Tuesday, April 19, 2011

እግር ያለው ባለ ክንፍ

ምክንያተ ጽሕፈት
ይህንን ጽሑፍ በዚህ ጊዜ እንድጽፍ ምክንያት የሆነኝ ወዳጄ በዕውቀቱ ሥዩም ነው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ልዩ ልዩ አካላት የሚያቀርቧቸውን ሃሳቦች የሚተነትን አንድ ጥናታዊ ነገር እየሠራሁ ነበር፡፡ በመካከል ሐራሬ እያለሁ በዕውቀቱ «እግር አልባ ባለ ክንፍ» ብሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ አንድ ጽሑፍ አወጣ፡፡ የኛ ባህል ሃይማኖታዊ ሳይሆን ተክለ ሃይማኖታዊ ነው፤ ተክለ ሃይማኖታዊ ማለትም በሰማዩ ላይ ያለ ቅጥ በማንጋጠጥ ምድርን ማጣት፣ በዚህም ለድህነት መዳረግ ማለት ነው የሚል ነው ሃሳቡ፡፡
 
ይህ ጽሑፍ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ እና ማንነት የወቅቱ መወያያ እንዲሆን አደረገው፡፡ እኔም ይህንን እንዳዘጋጅ ምክንያት ሆነኝ፡፡ በዚህ ጽሑፍ ሌሎች አካላት የሚያነሷቸውን ሃሳቦችም ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ የበዕውቀቱን ሃብ ደግሞ ለብቻው፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማናቸው?
አቡነ ተክለ ሃይማኖት 1186 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ ተወለዱ፡፡ አባታቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻን እና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡
በሰባት ዓመታቸው ከግብፃዊው አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለክህነት መጠራት በዚህ ዓለም ትዳር መሥርቶ፣ የዓለሙንም ሥራ ሠርቶ መኖር አያስፈልግም ከሚል ፍልስፍና የመነጨ አይደለም፡፡ 8ኛው መክዘ ጀምሮ በሀገሪቱ የመንፈስ መቀዛቀዝ ይስተዋል ነበር፡፡ ዮዲት ጉዲት መንግሥቱን ይዛ በክርስትናው ላይ ከዘመተች በኋላ ሰሜኑ እና ደቡቡ ተቆራርጧል፡፡ የሃሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ኢትዮጵያዊ ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህ ነው የተክለ ሃይማኖት የጥሪ ምክንያት፡፡
 አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ዕረፍት በኋላ ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር  ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው ለወንጌል ስብከት ወጡ፡፡ የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ከመሄዳቸው በፊት ቅስናን ተቀብለው በሸዋ እና በዳሞት ማገልገላቸውን ይገልጣል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዳሞት እና በሸዋ ካገለገሉ በኋላ መጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ወደ ነበረው ወደ ደብረ ጎል ገዳም ገብተው አሥር ዓመት(12 የሚልም አለ) በትምህርት እና በሥራ አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡
ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እንደሚለው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ሐይቅ የገቡት በሠላሳ ዓመታቸው ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን በሸዋ እና በወላይታ ያገለገሉት ገና በወጣትነታቸው ጊዜ መሆኑን ነው፡፡ 1216 ዓም አካባቢ ወደ ሐይቅ የገቡት አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሐይቅ ከመመንኮሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኮሱም በኋላ ሦስት ዓመት በትም ህርት በሥራ እና በአገልግሎት ቆይተዋል፡፡
ሐይቅ እስጢፋኖስ በዚያ ዘመን እንደ አዳሪ ትምህርት ቤት ያለ ዩኒቨርሲቲ ነበረ፡፡ ወደዚያ የሚገባ ሁሉ ሦስት ነገሮችን ይማራል፡፡ ትምህርት፣ የጥበበ እድ ሥራ እና ሥርዓተ ምንኩስና፡፡ ትምህርቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን መላ ትምሀርት ያካትታል፡፡ የሞያ ትምህርቱም መጻፍ፣ መደጎስ፣ ሕንፃ ማነጽ፣ ልብስ መሥራት፣ እርሻ፣ የከብት ርባታ እና የሥዕል ሥራን ይመለከታል፡፡ ከእነዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ጽሙድ እንደ ገበሬ ቅኑት እንደ በሬ እንዲሆኑ ሥርዓተ ምንኩስናን ይማራሉ፡፡
በእነዚህ ትምህርቶች የታነፁት መነኮሳት ከገዳሙ ሲወጡ ዛሬ የፒኤች ተማሪ ዴዘርቴሽን እንደሚያቀርበው የተማ ሩትን ጽፈው አንድ የብራና መጽሐፍ አዘጋጅተው ይወጣሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሐይቅ ከስምንት መቶ መነኮሳት በላይ በአንድ ጊዜ የሚማሩባት በመጻሕፍትም የበለጸገች ዩኒቨርሲቲ ነበረች፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እዚህ ነው አሥር ዓመታትን ያሳለፉት፡፡
ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዓተ ምንኩስና እና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ ሄዱ፡፡ በዚያም ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዓተ ምንኩስና እና ጥበበ እድ ሲማሩ ሰባት ዓመት አሳለፉ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡
