Thursday, April 7, 2011

«እያነቡ እስክስታ»


የሚከተለውን ታሪክ የሚያጫውተኝ በአንድ ዓለም ዐቀፍ ድርጅት ውስጥ በኃላፊነት የሚሠራ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
እኔ እዚህ ሥራ ተቀጥሬ መሥራት ከጀመርኩ አሁን ሰባተኛ ዓመቴ ነው፡፡ እስካሁን ወደ አርባ አራት አገሮች ለሥራ ሄጃለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቡድን መሪ ሆኜ ከሀገሩ ባለ ሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ወይንም በዓለም ዐቀፍ ጉባኤያት ላይ ለመገኘት እጓዛለሁ፡፡ ሀገሬን ስለምወድ ፓስፖርቴ አሁንም የኢትዮጵያ ነው፡፡
የሀገሩን ቪዛ ይዤ፤ የሥራ ኃላፊነቴ ተገልጦ፣ የቡድኑ መሪ ሆኜ አውሮፕላን ማረፊያ ቸው ላይ ስደርስና ለኢሚግሬሽን ዴስኩ ፓስፖርቴን ስሰጥ የኔ ጉዳይ ከሌሎቹ ይዘገያል፡፡ የምመራቸው ልዑካን ተስተናግደው እኔ ተጨማሪ ጥያቄ እጠየቃለሁ፣ አንዳንዴም ተጨማሪ ደብዳቤ፣ ሲብስም የሚቀበለኝ አካል እንዲመጣ ይደረጋል፡፡
 ምክንያቱ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ፓስፖርቴ የኢትዮጵያ በመሆኑ እንጂ፡፡ በዚህ ምክንያት አሁን የሀገሬን ፓስፖርት መያዝ ትቼ ድርጅቱ የሚሰጠውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት መያዝ ጀምሬያለሁ፡፡ ምን አማራጭ አለኝ?
እንዲህ ዓይነት ታሪክ በየሀገሩ ነው የምሰማው፡፡ በአፍሪካ ሀገሮች በሱዳን፣ ኬንያ፣ ብሩንዲ፣ ታንዛንያ፣ ሞዛምቢክ፣ አንጎላ፣ ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ካሳያችሁ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጥፋት እንደ ተዘጋጃችሁ አድርገው መቁጠር ይቀናቸዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ አሁን አሁን የላቲን አሜሪካ ሀገሮች የሆኑት እነ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ፓናማ፣ እንኳን በታናናሽ ደሴቶች በኩል አድርገው ወደ አሜሪካ በሚሻገሩ ኢትዮጵያውያን ምክንያት ሀገራችንን በክፉ እያወቋት ነው፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ በአብዛኞቹ ኤምባሲዎች ቪዛ ስትጠይቁ የመጀመርያው እምነታቸው ልትቀሩ ትችላ ላችሁ የሚል ነው፡፡ እናም ልትቀሩ አለመቻላችሁን ማስረዳት አደጋ የደረሰበት የጃፓን የኑክሌር ተቋም ፉኩሺማ ያስከተለውን ተጽዕኖ ከማስረዳት በላይ ከባድ ይሆንባችኋል፡፡
ይህ ጉዳይ ከሁለት ክስተቶች ጋር የተገናኘ ነው፡፡ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ኤምባሲዎቹ የሚጠይቁትን ካሟሉ በኋላ ቪዛ ሲያገኙ ከሄዱበት ሀገር አይመለሱም፡፡ እነርሱ ምናልባት የተሻለ ኑሮ እና የትምህርት ዕድል ፈልገው ወይንም ሌላም ፖለቲካዊ ምክንያት ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሌሎችን አያሌ ኢትዮጵያውያንን ዕድል ይዘጋሉ፡፡ የሄዱባቸው ሀገሮች «ኢትዮጵያውያን አይመለሱም» የሚለውን ድምዳሜ እንዲደርሱ ያደርጓቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ለሥራ እና ለትምህርት የሚሄዱትን ዜጎች ያሰናክላል፡፡ ኤምባ ሲዎቹ ወይ የቪዛ መስጫ መመዘኛውን እንደ መንግሥተ ሰማያት በር ያጠቡታል ያለበለዚያም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እምቢ ይላሉ፡፡
ሁለተኛው እና ከባዱ ምክንያት የሰዎች ሕገወጥ ዝውውር ጉዳይ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራልያ ሰዎችን የሚያጓጉዙ አካላት አሉ፡፡ እንደሚሰማው ከሆነ እነዚህ አካላት ከልዩ ልዩ የኤምባሲ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ቪዛ ያገኛሉ፡፡ ከዚያም ኢትዮጵያውያን አልፈውባቸው በማያውቁ ሀገሮች በኩል እያደረጉ ያሻግራሉ፡፡
