Friday, May 20, 2011

ተራራውን ያነሣው ሰው

የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡
ተአምረ ማርያም ላይ ከተጻፉት እና በትርጓሜ ወንጌልም ላይ በማቴ5÷29 ለሚገኘው ቃል እንደ ታሪካዊ ማስረጃ ከሚቀርቡት ታሪኮች አንዱ የስምዖን ጫማ ሰፊው ታሪክ ነው፡፡


979 ዓም የፋጢማይድ ሥርወ መንግሥት ግብጽን በሚያስተዳድርበት ወቅት በከሊፋ አል ሙኢዝ ዲን ኢላህ አል ፋጢሚ ዘመን እንዲህ ሆነ፡፡

ለሥልጣን ሲል ወደ እስልምና የተቀየረ ያዕቆብ ኢቢን ቂሊስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፡፡ ይህ አይሁዳዊ ምንም እንኳን ለሥልጣን ሲል እስልምናን ቢቀበልም ልቡ ግን ከአይሁድ ጋር ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም በጣም ይጠላ ነበር፡፡ ይህ ጥላቻው የመጣው በከሊፋው ዘንድ በሚወደድ እና እርሱ ይቀናቀነኛል ብሎ በሚያስበው በአንድ ክርስቲያን ምክንያት ነበር፡፡ ይህ ክርስቲያን ቁዝማን ኢቢን ሚና ይባል ነበር፡፡


ከሊፋ አል ሙኢዝ ደግ፣ ምክንያታዊ እና በሰዎች ነጻነት የሚያምን ዕውቀትንም የሚወድድ መሪ ነበር ይባላል፡፡ ምሁራን ሲከራከሩ መስማት የሚወድድ ሌላው ቀርቶ የእስልምና ምሁራን እስልምናን ከሚቃወሙ ሰዎች ጋር በነጻነት እንዲከራከሩ የሚፈቅድ ሰው ነበረ፡፡
በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ
ይህንን ጠባዩን የሚያውቀው ያዕቆብ ሙሴ የተባለውን የአይሁድ ረቢ ጠርቶ ከፓትርያርኩ ጋር እንዲከራከር እና ፓትርያርኩን እንዲያሳፍረው መከረው፡፡ ሙሴም ጥያቄውን ለከሊፋው አቀረበ፡፡ ከሊፋውም ለፓትርያርኩ መልእክት ላከ፡፡

በቀጠሮው ቀን በወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው አብርሃም ሶርያዊ በሃይማኖት ዕውቀቱ እና ትምህርቱ የታወቀውን ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ይዞት መጣ፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ «በከሊፋው ፊት ይሁዲን መናገር መልካም አይደለም» አለው፡፡

ይህንን ቋንቋ ሙሴ በሌላ ተርጉሞ «አላዋቂ ብለህ ሰደብከኝ» ሲል ተቆጣ፡፡

ከሊፋ አል ሙኢዝም «መከራከር እንጂ መቆጣት አያስፈልግህም» አለው፡፡

ያን ጊዜ ሳዊሮስ «አላዋቂ ብዬ የተናገርኩህ እኔ ሳልሆን ያንተው ነቢይ ኢሳይያስ ነው» ብሎ በትንቢተ ኢሳይያስ 1÷3 ላይ ያለውን ጠቀሰ፡፡ ከሊፋው ገረመውና «እንዲህ የሚል የእናንተ ነቢይ አለ ሲል ሙሴን ጠየቀው፡፡ ሙሴም «አዎ አለ» አለው፡፡ አባ ሳዊሮስም «እንዲያውም እንስሳት ከአንተ እንደሚሻሉም ገልጧል» አለው፡፡ ይሄን ጊዜ ከሊፋው ሳቀ፡፡ ክርክሩም እንዲቆም አዘዘ፡፡

ይህ ሁኔታ ያዕቆብን አበሳጨው፡፡ ራሱ ባመጣው ጣጣ በከሊፋው ፊት መዋረዱም ቆጨው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያኖቹን የሚያጠቃበት ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሙሴንም አንዳች ጥቅስ ከወንጌል እንዲፈልግ ነገረው፡፡

ሙሴ በመጨረሻ  በማቴ 17÷20 ያለውን «የስናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነሣ ብትሉት ይሆናል» የሚለውን አገኘ፡፡ ለያዕቆብም ነገረው፡፡ ያዕቆብም ወደ ከሊፋው በማምጣት «በክርስቲያኖች መጽሐፍ ላይ እንዲህ ስለሚል ይህንን ፓትርያርኩ ያሳየን» አለው፡፡ ከሊፋው ተገረመ፡፡ ፓትርያርኩንም ጠርቶ ጠየቀው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ይህ ቃል በእውነት እንዳለ ነገረው፡፡
ተራራው ካለበት ተነሣ፤
ከሊፋውም «በእውነት የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይሁን ውሸት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካቃታቸው ግን ሕዝቡን እያታለሉ ነውና መቀጣት አለባቸው» ብሎ አሰበ፡፡

