Monday, April 25, 2011

የፍቅር ቦምብ


ጋዳፊን አገኘሁት፡፡ ይገርመኝ ነበረ፡፡ አርባ ሁለት ዓመት አገር ገዝቶ እንዴት አልበቃውም፣ እንዴትስ አላቅለሸለሸውም ብዬ፡፡  
«አርባ ሁለት ዓመት እንደ ሰም አቅልጠህ እንደ ገል ቀጥቅጠህ ገዛህ፡፡ ለምን በቃኝ ብለህ አትተውላ ቸውም አልኩት ተገርሜ፡፡
«ይህንን ጥያቄ ለምን እንደምትጠይቀኝ ታውቃለህ? ሥልጣን ምን እንደሆነ ገና ስላልቀመስከው ነው፡፡ እነዚህ የኔ ሀገር ሰዎችም ይህንኑ ነው የሚጠይቁኝ፡፡ አያውቁማ፤ ሥልጣን ምን እንደሆነ አንብበው ይሆናል፣ ሰምተው ይሆናል፣ በቴሌቭዥን አይተው ይሆናል፡፡ ግን በተግባር አያውቁትም፡፡ ይኼ ነው ችግሩ፡፡ ካለማወቅ የመነጨ ነው፡፡»
«እኛስ እሺ ስለማናውቀው ይሆናል፤ ተቃዋሚዎችህም ምናልባት ሥልጣንን ቀምሰው የማያውቁ ይሆናል፡፡ ሌሎች የሀገር መሪዎችምኮ፣ ሥልጣንን የያዙትምኮ ይብቃህ እያሉህ ነው»
«እነርሱምኮ ሥልጣንን አያውቁትም፡፡ አሁን ኦባማን ባለሥልጣን ትለዋለህ? ባጀቱን ለማስጸደቅ ፓርላ ማውን የሚለምን ይኼ ምን ባለ ሥልጣን ነው? ዴቪድ ካሜሮንን ነው ባለ ሥልጣን ያልከኝ? አላየኸውም በዚያች ፊት ለፊት በምታፋጥጥ ፓርላማቸው ያም ይኼም እየተነሣ በጥያቄ ሲያፋጥጠው? ማንን ነው ባለ ሥልጣን የምትለኝ? ቤርሎስኮኒን ነው? እርሱ አሁን እንኳን ባለ ሥልጣን ባለ ሱቅ መሆን ይችላል? ዳኛው፣ ዐቃቤ ሕጉ፣ የግብር መሥሪያ ቤቱ እየተነሣ እከስሃለሁ እያለ መከራውን የሚያሳየው ሥልጣንን ምኑን ያውቃዋል፡፡ እስኪ የኔ ሀገር ምክር ቤት አንድም ቀን እኔ ያመጣሁትን ሃሳብ ሲቃወም ታውቃለህ? አጨብጭቦ ከመቀበል ውጭ፡፡
«ታድያ አንተ ያመጣህውን ካልተከራከረበት፣ ካልጨመረ ካልቀነሰ፣ ካልጣለ፣ ካላነሣ ምኑን ምክር ቤት ሆነው»
«አየህ ሥልጣንን ስለማታውቅ የምትጠይቀውን ጥያቄ? ምክር ቤት ማለትኮ አንተ ሃሳብህን የምትገልጥበት መድረክ ማለት ነው፡፡ መቼም ሕዝቡን ሁሉ ሰብስበህ ሃሳብህን ልትገልጥ አትችልም፡፡ ሕዝቡን ወክሎ ሃሳብሀን የሚሰማህ ማለት ነው፡፡»  
«አሁን አንጄላ ሜርኬልን ባለ ሥልጣን ልትላት ነው? የአካባቢ ምርጫ ድምጽ አነሰኝ፣ የፓርላማ ምርጫ ደረሰብኝ እያለች ስትባንን እያደረች? አሁን ሳርኮዚ በሚቀጥለው ምርጫ ለማሸነፉ ርግጠኛ ነው? እንዴት መኖርህን ርግጠኛ አትሆንም፡፡ እኔኮ ምርጫ አይኑር አይደለም ያልኩት፡፡ ምርጫ ይኑር፤ ግን ማን የሚያሸንፍበት ምርጫ? ነው ጥያቄዬ፡፡
