Friday, June 10, 2011

ድመት እና የነብር አጎት


ኦሮምኛ አንድ አባባል አለ፡፡ ድመትን ለምን ያለ ሥራ በየቦታው ጎርደድ ጎርደድ ትያለሽ ቢሏት አጎቴ ጫካ ስላለ ነው አለች ይባላል፡፡ አጎቴ ያለችው ነብርን እኮ ነው፡፡ ድመቷ የነብሩን ያህል ሥልጣን፣ ጀግንነት፣ ዐቅም እና ተፈሪነት የላትም፡፡ ነገር ግን አጎቷ ጫካ ስላለ ብቻ ይኼው በኩራት በየመንደሩ ጎርደድ ጎርደድ ትላለች፡፡ የምጠራጠረው ግን እርሷ አጎቷን የምታውቀውን እና የምትኮራበትን ያህል አጎቷ እርሷን ማወቁን ነው፡፡
ጎበዝ ዛሬ በሀገራችን ካሉት ችግሮች አንዱ ጫካ ባለ አጎት እየተመኩ መንጎራደድ ነው፡፡
የእነዚህ ድመቶች ጠባይ በቀላሉ የሚገለጥ ነው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን በሠሩት ሥራ፣ በራሳቸው ማንነት እና ደረጃ ወይንም በተማሩት ትምህርት እና በያዙት ክሂሎት አይመኩም፡፡ የሚመኩት አባቴ ሀብታም ነው፤ እናቴ አሜሪካ ናት፤ ወንድሜ ጀርመን ነው፤ አጎቴ እንግሊዝ አክስቴ ጃፓን ናት እያሉ ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፕሬዳንት በመሆናቸው ከሚኮሩት ኩራት ይልቅ እነዚህ ወገኖቻችን ወደ ኦባማ ሀገር በሄዱ ዘመዶቻቸው የሚኮሩት ኩራት ይበልጣል፡፡
ዛሬ ዛሬ «ቀዩ፣ ጥቁሩ፣ የቀይ ዳማው፣ ጠይሙ፣ ጠይም ዓሣ መሳዩ፣ አጭሩ፣ ረዥሙ፣ ወፍራሙ ቀጭኑ» እየተባለ ሰውን መግለጥ ቀርቷል፡፡
እገሌን ታውቀዋለህ?
የቱ?
እኅቱ አሜሪካ ያለችው
እገሊትን ታውቃታለህ?
የቷ?
እጮኛዋ ጀርመን ያለው
አቶ እገሌን ታውቃቸዋለህ?
የትኛው?
እኒያ ልጆቻቸው ዐረብ ሀገር ያሉት፡፡ ሆኗል መታወቂያው፡፡ ደግሞ እነዚህን ሰዎች ብታዩዋቸው፡፡ በአካሄድ፣ በአነጋገር፣ በሰላምታ፣ በከበሬታ፣ በአነጣጠር እና በአበጣጠር ይለዩዋችኋል፡፡ እኔ የምለው ግን ዘመዱ ውጭ ሀገር ያለ ሰው በቦሌ መንገድ ካሉት ካፍቴርያዎች ውጭ እንዳይዝናና ተገዝቷል እንዴ? እናንተ ውጭ ያላችሁትስ ብትሆኑ ገንዘብ ስትልኩ «ከቦሌ መንገድ ውጭ ከተዝናናህ ደግሜ አልክልህም» ትላላችሁ እንዴ? ወይስ ለአውሮፕላኑ ቀረብ ለማለት ነው? እዚያ መንገድ ስትገቡኮ ወሬው ሁሉ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አውስትራልያ፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ፣ ጣልያን ብቻኮ ነው፡፡ ነገሩ ካፌዎቹስ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ፣ ፍራንክፈርት፣ ዋሽንግተን፣ ዴንቨር፣ ቶሮንቶ ካፌ አይደል የሚሉት፡፡  ወደ እነዚህ ሀገር መሄድ ላቃተው ሰው መተከዣ ይሆናሉ፡፡
ሰላምታው ራሱ ይለይባችኋል፡፡ እንደምን ዋልክ እና እንደምን ሰነበትክ ከዚያ ተባርረዋል፡፡
«እሺ እኅትህ እንዴት ናት? አልጨረሰችልህም
«እሺ ወንድምሽ ፕሮሰሱ እንዴት ሆነለት
«እናትሽ ሄዱ አይደል»
«አባትሽ አለቀላቸው 

