Sunday, May 22, 2011

የድኾች ጳጳስ


ከካይሮ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ወደ ሚርቅ ፈዩም ወደሚባል ቦታ በመጓዝ ላይ ነን፡፡ በቦታው የአባ አብርሃም ገዳም ይገኛል፡፡ ዓባይ ግራ እና ቀኛችንን እየተመላለሰ ያጠጣዋል፡፡ እርሻው ይመስጣል፡፡ ግብጽን አረንጓዴ ሆና ስታዩዋት በሰሐራ በረሃ ውስጥ ያለች ሀገር አትመስልም፡፡

ግብፃውያኑ ገበሬዎች በትንንሽ ትራክተሮች ያርሳሉ፣ ያጭዳሉ ይወቃሉ፡፡ በየእርሻው መካከል ተራራ የሚያህሉ በጆንያ የተሞሉ የእህል ክምሮችን ታያላችሁ፡፡ በየእርሻው ዳር በቦይ ከመጣው የዓባይ ውኃ በመሳቢያ ማሽን እየጨለፉ ወደ እርሻው ይለቅቁታል፡፡ ከዚያም ከሦስት እና አራት ኪሎ ሜትር በላይ ለሚሆን ርቀት እየተጓዘ ማሳውን ያረሰርሰዋል፡፡

ፈዩም አባ አብርሃም ገዳም ደረስን፡፡ በር ላይ ከባድ ፍተሻ ነው ያለው፡፡ አክራሪዎቹ ብለው እየገቡ ቤተ ክርስቲያን ማቃጠሉን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ ሰሞኑን እንኳን አራት ቤተ ክርስቲያን ደርሷል ያቃጠሉት፡፡ እናም ፍተሻውን ጥብቅ ቢያደርጉት አይገርምም፡፡

ውስጥ ስትገቡ የምታዩትት ነገር የሚያስደንቅ ነው፡፡ የገዳሙ ስፋት የመስቀል አደባባይን ሁለት እጥፍ ይሆናል፡፡ በውስጡ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት፣ የመነኮሳት መኖርያ፣ ዐጸደ ሕፃናት፣ አንደኛ ደረጃ /ቤት፣ የቋንቋ /ቤት፣ የእንግዶች ማረፊያ ይዟል፡፡

የጥንቱ ቤተ ክርስቲያን ጠባብና 800 ዓመት በላይ እድሜ ያለው ሲሆን አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ግን ሰፊ እና የቅርብ ዘመን ሥሪት ነው፡፡ ጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን በእመቤታችን ስም የታነጸ ሲሆን አዲሱ ቤተ ክርስቲያን በአባ አብርሃም ስም የተሠራ ነው፡፡

አባ አብርሃም 1829 ዓም የተወለዱ ግብፃዊ ናቸው፡፡ እኒህ አባት 18 ዓመታቸው ጀምረው ወደ ደብረ ቁስቋም ገዳም ገቡ፡፡ እዚያ የሚታወቁት በታዛዥነታቸው እና የድኾች ወዳጅ በመሆናቸው ነው፡፡ የሰዎችን ችግር ሰምተው ዝም ማለት አይሆንላቸውም፡፡ ችግሩን ለመፍታት ይወጣሉ ይወርዳሉ፡፡ ለቅዱሳት መጻሕፍት ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ሌሊቱን በጸሎት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ነበር የሚያሳልፉት፡፡

1866 ዓም የደብረ ቁስቋም ገዳም አበ ምኔት ሲያርፉ በገዳማውያኑ ውሳኔ አባ አብርሃም አበ ምኔት ሆኑ፡፡ በዚህ ጊዜ የገዳሙን ክልል አሰፉት፡፡ /ቤት ከፈቱ፡፡ ቤተ መጻሕፍቱን አደራጁት፡፡