ቀሪዎቹን አምስት ዓመታት ሌሎችን የትግራይ ገዳማት እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆይተው ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለአሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ በስብከታቸው እንደገና ለነቃው ለመካከለኛው እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኩስና፣ ትምህርት እና ሥራ፡፡ መነኮሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡
ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፍተው አስፍተው ሰያደ ላድሉ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ በጸሎት ብዛትም እግራቸውን በማጣታቸው ስለ ክብራቸው ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ ሃያ አራት ቀን 1287 ዓም 99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡
 ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚነሡ ጥያቄዎች
አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የመንግሥት ለውጥ
«ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የተረገውን ሽግግር ያከናወኑት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው፡፡ ይህንንም ያደረጉት ይኩኖ አምላክ የሸዋ ሰው ስለሆነ ለዘራቸው አድልተው ነው» ይላሉ፡፡
በሸዋው ይኩኖ አምላክ እና በዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወራሹ በነአኩቶ ለአብ መካከል መቀናቀን የተጀመረው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ በትምህርት ላይ በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕፃን በነበሩበት ጊዜ ከዳሞት የሚመጣው የሞተለሚያውያን ኃይል ሸዋን ደጋግሞ በመውረር አብያ ክርስቲያናትን ዘርፏል ሕዝቡንም ማርኳል፡፡ ይህ ጉዳይ የሸዋን ሕዝብ ማስቆጨቱ እና ማነሣሣቱ የማይቀር ነው፡፡
በተለይም ከአኩስም የተሰደደው የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ዘር ሸዋ መንዝ ነው የገባው ተብሎ በሚታመንበት ሁኔታ ሸዋዎች ራሳቸውን ለመከላከል መደራጀት ጀምረዋል፡፡ ደቡቡ ኢትዮጵያ ከማዕከላዊው መንግሥት መቀመጫ ከሮሐ እየራቀ ሄዶ ስለነበር ለይኩኖ አምላክ ጥሩ መደላድል ሆኖታል፡፡
ገድለ ኢየሱስ ሞዓ እንደሚተርከው የመንግሥትን ነገር ከይኩኖ አምላክ ጋር የተነጋገሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳይሆኑ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በተማሪነት ሐይቅ ገዳም ውስጥ ነበሩ፡፡
አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እና ይኩኖ አምላክ በመንግሥት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የበቁት ይኩኖ አምላክ በሸዋ ላይ ይደርስ ከነበረው የሞተለሚ ጥቃት ሸሽቶ በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት ቤት ወጣትነቱን ያሳለፈ በመሆኑ ነበር፡፡
ሁለቱ ባደረጉት ስምምነት
የዐቃቤ ሰዓትነትን መዓርግ ለሐይቅ ገዳም መምህር እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም ማለት የንጉሡ ገሐዳ ግንኙነቶች በዐቃቤ ሰዓቱ በኩል እንዲፈጸሙ ማለት ነው፡፡
 • የንጉሡ ደብዳቤ ወደ ሐይቅ ገዳም ሲላክ መነኮሳቱ ተቀምጠው እንዲሰሙ
 • ለገዳሙ የተሰጠውን መሬት የመኳንንቱም ሆነ የነገሥታ ልጆች እንዳይነኩ
 • ነፍስ የገደለ፣ ንብረት የሰረቀ፣ እግረ ሙቁን ሰብሮ እዚህ ገዳም ገብቶ ቢደውል ከሞት ፍርድ እንዲድን
 • ለገዳሙ የተሰጠው ርስት ለአገልጋዮች ብቻ ስለሆነ ዘር ቆጥሮ ማንም ተወላጅ እንዳይወርስ
 • የገዳሙ ርስት መነኩሴ ላልሆነ ጥቁር ርስት እንዳይሰጥ
የሚሉት ታወጁ፡፡ ይህ ሁሉ ሲከናወን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ ትምህርት ላይ ነበሩ፡፡
በኋላ ዘመን ይኩኖ አምላክ ኃይሉ እየበረታ ነአኩቶ ለአብም ግዛቱ እየጠበበ እና ኃይሉ እየደከመ ሲሄድ ከወሎ በታች ያለውን ሀገር የያዘው ይኩኖ አምላክ እና ላስታን እና ሰሜኑን የያዘው ይኩኖ አምላክ ለጦር ይፈላለጉ ጀመር፡፡ በዚህ ዘመን ነበር አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከኢየሩሳሌም የተመለሱት፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያደረጉት ነገር ቢኖር ኃይሉ እየገነነ የመጣውን ይኩኖ አምላክን እና የወቅቱን ንጉሥ ነአኩቶ ለአብን ማደራደር ነበር፡፡ ይኩኖ አምላክ ለመንገሥ ከቅብዐት በቀር የቀረው ኃይል አልነበረም፡፡ የነአኩቶ ለአብ ኃይል ደግሞ ቢዳከምም አልሞተም፡፡ ሁኔታው ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳይሄድ ያሰጋቸው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለቱን በማደራደር ከአንድ ስምምነት ላይ አደረሷቸው፡፡
 • ይኩኖ አምላክ ምንም ኃይል ቢኖረው ነአኩቶ ለአብ እስኪያርፍ ድረስ ንግሥናውን እንዳያውጅ