አቤት ጫካ ባሉት አጎቶቻቸው እየተመኩ ጎርደድ ጎርደድ ሲሉ ድመቶቹን ብታዩዋቸው፡፡
ይኼ በየቢሮው የሚንጎራደደው ድመትስ ቢሆን፡፡ በአንድ ወቅት ኬንያ እያለሁ የሰማሁትን ላውጋችሁማ፡፡ እዚህ ሀገር ፕሮፌሰር አሥራት ታሥረው ነበር፡፡ ታድያ አበሻ ሆዬ ኬንያ ገብቶ ጥገኝነት ሲጠይቅ «የፕሮፌሰር አሥራት ልጅ ስለሆንኩ» ነበር አሉ የሚለው፡፡ በኋላ ታድያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ሰዎች ሲቆጥሩ ለካ የፕሮፌሰር ልጅ ነን የሚሉት አንድ መቶ ሃምሳ ደርሰዋል፡፡
«እንዴ» አሉ ባለ ሥልጣናቱ ተገርመው፡፡ «በዚህ ሁኔታ ከቀጠለኮ ሁሉም የእርሳቸው ልጅ ሊሆን ነው»
እኔ አሁን አሁን እገሌ የተባለው ከፍተኛ ባለ ሥልጣን ዘመድ፣ ወንድም፣ እኅት፣ አጎት፣ ጎረቤት፣ የእኅት ባል፣ የወንድም ልጅ፣ አምቻ፣ ጓደኛ የሚባሉ ሰዎችኮ እየበዙ ነው፡፡ አንዳንዴማ በየመሥሪያ ቤታችን እና በየመንደራችን አንዳንድ ዘመዶች የተመደቡ ሁሉ ይመስላል፡፡ እንዴት አንድ ባለ ሥልጣን ይኼ ሁሉ ወንድም፣ እኅት፣ አጎት፣ አክስት፣ ልጅ፣ የልጅ ባል፣ የልጅ ሚስት፣ የእኅት ባል፣ የወንድም ሚስት፣ ይኖረዋል፡፡
ወላጆቹ ገበሬዎች ከሆኑ ሲያርሱ፣ ነጋዴዎች ከሆኑ ሲወጡ ሲወርዱ፣ የመንግሥት ሠራተኞችም ከሆኑ ከጠዋት እስከ ማታ ሥራ ሲከውኑ ነው የሚውሉት፡፡ በየቀኑ እንኳን ቢወልዱ አንድ ባለ ሥልጣን ይህ ሁሉ ዘመድ ሊኖረው አይችልም፡፡ ታድያ በየመንደሩ አጎቴ ጫካ ነው እያሉ የሚፎክሩብን ድመቶች ከየት የመጡ ናቸው? ምናልባት ነብሩ የማያውቃቸው ድመቶች ይሆኑ እንዴ?  
ኧረ ደግሞ አሉላችሁ እገሌ የተባለውን ሀብታም እናውቀዋለን፤ እገሌ የተባለውን ባለ ሥልጣን እንቀርበዋለን፡፡ ከመቅረብም አልፈን ፀዋርያነ መንበር ምዕራገ ጸሎት ነን የሚሉም በየሠፈሩ አሉላችሁ፡፡ በኛ በኩል ካልሆነ በቀር ማንኛውም ዓይነት ጸሎት ወደነዚህ ባለ ሥልጣናት አያርግላችሁም ይሏችኋል፡፡
ወሬያቸው ሁሉ እገሌ ከተባለው ባለ ሥልጣን ጋር ሪሴፕሺን ግብዣ ተገናኝተን እንዲህ እና እንዲያ ብሎኝ፡፡ እገሌ የተባለው ባለ ሥልጣን ሞባይሉ አለኝ፤ ከፈለጋችሁ እዚሁ ልደውልለት እችላለሁ፡፡ እገሌ የተባለውን የፌዴራል ፖሊስ አውቀዋለሁ፤ ከፈለግኩ ማንንም ማስቀፍደድ እችላለሁ፤ እገሌ የተባለው ባዕለ ጸጋ እኔን ሳያማክር ምንም ነገር አይሠራም፡፡ ኧረ ስንቱ፡፡
በየቡና ቤቱ፣ በየቁርጥ ቤቱ፤ በየካፍቴርያው ሳይከፍሉ የሚበሉ፣ ሲጨርሱ ሂሳብ ተከፍሏል የሚባልላቸው ወገኖቻችንን እያየን ኮ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎችኮ እገሌን እናውቀዋለን ሲሉ አንድ ቀን ሰላም ያሉት ሳይሆን እንደ ትምህርት ሚኒስቴር ለዚያ ባለ ሥልጣን ቅድመ ዕውቅና የሰጡት ነው የሚመስሉት፡፡
የሚያውቁት ባለ ሥልጣን የማያስጠናውን እነርሱ ደጅ ያስጠናሉ፤ አንዳንዶችማ እናውቀዋለን የሚሉት ባለ ሥልጣን ተቀይሮ ወይንም ለቅቆ እንኳን ባለ መስማታቸው በሞተ ከዳ ያስደገድጋሉ ፡፡ ኩራታቸው ከኩራቱ፣ ትዕቢታቸው ከትዕቢቱ፣ ጥቅማቸው ከጥቅሙ፣ ክብራቸው ከክብሩ ይበልጣል፡፡ ምነው? ብትሏቸው አጎቴ ጫካ ነው ይሏችኋል፡፡
