Thursday, June 9, 2011

የጽሞና ጊዜPelican, St. Makarios monastery, Egypt.
በዓለም ላይ የሰዎችን አስተሳሰብ የመሩ እና የለወጡ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ ስናጠና አንዳች ነገር ገንዘባቸው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሰዎችን ለማስተማር እና ለመለወጥ የተጉትን ያህል ለራሳቸው ጊዜ በመስጠት ውስጣቸውን የሚያዩበትና ከራሳቸው ጋር የሚሟገቱበት የጽሞና ጊዜ ነበራቸው፡፡
በዚህ የጽሞና ጊዜያቸው ከሰዎች ርቀው ለብቻቸው በመሆን ራሳቸውን ይፈትሻሉ፤ ከራሳቸው ጋር ይሟገታሉ፤ ደግመው ደጋግመው ያስባሉ፡፡ ይጽፋሉ፣ ያነባሉ፡፡ አንዳንዶቹም ይጸልያሉ፣ ይጾማሉ፡፡ አካባቢያቸውን ይመረምራሉ፣ ከዚህ በፊት ያደረጓቸውን ነገሮች ይገመግማሉ፡፡ አዳዲስ ሃሳቦችን ያፈልቃሉ፣ አዳዲስ መንገዶችን ይተልማሉ፡፡
በዚህ የጽሞና ጊዜያቸው ማንም ሳይመክራቸው ራሳቸውን ይመክራሉ፤ ማንም ሳይገሥጻቸው ራሳቸውን ይገሥጻሉ፤ ማንም ሳያርማቸው ራሳቸውን ያርማሉ፡፡ ከሕይወት የተለመደው መንገድ ወጣ ይሉና ሕይወትን በተለየ መንገድ ያዩዋታል፡፡ ለጉዞአቸው ምእራፍ ይሰጡታል፡፡ እናም እንደገና ታድሰው ይነሣሉ፡፡
እስካሁን ያሉን የችግር መፍቻ መንገዶች ኮሚቴ ማቋቋም፣ መሰብሰብ፣ መመካከር፣ ሃሳብ መለዋወጥ፣ መማር፣ መገሠጽ፣ መቆጣት፣ ኮንፈረንስ፣ ስብሰባ፣ ሴሚናር፣ ግምገማ፣ ሥልጠና፣ ውይይት፣ ክርክር፣ ድርድር፣ የመሳሰሉ ናቸው፡፡ እነዚህ መንገዶች የሚፈቷቸው ችግሮች እንዳሉ ሁሉ የማይፈቷቸው ችግሮችም አሉ፡፡
ከላይ ያየናቸው መንገዶች የሚያመሳስሏቸው ጠባያት አሉ፡፡ ሆታ፣ ቸበርቻቻ፣ ስሜታዊነት፣ ፉክክር፣ አለመሸናነፍ፣ ግርግር፣ ይበዛባቸዋል፡፡ ሰዎች ወደ ውስጥ ሳይሆን ወደ ውጭ እንዲያዩ፣ ሃሳባቸውን ከራሳቸው አንፃር ሳይሆን ከሌላው አንፃር እንዲሠነዝሩ ያደርጋሉ፡፡ የመጠቃት እና ያለመጠቃት፣ የመናገር እና ያለመናገር፣ የመቻል እና ያለ መቻል፣ የማወቅ እና ያለ ማወቅ ነገሮች አሉባቸው፡፡ ከዚህም በላይ ሁሉም ሰዎች በብዛት በተሰበሰቡባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ስለሚደረጉ የሌሎች ተጽዕኖ ይጎላባቸዋል፡፡
እናም እነዚህን መንገዶች ምሉዕ የሚያደርግ አንድ ነገር ይጎላል፡፡ የጽሞና ጊዜ፡፡
ሰው ከሌሎች ጋር ብቻ የሚሆን ከሆነ ከራሱ ጋር መሆን አይችልም፡፡ ሰው ከሌሎች ጋር ብቻ የሚነጋገር ከሆነ ከራሱ ጋር መነጋገር አይችልም፡፡ ሰው ሌሎችን ብቻ የሚሰማ ከሆነ ራሱን መስማት አይችልም፡፡ ሰው ሌሎችን ብቻ የሚያይ ከሆነ ራሱን ማየት አይችልም፡፡ ስለዚህም ከራሱ ጋር ብቻ የሚሆንበት ጊዜም ያስፈልገዋል፡፡ የጽሞና ጊዜ፡፡
ሰው ሁለት ዓይነት ዓይን፣ ሁለት ዓይነት ጆሮ፣ ሁለት ዓይነት ልሳንም አለው፡፡ የሥጋ ዓይን እንዳለው ሁሉ ዓይነ ልቡና አለው፤ የሥጋ ጆሮ እንዳለው ሁሉ እዝነ ልቡና አለው፤ የሥጋ ከንፈሮች እንዳሉት ሁሉ ከናፍረ ልቡናም አለው፡፡
በሥጋዊ ዓይኑ ዓለምን ያይበታል፤ በዓይነ ልቡናው ደግሞ ውስጡን ያያል፡፡ በሥጋ ጆሮው በአካባቢው ያሉትን ድምጾች ይሰማበታል፡፤ በእዝነ ልቡናው ደግሞ ራሱን ይሰማበታል፡፡ በሥጋ ከናፍሩ ከሌሎች ጋር ያወራበታል፤ በከናፈር ልቡናው ደግሞ ከራሱ ጋር ይነጋገርበታል፡፡
በዓለም ላይ ብዙ ስሕተቶች የፈጸሙ መሪዎችን ታሪክ ስንመለከት አብዛኞቹ ውሎ አዳራቸው ከሰዎች ጋር ብቻ የነበሩ ናቸው፡፡ በብዙዎች በመከበባቸው፤ አድናቂዎቻቸውን እና አመስጋኞቻቸውን ብቻ በመማታቸው፤ ለሌሎች እንጂ ለራሳቸው ባለመናገራቸው ራሳቸውን የሚያዩበት ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ስለዚሀም በስሕተት ላይ ስሕተት መጨመር እንጂ ስሕተታቸውን ማረም አይችሉም፡፡ የአንዳንዶቹም ሕይወት ምእራፍ የለውም፡፡ ሲሾሙ የተጀመረው «ምእራፍ አንድ» ሲሻሩ ወይንም ሲሞቱ ይጠናቀቃል፡፡ ምእራፍ ሁለት እና ምእራፍ ሦስት የሚባል በሕይወታቸው የለም፡፡ ምክንያቱም ራሳቸውን በራሳቸው አይተው ያለፈውን ምእራፍ ዘግተው ሌላ ምእራፍ ከፍተው አያውቁምና፡፡