ከሊፋ አል ሙኢዝ ለአባ አብርሃም አራት ምርጫ አቀረበለት

 1. የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር ወይም
 2. እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው ወይም
 3. ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ወይንም
 4. በሰይፍ መጥፋት

ፓትርያርክ አብርሃም ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቀ፡፡ ከከሊፋው ዘንድ ከወጣ በኋላም ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱን እና ምእመናኑን ሰበሰበ፡፡ ያጋጠመውንም ነገር ነግሮ በመላዋ ግብጽ የሦስት ቀን ጾም እና ጸሎት አወጀ፡፡

በሦስተኛው ቀን ማለዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአባ አብርሃም ሶርያዊ ተገለጠችለት፡፡ «ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ፡፡ ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ አንድ ዓይና የሆነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱ ይህንን ተአምር ያደርግልሃል» አለቺው፡፡

አባ አብርሃም ወዲያው ከመንበረ ጵጵስናው ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ፡፡ በመካከሉም አንድ በገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ፡፡ ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ፡፡ ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው፡፡ የሆነውንም ነገረው፡፡

ሰው «እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ይህ እንዴት ይቻለኛል» አለው፡፡

አባ አብርሃምም ያዘዘቺው ድንግል ማርያም መሆንዋን ነገረው፡፡

ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል፡፡ አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ «ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ» ብትለው ጫማ በሚደፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው፡፡

«አባቴ ሕዝቡን ወደ ተራራው ሰብስብ፡፡ እኔ ከአንተ አጠገብ እሆናለሁ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ አንድ መቶ አንድ መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን በሉ፡፡ ከዚያም ስገዱ፡፡ ከስግደቱ በኋላ ስታማትብ ተራራው ይነሣል » አለው፡፡

አባ አብርሃም ወደ ከሊፋው ሄዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው፡፡

ኅዳር 15 ቀን 975 ዓም ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁድ፣ ሌሎችም ተሰበሰቡ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሰገዱ፡፡ ከስግደት ተነሥተው ጸጥ ሲሉ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ፤ ፈቀቅም አለ፡፡ እንደገና ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ፡፡ «በቃ፣ በቃ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች» አለ፡፡ ክርስቲያኖቹ በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ከሳሾቻቸው አፈሩ፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ጠፋ፡፡

አባ አብርሃም በብርቱ አስፈለገው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ ይህንን የድንግል ማርያምን ተአምር ለማስታወስ ከነቢያት ጾም ጋር ተያይዞ እንዲጾም አዘዘ፡፡ በገና ጾም የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንጾማቸው ናቸው፡፡

ዛሬ ተራራው ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል፡፡ ከምዕራብም ወደ ምሥራቅ ሸሽቷል፡፡ «ሙከተም» ማለትም «የተቆራረጠ» ማለት ነው ይባላል፡፡ ይህ ተራራ ዛሬ በአሮጌዋ ካይሮ ይገኛል፡፡

ከዚህ ተአምር በኋላ ከሊፋ አል ሙኢዝ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ አያሌ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት ተጠግነዋል፡፡ አዳዲሶቹም ተሠርተዋል፡፡ ይህ ተአምር የግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ እና በሌሎችም መዛግብት ተመዝግቧልÝÝ በተአምረ ማርያም ላይ የምናገኘው ታሪክ ከእነዚህ ጥንታውያን መዛገብት የተገኘ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተራራው እና በአሮጌዋ ካይሮ የመዓልቃ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተደረጉ የአርኬዎሎጂ ቁፋሮዎችም ይህንን መስክረዋል፡፡

በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ፡፡ ክርስቲያኖቹ ወደ አካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ በመጥረግ ታሪኩ እንዳይጠፋ ታገሉ፡፡ በመጨረሻም ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ዛሬ ለብዙዎች የሥራ እድል ከፍቶላቸዋል፡፡

ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩየአል ሙከተም ተራራ ተፈልፍሎ የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡ የስምዖን ዐጽምም በመዓልቃ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ቁፋሮ ተገኝቶ በዚሁ የተራራ ቤተ ክርስቲያን በክብር አርፏል፡፡ካይሮ፤ ግብጽ

18 comments:

 1. የቅዱሱ በረከት ይደርብን።ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 2. ዲያቆን ሀብታሙ ዘ ባህርዳር ፖሊMay 20, 2011 at 2:47 AM

