Saturday, May 21, 2011

ዓባይን በካይሮ


«ወይ ዓባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሕታዊ ነኝ ብለህ በረሃ ለበረሃ፣ ሸለቆ ለሸለቆ ስትመንን የኖርክ ወንዝ እዚህ ካይሮ መጥተህ ከተሜ ትሆን? እንዴው ምን ቢያቀምሱህ ነው እንዲህ የከተማ ወንዝ የሆንከው ጃል አልኩት ካይሮ ላይ ዓባይን ሳገኘው፡፡

«ከሀገሩ ሲወጣ ምናኔውን ብሕትውናውን ያልተወ ማን አለ? እህል አንቀምስም፣ ልብስ አንለብስም፣ ጫማ አናደርግም፣ ሬዲዮ አንሰማም፣ ሰዓት አናሥርም ሲሉ የነበሩት ሁሉ ውጭ ሀገር ወጥተው አይደለም እንዴ ከተሜ ሆነው የቀሩት? ምን በኔ የተጀመረ ታስመስላለህ

«ቆይ ግን አንተ ይህንን ያህል ዘመን ኖረህ ኖረህ ዛሬ ልትገደብ መሆኑን ስትሰማ ምን ተሰማህ

«በርግጥ ደስ ይላል፡፡ እነ ዐፄ ሐርቤ፣ እነ ዐፄ ዳዊት ያሰቡት ሲሳካ ማየት እንደገና መወለድ ነው፡፡ አይተህኛል ካይሮ ላይ፡፡ ወንዝ ሆኜ እገማደላለህ፣ ኩሬ ሆኜ ዕታቆራለሁ፣ የቦይ ውኃ ሆኜ መንደር ለመንደር እዞራለሁ፣ የመስኖ ውኃ ሆኜ ገጠር ለገጠር እንከራ ተታለሁ፡፡ የቧንቧ ውኃ ሆኜ ቤት ለቤት አዞራለሁ፡፡ የቆሻሻ መውሰጃ ሆኜ ቱቦ ለቱቦ እሰቃያለሁ፡፡ ምን ያልሆንኩት አለ፡፡»


«እናንተ ሀገርስ ዘፈን ብቻ ሆኜ ቀረሁ፡፡ ተረት ሆኜ ቀረሁ፡፡ አሁንም እንኳን ትተርቱብኛላችሁ አሉ፡፡»

«ምን ብለን የማይሆን ነገር ሰምተህ እንዳይሆን

«ዓባይ ማደርያ የለው ቦንድ ይዞ ይዞራል ትላላችሁ አሉ፡፡ ምናለ እንኳን ዓባይ ማደርያ ሊያገኝ ቦንድ ይዞ ይዞራል ብትሉት፡፡»

«አንተምኮ አበዛኸው፡፡ ገና ከጣና ከመውጣትህ እንዴው ገደል ለገደል ዝንጀሮ ይመስል ስትጓዝ ሰንብተህ ከሀገር ትወጣለህ፡፡»

«ሰው ለምን በረሃ እንደሚገባ፣ ለምን ገደል ለገደል እንደሚሸፍት ታውቃለህ? ሲከፋው እኮ ነው፡፡ አልመች ሲለው፡፡

ዓባይ ጉደል ጉደል ቀጭን መንገድ አውጣ
የከፋው ወንድ ልጅ ተሻግሮ እንዲመጣ

ትሉ የለም፡፡ እኔምኮ ከፋኝ፡፡

«ለምን
«ካይሮን አይተሃታል? እኔን ስንት ቦታ ነው የከፋፈሉኝ፡፡ ከኔ አጠገብ ቤት የሚሠሩኮ ሀብታሞች ናቸው፡፡ መርከቡ፣ ጀልባው፣ መዝናኛው፣ መናፈሻው ኧረ ስንቱ ሲገማሸልብኝ ይውላል ያመሻል፡፡ እስኪ ባሕርዳር ከተማን ሄደህ እያት፡፡ ለመሆኑ ዓባይ በዚያ የሚያልፍ ይመስላል፡፡ ገና ከጣና ስወጣ ፋብሪካ ገትራችሁ ቆሻሻ ትለቁብኛላችሁ፡፡ ደግ ነገር የጠፋ ይመስል ጅኒ፣ ዛር፣ ጋኔን የተሰበሰበብኝ አድርጋችሁ ነው የምታወሩት፡፡ እየዘለለ የገባውን ሁሉ ዓባይ ስቦት ነው ትላላችሁ፡፡

«አየህ ካይሮ ላይ የምጓዝበትን መንገድ ግራ ቀኙን አስተካክለው ጥልቀት እንዲኖረው አደረጉና መርከብ ነዱበት፡፡ አሁን ባሕርዳር ላይ እንዲህ ቢደረግ ምን ነበረበት? ጣናን አንድ ነገር ሳትሠሩ ከጥግ እስከ ጥግ ሻሂ ቤት አድርጋችሁት ቀራችሁ፡፡ እስኪ አንድ የመርከብ ላይ መዝናኛ አለ? እስኪ ምናለ ከተማዋን ወደ ምዕራብ ከመለጠጥ ወደ ምሥራቅ ወስዶ እኔን መካከል ብታደርጉኝ?

«እናም ከፋኝ ጥዬ ሄድኩ፡፡ ምን ታደርጉ ዋናው ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ከአሥር በላይ ወንዞች ነበሩ፡፡ ግን ምን ሆኑ? የቆሻሻ መጣያ ሆነው ነው የቀሩት፡፡ እኔኮ ምን ሆናችሁ ነው ከውኃ ጋር የተጣላችሁት? የተከራዩን ቧንቧ መዝጋት ነው እንዴ ለእናንተ የውኃ ልማት? ወንዙን አታለሙም? አፍሪካ ውስጥ እንኳን የኒጀር ወንዝ፣ የኮንጎ ወንዝ፣ የዛምቤዚ ወንዝ ያገኙትን ወግ መዓርግ እኔ መች አገኘሁ፡፡ ተወኝ ተወኝ ባክህ ክፉ አታናግረኝ፡፡»

«ይኼው ከትናንት ብንዘገይ ከነገ እንቀድማለን ብለን ተነሣንኮ»