አንድ ሰሞን በዳካር ሴኔጋል በኩል አሜሪካ ይገባል ተብሎ ብዙ ወጣቶች መሄድ ጀምረው ነበር፡፡ አንደ ሰሞን ደግሞ በጓንታናሞ በኩል አሜሪካ መግባት ተጀምሯል እየተባለ ይወራ ነበር፡፡ ከኬንያ ማላዊ፣ ከማላዊ ደቡብ አፍሪካ፣ ከደቡብ አፍሪካ አርጀንቲና፣ ከአርጀንቲና ብራዚል፣ ከብራዚል ኢኩአዶር፣ ከኢኩአዶር ፓናማ፣ ከፓናማ በሜክሲኮ በኩል አሜሪካ የገባች ልጅ አግኝቼ ተርካልኛለች፡፡ ምናልባት የሚመዘግብላት አጥታ ነው እንጂ ማጂላን ከተጓዘው በላይ ነው የተጓዘችው፡፡ አንድ ጊዜ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያን አሁን ስሙን ከረሳሁትና በመካከለኛው አሜሪካ ውስጥ ከሚገኝ ደሴት ደውለውልኝ ነበር፡፡
ይህ ጉዳይ ሁለት አደጋዎች አሉት፡፡ የመጀመርያው እነዚህ ስደተኞች በየሀገሩ መጉላላት፣ መታመም እና ሲብስም የሞት አደጋ ይደርስባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ሀገሮች ከኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነት የሌላቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ ምንም የማያውቁ፣ ችግር ቢያጋጥም እንኳን የሚጮኽበት ቦታ የሌለባቸው ናቸው፡፡ ሁለተኛው አደጋ ደግሞ በሀገሪቱ ገጽታ ላይ የሚቀባው ጥላሸት ነው፡፡ ኢትዮጵያን በዚህ መንገድ ለማያውቃት ዓለም ማስተዋወቁ በነገው ጉዞዋ ላይ የዕንቅፋት ድንጋይ ማስቀመጥ ነው፡፡ ዜጎች ለሥራ፣ ለትምህርት እና ለሌሎች ጉዳዮች በዓለም ላይ የሚያደርጉትን ዝውውር ያበላሻል፡፡
ዛሬ ዛሬ አያሌ ኢትዮጵያውያን ዓለም ዐቀፍ የሥራ መስኮችን እየተወዳደሩ በማሸነፍ በልዩ ልዩ ድርጅቶች እየተቀጠሩ ነው፡፡ ለዓለም ከተሰጠው ዕድል እየተቋደሱ ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ዓለም ዐቀፍ ሥራዎች ውስጥ ሲቀጠር እርሱ ብቻ አይደለም ተጠቃሚው፡፡ ሀገሪቱ ትጠማለች፡፡ ቤተሰቡ ይጠቀማል፤ ከዚህም በተጨማሪ ለሌሎችም ኢትዮጵያውያን መንገዱን ይከፍታል፡፡ እንደዚህ ስማችን እየጠፋ እና ፓስፖርታችን ከሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር እየተያያዘ በመጣ ቁጥር ግን ይህንን የኢትዮጵያውያን ዕድል እናበላሸዋለን፡፡
ይህ ዓይነቱ የሰዎች ዝውውር በሀገራቸው ስም እና ዕድገት ላይ የሚያመጣውን የወደፊቱን ተጽዕኖ የተገነዘቡ አንዳንድ የጎረቤቶቻችን ሕዝቦች በሕገ ወጥ ተግባራት ላይ ከተያዙ በመልክ ስለምንመሳሰል ብቻ «ኢትዮጵያውያን ነን» የሚሉበት አጋጣሚ አለ፡፡ ወንጀላቸውን ብናወግዝም ለሀገራቸው ስም እና ገጽታ ያላቸውን ጥንቃቄ ግን እናደንቃለን፡፡ ምክንያቱም ዛሬ የሰበሩትን ስም ነገ በምንም ኪሳራ ሊጠግኑት አይችሉም፡፡ እነርሱ ያልፍልናል ብለው ነው ይህንን ሁሉ ያደረጉት፤ ካለፈላቸው በኋላ የሀገራቸው ስም ጠፍቶ ከጠበቃቸው ምን ዋጋ አለው?
ስለ ሦስት ዓመት ነጻነት፤ ስለ አኩስም እና ላሊበላ ሥልጣኔ፣ ስለ ቅኝ አለመገዛት፣ ለአፍሪካውያን ነጻነት ስለ ከፈልነው መሥዋዕትነት፣ የራሳችን ፊደል እና ዜማ ያለን ስለ መሆኑ ብንጮኽ የማንሰማበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ አንዳንድ ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ከተጠናወታቸው የኢትዮጵያን አሉታዊ ገጽታ ብቻ የማሳየት አባዜ ጋር የኛም የእናትን ማኅፀን የመውጋት ተግባር ሲደመርበት ነገሩን ከእሳት ወደ ረመጥ ያደርሰዋል፡፡
መንግሥትም በዚህ ጉዳይ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዚህ ሁሉ ነገር ምክንያቱ ምንድን ነው? ይህንን ፍልሰት ለምን ማስቆም አልተቻለም? እነዚህ ሰው የሚያዘዋውሩ ሰዎች የት ነው ያሉት? ማን ነው የሚተባ በራቸው? ሰዎች በሕጋዊ መንገድ የመንግሥትን ትብብር አግኝተው የሚጓዙበት መንገድስ የለም? ሕንዶች፣ ቻይናዎች፣ ፊሊፒኖች እንዴት ነው የሚሠሩት? በጥብቅ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች ሳንፈታ ገጽታችንን እንገነባለን ማለት «እያነቡ እስክስታ» ነው የሚሆነው፡፡
 
