Thursday, May 26, 2011

ገዳመ አስቄጥስ

እየተጓዝን ነው፡፡ ክን በዓይናችን ለማየት፡፡ ስለ ገዳመ አስቄጥስ እና ስለ አባ መቃርዮስ በታሪክ መጻሕፍት ከማንበብ እና በትምህርት ከመስማት ያለፈ ነገር የለኝም፡፡ ግን እንደ በለዓም «አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም» እል ነበር በጉጉት፡፡ እነሆ ዛሬ ላየው ነው፡፡

በዋዲ ኤል ናትሩን ከሚገኙት ሰባት ገዳማት አንዱ ወደ ሆነውና ከካይሮ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወዳለው ወደ አባ መቃርስ ገዳም በመጓዝ ላይ ነን፡፡ ገዳሙ ከካይሮ ወደ እስክንድርያ በሚወስደው የበረሃ ጎዳና በስተ ምዕራብ በኩል ይገኛል፡፡
ለአራት ሰዓታት ያህል ከነዳን በኋላ መኪናችን ወደ ምዕራቡ አቅጣጫ ታጠፈ፡፡ ጭው ያለ በረሃ ነው የሚታየን፡፡ ያውም ነጭ በረሃ፡፡ ድንገት ግን በዛፎች የተሸፈነ መንገድ ውስጥ ገባን፡፡ ግራ እና ቀኝ ጥቅጥቅ ያለ ባሕር ዛፍ ከበበን፡፡ አብረውን ያሉ የካይሮ ልጆች አሁን ወደ ገዳሙ ክልል እየገባን ነው አሉን፡፡ በዚያ ደን ውስጥ ለሠላሳ ደቂቃ ከነዳን በኋላ አንድ ትልቅ ግቢ ከፊታችን ተነጠፈ፡፡

በጠባቧ በር ግቡ
የጥበቃ ፖሊሶች መጥተው ጠየቁን፡፡ አብረውን ያሉትን ካህናት በማየታቸው ፍተሻው ቀለል አለልን፡፡ ጥቁሩ እና ትልቁ በር ተከፈተ፡፡ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ሌላ ረዥም መንገድ ከፊታችን ተነጠፈ፡፡ ግራ እና ቀኙ በቴምር፣ በብርቱካን እና በወይራ ዛፎች የተሞላ ግቢ፡፡ ምናልባት አሁንም ለሠላሳ ደቂቃ በግቢው ውስጥ ሳንነዳ አልቀረንም፡፡

በመጨረሻ ገዳመ አስቄጥስ፣ የታላቁ መቃርዮስ ገዳም ደረስን፡፡
ፊት ለፊታችን የቤተ ክርስቲያኑ ደወል ቤት ይታያል፡፡ በስተግራ የመኪና ማቆሚያ ጥላዎች አሉ፡፡ የገዳሙ መግቢያ በር አጎንብሰው የሚገቡባት በር ናት፡፡ በኋላ ጥንታዊው መግቢያ መሆኑን ዐወቅን፡፡ በጠባቧ በር ግቡ አይደል የተባለው፡፡ የመግቢያው በር መዝጊያ እጅግ ጥንታዊ ከሆነ ብረት የተሠራ ነው፡፡ የተያያዘበት ሚስማርም የጥንቱን ቴክኖሎጂ የሚመሰክር ነው፡፡

ጎንበስ እያልን ስንገባ በግራ እና በቀኝ በሐረግ የተሠሩ ማረፊያ ቦታዎች አሉ፡፡ ከሥራቸው ወንበሮች እና ጠረጲዛዎች ተቀምጠዋል፡፡ ገና ቆም ስንል አንድ አባት ፈጠን ብለው ወደ እኛ መጡና እንኳን ደኅና መጣችሁ አሉን፡፡ ከዚያም ከየት እንደመጣን ጠየቁን፡፡ እኛም ከኢትዮጵያ መሆናችንን ተናገርን፡፡

በግብጽ ገዳማት እና ምእመናን ዘንድ ኢትዮጵያውያን ልዩ ክብር አላቸው፡፡ ከኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን መልካም ስምን ገንብተውልን አልፈዋል፡፡ በመንገድ ላይ ከነ ቀሲስ ስንታየሁ ጋር መጓዝ ያደክማል፡፡ ግብፃውያን ክርስቲያኖች ሁሉ እየመጡ ባርኩን፣ ጸልዩልን ይላሉ፡፡ እንዲሁ አያሳልፉም፡፡