«ባክህ እናንተ ውጭ የሄደ ስለምትወድዱ ነው

«እንዴት ባክህ

«ነዋ እናንተ ሀገር ከውስጥ ይልቅ የውጭ ስለሚከበር ነው፡፡ ምነው ለአዋሽ አትዘፍኑ? አሁን ከእኔ በላይ አዋሽ አላገለገላችሁም? ከእኔ በላይ ለሀገሩ አዋሽ አልሠራም? ችግሩ አዋሽ እና ዋልያ ከሀገር አይወጡም፡፡ እናንተ ደግሞ ሀገር ውስጥ ያለ ነገር አትወድዱም፡፡»

«ኧረ እባክህ የማይሆን ወሬ እየሰማህ አትማረር»

«ነው እንጂ እስኪ አንተ አዲስ ላብ ቶፕ ይዘህ ግባ? አይቀርጡህም

«ይቀርጡኛል፡፡»

«ግሪን ካርድ ወይንም የውጭ ሀገር ፓስፖርት ያለውን ኢትዮጵያዊስ

«እርሱማ አንድ ከያዘ አይቀረጥም፡፡»

«ለምን

«እንግዳ ተቀባይ ስለሆን ነዋ»

«እንደገና ሞክር»

«ሕጉ ይሆናላ»

«ሕጉ አይደለም አስተሳሰባችሁ ነው፡፡ እዚያው ሀገር ውስጥ ሆኖ ለሀገሩ አስፈላጊውን ሁሉ እየከፈለ ከሚኖረው ይልቅ ከዕለታት አንድ ቀን ብቅ የሚለው ዲያስጶራ ይከበራል፡፡ ከጋምቤላ ከምትመጣ ከካምፓላ ብትመጣ ትከበራለህ፡፡»

«እይውልህ ዓባይ፣ አሁን ሁሉም ነገር አልፎ ሀገር ተነቃንቋል፡፡ ወሬውኮ ዓባይ ዓባይ ብቻ ሆኗል፡፡ ግብፆችን እንኳን አታያቸውም፡፡ ኢትዮጵያን እንጎብኝ ብለው የማያውቁት እንደ ጥንቱ የሕዝብ መዝሙር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ብለው ሊሞቱኮ ነው፡፡»

«እሱ እሱንስ ሳይ አንጀቴ ይርሳል፡፡ እዚህኮ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አያውቁም ነበር፡፡ የመማርያ መጽሐፋቸው ላይኮ ዓባይ መነሻው ግብጽ ነው ብለው የሚጽፉ ደፋሮችኮ ናቸው፡፡ እዚህ ያሉ አበሾች አልነገሩህም»

«ምን

«እዚህ ያሉ ሰዎች ኢትዮጵያን አያውቁም፡፡ ደግሞ ጠባያቸው ሆኖ መንገድ ላይ ሲያገኙህ ሀገርህ የት ነው? ማለት ይወዳሉ፡፡ እና ሐበሾቹ ኢትዮጵያ ነው ሲሏቸው የት ነው? እያሉ ልባቸውን ያወልቁታል፡፡

«እሺ»

«እናም ሲሰለቻቸው ምን እንደሚሏቸው ታውቃለህ

«ከየት ነው የመጣህው»

«ከሽንኩርት፡፡»

«ሽንኩርት የት ነው

«ከድንች አጠገብ»

«ድንችስ የት ነው?»

«ከቃርያ አጠገብ»

«ቃርያስ

«ከዝንጅብል አጠገብ»

«ዝንጅብልስ

«ከጥቁር አዝሙድ አጠገብ»

ሁሉም ነገር አልገባው ሲል «አይ ዋ፣ አይ ዐወቅኩት፣ ዐወቅኩት» ይልና አንገቱን ነቅንቆ ያበቃል፡፡

«ዛሬማ አወቋትኮ ኢትዮጵያን፡፡ ጋዜጦቻቸው ያነሡት ጀመርኮ፡፡ መንገድ ላይ ሲያገኙህ ሐበሻ መሆንክን ሲያውቁ ይጠይቁሃል፡፡ ውኃ ልትዘጉብን ነው አሉ? ይሉሃል፡፡ ኮራሁኮ አሁንማ ሀገሬ ታወቀ፡፡»

« ሁሉ ሕዝብ ግለበጥ ብሎ ደመወዙን ያወጣውኮ ይህንን ሀገራዊ ኩራት ለማምጣት ነው፡፡»

«የሕዝቡ መነሣሣት፣ አንድ ልብ መሆን፣ ቁጭት ልቤን ነካው፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው፡፡»

«ደግሞ ምን ልታመጣ ነው

«እይውልህ አንድ አባት ነበረ አሉ፡፡ ለልጆቹ ሀብቱን ለማውረስ ሽር ጉድ ይላል፡፡ ልጆቹ ደግሞ ከአባታቸው ሀብቱን ለመንጠቅ ሽር ጉድ ይላሉ፡፡ አንድ ቀን ለልቅሶ ሌላ ሀገር በሄደ ጊዜ ራሳቸው ቤቱን ሰብረው ሀብቱን በሙሉ ነጠቁና ለሦስት ተካፈሉት፡፡ አባትዬው ሲመጣ ሀብት ንብረቱ የለም፡፡

«በኋላ በአውጫጭኝ ሲጣራ ለካስ ልጆቹ ናቸው የወሰዱት፡፡ አባት ይህንን ሲሰማ እንዲህ አለ ይባላል «መውሰዱንስ ውሰዱት፣ ሀብታችሁ ነው፡፡ ያስቀመጥኩትም ለእናንተ ነው፡፡ የሚያሳዝነኝ ግን መርቄያችሁ ልትወስዱት ስትችሉ ረግሜያችሁ መውሰዳችሁ ብቻ ነው» አለ አሉ፡፡

«ይህ ከአንተ ግድብ ጋር ምን አገናኘው ታድያ?»