 • ከነአኩቶ ለአብም በኋላ የዛግዌ ዘር የላስታን አውራጃ እንዲገዛ
 • የላስታው ገዥ በፕሮቶኮል ከንጉሡ ቀጥሎ እንዲሆን
ይህ ስምምነት ባይኖር ኖሮ ጦር በሰበሰበው በይኩኖ አምላክ እና ሥልጣን ላይ በነበረው በነአኩቶ ለአብ መካከል በሚፈጠረው ጦርነት የሀገሪቱ ልጆች ባለቁ ነበር፡፡ ዛሬ ቢሆን ይሄ ተግባር የኖቬል ሽልማት የሚያሸልም ነበር፡፡ ይህ ስምምነት በኋላ በዐፄ ይትባረክ ዘመን በመፍረስ የተከሰተውን ጦርነት ያየ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ያደንቃል እንጂ አይተችም፡፡
ሲሦ መንግሥት
«አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በዋሉት ውለታ ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ መንግሥት ተሰጠ» ይላሉ ይኩኖ አምላክ ሲነግሥ በኢትዮጵያ ውስጥ ጳጳስ አልነበረም፡፡ ከአቡነ ጌርሎስ ሞት በኋላ ከግብፅ የመጣ ጳጳስ አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ በመንፈሳዊ ትንሣኤ ላይ ለነበረችው ኢትዮጵያ የአገልጋዮች እጥረት አስከተለ፡፡ በዚህ ጊዜ የተሰባሰቡት የኢትዮ ሊቃውንት በትምህርትም በአገልግሎትም የበረቱትን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን መረጡ፡፡ የሚሾም ሲኖዶስ አልነበረምና እግዚአብሔር «ሐዋርያትን በሾምኩበት ሥልጣን ሾምኩህ» አላቸው፡፡
ይኩኖ አምላክ ምንም እንኳን በንግሥናው ቢገዛ እንደ ወጉ ሥርዓተ መንግሥት አልተፈጸመለትም ነበር፡፡ በመሆኑም በዘመኑ የነበሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጸሙለት፡፡ እርሱም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ርስት ሰጠ፡፡
ለቤተ ክርስቲያን ርስት መስጠት በይኩኖ አምላክ የተጀመረ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቅዱስ ላሊበላ ለአኩስም፣ ለላሊበላ፣ ለመርጡለ ማርያም እና ለተድባበ ማርያም የሰጠው ርስት ይበልጣል፡፡ በወቅቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት እና ለተማሪዎች ድርጎ ለቤተ ክርስቲያን ጥሪት ያስፈልጋት ስለነበር ይኩኖ አምላክ ርስት ሰጥቷል፡፡ ይህ ግን ከመንግሥት ዝውውር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ ዛሬም ቢሆን እኮ አንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ለቤተ ክርስቲያን የተለየ በጀት ይሰጣሉ፡፡
እጨጌ የሚለውን ስም ከርስት አስተዳዳሪነት ጋር የሚያገናኙት ሰዎች አሉ፡፡ እጨጌ የሚለውን ስም ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሰጣቸው መንግሥት ሳይሆን የወላይታ ሕዝብ ነው፡፡ በወላይተኛ «ጨጌ» ማለት «ሽማግሌ፣ ታላቅ፣ አባት» ማለት ነው፡፡ ወደ አማርኛ ሲመጣ «እጨጌ» ተባለ፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን አገልግሎት አይቶ ይህንን የሰጣቸው ሕዝቡ ነው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥልጣን ወዳድ አለመሆናቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡ ከብዙ ዘመናት በኋላ አቡነ ዮሐንስ 5 ከግብጽ መጥተው አቡነ ተክለ ሃይማትን በግማሽ ኢትዮጵያ በመንበረ ጵጵስና እንዲያገለግሉ ለምነዋቸው ነበር፡፡ እርሳቸው ግን ለሥልጣን ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸው እንዲያ ሲወዳቸው እና ሲፈልጋቸው ወደ በኣታቸው ነው የተመለሱት፡፡
«ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሌላ ናቸው »   
«በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን 8 እስከ 13ኛው መክዘ ባለው ጊዜ የኖሩ ሌላ ተክለ ሃይማኖት የሚባሉ ጻድቅ ነበሩ፡፡ የርሳቸው ታሪክ ከሌላ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ጋር ተዳብሎ አሁን ያለW ገድለ ተክለ ሃይማኖት አስገኘ፡፡ እናም ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ አይደሉም » ይላሉ 
እስካሁን ድረስ ይህንን አባባል የሚጠቅሱ ሰዎች ያቀረቡት ማስረጃ የላቸውም፡፡ እገሌ አይቶት ነበር፡፡ እዚህ ገዳም ነበር ከማለት ውጭ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ለሌለ ማስረጃ ሲባል ያለ ማስረጃ አይሰረዝም፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስን በተመለከተ ያሉት ማስረጃዎች አራት ዓይነት ናቸው፡፡
 1. ገድላቸው
 2. የሌሎች ቅዱሳን ገድሎች
 3. ዜና መዋዕሎች እና
 4. የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መረጃዎች
ገድለ ተክለ ሃይማኖት
እኔ ለማየት የቻልኩት የደብረ ሊባኖስ፣ የሐይቅ እስጢፋኖስ፣ የዋልድባ፣ የጉንዳንዳጉንዲ እንዲሁም ዐፄ ምኒሊክ ወላይታን ሲወጉ ያገኙት የወላይታ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቅጂዎች አልፎ አልፎ ከሚያሳዩት መለያየት በስተቀር የሚተርኩት 13ኛው መክዘ ስለነበሩት ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡ እኒህ ተክለ ሃይማኖት ጽላልሽ ተወልደው፣ በኢትዮጵያ ገዳማት ተምረው፣ በመላ ሀገሪቱ ሰብከው፣ ግብጽ እና ኢየሩሳሌም ተሻግረው፣ ደብረ ሊባኖስን መሥርተው ያገለገሉትን ተክለ ሃይማኖት ነው የሚናገሩት፡፡
