ አስባለሁ ማለትም
  ፩ ሀረር የሚናፈሰው የተሃድሶ ወሬ ምእመኑ አንዱ ለሌላው እያወራ ለመፈትሔው ደንታ የሌለው እየሆነ ነው በተለይ ማ.ቅዱሳን የራሱ ጳጳስ ልሾም ነው
  ፪ በግቢ ጉባኤ ያለን ተማሪዎች እገሌ እንድህ አደረገ እገሌ ነው እንድህ ማድረግ ያለበት እያልን ነው በጥላቻ መንፈስ እየተሞላን ነው
  እና ዲያቆን ለነዚህ መልስ የሚሆን ርእስ መርጠህ በምገባን መልኩ እንድታፅናናን ና እንድትመክረን እውነቱንም ብትነግረን መልካም ነው
  እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን

  ReplyDelete
 28. በዚ በክረምት ትኩስ ድንች እያላችሁ “የሚበላውን ትኩስ ድንች ” አሳመራችሁኝ ፡፡ ትኩስ ድንች በተልባ ኡኡኡ…… የአለቆች ትኩስ ድንች ግን መላ ቢገኝለት ጥሩ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 29. wud dn daniel it is good idea but our leaders,medias and newspaper(governmental)are not volunter to adress such ideas that bring change simply they speak aboroad's ideology to extend their reign and their carer(those who r employed in governmental medias)

  ReplyDelete
 30. hi dani,
  i love this article as always. In one of my comments on the other posts, i suggested that it would be nicer if u focus more on this kind of issues. Issues that changes the attitude of our ppl and I'm happy to see that u are working hard along this line. I believe that your insightful critics will definitely bring a change in attitude in our society. Keep it moving dani, God bless you and long live.

  yezewotir adinakih
  Wassihun, Greensboro, USA.

  ReplyDelete
 31. A jaw-dropping story so to speak!! As the writer argues, I am always yearn to know why we tend to forward issues to others where as we can cool it off right away? Why we always make a mountain out of a mole-hill? why we often sugar the pill? It always drove me up the wall! However, now a days, the wolves are getting the reward than the sheep's. No matter the case, we Ethiopians-as an individual, should start working to injure no man, but to bless all mankind!!!! LET US HAVE A POSITIVE MENTAL ATTITUDE!!!

  Tena Tabia folk (Kebele 03)
  Bahirdar

  ReplyDelete
 32. የትኩስ ድንች አስተሳሰብ «የሆኑ ሰዎች» የሚባሉ የማይታወቁ አካላትን ፈጥሯል፡፡ ይህንን ነገር መሥራት ያለባቸው፤ ይህንን ችግር መፍታት ያለባቸው፣ ቢሮውን ማስተካከል ያለባቸው፣ ለኢትዮጵያ መታገል ያለባቸው፣ ..................የየቤተ እምነቱን ችግር መፍታት ያለባቸው፣ .............የኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ያለባቸው፣ መብታችንን ማስጠበቅ ያለባቸው፣ ለነጻነታችን መሞት ያለባቸው፣ የትምህርትን ጥራት ማምጣት ያለባቸው፣ «የሆኑ ሰዎች» አሉ፡፡

  እስኪ ሁላችንም የራሳችን ሀላፊነት አለብን፡፡ ስለዚህ እስኪ እንነሳ፤ "ከእኛ የሚጠበቀው ምንድን ነው?" ብለን ህሊናችንን እንጠይቅ፡፡ ምንም ማድረግ ባንችል እንኳ መጸለይ አያቅተንም እና እስኪ እንነሳና ለሃይማኖታችን ልዩ ጸሎት እናድርግ፡፡

  በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉም ለሀገራችን እና ልወገናችን የሚሆን ነገር ሰርተን እንለፍ፡፡

  TESFAHUN, PHOENIX, ARIZONA

  ReplyDelete
 33. Dn.Daniel,
  I am confused on this two paragraphs:
  በመካከለኛው የሀገራችን የታሪክ ዘመን የተፈጠረው መመሰቃቀል ብዙውን ሰው ተስፋ አስቆርጦት ነበር፡፡ ችግሩ መቼ ይቃለላል? ማንስ ያቃልለዋል? ለሚሉት ጥያቄዎች መልሱን ማግኘት ከባድ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህ የተነሣ አንዳች መፍትሔ ያለው፣ ሁሉን የሚችል አንድ ሰው አለ ተባለ፡፡ ቴዎድሮስ የሚባል፡፡ በየመጻሕፍቱ ይህ ችግር ቴዎድሮስ የተባለ ንጉሥ ሲነግሥ ይስተካከላል፡፡ የአንድ ላም ወተት፣ አንድ ዘለላ እሸት አገር ይመግባል ተባለ፡፡
  ቴዎድሮስን ለማምጣት ወይንም ራስን ቴዎድሮስ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ «አንዳች የሆነ» ቴዎድሮስ የተባለ ትኩሱን ድንች የምናቀብለው ሰው ይመጣል፣ እስከዚያ ዝም ብላችሁ ጠብቁ ተባለ፡፡ ሁሉም በየዘመኑ ትኩሱን ድንች ለማያውቀው ለቴዎድሮስ እያቀበለ አለፈ፡፡ ማንም ድንቹን ለማብረድ መጣር አልፈለገም፡፡ ይሄው ቴዎድሮስም ሳይመጣ፣ ምስቅልቅሉም ሳይለቅቀን እዚህ ደረስን፡፡ ትኩሱ ድንችም እየተሸጋገረ እኛ ዘንድ ደረሰ፡፡
  Are you telling us we don't have such prophecy in our books?

