ብዙ ሰዎች ኢትዮጵያ በተባለች ከእንጨት በተሠራች መርከብ ይጓዛሉ፡፡ ሰዎቹ ለብዙ ሰዓታት በአንዳች ነገር ሲከራከሩ ቆዩ፡፡ በመጨረሻ አንድ ካህን ተነሡና ከመርከቧ እንጨት ማውለቅ ጀመሩ፡፡ ሌሎቹ ሰዎች ምንም አላሏቸውም፡፡ እየተመላለሱ ከመርከቧ እየነቀሉ እንጨት በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን መሥራት ቀጠሉ፡፡ አንድ ሼህም ብዲግ ብለው ተነሡና ከመርከቧ እንጨት መንቀል ጀመሩ፡፡ እየተመላለሱ እንጨቱን ወሰዱ፡፡ የጨረቃ ምልክት ካደረጉበት በኋላ መስጊድ መሥራት ቀጠሉ፡፡
በመርከቧ ውስጥ ካሉት ተሳፋሪዎች መካከል ሰኞ ዕለት የተወለዱት ተሰባሰቡና አንድ ቦታ ተቀመጡ፡፡ ይህንን ሲያዩ ማክሰኞም፣ ረቡዕም፣ ኀሙስም፣ ዓርብም፣ ቅዳሜም፣ እሑድም የተወለዱት ለየብቻ ተሰባሰቡ፡፡ ከዚያም ሁሉም በየራሱ መጥረቢያ፣ መጋዝ እና መዶሻ እየያዘ ተነሣ፡፡ ሃይ የሚል አልነበረም፡፡ የሚነጋገርም የለም፡፡ የሚመካከርም አልተገኘም፡፡ ሁሉም በየቡድኑ እየተነሣ የመርከቧን እንጨት እየገሸለጠ ወሰደ፡፡ ሁሉም በየጥጉ አንዳች ቤት ይሠራና «የእገሌዎች ቡድን ጽ/ቤት» ብሎ ይለጥፍበታል፡፡
መርከቧ ከግራ እና ከቀኝ ውኃ ማስገባት ጀመረች፡፡ ማንም ግን ከጉዳይ የጣፋት አልነበረም፡፡ ቀጥላም ከሥር ውኃ ማስገባት ያዘች፡፡ ማንም ምንም አልመሰለውም፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ መርከብ መሆንዋን የተሳፈሩባት ሰዎች እንኳ እስኪዘነጓት ድረስ ወላለቀች፡፡ ሁሉም የርሱ ቤት የቆመበትን ወለል እየተወ ሌላውን የመርከቧን ክፍል አወላለቀው፡፡ የሐይቁ ውኃ ከመታየት አልፎ መርከቧ ላይ ወጥቶ ይጋልብ ጀመር፡፡
መርከቧን አንድ አድርጎ የያዛት ምሶሶው ተሰብሮ ሐይቁ ውስጥ ገባ፡፡ ቀጥሎ የመርከቧን ካፒቴን የያዘው ክፍል ተነጥሎ ሰመጠ፡፡ ቀስ በቀስ መርከቧ እየተለያየች መጣች፡፡ ከዚያ ደግሞ እያንዳንዱ ቤት ብቻውን መቆም ስላልቻለ ወደ ሐይቁ ወለል መውረድ ጀመረ፡፡ አንዱ ቡድን አንዱን እንዳይረዳው መገናኛው ተቆርጧል፡፡ ያለው አማራጭ አንዱ ሲወድቅ አንዱ ማየት ብቻ ሆነ፡፡ ቤቶቻቸው እየሰመጡ ሲሄዱ በየቡድኑ የተሰባሰቡት ተሳፋሪዎች የቻለ እየዋኘ፤ ያልቻለም እየተገፋ ወደ ዳር ወጣ፡፡
ሁሉም ወደ ባሕሩ ዳር ከወጣ በኋላ ለምን እንዲህ ሆነ? እያለ ማሰብ ጀመረ፡፡ አንድ ሽማግሌ ተነሡና እንዲህ አሉ «ሁላችንም ለራሳችን ብቻ ስናስብ የጋራውን ነገር ተውነው፡፡ በተባበርን ጊዜ አብረን ስንሄድ ነበር፡፡ ለእኔ ብቻ ስንል ግን ሁሉንም ነገር አጣን፡፡ ሁላችንም ለራሳችን የሚያስፈልገንን ማድረጋችንን ነው ያየነው፡፡ በጋራ የሚያስፈልገንን ነገር ማየት አልቻልንም፡፡ እናም ይኼው መርከቧን አጣናት» አሉ ዕንባ በዓየናቸው እየሞላ፡፡
