መቼም አለማውቀን የመሰለ ደግ ነገር የለም፡፡ ዕንቅልፍ ለመተኛት፣ ሃሳብን ለመጣል፣ ከጨጓራ በሽታ ለመዳን እና ፀጉር ሳይነጭ እንዲኖር ለማድረግ ትልቁ መፍትሔ አለማወቅ ነው፡፡
ላላወቀ ሰው ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡ ወንዞች ይፈስሳሉ፣ ነፋሳት ይነፍሳሉ፤ ፀሐይ ትወጣለች ፀሐይ ትገባለች፡፡ እርሱ ያለበት ዓለም «በዓለም አንደኛ በአፍሪካ ሁለተኛ ነው» እያለ ይጽናናል፡፡ የደረሰበትን ዕድገት የዕድገት ሁሉ መጨረሻ አድርጎ ይመጻደቃል፡፡
እኔ የአባ መቃርስን ገዳም ስጎበኝ እንዲህ እያሰብኩ ነበር፡፡ የዓባይ ነገር አንጀቴን ሲያቃጥለው ከረመ፡፡ እኛ ውኃ ዛሬ መጣ ነገ ሄደ ስንል ግብጾች በየመንገዱ የቀዘቀዘ ውኃ በነጻ ለመንገደኛ ያድላሉ፡፡
የአባ መቃርስ ገዳም 3000 ሄክታር መሬት ይሰፋል፡፡ ከዚህ መሬት ውስጥ 1500 ሄክታሩ በእርሻ የተሸፈነ ነው፡፡ ብርቱካን፣ ፓፓየ፣ ሙዝ፣ የወይራ ተክል፣ ቴምር፣ አቡካዶ፣ አፕል፣ የአዝርእት እህሎች አካባቢውን ገነት አስመስለውታል፡፡ ከገዳሙ ወጥተን ከአንድ ጉብታ ላይ ስንቆም የገዳሙን የእርሻ መሬት ለማየት ዓይናችንን አድማስ መለሰው፡፡
አይ ዋልድባ፣ አይ ደብረ ሊባኖስ፣ አይ ማኅበረ ሥላሴ፣ አይ ዳጋ፣ አይ ደቅ፣ ይህን አላያችሁ፡፡ በእናንተ ውስጥ ስንት ወንዞች እንዲሁ ይፈስሳሉ? ስንት የሚታረስ መሬት ተኝቶ ያድራል? የአባ መቃርስ መነኮሳት በረሃውን ገነት ማድረጋቸውን ያየ ሰው የኛ ገዳማት በችግር የሚሰቃዩበት ምክንያት ይጠፋዋል፡፡
የአባ መቃርስ ገዳም ላዕላይን ግብጽ በምግብ እህል ቀጥ አድርጎ ይዟል፡፡ የግብጽ መንግሥት በተደጋጋሚ ገዳሙን ሸልሟል፡፡ እያንዳንዱ በገዳሙ ውስጥ የሚገኙት 120 መነኮሳት እያንዳንዱን የልማት ሥራ በኃላፊነት ይመራሉ፡፡ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ሃያ የነበሩት መነኮሳት ዛሬ 120 ደርሰዋል፡፡
ገዳሙ ከራሱ አልፎ እስከ 800 ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል ከፍቷል፡፡ በተለይም ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ከልዩ ልዩ ተቋማት የሚመጡ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ እየተከፈላቸው ገዳሙን በሥራ ሲያግዙ ይከርማሉ፡፡ ገዳሙ ለተማሪዎቹ ምግብ፣ ልብስ፣ ማደርያ እና ሙሉ የሕክምና ወጭ ይሸፍናል፡፡ ተማሪዎቹ ደግሞ ሙሉ ጊዜያቸውን ለመንፈሳዊ ትምህርት እና ለገዳማዊ ሥራ ያውላሉ፡፡ በዚያው ላይ ለትምህርት ወቅት የኑሮ ማገዣ የሚሆን ገንዘብ ለተማሪዎቹ ይከፈላል፡፡
ገዳሙ እርሻ ብቻ አይደለም ያለው፡፡ የከብት ርባታውን ለመጎብኘት እኛ በመኪና ነው የሄድነው፡፡ ከስፋቱ የተነሣ በእግር አይደረስበትም፡፡ እኛ ስንደርስ ሁለት መቶ ከብቶች ታልበው ሲመጡ ሌሎች ሁለት መቶ ከብቶች ደግሞ ለመታለብ እየወጡ ነበር፡፡ ገዳሙ ወተት፣ እርጎ እና ቅቤ ከግብጽ አልፎ ለሰሜን አፍሪካ እና ለጀርመን ያቀርባል፡፡
አስጎብኛችን ከከብቶቹ በረት አወጡንና ወደ አንድ ፋብሪካ ወደሚመስል ቦታ አስገቡን፡፡ የወተት ማቀናበርያ ፋብሪካ ነው፡፡ «እባካችሁ ቅመሱልን» አሉና እርጎውን አቀረቡልን፡፡ ምን ያስቆረጥማል ልበላችሁ? እናንተ ክፍት ቦታውን ሙሉት፡፡ በትንንሹ ታሽጎ ለገበያ ከሚቀርበው እርጎ ነበር ያቀረቡልን፡፡ ፋብሪካውን የሚመሩት መነኩሴ በሞያው የተመረቁ መሆናቸውን ነገሩን፡፡
አሁን ወደ በግ እርባታው እናምራ፡፡ ነጫጭ በጎች በረቱ ሞልተው ተኝተዋል፡፡ አስጎብኛችን፡፡ «ድምፅ አታሰሙ አሁን የእረፍታቸው ሰዓት ነው» አሉን፡፡ አቤት የገዳም በግ ታድሎ እዚያም ጸጥታ ይከበርለታል፡፡ የአዲስ አበባ በግ እርሱም ሲጮኽ እኛም ስንጮኽበት እንደምንውል ባዩ አልኩ በልቤ፡፡