ሌላው ቀርቶ ወሎ ጉባ ላፍቶ፣ ጎንደር አዞዞ ተክለ ሃይማኖት የተገኙት ገድላትም ተመሳሳይ ታሪክ ነው የሚተርኩት፡፡ እስካሁን ከኒህኛው ተክለ ሃይማኖት ውጭ ስላሉ ሌላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚተርክ ገድል አልተገኘም፡፡ አለ ከመባል በቀር፡፡
የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍትም ሆኑ በአካል ያልተገኙት ማይክሮ ፊልሞቻቸው በተከማቹባቸው በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት ወመዛግብት፣ በመንበረ ፓትርያርክ ሙዝየም እና ቤተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ቤተ መጻሕፍት፣ በብሪቲሽ ሙዝየም እና ቤተ መጻሕፍት፣ በቫቲካን ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት፣ አሜሪካ ኮሌጅቪል በሚገኘው ቅዱስ ዮሐንስ ኮሌጅ ያሉትን ማይክሮ ፊልሞች እና የብራና መጻሕፍት ዝርዝሮችን ብናይ ስለ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ እንጂ ስለ ሌላ ተክለ ሃይማኖት የተጻፈ ገድል የለም፡፡ (የዚህን ዝርዝር የጥናት ውጤት በቅርብ ለኅትመት አበቃዋለሁ፡፡)
ሌሎች ገድሎች 
ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚያነሡ አያሌ ገድሎች አሉ፡፡ ገድለ አኖሬዎስ ዘሞረት፣ ገድለ አቡነ አኖሬዎስ ዘወረብ፣ ገድለ አቡነ ፊልጶስ፣ ገድለ አቡነ ኤልሳዕ፣ ገድለ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ፣ ገድለ አቡነ ቀውስጦስ፣ ገድለ አቡነ ማትያስ፣ ገድለ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፣ ገድለ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘግድም፣ ገድለ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመርሐ ቤቴ፣ ገድለ አቡነ አድኃኒ ዘዳሞት፣ ገድለ አቡነ ኢዮስያስ ዘወጅ፣ ገድለ አቡነ ዮሴፍ ዘእናርያ፣ ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ሌሎች ወደ አሥራ ሦስት የሚጠጉ ገድላት ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተጨማሪ መረጃዎች ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ገድላት የሚያነሷቸው ተክለ ሃይማኖት ግን ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስን ነው፡፡
ዜና መዋዕሎች
የይኩኖ አምላክ፣ የዓምደ ጽዮን፣ የዘርዐ ያዕቆብ፣ የሱስንዮስ፣ እና የሌሎቹም ዜና መዋዕሎች ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ይተርካሉ፡፡
ግብፃውያን መዛግብት
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ቅዱሳን መካከል አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንዱ ናቸው፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያንዋ የአራት ቅዱሳንን ብቻ የልደት በዓል ታከብራለች፡፡ የጌታን፣ የእመቤታችንን፣ የዮሐንስ መጥምቅን እና የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጥንታውያንም ይሁኑ ዘመናውያን መዛግብት የሚገልጹት 12ኛው መክዘ ጽላልሽ ተወልደው ስላደጉት ስለ ደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡
እናም ወደፊት አዲስ ነገር ተገኘ ስንባል ያን ጊዜ እንከራከር ካልሆነ በቀር እስካሁን ድረስ ግን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የታሪክ ዝምድና ያላቸው ሌላ ተክለ ሃይማኖት መኖራቸውን የሚገልጥ ማስረጃ የለም፡፡
«አቡነ ተክለ ሃይማኖታዊ» ትውልድ
በዕውቀቱ ሥዩም ምድርን ትቶ ሰማይ ሰማይን ብቻ ሲመኝ በድህነት የሚዳክር ትውልድን «ተክለ ሃይማኖታዊ» ብሎ ሰይሞታል፡፡ ይህ የበዕውቀቱ ሥያሜ ከሁለት ነገሮች የመጣ ይመስለኛል፡፡ አንደኛው ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካለ የግንዛቤ ማነስ እና ሁለተኛው ከታሪክ ተፋልሶ የተነሣ፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሦስት ሥርዓተ ትምህርቶች በተቃኘው የሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት ቤት የኖሩ ናቸው፡፡ በትምህርት፣ በሥራ እና በምንኩስና፡፡ ሥራ ለዓለማውያን ብቻ ሳይሆን ለመነኮሳትም ግድ አስፈላጊ መሆኑን የተማሩም ያስተማሩም ናቸው፡፡ በተጓዙባቸው ቦታዎች ሁሉ ሦስቱንም ሲያከናውኑ ነው የኖሩት፡፡ በመጨረሻም ወደ ደብረ አስቦ ሲገቡ ገዳማዊው ሥርዓታቸው ትምህርትን፣ ምንኩስናን እና ሥራን ያዋሐደ ነበር፡፡
እናም «ተክለ ሃይማኖታዊ» ማለት «እየሠራ የሚጸልይ እጸለየ የሚሠራ» ማለት እንጂ በሰማዩ ላይ ብቻ ያለ ቅጥ እያንጋጠጡ ምድራዊ ሕይወትን መዘንጋት እና ለድህነት መዳረግ ማለት አይደለም፡፡
 እኔ ይህንን ስል ምድራዊ ሕይወት እንደማያስፈልግ የሚያስተምሩ፣ ሥጋ እንዳልተፈጠረ ቆጥረው በሥጋ መኖርን የሚያጣጥሉ የሉም ማለቴ አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሥጋ ተጋብቶ፣ ወልዶ ከብዶ፣ አርሶ ነግዶ፣ ወጥቶ ወረዶ መኖርን የሚያንቋሽሽቱ እና ለነፍስ ብቻ መኖር አለብን የሚሉት ማኔያውያን ተወግዘዋል፡፡ በዕውቀቱ ላነሣው ሃሳብ ትክክለኛ ስያሜውም «ማኔያዊ» እንጂ ተክለ ሃይማኖታዊ አይደለም፡፡