ከሁሉም በላይ አባ አብርሃም የሚታወቁት የመስጠት ጸጋ ስለነበራቸው ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ተቸግሮ ከመጣ ከገዳሙ ገንዘብ ወጭ አድርገው ይሰጡታል፡፡ ሙስሊምም ይሁን ክርስቲያን ለእርሳቸው ችግር የለውም፡፡ ግን ሰው መቸገር የለበትም፡፡ የሚለብሱት ልብስ እጅግ የተዋረደ እና ተራ ነበር፡፡ ከድኾች ጋር አብረው ያለቅሳሉ፡፡ «የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ የድኾች ገንዘብ ነው፡፡ መርዳትም ያለብን ድኾችን ነው፡፡ እኛ ልንዝናናበት አልሰበሰብነውም» ይሉ ነበር፡፡

በዚህም ምክንያት አያሌ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ወደ እርሳቸው ይመጡ ነበር፡፡ እርሳቸውም ሳይመረሩ ይሰጡ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ በገዳሙ የሚበላ እየጠፋ እንኳን የራሳቸውን ድርሻ ለድኾቹ ይሰጧቸዋል፡፡ «እኛ እንራብ ሕዝባችን ግን መራብ የለበትም» ይሉ ነበር፡፡

የገዳሙ መነኮሳት በአባ አብርሃም ሃሳብ አልተስማሙም፡፡ ገንዘባችንን ጨርሶ በረሃብ ሊገድለን ነው ብለው 1870 ዓም አባ አብርሃምን ደብድበው አባረሯቸው፡፡ አባ አብርሃም ከአራት ደቀ መዝሞሮቻቸው ጋር ከገዳሙ ወጡ፡፡ ለድኾች ሲሉም ድኻ ሆኑ፡፡

በእስክንድርያው ፓትርያርክ ፈቃድ ወደ ኤል ባራሙስ ገዳም ገቡ፡፡ በዚያም ለአሥራ አንድ ዓመታት ተቀመጡ፡፡ አባ አብርሃም ከምእመናን ገንዘብ እያሰባሰቡ ምእመናኑን ይረዱ ነበር፡፡ አያሌ ድኾች ከሩቅ ሀገር ሳይቀር ይመጡ ነበር፡፡

ይህንን ግብራቸውን ያዩት ቄርሎስ 5 1881 በግንቦት ወር የጊዛ እና ፈዩም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አድርገው ሾሟቸው፡፡

አባ አብርሃም ወደ ፈዩም ከመጡ በኋላ ዋናው ሥራቸው ጸሎት እና ምጽዋት ሆነ፡፡ «ሕንፃዎችን ለመገንባት ሳይሆን ሰዎችን ለመገንባት ነው የተሾምነው» ይሉ ነበር፡፡ እናም ዋናው ሥራቸው የሰዎችን ችግር በሥጋ እና በነፍስ መፍታት ነበር፡፡ ልጅ ያጡ፣ ሥራ ያጡ፣ ቤት ያጡ፣ ጤና ያጡ፣ ሰዎች ይመጣሉ፡፡ አብረዋቸው አልቅሰው ይጸልዩላቸዋል፡፡ ብዙዎቹም ያጡትን ያገኛሉ፡፡

በገንዘብ ችግር ለቤት ኪራይ፣ ለሕክምና፣ ለት/ቤት፣ ለዕለት ኑሮ የሚከፍሉት ያጡ ይመጡባቸዋል፡፡ የራሳቸውን ሰጥተው ሲጨርሱ ከገዳሙ ገንዘብ ይሰጧቸዋል፡፡ ሙስሊሞቹ እና ክርስቲያኖቹ የእርሳቸው ገዳም ዋና አገልጋዮች ነበሩ፡፡ አባ አብርሃም የሁሉም ወዳጅ ነበሩና፡፡

