የጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ደብር የተተከለችበትን 300ኛ ዓመት ለማክበር ወደ ጎንደር ስበርር አንድ ሰው አገኘሁ፡፡ ድሮ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አብረን ተምረናል፡፡ ከጥንት ወሬያችን መለስ ስንል ወደ ጎንደር የመጣንበትን ምክንያት መጨዋወት ጀመርን፡፡ እኔ የጎንደር ልደታን 300ኛ የትክል በዓል ለማክበር እንደምሄድ ነገርኩት፡፡ እርሱ ደግሞ ዘመድ ጥየቃ እንደመጣ አጫወተኝ፡፡
«ጎበዝ ኢትዮጵያዊ ሆነሃል ማለት ነው» አልኩት፡፡
«እንዴት?» አለ፡፡
«የኛ ዘመን ሰዎች ብዙ ጊዜ በዘመድ ይጠየቃሉ እንጂ ዘመድ አይጠይቁም ይባላል»
«የምሄደው ወደተለየ ዘመድ ስለሆነ ነው» አለኝ እየሳቀ፡፡
«የተለየ ዘመድ ደግሞ እንዴት ያለ ነው»
«እኔ የተማርኩት ባሕር ዳር ከተማ ነው፡፡ ወላጆቼ በልጅነቴ ስለሞቱ ከየዘመዱ ተጠግቼ ነበር በመከራ የተማርኩት፡፡ እኔ ያልቀመስኩት የመከራ ዓይነት የለም፡፡ ሲመቸኝ የቀን ሥራ፣ ሳይመቸኝ የሰው ቤት ተላላኪ ሆኜ ነበር የተማርኩት፡፡ ብዙዎቹ ዘመዶቼ በቤታቸው ለማስጠጋት አንጂ እኔን ለመርዳት ዐቅም አልነበራቸውም፡፡
እንደምንም ተግቼ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ተፈተንኩና አለፍኩ፡፡ ማለፌ ሲያስደስተኝ ወደ ተመደብኩበት አዲስ አበባ ለመሄጃ ገንዘብ ስላልነበረኝ አዘንኩ፡፡ በዚያ ጊዜ ፖሊ ቴክኒክ እና ፔዳ ጎጂ የሚባሉ ኮሌጆች ባሕርዳር ከተማ ላይ ነበሩና ወደ እነርሱ ለመቀየር ወጣሁ ወረድኩ ግን አልቻልኩም፡፡
ትዝ ይልህ እንደሆነ በዚያ ጊዜ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የስፖርት ቱታ፣ ሻል ያለ ልብስ ይዛችሁ መሄድ አለባችሁ እንባል ነበር፡፡ ከዚያም በላይ በማላውቀው ሀገር ማን እየረዳኝ እማራለሁ ብዬ ሃሳቡ ገደለኝ፡፡
አንድ ቀን አስቤ አስቤ ምንም ማድረግ ሲያቅተኝ የጉልበት ሥራ እሠራበት ከነበረው ድርጅት ወጣሁና መንገድ ዳር አንድ የኤሌክትሪክ ግንድ ተደግፌ አለቀስኩ፡፡ እዚያ ቦታ አንገቴን ደፍቼ ትክዝ ብዬ እንደ ቆምኩ ድንገት የመኪና ጥሩንባ ሰማሁ፡፡ ቀና ስል አንዲት ነጭ ልብስ የለበሱ ደልዳላ ወ/ሮ ወደ እኔ ያያሉ፡፡ በእጃቸው ጠሩኝ፡፡ ሄድኩ፡፡
እዚያ አካባቢ የሚገኝ ቦታ ጠየቁኝ፡፡ ትንሽ ራቅ እንደሚል ነገር ግን በዚህ አልፈው በዚህ ታጥፈው ቢሄዱ እንደሚያገኙት ነገርኳቸው፡፡
«ካላስቸገርኩህ አብረን ሄደን ብታሳየኝ» አሉ፡፡ እኔም ከኀዘኔ የመላቀቂያ ፋታ ስላገኘሁ አብሬያቸው ሄድኩ፡፡
መንገድ ላይ «ምን ሆነህ ነው እንደዚያ የተከዝከው? ለብዙ ሰዓት ክላክስ አድርጌ ልትሰማኝ አልቻልክምኮ» አሉኝ፡፡
«እንዲሁ ነው» ብዬ ዝም አልኩ፡፡
«ወንድ ልጅማ እንዲሁ አይተክዝም» አሉ አንገታቸውን እየነቀነቁ፡፡
ዝም አልኩ፡፡
«ሰው የማይሰማው ነገር ነው» አሉ እየሳቁ፡፡
«አንድ ችግር ገጥሞኝ ነው» አልኳቸው፡፡
«ምን?»
ነገሩን ነገርኳቸው፡፡ ስጨርስ መኪናቸውን ጥግ ይዘው አቆሙ፡፡
«እና አሁን ልኮሌጅ መሄጃ አጥተህ ነው የምታለቅሰው» አሉ ዓይናቸው ዕንባ አቅርሮ፡፡
«አዎ»
መሪያቸውን ተደግፈው ዝም አሉ፡፡
«እኔ ረዳሃለሁ፡፡ ዶክመንቶችህን ይዘሃቸዋል» አሉኝ፡፡
«ቤት ናቸው» አልኳቸው፡፡
«ቤትህ የት ነው»
«ትንሽ ራቅ ይላል»
መኪናቸውን አዞሩና ወደ እኔ ቤት ሄድን፡፡ አሁንም አሁንም አንገታቸውን ይነቀንቃሉ፡፡ ቤቴ ስንደርስ ሮጥ ብዬ ዶክመንቶቼን አመጣኋቸው፡፡ አገላብጠው አዩና ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
«እኔ የምኖረው እንግሊዝ ነው፡፡ አሁን ዘመድ ለመጠየቅ መጥቼ ነው፡፡ አሥር ሺ ብር እሰጥሃለሁ»
ብጆሮዬ «አሥር ሺ ብር፣ አሥር ሺ ብር፣ አሥር ሺ ብር» ጭውውውውውውው ይልብኛል፡፡
ከዘመዳቸው ቤት ደርሰው ሲመጡ ሆቴላቸው ጋ ወሰዱኝና አሥር ሺ ብር ሰጡኝ፡፡ ያን ቀን የሆንኩትን መቼም አልሆነውም፡፡ ደስታ ግራ አጋብቶህ ያውቃል? ደስታ በሽታ የሚባለው ያ ይሆን እንዴ? አድራሻቸውን ሰጡኝ፡፡ አብረን ፎቶ ተነሣን፡፡
አራት ዓመት ሙሉ ሳልቸገር ኮተቤ የተማርኩት በዚያ ብር ነው፡፡ ወዳጄ ያኔ አሥር ሺ ብር ማለት ሚሊዮን ብር ማለት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በደብዳቤ እንጂ በአካል አላገኘኋቸውም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘጠኝ ዓመት ሠርቼ ውጭ ወጣሁ፡፡ ከዚያም በዩኔስኮ ተቀጥሬ ኢንዶኔዥያ እሠራለሁ፡፡