ሰው ከዓለም ጋር የሚገናኘው በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቱ ነው ይላል የኑሲሱ ጎርጎርዮስ፡፡ ካላየ፣ ካልሰማ፣ ካላሸተተ፣ ካልዳሰሰ እና ካልቀመሰ ዓለም ከእርሱ ጋር ምንም ዓይነት ተራክቦ የላትም፡፡ እነዚህ አምስት በሮች ምንጊዜም ክፍት ከሆኑ ሰው ከውጭ ወደ ውስጥ ያስገባል እንጂ ከውስጥ ወደ ውጭ ማስወጣት አይችልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ንግግር አድራጊዎች፣ አስተማሪዎች፣ መካሪዎች፣ ተንታኞች፣ ሃሳብ ሰጭዎች የሚያቀርቧቸው ነገሮች እንጨት እንጨት የሚሉበት ጊዜ አለ፡፡ እገሌ ዛሬስ ምን ነካው? ነገር ዓለሙ ሁሉ አንጆ ሆነበትሳ? የሚባልበት ጊዜ አለ፡፡
እንዲህ ያለው ነገር ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች ዋነኛው የጽሞና ጊዜ ለማግኘት አለመቻል ነው፡፡ የማሰቢያ ጊዜ ሳይኖራቸው የሚናገሩና የሚሠሩ ሰዎች ያስታውቃሉ፡፡ እየጠፋባቸው፣ እያለቀባቸው፣ እየተበላሸባቸውም ይሄዳል፡፡ ለራሳቸው ያልጣማቸውን ለሌላው ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡
መሬት እንኳን በሰባት ዓመት አንድ ጊዜ እንድታርፍ እና ከማንኛውም ዓይነት አዝርዕት እንድትገላገል በብሉይ ኪዳን ተደንግጎ ነበር፡፡ ገበሬው ሳይደርስባት፤ በሬ ሳይጠመድባት፤ ጅራፍ ሳይጮኽባት፣ ማረሻ ሳያልፍባት፤ ከራሷ ጋር ብቻ እንድትሆን፡፡
ይህ ወቅት መሬት ለምነቷ እንደገና የሚመለስበት፤ ኃይል አግኝታ የምትነሣበት «የጽሞና ጊዜዋ» ነበር፡፡ በዩኒቨርሲቲ መምህራን ዘንድ «ሳባቲካል ሊቭ» የሚባለው ከዚህ የተወሰደ ነው፡፡ «ሳባቲካል» ማለት በእብራይስጡ «ሰባተኛው» ማለት ነውና፡፡
በብሉይ ኪዳን እንዲበሉ የተፈቀዱ እንስሳት ሁለት መመዘኛ ነበራቸው፡፡ ማመስኳት እና ሰኮና ስንጥቅ መሆን፡፡ የብሉይ ኪዳን ሊቃውንት የዚህን ምክንያት ሲተረጉሙት እንዲህ ይላሉ፡፡ የሰኮና መሰንጠቅ ቆንጥጦ እና አጽንቶ መያዝን ያመለክታል፡፡ ሰኮናው የተሰነጠቀ እንስሳ የሚራመድበትን መሬት ቆንጥጦ በመያዝ የራሱን ሚዛን ጠብቆ በማናቸውም አስቸጋሪ ቦታ ይጓዛል፡፡ ልክ የመኪና ጎማዎች ክርትፍትፋቸው መኪናውን መሬት እንዲቆነጥጥ እንደሚያደርጉት፡፡ ይህም መሠረትን ይዞ፣ ሚዛንን ጠብቆ በዓላማ መጓዝን ያሳያል ይላሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ እንስሳት ሁለተኛውን መመዘኛ ማሟላት የግድ ይላቸዋል፡፡ ማመስኳት፡፡ ማመስኳት ማለት በመስክ ጊዜ ያገኙትን ምግብ ይበሉና፤ ከመስክ መልስ ብቻቸውን ሆነው ቀን የተመገቡትን እያወጡ እንደገና ማድቀቅ፣ መሰለቅ እና ለሰውነታቸው ተስማሚ አድርጎ መፍጨት ማለት ነው፡፡
ይህም ማለት ሰው ምንም እንኳን በሩጫ ኑሮው፣ በወከባ ሕይወቱ፣ በግርግር ዓለሙ እና በፉክክር ጉዞው ያገኘውን ሁሉ ቢወስድም የጽሞና ጊዜ አግኝቶ የበላውን ማመስኳት አለበት ማለት ነው ይላሉ፡፡ እንስሳው ሲያመሰኳ አፉን ገጥሞ የውስጥ አካላቱን ብቻ ነው የሚያንቀሳቅሰው፡፡ ሰውም የራሱን ሕይወት ሲያመሰኳ የውጭ ሕዋሳቱን ዘግቶ በውስጥ ሕዋሳቱ መሆን አለበት፡፡