«መርከቧ ኢትዮጵያ ናት» አሉ አንዲት እናት፡፡ «እኛም ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ ኢትዮጵያ ከሁላችንም ጥቅም ትበልጣለች፡፡ ከሁላችንም ፍላጎት ትበልጣለች፡፡ ከሁላችንም ድምር ትበልጣለች፡፡ እኛ ግን የየራሳችንን ብቻ ነው የምናየው፡፡ ኢትዮጵያ ከየቤተ እምነቱ ትበልጣለች፡፡ ከየፖለቲካ ፓርቲው ትበልጣለች፡፡ ከየማኅበራቱ ትበልጣለች፣ ከየርእዮተ ዓለሙም ትበልጣለች፡፡ መርከቧ ውስጥ ሁነን የፈለግነውን ማድረግ አንችል ነበር፡፡ መርከቧን አፍርሰን ግን ምንም ማድረግ አልቻልንም፡፡»
«ልክ ነው» አሉ አንድ ካህን ጢማቸውን እያሻሹ፡፡ «የምንፈጥረው ቡድን፣ ማኅበር፣ ፓርቲ፣ ድርጅት፣ ኢትዮጵያን የማይጎዳ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል ነው የሚባለው፡፡ እምነትን ማራመድ እና ማስፋፋት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን የማይጎዳ መሆን አለበት፡፡ የፖለቲካ ትግል ማድረግ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን የማይጎዳ መሆን አለበት፡፡ አንድ ታሪክ ለንገራችሁማ» አሉ ካህኑ ሁሉም ቁጭ አሉ፡፡
«በአንድ ዘመን በአንድ ሰው ላይ ያሉ ዓይን፣ አፍንጫ፣ አፍ፣ ጆሮ እና እጅ ተጣሉ ይባላል፡፡ ካሁን በኋላ የሚያገናኘን ነገር የለም፤ ስለዚህ በየራሳችን እንኑር ተባባሉ፡፡ ጆሮም ለራሱ ትልቅ ቴፕ ገዛና ምርጥ ምርጥ ሙዚቃ ማዳመጥ ብቻ ሆነ ሥራው፡፡ ዓይንም ለራሱ ዴክ እና ቴሌዥን ገዝቶ ምርጥ ምርጥ ፊልሞች ማየት ጀመረ፡፡ አፍም ዘመናዊ ማስቲካዎች እና ከረሜላዎች ገዝቶ በጣዕማቸው መዝናናት ቀጠለ፡፡ እጅም በፊናው ወርቅ እና ብር እየገዛ ማጌጥ ሆነ፡፡ አፍንጫም በሽቶ ተንበሸበሸ፡፡ ለሦስት ቀናት ያህል በፌሽታ ከኖሩ በኋላ ድካም ድካም ይላቸው ጀመር፡፡
አራተኛው ቀን ላይማ እንኳን ፊልም ማየት፣ እንኳን ሙዚቃ ማዳመጥ፣ እንኳን ሽቶ ማሽተት፣ እንኳን ወርቅ ማንጠልጠል ከዕንቅልፍ ችሎ መነሣትም አቃታቸው፡፡ ዓይን ተስለመለመ፡፡ ጆሮ ዛለ፡፡ አፍ ደረቀ፡፡ እጅ ተዝለፈለፈ፡፡ አፍንጫ ከረደደ፡፡ ምን ይዋጣቸው፡፡