«ሕዝቡኮ ልጆቹን «ይገደብ ዓባይ» እያለ ስም ሲሰጥ የኖረ ነው፡፡ መሪ አጥቶ ኖረ እንጂ ገንዘብ አልሰጥም አላለም ነበር፡፡ አሁንም ዓባይ ሊገደብ ነው ሲባል በደስታ ነው የተነሣው፡፡ ታድያ አንዳንዶቹ በፈቃዱ መስጠት የሚችለውን በግዳጅ አደረጉትና ምርቃቱን ወደ ርግማን ቀየሩት፡፡

«እንዴት ዝቅ ብሎ የግማሽ ወር፣ ከፍ ብሎ የሁለት ወር የሚሰጥ ይጠፋል? እንዴት ሁሉም እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ይሆናል? ሕዝቡኮ ሀገሩ ነው፡፡ ይሰጣል፡፡ በራሳችን ገንዘብ እንገንባው መባሉም ልብ የሚያሞቅ ነው፡፡ ግን እወደድ ባዮች ፈቃዱን ወደ ግዳጅ፣ ምርቃቱን ወደ ርግማን እንዳይቀይሩት እፈራለሁ፡፡

« እሷኛዋ በቄላ በጊዜ ካልተከካች ልክነህ አትቆረጠምም፡፡ ግን አንተ ስታስበው ይሄ አንተን የመገደቡ ጉዳይ ጦርነት አያስነሣም ትላለሀ»

«የናንተ ሀገር ካህናት ምን እንደሚሉ ታውቃለህ

«ብዙ ነገር ይላሉ»

«ጅብ ከሚበላህ በልተህው ተቀደስ»

ይቀጥላል

44 comments:

 1. «ወይ ዓባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሕታዊ ነኝ ብለህ በረሃ ለበረሃ፣ ሸለቆ ለሸለቆ ስትመንን የኖርክ ወንዝ እዚህ ካይሮ መጥተህ ከተሜ ትሆን? እንዴው ምን ቢያቀምሱህ ነው እንዲህ የከተማ ወንዝ የሆንከው ጃል?» አልኩት ካይሮ ላይ ዓባይን ሳገኘው፡፡

  «ከሀገሩ ሲወጣ ምናኔውን ብሕትውናውን ያልተወ ማን አለ? እህል አንቀምስም፣ ልብስ አንለብስም፣ ጫማ አናደርግም፣ ሬዲዮ አንሰማም፣ ሰዓት አናሥርም ሲሉ የነበሩት ሁሉ ውጭ ሀገር ወጥተው አይደለም እንዴ ከተሜ ሆነው የቀሩት? ምን በኔ የተጀመረ ታስመስላለህ?»Nice interview with Abay!Tnx a lot

  ReplyDelete
 2. ዳኒ፤ ዉሃ ካይሮ ውስጥ ህዝቡ በነጻ ነው የሚጠቀምው የሚባለው እውነት ነው? በኛ አገር በሐረር፤ በአፋር፤ በድሬ ድዋ ... ያለው የውሃ ችግር ህዝቡ ያውቅዋል። የዛሬ 10 አመት ጎንደር ልጉብኝት ሄጄ አ.አ ተመልሼ ውሃ እስከምጠጣ ነፍቆኝ ነበር፤ ጎንደር የነበረው የባንባ ውሃ ጥራት አልነበርውም።

  ዳኒ - ደቡብ አፍሪካ ለሌሴቶ ፤ ሲንጋፖር ለማሌዢያ በውሃቸው ለመጠቀም ይከፍላሉ። ግብጽና ሱዳን በሃብት ይበልጡናል ለተፈጥሮ ሃብታችን መከፈል አላባቸው ብዬ እኔ አምናለው። እኛስ ለነሱ የተፈጥሮ ሃብት ለወነው ነዳጅ እንደጉድ እንከፍል አይደል አንዴ? በ1927 ንጉሱ እንግሊዝን ለማስከፈል አላማ እንደነበርቸው የአሜሪካ ጋዜጣ በጊዜው ዘግቦ ነበር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እባክህ የዚህን ሰው ጥያቄዎች የኔም ጥያቄ ነውእና አንድ በለን ዳኒኤል ክብረት

   Delete
 3. ABAY MADERYA ALEW!!God bless u D.DanielKibret!

  ReplyDelete
 4. ጽሁፎችህን በጣም እከታተላለሁ አነባለሁ: አስተያየት ግን መስጠት አይሆንልኝም:: ያ ማለት ግን ጽሁፎችህን አልወዳቸውም ለማለት አይደለም:: በጣም እወዳቸዋለሁ እንደውም ሱስ ሆኖብኝ ብሎግህን በቀን 1 ጊዜ ሳላይ አልውልም:: ዛሬ አስተያየት ለመስጠት የተገደድኩት ከአራት ወር በፊት ወደ ሃገሬ ለስራ ጉዳይ ሄጄ ነበር:: ስሄድ ላፕቶፕ ለእህቴ ገዝቼ ነበር የሄድኩት ፍተሻ ላይ ቀረጥ መክፈል እንዳለብኝ ተነገረኝ: 'ለምን? የያዝኩት አንድ ላፕቶፕ ነው: ለንግድ ወይም ለመሸጥ አይደለም የገዛሁት' አልኳቸው:: 'ቢሆንም ይከፈላል አሉኝ':: ውስጤ እያረረም ቀረጥ መክፈል እንዳለብኝ እራሴን አሳመንኩት:: ከዛ ፓስፖርቴን ሲመለከት ቭዛ አለኝ:: 'ወደ ውጭ ተመልሰህ ትሄዳለህ?' አለኝ: አዎ አልኩት:: እንደዛ ከሆነ ቀረጥ አትከፍልም አለኝ:: ባለመክፈሌ ደስ ብሎኛል:: ግን ደግሞ ያልከፈልኩት ወደ ሃገሬ በመግባቴ ሳይሆን ወደ ውጭ የምመለስ በመሆኑ በጣም እያዘንኩ ወጣሁ:: ለመነገድ እስካልሆነ ድረስ ማንም ኢትዮጵያዊ ቀረጥ መክፈል የለበትም:: ይሄ ብቻ አይደለም: በኢትዮጵያ ቆይታዬ ወቅት ሃገር ሊያይ የመጣ እንግዳ ነበረኝ: እንግዳው የኢትዮጵያ ቆይታውን ጨርሶ ወዳገሩ ሲመለስ እሱን ለመሸኘት Air Port ሄጄ ነበር:: ሸኚዎች በሚገቡበት በር ለመግባት ትኬት ቆርጬ ተሰልፌያለሁ:: እኛ ተሰልፈን እያለ አንድ የውጭ ዜጋ ሳይሰለፍ ቀጥ ብሎ ወደ በሩ ሄደ:: ጥበቃዎቹ ቲኬት የቆረጠ መሆኑን ቢቻ አረጋግጠው አስገቡት:: እንዴት እንደተቃጠልኩ ልነግርህ አልችልም:: እኔ ባለሁበት ሃገር እንኳን ሰልፍ ለመጣስ ከነሱ እኩል ስናወራም በጣም ይቆጫቸዋል:: ሰልፍ እነሱም ጥሰው አይገቡም:: በማንኛውም ነገር ቅድሚያ የሚሰጡት ለሃገራቸው ሰው ነው:: በሁለተኛ ደረጃ ለአውሮፓውያንና አሜሪካውያን:: በ3ኛ ደረጃ ከእስያ ለመጡ ሰዎች ሲሆን አፍሪካውያንን የሚያዩት በመጨረሻ ደረጃ ነው:: እኛን (አፍሪካውያንን) ከምንም አይቆጥሩንም:: በሃገራችን ላይም በነሱ ሃገር ላይም እንደ ዜጋ የማንቆጠር መሆናችንን ሳስብ በጣም እናደዳለሁ:: የሀገራችን ሰዎች ፈረንጆቹ ለኛ ያላቸውን ንቀት ቢያቁት ደስ ይለኝ ነበር:: እንደ ዝንጀሮ እንደሚቆጥሩን ህዝባችን ቢያቅ ጥሩ ነበር:: በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ትውልድ ሲፈጠር እንደዚህ አይነቱ ችግር እንደሚወገድ ተስፋ አደርጋለሁ::