እግር እና ክንፍ
በዕውቀቱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግራቸውን ያጡት ክንፍ ለማብቀል ሲሉ እንደሆነ አድርጎ ያስቀምጠዋል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትኮ ክንፍ ያገኙት እግራቸውን ከማጣታቸው በፊት ነው፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ አገልግለው ሲፈጽሙ ወደ ምድር በገመድ ወረዱ፡፡ የደብረ ዳሞ መውጫ እና መውረጃው ገመድ ነውና፡፡ ያለፈውን ትጋታቸውን፤ የወደፊቱን አገልግሎታቸውን ያየ ሰይጣን የሚወርዱበትን ገመድ በጠሰባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር አክናፈ ጸጋ ሰጥቷቸው ከተራራው ሥር ሁለት ክንድ ያህል ርቀው በሰላም ዐረፉ፡፡ ያም ቦታ በኋላ ዘመን በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተተክሎበታል፡፡
እናም ገና ሁለት እግር እያላቸው፤ ተዘዋውረው በሚያስተምሩበት ጊዜ፣ ግብፅ እና ኢየሩሳሌም ከመሄዳቸው በፊት ነው ክንፍ የተሰጣቸው፡፡ ታድያ ሁለት እግር እያላቸው ያገኙትን ክንፍ ለማግኘት እግር ማጣት ለምን ያስፈልጋቸዋል? አቡነ ተክለ ሃይማኖት በአንድ እግራቸው የጸለዩት በቅድመ ጲላጦስ የቆመውን ክርስቶስን በማሰብ እንጂ ክንፍ ለማግኘት ሲሉ አይደለም፡፡
እንደ ወንድሜ እንደ በዕውቀቱ አገላለጥ አቡነ ተክለ ሃይማኖት «እግር አልባ ባለ ክንፍ» ሳይሆኑ « ያለው ባለ እግር ናቸው»
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእግር የሚደረስበትን የዘመኑን ቦታ ሁሉ ደርሰውበታል፡፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ ዙረዋል፡፡ ግብጽ ወርደዋል፤ ኢየሩሳሌም ወጥተዋል፡፡ መንግሥተ እግዚአብሔር ደግሞ በጸጋ ክንፍ እንጂ በእግር አይደረስባትምና ወደ ሰማያዊው ኢየሩሳሌም ሄደው እንዲያዩ አስቀድሞ የሰጣቸውን ክነፍ እግራ ቸው በተቆረጠ ጊዜ ገልጦላቸዋል፡፡ ያንጊዜም በእግር ወደማይደረስበት ሰማያዊ መቅደስ ገብተው ከሱራፌል ጋር አጥነዋል፡፡ በእግር የሚደረስበትን ለፈጸመ ሰው ከክንፍ ውጭ ምን ሊሰጠው ኖሯል?
በእንተ በዕውቀቱ ሥዩም
ሀገራዊ መንፈስ ፍለጋ
በዕውቀቱ ሥዩም ነገሮችን በአዲስ መልክ ከሚያ ጥቂት የሀገራችን ጸሐፍት አንዱ ነው፡፡ ገና ብዙ ሥራ የሚጠበቅበት ወጣት ጸሐፊም ነው፡፡ ሕይወቱን ለጽሑፍ የቀየደ ሰውም ነው፡
እኔ በዕውቀቱ ሥዩም ይህንን ጽሑፍ ሲጽፍ ዓላማው ቤተ ክርስቲያንን መፃረር ነው ብዬ ኣላምንም፡፡ በጽሑፉ መግቢያ እንደገለጠው ነባሩን ባህል በዓለማዊ መነጽር ማየት እፈልጋለሁ ነው ያለው፡፡ ይህም ማለት የእስላሙንም የክርስቲያኑነም፣ ሃይማኖታዊውንም ሃይማኖታዊ ያልሆነውንም ነባር ባህል «ዓለማዊ´E መነጽር ሊያይ ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር በፈለገው መንገድ ማየት የተፈጽሮ መብቱ ነው፡፡ በዚህ አንከራከረም፡፡
በዕውቀቱ እንደዚህ ያለ ነባር፣ ሕዝብ የተቀበለውን እና መከራከርያ ያለውን ነገር ሲያይ እንደሌላው ነገር በሳቅ በሥላቅ፣ በቀልድ፣ በእግረ መንገድ ባያደርገው ግን እመርጣለሁ፡፡ ካነሣ ጠንካራ መከራከርያ አንሥቶ መሞገት ነው ያለበት፡፡ በአሁኑ ጽሑፉ ግን ይህንን አላየሁበትም፡፡
በዕውቀቱ እንደሚለው ለርሱ ዋናው ሃሳቡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ መከራከር ሳይሆን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድ ነቁጥ ታሪክ እንደርሱ አገላለጥ «እግር አጥተው ክንፍ ባወጡበት» ታሪክ ተምሳሌትነት የሕዝቡን ነባር ሁኔታ ማየት ነው፡፡ ይህም ቢሆን ግን ሕዝቡ ለሌላ ነገር ሲጠቀምበት የኖረውን ስያሜ አንሥቶ ምንም ዓይነት በቂ መከራከርያ ሳያቀርብበት ለሌላ ነገር ከሚጠቀም ይልቅ ሌላ ስያሜ ቢጠቀም የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ «ተክለ ሃይማኖታዊ» የሚለው ማሳያ ከእውነታው ውጭ ቀርቧልና፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በዕውቀቱን አደንቀዋለሁ፡፡ ብዙ ጸሐፊዎች ከውጭ በመጣ ሃሳብ ኢትዮጵያን ማየት ሲመርጡ በሀገራዊ ተምሳሌት እና ሃሳብ ራሳችንን ለማየት መሞከሩ በዕውቀቱ ውርጅናሌውን የያዘ ጸሐፊ ነው እንድልም አድርጎኛል፡፡ ምንም እንኳን «ተክለ ሃይማኖታዊ» ብሎ በሰጠው ሥያሜ ትርጉም ባልስማማም ሀገርኛ ስያሜ እና ተምሳሌት ለመምረጥ መጣሩን ግን አደንቃለሁ፡፡
1956 ዓም «የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ» የምትል ትንሽ፣ ግን እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ ያሳተሙት እጓለ ገብረ ዮሐንስ የኢትዮጵያን ሥልጣኔ «ያሬዳዊ ሥልጣኔ» ብለው ሰይመውት ነበር፡፡ «ከሥጋ መንፈስ ይበልጣል፣ ሥጋዊ ሕይወት ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ተመስጦ ማደግ አለበት፣ የመጨረሻው ደረጃ መንፈሳዊ አድናቆት እና ከኃይላተ ሰማይ ጋር መተባበር ነው» በሚል ዘይቤ የተቃኘ ሥልጣኔ ነው ይላሉ፡፡
እርሳቸውና በዕውቀቱን የሚያመሳስላቸው ሁለቱም ሀገራዊ ስያሜ እና መንፈስ ፍለጋ መኳተናቸው ነው፡፡
ኦርቶዶክስነት
ለእኔ ኦርቶዶክስነት ሃይማኖት ብቻ አይደለም፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ውስጥ ከነበራት የእምነት፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የሥልጣኔ፣ የትምህርት እና የሥነ መንግሥት ድርሻ አንፃር በሀገሪቱ ሕዝቦች ውስጥ እንደ ድር እና ማግ የተያያዙ ነገሮች አሏት፡፡