በዚህ ጊዜ ከወደ ታች አንድ ድምፅ ተሰማ፡፡ ያም ሆድ ነበረ፡፡ «እናንተ ሞኞች አፍንጫም ማሽተት፣ ዓይንም ማየት፣ ጆሮም መስማት፣ እጅም መንካት፣ አፍም መብላት የቻላችሁት እኔ ፈጭቼ በማቀርብ ላችሁ ምግብ መሆኑን እንዴት ረሳችሁት፡፡ የየራሳችሁን ጥቅም ብቻ ይዛችሁ ልትኖሩ አትችሉም፡፡ በጋራ የሚያስፈልጋችሁ ነገር አለ፡፡ ሰው ማለት የእናንተ ድምር አይደለም፡፡ ከድምርም በላይ ነው፡፡ በአእምሮ ሳታስቡ፣ በሳንባ ሳትተነፍሱ፣ በጨጓራ ሳትፈጩ፣ በብልቶቻችሁ ሳታስወጡ፣ በልብ ደም ሳትረጩ፣ በነርቭ ሳትገናኙ፣ በየራሳችሁ ብቻ መኖር አትችሉም፡፡» አላቸው፡፡ እኛም እንደዚያው ነን» አሉ ካህኑ፡፡ ሁሉም አጨበጨቡ፡፡
«ይበል ነው ወላሂ» አሉ ሼኩ፡፡ «ምንም እንኳን የተለያየ እምነት ቢኖረን፤ ምንም እንኳን የተለያየ ጎሳ ብንሆን፤ ምንም እንኳን የተለያየ ባህል እና ቋንቋ ቢኖረን፤ በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥም ብንሆን፤ አሸናፊ እና ተሸናፊ፣ ሀብታም እና ድኻ፣ ያገኘ እና ያጣም በንሆን፤ ከሁሉም የምትበልጥ ኢትዮጵያ የምትባል አንዲት ሀገር አለችን፡፡ የምንሠራው ቤት መርከቧን የሚያፈርስ ከሆነ ውጭ ማደራችን ይመረጣል፡፡ ብቻ የየራሳችንን ገመድ ስንስብ ዋናውን ገመድ እንዳንበጥሰው አደራ» አሉ፡፡
«ድንበራውያን እንስሳት /territorial animals/ የሚባሉ እንስሳት አሉ፡፡» አሉ አንድ ምሁር ተነሥተው፡፡ «እነዚህ እንስሳት በአንዳች እነርሱ በሚያውቁት መንገድ አካባቢያቸውን ያጥራሉ፡፡ ታድያ በአንዱ ክልል አንዱ አይገባም፡፡ ገብቶ ከተገኘ ደግሞ እርሱን አያርገኝ፡፡ እኛ እንደዚያ ለንሆን አንችልም፡፡ የራሳችንንም አስከብረን፣ የሌሎችንም አክብረን፤ ተጋግዘን እና ተሰጣጥተን መኖር ካልቻልን፤ ኢትየጵያ የሁላችን ለመሆን ካልቻለች የማናችንም መሆን አትችልም፡፡»
«እኛ ኢትዮጵያውያን ግን እስከ መቼ ነው የእንግሊዝ እግር ኳስ ተጨዋች የምን ሆነው?» አለና አንድ ወጣት ጠየቀ፡፡ ሁሉም ግራ ገብቷቸው ተመለከቱት፡፡ አንዳንዶቹም ኳስ ከማየት ያለፈ ነክተው የማያውቁ ናቸው፡፡ ሌሎቹም ስለ ኳስ ከመስማት ያለፈ አይተው አያውቁም፡፡ አሁን ግን ወጣቱ የእንግሊዝ እግር ኳስ ተጨዋች አደረጋቸው፡፡ አጃኢብ ነው፡፡
«የእንግሊዝ እግር ኳስ ከዋክብት የሆኑ እንግሊዛውያን ዓለምን በጨዋታቸው ያስደምማሉ፡፡ ክለባቸውን ዋንጫ በዋንጫ ያንበሸብሻሉ፡፡ በየቴሌቭዥን ጣቢያው ይታያሉ፡፡ ግን ምን ያደርጋል፤ እንግሊዝ ዋንጫ ከራቃት ዘመናት አለፉ፡፡ ለምን መሰላችሁ፡፡ ተጨዋቾቿ ለክለብ እንጂ ለብሔራዊ ቡድን መጨዋት አይች ሉበትም፡፡
«እና ከኛ ጋር ምን አገናኘው?» አሉ አንዲት እናት፡፡