  አግዚአብሔር ስቡሕ በምክረ ቅዱሳን =አግዚአብሔር በቅዱሳኑ ምክር የተመሰገነ ነው በአውነት 'ቅሩብ አግዚአብሔር ለየውሃነ ልብ ነው አኛም ከልቦናቺን ከነገርነው (ከለመነው ) ይሰማናል ። ዛሬ ብዙ ውስጣዊ አና ውጫዊ የቤተክርስቲያን ጠላቶች (ተሃድሶዎች ፣መናፍቃን አንዲሁም አሕዛብ---) አሉ ትግሉ ዛሬም ቢሆን አላቁአረጠም ስለሆነም አነኚንም መዋጋት የምንችለው የመንፈስን ጥሩር ስንለብስ ነው አና የመንፈስን ጥሩር በመልበስ የበረታን አንድንሆን አምላካችን ትጉሃ ልቡና ይስጠን ፣አግዚአብሔር አትዮጵያን ይባርክ ።አሜን
  ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ዳን ጥሩ አይታ ነው ።

  ReplyDelete
 3. ቃለ ህይወት ያሰማልን!በጆሮአችን ሰምተን ያደነቅነዉን ታዐምረ እግዝዕትነ ማርያም ይበልጡኑ በዓይናችን እንዳየን ሆን!

  ReplyDelete
 4. Dinqe new.yesenafchi qintat imnet yisten.

  ReplyDelete
 5. በረከትህ ይድረሰን ዲያቆን ዳኒኤል በጣም ልቤን ከሚነካው የቅዱሳን ታሪክ አንዱ የስምኦን ጫማ ሰፊው የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ አጽሙ ያረፈበትን ቦታ መጎብኘትህ መታደል ነው፡፡ እኛም በፎቶም ለማየት መብቃታችን ትልቅ በረከት ነው፡፡ የቅዱን አምላክ አገልግሎትህን አብዝቶ ይባርክልህ!

  ReplyDelete
 6. ዳኒ እባክህን የሰምኦን ጫማ ሰፊውን ሙሉ ታሪክ ንገረን? ከዛ ድንቅ ተዓምር በኋላ እንደጠፋ ቀረ? ከዛ በኋላ ያለው ቀሪ ህይወቱስ ምን ይመስል ነበር ?
  በተረፈ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ እንደ ቅዱስ ሰምኦን ያለ መተማመኛ /መጽናኛ አባት አያሳጣን፡፡

  ReplyDelete
 7. ተስፋብርሃንMay 20, 2011 at 12:51 PM

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ይደርብን::

  አብርሃም ሶርያዊ ስሙ እንደሚነግረን የሶርያ ሰው ማለት ነው:: ግልጽ ያልሆነልኝ ነገር ታሪኩ የተፈጸመው ሶሪያ ነው ወይስ ግብጽ? ግብጽ ከሆነ አብርሃም ሶርያዊ ከሶርያ መጥቶ የግብጽ ፓትርያርክ ሆኗል ማለት ነው? ስለ ስሙና ስለ ታሪኩ ጥቂት ብትለን::

  በተረፈ እግዚአብሔር ተረፈ ጉዟችሁን ይባርክላችሁ

  ReplyDelete
 8. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 9. Ye qidus simon Bereket Yiderebin.

  ReplyDelete
 10. Leka teamere Mariam ewnet new.

  ReplyDelete
 11. Kale Hiwot Yasemalin our brother. Thanks be to God now u did good. We're strived such detailed knowledge about our church things. We've alot of social thing advisors. What we need these days is such issues that could strengthen our faith. Now u compensated what u missed in the previous post " Zeitoun Mariam". Keep on in this manner. Please be in the way that we expect you. Let God be with you.

  Tekle Mariam

  ReplyDelete
 12. ውድ ወንድሜ-ዲን ዳንኤል በጉጉት ስጠብቅህ ፍፍት አድርገህ መንፈሳዊ እንጀራን አብልተህ አረካኸኝ። እግዚአብሔር ዋጋውን ይክፈልህ። የፉኝት ልጆች በበዙባት ዓለም እንዲሁም ለአምላክችን እናት የተሰጣትን ቃል ኪዳን በመዘንጋት እኔ ከእሷ በምን አንሳለሁ የሚሉ ባይናችን በምናይበት በአሁኑ ዘመን ከፈጸመቻቸው በርካታ የማማለድ ስራ ከቦታው ተገኝተህ በመተረክህ ጥላ ከለላ ሁና ትጠብቅህ። የተከፈተውን መንፈሳዊ አይንህ እስከ መጨረሻው ትጠቀምበት ዘንድ የአባቶቻችን አምላክ ይርዳህ።

  ReplyDelete
 13. Kale hiwot Yasemalen
  K&S

  ReplyDelete
 14. danie qale ywet yasmalen

  ReplyDelete
 15. እግዚአብሔር ይስጥልን ድንግል አትለይህ

  ReplyDelete
 16. ቅ/ስምኦን አባቶቸ የሉንምና ዛሬ ቶሎና

  ReplyDelete
 17. ቃለ ህይወት ያሰማልን አብዝቶ ፀጋውን ያድልህ በቀጣይም ታሪኩን ዘርዘር አድርገህ የቅዱሱን ታሪክ ብትጽፍን

  ReplyDelete