  M.M

  ReplyDelete
 5. nice interview with a ABAY

  ReplyDelete
 6. «ወይ ዓባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሕታዊ ነኝ ብለህ በረሃ ለበረሃ፣ ሸለቆ ለሸለቆ ስትመንን የኖርክ ወንዝ እዚህ ካይሮ መጥተህ ከተሜ ትሆን? እንዴው ምን ቢያቀምሱህ ነው እንዲህ የከተማ ወንዝ የሆንከው ጃል?» አልኩት ካይሮ ላይ ዓባይን ሳገኘው፡፡«ከሀገሩ ሲወጣ ምናኔውን ብሕትውናውን ያልተወ ማን አለ? እህል አንቀምስም፣ ልብስ አንለብስም፣ ጫማ አናደርግም፣ ሬዲዮ አንሰማም፣ ሰዓት አናሥርም ሲሉ የነበሩት ሁሉ ውጭ ሀገር ወጥተው አይደለም እንዴ ከተሜ ሆነው የቀሩት? ምን በኔ የተጀመረ ታስመስላለህ?
  Thank you very much Daniel for your experience sharing

  ReplyDelete
 7. አባይ እውነት ብላለች: M.M የጠቀሰው የላፕቶፑ ጉዳይ እኔም ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞኛል:: እኔም እንደ M.M. አዝኜ ነበር ወደቤቴ የገባሁት::
  Gebre

  ReplyDelete
 8. AGE:
  NICE MESSAGE DANI.

  ReplyDelete
 9. ርብቃ ከጀርመንMay 21, 2011 at 4:01 PM

  ሰላም እንደምን ከረምክ ዲያቆን ዳንኤል ሰሞኑን በመጥፋትህ በውነት በጣም ነበር ያሰብኩት ትናንትና ግን የቅዱስ ስምኦንን ጣፋጭታሪክ ይዘህ ብቅስትል በውነቱ ቀለልነው ያለኝ ዳኒ አባይን በሰፊው አግኝተህ የተሰማውን ጠይቀህ ስሜትን በሚኮረኩር መልኩ ታሪኩንና ሀሳቡንስላካፈልከን ማስተዋልንና ቅውቀትን የሰጠህ አምላክ የተመሰገነ ይሁን በተረፈግን ሰዎችያደረጉትንና ውጤታማ የሆነዘዴ ላካፍላችሁ ላብቶብ ይዘው ሲገቡ እንዳይቀረጡ በአልሙኒየም ወረቀት በደንብ አድርገው ከሸፈኑት ካሜራው (እስክሪኑ) እንደማያየው(እንደማያነበው) ሲያወሩና እንደተጠቀሙበት ሰምቻለሁኝ ይሄንስልግን ቀረጥ አትክፈሉ ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ!ቸርያሰማን!

  ReplyDelete
 10. You are great writer dani. I always like the way you like things. GOD be with you Dani.

  ReplyDelete
 11. AGE 2
  I Said mine 'feel happy & proud', nat coz am intellegent & gifted like this young man - Dani, but coz am lucky 2 b 1 of z many 2 came 2 eat his blessed & soothing messages.
  U r ßlessed Dani 4 sure, but am here 2 Beg God ßless u more!
  Tnxs God.

  ReplyDelete
 12. አባይ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ሆኖ ኖራል። እርግማንም ምርቃትም። ባብዛኛው መርገምት ሆኖ ቆይቷል። ምን አልባት ብልህ ኢትዮጵያዊ አንድ ቀን ሲፈጠር የሁለንተናዋ ምንጭ ሆኖ ቅዱስ የሚሆንበት ዘመን ይመጣ ይሆናል። የሚያሳዝነው ወደዚህኛው አመለካከት ሊወስደን የሚችል መንገድ ማየት አለመጀመራችን ነው። ሁሉም ለራሱ ጉደይ ማስፈጸሚያ ስሙን ብቻ መጠቀም። ዘፋኙም፤ፓለቲከኛውም፡ሕዝቡም፤የሐይማኖት አባቶችም። ተግባር የለሽ ቃላት ብቻ ማስተጋባት። አባይ ሁሌም ማንገራገሪያ እንደሆንህ ትኖር!

  ReplyDelete
 13. አፍሬብሀለሁ ዲ/ን ዳኒ
  ወዳጅህ ከዲሲ

  ReplyDelete
 14. ዲ/ን ዳኒኤል ክብረት(ወንድሜ)እሰካሁን ያነተ የግል ብሎግ መኖር አላውቅም ነበረ ዛሬግን የዳኒ እይታ አገኘሁኣት ደስብሎኛል:: በመንፈሳዊ ትምህርቶችን ና ታሪኮች እንዲሁም እውነተኛ ማህበራዊ ጉዳዮችን ላይ ብዙ ካንተ እማራለሁና እደላኛ ነኝ:: መንፈሳዊ አገልግሎት ቅድምያ ይሁን ታሪክ ሰርተን እንለፍ::
  ነጸብራቅ ሀዲስ ብርሃን/ነጸብራቅ ብርሃን/

  ReplyDelete
 15. korichebihalehu dani...
  wedajih ke canada

  ReplyDelete
 16. ዳንኤል ምንድነዉ ችግርህ ወደካድሬነት እየተቀየርክ ነዉ ታስረህ የተፈታህ ቢሆን ያዉ ታስረዉ የተፈቱት እንደሚያደርጉት ስላደረክ እስርቤት እንደሌሎቸሀ የቀመስከዉ ይኖራል ብለን እናዝልህ ነበር ግን.......ማን ይሆን ኢትዮጲያዊ? የስንትብር ቦንድ ገዛህ ግን?

