Saturday, April 30, 2011

ይድረስ ለእንግሊዝ ሠርገኞች


 አየ ሠርግ አየንላችሁ፡፡ እንዴው ምን ነክቷችሁ ነው እቴ፡፡ እናንተ አሁን ንጉሣውያን ቤተሰቦች ትመስላላችሁ፡፡ አካሄዳችሁ፣ አለባበሳችሁ፣ ንግግራችሁ፣ መኪናችሁ፣ ሥነ ሥርዓታችሁ ሁሉ ዘመናዊነት የጎደለው፣ ጥንታ ጥንት ብቻ፡፡ እንኳንም እኛ ሀገር አልሆናችሁ፡፡ እንዲህ ያለውን የጥንት ወግ ስታደርጉ ብትታዩ ምን ምን የመሳሰሉ ስሞች ዳቦ ሳንቆርስ እናስታቅፋችሁ ነበር፡፡
ነፍጠኛ፣ ያለፈው ሥርዓት ናፋቂ፣ ፊውዳል፣ ርዝራዥ፣ አድኃሪ፣ ጎታች፣ አክራሪ፣ ወገኛ፣ ያልገባው፣ ኧረ ስንቱ፡፡ እንግሊዝ ሆናችሁና ተረፋችሁ፡፡ አሁን እንደዚህ ጥንታ ጥንት ነገር ሰብስባችሁ እኛ ሀገር ሠርግ ብትሠርጉ እንኳን በቴሌቭዥን ልትታዩ ማንስ ይመጣላችኋል፡፡
ለመሆኑ የጥሪ ካርዳችሁ ከየት ነው የመጣው? እዚያው እንግሊዝ ነው የተሠራው እንዳትሉ ብቻ፡፡ ይኼው ድፍን አበሻ ከአሜሪካ አይደል እንዴ የሠርግ ካርድ የሚያስመጣው፡፡ የኛ መንግሥትኮ የወረቀትን ግብር ለሠርግ ካርድ ቢያደርገው ኖሮ እንኳን የሚያማርረው ትዝ የሚለው አይገኝም ነበር፡፡ የሚያማክር አጥታችሁ ነው እንጂ እንዴት ሀገር ውስጥ በታተመ የሠርግ ካርድ ትጋባላችሁ? ሠርጋችሁስ ላይ ምን ተብሎ ይወራል? መቼም ሠርግ ለወሬ ነው እንጂ ለዕድገት ወይንም ለጽድቅ ተብሎ አይደለም፡፡
አንቺስ ሙሽሪት ለመሆኑ ምን ስትይ ነው እንደዚያ በአያቶችሽ ጊዜ የተለበሰ የሚመስል የጥንት ቬሎ ዓይነት የለበስሺው፡፡ ነውርም አይደል እንዴ? ስንት ዓይነት ዘመናዊ የሆነ ብትፈልጊ ደረት፣ ብትፈልጊ ጡት፣ ብትፈልጊ ወገብ፣ ብትፈልጊም ሌላ ነገር የሚያሳይ ቬሎ ሞልቶ፣ በሀገርሺም ከጠፋ ከውጭ ሀገር ማስመጣት እና ሀገር ጉድ ማስባል ሲቻል ምነው ምነው ልጄ፡፡
አይ እንግሊዝ መሆን፡፡ ለዚህ ለዚህ ጊዜ ነበር አበሻነት የሚጠቅመው፡፡ አታይም እንዴ እኛ ሀገር የባህል ልብስ ለብሰው የሚያገቡትን እንዴት እንደምናንጓጠጣቸው፡፡ አንዳንዶቹ እንኳን ባህላዊ የሆነ ቬሎ እንሠራለን ሲሉ አዳሜ የሠርጉን እንጀራ ሲያነሣ ስማቸውንም በቢላዋ እያነሣ ይውላል፡፡ ሠርጉ ላይማ «አንቺ ቬሎውን ከየት ሀገር ነው ያመጣችው? ማነው የላከላት? እኅቷ ውጭ ናትኮ? እርሱም ከውጭ ነው የመጣው ይዞት መጥቶ ነው አሉ፡፡ ማንም ያልለበሰው አዲስ እንደ ወረደ ነው ይባላል» እየተባለ ካልተወራ ምኑን ሠርግ ሆነው፡፡
በተለይ ሙሽሪት የምትገርሚ ነሽ የኔን የሠርግ ልብስ የምትሠራው እንግሊዛዊት መሆን አለባት ብለሽ ነበር አሉ፡፡ እናንተ ሀገር «ለሀገር ውስጥ ምርት ቅድሚያ እንስጥ» የሚለው መፈክር ሠርቷል ማለት ነው፡፡ የሚገርማችሁ ግን ይህንን መፈክር በየኤግዚቢሽን ማዕከሉ የሚያሰሙት የሀገራችን ነጋዴዎች ይህንን መፈክር ሲያሰሙ እንኳን አንድም የሀገር ውስጥ ምርት አይለብሱም፡፡ እኛ ሀገር ይኼ መፈክር የሚሠራው ለድኻ ነው፡፡ እናንተ ለሀብታም መሥራቱ ገረመኝ፡፡ ሳስበው ሳስበው ግን አሜሪካ የሚኖር ዘመድ ያላችሁ አይመስለኝም፡፡ ምነው ዲቢ ሞልታችሁ ጥቂት ጊዜ እዚያ ሰንብታችሁ ብትመጡ ኖሮ፡፡ ብታጡ ብታጡ እንዴት ዱባይ ዘመድ የላችሁም፡፡
እኔ ያፈርኩባችሁ መኪናችሁን አይቼ ነው፡፡ ወይ የንጉሥ ልጅ መሆን፡፡ እኛ ሀገር እንኳን የንጉሥ ልጅ የድኻውስ ልጅ ቢሆን አፍንጫውን ነክሶ ተበድሮ በሊሞዚን ይሄዳል እንጂ ጋሪ የመሰለ መኪና ለዕድሉም አያሳየው፡፡ ርግጥ ዛሬ በሠላሳ ብር ሊሞዚን የተጓዘውን ሙሽራ በቀጣዩ ሳምንት ታክሲ ሲጋፋ ልታገኙት ትችሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ቢሆንም ለታሪኩስ ቢሆን፡፡ ኧረ ዋናው ለቪዲዮው፡፡ «ሠርግ አላፊ ነው፣ ቪዲዮ ቀሪ ነው» የሚለው ተረት እናንተ ሀገር የለም እንዴ? በርግጥ ሁሉ ወጭ የወጣበትን ቪዲዮ ሙሽሮቹ ሳያዩት አምስት ዓመት ሊሆነው ይችላል፡፡ ቢሆንም፡፡
አስታወሳችሁኝ፡፡ ለመሆኑ ቪዲዮ ቀራጮቹ የት ላይ ነበሩ፡፡ ወይስ ጭራሽ አልነበራችሁም፡፡ እናንተ እንግሊዞች ስትባሉ የማታመጡት ነገር የላችሁምኮ፡፡ ከፊት ከፊታችሁ እየተደረደሩ «ያዛት፣ ተያያዙ፣ ቀስ በሉ፣ መሥመሩን አስተካክሉ» ካላሏችሁማ አልተቀረፃችሁም ማለትኮ ነው፡፡ ተሸውዳችኋል፡፡