«እነ ኦባማኮ የኮንትራት ሠራተኞች ናቸው፡፡ ኮንትራታቸው ሲያልቅ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡ ሰው ከቤተ መንግሥት ወደ መቃብር እንጂ ከቤተ መንግሥት ወደ አፓርታማ ይገባል? ሥልጣን እና ትዳር በኮንትራት አይሆንም ወዳጄ፡፡ ሥልጣንኮ የአውሮፕላን ጉዞ አይደለም፡፡ በቀጣዩ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ አስተናጋጆቹ "እንኳን ደኅና መጣህ" ብለው እንደ ተቀበሉህ ሁሉ "ዕቃህን ሳትረሳ ውረድ" ብለው ያሰናብቱሃል፡፡ በአውሮፕላን ስትሄድ የነበርከው ሰው በእግርህ መሄድ ትጀምራለህ፡፡ እና ሥልጣን የምትለኝ ይሄንን ነው? በአውሮፕላን ስትሳፈር እዚያው ለመቅረት አይደለም፤ መውረድም እንዳለ እያሰብክ ጭምር ነው፡፡ በወጣህበት በር ነው የሚያወርዱህ፡፡ ይህ ነው የኮንትራት ሥራ ማለት፡፡ ሥል ጣንን በሚገባ የሚያውቋት ይህንን አልመከሩኝም፡፡ አጥብቀህ ያዝ ነው ያሉኝ፡፡
«እነማን ናቸው?»
«የየመኑ አብደላ ሳላህ፣ የግብፁ ሙባረክ፣ የአልጄርያው ቡተፍሊቃ፣ የሶርያው ሀፊዝ አል አሳድ፣ የዚምባቡዌው ሮበርት ሙጋቤ፣ ኧረ ብዙዎቹ አጥብቀህ ያዝ ብለው ነው የደወሉልኝ»
«ለሰላም ስምምነቱ የደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዙማ መጥቶ ነበር፡፡ ምንም አላለህም?»
«እርሱማ "እኔም እንዳንተ ግማሽ ምእተ ዓመት ብገዛ ነበር ደስ የሚለኝ፡፡ ማንዴላ የሚባል መና ፕሬዚዳንት ሁለት ዙር ሀገር እንደመራ በቃኝ ብሎ ወረደ፡፡ ሕዝቡ ቢለምነው፣ ፓርቲው ቢለምነው፤ እኔ ለሥርዓቱ እንጂ ለወንበሬ አልታገልሁም ብሎ እምቢ አለ፡፡ ክፉ ትምህርት አስተማረብን፡፡ የሀገሬ ሰው ይህንን ባየበት ዓይኑ እኔ ብዙ ዓመት ልቀመጥ ብለው ሊበላኝ ነው የሚደርሰው" ብሎ ተፀፀተ»
«ለመሆኑ ሌሎቹስ እሺ፤ ሙባረክ እንዴት እንደዚህ ያለ ምክር ይመክርሃል፤ እርሱ ወርዶ የለም እንዴ?»
«አየህ ሙባረክን ያየህ ተቀጣ ነው፡፡ ሙባረክ ሲያቀብጠው ነው የወረደው፡፡ አሁን መቆሚያ መቀመጫ አሳጥተውታል፡፡ ሀብቱን አገዱበት፣ መንቀሳቀስ ከለከሉት፡፡ ይባስ ብለው ለፍርድ ካልቀረበ እያሉ ያሟር ቱበታል፡፡ አየህ ይህ ሁሉ ከሥልጣን በመውረድ የሚመጣ ጣጣ ነው፡፡ እዚያች ወንበር ላይ ስትሆን ማን ይናገርሃል? እና እኔ ነገ ወርጄ ማንም ይጫወትብኝ እንዴ? እስኪ የኮትዲቯሩን ሎረን ባጎን እየው፡፡ እንዲያ ዓለም በሙሉ ሥልጣን ልቀቅ እና ሌላ ሀገር ሂድ ሲለው እምቢ ብሎ አሁን ለምን ራቁቱን ከጉድጓድ የወጣ ይመስልሃል? እስኪ ምን ታዘብክ አለኝ፡፡
«እኔማ "ሲለምኗት ትታ ሲጎትቷት" የሚለው የሀገሬ ተረት ነው ትዝ ያለኝ፡፡» መለስኩለት፡፡
«አየህ ሥልጣንን የማያውቁ ሰዎች በሚገባ አይረዱትም፡፡ ሎረን ባጎ ተራ ሰው ነበር፡፡ በኋላ እየወጣ እየወጣ ሄደና የሥልጣንን ስኳር ቀመሳት፡፡ አየህ አንድ ነገር ልንገርህ፡፡ ሜዳ ላይ ሆነህና ተራራ ላይ ሆነህ የምታየው ነገር አንድ ነው እንዴ
«ሊሆን አይችልም»