መሬት፣ ንግድ ፈቃድ፣ የውጭ ምንዛሪ፣ ከቀረጥ ነጻ መብት፣ የትምህርት ዕድል፣ የጨረታ ዕድል፣ የሥራ ዕድል፣ የቀበሌ ቤት፣ የኪራይ ቤት ሕንፃ፣ እነዚህ ሰዎች ኪስ ነው ያለው፡፡ «በኔ ጣለው» ሲሏችሁኮ ያላቸውን ያህል በራስ መተማመን ሁሉን መስጠት ይችሉ የነበሩት ምኒሊክ እንኳን አልነበራቸውም፡፡ እልፍ ብላችሁ ሌላውን ሰው «ይህ ሰው ምን አግኝቶ ነው እንዲህ የሚተማመነው» ብላችሁ ሹክ ስትሉት እርሱም ድምፁን ቀነስ አድርጎ «አጎቱ ጫካ ነው ያለው» ይላችኋል፡፡
ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡ እንዴት አንድ አጎት እነዚህን ሁሉ ድመቶች ያፈራሉ? ፋሚሊ ፕላኒንግ የለም እንዴ?
«ኤምባሲው በእጄ ነው» የሚሉ ድመቶችስ አልገጠሟችሁም፡፡ ምናልባት እዚያ ቤት የሚሠራ አንድ ጸሐፊ፣ ጥበቃ፣ የሂሳብ ሠራተኛ ያውቁላችሁና እንደ ድመቷ መንጎራደድ ይጀምራሉ፡፡ ምናልባትም እዚያ ኤምባሲ ግብዣ ሲኖር፣ ስጦታ ሲሰጥ፣ ወይንም በሌላ ምክንያት የሚታደሉ ካናቴራዎች፣ ጃኬቶች፣ የቁልፍ መያዣዎች፣ ቦርሳዎች፣ ስክርቢቶዎች እና የማስታዎሻ ደብተሮችን ይይዛሉ፡፡
የዚያ ኤምባሲ ፎርም ከእጃቸው አይጠፋም፡፡ አንዳንዴም ባንዴራውን በሜዳልያ መልክ ደረታቸው ላይ ይተክላሉ፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ ኤምባሲው የማያውቃቸው ጉዳይ አሥፈጻሚዎች ይሆናሏ፡፡
«እዚህ ሀገር መሄድ ከፈለግሽ እገሌን አናግሪው፤ እርሱ ብዙ ነገር ያውቃል፤ ቀላል ሰው እንዳይመስላችሁ» እየተባለ ይወራላቸዋል፡፡
«የዚያ ኤምባሲ ቁልፍ በእርሱ እጅ ነው፤ ገብቶ ያስጨርስላችኋል፤ እስኪ ጠጋ ጠጋ በሉት» ይባላል፡፡ እነርሱም አነጋገራቸው ይቀየራል፡፡ ጀርመን ኤምባሲ ከሆነ አንድ ሁለት ጀርመንኛ፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ ኤምባሲ ከሆነ አንድ ሁለት እንግሊዝኛ፤ ጣልያን ከሆነ አንድ ሁለት ጣልያንኛ፣ ጣል በማድረግ የትኛውን ኤምባሲ እንደወከሉ ያመለክቷችኋል፡፡
እናንተም ጠጋ ብላችሁ ስታዋዩዋቸው «እስኪ ይሞከርልሃል፤ ብቻ አንተ አትጥፋ፤ አሁን እንኳን አምባሳደሩ የሉም፡፡ ትናንት አግኝቻቸው ለአንድ ሁለት ሳምንት የለሁም ብለውኛል» ይሏችኋል፡፡ አቤት ኩራታቸው፤ አቤት ሲንቀባረሩ፡፡ ምን ያድርጉ ጫካ ውስጥ አጎት አላቸዋ፡፡ ምናልባትም የማያወቃቸው አጎት፡፡
መረጃ አለን የሚሉት ዘመዶቻችንስ፤ እገሌን አግኚቼው እንዲህ አለኝ፡፡ እገሌ የተባለው የመረጃ ሰው ይህንን ነገረኝ፡፡ እገሌን አናግሬው አሳምኜዋለሁ½ አጥምቄ አቁርቤዋለሁ፡፡ እገሌ ከኛ ጋር ነው፤ እገሌ ደግሞ ይደግፈናል፡፡ እነ እገሌ ደግሞ እየተነጋገሩበት ነው፡፡ ሳላውቀው የሚፈጸም፣ ሳልሰማው የሚደረግ ነገር የለም ይሏችኋል፡፡ በኋላ ግን የሚሆነውም ካወቁት ውጭ፣ የሚወሰነውም ከሰሙት ሌላ ሲሆን መግቢያ ቀዳዳ ያጣሉ፡፡ እነዚህኞቹ ናቸው በፈጠራ አጎቶቻቸው እየኮሩ እንደ ድምቷ የሚንጎራደዱት፡፡
አሁን እኛ ማወቅ ያቃተን አንድ ነብር ስንት ድመት አለው? አንድ ድመትስ ስንት ነበር አለው? የሚለውን ብቻ አይደለም፡፡ እውነት ይኼ ድመት ነብር አጎት አለው? የሚለውንም ነው፡፡