እንደ እኔ ግምት ሁለት ዓይነት ኦርቶዶክሶች አሉ፡፡ የሚያምኑ ኦርቶዶክሶች እና የማያምኑ ኦርቶዶክሶች፡፡ የሚያምኑት ኦርቶዶክሶች ኦርቶዶክስን የድኅነት መንገድ አድረገው የሚቀበሏት ናቸው፡፡ ዶግማዋ፣ ሥርዓቷ፣ ትውፊቷ የሚመራቸው ናቸው፡፡ የማያምኑት ደግሞ ባህልዋ፣ ፍልስፍናዋ፣ ሥርዓተ ኑሮዋ፣ ታሪኳ፣ ሥነ ምግባርዋ እና ሀገራዊ እሴ ቷን በማወቅም ባለማወቅም የተቀበሉት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣ ባህላዊ እምነት አማኝ፣ እምነት የለሽ፣ ሙስሊም፣ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በባህላቸው፣ በአስተ ሳሰባቸው፣ በታሪካቸው፣ በመሠረታቸው፣ በሥነ ምግባር እሴታቸው፣ በይትበሃላቸው እና በሀገራዊ ስሜታቸው ግን ኦርቶዶክሶች ናቸው፡፡ በተለያየ የክርስትና ባህሎች ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንስሳው ሁሉ ተቀድሷል እያሉ ሲያስተምሩ ቢሰሙም አይጥ እና ጉርጥ ሲበሉ፣ ወይንም ፈረስ እና አህያ አርደው ሠርግ ሲደግሱ ግን አልታዩም፡፡
በዕውቀቱ ከሁለተኛዎቹ ኦርቶዶክሶች የሚመደብ ይመስለኛል፡፡ በተደጋጋሚ እንደ ሚለው «እኔ በራሴ ትርጉም ኦርቶዶክስ ነኝ፤ የግድ እንደ እናንተ አድርጌ ማመን ግን አይጠበቅብኝም» ይህ አባባሉ ነው ከሁለተኞቹ እንድመድበው ያደረገኝ፡፡ በተደጋጋሚ ገድላቱን እና ትርጓሜያቱን ሲያነብብ እና ሲጠቅስ አየዋለሁ፡፡ ለሀገራዊ እሴቶች ዋጋ ይሰጣል፡፡ ቋንቋው «ኦርቶዶክሳዊ» ነው፡፡ የሥነ ምግባር መመሪያዎቹም እንዲሁ፡፡ በዐሉላ ቋንቋ በዕውቀቱ «ሲቪክ ኦርቶዶክስ» ነው፡፡
በዕውቀቱን የመረጠውን ሃሳብ እንዲወክልለት «ተክለ ሃይማኖታዊ» የሚለውን ቃል እንዲጠቀም ያደረገው ፀረ ቤተ ክርስቲያን ስለሆነ ሳይሆን ሲቪክ ኦርቶዶክስነቱ አይሎበት ነው ባይ ነኝ፡፡ ምንም እንኳን የትርጉም ስሕተት ቢፈጥር፡፡
አሉታዊ ጥቅም
ሃይማኖት ማኅበረሰቡ የሚቀበለውና የሕይወት ሥርዓት ሆኖ የሚቀጥል ነገር ነው፡፡ እናም በማኅበረሰቡ ውስጥ ይሰርጽና ዘወትራዊ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በመካከል ጥያቄ የሚጠይቁ፣ የተለየ ሃሳብ የሚያቀርቡ እና የሚሞግቱ ሲመጡ ግን ሃይማኖታዊ ጉዞ ከተለምዶአዊነት ወጥቶ ንቅናቄያዊ ይሆናል፡፡
ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍቷን በቀኖና እንድትወስን፣ ሥርዓቷን እንድትወስን፣ የሃይማኖት መግለጫዋን ወስና እንድታወጣ፣ ሕግ እና ደንብ እንድትሠራ፣ መጻሕፍትን እንድትጽፍ፣ ያደረጓት እነዚህን መሰል ተግዳሮቶች በየዘመናቱ መኖራቸው ነው፡፡ ሄሊቪዲየስ ተነሥቶ በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ የተለየ ትምህርት ባያመጣ ኖሮ አባ ጄሮም እና አባ ኤጲፋንዮስ የጻፏቸውን መጻሕፍት ባላገኘን ነበር፡፡
ቴዎድሮስ የተባለ የጦር አዛዥ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን ስለ ሃይማኖት ባይገዳደረው ኖሮ አስደናቂውን ርቱዐ ሃይማኖት የተሰኘ መጽሐፍ ባላገኘን ነበር፡፡ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዜና መዋዕል እንደሚነግረንም «በንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በሃይማኖት ምክንያት ክርክር ሆነ፡፡ አባ ጊዮርጊስም ከአንድ ፈረንጅ ጋር ተከራክሮ ረታው፡፡ መጽሐፈ ምሥጢርንም ደረሰ»
መልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬ ያንን የመሰለ ኮኩሐ ሃይማኖት የተሰኘ መጽሐፍ እንዲጽፉ ምክንያት የሆናቸው አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ካቶሊካዊ ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጻፈው ጽሑፍ ነው፡፡ እርሳቸው ባረፉ ጊዜ ይኼው ሰው እያለቀሰ መጣ አሉ፡፡ ዘመዶቻቸው ተናድደው «ደግሞ እንዴት ታለቅሳለህ ብለው ቢጠይቁት «እንኳንም ጻፍኩ፤ እኔ ባልጽፍ እኒህን የመሰሉ ሊቅ ገንዛችሁ ልትቀብሯቸው ነበርኮ፡፡ እኔ በመጻፌ እርሳቸውም ጻፉ ምነዉ ደጋግሜ በጻፍኲ ኖሮ» አለ ይባላል፡፡
እነ አስረስ የኔ ሰው ያንን የመሰለ «ትቤ አኩስም መኑ አንተ» የተሰኘ የታሪክ፣ የእምነት፣ የቅርስ እና የሥነ ልሳን መጽሐፍ የጻፉት በወቅቱ ለተነሡት የታሪክ፣ የቋንቋ እና የእምነት ተግዳሮቶች መልስ ለመስጠት ነው፡፡
እናም የበዕውቀቱ ጽሑፍ በዚህ ረገድ ከታየ ያለንን ይበልጥ ለመግለጥ እና ይበልጥ ለማብራራት ዕድል የሚከፍት አሉታዊ ጠቀሜታ አለው ብዬም አስባለሁ፡፡ እንደነ መንግሥተ አብ ያሉ ጸሐፍትም ከእምነት ነጻነት እና ከሃሳብ ነጻነት የቱ ይበልጣል? የሚል መከራከርያ ይዘው እንዲነሡም አድርጓል፡፡
የበዕውቀቱ ጽሑፍ እና የመጻፍ ነጻነት
በምንም መንገድ ይሁን በምንም እንደ በዕውቀቱ ያሉ ጸሐፍት የመጻፍ ነጻነታቸው መከበር አለበት፡፡ ጥያቄ ያለው ወይንም በሃሳባቸው የማይስማማ ሰው እስከ ሕግ አግባብ ድረስ በመሄድ ጤናማውን እና የሠለጠነውን መንገድ ተከትሎ ይሞግታል፡፡ 
አንድ ጸሐፊ በመጻፉ ምክንያት ብቻ አካላዊም፣ ሃሳባዊም ጥቃት እንዳይደርስበት የምንከላከለው በሚጽፈው ሃሳብ ስለምንስማማ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ለማንስማማበትም ሃሳብ ነጻነት መሟገት አለብን፡፡ ሃሳቡን እየተከራከርነውም፤ መብታችን ተደፍሯል ብለን በፍርድ ቤት እየከሰስነውም ቢሆን ለሃሳብ ነጻነቱ ግን መሟገት ግድ ይለናል፡፡

