Tuesday, June 7, 2011

ከካይሮ የተላከ ደብዳቤ


ይድረስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ይድረስ ለአምባሳደር መሐሙድ ድሪር
ሴትዮዋ በችግር ጊዜ የተነሣችውን ፎቶ ነበር አሉ፡፡ የትኛ ውም መሥሪያ ቤት ስትጠየቅ የምትሰጠው፡፡ ምክንያቱም ሌላ ፎቶ ለመነሣት ገንዘብ ስላልነበራት፡፡ ታድያ ክፉ ዘመን ማለፉ አይቀርም አለፈና ሴትዮዋ አመልማሎ መሰለች አሉ፡፡ ሀብቷ ጨመረ ውበቷ ነጥሮ ወጣ፡፡
በየቦታው ስትሄድ የምታገኛቸው ሰዎች ስሟን ስትነግራቸው ያቺ የጥንቷን ከሲታ ሴት ነበር የሚያስታውሱት፡፡ እናም ምንም ነገር ብትሠራ ሰዎቹ በድሮው ማንነቷ ስለሚያውቋት ተቸገረች፡፡ ፋይሏ በወጣ ቁጥር የከሳች፣ የጠወለገች እና የወየበች ሴት ፎቶ ነበር ከች የሚለው፡፡
ነገሩ ሲያስጨንቃት ጊዜ ምክር ዐዋቂ ዘንድ ሄደች፡፡ እናም ሰውዬው «በይ የዛሬውን መልክሽን በፎቶ ተነሥተሽ እየዞርሽ በየፋይሉ አስገቢው፤ ቢያንስ የድሮውን ያላወቀው ሰው ሲመጣ በአዲሱ ማንነትሽ ያውቅሻል» አላት ይባላል፡፡
ከአሥር ዓመታት በላይ የኖሩ የሀገሬ ልጆች እንደነገሩኝ ግብፃውያን ባለፉት አርባ ዓመታት ኢትዮጵያን በተመለከተ የሳሉት ሥዕል እጅግ የሚገርም እና የሚያሳዝን ነው፡፡ በመንገድ ላይ የምታገኙት ወጋው ሕዝብ ኢትዮጵያ ሀገር ትሁን መንደር አያውቅም ነበር፡፡ ሕዝቡ ዓባይ ከደቡብ ግብጽ ወይንም ብዙዎች እንደሚያስቡት ከአስዋን የሚመነጭ ነበር የሚመስለው፡፡ ከዚያ ከፍ ያለው ሰው ቢበዛ «አላህ የሰጠን ነው» ይላችኋል እንጂ ዓባይ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚመነጭ አልሰማም ነበር፡፡
ግብጻውያን አንድ መልካም ጠባይ አላቸው፡፡ መንገድ ላይ የሚያዩትን ፀጉረ ልውጥ ሰው «ከየት ነው የመጣህው» ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ታድያ ትናንት «ከኢትዮጵያ ነው የመጣሁት» ብሎ መንገር አስቸጋሪ ነበር፡፡ ምክንያቱም «ኢትዮጵያ የት ናት የሚለውን ለእነርሱ ማስረዳቱ ከባድ ነውና፡፡ በዚሀም ምክንያት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን
 