  ReplyDelete
 17. ዲያቆን ሀብታሙ ዘ ባህርዳር ፖሊMay 22, 2011 at 2:41 AM

  ጅብ ከሚበላህ በልተህው ተቀደስ»
  thank you D/Dani ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 18. Why ye Dani wedaj? lemen aferekebet@

  ReplyDelete
 19. Somebody can correct me, I think the whole idea about Dam is pure politics; I do not think we have the resource to build huge dam, let us not forget we are one of the poorest nations in the world; let do some math :
  "According to the U.S. Department of State, the minimum wage in the public sector, which equaled about US$16 per month in 1996, is insufficient to provide a decent standard of living for a worker and family. The Office of the Study of Wages and Other Remunerations, for instance, reports that a family of 5 requires a monthly income of US$61 in Ethiopia. Even with 2 minimum wage earners, therefore, a family receives only about half the income needed for adequate subsistence"

  So brothers and sisters do you think it is fair to take away this hard earned monthly income?
  I urge everybody who can read and analyze to stop being washed away by pure politics and think rationally.
  Read more: Ethiopia Working conditions, Information about Working conditions in Ethiopia http://www.nationsencyclopedia.com/economies/Africa/Ethiopia-WORKING-CONDITIONS.html#ixzz1N2Xr1qpH

  ReplyDelete
 20. With all due respect, Dn Daniel, I would recommend you to leave this issue for the time. I appreciate all your efforts and I am a consistent reader of your blog. But when it comes to abay...I think I have many good reasons to defend you. It is something that has not settled yet. I am physically connected to Abay and that makes me to be so concerned about it. This dam issue is not only about deploying Abay for good. Abay is now a targeted political victim. I think it is too optimistic to think the dam construction positively. WHY THIS TIME? It is insane to start collecting that huge amount of money from the people who is suffering from poverty. Dani, leave Abay for now. There is good time that you and others would write blogs about it.

  ReplyDelete
 21. ዲ/ን ዳንኤል እንዲህ አይነት ነገር ባትጽፍ ጥሩ ነው ማንን እየደገፍክ እንደሆነ አልገባኝም ከአንድ መንፈሳዊ ሰው ግን እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ሰበካ አልጠብቅም አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር አባይን መገደብ እንዳልሆነ አንተም ታውቀዋለህ ይህንን ዘመናዊ ቅስቀሳ ብትተወው ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 22. Dear pessimists, Do something otherwise please, let people to do something for themselves and even for you to let you free from conscious prison. Try and fail but don’t fail to try! Thanks a lot Dani, May God keep’s your rationality and critical thinking. I’m satisfied personally. May God bless the day!

  ReplyDelete
 23. MM ያለው ነገር እኔም ሁሌም ይቆጨኛል/ያናድደኛልም፡፡ እባካችሁን መጀመሪያ ለራሳችን ክብር እንስጥ ሌላው ይቅር ምግብ ቤት ውስጥ እንኳን አንድ የውጭ ዜጋ ካለ ቅድሚያ እሱን ለማስተናገድ የምግብ ቤት ባለቤቱ ሳይቀር ጐንበስ ቀና ይላል፡፡ ለእንግዳ ያለንን ጥሩ አቀባበል ለመግለጽም ቢሆን ክብራችንን አጥተን መሆን የለበትም፡፡ አንዴ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ስጠብቅ ያጋጠመኝን ልንገራችሁ፡፡ አንድ ህንዳዊ ነው የተሰለፍነውን በሙሉ ከምንም ሳይቆጥር ቀድሞ ሄዶ ትኬት ሊቆርጥ ሲል አንድ ወንድሜ ተራህን ጠብቅ አለው፣ ምን ብሎ መለሰለት መሰላችሁ “ I live here in Ethiopia more zan 6 years but any one not ask me this question before” አያችሁ አይደል ወገኖቸ ምን ያክል ለራሳችን ክብር እንደሌለን ለአንዲት የ60 አመት አሮጊት እናታች እኮ አንበሳ አውቶቡስ የቅድሚያ ተራ ለመስጠት ትዝ ብሎን አያውቅም፡፡
  ኢትዮጵያን ለማሳደግ መጀመሪያ ለኢትዮጵያዊነታችን ክብር እንስጥ፣ ኢትዮጵያዊነታችን እናክብረው፡፡ በተለይ ለህዝብ አገልግሎት የምትሰጡ ክፍሎች ኢትዮጵያዊ ወገናችሁን ንቃችሁ ለውጭ ዜጋ አታጐንብሱ ቅድሚያ ለወገናችሁ ክብር ይኑራችሁ፡፡ ያኔ ራሳችሁም ትከበራላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 24. በጣም የሚገርመኝ የአንዳንዶቻችሁ ተቃውሞ ነው ፡፡ እስኪ አመለካከታችንን እንቀይር ሁሌም ተቃዋሚ አንሁን፡፡
  ዳኒ በርታ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 25. For some commentaters above:-

  Some of us are saying that Dn.Daniel why you speak out about ABAY DAM...etc. as you said that it is politics,etc. Please don't be folish!!
  First of all, LET US UNDERSTAND NATIONAL INTEREST.
  National interest is not a matter of supporting EPRDF or other political group. Some people are still can't differentiate Ethiopian Airlines from EPRDF. Yes political system may be in Ethiopian Airlines but the national interest contribution of Ethiopian Airlines is more significant than other.
  The Abay dam issue is also the same us Ethiopian Airlines. Infact propaganda,raising issues for another issue, etc may be seen in Abay Dam case. BUT SINCE IT IS STRATEGIC ISSUE FOR NATIONAL INTEREST WHY WE OPPOSE???
  The case of ABAY Dam is/will continue being strategic issue for the coming Ethiopian Governments. So why atleast be positive for positive ideas.We can oppose the way how it implement.But why we oppose the idea of making Dam as it is?
  Infact Ethiopian ''historical'' enemies are saying we can't have resource,it is not important,Government do not have mandet to do so,....etc. This is pure hostility act against Ethiopia and Ethiopianism.Here I am not saying that you must support EPRDF But standing for National interest and supporting EPRDF are quite different.
  PLEASE STAND FOR NATIONAL INTEREST!!!
  GETACHEW