ከስድስት ዓመት በኋላ ወደ ሀገሬ ስመጣ እርሳቸውም ወደ ሀገራቸው መምጣታቸውን ጻፉልኝ፡፡ ያሉት ጎንደር ከተማ ነው፡፡ አሁን የምሄደው እርሳቸውን ላመሰግን ነው፡፡ እርሳቸው ባይኖሩ ኖሮ እኔ አልኖርም ነበር፡፡ እኔ የደግነታቸው ውጤት ነኝ፡፡ መወለድ ቋንቋ ነው ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ያኔ የተነሣነውን ፎቶ በትልቁ አሳጥቤዋለሁ፡፡ ስድስት ጓደኞቼም መጥተዋል፡፡ አንድ ፕሮግራም አድርገን እርሳቸውን ልናመሰግን ነው፡፡ ለቅኖች ምስጋና ይገባል ትሉ የለ እናንተ፡፡
እየነገረኝ በሃሳብ ጭልጥ ብዬ ሄድኩ፡፡ እውነቱን ነው አንድ ሰው ብቻውን ላሰበበት ቦታ ወይንም ዛሬ ለደረሰበት ቦታ አይደርስም፡፡ የሚያውቃቸውም ሆኑ የማያውቃቸውም አካላት አስተዋጽዖ አድርገውለታል፡፡ አንዳንዶቹ ባለ ውለታዎች ለረዥም ጊዜ የቆየ ሥራ የሠሩ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ለአጭር ጊዜ የቆየ ወይንም አንድ ጊዜ ብቻ የተፈጸመ ውለታ የዋሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን እናስታውሳቸዋለን፤ ሌሎቹን ግን ረስተናቸዋል፡፡
እኔ የማልረሳቸው አንድ ሾፌር አሉ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ስንፈተን ያጋጠመኝ ነገር ነው፡፡ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተና ፕሮግራም ይለያያል፡፡ እኔ እንዳጋጣሚ ፕሮግራሙን አምታታሁትና በዚያ ቀን ፈተና የሌለ መስሎኝ ቀረሁ፡፡ ጠዋት ለማጥናት ወደ ቤተ መጻሕፍት ስሄድ ልጆች በድንጋጤ ለምን ከፈተና እንደቀረሁ ጠየቁኝ፡፡ እኔም ዛሬ እኔ የምወስደው ፈተና የማይሰጥ መሆኑን ስነግራቸው መርሐ ግብሩን ገልጠው አሳዩኝ፡፡
ደነገጥኩ፡፡ ፈተናው ሊጀመር አሥር ደቂቃዎች ያህል ቀርተውታል፡፡ ት/ቤቱ ደግሞ ካለሁበት ቦታ የአንድ ሰዓት ርቀት አለው፡፡ በፍጥነት ወደ አውቶቡስ መያዣው ቦታ ሄድኩ፡፡ በዚያን ጊዜ በከተማዋ ውስጥ ያለችው አውቶቡስ አንድ ብቻ ነበረች፡፡ እርሷም የማትረግጠው ቦታ አልነበራትም፡፡
አውቶቡሷ ስትመጣ ሾፌሩን ገብቼ ነገርኳቸው፡፡ ወዲያውኑ «ግባ ግባ» አሉና በሩን ዘግተው ወደ ት/ቤቱ ሸመጠጡ፡፡ ትዝ ይለኛል በ15 ደቂቃ ውስጥ ነበር ያደረሱኝ፡፡ የመምህራኑ ደግነት ተጨምሮበት እንደ ምንም ተረጋግቼ ፈተናውን ለመፈተን በቃሁ፡፡ አሁን የኒህ ሾፌር ደግነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ ምን ልሆን እችል ነበር? እያልኩ ሁልጊዜ አስባለሁ፡፡
ልክ እንደ እኒህ ደግ ሾፌር ያሉ ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ አሉ፡፡ ልናመሰግናቸው የሚገቡ ጎረቤቶች፣ ዘመዶች፣ መምህራን፣ አለቆቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ በአንዳች አጋጣሚ ታሪካዊ ሥራ የሠሩልን ሰዎች፤ የሥራ ባልደረቦቻችን፣ የሃይማኖት አባቶቻችን፣ እንዴው በአጠቃላይ ለሕይወታችን መቃናት አንዳች አስተዋጽዖ ያደረጉ ቀና ሰዎች አሉ፡፡
ልጁ እንዳደረገው ሁሉ እነዚህ ሰዎች እና አካላት ምስጋና ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለምን?
ለእኛ ያደረጉት ነገር ምን ያህል በጎ ለውጥ እንዳመጣ ካወቁት በበጎ ሥራቸው ይገፉበታል፡፡ የልፋታቸውን ዋጋ ያውቁበታል፡፡ የኅሊና ርካታም ያገኙበታል፡፡ ያለበለዚያ «እጄ አመድ አፋሽ ነው» እያሉ በጎ ሠርተው እንዲፀፀቱ እናደርጋቸዋለን፡፡
በሌላም በኩል ሌሎች እንደነርሱ በጎ ይሠሩ ዘንድ ያበረታታቸዋል፡፡ በጎ ሠሪዎች ሲመሰገኑ፣ ስማቸው ከፍ ብሎ ሲነሣ፣ ውለታቸው ሲታወስ የተመለከቱ ሌሎች መንፈሳዊ ቅናት ያድርባቸዋል፡፡ ለካስ በጎ መሥራት እንደዚህ ዋጋ አለው ይላሉ፡ እያንዳንዷን ቅንጣት አጋጣሚም ለበጎ ሥራ ያውሏታል፡፡
ክፉ ሰዎችም ስማቸው ሳይነሣ ይወቀሱበታል፡፡ በጎውን ማመስገን ክፉውን መውቀስ ነውና፡፡ እኔም እንዲህ ባደርግ ኖሮ ብለው ይፀፀታሉ፡፡ የክፉ ሥራን ዋጋም ያውቁበታል፡፡
እኛም ከወቀሳ እንድናለን፡፡ ለበጎ ሥራ ዋጋ አለመክፈል በሰማይም በምድርም ያስወቅሳል፡፡ የነዚያ ሰዎች ታሪክ በተነሣ ቁጥር የኛ ውለታ ቢስነት አብሮ ይነሣል፡፡ እነርሱ በበጎ ሲታወሱ እኛ በክፉ እንታወሳለንና፡፡
ታድያ እንዲህ ያሉትን ሰዎች «ላደረጋችሁልን ነገር ሁሉ እግዜር ይስጥልን፣ የእናንተ ውለታ እኔን እዚህ አድርሷል» ብለን የምናመሰግንበት ቢያንስ በዓመት አንድ የምስጋና ቀን ያስፈልገናል ባይ ነኝ፡፡ በዚህ ቀን በስልክ፣ በአካል፣ በደብዳቤ፣ በኢሜይል፣ እነዚህን ሰዎች ያደረጉትን ነገር አውስቶ ማመስገን ይቻላል፡፡
በፌስ ቡክ ላይ ከተቻለ ከነ ፎቷቸው ያደረጉትን ሥራ ማውጣት፤ በጋዜጣ እና በሬዲዮ ከፍሎ በአደባባይ ማመስገን፣ ይቻላል፡፡ ከተቻለም የማስታወሻ ስጦታ መላክ ይገባል፡፡
እስኪ ሃሳብችሁን ስጡ፡፡ ይህንን እንደ ባህል ብንይዘው ምን ይመስላችኋል? የትኛው ቀንስ የምስጋና ቀን ተብሎ ቢታሰብ የተሻለ ይሆናል?