የእርሳቸው ጸሐፊ የሆነው ሰው ለገንዘብ በጣም ይስገበገብ ነበር ይባላል፡፡ አሥራ አምስት ብር ስጥ ከተባለ አምስት ብር፣ አሥር ሃያ ብር ስጥ ከተባለ አሥር ብር ነበር የሚሰጠው፡፡ አንድ የአባ አብርሃም ወዳጅ ሰው ለአባ አብርሃም በየወሩ 150 ፓውንድ ለመስጠት ይወስናል፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ ሃምሳ ፓውንድ እንጂ ከዚያ በላይ ለመስጠት ልቡ እምቢ ይለዋል፡፡

አንድ ቀን መጣና «አባታቸን እኔ አንድ መቶ ሃምሳ ብር ለመስጠት እመጣለሁ፤ ግን ከሃምሳ በላይ እንዳልሰጥ ልቤ እምቢ ይለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ያንን ጸሐፊ ጠሩትና «ለመሆኑ ለሰዎች አሥራ አምሰት ብር ስጥ ስልህ አምስት ብር ነው እንዴ የምትሰጣቸው አሉት፡፡

ደንግጦ «አዎ» አላቸው፡፡ ያንጊዜ አየህ «አስቀረህብኝ እንጂ አልጠቀምከኝም፡፡ አንተ አሥራ አምስቱን ሰጥተህ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር አሥር እጥፍ አድርጎ መቶ ሃምሳ ብር ይከፍለኝ ነበር፤ አንተ አምስት ብር ብቻ ስለምትሰጥ ግን ይኼው ሃምሳ ብር ብቻ ከፈለኝ» አሉት፡፡

አንድ ጊዜ ሰዎች ገንዘብ በሐሰት ለመቀበል ቸገረን ብለው መጡ፡፡ ምን ሆናችሁ ሲሏቸው የውሸታቸውን ወንድማችን ሞቶ የሬሳ ሳጥን መግዣ አጣን አሏቸው፡፡ አባ አብርሃምም ዋጋውን ጠይቀው ሰጧቸው፡፡

ሰዎቹ ገንዘብ በማግኘታቸው ደስ ብሏቸው ቤታቸው ሲደርሱ ወንድማቸው ሞቶ አገኙት፡፡ ደንግጠው ወደ አባ አብርሃም በመመለስ «ኣባታችን እኛ አታልለን ገንዘብ ለመውሰድ ነበር ወንድማችን ሞተ ያልንዎት፤ አሁን ግን እውነት ሆነብን፤ እባክዎን ገንዘቡን እንመልስልዎት እና ወንድማችንን መልሱልን» አሏቸው፡፡ አባ አብርሃምም «አሁንማ ከእኔ እጅ ወጥቷል» አሏቸው፡፡

አንድ ጊዜ ገንዘባቸውን ሁሉ ሰጥተው በጨረሱ ጊዜ አንዲት ሴት ልጇ ታምሞባት መጣችና አለቀሰ ችባቸው፡፡ አንድ ወዳጃቸው የገዛላቸው ጳጳሳት የሚለብሷት የክብር ካባ ነበረቻቸውና «ይህንን ሽጠሽ ልጅሺን አሳክሚ» ብለው ሰጧት፡፡ ሴትዮዋ ካባውን ይዛ ወደ ገበያ ስትሄድ መጀመርያ ካባውን የገዛላቸው ሰው ሱቅ ደረሰች፡፡ እርሱም ገንዘቡን ከፍሏት ካባውን መልሶ አመጣላቸው፡፡

ያረፉት ሰኔ አንድ ቀን 1914 ዓም ነው፡፡ ይህ ዜና ሲሰማ ሙስሊሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ገዳማቸውን ሞሉት፡፡ 1963 ዓም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናቸውን ዐወጀች፡፡
እነሆ ዛሬ ዐጽማቸውን ለመሳለም ከየትኛውም እምነት ሰዎች ሲጎርፉ ታያላችሁ፡፡ እርሳቸው የድኾች ሁሉ ወዳጅ ነበሩና፡፡ ለራሳቸው አንድም የሚያብረቀርቅ ወይንም የተንቆጠቆጠ ልብስ አልነበራቸውም፤ ሸጠው መጽውተውታል፡፡ በቤተ ሙዝየማቸው የምታዩት ሁሉ ሌላውን ለማክበር ሲሉ ድኻ እንደሆኑ ይመሰክራል፡፡