  ReplyDelete
 34. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲን ዳንኤል
  በየጉባኤያቱ፣ ዐውደ ጥናቱ፣ ሴሚናሩ እና መግለጫዎቹ ለችግሩ እኛ ምን መፍትሔ እንሰጣለን? ብሎ ከመወያየት ይልቅ ለአባቶቻችን ዐጽም ትኩሱን ድንች ለማሸከም ጥረት ሲደረግባቸው ይታያል፡፡ ያ ግን ድንቹን አላበረደውም፡፡
  ድንቹ ከልጅ ወደ አያት ብቻ አይደለም፡፡ የየዘመናቱ አንዳንድ አያቶችም ቢሆኑ ትኩሱን ድንች ሁሉ ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ ነው የሚፈልጉት፡፡ «የስምንተኛውን ሺ ትውልድ» መውቀስ እና ተጠያቂ ማድረግ የችግሩ ሁሉ መፍቻ ይመስላቸዋል፡፡ ትኩሱን ድንች ለማብረድ የበኩላቸውን ከማድረግ ይልቅ ለትውልዱ አስረክበው በሰላም ማረፍ ይሻሉ፡፡
  ትኩሱ ድንች ከዘመን ወደ ዘመን ብቻ አይደለም፡፡ ከብሔር ወደ ብሔር ከብሔረሰብም ወደ ብሔረሰብ ይጓዛል፡፡ እንዳንዱ ብሔረሰብ ዛሬ በእጁ ያጋጠመውን ትኩስ ድንች ለሌላው ብሔረሰብ አስረክቦ መገላገል ይፈልጋል፡፡ በየስብሰባውም ሌላውን ብሔረሰብ በመውቀስ እና በመክሰስ ድንቹን በተግባር ሳይሆን በኅሊናው ያበርደዋል፡፡
  ድንቹን መቀባበሉ ሁላችንም ይልጠን ይሆናል እንጂ አያበርደውም፡፡ ከኛ ወደ ሌላው ስናስተላልፈው እኛን ባለማቃጠሉ የበረደ ቢመስለንም ሌላውን ግን በማቃጠል ላይ ነው፡፡ ለዚህም ነው ተመልሶ ሳይበርድ እኛ ጋ የሚደርሰው፡፡
  የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን::

  ReplyDelete
 35. Dani what can i say about this article God bless you ya this is the problem why we(Ethiopian) stay here every activity needs ቢሮክራሲ and no body is voluntary to take a risk and responsibility for any thing you gave us a good story about the man who fix the pipe አንድ ጊዜ በእኛ ሠፈር የሚያልፍ ትልቅ የውኃ ማስተላለፊያ ፈነዳ እና ስንት ወጭ የወጣበት ንጹሕ ውኃ ሠፈሩን አጥለቀለቀው፡፡ አንድ ኅሊና ያለው ሰው አይቶ ማለፍ ከበደውና መሣርያውን አምጥቶ በጭቃው ውስጥ እየተንቦራጨቀ ሠራው፡፡ ውኃው ቆመ፡፡ የመንግሥት ወጭም ዳነ፡፡ ሠፈሩም ከውኃ እጥረት ተላቀቀ፡፡
  ከስንት ቀናት በኋላ ያ ሰው መከሰሱን ሰማሁ፡፡ ምነው መሸለም ሲገባው? ብዬ ስጠይቅ «አይ ለውኃ እና ፍሳሽ ማመልከት ነበረበት እንጂ መሥራት አልነበረበትም» ተብሎ ነው አሉ፡፡ this thing is enough to show who we are surrounded by a lot of ትኩሱ ድንች idea what I can say Dani God will forgive US God change our idea of thing of ትኩሱ ድንች

  BirukZ(GebiGebereale)

  ReplyDelete
 36. ዳኒ
  በርታ ....አትጠራጠር ቀስ በቀስ እየተለወጥን ነው :: የምታነሳቸው ህሳቦች ለስጋዊም ለመንፈሳዊ ህይወትም ጣኡም ምግብ ናቸው::

  እግዚአብሄር እውቀትን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 37. Dani excellent lesson. Only to comment: the water pipe maintainane done by a man is from his genuine mind but he did unauthorized. You know the problem? The resposible body has to do with accountability by protecting cross contamination to the next people getting the suppy. There are techniques to apply. Otherwise as a lesson you are right we have so many that type we pass on responsibility.