Thanks for sharing. Just one comment. Gondar Mekane Sibhat Lideta Lemaryam
ReplyDeleteዲን. ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ! እረጅም የአገልግሎት እድሜ ያድልህ!
ReplyDeleteበእኛ ሀገር ሰውን በክፉ ማንሳት እንጅ የማመስገን ባህል ተመናምኗል! ሰው የበጐ ስራው ማህተም የህሊናው መዝገብ ማረጋገጫ ምስክር የእኛ ምስጋና ነው! ምስጋናው ከንቱ ውዳሴ እንዳይሆን እየተባለ ሰውየው ስለሰራው በጐ ሥራ በተቻለ መጠን እርሱ ሳይሰማ በሐሜት መልክ እናደርገዋለን! ነገር ግን
በእኔ አመለካከት ከንቱ ውዳሴን መከላከል ለባለቤቱ መተው አለበት! ይልቁንም በጣም የሚያሳዝነው ክፉ ሥራ ሠርተው ከአእምሮ ወቀሳ ነፃ መሆን ስለማይቻል በህሊናቸው ክስ ያዘኑ ሰዎችን አንተ/አንቺ እኮ ልክ ነህ/ሽ እያልን ለክፉ ስራቸው ሐሰተኛ ውዳሴ የምናቀርብበት መንገድ ነው ሕዝቡን እና ሁላችንን የጐዳን ብዬ ነው የማስበው!
እውነትን እውነት ሐሰትን ሐሰት ማለት ብንለምድ ጥሩ ነው!
በእኔ በኩል ጳጉሜ ፭ በዓመቱ የተደረጉልንን ነገሮች በሙሉ በማሰብ ሰው ለሚቀጥለው ዓመት ከሚሰራው እና ከሚያቅደው ነገር ውስጥ ለሰዎች መልካም ውለታን መዋል ከእቅዱ ውስጥ እንዲያስገባው ባለፈው ዓመት የሰራውን በጐ ሥራ የምናስታውስበት እና የምናመሰግንበት ቀን ቢሆን መልካም ነው እላለሁ!
Dear Daniel,
ReplyDeleteWhat a wonderful article is this? We should be grateful to those people who contribute in our life. Late me tell you one thing, my father was a retired soldier. He loves his children too much. In 1984, he was sick and passed away for the same. Recently, I heard a very nice story that touched the bottom of my heart. I met an old man - after a long time - who was visited my father while he was sick. He told me that he was too happy when he saw me that I am very successful. It is because, when my father was sick he asked my mother to open the box and to pick something that was wrapped by the paper. When the paper was unwrapped, there were 700.00 Birr on it. My mother asked him what is this? He replied that I will pass away soon, however, my son will finish his high school next year. Thus, this is the money for his school. he said that, my son should finish his high school with out any problem. You know, I heard this after 27 years back. My father save that amount of money for me while he is needed that amount for his medical care. When I learned this, I was touched and thank him even if he passed away. One thing that I underlined is that we should be grateful for those who contribute something to our life.
It good history that we Ethiopian should accustomed to do such kind of culture. I mean the culture of thanks.
ReplyDeleteHaileyesus, from Debremarkos university.
ይህ አካሄድ መልካም የሆኑ ሰዎች ምስጋን የሚገባቸው እንደሆኑ ባወቁት ቁጥር ምስጋናው በሚፈጥርባቸው መታበይ እራስን ወደ ማክበርና ከንቱ ወደ ሆነ ውዳሴ ይወስዳቸዋል:: በዚህ መሀል ምስጋና የሚገባው አምላክ ይረሳል:: ሰዎች ለሰው መልካም ማድረጋቸው እግዚአብሄር በነዚህ መልካም ሰዎች ስለተገለጠ ነው:: ባመሰገናቸው ቁጥር ምስጋናውን መሸከም መቻላቸው ያጠራጥራል:: ማንም መልካም ሰሪ ምስጋናን ጠብቆ መልካም መስራት የለበትም:: እኛው ስንመሰጋገን ምስጋና የሚገባውን እንረሳዋለን:: በቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ይህ አይደል እየሆነ ያለው:: የቀደሙት አባቶች መልካም ሲያደርጉ እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር:: ዛሬ መልካም ያደረጉ ሰዎች አደባባይ ለምስጋና እንዲሰለፉ ለምን አስፈለገ:: መልካም የተደረገላቸው ሰዎች እነርሱም ለሌላው ለምን መልካም እንዲያደርጉ የትስስር መረብ አይፈጠርም::
ReplyDeleteßetam Tiru:
ReplyDeleteMeskerem 1
(AGE)
Dear Daniel, I always read your posts here in this blog. I got alot of ideas from you and from comments of others. coming back to the current issue, as to me, I support your Idea to have a thanks giving day for those individuals who had major role in our life. We most of us thank others when we get road directions, find missed property, etc from others support immediately.However, to thank those individuals who had place in our life should not be given thnks once only.Even though I can't put the specified time or day of thanks giving day for those person who had their own role in our life, I believe that we must have it.
ReplyDeleteI hope readers will more discuss on this issue and come up with specific and convenient day of thanks giving.
I reaally appreciate you and extend my thanks to you.