  ReplyDelete
 26. Wow,it is a good insight.
  Pj from Debremarkos

  ReplyDelete
 27. love the article. i actually love all ur writings. unique, somewhat hilarious, & lesson giving i find them ... May God be always with you and bless you Dani. & BTW i couldn't see the reason why we should always criticize - it seem as if we can't live with out reflecting the -ve side of everything? what issue is here which's "asafari"? what is wrong with the above article which can make some comment badly on it??? ... Abay yhen blog check maderg bichel 'ALGDEBEM!!!" YL NBR MN ALBAT :) can wait to read the continuation BTW

  ReplyDelete
 28. selame wendemachen tsgawen yabezalhe ,zare betame asekhegale kkkkkkkkkkk, endye le abaye megedbune letengereu yehedeke temeselalehe ,dese yemele keldena kume neger berta berta .............. adenke ehithe w.s

  ReplyDelete
 29. ዳኒ ቀጣዩ መቼ ነው ?

  ReplyDelete
 30. Ketayun betam nafkenal ebakeh tsafew!egziabeher kantegar yehun

  ReplyDelete
 31. Efrata's comment is sickening. How on earth can we call people 'cadres' just because they supported a good cause? And when on earth will we differentiate partisan politics from national interest?

  ReplyDelete
 32. dani kelehiwot yasemalin .

  I WOULD LIKE TO THANK Dn.daniel an insightful idea
  it gives clear understanding for the public at large.
  thank you....JOHN

  ReplyDelete
 33. Efrats's comment is sickening. When on earth will we be able to differentiate partisan politics from national interest? And when in this world will we begin to think positively? Why can't we see the grey area instead of classifying things just as black or white? How can we dub someone a 'cadre' simply because he supported a good cause? This doesn't mean that there aren't problems in our country, and that everything the government is doing is right. But we should know what we oppose. Open your eyes, Efrata! You can't oppose this project if you really are an Ethiopian.

  ReplyDelete
 34. Thanks for sharing such a good article D. Danny.

  Heay guys please try to differentiate your political view from national interest?! Abay dam will be constructed for common benefits of Ethiopian as well as Egyptian people not only for supporters of EPRDF.....Please note that I hate politics but i love to hear about the construction of Dam on Abay river....forget your personal political view of the current government but try to contribute for the successful completion of the DAM as much as you can...then one day u will proud of your self....
  as an Ethiopian this is my advice for you....

  Harry from Addis

  ReplyDelete
 35. Kale Hiwot yasemalin, GREAT Interview!

  Ameha Giyorgis
  DC Area

  ReplyDelete
 36. እንዲህ ብዬ ባስብስ፡-
  ወንድማችን ዲን ዳንኤል አባይ ጋር ባደረግኸው ቃለምልልስ አመሰግንሃለሁ። በተለይ ከምንጩ አልበገር ያለውን ወረድ ብሎ በሰው ልጅ ወደፈለገው አቅጣጫ ሲጠማዘዝ ማዬት ያስደስታል። ቃለ ምልልስህን እያነበብኩ በምናቤ ወደዃላ ተመለስኩ። እንዲህ ብዬ ባስብስ አልኩ። ከምንጩ ገደል ገብቶ ልቡን አልሰጥም ቢላቸው ተከትለውት ወረዱ። ምክንያቱም በወቅቱ ምንም ቴክኖሎጂ ስለሌለ ያላቸው አማራጭ ተከትለውት መውረድ ነበር። ወርደውም ሜዳ ላይ ሲያገኙት ከጎኑ አብረው መኖር እንደልባቸው መጠቀም ጀመሩ። ከምንጩ ስለራቁ በሂደት የሌላ ሃገር ዜጋ ተባሉ። ምን አልባት አሁን ወደ ውጭ በተለያየ ምክንያት እየነጎዱ እንዳሉት ኢትዮጵያውያን። ስለዚህ ያሁኖቹ ግብጻዉያን እንደ አባይ መነሻቸው ኢትዮጵያ ቢሆንስ? ይህን ይዞ በጥልቀት የሚመራመር ግብጻዊ ወይም ኢትዮጵያዊ እጠብቃለሁ። እስከዚያው አኔም በዚሁ ሃሳቤ እኖራለሁ።

  ReplyDelete
 37. DANI THE GOLDEN-MOUTH THANK VERY MUCH.
  TSEGAWUN YABZALIH. GOD BE WITH YOU......

  ReplyDelete
 38. ኤፍራታና የኤፍራታ ሃሳብ አራማጆች፣

  የዓባይ ግድብ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው በግሌ አምናለሁ፡፡ ምሑራኑም የሚያረጋግጡት ይኸንኑ ነው፡፡ በተለይም አንድ ተጨባጭ ምክንያቴን ላንሳ፡፡ ኢሕአዴግ አስደናቂ የሚባሉትን ጊቤ 2 ባለ 25ኪሜ የዋሻ ውስጥ ሃይል ማመንጫ ያለተጨማሪ ግድብ፣ በሁለት የተራራ ወሽመጥ ውስጥ አስደናቂውን የተከዜ ግድብ፣ ከ12 ኪሜ በላይ በሚረዝም ዋሻ በለስን ሲገነባ ሞያ በልብ ነው የሚል መንግሥት እንደነበር የገጠጠ ሃቅ ነው፡፡

  ከእነዚህ ሁለቱ ተከዜ ባለ 300 እና በለስ ባለ460 ሜዋ ማመንጫዎች የመንግሥት በጀት "እየተላጨ" የተገነቡ መሆኑን ላስተዋለ ደግሞ ተአምር ነው፡፡ ጊቤ 2 በዓለም አንቱ የተባሉ የሥነ ምድር ሳይንቲስቶች ሳይቀር መጥተው ይህን ችግር ያለዛሬ አይተነውም ሰምተነውም አናውቅም ያሉለት እሳት የገባ ቅቤ የተባለለት ጊቤ በአስደናቂ ሁኔታ ለፍጻሜ በቅቷል፡፡