33 comments:

 1. yessssssssssss........ it is real disease of we Ethiopians. we are proud of what we are not. let's know ourselves and ............

  ReplyDelete
 2. መቼም ይህንን ጽሑፍ ሳየው በጣም አዘንኩ፡፡ በአርአያ ስላሴ የተፈጠረ ሰው እንደ አምላኩ ትሁት፣ታጋሽ፣ቸር፣ደግ፣መልካም ወዘተ … መሆኑና በማህበራዊ ህይወቱ ከቅርብ ዘመድ ጀምሮ እስከ ጠቅላላው የዓለም ሕዝብ ግንኙነት ማድረጉ ጥሩ ነው፡፡ ይሁንና ሰው በልማቱም ይሁን በጥፋቱ የሚጠየቀው በግል ሥራውና ማንነቱ መሁኑን እንኳን ለሰማይ ቤት ለዚህም ዓለም ዳኞች ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በተመላለሰበት ጊዜ የአይሁድን ካህናትና መኳንንት ከሚገስጽባቸው ዋና ዋና ቃላቶች መጻሕፍት እንዲህ ይላሉ አለነበባችሁምን ነበር፡፡ እነዚህም የዘመናችን ፈሪሳውያን በሰውም በእግዚአብሔርም ተግሳፃቸው ይሄው ነው፡፡ እንኳን በውሸት ይቅርና የተባለው የነብሩ አጐትነት ትክክል ቢሆንም መጻሕፍትን ቢያዩዋቸው ኖሮ ማንም በሐብቱ፣በንብረቱ፣በስልጣኑ፣በጉልበቱ፣በዕውቀቱ፣በዘመዱ፣ በዓለም ባለሙ ማንነቱ እንዳይመካ ይመክራሉ ይገስፃሉና፡፡ ታዲያ ማን ይያቸው ወይም ያንብባቸው፡፡ ባዶነታቸው ያሳዝናል፡፡ ይህንን ስል በራሱ ጥሮ ግሮ የበላይ ቢሆን እንኳን ትዕቢትና ትዕዝዕርት ያስፈልገዋል ለማለት አይደለም፡፡ ‹‹ትዕቢት ወትዕዝዕርት ያወርዳ ለሞት ውስተ መቃብራት›› ይላልና ትዕቢት ማለት የልብ ኩራት (መነፋት) የጠጠረ ልብ ከውስጥ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእሁድ አርጋኖን ላይ ልበ ደንዳና ሰው እግዚአብሔርን ይቃወማልና እንዳሉት ዓይነት ማለት ነው፡፡ ትዕዝዕርት ማለት በአለባበስ፣በአነጋገርና በአካሄድ ቄንጠኛ መሆን ናቸው እነዚህ እንግዲህ የመጡት በራሳቸውም እያላቸውም ይሁን ሳይኖራቸው እንዲሁም በአጐታቸው ነብር በመመካት የሚንጐራደዱ ናቸው፡፡