የ ምስጋና ባህላችን ገና ብዙ ይቀረዋል። ለ አዚህ ማሳያ ንግድ ሥራ ኮሌጅ አያለሁ አንድ መምህራችን ክፍል ውስጥ ያሉን አይረሳኝም አውነተኛ ታሪክ ስለሆነ አስተማሪም ነው።መምህሩ ከ አንግሊዝ ሀገር የ ፒአችዲ ዲግሪአቸውን አንደያዙ አኛ ክፍል መምጣታቸው ነበር አና ባላቸው ጊዜ የ አኛን ባህል ጥሩውን በጥሩነት ማረም ያለብንን ደሞ አንዲሁ አየነቀሱ ያወጉን ነበር። አንድ ቀን ታድያ ክፍል ውስጥ አንዲት አንቀፅ ፅሁፍ ፃፉና ከ አናንተ ውስጥ ሶስት ሰዎች ተመርጠው ካነበቡ በሁአላ በ ሶስቱ ትሾፎች ላይ ሁላችሁም ሃሳብ ስጡ አሉን። ከ ግማሽ ሰዓት በሁአላ ሶስት ልጆች ተመርጠው አነበቡ አኛም ሃሳብ መስጠት ጀመርን። ከ አስራ አምስት በላይ ልጆች የሰጡትን ሃሳብ መዘገቡ። ሁሉም ሃሳቦች ታድያ በ ፅሁፎቹ ላይ ስህተቶችን አየነቀሰ፣አንዲህ ቢሆን ኖሮ፣ይሄ ቢስተካከል፣አዚህ ላይ ተሳስቷል፣ወዘተ የሚሉ ነበሩ።በሁአላ ዶክተሩ አንዲህ አሉን።-
ReplyDelete''አዚህ ፅሁፍ ላይ ሁላቺሁም ማለት ይቻላል ስህተት ነው ያወራችሁት። አንዴት ከ አንድ ነገር ላይ ትንሽ ጥሩ ነገር ይጠፋዋል? በጎውን የ ማበረታታት አና የ ማመስገን ባህላችን በ አጅጉ ተጎድቷል። በመጀመርያ በጎውን አና ጥሩውን ጎን አውርቶ ቀጥሎ ይሄ ይስተካከል ማለት በ ሌላው ዓለም የተለመደ ነው። አኛ ግን የመጣንበት ሕብረተሰብ የ ማመስገን ባህሉ ስለተጎዳ ሁሌ ወቀሳ ለምደናል።ምሳሌ ልንገራችሁ አናቶቻችን ጥሩ ዶሮወጥ ይሰሩ አና ለ ባላቸው ሲያቀርቡ 'አንደነገሩ ነው የሰራሁት አስኪ ብሉ' ይላሉ።ለትህትና አልያም ቀምሶ ይፍረድ ብለው ነው አንጂ በጣም የተጠበቡበት አና የለፉበት ወጥ መሆኑን አና መጣፈቱን ያውቃሉ።የ ተመቁትን ጠላም ይቀዱና ቀመስ አርገው 'አስኪ ይቺን አፍዎ ላይ አርጉአት ለውሃ ጥም ብትሆን ባይጣፍትም ከ ውሃ ይሻላል ' ብለው ይሰጣሉ። ምግቡን የበላውም ሆነ የጠጣው ባል ግን ሲቀምሰው ይጣፍተዋል በውስጡ 'አንዴት ይጥማል' ይላል ባፉ አውጥቶ ግን አያወራም ሚስቱንም አያመሰኝም ዝም ብሎ መብላት ነው ዛሬ 'ባለሙያ ካልኩ ደሞ ---' ብሎ ያስባል ።ልጆችም አናቶቻቸው ሲመሰገኑ ስሞገሱ አላዩም ፣አራሳቸው ልጆቹም አየተመሰገኑ ስላላደጉ ሌላውን ለማመስገን ለማድነቅ አና ለማበረታታት የሚይዘን የ ባህል ችግር ተጎጂዎች ይሆናሉ።ካሁን ካሁን ያደንቃል ብላ ስጠብቅ የነበረች ሚስትም ሳይደነቅላት ሲቀር አርሱ ሁለም አንዲሁ ነው ጥሩ አርጌ ብሰረው ባልሰራው አያለች ታስባለች።ባልም አንዲሁ ነው ዛሬ ሚስቴን ላስደስታት ብሎ የማትወደውን ነገር ትቶ፣በ ጊዜ አቤቱ ገብቶ ጥሩ አባት ሲሆን፣ለ ሚስቱ የምትወደው አቃ ነው ብሎ ገዝቶ ስመጣ ውስጧ አያወቀ አና አየተደሰተች ባፉአ ግን ብዙም ትኩረት አንዳልሰጠች መስላ መቅረብ በ ህብረተሰባችን አንደ ባህል ተለምዷል። አኛ ዛሬ ብናመሰግን ለነገ ይኩራራል ወይም ትኩራራለች ብለን አናስባለን።በተቃራኒው ግን ነገ ለ በለጠ ሥራ አንዳይተጋ አያረግነው መሆኑን ልብ አንልም። አሁን ከ አነኝህ ፅሁፎች ውስጥ አንድ ጥሩ ነገር አውጥቶ ከመናገር ይልቅ በሙሉ አስተያየቶቻቺሁ ትችቶች የሆኑት ለ አዚህ ነው'' ያሉን አስካሁን አይምሮዬ ላይ አለች። አሁን አሁን ሳስበው ያኔ ዶክተሩ አለብን ያሉን ችግር በ ሥራ ቦታ፣በ ፖለቲካ፣ማህበራዊ፣ባህላዊ አና ሃይማኖታዊ ተቁአሞቻችን አየተንሰራፋ መሆኑ ይታየኛል። አኔ ደሞ የምለው የማመስገን ባህላችን ብቻ ሳይሆን ስህተት አየሰራ፣አየሰረቀ፣አየዋሼ ፣ፀሐይ የሞቀውን ማታለል አየፈፀመ ያለውን ሁሉ ለመውቀስ አና 'አካፋን አካፋ' የማለት ባህላችን ሁሉ በ አጅጉ ተጎድቷል።ይሄው ባህላችንም በ አየ ተቁአሞቻችን ውስጥ ተንሰራፍቶ አንዳላዩ የማየት አባዜ ተጠናውቶናል። በ ቤተ አምነቱ ውስጥ የሚሰራውን ግፍ አና ሸፍጥ ቤተ አምነቱ ውስጥ ያለው አያየ አንዳላየ ያልፈዋል።ከ ውጭ ያለውም አማኙም ሆነ ግድግዳ ላይ አንደተለጠፈ ወረቀት አያየ ያለው መንግስትም ምንም አንዳልተፈፀመ ይመለከታል። የማመስገን ባህላችን ብቻ ሳይሆን የመውቀስ ባህላችንም፣አውነቱን የመናገር አና ለማስተካከል ቆርጦ የመነሳት ባህላችንም ተጎድቷል።ባህላዊ አሰቶችን በደንብ መፈተሽ አና ቀድሞ የነበሩንን በጎዎቹን መያዝ ማስተካከል ያለብንን ማረም ተገቢ ነው። ችግር ግን አንድ ቦታ መቆም አለበት።''ችግርን ማወቅ በራሱ የመፍትሄ ግማሽ መንገድ ነው'' አንዲሉ አኛ ዛሬ ችግራችንን አውቀን ካስተካከልን ችግራችን ታሪክ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም።
O my God, I am totally down. I could not stop my tear while reading this article. It seems that you publish the secret of my success. The only difference is that i am not lucky like that gay. The person who played for my success died while I was in a college. I do not know what to suggest!!!!!! I realllllllllly do not know! I do not know. May be I will try later.
ReplyDeletePraise to Him who has given you such powerful writing skill.
It is very touching. I can't agree more on the proposal to have a 'thanks giving day' I was thinking of many days, but couldn't think of a better day other than MESKEREM 1, our new year. this is a common holiday for all Ethiopians regarless of our demographic background. Let's express our gratitude to God and to humanity on this day.
ReplyDeleteGod bless you abundantly,
Yared
it is true D/n this culture should be continued? it is nice lesson
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው:: ለሴትዮዋ የተዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ሁኔታውን ባየሁ ነው ያሰኘኝ:: የትኛው ቀንስ የምስጋና ቀን ተብሎ ቢታሰብ የተሻለ ይሆናል ያልከው የፈረንጆቹን መኮረጅ አይመስልም?