ከዚያ ወጣንና ዶሮ እርባታው ውስጥ ገባን፡፡ የዶሮ ሥጋ እና ሽንቁላል በማቅረብ በሰሜን ግብጽ የአባ መቃርስን ገዳም የሚስተካከለው የለም ይባላል፡፡ የእርባታው ቦታ አንድ ስታድዮም ያክላል፡፡
ምን ይኼ ብቻ፡፡ መነኮሳቱ ፉድጓድ ቆፍረው በሰው ሠራሽ ኩሬ ዓሣ ያረባሉ፡፡ ጉብታው ላይ ሆነን በሩቅ ጎበኘነው፡፡ የጣና ገዳማት ይህንን እንኳን አላዩ፡፡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር፡፡ እነ ክብራን፣ እነ ዳጋ፣ እነ ናርጋ፣ እነ ደብረ ማርያም ጣናን ከሞላው ዓሣ መቼ ያተርፋሉ? ይኼው እዚህ ሐይቅ በሌለበት ሐይቅ ተሠርቶ ዓሣ ይመረታል፡፡
የገዳሙ መነኮሳት ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ለጸሎት የሰበሰባሉ፡፡ እስከ ጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይቀጥላል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላ የሥራ ሰዓት ነው፡፡ ገዳሙን ያቀኑት መታ አል ምስኪን ዘመናዊ አሠራሩን ከአውሮፓ ምናኔያዊ ሕይወቱን ከኢትዮጵያ ወስደው ማዋሐዳቸው ይነገራል፡፡ በገዳመ አስቄጥስ በልዩ የምናኔ ሕይወት ይኖሩ ከነበሩት ከኢትዮጵያዊ ገብረ ክርስቶስ (አብዱል መሲሕ) ጥንታዊውን የምንኩስና ሕይወት ወስደዋል፡፡
አባ መታ በአንዳንድ የግብጽ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት በሚያዩት የቅብጠት ሕይወት ያዝኑ ነበር፡፡ «ምናኔን ኢትዮጵያ ሄደን መማር አለብን፡፡ አሠራርን ደግሞ እነርሱ እዚህ መጥተው መማር አለባቸው፡፡ እኛም ስንፍናቸውን እነርሱም ቅብጠታችንን ከወረሱ ግን አደጋ ነው» ይሉ ነበር ይባላል፡፡
እውነትም ብዙ የግብጽ ገዳማትን ስጎበኝ በታሪክ የምናነበው ጥንታዊው የግብጽ የምናኔ ሕይወት እንጥፍጣፊው ብቻ ይታያል፡፡ እንዲያውም የነ አባ ገብረ ክርስቶስ የምናኔ ሕይወት ነፍስ ባይዘራበት ኖሮ ሁኔታው ከዚህም ይከፋ ነበር፡፡ ገዳማቱ ራሳቸውን እንዲችሉ፣ ያለ ፈቃድ የሚመጣውን ድህነትም እንዲቋቋሙ ማድረጋቸው፤ የአካባቢው ንጽሕና እና የቅርስ አያያዛቸው፣ መነኮሳቱ የዚህን ዓለም ትምህርት ተምረው፣ በተለያየ የመንግሥት ኃላፊነትም ሠርተው ዓለምን የተው መሆናቸው ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡
በተቃራኒው ግን የጸሎት እና የምናኔው ሕይወት የሚገኘው በኛ ገዳማት ነው፡፡ አባ እንጦንስ እና አባ መቃርስ ተመልሰው ቢመጡ ልጆቻቸውን የሚያገኙት ኢትዮጵያ ነው፡፡ አራዊቱን እና አቃርብቱን ሳይፈሩ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ቆራጥነት በየበረሃው ከመላእክት ጋር ሲነጋገሩ ውለው የሚያድሩ ብዙዎች ናቸው፡፡
ግብጽ ውስጥ ባሕታውያንን ማየት ብርቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ በረሃዎች ግን በባሕታውያን የተሞሉ ናቸው፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ «የተሰወሩ ቅዱሳን በግብጽ አሉን?» ተብለው ሲጠየቁ «ግብጽ ውስጥ እኛ የማናውቃቸው የተሠወሩ አባቶች የሉም፡፡ ይኖራሉ ብዬ የማምነው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው» ብለው መልሰዋል፡፡
ከግቢው ተሳልመን ስንወጣ እኛ ኢትዮጵያውያን ይህንን ዓለም የሚቀናበትን ያልተለወጠ መንፈሳዊነት ጠብቀን ገዳሞቻችንን የምናለማው መቼ ይሆን? እንል ነበር፡፡ «በገዳሞቻችን ጎብኝዎች እየዘለሉ ወደ መናንያን በኣት መግባታቸውን የሚያቆሙት መቼ ይሆን? የዓለማውያን እና የመናንያን ድንበር የሚለየው መቼ ይሆን? ለሱባኤ የሚሄዱ ምእመናን ተገቢ ማረፊያ አግኝተው፤ የመናንያኑን በኣት ሳይረብሹ ነገር ግን ተገቢውን አገልግሎት አግኝተው የሚመጡበት ዘመን መቼ ይሆን?» እንል ነበር፡፡
ቁጭት ብቻ ሆነ፡፡