  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 3. Andit dimet be ezih samint betekihnet mezgeb bet sitngoraded neber. Awka silk asre tawera neber.Hizbem ke Nebru gar eyawerach new ylat neber.neber endegena neber ahunm neber.wey dmetye? gobez endih ende Dani mayet malet ewnet dimetua mn yahil nebru yakatal? blo meteyek aykefam.

  ReplyDelete
 4. ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡ እንዴት አንድ አጎት እነዚህን ሁሉ ድመቶች ያፈራሉ? ፋሚሊ ፕላኒንግ የለም እንዴ?

  ReplyDelete
 5. ትውልዱ ከዘላለማዊው ይልቅ በጊዜያዊው፣ ከሰማያዊው ይልቅ በምድራዊው፣ ክብር ከሚያሰጠው ይልቅ በሚያዋርደው፣ ከመንፈሳዊው ይልቅ በሥጋዊው፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ በሰው የሚመካበት/የሚደገፍበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ እግዚአብሔር ልብ እንዲሰጠን አብዝተን የምንጮህበት ጊዜ አሁን ይመስላል፤ እስኪ ድምጽ አሰምተን መጮኻችን ሌላውንም እንዳረብሽ ቢያንስ የዝምታ ጩኸት እንጩኽ፤ በዝምታ ውስጥ የሚሰማ እግዚአብሔር መልስ አለውና፡፡

  መጣዓለም አማረ

  ReplyDelete
 6. ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ;Real This is Truth Our Betekehnet Know.
  Good Viwes.
  Thanks Dani.

  ReplyDelete
 7. I am happy this views.

  ReplyDelete
 8. "ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡" God bless you Dani!

  ReplyDelete
 9. ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡ እንዴት አንድ አጎት እነዚህን ሁሉ ድመቶች ያፈራሉ? ፋሚሊ ፕላኒንግ የለም እንዴ? ዘይገርም ኩሉ በምን ይህን ሁሉ አየህልን አዬ ጉድ
  ተባረክ ዲ/ዳንኤል

  ReplyDelete
 10. +++
  ግን ይገርማል::ጥሩ እይታ ነው:: ግን ድመቱንም ነብሩንም ምን እናድርጋቸው?

  ዳ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልን::

  ReplyDelete
 11. ቂቂቂቂ... ሳቄን ሁሉ መቆጣጠር ነው ያቃተኝ:: ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አንዴ ጓደኛዬን አንዴ የእህቴን ባል ዘመዶች በግድ ዘመድ ነኝ ዓይነት አቀራረብ እየቀረብኩ ኑሮዬን በምገፋው በእኔ ደካማ ሰውዬ ከሃገር ቤት የሚንጎራደዱ ጥቃቅን ድመቶች ትዝ አሉኝ:: አንዳንድ ቀንማ ይህንን ህይወቴን የምታውቀው የሴት ጓደኛዬ ዘመዶች ከዚያው ከሀገር ቤት ሲጨቀጭቋት ከት ብለን እንስቅና ቁም ነገር ሳናወራ ስልካችን ይዘጋል:: ድመቶቹ ሰርጋችን የሚደገስበትን ሆቴል ሁሉ መርጠዋል አሉ፤ ጨራሽ ባለሶስት ባለ አራት ኮከብ እየተባለ ክርክር ይካሄዳል በድመቶቹ ዘንድ:ምክንያቱም ገና ለጋ ለግላጋ የሆነ የብረት መዝጊያ ነብር አሜርካ ጫካ ውስጥ አለሁላቸዋ?! ወይኔ ነብሩ!!