ReplyDeleteማለፊያ የሆነ ሃሳብ ነው። እንዲህ አይነት ነገሮች በሌሎች አገራትም የተለመደ ነው። የማይረባውን ከምንኮርጅ እንዲህ አይነት ልማዶችን ወደራሳችን ብንጠቀም ምንኛ በታደልን። የገደልበትን ቀን ከምናስታውስ የዳንበትን ብናዘክር ምንኛ ባማረ። እንደ እኔ ከሆነ ካሉት ብሄራዊ በዓላት እንደ አንዱ ሆኖ ሁሉም ባለውለታውን የሚያሰብበት ቀን ቢሆን ደስ ይለኛል። ቀኑም አመቱን በሙሉ የሰራነውን አይተን ለአዲሱ አመት ስንዘጋጅ ለዚህ ያበቁንን አስታውሰን አመስግነን ለማለፍ የአመቱ መጨረሻ ቀን ቢሆን መልካም ነው። በተጨማሪም ክረምቱ ተገባዶ አብዛኛው ሰው በተስፋ ወደ በጋ የሚሸጋገርበት መሆኑ፣ እንዲሁም አብዛኛው አርሶ አደርም እሸት መብላት የሚከምርበትና ለምስጋናም የሚያዘጋጀው ስለማያጣ። እንዲሁም ለከተሜው በርካሽ እህል የሚሸምትበት ወቅት እየተቃረበ ስለሚመጣ ብዙው ማህበረሰብ ፈገግታ አይለየውም። ምስጋና ከፈገግታ ጋር ሲሰናሰሉ ያማረ ስለሚሆን-----እያለ ይቀጥላል።
ReplyDeleteዛሬ ከስንት ግዜ በኃላ እንባ አውጥቼ አለቀስኩ። አንተዬ ስንቱን ነገር ረስተነዋል እኮ...
ReplyDeleteshega neew dani kenuma bemengist akalat yiwosen ena achebechiben matsedek newa
ReplyDeleteggg
ReplyDeleteይሄ በእውነት ድንቅ ሀሳብ ነው:: በርግጥ ባለውለታዎቻችንን ማመስገን ይገባናል::
ReplyDeleteየሰው ልጆች ሁላችንም ያደግነው እየኖርን ያለውም ወደፊትም የምንኖረውም በሕይወታችን ላይ የሌሎች ደግነት ተጨምሮበት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስንወለድ ወላጆቻችን ባይንከባከቡን ዛሬ እኔ ብለን የምንጠራውን ማንነታችንን ማግኘት ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህ ከኛ ምንም ዓይነት ጥቅም ሳይፈልጉ ሳይተርፋቸው ከጉድለታቸውም በደግነታቸው ዝናም ሕይወታችንን ላረሰረሱት ሁሉ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ዘላለማዊ ሕይወትን አምላክ እንዲያወርሳቸው ልንለምንላቸው በእርግጥም ደግሞ ታላቅ ምሥጋናን ልንሰጣቸው ይገባል፡፡
ReplyDeleteጥሩ ነው አንዳንዴ ግን እግ/ር ዋጋዬን ይከፍለኛል ብሎ ነው በጐ ማድረግ እኔ በጣም በጐ ያደገ ሰው ያደረገላቸው ሰዎች ግን ጠላት ሲሆኑት አይቻለው ከሰው ምን ይገኛል ይሄንን ሳይ እንደውም በጐ ሰው መሆን ምን ያደርጋል ብዬ ነበር
ReplyDeleteDiakon yemigermih yihin hasab betam yemowedew besewlij nuro tilik bota yalewimnew.BeEgziabherim besewimyemiweded, yeEgziabherin fikir yesewin fikir yemigelts.Engida tekebayinet new.yehig hulu yebelayim.yesewinet megelecha.lesew begonet yihin yemiadergu endalu kifum yeminaderg alenina kezih
ReplyDeleteenimar.Kebego bereket enditelalef kekifu degmoergiman.
Egziabher keseranachewkifu negeroch tekotiben deg neger serten lemebarek yabkan
sharing is not only God's word but also happiness
ReplyDeletehttp://degusamrawi.blogspot.com/
http://www.betedejene.org
http://www.kesisyaredgebremedhin.com
http://www.zeorthodox.org
http://www.mahletzesolomon.com/
ምስጋናውን ካንተ ብንጀምረው ይህን የመሰሉ ግሩም ጽሁፎችንና ሀሳቦችን አንዳች ውለታ ሳትፈልግ ለእኛ በደግነት (ያለ ስስት) በማካፈልህ ላመሰግንህ እወዳለሁ። አዎን። እውነት ነው። እያንዳንዳችን በየፊናችን፣ ሀብታም ሆንን ደሃ፣ ምሁር ሆንን መሀይም፣ ብልህ ሆንን መሃይም፣ ሌላም ሌላም ብቻ ችግር ያጋጥመናል። ከዚህ ከችግሩ የተነሳም ውስጣችን ያዝናል፣ ፊታችን ይጠቁራል፣ ሕሊናችን ይቆስላል፣ ጨጓራችን ይላጣል። ሆኖም ግን። በተስፋ መቁረጥ አፋፍ ላይ ሳለን፡ ችግሩ በርትቶ በሕይወት መኖራችንን በጠላንበት ቅጽበት ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነውና እንደ መላእክተ ብሥራት ሁሉ እነዚህ ደጋግ ሰዎች ያጋጥሙናል። ችግራችን ይቃለላል። አዕምሯችን ያርፋል። ትልቅ ከሚባል ስፍራም ለመድረስ ድልድይ ስለሆኑልን ለዛሬ ህልውናችን ባለውለታና ተጠቃሽ ናቸው። ልናመሰግናቸው ይገባል። ከሁሉ በፊት እነዚህ ደጋግ ሰዎች የሰጠንን አምላክ ልናመሰግን ይገባል። እነዚህ ደጋግ ሰዎች ባይኖሩና ከራስ ጥቅም ይልቅ ለሰዎች ችግር መፍትሄ ለማግኘት የሚታትሩ እነዚህ ግሩማን መፍቀርያነ ሰብእ ባይገኙ ዓለም ዛሬ ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ ልትደርስ ባልቻለችም ነበር። "ጋን በጠጠር ይደገፋል" እንዲሉ በጎ ዋሉልን፣ መልካም አደረጉልን ብለን ልናመሰግናቸው የሚገባን ግን አንደባለታሪኩ በሺዎች የሚቆጠሩ የገንዘብ አስተዋጽዖ ያደረጉልልን ብቻ መሆን የለበትም። ምክርም፣ ስጦታ ነው፣ እውቀትን ማካፈልም ደግነት ነው፣ ማብላትም ቸርነት ነው፣ በጸሎት ማሰብም ልግስና ነው፣ ከዚህም አልፎ ተርፎ፤ በመጽሐፈ ቅዳሴአችን እንደምናገኘው ሊሰጡ ወደው የሚሰጡት የሌላቸው እንኳን ለመርዳት መፍቀዳቸውን ልናመሰገናቸው እና መልካም ጤንነት፣ ረጅም እድሜ፣ እንዲሰጣቸው ልናሳስብላቸው ይገባል። በአጠቃላይ "ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ" እንዲል፣ እኛም ጻቁን ጻድቅ ነህ ብለን ልናመሰግነው፤ ክፉ የሠራወንም ስለክፋቱ መወቀስ ስለሚኖርበት ሥራው መልካም እንዳልሆነ ነግረን ልንገስጸውና ልንወቅሰው ፣ አብነት ይሆኑትም ዘንድ ምሳሌ ልንጠቅስለት ይገባል።
ReplyDeleteላንተ ረጅም እድሜን ተመኘሁ።
መልካም ላደረጋችሁልኝ ብዙናችሁና በደፈናው አመሰግናለሁ።
The day doesn't matter.I definetly share the idea of having "Thanksgiving" on one of the 365 days.I still remember one gentleman's gift (25 cents) when he saw 99% result on my 6th grade report card.He didn't know how happy I was.He didn't know I still remeber that day.I never told him.Mezo (25 cents) meant a lot to me during 1976.Also it inspired me for higher achivement. On the contrary I offered some present to some people yet never heard anything from them.May be these people may learn from this article too.