ሲያትል ውስጥ አንድ የካቶሊኮችን ገዳም ጎብኚቼ ነበር፡፡ the monastery of Silence ይሉታል፡፡ የጽሞና ገዳም ማለት ነው፡፡ እዚያ ቦታ የተወሰኑ ቀናት ለማሳለፍ ከዓመታት በፊት ቦታ መያዝን ይጠይቃል፡፡ በዓለም ላይ የታወቁ የሀገር መሪዎች፣ ደራስያን፣ ፈላስፎች፣ ፖለቲከኞች፣ የእምነት መሪዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ነጋዴዎች፣ ምኑ ቅጡ የማይመጣ የሰው ዓይነት የለም፡፡
በገዳሙ ውስጥ በዓለም የሚለበሰውን ልብስ መልበስ ክልክል ነው፡፡ ለሴቶች እና ለወንዶች የተዘጋጀ ልብስ አለ፡፡ ማድረግ የሚቻለው ገዳሙ የሚሰጠውን ድምፅ የማያሰማ ጫማ ብቻ ነው፡፡ ሬዲዮ፣ ቴፕ፣ ቴሌቭዥን፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት አይፈቀድም፡፡ ድምፅ ማሰማት ክልክል በመሆኑ ከአስተናጋጆች ጋር የመግባቢያ ኮዶች ይሰጧችኋል፡፡ እዚያ ቦታ የሚሰማው ድምፅ የወፎች እና ነፋስ የነካቸው ዛፎች ብቻ ነው፡፡ ጸጥታ ብቻ፡፡
ማንበብ እና መጻፍ ይፈቀዳል፤ ሌላ ነገር መስማት ግን አይፈቀድም፡፡ እርስ በርስ ማውራት ክልክል ነው፡፡ ማውራት የሚቻለው ከራስ ጋር ብቻ ነው፡፡ በዛፎቹ መካከል መዘዋወር ይቻላል፤ ማፏጨት እና ማንጎራጎር ግን የለም፡፡
አምስቱ የስሜት ሕዋሳት እዚህ ምንም ሥራ የላቸውም፡፡ ሥራ ያላቸው አምስቱ የልቡና ሕዋሳት ብቻ ናቸው፡፡ ሰው ሌላውን ሳይሆን ራሱን ብቻ ያዳምጣል፡፡ አንዳንዱም ሰዎች ሲናገሩ መስማት ያቆምና ፈጣሪው ሲናገር መስማት ይጀምራል፡፡
ዮሐንስ ሐፂር ለምን ከሰዎች ጋር ብዙ እንደማይነጋገር ደቀ መዛሙርቱ ሲጠይቁት «ከሰው ጋር ብዙ ካወራሁ ከፈጣሪዬ ጋር ጥቂት አወራለሁ፤ ከሰው ጋር ጥቂት የማወራ ከሆነ ግን ከፈጣሪዬ ጋር ብዙ አወራለሁ» ብሎ ነበር፡፡
እስኪ የሀገራችንም መሪዎች የጽሞና ጊዜ ይኑራቸው፡፡ ሚኒስትሮች፣ አጃቢዎች፣ ካድሬዎች፣ ወሬ አቀባዮች፣ አወዳሾች፣ ግርግር ፈጣሪዎች፣ ግብዣ አሳማሪዎች፣ ደንገጡሮች፣ አፋሽ አጎንባሾች፣ አማካሪዎች፣ በሌሉበት እነርሱ ብቻቸውን እስኪ ራሳቸውን ይዩት፡፡ የመጡበት መንገድ ትክክል ነው? ለመሆኑ በዚህ ጸጥታ ውስጥ መንፈሳቸው ምን ይላቸዋል? ከውስጥ ምን ይሰማሉ? ይፀፀታሉ? ይደሰታሉ? ልክ ነበርኩ ይላሉ? ተሳስቻለሁ ይላሉ? የማይዋሻቸው ውሳጤ ምን ይላቸዋል?
እስከዛሬ የሠሩትን እና የሰሙትን መልሰው ሲያመሰኩት ምን ምን ይላቸዋል?
እስኪ የሃይማኖት መሪዎቻችን የጽሞና ጊዜ ይኑራችሁ፡፡ ማንም ወደ ሌለበት፡፡ ከራሳችሁና ከፈጣሪያችሁ ጋር ብቻ ወደምትነጋገሩበት ጽሞና ግቡ፡፡ ውዳሴውን እና አጀቡን ለጥቂት ጊዜ አቁሙት፡፡ እስኪ ብቻችሁን ሁኑ፡፡ ስብሰባው ለጊዜው ይብቃ፡፡ ጉባኤው ይገታ፡፡ ንግሡ ይብቃችሁ፡፡ በባለጉዳይ መከበቡ፣ ሳታስነጥሱ ይማራችሁ መባሉ ይብቃችሁና ራሳችሁን ብቻ እዩት፣ እራሳችሁን ብቻ ስሙት፣ ራሳችሁን ብቻ ዳስሱት፣ ራሳችሁን ብቻ አሽትቱት፣ ራሳችሁን ብቻ ቅመሱት፡፡ ምን አላችሁ? መቼም ውስጥ አይዋሽ፡፡
እስኪ የየመሥሪያ ቤቱ አለቆች ቤታችሁም ሆናችሁ፣ ከከተማም ወጥታችሁ፣ ገጠርም ወርዳችሁ፣ እስኪ ጽሞና ግቡ፡፡ በእጃችሁ የምታገላብጡትን ፋይል በእደ ልቡናችሁ ስታገላብጡት ምን ይላችኋል? ስብሰባችሁን እስኪ ለብቻ ገምግሙት? ውሳኔዎቻችሁን እስኪ መርምሯቸው፤ መመሪያዎቻችሁን እስኪ ፈትሿቸው፤ ምን ሆናችሁ ነበር? ማን ማድረጋችሁ ነበር? ለምን እንደዚያ አደረጋችሁ? ምን ነክቷችሁ ነበር? ውስጣችሁ ምን ይላል?
እስኪ ሌሎቻችንም የጽሞና ጊዜ ይኑረን፡፡ ስብሰባ፣ ስብሰባ፣ ስብሰባ፤ ሴሚናር፣ ሴሚናር፣ ሴሚናር፣ ሥልጠና፣ ሥልጠና፣ ሥልጠና፤ ግምገማ፣ ግምገማ፣ ግምገማ፤ ዐውደ ጥናት፣ ዐውደ ጥናት፣ ዐውደ ጥናት፤ የማኅበር ጉዞ፣ ጉዞ፣ ጉዞ፤ እስኪ ይብቃንና ብቻችን እስኪ እንሁን፡፡  መሥመራችንን እንፈትሸው፡፡ ማንም ሳይጠይቀን ራሳችንን እንጠይቀው? ማንም ሳይመረምረን ራሳችንን እንመርምረው፡፡ ውስጣችን ምን ይላል?