«አዩ እናቴ እኛም ለክለብ እንጂ ለብሔራዊ ቡድን መጨዋት አንችልበትም፡፡ ለጎሳ፣ ለብሔረሰባችን፣ ለክልላችን፣ ለፓርቲያችን፣ ለድርጅታችን፣ ለቤተ እምነታችን፣ ለመሥሪያ ቤታችን፣ ለቤተሰባችን፣ ካልሆነ በቀር ከፍ አድርገን ነገሮችን በብሔራዊ ጥቅም ደረጃ ለማየት እንቸገራለን፡፡
አንዳንዱ ማንኛውንም ነገር ከክልሉ እና ከጎሳው አንፃር ብቻ ነው የሚያየው፡፡ ስለዚህ የራሱን ክልል እና ጎሳ ለመጥቀም ሲል ሌላው ቢጎዳም ቢጠቀምም፣ ቢከፋውም ቢደሰትም፣ መብቱ ቢነካ ቢከበርም ማናቸውንም ነገር ያደርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ስለምትባለው ብሔራዊ ቡድን መጨዋት አይችልበትም፡፡ ሥልጣኑን፣ መሬቱን፣ ሀብቱን፣ ዕድሉን ሁሉ በጎሳው ሰዎች ሲሞላው እርሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌሎች ያሉ አይመስለውም፡፡ እርሱ በክለቡ ውስጥ ሆኖ ከሌሎች ክለቦች ጋር መጋጠምን እንጂ በሌሎች ክለቦች ውስጥ ካሉ ተጨዋቾች ጋር አንድ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ መጨዋትን አያስበውም፣ አይጥመውምም፡፡
ዕድል ገጥሞት ለብሔራዊ ቡድን ከተመረጠ እንኳን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለክለብ ሲጫወት ታዩታላችሁ፡፡ የሚያቀብለው ለክለቡ ልጅ፣ ጎል ከገባ የሚጨፍረው ከክለቡ ልጅ ጋር፣ የሚቀራረበው ከክለቡ ልጅ ጋር ብቻ ነው፡፡ የክለቡ ልጅ ጎል ካላገባ ጎል ሳይ ገባ ቢቀር ይሻለዋል፡፡
ለብሔራዊ ቡድኑ ሲጫወት እግሩን እየተጠነቀቀ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ግን የራሱን እግር የሚጠነቀቀውን ያህል የሌሎችን እግር አይጠነቀቅም፡፡ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ የሚገኙ የሌላ ክለብ ተጨዋ ቾችን እግር ለመሥበር ቀዳሚው እርሱ ነው፡፡
እስኪ የየቤተ እምነቱ ሰዎች ራሳችሁ ተናገሩ፡፡ ለመሆኑ ሁላችሁም ለብሔራዊ ቡድን መጨዋት ትችላላችሁ? አሉ በሚገባ መጨዋት የሚችሉ፡፡ ግን ሁላችሁም አይደላችሁም፡፡ እውነት ከየቤተ እምነቱ አጀንዳ የዘለለ ሊያገናኛችሁ የሚችል ሀገራዊ ጉዳይ የለም? በአንዱ ክለብ ታቅፋችሁ ከሌላው ክለብ ጋር መጋጠም እንጂ በሌሎች ክለቦች ከሚገኙ ተጨዋቾች ጋር በብሔራዊ ቡድን ደረጃ መጨዋት ትችላላችሁ?
እናንተ አንድ ብሔራዊ ቡድን መሥርታችሁ በዚህች ሀገር ብልጽግና፣ ዕድገት፣ ዲሞክራሲ፣ ሰላም፣ አንድነት፣ ተከባብሮ እና ተፈቃቅዶ መኖር፣ ብሔራዊ መግባባት፣ ዕርቅ እና ይቅርታ እንዳይሰፍን ከሚጥሩ ኃይሎች ጋር ለምን አትጋጠሙም?