8ኛው መክዘ ተገንብቶ በቅርቡ ጥገና በተደረገለት የቤተ ክርስቲያኑ ግቢ መግቢያ ጥንታዊ በር በኩል አልፈን ወደ አባ መቃርዮስ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ገባን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በአራተኛው መክዘ በተሠራው መቅደስ ቦታ ላይ 7ኛው መክዘ የዛሬ አንድ ሦስት መቶ ዓመት የተገነባ ነው፡፡ ከስምንተኛው እስከ አሥረኛው መክዘ የተሳሉ እጅግ ጥንታውያን የሆኑ ሥዕሎችን ይዟል፡፡ በተለይም የቤተ ክርስቲያኑ ጣርያ በጥንታዊው አሠራር ከጡብ የተገነባ ነው፡፡

በመቅደሱ መግቢያ በር ጣርያ ላይ የዛሬ አንድ ዓመት የተሳሉ ሥዕሎች አሉ፡፡ ሥዕሎቹ የጌታችንን የሕማማት ወቅት የሚገልጡ ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ የሚገኙት ጥንታውያን ሥዕሎች ተጎድተዋል፡፡ ይህ ጉዳት የተከሰተው ገዳሙ ለብዙ ዘመናት ያለ ጥገና እና ክብካቤ ባለመኖሩ ነው፡፡

ከመካከለኛው ዘመን እስከ 1969 ዓም ድረስ በውስጡ ከስድስት የማይበልጡ መነኮሳት ነበር የሚኖሩበት፡፡ የገዳሙ ሕይወት የተቀየረው 1969 ዓም አሥራ ሁለት መነኮሳት ወደዚህ ገዳም በአንድ ጊዜ ሲገቡ ነው፡፡

እነዚህ አሥራ ሁለት መነኮሳት ድኻው ማቴዎስ ወይንም አባ መታ ኤል ምስኪን በሚባሉት አባት መሪነት ለአሥር ዓመታት ከፈዩም ሃምሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዋዲ ኤል ረያን በተባለ በረሃ በምናኔ የኖሩ ናቸው፡፡ አሥራ ሁለቱም ከዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሞያ ተመርቀው ገዳማዊ ሕይወትን የመረጡ ነበሩ፡፡

አንድ መቶ አስራ ስድስተኛው የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ስድስተኛ እነዚህን መነኮሳት ወደ አባ መቃርስ ገዳም ገብተው ገዳሙን እንዲያቀኑ ነገሯቸው፡፡ እነርሱም ቃላቸውን ተቀብለው መጡ፡፡ በዚያ ጊዜ በእድሜ የገፉ ስድስት መነኮሳት ብቻ በገዳሙ ነበሩ፡፡

የገዳሙ ሕንፃዎች ሊፈርሱ ደርሰዋል፡፡ ክልሉ ተራቁቷል፡፡ እነዚያ አባቶች ዕቃውን እና ቃል ኪዳኑን እየጠበቁ ተቀምጠዋል፡፡ ወደ ገዳሙ የገቡት መነኮሳት በእርሻ፣ በሕክምና፣ በፋርማኮሎጂ፣ በእንስሳት ጤና፣ በሥነ ትምህርት፣ በምሕንድስና፣ እና በሌሎችም ሞያዎች የተመረቁ ነበሩ፡፡

ከገዳማዊው ሕይወት ጎን ለጎን ገዳሙን ለማቅናት ተጉ፡፡ በተለይም የመነኮሳቱ መሪ አባ መታ ኤል ምስኪን ምናኔን የሚወድዱ ሥራን የሚያከብሩ፣ ጥንታዊው የአባቶች ሥርዓት እንዲከበር የሚጥሩ አባት ነበሩ፡፡ 35 ዓመታት በላይ በገዳማዊ ሕይወት አገለግለዋል፡፡ ከሰባ በላይ መጻሕፍት እና 200 መቶ በላይ ጽሑፎች አበርክተዋል፡፡ በተለይም ታላላቅ የጾም ወቅቶችን ከሰው ርቀው ማሳለፍ ይወድዱ ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ለጵጵስና ቢመረጡም እኔ አልበቃሁም ብለው እምቢ አሉ፡፡