ግብፅ፡ውስጥ ባህታውያን ማየት ብርቅ ነው።ዳኒ በጣም ደስ ይላል አንተ ግን የምለው የለኝም አምላክ ከነ ቤተሰብህ ይባርክህ።
ReplyDeleteብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ «የተሰወሩ ቅዱሳን በግብጽ አሉን?» ተብለው ሲጠየቁ «ግብጽ ውስጥ እኛ የማናውቃቸው የተሠወሩ አባቶች የሉም፡፡ ይኖራሉ ብዬ የማምነው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው» ብለው መልሰዋል፡፡
ReplyDeleteMENFESAWINETEN HEGE BETEKRSTIYANEN BEMAYKAREN MELKU ZEMENAWINET YASFELGATAL !!!
ReplyDeletei wish i didn't read it.i feel sory for us
ReplyDeleteግብጽ ውስጥ ባሕታውያንን ማየት ብርቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ በረሃዎች ግን በባሕታውያን የተሞሉ ናቸው፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ «የተሰወሩ ቅዱሳን በግብጽ አሉን?» ተብለው ሲጠየቁ «ግብጽ ውስጥ እኛ የማናውቃቸው የተሠወሩ አባቶች የሉም፡፡ ይኖራሉ ብዬ የማምነው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው» ብለው መልሰዋል፡
ReplyDeleteenesun alematatachin egiziabher ymesgen
ውድ ዲ/ን ዳንኤል፤ እኛም ኃይላችንን አስተባብረን፣ ልዩነቶቻችንን እጥብበን፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለምነን ብንንቀሳቀስ እንደነሱ የማንሠራበት ምንም ምክንያት አይኖርም። በማህበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት እስካሁን ብዙ ሥራዎችም ተሠርተዋል። ከዚህ ጉብኝትህ የቀሰምከውን ዕውቀት መሠረት በማድረግ እየተገበሩ ያሉቱ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚጠናከሩበትን መንገድ መቀየስ እንደማያዳግትህ እተማመናለሁ። እኛም እንዳንተ በቅናት እና በቁጭት ተብከንክነን እንዳንቀር ገዳማቱን የምንራዳበትን ሁኔታ አመቻችልን። አንድ ሚሊዮን የሚሆኑትን የብሎግህ ተከታታዮች ብታስተባብር ታላቅ ሥራ ሊሠራ ይችላል።
ReplyDeleteመድኀኃዓኒለም በእውነት አንተን አዚያ ወስዶ እኛን እዚህ አቁሞ ምንም ድንበር ሳያገግደን የያሀውን አየን፡፡ እግዚአብሔር የስጥልን ቃለ-ህይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን ዳኒ የአባ እንጦንስና የአባ መቃርስ በረከታቸው ይደርብን:: በግብጽ ያሉት መነኮሳት በእውነት በጣም ያስቀናሉ:: ያ ሁሉ ፈተና እያለባቸው ፈተናውን ተቋቁመው በመንፈሳዊ ሕይወት ጠንክረው ይህንን የሚያስደንቅ ልማት ማልማታቸው ትልቅ ትምህርት ሰጪ ነው::
ReplyDeleteአወ ቁጭት ብቻ፡፡ የኛ ነገር ከቀን ቀን እየተባባሰ መጣ፡፡ቤተክርስቲያናችን አስፈሪ ውጥረት ነገሰባት፡፡ አሁንስ ማነው ተስፋዬ……….. በእውነት ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰወሩ አባቶች አሉ ? ምነው ታዲያ እንዲህ ፈተናችን ሲበዛ ዝም አሉ? በየቦታው ፈራርሰን ልንቀር እኮ ነው፡፡ አቤቱ ስለ አንድ ቅዱስ ብለህ እንኳን አትምረንም? ጆሮአችን መልካም ነገር መስማትን ናፈቀ፣ አይናችንም………. ፣ እኛም የእርግማን ልጆች እንደሆንን እንድናስብ ሆን፡፡ አሁንስ ማነው ተስፋዬ………… የአባታችን የአባ በርናባስን ሞት በሰማሁ ጊዜ ባዶነት ተሰማኝ…….. ብቻችንን/ክፋዎቹ/ ልንቀር ነው እንዴ? አባታችን ዛሬ የቀብር ስነስርዓታቸው ይከናወናል፡፡ አቤቱ ነፍሳቸውን በሀሴት ተቀበልልን፣ እኛንም ይቅር በለን፡፡
ReplyDeleteቃል ሕይዎት ያሰማልን!
ReplyDeleteብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ብለው መልሰዋል፡፡....
ማህበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ላይ የማብቃት ስራ ሲሰራ ብዙዎችችን ግቢላይ ትንሹን ከማዎቅ (ከቲዎርይ የዘለለ) መንፈሳዊነት የለንም {መንፈሳይ} አልነበርንም ስንዎታም ጠፋን መንፈሳውይ ግዴታችንም ረሳነው ፣ አሁን ያሉን አባቶች ላይም ሙያውይ ትምህርቶችን በስልጠና መልክ በገዳማቸው ተግባር ላይ አትኩሮ ማሰልጠን፣ ማስጎንኘት ከሚጠፋው ብዙ ሚሊዮኖች ትንሹን አንድሰሩበት አንድያደርጉ ማሳሰብ አናም አንደተረዳሁት ይህን ያህል ትልቅስራ ካሉን ገዳማት ዉስጥ አንዱን በኃላፊነት አንተም ተንቀሳቅሰህበት ተሞክሮ ማሳየት።
ፀጋውን ያብዛልህ!!!
Dn. Daniel you have presented in a very good manner. You are leading us to create awareness and motivations.
ReplyDeleteI think now you are greatly an influential person. You can exercise some practical leadership for us and we can follow that.
As per you see there in Egypt, please organize us and make some innovative additions to our monasteries. Please create some discussion topics either to redirect some motivations to Mahbere Kidusan Gedamat ena Adbarat Kifil or use that motivations directly on your own coordinating activities to develop our monasteries without affecting their spiritual serenity.
May God Bless you!
May Holy Virgin Mary with all the time!
Amen!
Egziabher Amlak agolglotachin yibark, wendmachinin degmo amlak Egziabher Agolglotihn yibarkilh antenim yabertah, Amen
ReplyDeleteሰላም ውድ ወንድሜ ትላንት ከባለፈው ካቀረብኸው ላይ እንደ አስተያዬት ቢጤ ሰንዘር አድርጌ ነበር። ከባለፈው ጽሑፍህ መነሻ አድርጌ እንደ ግብጻውያን እኛም ገዳማቶቻችንን እንዴት እንታደጋቸው የሚል ጠቅለል ያለ ሊያነሳሳ የሚችል ጽሑፍ ጠቆም ብታደርገን የሚል ነበር። ዛሬ ጭራሽ የበለጠ---ውስጣዊ ቁጭት የሚቀሰቅስና ምን ነክቶን ይሆን የሚያሰኘውን ቅኝትህን አሳየኸን። እግዚአብሔር ይባርክህ። አሁንም ተጨማሪ አስተያየት አለኝ። በአሁኑ ስዓት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ እያነበበው ነው። አንብበን መሄድ ብቻ ወይስ እንደዚህ ያሉ ማለፊያ ነገሮችን አዳብረን፤ እንዴት ወደ እኛ እናምጣቸው የሚል ሐሳቦችን አንሸራሽረን ለሚመለከተው የቤተክርስቲያኒቱ አካል የመነሻ ፕሮጀክት ዶክመንት ማዘጋጀት?እርግጠኛ ነኝ ይህን ጽሑፍ ያነበበ ሰው ያገኘውን እውቀት በምን መልኩ ለገዳማት ላበርክት የሚል ሃሳብ ይጭራል። እናም ከዚህ ልምድ በመነሳት በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ክፍት የመወያያ ብትሰጠንና ሁሉም ያለውን ቢሰነዝር። እናስታውስ የሃገራችን ገዳማት ዘርፈ ብዙ ሊሰጥ በሚችደል የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። ላካባቢው ማህበረሰብ ከመንፈሳዊ አግልግሎታቸው ባሻገር ለሞዴልነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የልማት ማዕከል መሆን ይችላሉ። ይህም በግብርና፤በተፈጥሮ ሃብት፤እንዲሁም አነስተኛና ጥቃቅን እንዱስትሪዎች ማቋቋም ይቻላል። ዋናው ነገር እንዴት እንሁድበት? ከየት ይጀመር? ምን አይነት መመሪያ ይዘጋጅ? የገዳማዊ ህይወትን መኖር የፈለጉትን አባቶቻችን እንዴት እንለይ? እንዴት አድርገን ከአስመሳዮች እንታደጋቸው? ገዳማቱ ባሉበት አካባቢ ምን አይነት ይልማት እስተዋጵኦ ማድረግ ይችላሉ? ገዳማትን ባለባቸው የችግር አይነቶች መለዬት እያለ ይቀጥላል------------------------
ReplyDeleteit is a good looking for future of our monasteries. we have to learn their way of development and self reliance..and adding to our way of pursing our spiritual life . if we copy it by preserving our heritage and way of living it will be a future spiritual kingdom anyone wants to be part.