ለመሆኑ ፓርቲዎቻችን በብሔራዊ ደረጃ መጨዋት አይችሉም? ለክለባቸው ብቻ ነው የሚጫወቱት? ለእነርሱ የፖለቲካ ክለብ ከተመቸ እና ጥቅም ካስገኘ ሀገር ብትጎዳ፣ ዋንጫ ብታጣ ግድ የሌላቸው እኮ ሞልተዋል፡፡ ለመሆኑ መቼ ነው የኛ ሀገር ፓርቲዎች በሚያግባባቸው ነገር ብሔራዊ ቡድን መሥርተው ለብሔራዊ ጥቅም በዓለም ዋንጫ ላይ የሚጫወቱት፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ መሥራች ሆና ከአፍሪካ ዋንጫ የጠፋችው ለምን ይመስላችኋል? የፌዴሬሽን ሰዎቻችን ለክለባቸው እንጂ ለብሔራዊ ቡድን መጨዋት አይችሉማ፡፡ የሊግ ኮሚቴ የመያውቀው፣ ያልተመዘገበ፣ ሲጫወት በግልጽ የማይታይ የጥቅም ክለብ አላቸው፡፡ በብሔራዊ ደረጃ ስለሚያድገው እግር ኳስ ሳይሆን በዚህ ክለባቸው ደረጃ ስለሚያገኙት ጥቅም ነው የሚያስቡት፡፡
አሁን አሁንማ እግር ኳሳችን ብቻ ሳይሆን ሩጫችንም ክለባዊ እየሆነ ነው፡፡ ሁሉም ስለ መሪ እና ተመሪው፣ ሠልጣኝ እና አሠልጣኙ፣ ቡድን መሪው እና የፌዴሬሽን ኃላፊው ለየራሱ ክለብ ብቻ ነው የሚያስበው፡፡ እናም ከጥቂት ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ የሚባል ይጠፋ ይሆናል፡፡ «በድሮ ጊዜ ኃይሌ፣ ቀነኒሳ፣ ደራርቱ፣ መሠረት፣ ጥሩነሽ የሚባሉ ሯጮች ነበሩ» ብለን ለልጆቻችን ተረት የምንነግርበት ዘመን እየመጣ ነው፡
እናንተ ብቻ አይደላችሁም እኛም ክለባውያን ነን፡፡ አታዩንም ቆሻሻ ከቤት አውጥተን ደጃችን ላይ ስንደፋ? ለመንደራችን ግድ የለንም ዋናው ቤታችን ነው ማለታችን እኮ ነው፡፡ ወደ መንደሩ የሚያስገባውን መንገድ አጥራችንን እያሰፋን እያሰፋን ያጠበብነውኮ ክለባውያን ስለሆንን ነው፡፡
«አሁንም መርከቧን የጎዳት ይህ ክለባዊ አመለካከት ነው፡፡ ሌላ አይደለም» ሲል ሁሉም ሳያስቡት አንድ ላይ «ትፍትፍ ከዓይን ያውጣህ» አሉት፡፡
እናም የነቃቀሉትን እንጨት እየመለሱ፤ ሌላም እያስገቡ፤ መርከቢቱን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ሊሠሯት ተነሡ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ.የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ” መጽሔት ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።
Egziabher yitebikehe
ReplyDeleteyou right dani, egzer yichemirlih.
ReplyDeleteKeep the good job up bro, I'm sure your work will bring a lot change in our society's way of thinking.
wassihun
Thank you Dani
ReplyDeleteendixs
ቃለ ሕይወት ያሰማልን! ለአንባብያን እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን እና ዓይነ ሕሊናችንን ያብራልን!
ReplyDeleteYou are really happy, am also happy by your speciall articles.GOD BLESS YOU!!