ፔሊካን ወይም በኛ ቋንቋ ጳልቃን የሚባል ወፍ አለ፡፡ በጥንት ሰዎች ዘንድ እንዲህ ተብሎ ይታመን ነበር፡፡ ማርጀት ሲጀምር ከመንጋው ተለይቶ ብቻውን አንድ ቦታ ይሄዳል፡፡ ከዚያም ዝም ብሎ ትኩር ብሎ እያየ ይቀመጣል፡፡ ኃይሉ በውስጡ ከመከማቸቱ የተነሣ እሳት ይፈጥራል፡፡ ከዚያም እሳት ሰውነቱን ይበላዋል፡፡ የተወሰነ ጊዜ አቅሉን ስቶ ይሰነብታል፡፡ በኋላም እንደገና ሰውነቱ ይመለስለትና ታድሶ ይነሣል፡፡ በዚህ ምክንያት የፔሊካን/ ጳልቃን ሥዕል በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የትንሣኤ ምሳሌዎች ሆነው ይሳሉ ነበር፡፡
እስኪ አልፎ አልፎ ፔሊካንን እንሁን፡፡

40 comments:

 1. DO YOU MEAN LIVING IN THE WORLD BEING OUT OF IT?
  Thank you very much.

  ReplyDelete
 2. ዝምታ መጣ፤ ጉድ ፈላ። ይሄኔ ነው ጉድ። እናቶቻችን እንደሚሉት የኃጢያታችን ክምር ዘነዘናውን ያመጣና ይወቅጠናል። ከዚያ እድፋችንን ጥርት አድርጎ ያሳየንና በብረት ምጣድ ላይ ይጠብሰናል። ከዛ ደሞ ወስፌውን ያመጣና መሶብ እንደምትሰፋ ሴት አንዴ ክፌት አንዴ ደግሞ ከኋላ እየመጣ ይወጋናል። ልቦና ያለው እንባው ዱብ ዱብ ይላል የሌለው ደግሞ ተነስቶ ይሄዳል። የውስጡ ጩኽት የበዛበት ደግሞ በራሱም ፤ሊፈርድ ይችላል። አንድ ሰው በራሱ መፍረድ ከጀመረ ደግሞ ወይ ስህተቱን ያርማል አለበለዚያ እራሱን ይጎዳል (ፈጣሪ ደግ ስለሆነ ይህ ተገቢ አይደለም ንስሐ የተሰራው ለዚህ ነው)።
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 3. it is very itersting

  ReplyDelete
 4. Yes It helps u Find z Truth & Yourself!
  Thanxs.
  ßless U More.
  (AGE)