ReplyDeleteHi Dany, I am your regular reader but today is my first time to comment on your blog. I live in USA Chicago. I share many of the ideas you and your friend unfold to us. However, the way we give thanks should be with cautious; I say this because from my experience, people who helped others become pompous and proud of their good deed instead of accepting the thanks humbly. Their contribution in sombody's life may make them to proud indefinetly than passing the "thanks" to God who used them to help others. In other words it will be " Kentu Wodase" when we publicise their work. I say this becasue I have seen many people entangled with this sloppy "good deed".
ReplyDeleteTo summerize my comment I would say, let us reward them privately instead of publicizing it.
Askale Mariam
I strongly agree with the idea.
ReplyDeleteሁላችነንም ዘወር ብለን እንድናስብ የሚየያደርግ ታሪክ ነው፡፡
ReplyDeleteእኔ የደግነታቸው ውጤት ነኝ............ለቅኖች ምስጋና ይገባል
ReplyDeleteso touchy and I was imagining his feelings at the time and now.
yea I have my own brave man with whom am here today but I always don't feel comfortable since am not in a position to help him but I always tell him and all the ppl around me what he did. and still I don't think it is enough for what he did for me.
thanks dani
Dear dn Daniel thank you so much for this touchy article and very nice idea. I read it with tears for I am also among those who received help from such kind people and reach to the position i am now. The idea is so nice. But, I know there are people who don't need praise and prize from people and need it only from God and even warn those whom they help not to tell to anybody as they are helping him/her/them mentioning that they need the prize only from God. So, if we do what you suggested (public thanks giving) we may with no doubt lose those people. The word of God also teaches us that we shouldn't need praise and prize from others except from Him. What does 'Qegn ejih yemitsetewn gira ejih ayweq' teaches? I also share the concern of Zelalem and the idea by one anonymous who said let's reward them privately... because it may leave a bad scare for the future generation in that people may do good things to get public attention and make a sort of competition. But I strongly support the idea to give thanks privately, like our brother in the article, late alone for those who did good things for us but also for those who did bad for they may be a part and source of our success.
ReplyDeleteIn general, what I learnt from those people who did good for me without any knowledge and relation before their help, is to do the same for others irrespective of race and any other relations. So, as to me it is better to take their good deeds and practice in our daily life, do what we can for them individually and remember them in our daily prayers for they are part of our life. Hence, I suggest no need to declare a separate thanks giving day. This is my view and opinion. Hope Dn Daniel you will give a summary looking from different directions, what are the pros and cons according to the teaching of our Church.
Thank you.
enam balewiletayen endasib adrigehegnal enate tama eraswan mastamemsigebat enan lemastemar bilatesekayech ema wiletashenamlak yikifelishe.
ReplyDeletewow,dink new
ReplyDeleteበጣም የሚደነቅ ሀሳብ ነው። ልክ እንደ ልደት ቀን፣ የጋብቻ ቀን..... እንዲህ ያለ ቀን ቢኖረን እንዴት ያለ ግሩም ነው።
ReplyDeleteselam D/n Dani
ReplyDeleteእርሳቸው ባይኖሩ ኖሮ እኔ አልኖርም ነበር፡፡ እኔ የደግነታቸው ውጤት ነኝ፡፡ መወለድ ቋንቋ ነው ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ያኔ የተነሣነውን ፎቶ በትልቁ አሳጥቤዋለሁ፡፡ ስድስት ጓደኞቼም መጥተዋል፡፡ አንድ ፕሮግራም አድርገን እርሳቸውን ልናመሰግን ነው፡፡ ለቅኖች ምስጋና ይገባል ትሉ የለ እናንተ፡፡
beewenet betam yemiasedeset tarik new ena tebarek!
Hailemeskel Z Maputo
በጣም ግሩም ሃሳብ ነው። እግዚአብሔር በሚያውቀው የኔ የሁል ጊዜ ጸሎቴ ይነስም ይብዛም መልካም ያደረጉልኝን ሰዎች ምንም ባላደርግላቸው እንኳ መልካም ስራቸውን እንዳልረሳ ነው። ብዙ ጊዜ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ስላለፈው አመት በትዝታ ስለሚመጣው ዓመት ደግሞ በተስፋ ማሰባችን የታወቀ ነው። እንኳን አደረሳችሁ የማለት ባህልም አለ። ስለሆነም ጳጉሜ 5/6 የምስጋና ቀን ቢሆን ለሚመጣው አዲስ ዓመትም መልካም ማህበራዊ ትስስርን ለመፍጠር ይረዳል ብየ አስባለሁ።
ReplyDeleteI just called three people who contribute thier part to shape my life and help me to reach where I am now ;immidiatly after i read your article.and this gave me a relife.
ReplyDeleteso giving thanks to people who did good to us or still doing good to us starting from our life partner is a crucial way of making life more enjoyable and happey.
so having a day to thank people is really very very important.
thanks dn.daniel
semone k
የሰው ልጆች ሁላችንም ያደግነው እየኖርን ያለውም ወደፊትም የምንኖረውም በሕይወታችን ላይ የሌሎች ደግነት ተጨምሮበት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስንወለድ ወላጆቻችን ባይንከባከቡን ዛሬ እኔ ብለን የምንጠራውን ማንነታችንን ማግኘት ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህ ከኛ ምንም ዓይነት ጥቅም ሳይፈልጉ ሳይተርፋቸው ከጉድለታቸውም በደግነታቸው ዝናም ሕይወታችንን ላረሰረሱት ሁሉ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ዘላለማዊ ሕይወትን አምላክ እንዲያወርሳቸው ልንለምንላቸው በእርግጥም ደግሞ ታላቅ ምሥጋናን ልንሰጣቸው ይገባል፡፡
ReplyDeletedear diaqon
ReplyDeletei am the one who admire you a lot because of how much you deeply devoted yourself to Ethiopia and our belief.well i found a sentence in our Holy Book though i forgot the other word. i found it in songs verse:32-1. so what is your saying is supportable. Our God told us to honer those your deed Good jobs. i would like to know when u come to dc. let our God be with you all the way you go.