የወንድ ሚዜዎችን ኮት ሴቶች ሳይይዙ፣ ወንዶቹ ሴቶች ላይ፣ ሴቶቹ ወንዶች ላይ ሳይደገፉ፣ ሁለት ሁለት እየሆኑ ሳይለቀቁ፣ እንዴት ቪዲዮ ይቀረፃል? ለመሆኑ የናንተን ሠርግ የመራው ማነው? እኛ ሀገር ሠርግ ምርጥ የሚሆነው ቪዲዮ ቀራጭ ሲመራው ነው፡፡ ቁም፣ ተቀመጥ፣ ያዝ፣ ልቀቅ፣ ቀና፣ ደፋ፣ ሳቅ፣ ፈገግ፣ ና፣ ሂድ፣ ውረድ፣ውጣ፣ እዚህ ዛፍ፣ እዚያ ዛፍ፣ እያለ እንደ ኮንዳክተር ካልመራውማ አልተጋባችሁም ማለት ነው፡፡
ኧረ ደግሞ የገረመኝ በሀገራችሁ መንገድ ጠፍቶ ነው አያቶቻችሁ በሄዱበት መንገድ በሠረገላ የሄዳችሁት፡፡ ምነው እኛ ሀገር ብትመጡ ኖሮ፤ በቀለበት መንገድ፣ በወሎ ሠፈር፣ በጎተራ መሣለጫ መንገድ፣ በመገናኛ አዲሱ መንገድ፣ በስድስት ኪሎ፣ በአራት ኪሎ፣ በላፍቶ፣ በጉለሌ በስንቱ እናዞራችሁ ነበር፡፡ ያውም ጲጵ ጲጵ ጲጵ እያስባልን፡፡ ደግሞ የመንገድ ላይ ደሴት ስናገኝ ቪዲዮ ቀራጩ ያሰልፋችሁና አዙሪት እንደ ለከፈው ሰው ደሴቱን ስትዞሩት ስትዞሩት መዋል ነው፡፡ ለቪዲዮ አሪፍ ነዋ፡፡ በርግጥ ያንን መንገድ ከልጅነታችሁ ጀምሮ የሄዳችሁበት ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ማን አድርጎ ማን ይቀራል፡፡
አንድ ያላማረባችሁን ነገር ልንገራችሁ፡፡ እንዴት የንጉሥ ልጅ ሆናችሁ ቤተ ስኪያን ገብታችሁ ተጋባችሁ? ለክብራችሁ ጥሩ አይደለም፡፡ አይ እኛ ሀገር አለመሆናችሁ ጎዳችሁ? እኛ ሀገር የበላይ መሪዎቻችን በተስኪያን ገብተው አይተን አናውቅም፡፡ ነውር መስሎን ነበርኮ፡፡ እናንተ ግን ስትገቡ ዝም ተባላችሁ? የናንተ ሀገርት ፓርቲ አይከለክልም? አንዱ በተስኪያን ገብታችሁ ከሌላው ስትቀሩ «መብታችን ተነካ፣ የሃይማኖት አድልዎ ተደረገብን፣ እነ እገሌ በተስኪያን ተገብቶ እኛጋ ለምን ይቀራል የሚል የለም እንዴ? አይ እንግሊዝ መሆን፡፡ ኢትዮጵያ ብትሆኚ አድልዎ ፈጽመሻል ተብለሽ ትገመገሚያት ነበር፡፡
አንድ ሌላ የገረመኝ ነገር አለ፡፡ እናንተ ሀገር ያሉት የቤተ ክርስቲያን መሪ ምነው በደንብ ሳናያቸው ቀረን፡፡ እንዲህ የንጉሥ ልጅ አግብቶ ቀርቶ አንድ የታወቀ ነጋዴስ ሲሞት በሚገባ መታየት አልነበረባቸውም እንዴ?፡፡ ትዝብት ነው ትርፉ፡፡ እንዲህ ባለ ጊዜ ነበርኮ የንጉሥ ወዳጅ መሆናቸውን ጎላ ጎላ ብለው ማሳየት የነበረባቸው፡፡ ተሳስተዋል፡፡ መቼም መካሪ አሳስቷቸው መሆን አለበት እንጂ እርሳቸው ደፍረው አያደርጉትም፡፡ ለወደፊቱ ባይደገም ጥሩ ነው፡፡
ምን ነው ግን የካንትበሪው ሊቀ ጳጳስ ባለ ሥልጣን አይመስሉምሳ፡፡ ከግራ ከቀኝ የሚደግፋቸው፣ ጎንበስ ቀና የሚያደርግላቸው፣ ሕዝቡን የሚገፋላቸው አጃቢ የላቸውም፡፡ በሰው ሠርግስ ቢሆን መወድስ ምናምን አይቀርብላቸውም እንዴ እንዴት በሼክስፒር ሀገር ቅኔ ሳይወርድ ቀረ? አይ እኛ ሀገር ቢሆን እንኳን እንዲህ በቴሌቭዥን የሚተላለፍ ሠርግ ቀርቶ በፎቶ ግራፍ የሚተላለፍም ከተገኘ ማን ይለቅቃል፡፡ ከብለል ከብለል የሚሉ አጃቢዎች መድረኩን ይሞሉላችሁ ነበር፡፡ ወይ ነዶ፤ ወይ እንግሊዝ መሆን፡፡
ግን እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ ሁሉ ሕዝብ አደባባይ የወጣው በገዛ ፍቃዱ ነው ወይስ በቀበሌ በኩል ተነግሮት፡፡ መቼም መመሪያ ከዴቪድ ካሜሮን ተላልፎ መሆን አለበት፡፡ እርግጥ ብዛቱ ደስ ቢልም የአደረጃጀት ችግር ግን አለበት፡፡ እንዴት አንድ የረባ መፈክር አይያዝም፡፡ ሲሆን ሲሆን ከበላይ አካል አምስት ስድስት መፈክር ተጽፎ በመመርያ መልክ መተላለፍ ነበረበት፤ ካልሆነም በቀበሌ በኩል መዘጋጀት ይገባ ነበር፡፡ ደግም አልሠራችሁ፡፡
አንድ ነገር ልምከራችሁ፡፡ ይህንን ቢቢሲ የሚባል ቴሌቭዥን እናንተ ሥልጣን ስትይዙ መቅጣት አለባችሁ፡፡ «በሠርጉ ሕዝቡ መደሰቱን ገለጠ፤ ሠርጉ ቀጣይነት እንዲኖረው ተጠየቀ፤ ይህ ሠርግ ለሌሎች አገሮች አርአያነት እንዳለው ተጠቆመ፣» እያለ እንዴት ዜና አልሠራም፡፡ እንዲህ ያለውን ከቴሌቭዥን አትቁጠሩት፡፡
ይህንን ሁሉ የለፈለፍኩት ታዝቤ ታዝቤ ሳልነግራችሁ ብቀር አምላካችሁ ይታዘበኛል ብዬ ነው እንጂ ባህላችን ስለሆነ አይደለም፡፡ እንደ ባህላችንማ ሠርግ ላይ ተገኝቶ እየበሉ ማማት እንጂ ያሙትን መናገር ነውር ነበር፡፡ በሉ ይኼ በናንተ ያየነው በለሌሎች እንዳይደገም ቢቢሲ ባለሞያዎችን ጋብዞ ውይይት ያካኺድበት፡፡
በሉ ጋብቻችሁን የአብርሃም የሣራ ያድርግላችሁ፤
ያልተጋበዘው ታዛቢያችሁ ከአዲስ አበባ