23 comments:

 1. Dn. Daniel Egiziabehere yistilin. Bewunet legnam edih yale yebetchrstian meri egziabehere yisten. Kale hiwot yasman. Bereketu yidiresen.
  Z from Botswana

  ReplyDelete
 2. U r blessed & God ßless u more!
  This Abun was dead 4 zis worled & wise coz his did exactly what his God wishes!
  May God Give us A similar Spritual 4 us?
  (AGE - ß/Dar)

  ReplyDelete
 3. ‎"የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኃልና፤ እርሱ ሀብታም ሲሆን፣ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናተ ድሃ ሆነ።" ቆሮ. ፰፥፱
  በእርግጥም የአባ አብርሃም ታሪክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከበዛው ባለ ጸግነቱና ቸርነቱ የተነሳ ራሱን ባዶ አድርጎና ዝቅ ብሎ ነፍሱን እስከመስጠት በወደደን ፍቅሩ ስለ እኛ በእውነትም ድሃ ሆነ፣ እኛ በእሱ ድሃ መሆን ባለ ጸጋ እንሆን ዘንድ።

  አባታችን አባ አብርሃም የጌታችውንና የአምላካቸውን ፍፁም ፍቅር የገለጹ ታላቅ አባት ናቸው፤ ጌታችንና አምላካችን በምድር ላይ ሲመላለስ ሳለ ሁሉ የእሱ ሆኖ ሳለ ራሱን የሚያስጠጋበት ቤት እንኳ የለውም ነበር፣ በባንክ የሚያስቀምጠውም ብር አልነበረውም፣ የተንቆተቆጠ ካባና ውድ የሆነ መጫሚያም አልነበረውም፣ የእጁም በትር በእቁና በወርቅ የተለበጠ አልነበረም። ዘመኑን ሁሉ የኖረው ከድሆችና ከኃጢያተኞች ጋር ነበር፤ የወደቁትን ሲያነሳ፣ ልባቸው የተሰበረውን ሲጥግን፣ በቀቢጸ ተስፋ ሕይወት ለመረራችው የተስፋን ብርሃን እየለገሳቸው፣ ሰዎች የናቋቸውንና የገፏቸውን በማጽናናት፣ የኃጢያት ቀንበር የተጫናቸውን በፍቅር ተቀብሎ ነፃነትን እያቀዳጃቸው፣ ሰዎችን ሁሉ ከህመማቸውና ከደዌያቸው እየፈወሰ...ነበር አምላካችንና መድኅኒታችን የኖረው።

  ዛሬ በረጃጅም ግንብና በኤሌትሪክ አጥሮች ተከልለው እንዲያም ሲል መሳሪያ በታጠቁ ስጋውያን ራሳቸውን እያሰጠበቁ የድሆችንና የህዝባቸውን ጩኸት ላለማዳመጥ በራሳቸው ዓለም እየኖሩ ያሉት አንዳንድ አባቶቻችን ይሄን ቅዱስ ገድልና ህያው ታሪክ ለማየት፣ ለማወቅም ሆነ ለመስማት ዓይን፣ ጆሮና ልቦና ይኖራቸው ይሆን? ልክ እንደ አባ አብርሃም መንፈሳዊ አባቶቻችን ሸክማችንን ሊያቀሉልን፣ ፍቅራቸውን ሊለግሱን፣ ዕንባችንን ሊያብሱልን፣ ከተጫነብን የኅጢያት ቀንበር ነጻ የምንሆንበትን የወንጌል ቃል ልጆቼ ብለው አቅፈውንና ደግፈውን ሊነግሩን፣ ሊያጽናኑን ይገባቸዋል። እስከ መቼ የአባቶቻችን ቤት ለባለ ጸጎችና ለባለ ዝናዎች ብቻ ክፍት ሆና ትኖራለች? የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅርና ውለታ የምናስብበት ቅዱስ መስቀላቸውስ እስከ መቼ ለድሆችና በኅጢያት ለጎሰቆሉት እንግዳ እንደሆነች ትቀጥላለች፣ በአባቶቻችንና በእኛ መካከል ያለው የመለያየት ገደል ይናድ ዘንድ ያስፈልገዋል፣ ልክ እንደ አባታችን አባ አብርሃም የአምላካችንና የመድኅኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅርና ፍጹም ቸርነት በአባቶችችን ውስጥ ልናየው እንሻለን።

  ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ይሄን አጥንትን የሚያለመልም፣ መንፈስን የሚያበረታ ለበጎና ለፍቅር ሥራ የሚያነሳሳ የአባቶችችንን ህያው ገድል ስላስነበብከን እግዚአብሔር ያክብርልን፣ ረጅም ዕድሜን ይስጥልን! የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር በፍቅርና በርኅራኄ የሚያገለግሉንን አባቶችቻንን ረጅም ዕድሜ ሰጥቶ ይጠብቅልን! አሜን!
  ፍቅር ነኝ ~ከደቡብ አፍሪካ።

  ReplyDelete
 4. ወየው ለእኔ። የጻፍኸው ጽሑፍ እንደ እሳት አቃጠለኝ።

  ReplyDelete
 5. Kale Hiwot Yasemalin! Great lesson. Aba Abraham was giving his own properties 4 z poor. But some of our church leaders especially z "Head" are robbing the properties of the poor and church voraciously. Let God end the intestinal pain of our church.

  Tekle Mariam

  ReplyDelete
 6. ዲ/ን ዳንኤል ይህንን ጽሁፍ ሳነበው ራሴን ወደ ውስጥ እንድመለከት አደረገኝ!! በእውነት እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
  በርታ ወንድማችን!!

  ReplyDelete
 7. Dear Daniel,

  We are expecting our religious leaders to act as selfless humanity. They should live for others rather than to themselves.

  ReplyDelete
 8. አባት ከተባለ እንዲ ነው፡፡

  ግን ዳኒ አባ ጳውሎስ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ቆብና ካባቸውን አንድ ለተቸገረ ሰው ሽጥና ተጠቀም ብለው ቢሰጡና፣ ታሪክን ለውጠው ቢያስደምሙን ምን እንላለን፡፡ ማን ያውቃል……..፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 9. ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ይሄን አጥንትን የሚያለመልም፣ መንፈስን የሚያበረታ ለበጎና ለፍቅር ሥራ የሚያነሳሳ የአባቶችችንን ህያው ገድል ስላስነበብከን እግዚአብሔር ያክብርልን፣ ረጅም ዕድሜን ይስጥልን! የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር በፍቅርና በርኅራኄ የሚያገለግሉንን አባቶችቻንን ረጅም ዕድሜ ሰጥቶ ይጠብቅልን! አሜን!

  ReplyDelete
 10. በእውነት አባ አብርሃም ናፈቁኝ..........
  እግዚአብሄር ሆይ እንደ አባ አብርሃም ያሉ ለመንጋውና ለቤተክርስቲያን እንጂ ለራሳቸው አለማዊ ክብር እና ለገንዘብ የማይጨነቁ አባቶችን አድለን!
  ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ. ዳንኤል