ዳኒ ምስጋና እንደሚገባ ባምንም ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ ይላል ያገሬ ሰው ፡፤እንደው ምስጋናው ቀርቶ አንዱ አንዱን መኮነኑን ቢተው መልካም ነበር።ከዝያ ቀጥሎ ወደ ምስጋና እንሄዳለን።
ReplyDeleteበስመ ሥላሴ
ReplyDeleteጎንደር መድኅኔዓለም ድምጻቸው የሚያምር አባት ነበሩ አሉ እናም አንድ ቀን ቅዳሴ አልቆ ሕዝቡ ከተበተነ በኋላ አንድ ምእመን ተክዞ ያዩታል ምነው ብለው ቢጠይቁት ራቅ ካለ ቦታ እንደመጣና ቅዳሴው ካለቀ በመድረሱ የኒያን አባት ድምጽ ባለመስማቱ እንዳዘነ ነገራቸው ያኔ እኒህ አባት በጣም አዝነው ወደገዳም ሄዱ ይባላል (ታሪኩ አያቴ የነገሩኝ ነው ከጎደለ ወይም ከተዛባ የምታውቁት አርሙኝ)አባቶቻችን እንዲህ ምስጋናን/ሙገሳን ይፈሩት ይሸሹት ነበር እኔ በበኩሌ በተለይ በመንፈሳዊ ስራ ላይ መመስገንን በጣም እጠላለሁ በገሃድ ማመስገንም አልችልም በዚህ የጡመራ መድረክ የማየው ደካማ ጎንም ይህ ነው ሃሳብ ከመስጠት ይልቅ ባዶ ማድነቅ እጅግ ይበዛዋል ለኔ የምስጋና ቀን ምናምን እያሉ ከመፎጋገር አድናቆትን በስራ መግለጥ ይበልጣል እላለሁ ለምሳሌ በዚህ የጡመራ መድረክ ጥሩ ሃሳቦች ሲቀርቡ በዚህ ዘመን ላለን ክርስቲያኖች መካሪ ትሆነን ዘንድ ዕውቀቱን እና ማስተዋሉን ለአንተ የሰጠ ፈጣሪን ከልብ አመሰግነዋለሁ፣ ቱፍ ቱፍ አይይብን ምናምን ከማለት ሃሳቡን በተግባር መግለጥ ይሻል ነበር እላለሁ እናም በጎ ነገርን ስንሰራ ዋጋችንን ከአምላክ ብቻ ብንጠብቅ በጎ ስራ ለሚሰሩም እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይከፍላቸው በበጎ ስራም ያጸናቸው ዘንድ ብንለምን ይበልጣል እላለሁ አባቶቻችን መምህራኖቻቸው የዋሉላቸውን ዉለታ እንዴት ነው የሚከፍሉት ባደባባይ ምስጋናቸውን ባያውጁ በዘወትር ጸሎታቸው ሳያነሷቸው ቀርተው አያውቁም እኮ እናም ለኔ የራሳችን በልብ የማመስገን ባህላችን ይበልጥብኛል
I support zelalem's idea. girum story though.
ReplyDeleteIt is not attractive topic as it is common in Ethiopian culture
ReplyDeleteሴትዮዋ ምንኛ እድለኛ ናቸው!! የሥራቸውን ፍሬ ማየት መቻል ምንኛ ደስ ይላል!! ወገኖቸ ኩረጃም ሆነ….. የማይጠቅመንን ነገር ከመኮረጅ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን እንኮርጅ እና ክፉ ክፉ ነገሮቻችንን እንቀንሳቸው፡፡ ማመስገን ምን ክፋት አለው ክፋስ መሳደብ እና ሀሜት፡፡ እግዜአብሔር እኮ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ነው ያለ፡፡ ምስጋና ደግሞ አንዱ የፍቅራችን መገለጫ ነው፡፡ እናም እናመስግን፡፡
ReplyDeleteሌላው ይቅር ብዙዎቻችን በቢሮዎቻችን፣ በአገልግሎት መስጫ አካባቢዎች፣……. ለሚደረግልን አገልግሎት “አመሰግናለሁ” ማለት ስህተት ይመስለናል፡፡ አንዴ ያጋጠመኝን ልንገራችሁ ቦታው ቲያትር ቤት ነው አንድ ጐልማሳ ወንበሩን ለቆ ስላስቀመጠኝ አመሰግናለሁ አልኩት ፣ ምን አለኝ መሰላችሁ “ እዚ አገር ከመጣሁ በኋላ “Thank you & Sorry “ የሚሉ ቃላቶች ናፍቀውኛል” አለኝ፡፡ እኛ ማለት እስከዚህ ድረስ ነን፡፡
ውድ ዲያቆን ዳንኤል፡
ReplyDeleteከምትጽፋቸው ጽሑፎች እንደተረዳሁት ለአገር ለወገንና ለቤተክርስቲያን ጥልቅ የተቆርቋሪነት ስሜት እንዳለህ እረዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር አይለውጥብህ፡፡ በዚህ ጽሑፍህ ላይ ያሰፈርከው ሀሳብም በጎ ሥራን ለማበረታታት መሆኑ ደስ ያሰኛል፡፡ መልካም የሠራን ማመስገን ባያስከፋም ቅሉ ጉባዔ ሠርቶ ቀን ሰይሞ ማድረጉ ግን ትንሽ ከመስመር የወጣ አካሄድ ይመስለኛል፡፡ ይህ አካሄድ ምናልባት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውስጥ ለሌሉቱ እጅግ የሚያስጨበጭብ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ካለፉ አባቶቻችን ግን ይህንን አልወሰድንም፡፡ አልተማርንምም፡፡ ቀን ተወስኖ መታሰቢያ ሲደረግላቸው ያየነው ደግመ ሕይወታቸውን ሃሳባቸውንና ኑሮአቸውን ፍፁም ለእግዚአብሔር አሳልፈው በመስጠት እና ይህንን ዓለም በመናቅ አርአያ ሆነው ላለፉ እና ቅድስናቸው ለተረጋገጠ ቅዱሳን አባቶቻችን ብቻ ነው፡፡ እንድትረዳልኝ የምፈልገው መልካም የሠሩ ሰዎች አይመስገኑ ማለቴ ሳይሆን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በሚጋፋ ሰዎችን ከመንገድ ጠልፎ ከሚያሰቀር ውዳሴ ከንቱን በሚያስፋፋ መልኩ ከሚሆን ሲሆን ሲሆን ከላይ በጽሑፍህ ላይ በገለጽክልን ምሳሌ ዓይነት ባለጉዳዮች እርስ በርስ የሚያደርጉበት ፤ ከፍ ብሎም ለአርአያነት ሲጠቀስ እና ትብብር ሲያስፈልገው ደግሞ እንደዚህ በጽሑፍ ቢወጣ መልካም ነው፡፡ እንደዚህ ጠለቅ ብለን ካሰብንበት ደግሞ እንደእድል ሆኖ እግዚአብሔርን መለመን እንጂ ማመስገኑ ላይ ሰነፎች ስለሆንን ምስጋና ለሚገባው ለእርሱ እና ለቅዱሳኑ የተሠራልንን ድንቅ ሥራ እያነሳን አንተ ባልከው መልኩ ቢወሳ ለሥጋም ለነፍስም በረከት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
pls watch this about awasa miemenan
ReplyDeletehttp://www.youtube.com/watch?v=3lyuwlLgqdw&feature=related >
I was forget to give "Mesegana" for the person who do me a favor for my life!!! thank you dn.dani may God bless you!!