68 comments:

 1. dani betam desi yilal gin ket canada wist yetewesen family yenore yimesilel yantew akbarih zekiwos

  ReplyDelete
 2. አንድ ያላማረባችሁን ነገር ልንገራችሁ፡፡ እንዴት የንጉሥ ልጅ ሆናችሁ ቤተ ስኪያን ገብታችሁ ተጋባችሁ? ለክብራችሁ ጥሩ አይደለም፡፡ አይ እኛ ሀገር አለመሆናችሁ ጎዳችሁ? እኛ ሀገር የበላይ መሪዎቻችን በተስኪያን ገብተው አይተን አናውቅም፡፡ ነውር መስሎን ነበርኮ፡፡ እናንተ ግን ስትገቡ ዝም ተባላችሁ? የናንተ ሀገርት ፓርቲ አይከለክልም? አንዱ በተስኪያን ገብታችሁ ከሌላው ስትቀሩ «መብታችን ተነካ፣ የሃይማኖት አድልዎ ተደረገብን፣ እነ እገሌ በተስኪያን ተገብቶ እኛጋ ለምን ይቀራል?» የሚል የለም እንዴ? አይ እንግሊዝ መሆን፡፡ ኢትዮጵያ ብትሆኚ አድልዎ ፈጽመሻል ተብለሽ ትገመገሚያት ነበር፡፡

  this is true

  God bless you.

  ReplyDelete
 3. ዳንኤል፤ ከትናንትናው የጋብቻ ሥርዓት ለትልቁም ለትንሹም፤ ለባለ-ጸጋውም ለድሀውም፤ ቀስቃሽ ሆኖ ያገኘሁት የኔንም መንፈስ ያረካው እነኚህ ሁለት ወጣቶች አብረው ያቀረቡት ፀሎት ነው።

  «አባታችን ሆይ! ስለቤተሰቦቻችን፣ ስለምንካፈለው ፍቅራችን እና ስለጋብቻችን ፍስሐ እናመሰግንሀለን።

  በየዕለት ዕለቱ ውጠራ መኻል ልቦናችንን እውነተኛ እና ለሕይወት አስፈላጊ ነገሮች ላይ አተኩርልን። በጊዜያችን፣ በፍቅራችን እና በኃይላችን ቸር እንሆን ዘንድ እርዳን።

  በጋብቻችን ተጠናክረን ለሚሠቃዩት/ለሚጉላሉት ሁሉ አገልጋዮችና አጽናኒዎች እንድንሆን እርዳን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንለምንሀለን። አሜን»

  እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ኧረ እንደው ምን ይሻለናል?

  ሰይፈ ገብርኤል

  ReplyDelete
 4. ጥሩና አስተማሪ ትዝብት ነው በተለይ ለኛ ለሰርግ አፍቃሪ(ወዳድ)ሴቶች <>

  ReplyDelete
 5. thank you Dn. Daniel K.
  "Woyinon girefew fenzon endisemaw" ale ye agerachin geberie!Endih be "worq" melku lik likachin yinegeren enji!!!!!!

  ReplyDelete
 6. Thanks Dani! It's impressive to view this way. Your way of writing is always an optimist idea that gives a solution for our key problems. I believe that everybody who are an artist should do and act this way. We need hardly a solution for our grand problem. This kind of problem-solution article helps much more for our leaders in any institution either in religious or governmental. Please keep on writing always problem-solution article. I always appreciate you when you write and come with problem-solution. Most of our country writers and artists,especially those who write in the politics side are writing only the problems. As I mentioned It would be a nice article and have full meaning if they could include a solution in their argument but not necessary.
  Glory to God!
  May God gives you long life!
  Sweden.

  ReplyDelete
 7. ዲ/ን ዳንኤል የነልዑል ዊሊያምን ትውፊታዊ የሠርግ ሥነ-ሥርዓት በአጉሊ መነጽርነት ተጠቅመህ ሥርዓት አልበኝነታችንን፣ የውዳሴ ከንቱ ሱሰኞች መሆናችንን፣ ሳይኖረን የሚያንጠራራ የድሃ ወኒያችንን፣ ክብር ለሚገባው ውርደትን የማጎናጸፍ ክፉ አባዜያችንን፣ ለራሳችን እምነት ባህልና ወግ ያለንን ደካማ ግምት፣ ቀናተኛነታችንን፣ እኛም ሆንን ባለሥልጣኖቻችን ለእምነት ያለንን የተዛባ አተያይ (ባለሁበት አካባቢ ያሉ ባለሥልጣናት የንስሐ አባት መያዝ ፈልገው ሰው እንዳያያቸው ስለሰጉ ከከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ አነዲት ቤተ ክርስቲያን ሄደው መያዛቸውን አስታወስከኝ)በጠቅላላው ማንነቱን ያጣ ኢትዮጵያዊነታችንን ጨልፈህ አሳይተህናልና ምስጋናዬ የላቀ ነው።