በርግጥ ልጁ ይህንን ተግባር እንደ ዓላማ የያዘ ልጅ አለመሆኑን ከጓደኞቹም ከራሱም አረጋግጫለሁ፡፡ በዕውቀቱን ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በዕውቀቱም ይቅር ብሏል፡፡ በሃሳቡ ባይስማማም ባደረገው ነገር ግን መፀፀቱን ገልጧል፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ሚዲያዎች ሁኔታውን ያራገቡበት መንገድ ግን ነገሩ አሁንም የቀጠለ እና ሌላ አደጋ ያለ በሚያስመስል መልኩ ነው፡፡ 
እናም በዕወቀቱ ይጻፍ፣ የማልስማማበትንም ነገር ይጻፍ፣ እኔም የምስማማበትን እይዛለሁ፣ የማልስማማበትን እሞግታለሁ፡፡ ለበዕውቀቱ የመጻፍ ነጻነት ግን ጥብቅና እቆማሁ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በአንድ እግራቸው የጸለዩት ለበዕውቀቱም ጭምር ነዉና፡፡

133 comments:

 1. Egziabiher Yistilin Dn Daniel, Betam Yemiyasdesit mels new. Because human beings are created with free will and freedom, we can't oppose that natural right. But using our freedom too, we can ague them, we can response with out violating their right!