  ኧሬ ሌሎች ድመቶች ደግሞ ትዝ አሉኝ፤ ቤተክርስቲያን ለማሰራት አስበናል እንግዲህ ያለእናንተ ማን አለን፤ እናንተኑ ተማምነን አፍርሰናል እንግድህ አደራ:: ወይ ጉ..ድ እኔ እኮ በዬ..ት እና እንዴት ጫካ እንደገባሁ ሳያውቁ የነብር ሁሉ አውራ አድርገው ሲያውኩኝ እኮ ነው የሚገርመኝ:: ጫካ ስገባ ፈርቼ ይሁን ሸፍቼ? ምኔንም ሳያውቁ ነብር ሆነሃልና የግድ አጎትነትህን ተወጣ ሲሉኝ ምን ልበላቸው እነዚህን ድመቶች? ኧረ እስቲ መላ በለኝ አንተዬ!

  ደግሞ ሌላ ጉድ እንጂ: የዛ...ሬ ሰባትና ስምንት ዓመት ልቤ የደነገጠላትን ልጅ እንደው ባክሽን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ልወዳጅሽ ከንስሓ አባትሽ ተማክረሽ አሳውቂኝ ብላት " ምናችንም አይገጥምም የእኔና ያንተ" ያለችኝ ዛሬ በባሌም በቦሌም ብላ እባክህ ከይቅርታ ጋር ዛሬ ካለህበት አንዲት መስመር ምልዕክት እንኳን ላክልኝ ስትለኝ ምን ለበላት? ገና ግልገል ነብር ነኝ ልበላት? ወይስ ዛሬ እንዴት ድመት ሆንሽ ልበላት:: ለነገሩ ልኬላታለሁ እቺኛዋን መጣጥፍህን:: ውይ ውይ የድመቶችንስ ነገር ተወኝ:: የኔን የነብሩን ኑሮ ያቃወሱት እነዚህ ድመቶችና የአይኔን ቆሻሻ የለመዱት ትንኞች ናቸው:: ልዩነታቸው ትንኞቹ አጠገቤ ስለሆኑ ድካሜን አይተው ነው ድመቶቹ ግን ራሳቸው ደክመው ወይም የሃገር ቤት አይጦች አልቀውባቸው ነው::

  ነብሮ ነኝ

  ReplyDelete
 12. ayee daneal kanete andebt temhert becha yemiweta yemeslegn nebr ????? leka yiker kersteyan yehone sew bedefena ayenagerem gelts yaweral motem bihon ayeferam ahun dejeselamen askefetu enanete ewenetegna sewoch kehonachehu mk

  ReplyDelete
 13. ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡ እንዴት አንድ አጎት እነዚህን ሁሉ ድመቶች ያፈራሉ? ፋሚሊ ፕላኒንግ የለም እንዴ?
  June 10, 2011 1:01 PM

  ReplyDelete
 14. Nigusie DZ

  Dani. now the problem may occur and get visible when the tiger asked which cat is your relatives? Don't forget that this is true if the tigr is a true tiger
  thank you

  ReplyDelete
 15. Innante libbachiw yabete ye GLOBALIZATION LIJOCH HULLUM NEGER TAWUKOBACHIWAL! Ye video mebrat fitachiw tedekino bog sil,BIRHAN TEGELETELIN BILACHIW YIHON???atisemum inji kesemachiw gin lawerachiwut tetsetsetuna metsaf Anbibu(10).