«ሀገርህ የት ነው»
«በርበሬ»
«በርበሬ የት ነው»
«ሽንኩርት አጠገብ»
«ሽንኩርትስ የት ነው»
«ከቃርያ አጠገብ»
ከዚያ የሰለቸው ግብፃዊ  «አይ አይዋ» ነበር የሚለው፡፡
 አሁን ግን እድሜ ለዓባይ ግብጻውያን ኢትዮጵያን እያወቋት ነው፡፡
«ከየት መጣህ» ብለው ይጠይቋችኋል፡፡
«ከኢትዮጵያ» ስትሏቸው፡፡
«ውኃውን የምትቆልፉብን ለምንድን ነው ይሆናል ቀጣዩ ጥያቄያቸው፡፡ ቢያንስ ኢትዮጵያ የዓባይ መነሻ ሀገር እና በዓባይም ላይ ሥልጣን እንዳላት ገብቷቸዋል፡፡ ይህንን ጥያቄ ከታላላቅ ባለ ሥልጣናት እስከ ተራው ሕዝብ፣ በከተማ ካለው እስከ ገዳማውያን ያነሡባችኋል፡፡
ግን አንድ ያልገባቸው ነገር አለ፡፡ ኢትዮጵያ ዓባይን ለመገደብ ዐቅሙን ከየት ታመጣዋለች? አንዳንድ ሚዲያዎች የግድቡ ዜና በተሰማ ሰሞን ኢትዮጵያ ድኻ እና በረሃብ የምትጠቃ ሀገር እንደሆነች፡፡ ይህንንም ሥራ ለመሥራት ዐቅም እንደሌላት ነበር የሚገልጡት፡፡
እኔ በየቦታው የገጠመኝን ነገር አይቼ አንድ ነገር እንደሚቀረን ተረዳሁ፡፡ እንደዚያች ሴትዮ በየቦታው የተቀመጡትን ፎቶዎቻችንን መቀየር፡፡ ኢትዮጵያ ማናት? ኢትዮጵያ እና ዓባይ ምን ግንኙነት አላቸው? ኢትዮጵያ ግድብ ትሠራለች ማለት ምን ማለት ነው? እነዚህ ጥያቄዎች ለግብጻውያን ሊመለሱላቸው ቢችሉ ፎቷችንን የሚቀይሩት ይመስለኛል፡፡
እኔ ወደ ግብጽ ለመምጣት ቪዛ ያገኘሁበት የግብጽ ኤምባሲ ሰፊ፣ ውብ እና በዐጸድ የተሞላ ነው፡፡ ካይሮ ያለውን ኤምባሲያችንን ሳየው ግን እንኳን ዓባይን ለመገደብ የተነሣንና በሠፈራችን የሚወርደውንም ጎርፍ ለመገደብ የተነሣን አይመስልም፡፡ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ለብዙ መቶ ዓመታት የቆየ የግንኙነት ታሪክ ያላቸው ሀገሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመርያውን በረራ ካደረገባቸው ሀገሮች አንዷ ግብጽ ናት፡፡ ካይሮ ያለው ኤምባሲያችን ግን ኢትዮጵያን አይመጥንም፡፡ በተለይ ዛሬ፡፡
ሌላም አሳዛኝ ነገር አለ፡፡ ካይሮ ውስጥ ዛማሌክ በተባለው ክፍለ ከተማ የሚገኝ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የሆነ ባዶ ቦታ አለ፡፡ በኤል መንሱር መሐመድ እና በጁላይ 26 መንገዶች አዋኝ ላይ የሚገኘው ይህ ቦታ ስፋቱ ወደ 2200 ካሬ ሜትር ያህል ይሆናል፡፡ በዋናው የግቢው በር አጠገብ property of the Ethiopian embassy  የሚል ጽሑፍ በአሮጌ ሰሌዳ ላይ ከላይ በዐረብኛ ከታች ደግሞ በእንግሊዝኛ በጥቁር ተጽፏልÝÝ በእውነቱ ይህንን የሚያህል ቦታ ያለው ሀገር የበሬ ግንባር በምታህል ቦታ ላይ የተሠራች ቤት ተከራይቶ መቀመጥ ምን ይሉታል፡፡
በአካባቢው ለረዥም ጊዜ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ቦታው ከተገዛ ወደ ስድሳ ዓመታት ያህል እንደሆነው ነግረውኛል፡፡ በዚህ ስድሳ ዓመት ውስጥ የመሬት ግብር እየገበሩ ከመቀመጥ ይልቅ አንዳች ጠቃሚ ሥራ ቢሠራበት ምን ነበረበት?
እንደዚህ ያሉ ታሪኮች ናቸው ፎቷችንን ያበላሹት፡፡ አሁን ግን ፎቶውን ለማስተካከል መልካም ጊዜ ላይ ያለን ይመስለኛል፡፡ አንደኛ ግብጻውያን ስለ ኢትዮጵያ ማወቅ የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ እንዲህ ባለው ጊዜ ታድያ የሃይማኖት አባቶች፣ ሚዲያዎቹ፣ ምሁራኑ፣ ታላላቅ ተሰሚ ሰዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች እና ሌሎች እየተጋበዙ ስለ ሀገራችን ትክክለኛውን እንዲረዱ ማድረግ ይገባናል፡፡ ኤምባሲያችንም ለዚህ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ አምባሳደሩ፣ ዲፕሎማቶቹ እና ሠራተኞቹ ብቁዎች ሆነው እያሉ ኤምባሲያችን ግን አይመጥነንም፡፡
በኤምባሲው እና በኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ግንኙነት ለውጥ እንዳለው ኢትዮጵያውያኑ ይመሰክራሉ፡፡ አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት እና ኤምባሲውን የኢትዮጵያውያን ቤት ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረትም ሲደነቅ ሰምቻለሁ፡፡
ታድያ ያንን ስድሳ ዘመን ርስት የምናለማበትና እንደ ግብጽ ፒራሚድ የኢትዮጵያን ማንነት ከፍ አድርገን የምናሳይበት ጊዜ አሁን ይመስለኛል፡፡ ያለበለዚያማ ዋናው ከተማ ዛማሌክ ላይ ያንን የመሰለ ቦታ በአሮጌ አጥር አጥሮ ለስድሳ ዓመት የሚያስቀምጥ አገር ዓባይን ይገነባል ቢሏቸው ግብጻውያን እንዴት ያምኑናል?
ኧረ እባካችሁ ፎቶውን ካይሮ ላይ ቀይሩት፡፡