ReplyDeleteኢትዮጵያ አንዲት እናት ናት የእናት ሆድ ዝንጉርጉር እንዲሉ እኛም ብዙ አይነት ነን ይህ መለያየታችን እንዴት ዝምድናችንን ይውጠዋል ስለኢትዮጵያዊነታችን እንዳናስብ ምን አገደን ቆም ብለን እናስብ ወገን ይህን ችግር ሳይጠፋን እናጥፋው
ReplyDeleteዲ ዳንኤል እናመሰግናለን
እግዚአብሔር ይመስገን በጣም የሚገርም እይታ ነው፡፡ ይህ መቼም አንድን ሰው ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ሁላችንንም የሚነካ፣ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እግዚአብሔር እድሜ እና ጤናውን ይስጥልን፡፡ አሜን፡፡
ReplyDeleteDear Dn Daniel
ReplyDeleteYhank you for the article !!! Egziabher yistelin yihe ye hilewena guday selehone ahun newu Lebeherawi Budenachin mechawet yalebin Egziabher hulun yayal ena lib seteto merkebwuan Tebelashta kalechibet kebefituwa beteshale melku lemesrat yabkan.
አሁንም መርከቧን የጎዳት ይህ ክለባዊ አመለካከት ነው፡፡ ሌላ አይደለም» ሲል ሁሉም ሳያስቡት አንድ ላይ «ትፍትፍ ከዓይን ያውጣህ» አሉት፡፡
ReplyDeleteEgziabher Yedkamhin FIRE Yasayih
ReplyDeletei always read your literature but this one have something spacial,u know why? it touch every one me ,you,and them all Ethiopian. This is what we need play for country not for club.
ReplyDeletewhen we play for Ethiopia, she need all the effort and play like Manchester United B/C the time is change we need to win poverty,we need to win corruption.....
So lets play......to win
God bless daniel and Ethiopia.
Ethiopia chen Yehulachen! ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ረጅም እድሜ እንመኛለን። ኢትዮጵያ ሀገራችን የሁላችንም እንደ መሆኗ መጠን ልናለማት ልንንከባከባት ይገባናል። ሀገርን መውደድ ማለት ከፍቅረ እግዚአብሔር የሚመደብ ታላቅ መንፈሳዊ ተግባር ነውና።
ReplyDeleteDaniel, Thanks again for this beautiful insight
ReplyDeleteDifference in religious belief, in political view, identity, and the way of thinking are common in all parts of the world. The best thing here is that living under the principle of unity in diversity. Whatever the case it is we have certain and basic commonalities. The commonalities are based on our countries national interest that predominantly targeted to the well being of all citizens. A society without thinking to the national interest the; destiny could be unknown. Synergy could come if we agree at least at the issue of national interest and work for that. Keep the club, but the club should be the building blocks to the National agenda and interest.
I read it in Addis Guday and still interesting.
ReplyDeleteአድናቂህ ነኝ ዳንኤል:: እይታህ እጹብ ድንቅ ነው::
ReplyDeleteዛሬ እራሴን ጨምሮ ብዙ ክለባዊያን እንዳሉ ተረዳሁ::
"እናንተ ብቻ አይደላችሁም እኛም ክለባውያን ነን፡፡ አታዩንም ቆሻሻ ከቤት አውጥተን ደጃችን ላይ ስንደፋ? ለመንደራችን ግድ የለንም ዋናው ቤታችን ነው ማለታችን እኮ ነው፡፡ ወደ መንደሩ የሚያስገባውን መንገድ አጥራችንን እያሰፋን እያሰፋን ያጠበብነውኮ ክለባውያን ስለሆንን ነው፡፡"
እናም የነቃቀሉትን እንጨት እየመለሱ፤ ሌላም እያስገቡ፤ መርከቢቱን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ሊሠሯት ተነሡ፡፡ ይሁንልን: ይደረግልን: እንደዛ ለማድረግ ልቡን ይስጠን::
ReplyDeleteእግዚያብሔር ይስጥልን !!!
Dani Egziabher yebarkehe egejege betame arife eyeta new Egziabher ke kelebawinete yetebekene
ReplyDeletethis what Ethiopia want at this time !!!!!!!