  ReplyDelete
 16. የጽሑፉን ጭብጥ ወደፈለግነው በመቅዘፍ የአንዲትን ደካማ ግለሰብ (የእጂጋየሁን) ማህበራዊ ችግር ነቅሰን ከማውጣት ይልቅ እያንዳንዳችን የለበስነውን የድመት ገጸ ባህርይ ከላያችን እንግፈፍ፡፡

  እንደኔ እጂጋየሁን ድመት ሳይሆን አቦሸማኔ ይገልፃታል - ምክንያት -አጎቷ ነብር በሚገባ ያውቋታል፤ የፍላጎቷንም ይፈጽሙላታልና፡፡

  ብንያም ባህር ዳር

  ReplyDelete
 17. Kale hiywet yasemalin mechem dani des yemil ayin new yaleh.begna fanta ante honehal yemitayln beteley ine wiste yemisemagnin wey yemamnbetin ante sititsfew yigermegnal.Igziabher yibarkh lela yeteshale mirkat binor tiru neber

  ReplyDelete
 18. Can anyone tell me what I am missing here? The whole essay and the conclusion seem to infer that "Dimetochu enesu endemilut chaka minor yenebir zemed yelachewim, BINORACHEW GIN IT IS NATURAL AND REASONABLE that they can benefit from them..."

  Is that so? We all know the answer to this is "no!", but there is no single paragraph that explicitly prevents the reader from drawing this inference. I'll be happy if someone can signal me ...

  ReplyDelete
 19. ESAYE ANJETEN ARASEKEU D.DANEAL KKKKKKKKKKKKK YE AGOTUCHE BEZATE ALKE SEWES BE AGOTU YASABEBE ,MELKOSATUSE YETE YALEU AGUOTACHEW YEHUNE ENZHE WEFE ZERESHIUCHE UUUUUUUUUUU BEWENTE ANJETEN ARASEKEU TEBALKE WELADETE AMELAKE TELA KELELA TEHUNEHE KE SIWZERLAND

  ReplyDelete
 20. No obligation to infer a single conclusion. Daniel's idea is not as compacted as your's. Think differently.

  ReplyDelete
 21. Danie, yes you are right.There are so many "people" who claim as a "great uncle"behind their life span in church politics, politics,social issue....However,Danie don't forget on the other side of the coin that some claimant are true what they said. Because,their uncle help them to fulfill their interest at the expense of innocent people... at the expense of innocent people... PJ, from Debere Markos University.

  ReplyDelete
 22. ከአራተ ዓመት በፊት ለሥራ ጎንደር ሄድኩና የሚከተለውን የድመቶች ታሪክ ሰማሁ

  የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ በዘመነ ቅይ ሽብር ነፍሱን ለማዳን ይሰደድ እና በዚያው ወደ አሜሪካ ይሄዳል፡፡ ከሄደ ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቹን ባለው እቅም ይደግፋል፡፡ ድመቶቹ ግን በዚህ ወንድማቸው ከመኩራተ ያለፈ ሕይወታቸውን የሚቀይር ነገር አልሰሩም የሚላከውን ዶላር ይከፋፈላሉ ከዚያ በየካፌው ማውደልደል ብቻ ሆነ፡፡ ከ25 ዓመት በኌላ ተመልሶ ሲመጣ ከሀገር ሲወጣ የነበረው የግቢያቸው የቆርቆሮ በር እንኴን አልተቀየረም፡፡ ነብሩም ተቆጥቶ እኔ ይህንን ብር ስልካላችሁ ምን ዓይነት ሥራ ሰርቼ እንደሆነ ታውቃላችሁ? ምንያህል እንቅልፍ እያማረኝ እንደሆነ አላወቃችሁም የእናንተን ሕይወት እቀይራለሁ ብዬ ላለፉት ብዙ ዓመታት ትዳር ሳልመሰርት እንደቆተሁ እንኴን አልተረዳቸሁኝም ስለዚህ እስከዛሬ ለእናንተየገበረኩት ሕይወቴ ይቆጨኛል ብሎ የመጣበትን ዕረፍተ ሳይጨርስ ተመልሶ ሄደ ከዚያ ወዲህ ይኸው አይደውልም አይጽፍም፡፡ እናም ብዙ ነብሮች በደከሙት መኩራት ድመትን ነብር አያደርጋትም እና በሰው ሃሳብ የምናድር እስቲ መለስ ብለን ራሳችንን እንመልከት አለበለዚያ በስው ሃሰብ የሚየድር ቱባ ጥይት አይበሳውም ያሉት እንዳይደርስብን

  ReplyDelete
 23. ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡ እንዴት አንድ አጎት እነዚህን ሁሉ ድመቶች ያፈራሉ?