13 comments:

 1. ዘሐመረኖህJune 7, 2011 at 1:20 PM

  ሰላም ለዳኒና ለእድምተኞቹ ወንድም ዲያቆን ዳኒ መቼም የምታነሳቸው ቁም ነገሮች ሁሉ ማስተዋል ለሰጠው ሰው አንዱም መሬት ጠብ አይልም ግብጾች ግን ሃገራችን የት እንደምትገኝ የአባይ መነሻ ከየት እንደሆነ ያለማወቃቸው አንድም አንተ እንዳልከው ፎቶው ያለመቀየሩ ጉዳይ ነው አንድም እያወቁ ለንቀት ነው ከስንት አንዱ አጠገቡ የምትገኝን ጎረቤት ሃገር ትምህርት ቤት ባይገባ እንኳን በሆነ ጉዳይ በመገናኛ ብዙሃን መስማቱ አይቀርም እያወቀ ግን ንቀት ስላለበት አውቆ በጥያቄ ያደክምሃል አሁን ግን አባይ ሊገደብ ነው ሲባል የግዱን የሃገራችንን ስሟንና ማንነቷን ማወቁን ገለጠ አባይን ሊገድብ የሚችል አቅም አለን ሲባል ድሮም የሚያውቀውን ሀቅ እንዲያወጣው አስገደደው አንዳንዱ ጭራሽ አለማወቁ ያሳዝናል የፎቶው ነገር ግን በአባይ ምክንያት ከግብጽ ጀምሮ በመላው ዓለም ባለው ፋይል ውስጥ የሃገራችን ፎቶ መቀየር ቢጀመር መልካም ነው ምንም እንኳን በኢኮኖሚ ከመጨረሻዎቹ ድሃ ሃገሮች አንዷ ብንሆንም ጦም ማደር የለመደ ሆድ ስለማያስቸገር አንጀታችንን አስረን አባይን ለመገደብ ብንችል ይህም በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካውም የጠፋውን ሰላምን ነጻነትን እኩልነትን አንድነትን በብሄራዊ እርቅ በማምጣት በዘር በቋንቋ በጎሳ በሃይማኖት መከፋፈላችንን አስወግደን እውነተኛውን ዲሞክራሲ በመገንባት የሃገራችንን ፎቶ መቀየር እንችላለን

  ReplyDelete
 2. ዳንኤል ጥሩ ታዝበሃል እግዜር ይባርክህ !የሚመለከታቸው ይንቁ::

  ReplyDelete
 3. አይ ዳንኤል በየትኛዉ ፎቶ ነዉ የምንቀይረዉ መቀሌና አንዳንድ አዲስአበባ ላይ ባሉ ፎቶዎች ነዉ? ወይስ ከ90% በላይ በርሃብና በስቃይ ላይ ባለዉ በባዶ እግሩና በባዶ ሆድ በሚሄደዉ ኢትዮጲአዊ ፎቶ?ተዉ ዳንኤል የኢትዮጲያስ ፎቶ ከ20 አመት በፊት ያለዉ ይሻላል!ፎቶ መቀየሪያዉ ጊዜዉ አሁን ነዉ ማለትህ........?ባይሆን ጊዜዉ በቃ ብለን ሌላ የምንቀይረዉ ነገር አለ!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. ኧረረረ ኡኡኡኡ……… ኧረ ወሬ ሰለቸን፡፡ እባካችሁ እናንተ የመንግስት አካላት ከወሬው ቀንሱ እና ትንሽ ሰርታችሁ አሳዩን፡፡ ልታሳብዱን ነው እንዴ? ተግባር ተግባር ተግባር………

  ReplyDelete
 5. Dear Daniel,

  It is good observation. Image building is necessary. Ethiopian diplomats and any responsible citizens who lives in every corner of the world should work hard to build the image our country. Ethiopia is the cradle of civilization and humankind but remained forgotten. Let's move and repair our image and prestige together.May God Bless Ethiopia

  ReplyDelete
 6. you are so amazing person!! please yemimeleketachu kefeloch yehen eyeta enantem eyut!!