  ReplyDelete
 38. ይሄው ቴዎድሮስም ሳይመጣ፣ ምስቅልቅሉም ሳይለቅቀን እዚህ ደረስን፡፡

  ReplyDelete
 39. It is really an interseting issue that u raise Dani. U know what i remeber a proverb saying that " a picture is worth than 1000 words". and the lesson "tikus dinech" can realy depicts our problem clearly. most of us are suffering with this problem of passing responsibility rather than attempting to eradicate it.Thxx DANI, cos u depict our weakness in a clear fashion.

  May G od bless uuuuuuu

  ReplyDelete
 40. ይሄው ቴዎድሮስም ሳይመጣ፣ ምስቅልቅሉም ሳይለቅቀን እዚህ ደረስን፡፡
  I guess they were afraid the so Called Tewodrose and Jailed Tewodrose Kassahun and Surounded and beat monks in Yerer !!

  so funny.

  ReplyDelete
 41. I saw the comedy version of this article. A nice one. Keep it up, one more thing Please give credit to the Comedians.

  Thanks

  ReplyDelete
 42. ይሄው ቴዎድሮስም ሳይመጣ፣ ምስቅልቅሉም ሳይለቅቀን እዚህ ደረስን፡፡ ትኩሱ ድንችም እየተሸጋገረ እኛ ዘንድ ደረሰ፡፡

  አረ ቀስ ልጅ ዳንኤል ፡፡ ደግሞ ብለህ ብለህ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ጥልቅ ምስጢር-ቴዎድሮስ- የጽሑፍህ ቧልት ማሳመሪያ አደረግከው? ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው አሉ፡፡ ወዳጄ ልቤ ይሄ የሚገለጸው በዕውቀት ንባብ ሳይሆን በሱባዔ ነው፡፡ ይሄማ የከበረ ትውፊታችን ነው፡፡ እንደሚፈጸም የማንጠረጥረው፡፡ ደግሞም ይህንን ማረጋገጥ ከፈለግክ እንደቤተክርስቲያን ልጅነትህ ጸሎት አድርግበት-ሱባዔ ያዝበት-አባቶችን ጠይቅበት፡፡ ቴዎድሮስ እኮ በእንዳንተ ዓይነቱ የፖለቲካ ዝባዝንኬ ጽሑፎች የሚዳሰስ የዓለም መሪ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የሚቀባ ቅዱስ ንጉሥ ነው፡፡ በአይነ ሥጋ ባታየውም በመንፈስ ሊያየኝ ይችላል ብለህ ተጠንቀቅ፡፡ ምነው ጃል፡፡ ትውፊታችንን ለማንቋሸሹ መናፍቃን መች አነሱንና ነው

  ReplyDelete
 43. The theory of "yetekekele dinch" is more practiced in Europe and America, especially with their freedom of everything and democracy, than in Ethiopia, a country: without democracy and freedom,formed by around eighty ethnics, cultures, interests.

  In America, for instance, everybody has a bill to be paid at the end of the month. Nobody wants to accept anybody's dinch. You are not allowed to do somebody's job and pass your yetekekele dinch to others too. All are responsible for his/her jobs. If that plumber were in USA, he would have faced the same situation as he had in Ethiopia. He supposed to call and report for the right authority (that is his responsibility here) to be fixed by them.

  The thing is we all have to be accountable for our responsibilities. We all have to respect the law and rules of our surroundings and do our jobs. Eventually everything will be fine, if we all do abide by that. Hierarchy is a must.

  Of course, everything have to be conducted by moderation. At the same time we have to take our people cultures and assets in to consideration before we conclude Ethiopians are the worst in everything. All foreigners are always telling us the same single story of our famine, poverty, and others, which aren't encouraging and insulting words. I think that is enough for us, no more insult is appreciated.

  I don't deny some facts that are argued in this article, but, we also have to write and report staffs without exaggeration and as if the problem is just ours. A lot of comments show that they understand the article the way we are the only people and country with such problems.

  As we all know, we have so many good assets to be told to the world. However, the foreign medias always report a single story. Even sometimes they do show us our own films which were recorded long time ago to say something new about Ethiopia in their news.

  Adoration is not always good. We need to comment something from different perspectives so that Daniel can write more and more by considering so many elements and ideas.

  Some comments in here even are like passing the dinch to Daniel such as "Please Daniel say something about this and that".

  ReplyDelete
 44. በእውነት ገጥሞኛል፡፡ ድንቅ ጽሑፍ፡፡

  ReplyDelete