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሄር ይስጥልን ዳኒ ለእኔ በወቅቱ የተላከልኝ መልክት እንደሆነ አልጠራጠርም።
  ግን ከባድ የቤት ሥራ ነው። በአንድ ወቅት ከዛሬ 19 አመት በፊት አንድ የቤተ ክርስቲያን
  ታላቅ አባት ያሉትን አስታወሰኝ፡ ቦታውም እንደ እግዬአብሄር ፈቃድ ደብረ ጽሙና የ ጻድቁ
  ተክለ ሃዋርያት ገዳም ነው እኔ ለንግስ እርሳቸው ለዝምታ መጥተው ነው የተጋናኘነው እዚያ የመጡት ያንድ ታላቅ ገዳምና ደብር አስተዳዳሪነታቸውን አስረክበው ነበር እኔ ቀደምብዬ ሴነበር የደረስኩት አንድ ጥላ ቦታ ጋደም ስል ያችን ቦታ እሳቸውም ለጥላዋ ብለው መጡ እኔም ተነስቼ እዚህ ይቀ መጡ አልኩና ተዋውቀን እኔም ከየት እደመጣሁና ለምን እንደመጣሁ ነገርኳቸውና እርሳቸውም የመጡበትን ሲገልጹልኝ ለዝምታነው አሉኝ ምን አ ሉ መሰለህ ግን ተቃጠልኩ ሰው ሳይናገር ከኖረ ያመዋል እንዴ እንደዛ ነው ያረገኝ አሉኝ እርሳቸው ግን ዝም ያሉት ለ አንድ ዓመት ነበር።ማንነታቸውውንም ያወኩ ማታ ማህሌት ላይ ነው ከሌላ ሃገራት የመጡት ሁሉ ባርኩ ሲባሉ እንቢ እያሉ ለ እርሳቸው ያስተላልፉ ነበር።

  እኚህ አባት ዛሬም ትልቅ የቤተክርስቲያን አባት ሆነው በትህትና ላይ ሆነው ሃገረ ስብከታቸውን ያስተዳድራሉ እስቲ እርሳቸው ተቃተልኩ ያሉ እኔማ ትንሽ ስልኩ ዝም ያለ ከሆነ ወደ ቴሌቪዢን የምሃደው እሱ ዝም ካለ ወደ ኢንተርኔት ...እዴት ይሆን ዝም እምለው?

  ReplyDelete
 6. absolutly right enam bizu alaweram wederasachin enimalise, lemanore sinile masimaselu yibiqa
  dani Egizibihare rejime edime yadelihe

  ReplyDelete
 7. ዲያቆን ዳንኤል ጥሩ ምክር ነዉ እግዚአብሔር ይስጥልን ዝምታ ወርቅ ነዉ ፣ ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ወዘተ ወዘተ የሚሉ ብሒሎች አለን ፡፡በአንፃሩ ደግሞ ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል የሚልም አለመ፡፡
  ያንተ ጽሁፍ ግን ዝም ስለ ማለትም ስለ መናገርም አይደለም የሚያወራዉ መናገር ስል ከሰዎች ጋር ማዉራት ማለቴ ነዉ፡፡
  የሚያወራዉ ስለ ተመስጠ ነዉ ፣ ስለ ጽሞና ነዉ ዉስጥን ስለ መመርመር ዉስጥን ስለ ማዳመጥ ነዉ፡፡
  እኔ እንደገባኝ ይህ ነገር ማኘክ ወይንም ነገር ማመንዠግ አይደለም ዉስጥን ነብስን ማዳመጥ ለዉስጥ ለህሊና ጥያቄ መልስ መስጠት የአካልን ተግባር መመርመር ነዉ፡፡
  በአሁኑ ወቅት ከመሪዎች ፣ከአስተዳዳሪዎች ፣ከሀይማኖት አባቶችና ከሊቃዉንቱ ጀምሮ እስከታችኛዉ ህብረተሰብ ድረስ ሁላችንም ያጣነዉ ይህንን ነዉ ራስን ማዳመጥ ፣ ከራስ ጋር መነጋገር ለዉስጣችን ጥያቄ መልስ መስጠት፡፡
  ይህ ለሁላችንም ይጠቅማል ያለፈዉን ተግባራችንን ለመገምገመ የወደፊቱን አቅጣጫ ለማስያዝ ስህተቶችን ላለመድገም ይረዳናል ብዬ አስባለሁ፡፡

  ሰብስቤ ነኝ

  ReplyDelete
 8. ሳታስነጥሱ ይማራችሁ መባሉ ይብቃችሁና ራሳችሁን ብቻ እዩት፣ እራሳችሁን ብቻ ስሙት፣ ራሳችሁን ብቻ ዳስሱት፣ ራሳችሁን ብቻ አሽትቱት፣ ራሳችሁን ብቻ ቅመሱት፡፡ ምን አላችሁ? መቼም ውስጥ አይዋሽ፡፡

  ReplyDelete
 9. Dear Dani,

  What a great, timely advice! I like the way you approach things; you definitely know what, how, when, and whom to express ideas and opinions, as well as spiritual teachings. May Him help us listen to our heart!

  Your brothers from UK

  ReplyDelete
 10. ጽሞና ያስፈልጋል::በሌላ ቃንቃ ሱባኤ እንግባ ማለት ነው :: በኧንዳንድ ገዳማት የግል ሱባኤ የያዘ ሰው ከማንም ሰው ጋር መነጋገር ኣይፈልግም:: ስለዚህ በተለይ የሃይማኖት መሪዎቻችን ከራስና ከእግዚኧብሄር ጋር መነጋገርን ትተው በስጋ ምኞት ና ምቾት እራሳቸውን ከሞነኮሱለት ኧምላክ እያለየዩ ነውና ጽሞና ሱባኤ ቢገቡ መልካም ነው:: ለእነሱም ለጊዜውም ቢሆን ከነኤልሳቤት የተለመደ ትርኪምርኪ ወሬ ተለይተው ለህዝብ ሰላም ለቤተክርስቲያን ኧንድነት ይጸልዩ ዘንድ ኧምላክ ይርዳቸው::

  ReplyDelete
 11. Thank you very much! It is very helpful to anyone.