ReplyDeletewhat can I say about this amazing naration and development activity of Aba Mekarse monastery which can be a model for our monasteryies of 21st century.Relly God be with u and urs. I wish some one or I think u urself will send this as report prepared by Dn.Daniel sented to visit this monastry to show us or see what we lack....Aphrahat says much is expected from who has got much....blessings of these fathers be up on all of us who wishes good....I write this b/c I can't keep silent as usuall after reeding....
ReplyDeleteCan you tell us more about the monastic life there? Please, please, please....
ReplyDeleteDn. Dani Egiziabeher yibarkih, kalhiwot yasmah, tadileh, egnam bereketu yideresen. Egnam le betchrstian yemiasebu papasaten yeminagegnew mechie yihon? Ebakachihun tegeten entseley.
ReplyDeleteBereketun yadilen lehulum hizebe chrstian
Z from Botswana
እግዚአብሔር ይስጥልን ዳኒ፡-
ReplyDeleteእናንተ በአካል ተገኝታችሁ የተሳለማችሁትንና በዓይናችሁ ያያችሁትን ነገር እኛም በዓይነ ህሊናችን ማየት በሚያስችለን መልኩ ስላቀረብክልን እኔ ልክ እዛዉ ተገኝቼ እንደተመለከትኩትና እንደተሳለምኩት ነዉ የቆጠርኩት። ይህ በእዉነቱ ትልቅ ጥበብና አገልግሎት ነዉ። ላለፈዉ ብንቆጭም .... የወደፊቱን ማን ያዉቃል ... እርሱ ከፈቀደ ሁሉ ነገር ይሆናል .. እስቲ እኛ የሚጠበቅብንን እናድርግና ያለዉን ጠብቀን ለትዉልድ እናስተላልፍ። ላለፈዉ ስንቆጭ ያለንን እንዳናጣ!
ወንድምህ ከእንግሊዝ
ዓባይ ሊገደብ ነው፡ቁጭቱ ሊያበቃ ነው፡፡ የገዳማቱ ችግር መቼ ይቆም ይሆን?እስኪ እንጸልይ፡በሥራ ታታሪ ፤በመንፈሳዊ ሕይወት ብርቱ የሆኑ መናንያንንፈጣሪያችን እንዲያድለን፡፡ዲ,ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteሰሎሞን ደጀኔ ከኮምቦልቻ
ቃለ ህይወት ያሰማልን ለእኛም ገዳማት እግዚአብሄር ቀን ያውጣላቸው እውነተኛ አስተዳዳሪ ይስጣቸው
ReplyDeleteI like the way you put "በተቃራኒው ግን የጸሎት እና የምናኔው ሕይወት የሚገኘው በኛ ገዳማት ነው፡፡ አባ እንጦንስ እና አባ መቃርስ ተመልሰው ቢመጡ ልጆቻቸውን የሚያገኙት ኢትዮጵያ ነው፡፡ አራዊቱን እና አቃርብቱን ሳይፈሩ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ቆራጥነት በየበረሃው ከመላእክት ጋር ሲነጋገሩ ውለው የሚያድሩ ብዙዎች ናቸው"
ReplyDeleteWhich one you guys perfer, lemat or pray, wether we eat lot or one bread everything will pass, however lemat is better ??????????????????? this days money become very important , no money ??? no one will even say hi ,,,,,"money makes man "
Dn cherinet mn
ባለፈው ዓባይን በካይሮ ጽሑፍህ ላይ
ReplyDelete«ሕዝቡኮ ልጆቹን «ይገደብ ዓባይ» እያለ ስም ሲሰጥ የኖረ ነው፡፡ መሪ አጥቶ ኖረ እንጂ ገንዘብ አልሰጥም አላለም ነበር፡፡ አሁንም ዓባይ ሊገደብ ነው ሲባል በደስታ ነው የተነሣው፡፡ ታድያ አንዳንዶቹ በፈቃዱ መስጠት የሚችለውን በግዳጅ አደረጉትና ምርቃቱን ወደ ርግማን ቀየሩት፡፡
«እንዴት ዝቅ ብሎ የግማሽ ወር፣ ከፍ ብሎ የሁለት ወር የሚሰጥ ይጠፋል? እንዴት ሁሉም እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ይሆናል? ሕዝቡኮ ሀገሩ ነው፡፡ ይሰጣል፡፡ በራሳችን ገንዘብ እንገንባው መባሉም ልብ የሚያሞቅ ነው፡፡ ግን እወደድ ባዮች ፈቃዱን ወደ ግዳጅ፣ ምርቃቱን ወደ ርግማን እንዳይቀይሩት እፈራለሁ፡፡
ዛሬ ደግሞ በዚህኛው
[መቼም አለማውቀን የመሰለ ደግ ነገር የለም፡፡ ዕንቅልፍ ለመተኛት፣ ሃሳብን ለመጣል፣ ከጨጓራ በሽታ ለመዳን እና ፀጉር ሳይነጭ እንዲኖር ለማድረግ ትልቁ መፍትሔ አለማወቅ ነው፡፡ ላላወቀ ሰው ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡ ወንዞች ይፈስሳሉ፣ ነፋሳት ይነፍሳሉ፤ ፀሐይ ትወጣለች ፀሐይ ትገባለች፡፡ እርሱ ያለበት ዓለም «በዓለም አንደኛ በአፍሪካ ሁለተኛ ነው» እያለ ይጽናናል፡፡ የደረሰበትን ዕድገት የዕድገት ሁሉ መጨረሻ አድርጎ ይመጻደቃል፡፡]
እናም አንዳንዴ አጻጻፍህ “ሁሉ አማረሽን ገቢያ አታውጧት” ይሆንብኛል:: ትችት ትችት ትችት...