Long life for you and your family
Biruk Z
ምንም እንከን የማይወጣው ምክር አዘል መልዕክት ነው::
ReplyDeleteብቻ ላንተ ብርታቱን ይስጥህ እግዚአብሔር::
Love it
ReplyDeleteእንኩዋን ለመቤታችን ለደንግል ማርያም የልደትበአል አደረሰህ ዳኒ በውነቱ ማስተዋልን ከሰጠን በጣም አስተማሪና ከምንም በላይ ቅድሚያ ለኔ ብለን የሀገራችንና የወገናችንን ብሎም የቤተክርስቲያናችንን ችግርና ጥፋት እያየን እኔን ካልነካኝ ምንአገባኝ ብለን በግዴለሽነትና በራስወዳድነተ ተሸፍነን ለተቀመጥነው ልባችንን ሰፊአድርገን መቻቻልንና መተሳሰብን ባህርያችን ለማድረግ የሚያስችል ብሄራዊነትን የሚያነሳሳ መጣጥፍነው አንብበን ለፍሬለመብቃት የመቤታችን አማላጅነት አይለየን ላንተም ብርታቱንናእውቀቱን ያብዛልህ አሜን!
ReplyDeleteIf there were 1000 people like you, the story what you stated would have been avoided. But the world is not a perfect place. The greed, egoism is the growing epidemic that will not go away right after you publish this wonderful and very impressive script and account which is based on facts. What ever the case and outcome will be, keep doing what you have been doing to make Ethiopia a better place to live, work, learn and so on and so forth.
ReplyDeleteኢትየጵያ የሁላችን ለመሆን ካልቻለች የማናችንም መሆን አትችልም፡፡»የምንሠራው ቤት መርከቧን የሚያፈርስ ከሆነ ውጭ ማደራችንይመረጣል፡፡ እናም የነቃቀሉትን እንጨት እየመለሱ፤ ሌላም እያስገቡ፤ መርከቢቱን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ሊሠሯት ተነሡ፡፡
ReplyDeleteevery day I'm eager to read your new things on blog
ReplyDeleteyou make my soul happy full
ልዩነታችን ውበታችን ፣ ውበታችን ደግሞ አንድነታችን ነው፡፡ ከምንም በላይ አንድ ስለሚያደርጉን ነገሮች እናስብ፡፡ ብዙ አንድ የሚያደርጉን/የሚያመሳስሉን/ ነገሮች አሉን፡፡ ሌላው ይቅር ሰው መሆናችን እንኳን እንደሰው እንድናስብ ሊያደርገን ይገባል፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ሆይ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ባርክ፡፡
Really Interesting and we all Ethiopians should have to stand now for national wellbeing other than insight of selfishness
ReplyDeleteHi Dani, it is really a nice article. But the problem is that most of us including U still prefer to play for our club.
ReplyDeleteጥሩ ዕይታ ነው ዲያቆን ዳኒ
ReplyDeleteየምንፈጥረው ቡድን፣ ማኅበር፣ ፓርቲ፣ ድርጅት፣ ኢትዮጵያን የማይጎዳ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል ነው የሚባለው፡፡ እምነትን ማራመድ እና ማስፋፋት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን የማይጎዳ መሆን አለበት፡፡ የፖለቲካ ትግል ማድረግ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን የማይጎዳ መሆን አለበት፡፡Keep the club, but the club should be the building blocks to the National agenda and interest. thank you,D/Danie
ቃለህይወት ያሰማልን ዕድሜና ጤና ይስጥልን
ቃለ ሀይወት ያሰማልን
ReplyDeleteዳኒ
dear almighty GOD bless daniel and all his family.....
ReplyDeleteእናንተ አንድ ብሔራዊ ቡድን መሥርታችሁ በዚህች ሀገር ብልጽግና፣ ዕድገት፣ ዲሞክራሲ፣ ሰላም፣ አንድነት፣ ተከባብሮ እና ተፈቃቅዶ መኖር፣ ብሔራዊ መግባባት፣ ዕርቅ እና ይቅርታ እንዳይሰፍን ከሚጥሩ ኃይሎች ጋር ለምን አትጋጠሙም?
ReplyDeleteIt is a great advice God bless you.