«ሜዳ ላይ ሆነህ የምታየው ነገር ውሱን ነው፡፡ አንዳንዱንም ትገምታለህ እንጂ አታየውም፡፡ ታራራ ላይ ስትሆን ግን ሜዳ ላይ ያላየኸውን ሁሉ ታየዋለህ፡፡ በተለይ ደግሞ የምታየው ነገር የሚያስደስት ከሆነ ውረድ ውረድ አይልህም፡፡ ሥልጣን ተራራ ነው፡፡ እዚያ ስትወጣ ብዙ የምታያቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሜዳ ላይ ሆነህ በተራራው ላይ ስላለው ነገር ትገምታለህ እንጂ ርግጠኛ አትሆንም፡፡ እዚያ ላይ ስትወጣ ግን አይተህው የማታውቀውን ነገር ታያለህ፡፡ አንተ ምን እንዳየህ ሌላው ሰው አያውቅም፡፡ ልክ እንደ ሜዳው ይመስለዋል፡፡ እና ውረድ ውረድ ይልሃል፡፡
«ሎረን ባጎ በአሥራ አንድ ዓመታት ውስጥ ብዙ ነገር አየ፡፡ ገንዘብ ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደሚገኝ አየ፡፡ ሀገርን እንደ ጓዳህ ማዘዝ እንደሚችል አየ፡፡ በኤምባሲ፣ በዲፕሎማሲ፣ በስብሰባ፣ በቴሌቭዥን ከሚባለው ውጭ ያለውን ምሥጢራዊ ቋንቋ ተማረ፡፡ ይህ ቋንቋ ባለ ሥልጣናት እና በአካባቢያቸው ያሉ አጋሮች ብቻ የሚግባቡበት ቋንቋ ነው፡፡ ይህንን ቋንቋ ከለመድክ በኋላ በሌላ ቋንቋ ማውራት ይቸግ ርሃል፡፡ ውጭ ሀገር የኖሩ ልጆችን አታይም፡፡ ቋንቋቸውን ይረሱና የሚኖሩበትን ሀገር ቋንቋ ይለምዱታል፡፡ ከዚያ ሀገራቸው ሲመለሱ በእናት ቋንቋቸው ማውራት ይቸግራቸዋል፡፡ ከሥልጣን መውረድም እንደዚህ ነው፡፡
«ሎረን ባጎን ተሸንፈሃልና ውረድ አሉት፡፡ ተራራውን ልቀቅ፣ ሜዳው ላይ ኑር፣ በተራ ሰው ቋንቋ ማውራት ጀምር ማለታቸው ነው፡፡ እንዴት ይቻላል? በተለይ አብረውት ሥልጣናቸውን ያደላደሉ ብዙ ሲቪል እና ወታደራዊ ባለ ሥልጣናት አሉ፡፡ ነጋዴዎች አሉ፡፡ የዲፕሎማሲው ማኅበረሰብ አለ፡፡ እንዴት ጥለህን ትሄዳለህ ይሉሃል? ብቻህን አይደለህምኮ፡፡ አንተ ዋርካ ነህ፡፡ ስትወድቅ ብዙ ቅርንጫፎች ከላይም ከታችም ይጎዳሉ፡፡ ዋርካ ሲወድቅ ይዟቸው የሚወድቀው ቅርንጫፎችም ሆኑ የሚወድቅባቸው ተክሎች ይጎዳሉ፡፡
«ስለዚህ እስከ ደም ጠብታ ታገለ፡፡ በመጨረሻ ተያዘ፡፡ አሁን ማንም ወዳጁ አያማውም፡፡ በወዳጆቹ እጅ ከመገደል ተርፏል፡፡ አሁን ሰው የሚሆነውን ይሆናል፡፡ ለመሆኑ እርሱ ሥልጣን እናስረክብ ቢል ማን የሚቀበለው ይመስልሃል? አንቀው ነበር የሚገሉት፡፡ አሁን እኔ ሥልጣን ልልቀቅ ብል እነዚህ ክፉ የለመዱ ልጆቼ በጤና የሚያውሉኝ ይመስልሃል
በሃሳብ ተመሰጥኩና ወደ ሀገሬ ሄድኩ፡፡
«ምን ትዝ አለህ? አለኝ፡፡»
«ብላቴን ጌታ ኅሩይ የሚባሉ አንድ ባለ ሥልጣን ነበሩ፡፡ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን፡፡ እቤታቸው የሚያሳድጉት አነር ነበራቸው፡፡ አንድ ቀን ስልክ እያወሩ በእጃቸው ለአነሩ ምግብ ይሰጡታል፡፡ እርሳቸው በስልኩ ተመስጠው ምግቡ ሲያልቅ አላወቁም፡፡ አነሩ ምግቡን ጨርሶ ምግቡ የነበረበትን የእጅ መዳፋቸውን መላስ ይጀምራል፡፡ በኋላ መዳፋቸው እየተላጠ ይሄድና ደም መውጣት ጀመረ፡፡ አነሩ ደም ሲቀምስ ይበልጥ ላሰው፡፡ በመሐል ሕመም ተሰማቸውና እጃቸውን ሰብሰብ ሲያደርጉት አነሩ በቁጣ «እምምምም» አለባቸው፡፡ ደም ቀመሳ፡፡ ከዚያ ታግሠው ጠበቁት፡፡ ልክ አሽከራቸው ሲመጣ ሽጉጣቸውን እንዲያቀብላቸው ነገሩትና በሽጉጥ መትተው ገደሉት»