አባ መታ ኤል ምስኪን የተሽቆጠቆጠ ልብስ፣የክብር ወንበር እና ውዳሴ አይወድዱም ነበር፡፡ ዋናው ዓላማቸው በአባቶቻቸው መንገድ መጓዝ ነበር፡፡ ጸሎት፣ ትምህርት እና ሥራ ዋና መመርያቸው ነው፡፡ ሲያርፉ የተቀበሩት በረሃው ላይ ነው፡፡ «ምንም ዓይነት ጌጣ ጌጥ በመቃብሬ ላይ እንዳታደርጉ½ እንደ አባቶቼ ዝም ብላችሁ ቅበሩኝ ባሉት መሠረት እንዲሁ ነው የተቀበሩት፡፡
ሲያርፉ የተቀበሩት በረሃው ላይ ነው

ከዚያው ከቤተ ክርስቲያኑ ሳትወጡ በስተ ግራ በኩል 10ኛው መክዘ ወደ ገዳሙ የመጡትን የነቢዩ ኤልሳዕን እና የመጥምቁ ዮሐንስን ዐጽም ትሳለማላችሁ፡፡ አቤት ዕድል፡፡ እነሆ ሁለት ዓመት ሄድን፤ ከዚያም ተሻግረን ሁለት ሰባት መቶ ላይ ደረስን፡፡ ኤልሳዕንም አገኘነው፡፡ መጥምቀ መለኮትንም ተሳለምንው፡፡ «ዓይኔ ዓለም አየ እግሬ ደርሶ» አሉ እናቶቻችን፡፡
የሁለቱ ነቢያት ዐጽም መጀመርያ አርፎበት የነበረው የጥንት መቃብር

ጥንታውያን መዛግብትን እና የአርኬዎሎጂ ቁፋሮን በመጠቀም የሁለቱን ነቢያት ዐጽም እንዴት እንዳገኙ መረጃ እያጣቀሱ አስጎብኚው አባት አብራሩልን፡፡
የነቢዩ ኤልሳዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ዐጽም
10ኛው መክዘ በእስክንድርያ ችግር በነበረ ጊዜ የብዙ አባቶች ዐፅም ወደ ገዳሙ መምጣቱን ነገሩን፡፡ የሁለቱ ነቢያት ዐጽም መጀመርያ አርፎበት የነበረውን የጥንት መቃብርም አሁን ዐጽሙ ካለበት በታች ከፍተው አስጎበኙን፡፡
የአባ መቃርዮስ ታላቁ ዐጽም
የአባ መቃርዮስ ታላቁ፣ የመቃርዮስ ዘግብጽ እና የጳጳሱ መቃርዮስ ዐጽም ያረፈው እዚህ ነው፡፡ እነሆ ወድቀን ተሳለምነው፡፡ አባቶቻችን ይህንን በረከት ለማግኘት ነበር የሱዳንን እና የግብጽን በረሃ ያቋርጡ የነበረው፡፡ እኛ ግን በእነርሱ ጸሎት ተደግፈን በአውሮፕላን እና በመኪና መጣን፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሠገሡ አይደል የሚባለው፡፡

ከሦስቱ መቃርዮሶች ዐጽም ጎን የአሥራ አራት ፓትርያርኮች ዐጽም አርፏል፡፡ እነዚህ ፓትርያርኮች የግብጽን ቤተ ክርስቲያን አገልግለው ዐጽማቸው እዚህ እንዲያርፍ በመናዘዛቸው ምክንያት እዚህ ገዳም የተቀበሩ ናቸው፡፡
ንታዊው መነኮሳት አት

አሁን ያለንበት ገዳም የተገደመው 360 ዓም በታላቁ መቃርዮስ ነው፡፡ መቃርዮስ 400 የሚበልጡ መነኮሳትን በዚህ ገዳም ሰብስቦ ነበር፡፡ እነዚህ መነኮሳት ኢትዮጵያውያን፣ ግብጻውያን፣ ሶርያውያን፣ ፍልስጤማውያን፣ ግሪኮች፣ ፈረንሳዮች፣ ስፔናውያን እና ሌሎችም ነበሩ፡፡