  እነዚህን በአስረጅነት አቅርበን ስንመዝነው ዓባይ ትኩሳት ማብረጃ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

  ዳንኤል እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ግድቡን የመንቀፍ ወይም የመደገፍ መብት እየቆነጠርን የምንቸረው የጡመራው ታዳሚዎቹ ከሆንን ዳንኤል የሚያነሳቸውን ሌሎች ጉዳዮችንም እኛው ልንመርጥለት ይገባል፡፡ ኢሕአዴግ ከሚወቀስበት አንዱ ሰው ሁሉ ሳሙና ያውም ቢ29 አለያም ኦሞ ነው ከ2ቱ አንዱ እንጂ 2ቱንም ወይም በዚያ በላይ መሆን አይችልም ብሎ የሰው ልጆችን ረቂቅ ተፈጥሮ የሚቃረን የፖለቲካ አንድምታ ይዞ በመሞገቱ ነው የሚወቀሰው፡፡ ዳንኤል አንባቢዎቹ የሚጠፈጥፉት ሳሙና ከሆነ ሃሳብን በነጻነትና ያደገደብ የሚለው የዴምክራሲም በሉት ተፈጥሮአዊ መብት አዲዮስ መሆኑ ነው፡፡

  ልጁ ያነሳው ነገርን ነገር ዓባይን መንገድ እንዲሉ ካይሮ በመግባቱ ነው፡፡ እዚያ ቤት ደግሞ ዓባይ የልማት አጀንዳ ሆኖ ያለዘይት የቀረበ ክትፎ ነው፡፡

  ታዲያ ግጥምጥሞሹ እንኪረሳ አትጻፍ ማለት ይቻላል? የዳንኤል ካድሬነት ከእውነትና ለኢትዮጵያውያን ጥቅም እስከሆነ ድረስም የሚደገፍ እንጂ የሚነቀፍ አይደለም፡፡

  እናም ኢሕአዴግ የሚወቀስበትን በአንድ ሳንባ ተንፍሱ (በአብዮታዊ ዴሞክራሲ) የተባልነው አልበቃ ብሎ ዳንኤልን በዚሁ ሳንባ ተንፈስ ማለት ጤናማ እየታ አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete
 39. ዲ. ዳንኤል እግዚያብሄር አንተንና ስራዎችህን ይባርክ!
  አገራችን እንዳንተ ያለ በሺዎች የሚቆጠሩ ምክንያታዊ ጀግና በየ ዘርፉ ብታገኝ ባጭር ጊዜ ባደገች ነበር! ለምን ይሆን እኛ ኢትዮጵያውያን እርስ በ እርሳችን ተሳስረን ይምንኖረው? ለምን ይሆን ከመተባበር ይልቅ መጠላለፍ የሚቀናን? ለምን ይሆን አቋም የለሽ የጭፉን ደጋፊነትና የጭፍን ጥላቻ ሰለባ የሆንን? ትናንት በ ፕኦለቲካ ምክንያት ብቻ ብዙ ወንድሞች ሃይማኖታቸውን (እምነታቸውን) ሲቀይሩ ሳይ ገርሞኝ ነበር ዛሬ ደግሞ በዚህ ምክንያት ሃብታቸውን እና ልዋላዊ ክብራቸውን አሳልፈው ሲሰጡ በማየቴ ግራ ግብቶኛል!!! ሀዲስ አለማየሁ በ ጉዱ ካሳ አንደበት 'እንደ ድንጋይ ካብ...... እንደ በግ መንጋ.....' ሲል የገለጸው ማህበረሰብ ዛሬም ይገልጸን ይሆን?

  @ ከላይ ለ 'ኤፍራታና የኤፍራታ ሃሳብ አራማጆች' የጻፍህ ወንድሜ ሃሳብህ ጥሩ ነው ተመችቶኛል:: ምን አልባትም ልብ ካሉት ይመከሩበታል ብዬ አስባለሁ:: በየትኛውም ሃገር መንግስታት የሚሰሩት ስራዎች ሁሉ ምንጫቸው (motives) political interest ይመስለኛል:: ቁምነገሩ የተሰራው ስራ ለ አገሪቱ ያለው ፋይዳ ላይ ነው:: ወደ እኛው ጉዳይ እንምጣ እና ማንም ይስራው ማን የ አባይ ግድብ አንድምታ ከዚህ ቀደም እንደተሰሩት ግድቦች በሃይል ምንጭነቱ ብቻ የሚለካ አይደለም:: አባይን በተለይ በራስ አቅም መገደብ መቻል ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በዘለለ የሃገራችንን አለም አቀፋዊ እና የውስጥ political status የሚቀይር ይመስለኛል:: አለማቀፉ ማህበረሰብ ሃገሪቱን እና ህዝቡን እንደ ተራ አቅም የለሽ እና ወኔ ቢስ ድሃ ህዝብ መቁጠራቸውን እንዲያቆሙ የሚያስገድድ ሲሆን የውስጥ ፕኦለቲከኞቻችንን (ማለትም ተቃዋሚ እና ገዢ ፓርቲዎችን) ደግሞ የ ህዝብ ህብረት ይህን ትልቅ ፕሮጀችት ከሰራ እነሱንም አይቀጡ ቅጣት ሊቀጣ እንደሚችል ያስገነዝባቸዋልና እራሳቸውን እንዲፈትሹ ያስገድዳቸዋል የሚል እምነት አለኝ:: እናም የዚህን ግድብ ፕሮጀክት የሚቃዎሙ ሰዎች ለምን እንደሚቃዎሙ አይገባኝም የሚገርመው ደግሞ ይሄን ታላቅ አገራዊ ፋይዳ ያለውን ፕሮክት የሚደግፉ ሰዎችን እንደካድሬ መቁጠራቸው ከኖርንበት 'ነጭ ወይም ጥቁር ሁናችሁ መኖር አለባችሁ' የሚል እሳቤ የምንዎጣበትን ተስፋ የሚያጨልም ይመስለኛል ምክንያቱም ይህ ተቃውሞ የተቃዋሚ ፓርቲውም ጎራ የ እኔ አውቅልሃለሁ እሳቤ ሰለባነቱን የሚያሳይ ነውና:: ይገርማል ግፆች እኮ አስዋንን ሲገድቡ የዴሞክራሲ ባለቤቶች አልነበሩም:: ከ አስዋን በፊት ዴሞክራሲ ብለውም ሰልፍ አልዎጡም በ አስዋን ግድብ ሆዳቸውን ሞልተው ጥማቸውን አርክተው ስንቃቸውን ይዘው ለ ዲሞክራሲ ለዲሞክራሲ ግንባታ ጣሂር አደባባይ ተሰበሰቡ እንጂ:: በ ነገራችን ላይ ይሄን ስል ሆዳችን እስኪሞላ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መታገል የለብንም እያልሁ አይደለም አካሄዳችንን በዎግ እናድርገው እያልሁ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እስክንመሰርት እድገት ይቁም ይሚለዉን ሃሳባችሁን ግን በ ጽኑ እቃዎማለሁ:: እናም ውድ የሃገሬ ልጆች እባካችሁ ጭፍን ተቃዋሚዎች አትሁኑ ጥሩ ሲሰራ እንደግፍ መጥፎ ሲሰራ እንቃዎም ካለበለዚያ በዚህ አካሄዳችን በዚች አገር ላይ የመላዕክት መንግስት ብንመሰርትም ወደ ሰይጣንነት እንደምንቀይረው አያጠራጥርም:: አዎ ይህ ባህሪያችን ባለፉት ጊዜያት ከጉያችን የዎጡ ጭራቆችን እንዳሳየን መዘንጋት የለብንም:: ደግሞም መቃዎም ልማዳቸው ነው መባል እኮ ይሰለቻል:: የ...... መዝጊያ ሳይዘጋ ያድራል እንደሚባለው አደረጋችሁት እኮ:: የ ኢትዮጵያ አምላክ ልብ ይስን!!!!!!