  ከዘረዘርከው የእንግሊዛውያን ስህተት የሚያይለው ግን አንተ በአካል እንድትገኝ አለመጋበዛቸው ነው። ምክንያቱም በቴሌቪዥን መስኮት ጠባ የተመለከትካትን ክስተት እንዲህ ካየሃት በአካል ብትገኝና የቀረውን ሥርዓታቸውን ብትመለከትማ ስንቱን ጉዳችንን ባዝረከረክኸው ነበር። እንኳንም አልጠሩህ።

  ቢንያም ዘባህርዳር

  ReplyDelete
 8. D/n Daniel
  Aleqa Zenebin astaweskegn!
  Tiru tizibit

  ReplyDelete
 9. ante ahun tsehafiew menfesawi sew atemeselegnem zim belhe antaram yehone neger tesefalehe yewech kemadenek yeagerhen kemesedeb masetemar kawek awekech siluat yekesun miset metsehaf kidusun atebech alu poletikegna atehun wendeme

  ReplyDelete
  Replies
  1. Let Almighty God be with you! I don't believe that you understood the context of this essay or story at all. Either you need to go back to school to study Amharic or require a translator for you to get a clear understanding. Well as they said ignorance is a bliss.

   From Falls Church Virginia, USA

   Delete
 10. እነርሱ ጋር ያለው ሁሉ የአገር ውስጥ ነው፤የሠርግ ካርድቸው፤ ቬሎቸው ወዘተ ጭንቅላታቸውም የአገር ውስጥ ነው የሚገርመው እርሱነው ስንቶቻችን ኢትዮጵያዊ ጭንቅላት አለን?

  ReplyDelete
 11. ዳኒ ዛሬ ደግሞ ጥሩ ባለቅኔ ሆነሀል፡፡
  ቤተክነትን፣ የመገናኛ ብዙሀንን፣ ቤተመንግስትን ሞለጭካቸው እኮ፡፡ ግን አንድም ሀሰት የለውም፡፡ እኔ የሚገርመን ሌላውስ አለማዊ ስለሆነ አይደንቅም የቤተክነቱ ግን መንፈሳዊ ተብዬ ስለሆነ በትንሽ ትልቁ አሸርጋጅ መሆኑ ያቃጥላል፡፡ አሁን እስቲ ዳኒ የባለፈውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብበባ ያሁሉ ጉዳይ እንደዛ በእንጥልጥል አስቀርተው በአባይ ግድብ አስቸኳይ ስብሰባ መሰብሰብ አያበግንም፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 12. ያምራል ሙሽሮቹ ባድራሻቸው ቢደርሳቸው በወደድኩ ነገር ግን የኛ ሃገር ሙሽሮች ራሳቸውን ይገመግሙበት ይሆናል
  እግዚአብሔር ይስጥልን

  ReplyDelete
 13. ketegabahu 5years alefegn but i didn`t watch my weeding video.
  thank you dani for you telling me..

  ReplyDelete
 14. dani good job i really like it.Very good points. keep it up bro

  ReplyDelete
 15. "አንድ ነገር ልምከራችሁ፡፡ ይህንን ቢቢሲ የሚባል ቴሌቭዥን እናንተ ሥልጣን ስትይዙ መቅጣት አለባችሁ፡፡ «በሠርጉ ሕዝቡ መደሰቱን ገለጠ፤ ሠርጉ ቀጣይነት እንዲኖረው ተጠየቀ፤ ይህ ሠርግ ለሌሎች አገሮች አርአያነት እንዳለው ተጠቆመ፣» እያለ እንዴት ዜና አልሠራም፡፡ እንዲህ ያለውን ከቴሌቭዥን አትቁጠሩት፡፡" Interesting Dani, bertabet.

  GOD be with us to see things in different angle.

  ReplyDelete
 16. WOW! You really are an amazing observer and a great teacher. This is an important message to everyone who views their history ,the life of their ancestors as something to be ashamed off. We all have to know that our history is our identity and it is who we are.We should take pride in it as we can ONLY become GREAT by being our own unique self instead of becoming a second hand copied version of something else.

  ReplyDelete
 17. Wey Englizoch - Ethopiawian be rucha bicha yekedemuwachihu meslon neber. Dani be weg almatbekm endkedemnachihu asredan. Girum tsihuf blenal.

  ReplyDelete
 18. ዳኒ ጥቂት የታዘብኳቸውን ነገሮች ላካፍል

  1. ይህንን ለዓለም ያለው ፖለቲካዊም ሆነ ኤኮኖሚያዊ ፋይዳው እዚህ ግባ የማይባል፣ የፓፓራዚና የፋሽን መጽሔቶች እራት ከመሆን የማያልፉ፣ የሁለት እንግሊዛውያን ሠርግ “ዓለማቀፍ” ሠርግ ያደረገው ዐቢይ ተዋናይ በብዙዎች ዘንድ “ታማኝ የዜና ምንጭ” ተደርጎ የሚቆጠረው ቢቢሲና የነዛው ወሬ ይመስለኛል፡፡ በዚህም አውሮፓውያን የራሳቸውን ነገር ሁሉ “ዓለማቀፍ” የማድረግ ዐቅማቸው ሚዲያቸው ላይ እንዴት እንደሚመሠረት ማስተዋል ይቻላል (የእነርሱው ሊቃውንት ይህንን ማኅበራዊ ፕሮፓጋንዳ” (Social Propaganda) ይሉታል፡፡ እዚህ ላይ ራሳቸውን ሲጠሩም “ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ” ብለው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እኛም አምነን “ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ”፣ “ዓለማቀፍ ሽልማት” ስንል እንኖራለን- አንድም በድኽነታችን፤ አንድም በድንዛዜያችን፡፡

  2. እኛን ባህላችንን ይዘን ማንነታችንን መሠረት አድርገን የተሻለ ኑሮ እንዳይኖረን በየኤትኖግራፊያቸው፣ በየማስተማሪያ መጻሕፍታቸው፣ በእርዳታ ፖሊሲዎቻቸው፣ በብድር ፖሊሲዎቻቸው መከራችንን የሚሳዩን አውሮፓውያን እነርሱ ለባህሎቻቸው ምን ያህል ቀናዒ እንደሆኑ ለዚህ ሠርግ በወጣው ወጪ፣ በተደረገው ሽርጉድ ማየት ይቻላል፡፡ ከልዩ ልዩ የዓለምክፍሎች ሰዎቻቸው መምጣታቸውን በርከት ያሉ የሀገሬው ቱሪስቶች ለሁለት ቀናት ጎዳና ላይ ድንኳን ተክለው ማደራቸውን ልብ ይሏል፡፡