ከአባ መቃርዮስ ቤተ ክርስቲያን ወጥተን ወደ አርባ ዘጠኙ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያን አለፈን፡፡ ይህኛውም ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ነው፡፡ በመቅደሱ በር አጠገብ ከአንድ ዓመታት በላይ የቆሙ ሁለት ዓምዶች አሉ፡፡ እነዚህ አርባ ዘጠኝ ሰማዕታት በአራተኛው መክዘ በርበሮች ገዳሙን ሲያቃጥሉ በሰማዕትነት ያለፉ መነኮሳት ናቸው፡፡ ከመቅደሱ በስተግራ የሁሉም ዐጽም በክብር አርፏል፡፡
ታላቁ አባት የዮሐንስ ሐፂር ዐጽም

ከዋናው መቅደስ በስተ ቀኝ በኩል ሌላ መቅደስ ይገኛል፡፡ የታላቁ አባት የዮሐንስ ሐፂር ዐጽም እዚያ አካባቢ ነው የሚገኘው፡፡ ከዐጽሙ በላይ ካሉት ሥዕሎች የእመቤታችን ሥዕል በኢትዮጵያውያን የተሳለች ሲሆን ቢያንስ ሦስት መቶ ዓመት እንደ ቆየች ይነገራል፡፡
በኢትዮጵያውያን የተሳለች የእመቤታችን ሥዕል 17ኛው መክዘ

አሁን ከቤተ መቅደሱ ወጥተን ወደ ገዳሙ የግብርና ክልል እናምራ፡፡

ይቀጥላል፡፡

32 comments:

 1. ከደብረ ቁስቋም
  ምንማለት እንዳለብኝ አላውቅም ውስጤን ነው የነካው በርግጥ በጣም ነው ደስ ያለኝ ምክንያቱም የአባቶቻችንን ታሪክ ስሰማ ውስጤ በጣም ይደሰታል
  ዲ ዳንኤል እግዚአብሄረ አንተንም ቤተሰብህንም ሙሉ ጤንነትና ፍቅር ያድላችሁ መልካሙን እንዳሰማኽን አምላክ በምንግስቱ ሲመጣ መልካሙን ያሰማህ

  ReplyDelete
 2. ዳኒ ታድለህ!! አቤቱ እባክህን የቀደሙ አባቶቻችንን በረከት ላክልን?????

  ReplyDelete
 3. wow Dani, thank you very much

  ReplyDelete
 4. Dear Dn Danile what you are writing from Egypt is very interesting. As there are many people who do not have internet access, it is better you write it in any form that can be published and will be available for readers that shows your observation in Egypt.

  ReplyDelete
 5. Dn. Dani Egiziabehere edimiwunena tenawun yistih. Kale hiwot yasmin. Dani be ewunetu betam edelegna neh. Egziabehere yakiberehe le egnam ye abatochachin bereketu yideresen. Hule simegnew yeneberekut negere new. Egiziabehere beselam yimelisachih.
  Gebereysuse (z) from Botswana

  ReplyDelete
 6. ኦ ዲያቆን ዳንኤል ስታቋርጠዉ ልቤም አብራ ነዉ ቀጥ ያለችዉ በጣም ተመስጬ እያነበብኩ ነበር ለምን እንደሆነ ባላዉቅም እምባ እየተናነቀኝ ነዉ ያነበብኩት በተለይ “በተደጋጋሚ ለጵጵስና ቢመረጡም እኔ አልበቃሁም ብለው እምቢ አሉ፡፡” የሚለዉን አረፍተ ነገር ሳነብ አባቶቻችን ምን አይነት ትህትናና ፈሪሃ እግዚአብሄር የነበራቸዉ ነበሩ እያልኩ ስገረም ነበር ምክንያቱም በእኔ እድሜ የደረስኩባቸዉ አባቶች ጵጵስና ለመቀበል እስከ 500 ሺ ብር ጉቦ የሚክፍሉ መሆናቸዉን በመስማቴ ነዉ አግራሞቴ የጨመረዉ፡፡