«አሁን ሥልጣን ገባህ ማለት ነው፡፡ አየህ ከዚያ በፊት አነሩ የርሳቸውን ደም አልቀመሰም፡፡ አሁን ከቀመሰ በኋላ ግን ተው ማለት አደጋ ማምጣት መሆኑን ዐወቁ፡፡ ሥልጣንም እንደዚያ ነው፡፡ እነ ኦባማ በአራት ዓመት ሥልጣንን ሊያውቁት አይችሉም፡፡ ገና መቅመስ ሲጀምሩ ያባርሯቸዋል፡፡ ስለዚህ የቀድሞ ውን ኑሮ አይረሱትም፡፡ እኛ ግን ስንት ነገር አይተናል፡፡ ተራ ሆኖ መኖርን ረስተነዋል፡፡ የተራነት ትዘታው ሳይጠፋብን እንደነርሱ በጊዜ ብንመለስ ጥሩ ነበር፡፡ አሁን ግን ዘገየን፡፡ ኖርንበት፡፡ ተመልሶ ተራ ሆኖ መኖር ማርስ ሄዶ እንደ መኖር ነው ለኛ፡፡»
«ቆይ አንተ ሕዝቡ አንፈልግህም እያለህ እስከ መቼ ትቀጥላለህ?»
«ሕዝብ ምን ያውቃል? መሪኮ አባት ነው፡፡ አባት ለልጁ የሚያስፈልገውን ያደርጋል እንጂ "ልጄ ያለው ይሁን" ይላል እንዴ? ልጁ አልማርም ቢል፣ አልበላም ቢል፣ አልጠጣም ቢል፣ አልተኛም ቢል፣ አልታ ከምም ቢል፣ መብቱ ነው ብሎ ሊተወው ነው? መሪም እንደዚህ ነው፡፡ ሕዝቡ የሚያምረውን ይጠይ ቃል፤ እኛ ደግሞ የሚያምርበትን እንሰጠዋለን፡፡ ሕዝብ የሚፈልገውን ሲጠይቅ፣ የሚያስፈልገውን እንሰጠ ዋለን፡፡»
«እንዴት ግን እወድደዋለሁ ይወደኛል የምትለውን ሕዝብ በአውሮፕላን እና በመድፍ ትቀጠቅጠዋለህ?»
«ጠብኮ በሚፋቀሩ ሰዎች ይጸናል፡፡ እንደዚያ ስወዳቸው ከዱኝ፤ ውለታዬን ዘነጉት፡፡ ያንን ሁሉ መዓት ያዘነብኩባቸው ስለጠላኋቸው እንዳይመስልህ ስለምወዳቸው ነው፡፡ ከስሕተት እንዲመለሱ ብዬ ነው፡፡ ፈጣሪ መዓት የሚያወርደው ጠልቶን መሰለህ? ከስሕተት እንድንመለስ እኮ ነው፡፡ መሪም እንደዚያ ነው፡፡ ይህንን አሠራር ግን ሥልጣንን የማያውቁ ሰዎች ሊገባቸው አይችልም»
«የቱኒዚያው እና የግብጽ መሪዎች ሲወርዱ አልደነገጥክም? ይቺ ባቄላ ካደረች አላልክም?»
«ይበላቸው ነው ያልኩት፡፡ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ የግል ሬዲዮ፣ ቴሌዥን ተው ብያቸው ነበር፡፡ ሕዝብ ይብላ፣ ይጠጣ፣ ይልበስ፣ ይታከም፣ በቃ፡፡ ሌላው ነገር እባብ ማሳደግ ነው ብያቸዋለሁ፡፡ ይኼንን ኢንተ ርኔት የሚሉ ነገር ተው ብያቸዋለሁ፡፡ አልሰሙኝም ነበር፡፡ ይኼው ጦሳቸው ለኛም ተረፈን፡፡»
«አሁን ምን ይደረግ ትላለህ?»
«"ልኑርበት" የሚለውን የሀገራችሁን ሙዚቃ ጋብዝልኝ እባክህ፤ የቀረውን ነገር ከሞትኩ በኋላ ተጨቃ ጨቁት በላቸው፡፡»
© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ .የተወሰነ የግ. በሚታተመው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።