ሰላም ላንተ ይሁን ዲያቆን ዳንኤል የኔ አስተያየት እነኳን ከፅሁፍህ ጋር በቀጥታ የተገናኘ አይደለም በአደባባይ የጡመራ መድረክ የተለያዩ ጽሁፎችን የሚያስነብበን ወዳጅህ ዲያቆን ኤፍሬም ምን ነክቶት እንደጠፋ የምታዉቀዉ ነገር ካለ ብትነግረኝ ብዬ ነዉ፡፡ በሱ የጡመራ መድረክ ላይ እኔን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች ስለ ዲያቆን ኤፍሬም መጥፋት ቢጠይቁም መልስ ስላላገኘን ነዉ እባክህን ዲያቆን ዳንኤል ምላሽህን እጠብቃለሁ፡፡
ReplyDeleteቸር ወሬ ያሰማን
Wow,I found it interesting.Thankyou.Let me complement your thought from 1corinthians 12 :14-26.For the body does not consist of one member but of many....And if the ear should say, ``Because I am not an eye,I do not belong to the body, ``that would not make it any less a part of the body.If the whole body were an eye,where would be the hearing?....If all were a single organ,where would the body be?As it is ,there are many parts,yet one body....but that the members may have the same care for one another.If one member suffers,all suffer together;if one member is honoured,all rejoice together.
ReplyDeleteYes!
ReplyDeletePlease tell us about D. Ephrem
if you have info. He used to give
reply for his readers concern. But,
now he is silent.
Kale Hiwot Yasemalin
ReplyDeleteAmeha Giyorgis
DC Area
ችግሩ እንኳን የካፒቲኑ ነው !!!! ምኑን ሊነዳ ነው ሰገነጣጥሏት ቆሞ የሚያየው፤ ወይም ለግዜው ያልተጠቀሰ ጀልባ አዘጋቷል (ዳንኤል የደበቅከን ካለ)! ህዝብ ለሀገሩ ፍቅር መስራት የሚየቆመው፤ ወንዙ ፣ ተራራው፣ አምቅ ሀብቱ፤ በህሉ …. አስጠልቶት አይደለም!! ችግሩ ከመሪው ነው፡፡ መንግሰት ቅን ካልሆነ ምን ይደረጋል! መንገዱን የውቁታል ተብለው ከፊት ስለሆኑ ብቻ መረ ናቸው ብለን ዝም ካልን፤ ለአህያም ግዜ የድረሳት፡፡
ReplyDelete«አዩ እናቴ እኛም ለክለብ እንጂ ለብሔራዊ ቡድን መጨዋት አንችልበትም፡፡ ለጎሳ፣ ለብሔረሰባችን፣ ለክልላችን፣ ለፓርቲያችን፣ ለድርጅታችን፣ ለቤተ እምነታችን፣ ለመሥሪያ ቤታችን፣ ለቤተሰባችን፣ ካልሆነ በቀር ከፍ አድርገን ነገሮችን በብሔራዊ ጥቅም ደረጃ ለማየት እንቸገራለን፡፡
ReplyDeleteአንዳንዱ ማንኛውንም ነገር ከክልሉ እና ከጎሳው አንፃር ብቻ ነው የሚያየው፡፡ ስለዚህ የራሱን ክልል እና ጎሳ ለመጥቀም ሲል ሌላው ቢጎዳም ቢጠቀምም፣ ቢከፋውም ቢደሰትም፣ መብቱ ቢነካ ቢከበርም ማናቸውንም ነገር ያደርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ስለምትባለው ብሔራዊ ቡድን መጨዋት አይችልበትም፡፡ ሥልጣኑን፣ መሬቱን፣ ሀብቱን፣ ዕድሉን ሁሉ በጎሳው ሰዎች ሲሞላው እርሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌሎች ያሉ አይመስለውም፡፡ እርሱ በክለቡ ውስጥ ሆኖ ከሌሎች ክለቦች ጋር መጋጠምን እንጂ በሌሎች ክለቦች ውስጥ ካሉ ተጨዋቾች ጋር አንድ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ መጨዋትን አያስበውም፣ አይጥመውምም፡፡
You have put your finger print in all Ethiopian heart so far.But u must record all your things soon ,coz We're uncertain about tomorrow.
ReplyDeleteKeep it up Dani
thanks...
ReplyDeleteI liked it.
DeleteGod bless you Dear Dani.