  በተረፈ በጣም ቀንቼባችኋለሁ እኔስ እናተ ያያችሁትን አይ ይሆን ለዚህ ክብረ እበቃ ይሆን የሚለዉ ጥያቄ ነዉ ሀዘኔን ያበዛዉ፡፡

  ለማንኛዉም ግን ባንተ በኩል በምናባችን ተጉዘናል የአባቶቻችን በረክት ይደርብን እናንተም በዚያ ቅዱስ ስፍራ ሆናችሁ በፀሎታችሁ አስቡን፡፡

  እግዚአብሔር ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልካሙን ጊዜ እንዲያመጣ ለምኑልን ምክንያቱም የምንሰማቸዉ ነገሮች ሁሉ አስፈሪ ሆነዋልና፡፡

  በተረፈ ቀጣዩን የታላቁን የገዳመ አስቄጥስን ታሪክ በጉጉት እየጠበኩ መሆኔን ላሳዉቅህ እወዳለሁ፡፡
  ሰብስቤ ነኝ

  ReplyDelete
 7. ጥበበ ስላሴMay 26, 2011 at 3:15 PM

  ውድ ዲ. ዳንኤል
  ቃለ ህይወት ያሰማልን
  ጽሁፎችህን ሁሌ በንቃት ነው የማነባቸው፡፡ በጽሁፎችህ የምናውቀውን አጽንተን እንድንይዝ ከማድረጋቸው በተጨማሪ አዲስ ነገር እንድንማርባቸው ያደርጉናል፡፡ በአሁኑ ጽሁፍና በአካተትካቸው ፎቶዎች መረዳት እንደሚቻለው ግባጻዊያን ወንድሞቻችን ገዳሞቻቸውን በጥንቃቄ ና በእቅድ ተንከባክበው እያስተዳደሩአቸው እንደሆነ ያሳየናል፡፡ በዚሁም እኛ በገዳሞቻችን ያልሰራናቸውን ከማሳየቱም በተጨማሪ እንዴት መስራት እንዳለብን ያስተምራል፡፡ በገዳመ አስቄጥስ እነ አባ መታ ኤል ምስኪን የሰሩትን ስራ በእኛ ገዳማት ለመድገም ምን እንደሚያስፈልገን አስተምሮናል፡፡ ወደ ገዳሙ (ገዳመ አስቄጥስ ) የገቡት መነኮሳት በእርሻ፣ በሕክምና፣ በፋርማኮሎጂ፣ በእንስሳት ጤና፣ በሥነ ትምህርት፣ በምሕንድስና፣ እና በሌሎችም ሞያዎች የተመረቁ ነበሩ፡፡

  ReplyDelete
 8. "አባ መታ ኤል ምስኪን የተሽቆጠቆጠ ልብስ፣የክብር ወንበር እና ውዳሴ አይወድዱም ነበር፡፡ ዋናው ዓላማቸው በአባቶቻቸው መንገድ መጓዝ ነበር፡፡ ጸሎት፣ ትምህርት እና ሥራ ዋና መመርያቸው ነው!!!" taddilew! egnam indersachew inihon zend bereketachew yideribin! AMEEN!!!!

  ReplyDelete
 9. የናዝሬቱ(Ze-Nazareth)May 26, 2011 at 3:33 PM

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ስሜትን ይነካል፡፡ መቼ ይሆን የእኛም ገዳማት እንደዚህ ታሪካቸው ታድሶ ማንነታቸው ለዓለም ይፋ ሆኖ የምናየው?

  ReplyDelete
 10. Egziabhar Yibarkh, Ante Beaynh yayehawunna bejoroh yesemahawun yahl zigjithn saneb des bilognal.

  Temesgen, Dire dawa

  ReplyDelete
 11. ዮናስ አበበMay 26, 2011 at 4:32 PM

  ዳኒ በርትአ በ2ለት በኩል የተስአለ ስልት ምአለእት እንዲ ነው:: ጽጋውእን ያብዝአልህ::

  ReplyDelete
 12. በግብጽ ምእመናን ዘንድ ኢትዩጵያውያን ልዩ ክብር አላቸው።ከኛ በፊት የነበሩት አባቶች መልካም ስምን ገንብተውልን አልፈዋል።

  ReplyDelete
 13. Dear Dn Daniel Rejim edme yistih. Ejig bizu bereket yibzalih. Minew tadya Yiketilal bileh ....