40 comments:

 1. Wow Dani betam yemegerm teufe new dese yelal

  ReplyDelete
 2. Lib yalew lib yibel!!!

  Thank you D.Daniel

  ReplyDelete
 3. 'ሕዝቡ የሚያምረውን ይጠይቃል፤ እኛ ደግሞ የሚያምርበትን እንሰጠዋለን፡፡
  ሕዝብ የሚፈልገውን ሲጠይቅ፣ የሚያስፈልገውን እንሰጠ ዋለን፡፡'
  thank you for sharing this article.

  ReplyDelete
 4. Wey Dani... Lik Bilhal...

  ReplyDelete
 5. GOOD COMENT LEB YALEW LEB YEBEL

  ReplyDelete
 6. Just Wawu!!!!Berta Dani.

  ReplyDelete
 7. tsihufu arif new, gin Ategebih 20 amet yalefewu dictator eyale, ye soriyawun Al Asad( 11 ametu new besiltan lay) metikesu ayasfeligim. Let's begin with the elephant in the house.
  I appreciate all ur views zo, berta.

  wassihun

  ReplyDelete
 8. ሰላም ላንተ ይሁን!! ይህን ፅሁፍ በደንብ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ ፡፡ እጅጉንም ወድጄዋለሁ፡፡በጣም የሚገርም ምናባዊ ወግ ነው፡፡ያውም ደግሞ ……….ጋር፡፡እባክህ የአምሳዮቹን ደግሞ አስኮምኩመኝ!!መልካም በዓል ይሁንልህ፡፡

  ReplyDelete
 9. wow great"sem ena woreqe" tehufe nwe , thanks a lot.

  ReplyDelete
 10. wow its so right. ye anerun misale wedigewalehu

  ReplyDelete
 11. Wow ዳኒ ግሩም ቃለ መጠይቅ፤ እኛ በሐራሬ ዚምባቡዌ የመንጌን ቃለ መጠይቅ ታደርጋለህ ብለን ስንጠብቅ፤ አንተ ከጋዳፊ ጋር የምናብ ውይይት አደረክ?/የመንጌ ታለቅ ወንድም ነው ብለህ ይሆን እንዴ?/፡፡ ለማንኛውም የአካሉን ካለሆነም የምናቡን የመንጌን ቆይታህን እንደምታስነብበን ተስፋ አለኝ፡፡ /ልኑርበት …/ካልክም እንግዲህ እቀበላለሁ፡፡
  አዜብ ዘሚኒሶታ

  ReplyDelete
 12. እኔ እንደዚህ ተረድቼዋለሁ !!!

  "የጎረቤቶቻችን ውድቀትና ሞት ለእኛ ማስጠንቀቂያ እንጂ የጫወታ ርእሳችን አይደለም "፡፡


  በአንድ ኩሬ ውስጥ የሚኖሩ እንቁራሪቶች ይዘላሉ ይጨፍራሉ፡፡

  ከመካከላቸው ግን አንዷ ጥግ ይዛ «አውጣኝ አውጣኝ አውጣኝ » እያለች

  ትጸልያለች ፡፡ ባልንጀሮቿም ወደ እርሷ መጥተው ፦ «ከእኛ ጋር

  የማትደሰችው ጥግ ይዘሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው? » አሏት ፡፡

  እርሷም ፦«እዚያ ማዶ ቤት ሲቃጠል አያለሁ፣ ስለዚህ አውጣኝ አውጣኝ

  እላለሁ» አለች ፡፡ እነርሱም፦ «ቤት የሚቃጠለው እዚያ ማዶ ነው ፣ እኛ

  ያለነው ውኃ ውስጥ ነው ምን አስጨንቆሽ ነው ?»አሏት እርሷም ፦«እሳቱን

  ለማጥፋት በአቅራቢያቸው ያለውን ውኃ ተጠቅመው አልጠፋ ካላቸው ውሀ

  ለመቅዳት የሚመጡት ከዚህ ነውና አውጣኝ እላለሁ»አለቻቸው፡፡ እነርሱ

  ግን ዘብተውባት ዝላያቸውን ቀጠሉ፡፡ እሳቱም እየፀና መጣ ፡፡ አቅራቢያው

  ባለው ባለው ውኃ፣ ቅጠልና አፈር ቢሞከር አልጠፋ ስላለ ያካባቢው ሰው

  ባልዲውን እየያዘ ወደ ኩሬው መጉረፍ ጀመረ፡፡ እነዛ ይዘሉ የነበሩት

  እንቁራሪቶችን ዝቀው እሳት ውስጥ ጨመሯቸው ያቺ አውጣኝ የምትለው

  እንቁራሪት ግን ዳነች ፡፡ «አውጣኝ ያለም ወጣ ፣ ያላለም ተቀጣ፡፡»