  3. እነርሱ ባህሎቻቸውን ይበሉባቸዋል እንጂ አይባሉባቸውም፡፡ ለቱሪዝም ገበያ ይፈጥሩባቸዋል፤ ራሳቸውን ያስተዋውቁባቸዋል፤ በተመልካች ዘንድ የገጽታ ግንባታ ይሠሩባቸዋል እንጂ የእገሌን ዘር ጭቆና አይዘክሩባቸውም፤ በጎሳዎች መካከል ጥላቻ እንዲጎለብት አያደርጉባቸውም፡፡ ሙሽሪቷ ከእንትን ጎጥ ስለሆነች የእኛን ጎጥ አይመለከትም እያሉም አይሸራደዱባቸውም፡፡ ተቃውሞ ቢኖራቸው እንኳን ተቃውሟቸውን በጨዋ መንገድ ይገልጣሉ፡፡ (በዚሁ ሠርግ ላይ አንዱ አደባባይ ጥግ ተሰብስበው የነበሩ “ዘውዳዊ ሥርዓት ያረጀና ያለፈበት ነው!” ሲሉ እንደነበሩት ሰዎች ማለቴ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህን ሰዎች ቢቢሲ ያሳያቸው አልመሰለኝም፡፡)

  4. አውሮፓውያን ምንም እንኳ ዛሬ ሃይማኖት የለሽነት የሚባል ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ታሪካቸው ከክርስትና ሃይማኖት ጋር የተሣሠረ፣ ሥልጣኔያቸው የተገነባበት የባህላቸው (የአእምሯቸው ሶፍትዌር) መታገጊያ (framework) ከክርስትና አስተምህሮ የተነሣ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ ምንም እንኳ በክርስትና ስም የሠሯቸውና የተሠሩባቸው ለቁጥር የሚያታክቱ ክፉ ሥራዎች ቢኖሩም ክርስትናን ከባህላቸው መፋቅ የሚያጎድለው ታሪክ፣ ብሎም ማንነት እንዳለ ይረዳሉ፡፡ በአባቶቻቸው ሃይማኖት ባያምኑበትም የገዛ ባህላቸውን አያንቋሽሹም- ታሪክ ነዋ! ሀገር ያለማንነት ህላዌ የላትም፡፡ ማንነት ደግሞ ያለታሪክና ያለተረክ (narrative) አይሠራም፡፡ (“ምናልባት “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም፡፡” የሚባለውን የኛን ተረት ምናልባት ጀነራል ናፒየር ከመቅደላ ከዘረፋቸው ቅርሶች ጋር ወስዶ አስተምሯቸው ይሆናል፡፡” ብለን ራሳችንን ማጽናናት ይቻላል፡፡)
  Jacques Ellul. Propaganda: The Formation of Men’s Attitudes. New York: Vintage Books, 1973

  ReplyDelete
 19. Interesting and well said! I
  was expecting your reflection
  on the wedding. There was also
  an interesting presentation on
  sheger FM 102.1 by Abdu Ali Hijira
  (ERE BEHIG)on the same issue.

  May God give us the wisdom to
  learn from this event.

  As to me there is a lesson that we
  can learn from the diverse composition
  of Egyptians Delegate that is now in
  Addis to negotiate on ABAY.

  How do you see the event?

  Thanks for sharing!

  ReplyDelete
 20. Wow really Nice obeservation thanks Dear Dn Daniel.You reminded me one of my lil sister(she was 6years old) when i got married 8years ago & she was surprised that the car was rounding every island in addis(she grew up in small towen) & finally there was a samll one she said i would lough if they did it agian & we did she was loughing & we still talk about it when ever some body gets married.U did not have choice u had to follow the camera man.

  ReplyDelete
 21. Wawu....What an observation!!!

  ReplyDelete
 22. አባግንባርApril 30, 2011 at 8:35 PM

  ኧረ ኧረ ምነው ደግሞ በስልክ ከአሜሪካ አስደውላችሁ እገሌ ከቦስቶን እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል.... ቆየ ቆይ... እገሌ ከኒው ዮርክ ደወለ.... አንዴ አንዴ እንትና ከሲያትል ደውላ ግጥም አለኝ ብላለች.... ማይኩን ጠጋ አርጉላትማ ህዝቡ ይስማ... ህምምም.... የኛ ቅኔ ዘራፊዎች ተሰደው አልቀው የለም እንዴ “ከሲኖዶሱ” ጋር ብላችሁ እንዳታዝኑ እኮ ነው ሰርጋችሁ ላይ ዝም ያሏችሁ::

  አባግንባር
  ከቦስተን

  ReplyDelete
 23. አቤት ሐበሻ! ማን ነው ባህል መጠበቅ ለ ሐበሻ የ ሚያስተምር ማንም፡፡ታዲያ እንግሊዝ ተካሄደ ተባለው መቼ ባህሉን ጠበቀ፣ መቼ የአባቶቻቸውን ሥረዓት ጠበቁ፣መቼ የሀገራቸውን የድሮ ገፅታ የሚገልጥ ልብስ ለበሱ፣መች ታዲያ ባህሉን በጠበቀ መልኩ ተጓዙ፣እንደወትሮው መች ቅኔ ተቀኘ፣መወድስ ተወደሰ ዝም በሎ ዝርው፡፡ባህልን መጠበቅስ መች እነደ ሀገሬ(ትህምርተ ስላቅ ተባበሩኝ)፡፡እግዚአብሔር ከ አንተ ጋር ይሁን!!!!