  ReplyDelete
 14. በምናቤ እንዳመራሁ ቀረሁ። ሁሉ የማይጎልበት አምላክ ምን አለ ለእኔም በውኔ ቢያሳዩኝ።
  ለትንግርታዊ አቀራረብህ ያባቶቻችን አምላክ ሁሉን ነገር አትረፍርፎ ይስጥህ.

  ReplyDelete
 15. የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን። መቼም የሙሴ ጸሊም(ጥቁሩ ሙሴ) እና ቅዱስ መርቆሬዮስ(አቡሲፌን)ቅዱስ ቦታም ሔደህ በረከቱን እንደምታካፍለን አምናለሁ። ከተቻለ ደግሞ የሲና ተራራ ጫፍ ወጥተህ ቪድዬውን ቀርጸህ ብታስተራልፈው ወቅቱ ጥሩ ባለመሆኑ በመንገዳችሁ ፈተና ካልበዛባችሁ።

  ReplyDelete
 16. d/daniel egziabher amlak nefsachenen endarekahat lantem qale hiwet yasemalen betesebochhen yetebk gen yekerta sele and yalgebagn neger selale btasredagn esum ye metmke yohans atsm endeat wede gbts (egibt) endehede glts betaderglegn selalgebagn new beterefe betam amesegnalehu yedngl maryam lje ftsamehen yasamrleh betesebhen yetebk dingl bemlgawa tetebkh

  ReplyDelete
 17. ዲ/ዳንኤል በረገጥከው ምድር ባየኸው በሰማኸው የደረሰህ በረከት ለሃገራችን ለህዝቡ ሁሉ በያለንበት ይደርስ ዘንድ የአምላካችን ፈቃዱ ይሁን እናንተም በሰላም ግቡ አገልግሎታችሁንም እግዚአብሑር ይባርክልን

  AD

  ReplyDelete
 18. እ/ር ይስጥልን፣

  ReplyDelete
 19. ኪዳነማርያምMay 27, 2011 at 5:54 AM

  ሠላም ዳኒ እንደምን አለህ እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ። ስለ አባ መቃርዩስ እና ስለ ገዳመ አስቄጥስ ድሮ ካነበብኩት የበለጠ በስዕላዊ አገላለፅ በፎቶ የተደገፈ ነገር በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ምንም እንኳን በገዳም አመሰራረት ተቀዳሚዉን ስፍራ ቢይዙም፡ መነኮሳቱም ቅን እና የዋሆች ከኔ ይልቅ ለሌላዉ የሚሉ ስለሆኑ ስራቸዉ ሁሉ ያመረ ነዉ። ታዲያ በክርስትና መኮራረጅ ስለሚቻል በጎ በጎዉን ከነሱ ወስደን ገዳማችንም አባቶቻችንም ተለዉጠዉ ለማየት ያብቃን።
  ኪዳነማርያም
  ከሎንደን

  ReplyDelete
 20. dani this is very interesting,can you get some info about abune abdul mesih al habeshi(aba gebrekirstos ethiopiawi)hes time of staying in egypt and everything about him.thank you i hope you will,,,,,,,

  ReplyDelete
 21. Thanks a Lot D. Danny. Egnase meche yehone endihe ymenehonew? dese Ymile tarike new.....

  Harry from Addis

  ReplyDelete
 22. "እነሆ ወድቀን ተሳለምነው፡፡ አባቶቻችን ይህንን በረከት ለማግኘት ነበር የሱዳንን እና የግብጽን በረሃ ያቋርጡ የነበረው፡፡ እኛ ግን በእነርሱ ጸሎት ተደግፈን በአውሮፕላን እና በመኪና መጣን፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሠገሡ አይደል የሚባለው፡"

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ፣ሰሎሞን ደጀኔ ከኮምቦልቻ

  ReplyDelete
 23. Dear Dn Daniel betam betam new yekenahut, ye abatochachin bereket kehulachin gar yehun. Amen !