  «ዳር ሲነካ መሐል ይሆናል » እንደሚባለው እሩቅ የሚመስለው የሰዎች

  ጥፋት ካልተጠነቀቅነውና ካልጸለይን ወደ እኛም ይመጣል፡፡ የጎረቤቶቻችን

  ውድቀትና ሞት ለእኛ ማስጠንቀቂያ እንጂ የጫወታ ርእሳችን አይደለም ፡፡

  በባላገር ዳስ ጥለው ይዘፍናሉ ፡፡ ዳሱም ቶሉ ይፈርሳል፡፡ በዚህ ምክንያት

  «የዘፈን ቤት ሳይፈርስ አይቀርም »ይባላል፡፡ እንዲሁም ጭፈራና ብዙ

  ደስታ ለቅሶ እና ዋይታ ሳይመጣ አይቀርም ፡፡ ለሰዎች ማዘን ሲያለቅሱ

  ሳይሆን ዘፈን ዘፈን ሲላቸው ነው፡፡ የሚቀጥለው ለቅሶ ነውና፡፡ በእውነት

  ከክፉ ዘመን የማምለጫው መርከብ መረጃ ሳይሆን ጸሎት ነው ፡፡ አዎ

  ለመጸለይ ያለን ምክንያት ከምክንያት የሚልቅ ነው ፦

  ከዲ/ን አሸናፊ መፅሀፍ

  ReplyDelete
 13. አንድ አንድ ግዜ በስልጣን ላይ የአሉ ሰዋችን መውቀሥ ከአውነት የራቀ ይመሥለኛል፤ ሕዝቡ እራሱ እርሶ ከሥልጣን ከወረዱ ሰማዩ ከላይ ወርዶ ከምድር ጋር ይገናኛል ስለዝህ በድድሆትም ቢሆን መግዛት ይኖርቡሆታል ለህዘቡ ሰላማዊ ኑሮና ጤንነት ሲባል ብሎ ሲያበቃ ሰውን እንደ አምላክ በለወጠበት ዓለማችን መሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡንም አብሮ መውቀስ ትችቱን እውነተኛና የተሞዋላ ያደርገዋል። ሥለዚህ ሕዝቡንም አንፍራ።
  በተረፈ ጥሩ ትምህርታዊ አቀራረብ ነው፡ አርባ ዓመት ሙሉ አምኖ ተቀብሎና ሲያሞግስ ከርሞ በስተመጨረሻ ማልቅስ ተገቢ አይምስለኝም። እኔ ደፋር ነኝ ከሕዝብ ጋር መጣላት እወዳለሁ።

  I like to see things in reverse. What happened in our country and the other part of the world, the direct participation of the people. The people has the power to limit the role of the government honestly speaking. If Meles read your interview (humorous), or if you interview him you may get a different answer. He may not sit and spend time with you. He will end the conversation before it is matured. The people themselves emboldne him at the beginnning of his reign. Now, everybody who was not happy about the entire exercise is paying the price. So you need to give credit for Gadaffi for giving you honest answer.

  ReplyDelete
 14. ዳንኤል
  በዚህ ጽሑፍህ ወትሮውን እንዳስለመድከን ጉዳዮችን ጠለቅ አድርገን እንድናይ ለየት ባለ አመለካከትህ እየጠኮምከን እንደሆነ ይገባኛል። ታዲያ በዚህ መሠረት ይሄ ድርሰት ለኛ ኢትዮጵያውያን ምን የሚል መልእክት ይሆን የሚያስተላልፈው?

  ከብላቴን ጌታ ኅሩይ ምሳሌ («...አየህ ከዚያ በፊት አነሩ የርሳቸውን ደም አልቀመሰም፡፡ አሁን ከቀመሰ በኋላ ግን ተው ማለት አደጋ ማምጣት መሆኑን ዐወቁ፡፡») ሌላ በቀጥታ የሚመለከተን ምን ይሆን?

  ስለዋርካ የጠቀስከው አንድ በገጠር የታዘብኩትን አስታወሰኝ። ታዲያ በዚያ መንደር ከመቶ ዓመት በፊት ለቤተ ክርስቲያኑ ግርማ ሞገስ ይሆናል፤ ለሰው ጥላ ይሰጣል ብለው አንድ አዛውንት የተከሉት ዋርካ እውነትም ለዚያ ቤተ ክርስቲያን ግርማ ሞገስ ሆኖ ተከብሮ የኖረው ዋርካ ከግዙፍነቱ ብዛት የሰደደው ሥር፣ ያስከብረዋል የተባለውን ቤተ ክርስቲያን መሠረቱን አናግቶት ከነአካቴው አስጊ ደረጃ ላይ ደረሰ። ቅርንጫፎቹ ጣሪያውን፣ ሥሮቹ መሠረቱን ሲያጠቁት ጊዜ ልክ ሕዝብ መጀመሪያ ያስከብሩናል፣ ይሠሩልናል፣ ያበለጽጉናል ብሎ ተራራ ላይ ያወጣቸው መሪ ተብዬዎችን ሜዳው ላይ ውረዱ እንደሚላቸው፣ ያንንም ዋርካ ሕዝቡ ተሰብስቦ፣ መጥረቢያውን ስሎ፣ ቅርንጫፍ በቅርንጫፍ፣ ግንድ፣ በግንድ ከረታትፎ ሜዳ ላይ ከመረው። የእምነት ቤቱን፣ የማንነት ምልክቱን፣ ክርስትና መነሻውን፣ መቀበሪያውን ቤተ ክርስቲያኑን ሊያጠቃበት ተነሳበታ! በአካባቢው ያለውን የእርሻ ማሳ ሁሉ ውሐውን እየመጠጠ ቦና ማድረጉን እንኳ ይቅር ብሎት ኖሮ ነበር።