ሐራሬ፣ ዚምባብዌ

24 comments:

 1. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel
  What a sad story. Please God help us!!!! i also want to say about the comment above by Marie Kurlan seems an advertisement. I just want you to look at it since people try to take advantage of such blog. Atlanta.

  ReplyDelete
 2. what you said is absolutely right& correct
  it is each and everyone's responsibility of building our countries view. the chance is on our hand.now is the time to make difference the time that we live in pride is now past.this generation has to make his own history. really interesting tnx for sharing

  ReplyDelete
 3. ማን ያዘዋልApril 7, 2011 at 8:54 PM

  ዙንባቤ ሃራሬ እንዳለህ ነው የተረዳሁት እባክን ዳኒ ለመንጌ የከበረ ሰላምታ አቅርብልኝ። ምንም እንኳን ስለእርስዋ አሁን የምሰማው ጥሩ ነገር ባይሆንም አሁን ለአገሬ ያለኝም የፍቅር
  እርሾ እርስዎ በልቤ ያስቀመጡት ይመስለኛል። ሀለወተ እግዚአብሔርን የሚክድ ዕርዮተ አለም መምራትዎ አመራርዎትን በጥሩ እንዳልመለከትዎት ቢያደረገኝም። ለኢትዮጵያ ለቀደምት ታሪክ ያሎትን ፍቅር አደንቃለሁ። ሰላምን ሁሉ እመኝሎታለሁ ለወ/ሮ ውባንቺና
  ለልጆቻቸው ለልጅ ል ጆቻቸው የከበረ ሰላምታ እንዲያቀርቡልኝ ንገርልኝ። ቢቻልህ ቃለ መጠይቅ ብታደርግላቸው ዳኒ ደስ ይለኛል። የሞተውን የአገረና የወገን ፍቅር ትንሣኤ ሊዘሩበት
  ይችላሉ ማን ያውቃል። መልካም ዳኒ።

