በተአምረ ማርያም መግቢያ ላይ «የምሥር ዕጣ ከምትሆን ከመዓልቃ» የተገኘ መሆኑን ይነግረናል፡፡ «ምሥር» የሚላት ግብጽን ነው፡፡ ዓረቦች ግብጽን ምሥር ብለው ነው የሚጠሯት፡፡ ግብጽ የሚለው ስያሜ ከግሪኩ ስያሜ የመጣ ነው፡፡
መዓልቃ ዛሬ በአሮጌው ካይሮ የምትገኝ ቦታ ናት፡፡ ከ12ኛው መክዘ ጀምሮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ መንበር ሆና ነበር፡፡ አብርሃም ሶርያዊም የነበረው እዚያ ነው፡፡ ብዙ አባቶቻችን ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዙ የእስክንድርያውን ፓትርያርክ ለማግኘት ይመጡባት ነበር፡፡ በዚያም ብዙ የኢትዮጵያ መነኮሳት ስለነበሩ በአካባቢው ቤተ ክርስቲያን ነበራቸው፡፡ እስከ አሁን «አል ሐበሽ» እየተባለ የሚጠራ የራሳቸው መቃብርም ነበር፡፡ አሁን በዐረብኛ «ሙዓለቃህ» ትባላለች፡፡ በቦታው የተንጠለጠለችው ቤተ ክርስቲያን እየተባለች የምትጠራ የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን አለች፡፡
Girum wietu.
ReplyDeleteegziabeher kante gar yihun.
ReplyDeleteDani please such a new thing
ReplyDelete