  እንጋዳፊም «ጠብኮ በሚፋቀሩ ሰዎች ይጸናል፡፡ እንደዚያ ስወዳቸው ከዱኝ፤ ውለታዬን ዘነጉት፡፡ ያንን ሁሉ መዓት ያዘነብኩባቸው ስለጠላኋቸው እንዳይመስልህ ስለምወዳቸው ነው፡፡ ከስሕተት እንዲመለሱ ብዬ ነው፡፡ ፈጣሪ መዓት የሚያወርደው ጠልቶን መሰለህ? ከስሕተት እንድንመለስ እኮ ነው፡፡ መሪም እንደዚያ ነው፡፡ ይህንን አሠራር ግን ሥልጣንን የማያውቁ ሰዎች ሊገባቸው አይችልም» የሚሉትን ከአምባ ገነን ውጭ ለሌላ የማይመስለውን ዓይነት ጥሬ ሥነ ልቦና ትተው ይልቁንስ መጀመሪያውን የተራራውን አቀበት ተሸክሞ ያወጣቸው ሕዝባቸው እንደሆነና አናት ላይ ቁጭ ብለው በየተፈጥሮ አቅጣጫው ወደሜዳው መፍሰስ የሚገባውን የእግዚአብሔርን ንፁህ ዝናብ እንገድበው፣ እጣቢያችንንም ቢሆን በአንድ ቦይ ብቻ እናውርደው ሲሉ፤ ከአናት ወደቁልቁል ሜዳው ገፍትሮ እንደሚያኮበልላቸው ቢገነዘቡ ነው የሚሻላቸው።

  ሰይፈ ገብርኤል

  ReplyDelete
 15. Thanks! Lib yalewu lib yibel

  ReplyDelete
 16. ክልኤቱ አኃው መንገለ ቀላይ ወረዱ፤
  አሐዱ ተመይጠ ወኢተመይጠ አሐዱ፡፡

  በሚለው ጉባኤ ቃና የሚጀምረውን የአበባው መላኩን ግጥም (“ደግ አይበረክትም” ከሚለው ሲዲው ላይ) አዳምጡት፡፡ ሰዎች በታዳጊ ሀገር ለምን ከሥልጣን እንደማይወርዱ አንድ መልስ በቆንጆ አቀራረብ ታገኛላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 17. Seltan Yezew Yeseltanen Taem Sayaweku, Lekek Kemilu Egziabehere Yetebeken.

  ReplyDelete
 18. Abebe M. Beyene said thatApril 26, 2011 at 6:22 PM

  What I learn from this nice article is that, tyrant leaders like Khadaffi creates their own world. They are perceiving what they want to perceive. They enjoyed the world they themselves created and they didn't recognize the actual world beyond their self-centric imagination. Thus, Khadaffi's perception regarding the power is reflected from his own personal tailored world.

  Abebe M. Beyene

  ReplyDelete
 19. a joy to read through this article. it helped me see the "human" side and reasoning of dictators, though its absolutely insane. And the obligation (to stay alive) they have for their close friends and allies that are very close, intimate and dangerous!!!!. They do not have the luxury to say "i am done, and call it quits" as we usually simplify it. there are hungry sharks to be fed day in day out, or else you are it.

  Those brothers who are on the side of a dictator, please realize you are supporting incredibly insane personality that has nothing to relate to you, the ordinary guy. He does not feel your pain, rather they hurt you because they love you. that is what you are supporting.

  Thank you for this beautiful piece

  ReplyDelete
 20. Becarfull!!!!!!!!!!!!!

  Minnesota ,,cherinet

  ReplyDelete
 21. . . . እኛ ግን ስንት ነገር አይተናል፡፡ ተራ ሆኖ መኖርን ረስተነዋል፡፡ የተራነት ትዘታው ሳይጠፋብን እንደነርሱ በጊዜ ብንመለስ ጥሩ ነበር፡፡ አሁን ግን ዘገየን፡፡ ኖርንበት፡፡ ተመልሶ ተራ ሆኖ መኖር ማርስ ሄዶ እንደ መኖር ነው ለኛ፡፡»

  KHY ................... Amen!

  Hiwot M.

  ReplyDelete
 22. ዲያቆን ሃብታሙ ዘ ባህርዳር ፖሊApril 28, 2011 at 12:53 AM

  «ቆይ አንተ ሕዝቡ አንፈልግህም እያለህ እስከ መቼ ትቀጥላለህ?»እንዴትስ እወድደዋለሁ ይወደኛል የምትለውን ሕዝብ በአውሮፕላን እና በመድፍ ትቀጠቅጠዋለህ?»Thank you Danie
  ቃለ ህይወት ያሰማልን.