  ReplyDelete
 4. dane egzeabeher kante gar yhune ant ewntga ye tewhedo leje nehe

  ReplyDelete
 5. ዘ ሐመረ ኖህApril 8, 2011 at 8:45 AM

  ሰላም ለዳኒና ለእድምተኞቹ በሙሉ እኔ የማን ያዘዋልን ሃሳብ እጋራለሁ መንጌ ለሰሩት ስህተትም ይሁን ላጠፉት ጥፋት ተጸጽተው ሊሆን ይችላል ንስሃ ገብተውም ሊሆን ይችላል አረረም መረረም ስለሃገር ፍቅር ስለኢትዮጵያ አንድነትና ዳር ድንበር መከበር ያሁኑ ትውልድ ከመንጌ የሚማረው ብዙ ነገሮች አሉ የመንጌ ደካማም ሆነ ጠንካራ ጎን ጥፋትም ሆነ ልማት ብዙ ትምህርት ሊሰጥ ይችላል ከሁሉም በላይ ለመንጌም ሆነ ለበታች ሹማምንቶቻቸው የይቅርታ ልባችንን ልንከፍትላቸው ይገባል ይቅር ለእግዚአብሔር ልንባባል ያስፈልጋል የመበቃቀል እና የመወጋገዝ ታሪካችን ተለውጦ ይቅር የመንባባልበትን የመንፈሳዊና የታሪክ ጉዞ መጀመር አለብን በበኩሌ በኔና በቤተሰቦቼ በሃገሬም ላይ ለተደረጉብን ሁሉ ይቅር ለእግዚአብሔር ብያለሁ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ትንሳዔ እንዲያሳየን ይቅር እንባባል ዳኒ የታሪክ ተመራማሪ እንደመሆን መጠን እድሉን ካገኘህ ከመንጌም ሆነ ከቤተሰቡ በጣም ብዙ የታሪክ አሻራዎችን ማግኘት ትችላለህ ቸር ይግጠመን ለመንጌና ለቤተሰቡ የከበረ ሰላምታ አቅርብልኝ

  ReplyDelete
 6. Dani wat is wrong on ur pic? I cant see it.

  ReplyDelete
 7. betam tckelalek dani boy!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 8. አንዳንድ የጎረቤቶቻችን ሕዝቦች በሕገ ወጥ ተግባራት ላይ ከተያዙ በመልክ ስለምንመሳሰል ብቻ «ኢትዮጵያውያን ነን» የሚሉበት አጋጣሚ አለ፡ወንጀላቸውን ብናወግዝም ለሀገራቸው ስም እና ገጽታ ያላቸውን ጥንቃቄ ግን እናደንቃለን፡፡
  መንግሥትም በዚህ ጉዳይ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዚህ ሁሉ ነገር ምክንያቱ ምንድን ነው? ይህንን ፍልሰት ለምን ማስቆም አልተቻለም? እነዚህ ሰው የሚያዘዋውሩ ሰዎች የት ነው ያሉት? ማን ነው የሚተባ በራቸው?
  diakon manbeb yalebachew akalat yehinen blog miyanebu aymeslengem malete

  ReplyDelete
 9. Thank you Dn.Daniel, keep it up

  ReplyDelete
 10. selome ke GeremenApril 8, 2011 at 5:09 PM

  selameh yebezalen wendem Dani!!!

  yehe tekekel yehonena betam litasebebet yemigeba guday selehone yemimeleketew akal biyasebebet elalew

  cher yaseman Amen

  ReplyDelete
 11. well said!!! it reminds me what hapenned only to me in one of the airport as i hold ethiopian passport but my three kids they hold a canadian passport it was such a sad moment... rejeme edemieee

  ReplyDelete
 12. የሰሜን ሱዳን ሰው ወደካናዳ ከመምጣቱ በፊት በአዲስ አበባ ለተውሰነ አመታት ኖሮ ነበር። እርሱ ለቀበሌ የተሰወሰኑ መቶ ብር ሰጥቶ የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ ካወጣ በዋላ ከኢምግሬሽን ደግሞ የአገራችን ፓስፖርት እንዳወጣ ፤ ከክልል የምክርቤት አባላት መኪና በመጠቀም ወርቅ እንዴት ወደአዲስ አበባ እያመጣ ይነግድ እንደነበር ከጥቂት አመታት በፊት አጫወቶኛል። እርሱ አረቢኛ ከመናገሩ በስተቀር በመልኩ ከመሃል አገር ሰው በምንም አይለይም። እስቲ እናስተውል በግቦ ፓስፖርት ያገኘው ሰው አሸባሪ ቢወንና ከነፓስፖርቱ በምእራቡ አለም ቢያዝ፤ ለህዝባችን አሳፋሪ አስፋሪ አይደለም ትላላቹ።

  ReplyDelete
 13. ፍቅርተማርያምApril 11, 2011 at 2:05 PM

  ሰላም ለሁላችን
  የተነሳው ሀሳብ ጥሩ ነው
  ኢትዮጵያን ሁሉ በህጋዊ መንገድ ከሀገር መውጣት ቢፈቀድ ------
  ማነው የሚቀረው -------
  አንዷም ነኝ ለምን ብባል ከዛሬ ትላንት ይሻላል
  ሁሌም የሚገርመኝ ኢትዮጵያዊ ደማችን አንድ ነው
  ሀገራችንን ጥለን ብንሄድም አንረሳትም፡
  ሌላው ሰለመንግሰቱ ኃይለማርያም በተነሳው ሀሳብ እስማማለሁ
  ለአገሬ ያለኝም የፍቅር
  እርሾ እርስዎ በልቤ ያስቀመጡት ይመስለኛል።
  በበኩሌ በኔና በቤተሰቦቼ በሃገሬም ላይ ለተደረጉብን ሁሉ ይቅር ለእግዚአብሔር ብያለሁ፡፡
  እናም ሌሎች ------
  ያንተን ብሎግ የሚከታተሉ ከሆነ ጉዳዩን ያቀለዋል
  አምላክ ይርዳክ
  አምላክ ሀገራችንን ይባርክ
  አሜን