  ReplyDelete
 24. THANK YOU THANK YOU Dani. Atleast 20 million people must be read in Ethiopia.i.e with in the coming next two weeks.PLEASE ADDIS ABABA RESIDENCE PRINT AND GIVE TO ALL PEOPLE IN FREE in 4 KILO,PIASA,6 KILO....HAWASSA...MEKELE....etc.please distribute to be readable.
  Getachew

  ReplyDelete
 25. serg lezina new enji letisdikweym le edget ayhonim

  ReplyDelete
 26. ጥሩ ታዝበሀል... ወይ ነዶ አለ እኔ ተጀምሮ እስኪያልቅ ስገረም ስገረም ነበር... እውነተኛ ሰርግ እንጂ የሾው ሰርግ አልነበረም። በሰርጋቸው እግዚአብሔርን እንዳከበሩት እርሱ ኑሮአቸውን ይባርክላቸው።

  ReplyDelete
 27. Wendeme Dani good comparison Egezeabher Edemehen yarezemelen

  ReplyDelete
 28. ዲያቆን ሃብታሙ ዘ ባህርዳር ፖሊMay 1, 2011 at 12:01 AM

  በሉ ይኼ በናንተ ያየነው በለሌሎች እንዳይደገም ቢቢሲ ባለሞያዎችን ጋብዞ ውይይት ያካኺድበት፡፡
  thank you Danie ቃለ ህይወት ያሰማልን.

  ReplyDelete
 29. "መቼም ሠርግ ለወሬ ነው እንጂ ለዕድገት ወይንም ለጽድቅ ተብሎ አይደለም" አሪፍ ነው ግን ሠርግ ለወሬ ብቻ ነው የሚደረገው?

  ReplyDelete
 30. woooooooooooooow it's a good vision be iwnet tilant ke hulum belay yegeremegn ye papasu neger neber inam ahun dani degemkew lelawn gin alayehutm neber dani aayehegn .ameseginalew

  ReplyDelete
 31. እኔ ያፈርኩባችሁ መኪናችሁን አይቼ ነው፡፡ ወይ የንጉሥ ልጅ መሆን፡፡ እኛ ሀገር እንኳን የንጉሥ ልጅ የድኻውስ ልጅ ቢሆን አፍንጫውን ነክሶ ተበድሮ በሊሞዚን ይሄዳል እንጂ ጋሪ የመሰለ መኪና ለዕድሉም አያሳየው፡፡ ርግጥ ዛሬ በሠላሳ ሺ ብር ሊሞዚን የተጓዘውን ሙሽራ በቀጣዩ ሳምንት ታክሲ ሲጋፋ ልታገኙት ትችሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ቢሆንም ለታሪኩስ ቢሆን፡፡ ኧረ ዋናው ለቪዲዮው፡፡ «ሠርግ አላፊ ነው፣ ቪዲዮ ቀሪ ነው» የሚለው ተረት እናንተ ሀገር የለም እንዴ? በርግጥ ያ ሁሉ ወጭ የወጣበትን ቪዲዮ ሙሽሮቹ ሳያዩት አምስት ዓመት ሊሆነው ይችላል፡፡ ቢሆንም፡፡

  most people spend a lot of money on some thing unimportant like limozine why for?

  Any way it is a good advise.thanks and God bless you.

  ReplyDelete
 32. It is very interesting fun with a good message!! Dani tiru kene new yezerekew!!! Kale hiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 33. ዲ.ን ዳንኤል መቸም ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ነገሮች በቅርብ እና በሩቅ ጊዜ እንዲፈፀሙ የዘወትር ጸሎቴ ነው
  የቅርቡ፡ አበበች ጉበና ኖቤል ስትሸለም
  የሩቁ አንተ ስትሸለም፡፡፡፡፡፡

  ReplyDelete
 34. ዉድ ዲ/ን ዳንኤል፣

  በጣም እናመሰግናለን። በማስተዋል የተፃፈ፤የስነ-ጽሁፍ ሙያና ጥበብ የታየበት፤ በሀገራችን እየተስተዋለ ያለዉን የአላዋቂ 'ዘመናዊነት' ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ፤ ለባህላችንና ለሃይማኖታችን ትኩረት እንድንሰጥ የሚጠቁም፤ ራሳችንና የራሳችንን እንድናከብር የሚያበረታታ ጽሑፍ ነዉ። ለሁላችንም ማስተዋሉን ያድለን።

  ከንግስቲቱ ሀገር (እንግሊዝ)

  ReplyDelete
 35. Dear Daniel,

  Thanks for your significant intervention on the British Royal Wedding. Your analysis strengthened the ideal assumptions of "The one who didn't recognize his/her past will not have his/her future." Truly, speaking we the new generation are not children of our families. Every body is attempting to assimilate to the world which they didn't even know. Your analysis entail us to maintain our cultural and social values which will enable us to live our own life. Cultural diffusion and erosion will make us selfless and someone from no where. The bride and groom of the British Royal Wedding taught us how they abide themselves to their own norms and social values. Thus, it is advisable to search and being our self.

  ReplyDelete
 36. abo daniye lij nehde tsegawn yabzalh

  ReplyDelete
 37. አቤት! እኛ ግን መቼ ይሆን የምንለወጠው? በራስ መተማመን እና ማንነትን ፈልጎ ማግኘት በጣም ያስቀናል፡

  ReplyDelete
 38. wey dani,metelew mechem atata.betam new yasakegn hulachenenem neka selemetaderg malet new.egnama YERASUN AYAWEK YESEW NAFAKI honen keren keo.ahunema andand zemenawi nen bay temehert betoch,AMAREGNA MAWERATENA DENGAY MEWERWER kelkel new yelalu alu letemariwochachew.endew engelizegna mawerat eweket meslowachew yehone? besentu enkatel

  ReplyDelete
 39. This is the big issue in our mother land. Some who doesn’t have a house wants to spend thousands of birr in his/her weeding. I am not trying to judge anybody’s right because all of us have a right to do whatever we want to do. I am saying, if we focus more in cultural marriage than modern, we will be more beneficial in terms of financially and culturally. We can save some birr and help our culture to alive. I spent $1000 in my weeding 4 years ago.

  ReplyDelete
 40. Wow,you are right about our country danny.We have to make changes to our...weeding plans

  ReplyDelete
 41. እናንተ ሀገር ያሉት የቤተ ክርስቲያን መሪ ምነው በደንብ ሳናያቸው ቀረን፡፡ እንዲህ የንጉሥ ልጅ አግብቶ ቀርቶ አንድ የታወቀ ነጋዴስ ሲሞት በሚገባ መታየት አልነበረባቸውም እንዴ?፡፡ ትዝብት ነው ትርፉ፡፡ እንዲህ ባለ ጊዜ ነበርኮ የንጉሥ ወዳጅ መሆናቸውን ጎላ ጎላ ብለው ማሳየት የነበረባቸው፡፡

  ReplyDelete
 42. ወይ ነዶ፤ ወይ እንግሊዝ መሆን፡፡
  እንዴት የንጉሥ ልጅ ሆናችሁ ቤተ ስኪያን ገብታችሁ ተጋባችሁ?
  ለመሆኑ የናንተን ሠርግ የመራው ማነው? እኛ ሀገር ሠርግ ምርጥ የሚሆነው ቪዲዮ ቀራጭ ሲመራው ነው፡፡
  des yilal diakon enkuanem englizawi alhonku yasbelal.
  selitane mongenet mesloachew...."kemong dejaff mofer yikoretal" enersu beserut technology enga zemenenebet..esti yihen anbebew kebanenu yihun.