ሰረቀም፡ ዘረፈም፡ በላም፡ ሸጠም.... ምንም በለው ምን አሁን መንግሥት የወሰደው አቋምና እርምጃ በምንም መልኩ የሚነቀፍ የለውም:: እንኳን ለአባይ ግድብ ይቅርና 75ሺህ ድረስ ለሚገመተው የሰው ልጅ ህይወት እልቂት መንስኤ ለነበረው ለባድሜ ጦርነትም አዋጥተናል:: ያኔም ቢሆን ኑሮ ደልቶ ሁሉ ተሟልቶ አይደለም፤ ከጉሮሮ ነጥቆ ከልጁ አፍ መንትፎ ነው የሰጠው የሀገርህ ሰው:: እኔ አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ስብከትህ ላይ “አባይ ዳር ሽንብራ እንደ መዝራት አባይ አባይ እያልን አታሞ ስንመታ እንኖራለን” ስትል ሰምቻለሁ:: ታዲያ ምነው አሁን አንተ ደግሞ የተቃውሞ አታሞ መምታት ጀመርክ? አልወደድኩልህም ሁልጊዜ ትችትህን ብቻ ማየት:: ተቺ መሆን ብቻውን መፍትሔ አይሆንም:: ሃሳብህን ተቃወምኩ እንጂ ስብዕናህን እንዳልነካሁ ትረዳኛለህ መቼም::
dani meni menew semonun ye-sinodosu sebseban temelketo wektawi zeana eyale menew zemetan meretik ? ahun degemo abune BERNABAS siyarfu menew daniye! dani min tilaleh ?
ReplyDelete'አባ መታ በአንዳንድ የግብጽ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት በሚያዩት የቅብጠት ሕይወት ያዝኑ ነበር፡፡ «ምናኔን ኢትዮጵያ ሄደን መማር አለብን፡፡ አሠራርን ደግሞ እነርሱ እዚህ መጥተው መማር አለባቸው፡፡ እኛም ስንፍናቸውን እነርሱም ቅብጠታችንን ከወረሱ ግን አደጋ ነው» ይሉ ነበር ይባላል፡፡ "
ReplyDeleteዳኒ እነረሱስ ምናኔያችንን ወረሱ እኛስ መቼ ይሆን አሰራራቸውን የምንወርሰው ??????
TESFAHUN(TES)
«ምናኔን ኢትዮጵያ ሄደን መማር አለብን፡፡ አሠራርን ደግሞ እነርሱ እዚህ መጥተው መማር አለባቸው፡፡ እኛም ስንፍናቸውን እነርሱም ቅብጠታችንን ከወረሱ ግን አደጋ ነው»
ReplyDeleteመልካም አባባል!
ቃለ ህይወት ያሰማልን! ዲ/ን ዳንኤል
ራስህን ትችት ብለህ የጠራህ ፣ ለመሆኑ የዳንኤልን ጽሁፍ በደንብ አንብበኸዋል? ምኑ ላይ ነው ተቃውሞው ? ትገርማለህ መጀመሪያ በደንብ አንብብ ፡፡ ማንም ቢሆን መገደድን አይፈልግም፡፡ ጽሁፋም መገደድን ነው የተቃወመ፡፡ ስለተጨበጨበ ብቻ አናጨብጭብ፣ ለምን እንደተጨበጨበ ይግባን፡፡
ReplyDeleteመቼም አለማውቀን የመሰለ ደግ ነገር የለም፡፡ ዕንቅልፍ ለመተኛት፣ ሃሳብን ለመጣል፣ ከጨጓራ በሽታ ለመዳን እና ፀጉር ሳይነጭ እንዲኖር ለማድረግ ትልቁ መፍትሔ አለማወቅ ነው፡፡
ReplyDeletethat is true...