  ReplyDelete
 14. D/n Dani look am legal and professional worker but i have big problem at every my holly day journey coz of illegal immigrant . መንግሥትም በዚህ ጉዳይ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዚህ ሁሉ ነገር ምክንያቱ ምንድን ነው? ይህንን ፍልሰት ለምን ማስቆም አልተቻለም? እነዚህ ሰው የሚያዘዋውሩ ሰዎች የት ነው ያሉት? ማን ነው የሚተባ በራቸው? it is easy for Government to find out this group.coz it is YADEBABYE MISTER NEWENA.

  ReplyDelete
 15. tizazu .... ....... Dani keep it up

  ReplyDelete
 16. As far us our economy stayed underdeveloped and unjust. In addition to that if the government controlled by one party i don't think we can get ride of illegal immigrant.

  Ethiopians are not the only one exposed to this problem.
  From Canada

  ReplyDelete
 17. KHY Dn.Dani. Please interview the Ex-president if you get the chance. Despite the mistakes he did while in office he could share us a lot. Specially about unity, love of country and flag.

  ReplyDelete
 18. Girimbit Twldi!!!

  ReplyDelete
 19. ኤርሚያስ/ሳንሆዜ/April 18, 2011 at 12:41 AM

  መቼም ብዙ ጊዜ የሆድ የሆዴን ስለምትጽፍ እስኪ ደግሞ አንዲት ወዳጄ ያካፈለችኝን እኔም ላካፍልህ። ይህቺ ልጅ ካገሯ ከወጣች አስር አመት በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ለእረፍት ልትሄድ አንዲት ነጭ አሜሪካዊት የስራ ሃላፊዋን ስታናግራት ከመግባባታቸውና ለኢትዮጵያ ካላት የተሳሳተ አመለካከት አንጻር አልቅሳ በራብ እንዳትሞት እንዳትሄድ ማከላከሏን ስትነግረኝ በጣም ከሚያሳዝናት ገጠመኞች አንዱ መሆኑን በመግለጽ ነበር።የተለያዩ አለማት በተለያየ መልኩ ለሀገራችን ያለቸውና የሚኖራቸው አመለካከት ተጽእኖው አለምአቀፋዊ መሆኑን ከመንግስት እስከ ህዝብ ማስተዋሉ ጠቃሚ ነው። በዚህ በምኖርበት በአሜሪካ ቆይታዬ ያስተዋልኩት አንድ ነገር ቢኖር ስለሀገር ልዕልና/የበላይነት/ የሚጨነቅ ህዝብና መንግስት ማየቴን ነው። የኛን ዘመን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ፈተን ለልጆቻችን ምን አይነት አገርና የአገር ፍቅር እንደምናስረክብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው። ይህን ሀሳቤን እኔም በስደት አገር ላይ መጻፌን አልረሳሁትም አይዟችሁ። መቼ ይሆን እንደሌሎች ሀገሮች ህዝቦች የሀገራችን ችግር ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ የሚሆነው? ብቻ ብዙ ማለቱ ሳይሆን ብዙ መስራቱ ብዙ ይጠቅመናል?

  ReplyDelete
 20. i don't know the reson!

  ReplyDelete
 21. bizu danieloch egiziabher endiseten hulachinim enitselyalen

  ReplyDelete
 22. Dn. Daniel the same thing happend to me. I get a training on US. I passed all the interview, etc. but finally do you know what happened...they replied to me you are youung when you went to America you will not return back. Therefore, you are not allowed to go. Finally, I became dissapointed..... Really if I got the chance I will come back to my country. Now I am in Europe for my PhD. I will return back to home as soon as I completed my studey.....kale hiwot yasemalen

  ReplyDelete
 23. ብቻ ብዙ ማለቱ ሳይሆን ብዙ መስራቱ ብዙ ይጠቅመናል?

  ReplyDelete