  ReplyDelete
 43. Dehna teqoma new metset bihonem yegna hager sewoch bezu limarubet yegebal

  ReplyDelete
 44. ውድ ዲያቆን ዳንኤል የከበረ ሰላምታየን እያስቀደምሁ ፣ ስለአቡነ ተክለ ሃይማኖት በጻፍኸው ውስጥ “የሃሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡” ብለህ ነበር። አሁንም ስለአገሬ የሚያስጨንቀኝ ትልቁ ጉዳይ ፣ ማንነታችን ከውስጣችን ተሸርሽሮ አልቆ ፣ የመንፈስ ልዕልና ተሟጥጦ ሃሳባችን ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ሲሆን ፤ አንተ የምታቀርባቸው ታላላቅ ቁምነገሮች ሳነብ ልቤ ትልቅ እርካታ ይሰማዋል። ከምንም በላይ ተስፋ ትዘራብኛለህ። የአንተ ጽሁፎች ለሁሉም ህዝባችን የሚደርስበትን መንገድ ሁሉ የማመቻቸት ጥረት ፣ የሁሉም አንባቢህ ሃላፊነት ሊሆን ይገባል እላለሁ። እግዚያብሄር ኢትዮጵያን እንደሚወድ ከማረጋግጥበት አንዱ እንደአንተ አይነት ጸጋውን የቀባው ኢትዮጵያዊ ማየቴ ነው። እግዚያብሄር ጸጋውን ያብዛልህ።
  ከፍያለው
  ካናዳ

  ReplyDelete
 45. Selome ke GeremenMay 2, 2011 at 7:17 PM

  wey daniiiiii Ene menem alelem betam asedememogal tebarek !!!! EGZIABHER TEGAWEN YABEZALEK yehe telek tega new telanet yauten zare be miyasegerem huneta megelet nechal tebarek tebarek tebarek !!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 46. God please give us a good heart!!!!!!!!!!!!!! thankyou Dani!

  ReplyDelete
 47. Dn. Dani ere gud honaul be hawssa , Getachew doni is appointed as a general manager of sidama hager sibket .

  ere pls chuhetachinin enasema , asema , ;;;;;;;;;;;;

  ReplyDelete
 48. "ትገመገሚያት ነበር"
  ህይወት ያለግምገማ እስኪ አስቡት
  አረ ወዲያ!

  ReplyDelete
 49. you observe it that good.
  I thank
  tokichawu

  ReplyDelete
 50. ሰላም ላንተ ዲ/ ዳንኤል ያበርታሕ የጻፍከው አሰደስቶኛል እግዚአብሔር ይጠብቅልን! እያልኩ ከሰማህ ስለዚ ጉዳይ
  አንድ ነገር ተሰማኝ ሰርጉ በዓለም ላይ ክ 2 ቢሊዎን በላይ ተመልካች ነበር የሚል
  ዜና ይደመጥ ነበር> እኔ ሰሞኑን ስጠብቅ የነበረው 2 ቢሊዎን የሚለው ተጭበርብሯል
  እነ እንትና ቢቢሲ በሚለው ሀገርኛ ተቃውሞ አለመኖሩም ደንቆኛል

  ReplyDelete
 51. kkkkkk kir kir kir kir besaq

  ReplyDelete
 52. እንኳንም አልጠሩህ አለ ወንድሜ ቢኒያም እውነቱን ነው ቢጠሩህ ኖሮ ብዙ ጉድ ነበር፡፡ ሰላመ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 53. To Anonymous before Yoni-mahider and Seyfen...,
  Please don't comment on something if you couldn't understand it. Either you didn't understand this article or you are a kind of person who is not proud of his/her culture. Unless you have some problem..., this article (view) is perfect and any positive thinker will appreciate the way how the writer viewed the wedding ceremoney.

  Ayine libonahin Yigiletsilih, deg degun endinasib yirdan fetari

  Mekonnen

  ReplyDelete
 54. ውድ ዳንኤል፣

  ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛልህ፡፡

  ላለፉት አሥር ወራት ያህል ጽሑፍህን በጥብቅ ከሚከታተሉት ተረታ ተሰልፌአለሁ፡፡ ከዚያ በፊት እድሉን ማግኘት ባለመቻሌ ነው እንዲህ ያልኩት፡፡

  በአንደኛ ዓመት አከባባር ላይ ከቀረበው ሪፖርት እንደተረዳሁት ከ100 ሺህ በላይ የጡመራው ቤተኛ መኖሩን ነው፡፡ ከእዚህ ውስጥ ከንባቡ በኋላ አስተያየት የሚሰጠው ከ10 በመቶ የሚበልጥ አይደለም፡፡

  ከእነዚህ ውስጥ በጣም ጥቂት የሚባሉት አሰተያየቶቻቸው ጽሑፉ ሊያስተላልፍ የፈለገውን መልእክት ለማጉላት ወይም ተጨማሪ መረጃ በመስጠት የጽሑፉን አስፈላጊነት ሲያጠናክሩት የሚጠልጡት ግን ድሪቶ(junk)፤ከአድናቆት ያልዘለሉ ናቸው፡፡ ዳኒ ከሚለው ጀምሮ የአድናቆት መግለጫ ቃላቶች ይወረወራሉ፡፡

  የዚህ ጡመራ መሠረታዊ ዓላማ አድናቂን ማብዛት አይደለም፡፡ ያጣነውን የማኅበረሰብ ትምህርት በሰፊው ማዳረስ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ የጡመራው አዲስ ታዳሚ በመጀመሪያዎቹ ቀናት በመገረም ቢያደንቅ አይደንቅም፡፡ ነባሮቹ ማዳነቅን እንደ ተሳትፎ ከቆጠርነው ግን ሌላ የማንቂያ ጽሑፍ የሚያስፈልገን ይመስለኛልን፡፡ የሚጻፈልንን እንደ መስታወት ተጠቅመን ራሳችን እንድንመረምርበት፥ ከዚያም በጽሑፉ መነሻነት ተገቢ ካልሆነው አካሄዳችን ወይም ጠባያችን እንድንርቅ ነው፡፡