  Specially the right problem of our Church (Bete Kuhnet )
  It is good view

  ReplyDelete
 24. DN. DANIEL KALE-HIWOT YASEMALEN!
  . .. ወሬያቸው ሁሉ እገሌ ከተባለው ባለ ሥልጣን ጋር ሪሴፕሺን ግብዣ ተገናኝተን እንዲህ እና እንዲያ ብሎኝ፡፡ እገሌ የተባለው ባለ ሥልጣን ሞባይሉ አለኝ፤ ከፈለጋችሁ እዚሁ ልደውልለት እችላለሁ፡፡ እገሌ የተባለውን የፌዴራል ፖሊስ አውቀዋለሁ፤ ከፈለግኩ ማንንም ማስቀፍደድ እችላለሁ፤ እገሌ የተባለው ባዕለ ጸጋ እኔን ሳያማክር ምንም ነገር አይሠራም፡፡ .....

  ReplyDelete
 25. ohh Dani thanks a lot for ur great articles. you should consider to have a weekly Radio program some where to get more audience. it is not fair only few have access to your entertaining but also substantial messages.

  ReplyDelete
 26. Hey Daniel, I am gonna call you a Dr. for a reason thou; All we Ethiopians have this disease and you are smart enough to figure this out and I think we should call you a Dr. Seriously! We should proud of ourselves.

  ReplyDelete
 27. Dani Egziabhire yebarekehi it is very nice view Dani not only few Ethiopian Problem it is almost majority of Habesha problem what can I say Dani God will forgive Us

  Biruk.Z(GebiGebereale)

  ReplyDelete
 28. U r a great researcher,
  so i 1oo% agree w z rank Doctor! Even More!
  AGE.

  ReplyDelete
 29. It's quite satirical and yet educative. I was also amazed by the theme and the analogy as well. The writer vividly depicts the current "Scratch my back and I will scratch yours' sort of governmental infrastructure which is indeed a bitter pill to swallow. So, to cut a long story short, let us build an individual confidence and stop fiddling with something which doesn't relate to us or piggy backing with others, if you will. Hats-off Daniel.

  Tena Tabia folk
  From Bahirdar

  ReplyDelete
 30. ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው የሚለው ድመት በዛብንኮ፡፡ ጸሐፊዋ፣ ጥበቃው፣ ተላላኪው፣ ጸሐፊው፣ አስተዳዳሪው፣ ሰሞነኛው፣ ሾፌሩ፣ እልፍኝ አስከልካዩ፣ ሴት ወይዘሮው፣ ወንድ መኳንንቱ፡፡ እውነት በእነዚህ ሁሉ እጅ ካሉማ በእግዜር እጅ የሉም ማለትኮ ነው፡፡ እንዴት አንድ አጎት እነዚህን ሁሉ ድመቶች ያፈራሉ? ፋሚሊ ፕላኒንግ የለም እንዴ?

  ReplyDelete
 31. May God give a long life to you! I appreciate your view of about any thing. so how can to identify good people from such stupid. really, now days it is so difficult to get good thinker man especially to think about our church to remind the current problem and patriotism person.
  May God give a solution for all problem!

  ReplyDelete
 32. Dani Really Thank you! KALEHIWOT YASEMALIN. Nothing I can say.
  Let God keep tewahido church from false prophets. Long live for tewahido and for persons like you those stand for truth. I am sure tewahido live forever. But, false prophets, who come to us in sheep's clothing, but which are inwardly ravenous wolves (those stands to exterminate our tewahido church will be exterminated themselves.
  Let God help you in all things. Be strong always.

  D.B from Haramaya University

  ReplyDelete
 33. ዳኒ አንተ እኮ ለኛ መድሀኒታችን ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ጽሁፍህ እራሴን እንድመረምርና እንድታረም ነው ያረገኝ አመሰግንሀለሁ፡፡

  ReplyDelete