  ReplyDelete
 11. እግዚአብሔር ሆይ አለማመኔን እርዳው ብያለሁ፡፡

  ReplyDelete
 12. ዲያቆን ሀብታሙ ዘ ባህርዳር ፖሊMay 23, 2011 at 8:24 PM

  አንድ ጊዜ ገንዘባቸውን ሁሉ ሰጥተው በጨረሱ ጊዜ አንዲት ሴት ልጇ ታምሞባት መጣችና አለቀሰ ችባቸው፡፡ አንድ ወዳጃቸው የገዛላቸው ጳጳሳት የሚለብሷት የክብር ካባ ነበረቻቸውና «ይህንን ሽጠሽ ልጅሺን አሳክሚ» ብለው ሰጧት፡፡ ሴትዮዋ ካባውን ይዛ ወደ ገበያ ስትሄድ ያ መጀመርያ ካባውን የገዛላቸው ሰው ሱቅ ደረሰች፡፡ እርሱም ገንዘቡን ከፍሏት ካባውን መልሶ አመጣላቸው፡፡ዛሬም እንደ አባ አብርሃም ያሉ ለመንጋውና ለቤተክርስቲያን እንጂ ለራሳቸው አለማዊ ክብር እና ለገንዘብ የማይጨነቁ አባቶችን አግዚአብሔር አምላክ ያድለን.!
  ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ. ዳንኤል

  ReplyDelete
 13. ዛሬም እንደ አባ አብርሃም ያሉ ለመንጋውና ለቤተክርስቲያን እንጂ ለራሳቸው አለማዊ ክብር እና ለገንዘብ የማይጨነቁ አባቶችን አግዚአብሔር አምላክ ያድለን!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 14. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳኒ እግዚአብሔር ከአባ አብርሃም በረከት ያድለን አንተንም ይጠብቅልን እንደሳቸው አይነት እውነተኛ አባት ለኛ ቤተክርስቲያን ያድለን

  ReplyDelete
 15. Addisu
  this is how Christianity is implemented. saints like Aba Abrham are mirror of our Lord Jesus Christ.Pops like Abune Pawulos struggling how to destroy our church.Let God protect our church. Dani kalehiwot yasemalin. by the way since last about two weeks i can't see pictures you are posting, why that so?

  ReplyDelete
 16. This shouldn't be used for comparative not only between the late Aba Abreham and Aba poulos... it's should be used as benchmark for any level of priest or pastor or sheik..or any other spiritual leader...

  Thanks Danny

  ReplyDelete
 17. ኡፍ ምን አይነት ደስ የሚል ተፈጥሮ ነው? ታድለው!! እኛስ መቼ ይሆን እንዲ የምንሆነው? እርሱ ይርዳን…አሜን!!!!

  Thanks for sharing D. Danny

  Harry From Addis

  ReplyDelete
 18. አለማችን እንደ አባ በሆኑ ሰዎች ሳይሆን በማያጭበረብሩ ሰዎች ብትሞላ እንዴት በበቃትና ባማረች? እንደ አባ ሳይሆን እንደ አጭበርባሪው ሰው ከመሆን ይሰውረን:: ምክንያቱም እንደ አባ አይነት ሰው አንድ ብቻ በቂ ነውና::

  ReplyDelete
 19. Thankyou D.Dani for sharing as
  kehulum neger gen betam dese yemilgi egziabher alemen yalekidusan & melkam sewochen saytewelen altewenm rear bihonum.

  ReplyDelete
 20. thanks dn.daneil life of church fathers is good to hear because you get their love u trys to be like them.kale hiywot yasemaen.

  ReplyDelete
 21. thank u for this article always u are post great and adventure things the almighty God be with u.

  ReplyDelete
 22. ቃለ ህይወት ያሰማልን
  «አስቀረህብኝ እንጂ አልጠቀምከኝም፡፡ አንተ አሥራ አምስቱን ሰጥተህ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር አሥር እጥፍ አድርጎ መቶ ሃምሳ ብር ይከፍለኝ ነበር፤ አንተ አምስት ብር ብቻ ስለምትሰጥ ግን ይኼው ሃምሳ ብር ብቻ ከፈለኝ»

  ReplyDelete