  ReplyDelete
 24. “በተደጋጋሚ ለጵጵስና ቢመረጡም እኔ አልበቃሁም ብለው እምቢ አሉ፡፡” የሚለውን ካነበብን በኋላ በአኢትዮጵያ ሲኖዶስ ደግሞ ጵጵስና ከፍተኛ ገንዘብ በጉቦ መልክ ለሰጠ ሲቸበቸብ ስናይ በእውነቱ በዚህ ሲኖዶስ ስብሰባ መንፈስ ቅዱስ በመሃላቸው ይገኛል ብሎ ማለት በመንፈስ ቅዱስ ማሾፍ አይሆንምን?

  ReplyDelete
 25. dani amlak yetebekeh.

  ReplyDelete
 26. Nice article!It initiates me to do good. Let us try to be strong as our fathers! God bless Ethiopia and Ethiopians! Amen!

  ReplyDelete
 27. ውድ ወንድማችን ዲን ዳንኤል፡-
  በአምላካችን ፍቃድ የተቀደሱ ቦታዎችን እንዲሁም የቅዱሳንን አጽም ለማየት በመታደልህ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። በተለይ የቤተክርስቲያን ፈታኞች እጅግ እንደ አሸን በፈሉበት በዚህ ዘመን ወደዃላ መለስ ብለን እንድናይ የሚጋብዝና የሚለውን የእግዚአበሔር ቃል የሚያስታውስ ግሩም ለሆነው ጽሑፍህ ምስጋናዬ ከፍተኛ ነው። ባሁኑ ስዓት በሃገራችን የሚገኙ ገዳማት ብዙ የተጋረጠባቸው ችግሮች አሉ። በተለያዩ ማህበራት የሚደረጉ የማቋቋሚያ ጅምር ፕሮጀክቶች ቢኖሩም ከችግሩ ስፋት አንጻር ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ይመስለኛል። እንዳለ መታደል ሆኖ በቤተክርስቲያኒቱ ያሉ ታላላቅ አባቶች ይህን አጀንዳ በዋናነት ይዘው ስር ነቀል የሆነ ለውጥ ለማምጣት ሰፋ ያለ እቅድ ተዘጋጅቶ በይፋ ሲተገበር አላየሁም። ብዙሃኑ በተናጥል ከመሯሯጥ በስተቀር። እንደ እኔ አመለካከት እነዚህ የሊቃውንት መፍለቂያ እንዲሁም ለሃገርና ለወገን የሚጠቅም ጸሎት ማድረሻ የሆኑ ገዳማትን ለመታደግ የሚያስችል የገንዘብና የዕውቀት አቅም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን ጠፍቶ አይመስለኝም። ችግራችን የልምድና የማስተባበር አቅም ማነስ ይመስለኛል። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ግብጻውያን ምዕመናን እንዴት አድርገው ገዳማቶቻቸውን ለዚህ እንዳደረሷቸው ሰፋ ያለ ጥናታዊ ጽሑፍ ብታዘጋጅ በጣም ጥሩ ይመስለኛል። በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ገዳማት በተናጥል የሚደረገው እሩጫ አደጋ የሚኖረው ይመስለኛል። እናም እንዴት አድርገን ገዳማቶቻችንን አንድ ወጥ በሆነ አሰራር እንታደግ? እንዴት አድርገን ሰማያዊ ተምሳሌትነታቸውን በምድር ላይ እናሳይ? እና ሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎችን ሰፋ ባለ ነገር መልስ ብናገኝ መልካም ነው።
  ፈጻሚ እንጅ ጀማሪ ሆነህ እንዳትቀር አምላካችን ይርዳህ። ቅድስት ድንግል ማርያም ጥላ ከለላ ትሁንህ።
  ወንድምህ
  ግንቦት 21፣2003

  ReplyDelete
 28. የዮሐንስ ሐፂር ዐጽም መሳለም ምን ያህል መታደል ነው፡፡ እኛንም ሄደን ለማየትና የአባቶቻችንን በአት ለማየት እና ለመሳለም ያብቃል፡፡

  ReplyDelete
 29. Egziabhere yabertahi!

  ReplyDelete
 30. kale hiywot yasemalin
  tokichawu

  ReplyDelete
 31. what happen to deje selam? please ......... there is a problem of openning

  ReplyDelete
 32. አንተ ታድለህ።

  ReplyDelete