  ReplyDelete
 7. Nigusie from Dz

  Dn. Dni. the one who have ear will hear! your observation is intersting! my God blessing you

  ReplyDelete
 8. TeklehaymanotawianJune 7, 2011 at 10:42 PM

  It's good, of course, but at this time, especialy these days, we need about our church and the TEHADISO movement. Or else tell us who you are. Before God punish you we'll punish you as we did in Mercato together with Ashenafi, Dagmawi,etc. "Minahin Ley!"

  ReplyDelete
 9. ይህ ሁሉ የስድሳ ዓመታት ስንፍና ፊታቸው ገትረን አባይን ልንገድብ ነው የሚለው አስቂኝ ሊሆን አይችልም ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ፎቶው ይቀየር፣ አባይም ይገደብ፡፡ ግን እባካችሁ በአባይ ጉዳይ ላይ የጫናችሁትን ቫት (ግነቱን)አንሱልን ወይም ቀንሱልን፡፡ ከሚነገረው 60 በመቶው ቫት ነው፤ ታዲያ 20 በመቶ ይዞ "እምቢ" ማለት እንደ ቴአትረኛው መሆን ማለት አይደል?

  ReplyDelete
 10. አይ ወንድሜ የምትጽፈው አለቀብህ እንዳልል የዚህ ሰሞን ጉዳየ ለመጻፍ አይደለም ለሌላም ይበቃ ነበር ብቻ ኢትእታመኑ በዕጓለዕመህያው ነው ያለው መጽሀፍ በዚህ ግዜ የከበበንን ፈተና እንዴት እንወጣ ብለን የምንወያይበት መድረክ ይሆናል ብየ እገምት ነበር ግን ምን ያደርጋል
  ወንድሜ እኔ ሀኪም ነኝ ነብሴ እስኪወጣ ስሰራ ውየ በመሃል በባነንኩ ቁጥር በእግዚአብሔር ስም ነው የምልህ ወጥቸ ምን እበላ የሚለው ነው የሚያባንነኝ እኔም ሆንኩ ጓደኞቸ ቤት የለንም አከራዮቻችን ደግሞ በዘር ወይም በፖለቲካ አመለካከታቸው ያገኙትን ቤት ቀበሌ ቤት እየኖሩ ሲያሻቸው በየወሩ እየጨመሩብን ታድያ ሲያሻቸው ያለህግ እያባረሩን ነው የምንኖረው ታድያ የግብጽ ኤምባሲያችን መሰራትን Image building ነው ማለት ምን ማለት ነው
  ዳንኤል ሆይ ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግና ወዳድነት የጻፍከውን ጽሁፍ አስታውስ ብዙ ባልኩ ነበር
  ማኔ ቴቄል ፋሬስ

  ReplyDelete
 11. Nigusie DzARC
  dear tekle------

  before giving any comment please read the the missage of the write up b/s giving of comment is the simplest one even aman like you simply give acomment

  ReplyDelete
 12. is it possible to change the image of something only by talking? if we are going to tell some one about the current situation of Ethiopia,what are we going to say? I don't think it will be about our strong institutions or about our vibrant and prosperous economy? then please daniel if you are convinced that the current image of ethiopia needs changing then tell us also in detail the real changes on the ground which are going to accompany the image building.

  ReplyDelete
 13. I observed most of the comments forwarded on this piece of writing. Yet, I couldn't understand why most of those who commented tell the price of sugar when they are asked the price of coffee. Most of the comments are utterly IRRELEVANT. Obviously, Daniel was in Egypt recently, and he is sharing his experience and suggesting what is good for our country and people. I firmly believe that we should care about our country as we care about our church. Why can't we understand Daniel's good motive? This is not to say that he shouldn't write about our church or about other social and political issues. But he is the one in charge, the one behind the stirring wheel! We can't dictate him to do this or that. In the end, it is his blog.

  ReplyDelete