  ReplyDelete
 12. Nigusie from Netherland

  Thank you Dn.Dani. this will have to be practiced in all of our life

  ReplyDelete
 13. የጠፋው መሪ፣ የተዳፈነው መድኃኒት ጽሞና፡፡
  ይህን መድኃኒት በመጠቀም የማይፈታ ችግር፣ የማይረግብ ውጥረት፣ የማይሽር የጠላትነት ጠባሳ የለም፡፡ አገራችን የዚህ ሁሉ ፈተና አዙሪት ውስጥ የገባችው ይህን መድኃኒት መጠቀም የደፈሩ መሪዎች ባለመኖራቸው ነው፡፡

  ያለንግሥቲቱ የንብ ሠራዊት ኢምንት እንደሆነ ሁሉ ያለመሪዎቻችን (የፖለቲካ፣ የሃይማኖት፣የማኅበረሰብ፣የሲቨል ሰርቪስ ማለቴ ነው) እኛም ገለባ ከመሆን አናመልጥም፡፡ መሪዎቻቸን የዚህ ፍቱን መድኃኒት ተጠቃሚ ከሆኑ የሚጎረብጠው ሁሉ መደላደሉ አይቀርም፡፡

  ጽሞና ለመሪዎቻችን፡፡ አሜን

  ReplyDelete
 14. Dear Daniel,

  Yes indeed I agree with you. No single human being can be free his own mental judgement. Inward looking will give you the real picture of your own response. I do remember one good saying that stated measure twice and cut later. The message behind this statement is analyze what you are going to do before you implemented. Thus, self evaluation, inside of in debate, and personal analysis mirrored yourself exactly. I would like to underscore that no one can be safe from his/her mind setup and personal critics.

  ReplyDelete
 15. -- written by Max Ehrmann in the 1920s --
  Not "Found in Old St. Paul's Church"! -- see below

  Go placidly amid the noise and the haste,
  and remember what peace there may be in silence.

  As far as possible, without surrender,
  be on good terms with all persons.
  Speak your truth quietly and clearly;
  and listen to others,
  even to the dull and the ignorant;
  they too have their story.
  Avoid loud and aggressive persons;
  they are vexatious to the spirit.

  If you compare yourself with others,
  you may become vain or bitter,
  for always there will be greater and lesser persons than yourself.
  Enjoy your achievements as well as your plans.
  Keep interested in your own career, however humble;
  it is a real possession in the changing fortunes of time.

  Exercise caution in your business affairs,
  for the world is full of trickery.
  But let this not blind you to what virtue there is;
  many persons strive for high ideals,
  and everywhere life is full of heroism.
  Be yourself. Especially do not feign affection.
  Neither be cynical about love,
  for in the face of all aridity and disenchantment,
  it is as perennial as the grass.

  Take kindly the counsel of the years,
  gracefully surrendering the things of youth.
  Nurture strength of spirit to shield you in sudden misfortune.
  But do not distress yourself with dark imaginings.
  Many fears are born of fatigue and loneliness.

  Beyond a wholesome discipline,
  be gentle with yourself.
  You are a child of the universe
  no less than the trees and the stars;
  you have a right to be here.
  And whether or not it is clear to you,
  no doubt the universe is unfolding as it should.

  Therefore be at peace with God,
  whatever you conceive Him to be.
  And whatever your labors and aspirations,
  in the noisy confusion of life,
  keep peace in your soul.

  With all its sham, drudgery, and broken dreams,
  it is still a beautiful world.
  Be cheerful. Strive to be happy.

  ReplyDelete
 16. I like it.
  It is really nice to get even silence within a day,
  just as we need some tea/coffee time,little nap, break time,it is part of our nature to get all these kind of things for our soul like kindness,love hope etc.

  Let us start comparing what we have done for our soul like we do for our flesh. Daily,weekly, monthly,annually etc plans.Our soul needs vacation(silence).

  Sharing is happiness

  ReplyDelete
 17. ርብቃ ከጀርመንJune 9, 2011 at 9:35 PM

  ሰላም ዲያቆን ዳንኤል እንደምን ከረምክ ብሎግህላይ ያለውን የንስር ምልክት ሳይ ሁሌ የማስበው ነገር ነበር ንስሩንና አንተ የምታነሳቸውን ሀሳቦች በድንገት ወይም እንዲሁ ለምልክትነት አይመስለኝም መለያምልክትህን የንስር የደረከው አዎእግዚአብሄር ባወቀ ከስምህ እንደነቢዩ ዳንኤል ብልሀትን እንደስሩ የሀሳቦችህ ጥልቀትን ስለማስብ ይሆናል እናምዳኒ ይሄንየተሰጠህን ጸጋ እስከሂወትህ መጨረሻ ያቆይልህ ዘንድ ሁሌም ምኞቴ ነው ላንተ አዝኘብቻእንዳይመስልህ ለራሴ ነው እንዲህ እንዳንተ በሰላብዕሩ ውስጤን እንዳይ ማንነቴን እንድበረብር የሚያደርገኝ ባዶነቴን በጣፋጭ ቀሉ የሚነግረኝ ስለሌለነው ስለለዚህ ዳኒ አሁን እንኩዋ ጸሞናን በተመለከተ ይሄን የመሰለ ጣፋጭትምህርት (ተግጻጽ) እየተነገረኝ እኔማነኝ ብየ ወደውስጤ ከመይይልቅ ያስቀደምኩት ላንተ ይሄን መጻፍነውና በውነቱ በጸሎትህ ልታስበኝ ይገባል እግዚአብሄር አምላካችን ማስተዋልን ሰጥቶን በምክርህ ተጠቃሚ ያድርገን ላንተም እድሜና ጤናውን ከነቤተሰብህ ይስጥልኝ ቸርያሰማን!