ReplyDeleteDear Dn. Daniel,
ReplyDeleteI have been you reader since you started the blog. You have given us much knowledge that has helped us improve our spiritual life.
As it is clear to you, currently so many sad things has happening to our church since the last holy synod meeting. The recent news emerging from the church, I think requires coordinated effort to correct the irregularities. Please advise us how we should react to the situation as followers and clergies of the church. We need to plan and work accordingly before the situation has become out of every body's control. Because, I and So many people I have known have become disappointed and angry.
God Bless Our Church and Country.
God bless u dn dany it is good idea
ReplyDeleteእስኪ ስለምስጋና ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርምኝን ላካፍላችሁ
ReplyDeleteተናጋሪዉም አቡነ በርናባስ ነበሩ እናም አንድ ቀን መምህሩ
ሲያስተምሩ ቆዩና ስለአቡነ በርናባስ አነሱ ስለባህሪያቸዉ
ስለስራቸዉ ጥቂት ተናገሩ ሲጨርሱ አቡነ በርናባስ ማይኩን
ተቀበሉና ”አያችሁ ምእመናን ንፉግን ሰዉ እክሌ እኮ ለጋስ ነዉ
ሲሉት ትንሽ እጁ ይፈታለታል እና አሁንም ይህ ሰዉ የተናገረዉ
ለዚያ ነዉ እንጂ እኔ የተናገረዉን ነገር አንዱንም አላደርገዉም”
ነበር ያሉት። እናም በጎ ስራ ልማዱ የሆነ ስዉ ምስጋናን አይወደዉም
ግን ደግሞ አመስጋኙን ትንሽ ሸክሙን ያቀልለታል። ስለዚህ ቢለመድ
መልካም ነዉ።
ጥሩ ነዉ ግን ደግሞ አሁን አሳሳቢ ጉዳይ የምስጋና ቀን ሳይሆን
ReplyDeleteየፀሎት ቀን ነበር ምክኒያቱም ቤተክርስቲያናችን ትልቅ ችግር
ተጋርጦባታል እባክህ ዳንኤል በዚህ በሚመጣዉ ጾም ቀን ይመረጥ እና
በአንተ ብሎግ የቀን የቀኑን ጸሎት ብትጽፍልን
በዉጭም በዉስጥም ያለን ክርስቲያን የሆን ሁላችን
እንጸልይ እግዚአብሔር ቸር ነዉ ይቅር ይለናል። እያነበቡ
መሰዳደቡ መፍትሄ አይሆንም የቀረፍነዉም አንድም ነገር የለም።
እንዴዉ የስድብን ችሎታ ከማዳበር በቀር ችግሩ አልቆመም እሄ
ደግሞ የክርሰቲያን ባሀሪ አይደለም ሰይጣን የዉጊያዉን ስልት
ስለቀየረዉ እንጅ። ኢንፎርሜሽ ለሚጽፉ ሰወች እግዚአብሔር
ብርታትን ይስጥልንና ማንበቡ መከታተሉ ጥሩ ሆኖ ሳለ መፍትሄዉ
ግን ስድብ ሊሆነን አይችልም እስኪ አሁን ጾም ሊገባ ነዉ
ሰይጣንን ነቅተናል እንበለዉና ሰዉም ላልሰማ እያሰማን በህብረት
ብንጸልይና ስድቡም የስከዛሬዉ ይበቃናል ቁና ሙሉ ስድብ ቅንጣት
ታክል ቁም ነገር ላይሰራ አስተያየትም መፍትሄ መጻፍ ነዉ የሚሻለዉ
እኛ የስድብ ክር ስንተረትር ቤተክርስቲያን እየዘመመች ነዉ ሳትወድቅ
እንመልሳት።
Hi Daniel,
ReplyDeleteWe don't need to nominate any day.Why not HIDAR MICHAEL? it was our thanks giving day.It is time for its renascence!!!!
Your bro
Wondesen (London)
ዲ/ን ዳንኤል ሁሌም የምታቀርበው ሃሳብ የብዙዎቻችንን ህይወት ይዳስሳል ብዙ ቁም ነገሮች አሉበት አንድ ጊዜም ቆም ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ ናቸው ማንኛውም ሰው ህይወቱን ሊመረምርበት የሚችልበት አጋጣሚ ይፈጥራሉ እግዛብሄር ብዙ እንድትስራ ጤናና ዕድሜ ይስጥልን ለምስጋና ለወቀሳ ቀን እንሰይምለት ለተባለው ቀን መቁረጥ ሳይሆን ክርስትያን ይቀርታውንም ወቀሳውንም ዛሬ ቢያደርግ ጥሩ ነው እላለው ያቺን አንዳን ቀን ከምንጠብቅ፣
ReplyDeleteበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል ሰላም ለአንተና ለህዝበ ክርስቲያን ይሁን አሜን፡፡
ከላይ አንድ አስተያየት ሰጪ እንደገለፁት በአሁኑ ሰዓት መጀመሪያ የተጋረጠብንን የሰይጣን ፈተና ለመወጣት ምናለ ለፀሎት እንድንተጋ፣ እግዚኦ እንድንል በአንተ በኩል መልዕክቱ ቢተላለፍልን እና ቤተክርስቲያንን ብንታደጋት፡፡ የእኛ መመሰጋገንም ሆነ መወቃቀስ እንዲሁም መልካም መስራት የሚኖረው ቤተክርስቲያን ስትኖር እግዚአብሔር ይቅር ሲለን ነውና ብታስብበት፡፡ አመሰግናለሁ
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የፃድቃን ሰማዕታት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ቤተክርስቲያንን ጠብቃት፡፡ አሜን፡፡
This is generally a good idea. But Dn. Daniel, I would like to draw your attention to our father Abuna Shenouda III said in one of his books ... it goes like this ... do not send your complements and appreciation to those who are good as you are sending Satan/ Devil to tempt that good man ... when I see it from this angle, I insist that we need just appreciate those people in the heart and show in deeds rather than sending words of appreciation in front of people and I also feel that it is their deed that shines their personality apart from what we talk about them ... on the other hand, the bible on Proverbs 31:20 states that a husband needs to talk about the good of his wife in front of the public ...that is why I want to say, it is generally a good idea but specifics are debatable
ReplyDeleteYes it is good idea !
ReplyDeleteAwgichew