  ይህ መሠረታዊ ነጥብ ተዘንግቶ ማድነቅ ብቻ ከሆነ የዜና ጋዜጣ አንብቦ ዞር ከማለት አይለይምና በዚህ ጉዳይ ላይ ጡመራዋ የራሷን አቋም ለታዳሚዎቿ ማቅረብ አለባት ባይ ነኝ፡፡

  በውቀቱ ስዩም የጻፈውን ጉዳይ ሞግቶ በሚያሳምን አቀራረብ መቀልበስ እየተቻለ፥ በውቀቱን በጡንቻ የሚያሸማቅቅ ትውልድ የምናፈራበት ደጀ ሰላምና የዳ.ክ እይታዎች ከሚኖሩን ይልቅ ባይኖሩን ይሻላል፡፡ ስድብ ከዚያም ሲያልፍ እንካ ቅመስ በሃሳብ ልዕልና እንዲጀግን ከሚፈልግ ትውልድ የሚወጡ መልካም ጎኖች አይደሉም፡፡ ነግ በእኔ ነውና ጡመራዋ አድናቂዎችን እንዳያዳንቁ ይልቁንስ እያንዳንዱ ጽሑፍ በራሳቸው ውስጥ ያለውን መጥፎነት ስለማሳበቁ እያስተዋሉ እንዲደነግጡ፥ እንዲለወጡም ታደርግ ዘንድ በጋራ እንትጋ፡፡

  ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሕዝቦቿ፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 55. እግዜአብሔር ይስጥልን ዲ/ዳንኤል፡፡ እኛም እኮ በክብር ብንሥቀምጣቸው ምን ያህል አገራችን ጥሩ image ይኖራት ነበር ብየ ለአንድ የሥራ ባልደረባዬ ሥነግረው በትክክል አንተ የገለጽከውን "ያለፈው ሥርዓት ናፋቂ" ነው ያለኝ፡፡

  እንደው እነደው ባህር ማዶ እንኳን ሣንሄድ ያንተ ጋብቻ ሥነሥርዓት ለብዙዎቻችን ትልቅ አስተማሪ ነበር፡፡ መቼ ይሆን እራሳችንን የምንሆነው?

  ReplyDelete
 56. dase yelale gene dagemo yegaremale

  ReplyDelete
 57. what surprised me more is prince william postpond his honeymon and went for job the next day of his marriag. by the way he works as a rescue team of RAF. he ws part of a mission who rescued a 70 year old man after his wedding. the way we give value in life is totally different

  ReplyDelete
 58. 99% men should have hated this article as opposed to 99% women should have liked the article. I like the idea in the article as I belong to 99% men.

  ReplyDelete
 59. waw, so intersting ideas u Post,

  ReplyDelete
 60. Dear Dani
  had all this happend a year before,Had i read this article thene I would be free of the mistake i have made. I rent a Limosien for my wedding day. My family in Law and i my self Had spent a lot amount for the wedding. It was a kind of full feastfull . But what i realized now i was very fool. " Jib kehede Wesha Chohe " 'Endemebalew'. I am really get ashamed whenever i fight for taxi for the trip in City. i am really get ashamed whenever i get into home for which i rented. whereus we spent more money for wedding. a huge amount of money. . 'yedeha wegegna hogne neber malet new !' .
  any how thank you very much dani your say became a mirror which showed the mistake.

  EGZIABEHRE silastemaren simu yebarek

  ReplyDelete
 61. እኔ የምለው ይሐ ጋብቻ "Royal Family Wedding" ያሉት"Unroyal Family Wedding"ኣለ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 62. wey amlakie, Antes seleseten enamesegenewalen.

  Bertalen

  ReplyDelete
 63. As usual, you have brought an issue that has plagued our society. When it comes to a psuedo- wedding,it now becomes a national cancer. I called it "psuedo" because most of the weddings are falsely represented. People spend money they never had.People are considering their wedding day as the "judgement day" where there is no tomorrow at all.Our society is so pouplist in any political, social and persobnal aspects. Wedding takes the lion share.

  ReplyDelete
 64. ዳነኤል በመጀመሪያ የምታነሳቸውን ሃሳቦች አደንቃለሁ! ነገር ግን አንተ ከነጮች ሰፈር ያየኽውን ጥንታዊ የጋብቻ ስርዓት አድንቀህ አቅርበሃል። በጣም ጥሩ ነው። እኔን ግን ከፍቶኛል ምክንያቱም ስንት ባህሉን ታሪካዊ ይዘቱን ያልለቀቅ ጋብቻ ሃገራችን ዉስጥ እንድሚካሔ እያወቅህ አንዱንም ግን ለማቅረብ አልደፈርክም። ለምን? በደምሳሳው የኛን ሃገር ጋብቻ ነቀፍክ። ጥሩም እንዳለ እያወቅን ለምን? በእርግጥ አንተ ያነሳኽው ነገር የለም ማለቴ አይደለም ደጉንም እናውራው ነው። አንተ ደግሞ እነዚህን ነገሮች አጣፍጦ የማቅረብ ችሎታ አለህ። እናም ዳንኤል የኛንም እስኪ ለማጣፈጫ ያክል ጣል አድርግልን?

  ReplyDelete
 65. የትነው አትበለኝ እኔ የተማርኩበት አገር ድንገት ነው ወደ መናፈሻው ልንዝናና እኔና ጉዋደኞቼ የደረስነው ፊት ለፊቱ ቤተክርስቲያን አለ ከፊታችን ዝምብሎ ጋሪ የሄዳል ደሞጋሪ ከተማ ምንያደርጋል አልንና ቆመን ስናይ ሙሽራውና ሙሽሪት ወርደው ቤተክርሲቲያን ገቡ ጋሪስላችሁ ሰረገላና ጋሪ የተምታታብኝ እንዳመስላችሁ ልተሞሸረ ጋሪ በቃ ጋሪ እኛ በጣም ስቀናል ለዚያውም ወጪ አገር እዚህ መጥተን እኛ በኪራይ ጭንቀት ቤተሰብ አስከብሪን ጫጫታ ነገ ሹሮ መብያሊ ሲጠፋ አብረን ልንቸገር አበሻ ራሱን ሳይሆን ለሰው ነው የሚኖረው በሬ ግዛ ግዛ አሞሌ ላይገዛ የሚባል አባባል ለኛ ልካችን ነው…

  ReplyDelete
 66. yebetekristiyan yesesete lij amlak yetebkh!!!

  ReplyDelete