  ReplyDelete
 18. nigusie dz
  thank you Dn.Dani. don't fear the God is with you and your family

  ReplyDelete
 19. Thanks Dn Daniel!i am in campus and realised the value of meditiation here! May God bless you. Our church please read this!!!

  ReplyDelete
 20. መምህር የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልህ
  ዝምታ እጅግ በጣም አስደሳች ነገር ነው የሚቻል ከሆነ ለቆረጠለት ሰው። በቃ እራስን ብቻ ማነጋገር እኔ ማን ነኝ ብሎ እራስን መጠየቅ ለአለፈው ንስሃ መግባት ለወደፊቱ በዚያ መንገድ ላለመሄድ ጥረት ማድረግ እራስን መፈለግ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው። መምህር አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ በአገር ውስጥ ያሉ ሰዎች ዝም እንበል እራሳችን እንፈልግ ንስሃ እንግባ ቢሉ በጣም ብዙ ባታዎች አሉ ከአ.አ ብዙ ሳንርቅ። በውጭው ያሉ ሰዎችስ? በጣም ብዙ ጊዜ ያሳስበኛል ንስሃ ሳይገቡ ይቀራሉ ማለቴ አይደለም እንደው እራሳቸውን ለመፈለግ ምን አይነት ባታ ትመርጥላቸውለህ መቼም አንተ የውጭውን አለም አናናር በደንብ ታወቀዋለህ? በቸር ያሰንብተን...

  ReplyDelete
 21. ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እግዚአብሔር በአንተ ላይ አድሮ የሚሰራው ሥራ በዚህ ዘመን ብዙ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ በዚህ ጽሑፍም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ሰው መጀመሪያ ውስጡን ካየ በራሱ መገሠፁ አይቀርም፡፡ ሌላም ቢወቅሰው፣ቢገስፀው ይገባኛል፣ጥፋቴ ነው፣እንዲያውም ሲያንሰኝ ነው ይላል፡፡ እግዚአብሔርም ቢገስፀው ያመሰግናል ይህንን እንደንስሀ ይቁጠርልኝ ይላል እንጂ ቅር አይለውም (አያማርርም) ቤተ ክርስቲያናችን ቀድማ ትህትናን ታስተምራለችና፡፡ አባ አጋቶን ‹‹እምተናግሮ ይሔይስ አርምሞ›› ለ 7 ዓመታት ድንጋይ ጐርሰው በዝምታ እንደኖሩ ተምረናል፡፡ ይህንን ያደረጉት አንድ ሰው ከኋላቸው እየሮጠ መጥቶ አልፏቸው ሲሄድ አይተው ነበርና ሌላ ሰው ከኋላ እንዱሁ እየሮጠ መጥቶ አንድ ሰው በዚህ አልመጣም ብሎ ሲጠይቃቸው ለሰላም መስሏቸው በመንታ መንገድ እንዳይሳሳት በቅንነት የሄደበትን መንገድ በመናገራቸው እየሮጠ ሄዶ ገድሎት በመመለሱ እርሳቸው ሲደርሱ ይህንን ትዕይንት ተመልክተው እኔ ባልናገር አይሞትም ነበር እንዳሉ ተምረናልና ራሳቸውን በጽሞና ጊዜ በቅጽበት በማየታቸው ለዚህ እንደበቁ ስለተገነዘብን በጣም ታላቅና ዋና መመሪያና ምክር ነውና እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር የያዝከውን መንገድ እስከመጨረሻው የቀና አድርጐ ያስፈጽምህ፡፡

  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 22. Hi Dani, this is rely very valid message which helps us checking and learn from our past experiences.Your message also remind me "St.Arsema Gedam" which is a place of silence.

  God Bless you,

  Temesgen, Dire Dawa

  ReplyDelete
 23. Dn.Dani melkam hasab new yemiyaschilen bihon ''Lebego enkuan zim alku '
  'mezmur38:2
  መሬት እንኳን በሰባት ዓመት አንድ ጊዜ እንድታርፍ እና ከማንኛውም ዓይነት አዝርዕት እንድትገላገል በብሉይ ኪዳን ተደንግጎ ነበር፡፡ ገበሬው ሳይደርስባት፤ በሬ ሳይጠመድባት፤ ጅራፍ ሳይጮኽባት፣ ማረሻ ሳያልፍባት፤ ከራሷ ጋር ብቻ እንድትሆን፡፡
  yemigrm new ISRAEL AGER akirari yehudi yehonut eko yehenin be 7 amet ande yefetsmutal yebet west Abebawochin enkuan weha ayatetum

  ReplyDelete
 24. የምትሰጠቸዉ ሀሳቦች በሙሉ በጣም ደስ ይላል በተለይ ስለሀይማኖት ግን፣ ለምን ችላ እንዳልክ ይሁን ወይ ሳታዉቅ ይሁን ስለኦርቶዶክስ ተሃድሶ የጥንት ሀይማኖታችን፣ ሀገራችንን ሊያጠፉ ታጥቀዉ ተነስተዎል በኛ ቤተክርሲቲያን ገብተዉ ምእመኑን እያወዛገቡ ሁከት እየፈጠሩ ሀይማኖቱን እንዲቀይሩና እንዲጠራጠሩ እያደርጉ ነዉ አንተ በተቻለህ እግዚአብሄር በሰጠህ ተሰጥሆ የተዋህዶን ልጆች እባክህ ታደግ አምላክ ሀይማኖታችን ይጠብቃት አሜን