ቁጭት ብቻ ሆነ፡፡ ayhonim!!!ahun yetesellefutin yetehaddiso yewust arbegnochin Egzi'abheer becherinetu siystagisilin Mahibere Kidusanin yizen be EGZI'ABHEER cherinet, be KIDUSAN hullu ammalajinet tagizen ke kuchit indeminweta irgitegna negn!!! yebetekiristian telatoch gin hullem lelimat sayhon letifat indemaytegnu ahun begilt iyyayen new. betekiristianin lematfat kemechewum gize belay ahun iyyeserru new. be irgitegninet gin ayatefuatimina igna ye Tewahedo lijoch be ANDINNET LELIMAT KETENESAN TARIK YIKKEYERAL! ATITERATERU IGNA AHUN YALLENEW TIWULID TARIK MEKEYYER INNICHILALEN! ahun mi'imenu MK le betekiristian limat lemmiyadergew tirri fettan mels mestet lay new. le tehadiso kitregnochim ye igir isat yehonew yihe haq new. neger gin, YETEWAHEDO LIJOCH, tenesten innisira! IGZI'ABHEER fekdollinalinna tenesten innisiraaaaaaaaaa!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteDn Daniel: Thank you for the great article/observation. Qale hiwot yasemalin.
ReplyDeleteOne has to be critical of himself to make a change or grow. If not, there is no motivation for growth. That is how the West developed itself.
አቶ ትችት (above)-that is how you should read the articles. Do Not make it personal. Dn Daniel is presenting a "critical view" in the topic. You take it as a whole and apply it for a +ve change.What do you think?
God bless, Peace
YeAwarew
እኔም ግብጽ ገዳማት የጎበኘሁ ግዜ የተሰማኝ ነገር ብዙውን ተናገርከው….....በነሱ ልማት ስኮራ በእኛ ገዳማት የጸሎት ህይወት ደግሞ እጅግ ኮራሁ.... አቡነ ሽኖዳ በጉባኤ ሲያስተምሩ ብዙ ጊዜ አብዱል መሲህ (ገብረ ክርስቶስን) በምናኔ ህይወታቸው ይጠቅሳሉ እድሉን አግኝተህ ስለርሳቸው ብትጠይቃቸው አቡነ ሽኖዳ ስለርሳቸው የሚነግሩህ ብዙ ነገር አለ።
ReplyDeleteግን ያዘንኩት...ግብጻውያን ሰለ አብዱል መሲህ(አባ ገብረ ክርቶስ) ከፎቶአቸው ጋር መጸሀፍ ጽፈው ገድላቸውን አስቀምጠዋል። እኛ ግን አብዛኛው ኢትዮጵያውያን የርሳቸውን ገድል እንኳን ያማያቅ አለን። ታሪካቸው እጅግ የሚያስገርም ነው። የርሳቸውን የህይወት ታሪክ ከፎቶኧው ጋር አስደግፈህ በዚሁ አምድ ማስቀመጥ ብትችል ደስ ይለናል።
ስለገዳማቶቹ እንዳልከው “…የሚታየው ነገር ሁሉ እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭን ነው.” በህሊና ከሚታሰብ በላይ ….የገዳማቱ እድገት ንግግር አይገልጸውም እንደው ዝም ጭጭ እሚያስብል ነው.....እኔ ቦታውን ባየሁ ጊዜ...የእኛ የፈረሱት ገዳማት ቅዳሴ እንኳን የመቀደሻ ጧፍ አጥተው የተዘጉት ቤተክርስቲያኖች እያሰብኩ ሁለቱን ማነጻጸር እማይሞከር ነበር ግን....ግን....በመከራ ውስጥ ያልተቋረጠው የቅዱሳን አባቶቻችን የጸሎት ብርታት....መከራ ያልገታው ....የአባቶች መንፈሳዊ ህይወት.....ያለምንም ማጋነን ከግብጻውያን ጋር ሲወዳደር እሩቡን እንኳ አይሆንም... አንተ እንደጻፍከው የግብጽ አንዳንድ ገዳማት.."....ቅብጠት……” የሚለው ቃል ይገልጸዋል።
በአጽዋማት፣ በጸሎት…..ማን እንደነ ተክልዬ ገዳም……..ለግብጻውያን የደረሊባኖስ ስረአት ቢሰጣቸው እንደማይችሉት በአፌ ሙሉ እናገራለሁ።
የገዳም መሪ የሆኑ አበምኔቶችና እመምኔቶች ይህንን ታሪክ እንዲያውቁት ቢደረግ በመንፈሳዊነትና በልማት ቁጭት ሊነሳሱ ይችላሉ፡፡ እኛ ለገዳማዊያን ፈተናና መሰናክል የሚሆን ሥራ ከመስራት እንድንቆጠብ እግዚአብሔር ይርዳን እንጂ በቤተ ክርስትያናችን ያለው የገንዘብ ችግር አይደለም ገንዘብማ ሞልቶ ግለሰቦችም ጭምር እየከበሩበት ነው፡፡
ReplyDeleteአምላካችን በደላችንን ይቅር ይበለን፡፡ የበደል ብዛት ይህን ሁሉ አምጥቶብናልና፡፡
መሰረት ከሀዋሳ
Dn Daniel Egziabher yebarkeh yeagelgelot zemenehen yabezaleh. Beterefe yemelew negre legna abatoch egziabher leb yestachew....