  ReplyDelete
 23. Daniel to be frank Gadafi didn’t tell you anything about Meles ? At least he is in power for the last 20 years, why you delete the name of MELES from the list? I know you are living in Ethiopia Eskinder Nega too.

  ReplyDelete
 24. but you forgot ours dectator name on the list, anyways i know why you fear to mention that. hod siyawk doro mata aydal yamibalaw.

  ReplyDelete
 25. ይገርማል ጥሩ ቅንብር ነው አንድ ነገርም አስታውሶኛል ስልጣን በአፍሪካ የነብር ጅራት ነው አሉ እናም አይዙትም ከያዙትም ደግሞ አይለቁትም አሃ ምንነካዎ ይበላሉዋ! ምን ይሁን በጊዝዎ ምንም ምንም አድርግው የከደኑት ይከፈታላ!አሁን አሁን ደግሞ ሰርቀው ያከማቹትን እንካ ማግኘት ቀላል አልሆነም እዚላይ ደግሞ አለማቀፍ ፍርድ ምናምን እያሉ መዋከብም አለ አረ እንደው ወንበሩ ላይ መሞት ነው የሚበጅ

  ReplyDelete
 26. -----ከጀመርክ ጨርሰዉ የአንባገነኖችን ስም ጠቅሰህ የመለሰን አለመጠቀስህ መለሰ ከነሙጋቤ ርቆ አይደለም ለአምድህ አንባቢዎች። ወይ አለመጀመር ወይ አለመፍራት ---ማነዉ ለኢትዮጲያ መናገር ያለበት እስክነድር በቻነዉ ያለዉ እሱም እነደናንተዉ አነድ ነፍስ ነዉ ያለዉ ....ተናገሩ አትፍሩ...እኢደናንተ ያለሰዉ ለሀገሩም ጭመር ነዉ መኖር ያለበት....

  ReplyDelete
 27. ከጀመርክ ጨርሰዉ የአንባገነኖችን ስም ጠቅሰህ የመለሰን አለመጠቀስህ መለሰ ከነሙጋቤ ርቆ አይደለም ለአምድህ አንባቢዎች። ወይ አለመጀመር ወይ አለመፍራት ---ማነዉ ለኢትዮጲያ መናገር ያለበት እስክነድር በቻነዉ ያለዉ እሱም እነደናንተዉ አነድ ነፍስ ነዉ ያለዉ ....ተናገሩ አትፍሩ...እኢደናንተ ያለሰዉ ለሀገሩም ጭመር ነዉ መኖር ያለበት....
  hailewwa

  ReplyDelete
 28. Kidanemariam the Dire DawaMay 2, 2011 at 11:06 AM

  Enebo Semune said...."What happened in our country and the other part of the world, the direct participation of the people. The people has the power to limit the role of the government honestly speaking"??? KKKKKK R U joking Enebo? come to your heart please.

  ReplyDelete
 29. ኪኪኪ……… ጐበዝ ገብስ ገብሱን እናውራ፡፡ we live in Ethiopia don’t forget that.

  ReplyDelete
 30. I like your third eyes always!

  ReplyDelete
 31. I always like your way of reasoning and writing skills. I mostly check your site to read articles which you might have written on topics of current situations. I wish you could write about abay (nile river). i can see most people have the same perspective about the recent things happening regarding this issue but i want to see the way you look things from different perspective and angle. please do if you could

  ReplyDelete
 32. What a reality u wrote about power that is why everybody needs power and doesn't want to come down from his post.

  ReplyDelete
 33. I like it because it gives good message.
  Thank you.
  God bless you!

  ReplyDelete
 34. ዳኒ ምን ልልህ እንደምችል አላውቅም ግን በቃ አንተ የምትፅፋቸውን ነገሮች በብዙ አቅጣጫዎች አያቸዋለሁ፡፡ አንተ የምትላቸውን ነገሮች አንብቤ እኔ እራሴ አንድ ደረጃ አስተሳሰቤን አሳድጋሁ እባክህን ዳኒ ቶሎ ቶሎ አዳዲስ ነገሮችን በመፃፍ መንፈሴን አስደስታት፡፡ ይሄንን የፍቅር ቦንብ የሚለውን ፅሁፍ ሳነብ በሆነ በማያስደስትና በሚያበሳጭ መንፈስ ውስጥ ነበርኩ ወዲያው ስነቃ ይታወቀኛል፡፡ እናም ዳኒ በቃ ቶሎ ቶሎ ቶሎ ፃፍ፡፡

  ReplyDelete
 35. ere diyakon betam yemigerm newu
  kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 36. WOW IT IS NICE AND DOCUMENTARY FOR THE SAME PEOPLE HERE...WE BOTHER

  ReplyDelete