  ReplyDelete
 25. Dn Daniel Kale Hiwot Yaseman I work for a security company and most of the time(2-3) hrs per day dont talk to any one and i had a lot of moment totalkto my self.Honestly all u said is true.What a good analysis Egziabher Yebarkeh Yasnah

  ReplyDelete
 26. Demmellash, /Adea Berga, Eth/June 11, 2011 at 2:38 PM

  A nice advice I have got. God bless u and ur spiritual service more.

  ReplyDelete
 27. Demmellash /Adea berga EthJune 11, 2011 at 2:51 PM

  A nice advice I have got. May God bless u and ur spiritual service.

  ReplyDelete
 28. Danie, you made me to see the issue in different angle. Wow... It is a good insight.Thank you. Pj,from Debre Markos University.

  ReplyDelete
 29. No Word, it is simply perfect!!

  ReplyDelete
 30. bettam webe mekere nwe egezihabehere yaglegelote gizehene yabezalehe

  ReplyDelete
 31. በትክክል ሰውን ሰው ሊያደርግ የሚችል ምክር ከስህተትም ለመመለስ ሁነኛ መንገድ፤፤

  ReplyDelete
 32. ዲያቆን ዳንኤል ጥሩ ምክር ነዉ እግዚአብሔር ይስጥልን

  አምስቱ የስሜት ሕዋሳት እዚህ ምንም ሥራ የላቸውም፡፡ ሥራ
  ያላቸው አምስቱ የልቡና ሕዋሳት ብቻ ናቸው፡፡ ሰው ሌላውን ሳይሆን ራሱን ብቻ ያዳምጣል፡፡ አንዳንዱም ሰዎች ሲናገሩ መስማት ያቆምና ፈጣሪው ሲናገር መስማት ይጀምራል፡፡
  running....running....running...the life become boring.
  Hailmeskel Z Maputo

  ReplyDelete
 33. Kale hiwetn yasemaln D.Dani,bewnet reasi endmeleket new yaderekegn,Fetari tegstu yesten

  ReplyDelete
 34. thanks to God that gave you such mind and it is realy interesting message for all of us who are voluntary to accept our failure and to be shaped

  ReplyDelete
 35. ሰው ከራሱ ጋር መነጋገር ሲጀምር ከሰው ቁጥር ገባ ይባላል እንዲሉ “ የጽሞና ጊዜ” አልከን ዳኒ? ደግ ብለሃል ፣ እሱ ነው እልፍ እሚያደርገን ፡ እርሱ ነው ከኛነታችን ጋር እሚያስታርቀን.

  ንግርታችው አፈ-ታሪክ እንጂ እውነት ሆኖ ያልተቀበልንላችው አበው ( ያገሬ አዛውንቶች) ወደ ፊት ረጅም ለመዝለል ወደ ህዋላ መንደርደር ግድ ነው ያሉን እኮ ሮጠን ሮጠን፡ ወጥተን ወርደን ቆም እያልን የሮጥንበትን የወጣን የወረድንበትን ውጤቱን እንክዋ ለማየት ጊዜ መውሰድ ካልቻልን ሩጫችን ሁሉ የጉንዳን እንዳይሆንበን ፈርተው እኮ ነው!

  እባክህ ዳኒ እንዲህ እንዲህ አይነቱን ወግ አብዛልን?

  የነግ ሰው ይበለን.

  ፍቅር-ዓለም ከጆበርግ

  ReplyDelete
 36. “ሰው ከሌሎች ጋር ብቻ የሚሆን ከሆነ ከራሱ ጋር መሆን አይችልም፡፡ ሰው ከሌሎች ጋር ብቻ የሚነጋገር ከሆነ ከራሱ ጋር መነጋገር አይችልም፡፡ ሰው ሌሎችን ብቻ የሚሰማ ከሆነ ራሱን መስማት አይችልም፡፡ ሰው ሌሎችን ብቻ የሚያይ ከሆነ ራሱን ማየት አይችልም፡፡ ስለዚህም ከራሱ ጋር ብቻ የሚሆንበት ጊዜም ያስፈልገዋል፡፡ የጽሞና ጊዜ፡፡”
  You are right a lot of us need our own time. We need to find our soul, our spirit we need to know who we are inside. Some of us we live in a world full of people who challenge us. So we wouldn’t have much time to know our selves challenging with those people. But sometimes we have got to let it go we got to ask our self’s.
  Who am I? What part of me is good? What part of me is bad? What shall I do to make my life better? e.t.c. Yes you are Dn Daniel, sometimes we should be like a pelican.

  ReplyDelete
 37. እስኪ አልፎ አልፎ ፔሊካንን እንሁን፡፡

  ReplyDelete
 38. በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው በተግባር እንዳውለው እግዚአብሄር ይርዳኝ ይርዳቺሁ አሜን!!!

  ReplyDelete
 39. iM GOING TO CHURCH KNOW TO LISTEN MY SELF...I STRONGLY AGREE WITH THIS IDEA...THANKYOU DANNY!!!!

  ReplyDelete