ReplyDelete@ ትችት አንድ አኔ የማዉቀውን አዉነት አንሆ
ReplyDeleteየአንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ለአባይ መዋጭሆ ተብለዉ ተሰባሰቡ ለትምህርት ቤቱ ርአሰ መምህር ፻% ያዋጡ ተብሎ መመሪያ ወርደ መምህራኑ ደግሞ ፪፭% ፍንክች አንልም ተባለ። ዘገባላይ ፻% ተብሎ ተዘገበ መምህራኑን ሌላ ስብሰባ ተጠርቶ ለማግባባት ሲሞከር ፬ ዓመት ለመክፈል አሺ ታባለ ፪ ዓመት አማራች መጣ አልተቀበልነዉም ዎዳጀ ይህን ምን ትለዋለህ??? ማን ያዉራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ። አናም ድርሻ ካለዎት አሰራራችሁን ፈትሹ ከለልዎትም አዉነቱን ይዎቁ።
ዳንኤል የምፅፋቸው ፅሁፎች የመረጃ ያላችዉ መሆኑን በዚህ ብች ሳይሆን ብዙ ፅሁፎchu lay mawok chyalehu ende 171 hospital atawugabn kehone besterer
ከግቢው ተሳልመን ስንወጣ እኛ ኢትዮጵያውያን ይህንን ዓለም የሚቀናበትን ያልተለወጠ መንፈሳዊነት ጠብቀን ገዳሞቻችንን የምናለማው መቼ ይሆን? እንል ነበር፡፡ «በገዳሞቻችን ጎብኝዎች እየዘለሉ ወደ መናንያን በኣት መግባታቸውን የሚያቆሙት መቼ ይሆን? የዓለማውያን እና የመናንያን ድንበር የሚለየው መቼ ይሆን? ለሱባኤ የሚሄዱ ምእመናን ተገቢ ማረፊያ አግኝተው፤ የመናንያኑን በኣት ሳይረብሹ ነገር ግን ተገቢውን አገልግሎት አግኝተው የሚመጡበት ዘመን መቼ ይሆን?» እንል ነበር፡፡ቁጭት ብቻ ሆነ፡፡
ReplyDeleteDn.Dani Egziabher yestiln yehenin tshufe saneb weste beande neger eyazene be Israel ager lay 7 gedamat sinorun lezawum ketkur yeafrica hizboch egna nen bezu (gedamat ) bezam west wede 60 yrmitrgu menekosatoch alun yedear sultan chger endale entewewuna beleloch gedamatoch min eytesera new ?? limatawi honu leloch serawoch ?Yemenkosatus nuro?gizeyachewun endet yasalfalu?.... yehenin say betam ebesachalehugn lelaw kerto besamin 2 ken lemkedes endet endmiselechu....endhu negestatu swrtew yasekemtut betoch alu ensun yakeraunale eyandandu menkuse bewr 1350 ye israel shekel demoz eytekfelachew beamet yelibs 1000 dolar eytkeflachew kuch belo menor kirstna ansulin belo sewu simeta 120 dolar kifelu yelalu esum kekidame ena ehud weym bealat huno kidase yale ken kalehone ayhonim yelalu leserg degmo 400 dolar kifelu yelalu ere sentu yenegstatun nefis yemarilin ena kuch bilew endibelu adergewachewal betam new yemigermew gizeyachewun eko kuch belew tesebasbewu bemawerat new yemiyasalfut wey kuankua aymaru wey edetibeb ayseru wey yegedam metedadriya bilew ayasebu min libelh wey gud sent yemisera eyale botaw altefa gize alatu lelaw biker endhu yaleminm sera yetkemte sefi bota eyale bezu Ethiopiawi hitsanatoch alu lenesu enkuan beza bota lay kinder garden mekfat yechalal lijochu berasachew kuankua afachewun enkuan endaykeftu ye tikur eras asetyayet ankeblim yelalu ere sentun libel Aneta endalut''Aye Jerusalem minew bemtshaf bet endawekush bekerw nuro '' yasegnal enam meche yehon እኛ ኢትዮጵያውያን ይህንን ዓለም የሚቀናበትን ያልተለወጠ መንፈሳዊነት ጠብቀን ገዳሞቻችንን የምናለማው መቼ ይሆን? እንል ነበር፡፡ «በገዳሞቻችን ጎብኝዎች እየዘለሉ ወደ መናንያን በኣት መግባታቸውን የሚያቆሙት መቼ ይሆን? የዓለማውያን እና የመናንያን ድንበር የሚለየው መቼ ይሆን? ለሱባኤ የሚሄዱ ምእመናን ተገቢ ማረፊያ አግኝተው፤ የመናንያኑን በኣት ሳይረብሹ ነገር ግን ተገቢውን አገልግሎት አግኝተው የሚመጡበት ዘመን መቼ ይሆን?» እንል ነበር፡፡ቁጭት ብቻ ሆነ፡፡
beatam dase yalalale kale hewet yasamalene
ReplyDelete