  ReplyDelete
 40. ኢዮብ ነኝ
  ዳኒ ሰላም ላንተ ይሁን የብሎግህ ደንበኛ ነን አስተያየት ለመስጠት የመጀመሪያዬ ቢሆንም መልካም ፅሁፍ ነው ለተቃውሞ የተነሳ ሰው ሁሌም ከመቃወም ወደኃላ ኤይልም አንተ ግን በርታ ይህ አገራዊ ጉዳይ የሁሉም ህብረተሰብ ጉዳይ ስለሆነ በደንብ ቀጥለህበት ጥሩ ትምህርት እንድናገኝበት አድርገን፡፡ በተለይም አባይ የኢትዮጵያውያን የልብ ትርታ ስለሆነ ቀጥልበት፡፡ ባለፈው ስለትዳር የፃፍከውን አንብቤ አዝኛለሁም ተደስቻለሁም ፡፡በዚህ ርእስ ሰፋ ያለና ሙያዊ አስተያት የታከለበት ሀሳብ ቢቀጥል ጥሩ ይመስለኛል፡፡ለባለትዳሮችም ይሁን ላላገቡ ጠቃሚ በመሆኑ፡፡ እግዚአብሄር ስራህንሁሉ ይባርክ፡፡እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ይሁን

  ReplyDelete
 41. እንዲህ ብዬ ባስብስ፡-
  ወንድማችን ዲን ዳንኤል አባይ ጋር ባደረግኸው ቃለምልልስ አመሰግንሃለሁ። በተለይ ከምንጩ አልበገር ያለውን ወረድ ብሎ በሰው ልጅ ወደፈለገው አቅጣጫ ሲጠማዘዝ ማዬት ያስደስታል። ቃለ ምልልስህን እያነበብኩ በምናቤ ወደዃላ ተመለስኩ። እንዲህ ብዬ ባስብስ አልኩ። ከምንጩ ገደል ገብቶ ልቡን አልሰጥም ቢላቸው ተከትለውት ወረዱ። ምክንያቱም በወቅቱ ምንም ቴክኖሎጂ ስለሌለ ያላቸው አማራጭ ተከትለውት መውረድ ነበር። ወርደውም ሜዳ ላይ ሲያገኙት ከጎኑ አብረው መኖር እንደልባቸው መጠቀም ጀመሩ። ከምንጩ ስለራቁ በሂደት የሌላ ሃገር ዜጋ ተባሉ። ምን አልባት አሁን ወደ ውጭ በተለያየ ምክንያት እየነጎዱ እንዳሉት ኢትዮጵያውያን። ስለዚህ ያሁኖቹ ግብጻዉያን እንደ አባይ መነሻቸው ኢትዮጵያ ቢሆንስ? ይህን ይዞ በጥልቀት የሚመራመር ግብጻዊ ወይም ኢትዮጵያዊ እጠብቃለሁ። እስከዚያው አኔም በዚሁ ሃሳቤ እኖራለሁ። ስማቸው ነኝ ዘአ.አ ዘመንበረ ከተማ

  ReplyDelete
 42. ኢትዮያ ስትራብ ሁሉም ኢትዮያዊ ረሃብተኛ ተብሎ ይሰደባል እንድንራብ ያደረገን ተጠያቂው አካል ሊኖርም ላይኖርም ቢችል ኢትዮያ ስታድግ ለእድገቱ አስተዋጾኦ ያደረገ ማንም ይሁን ማን ሁላችንንም እንኮራለን ነገር ገን እንንተ እንዳላችሁት መንግስት ለፖለቲካ ፍጆታ ያውለውም አያውለውም የራሱ ጉዳይ እንደሆነ ተጠብቆ በመገደቡ ዙሪያ ልንከራከር አይገባንም ስለዚህ ርእዮተ አለም እና የሃገርን ጉዳይ ብንለይ አሪፍ ነው ከዛ በተረፈ በአለም ላይ ዳኒን ሆኖ የተፈጠረ የለም እንዲህ ስል ዳኒ እንደርሱ ነው እንጂ የሚያስበው እንጂ እንደኛ እናስብ ወይም አስብ ብለን አናስገድደው ከሃይማኖት ትምህርት ውጭ ስለዚህ እይታውን ሲያቀርብ ምክንያታዊ በሆነ ትንታኔ እንቃወመው እንጂ በዘለፋ መልኩ ከሃይማኖት አስተማሪ አይጠበቅም ካድሬ ነህ ወይ ምናምን ባንል አሪፍ ነው ልክ አይደለህም ካልነው ልክ ያልሆነበት ምክንያት ግልጹልን እርሱም እኛም እንረዳው ያኔ የሰለጠነ መማር ዘዴ እንፈጥራለን እላለው እግዚአብሄር ይባርክህ ይርዳህ

  ReplyDelete