  Berta! Melkam semune Himamat!

  ReplyDelete
 2. Daniel!
  Egziabher endante yalewun ayasatan.
  Ke Trondheim.

  ReplyDelete
 3. Dani, what happen to you????

  ReplyDelete
 4. God bless you Dani,

  Your idea is very positive as a Christian I am with your idea. I don't mean በዕወቀቱ but out there some people write a lot false acquisitions about our church.

  Those bad apples (I don't mean በዕወቀቱ) they right in back ground ( in dark), no address or author name for their news- papers, flayers, books or magazines. Their aims is to destroy our Christian personality.
  Their writing is not for the purpose dialogue (exchange of ideas or opinions). They are manipulative to the ordinary people, in other words they are armed robbers. Robbers has to face justice.

  ReplyDelete
 5. መቼም አታወጣው!April 20, 2011 at 6:04 AM

  ተረት ተረት፤ የላም በረት።
  ያው ከንጉሳችንና ከአምላካችን ላይ አይናችንን እንድናነሳ ከሚያደርጉ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከሚተረኩት አንዱን ዛሬ አስነበብከን።

  ReplyDelete
 6. Selam Daniel;
  ijig yekebere misgana aqerbalehu. asteamri yehone tsihuf silaqerebk.

  As we all know names are used as terminology. Ariyos, Eyesusawiyan, Yaredawi etc. Tekile haymanotawi can be one. Once these terminologies derived from names are attached to a certain meaning especially the negative one, then it is difficult to scrap it back. That is why we have seen all these uproar.

  By any standard religious, historical or otherwise the name tekele haymanot and the person tekle haymanot does not deserve Bewqetu's negative terminological connotation.

  After all we all speak the same language and we all know the same history so we did not and could not accept this attempt of smearing St. Tekle Haymanot's name.

  Thank you again for your extraordinary effort.

  ReplyDelete
 7. መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል

  “የሚወዱአችሁን ብቻ ብትወዱ ምን ብልጫ ታደረጋላችሁ አህዛብስ ይህን ያደርጉ የለምን? “ ስለዚህ ለበዉቀቱ ልቦና ይስጥህ በሉት


  ወ/አማኑኤል ከሚኒሶታ አሜሪካ

  ReplyDelete
 8. ዳዊት ሞገስApril 20, 2011 at 9:30 AM

  ‹‹አሌ ሎን ለከናፍረ ጉሕሉት እለ ይነባ አመፃ ላዕለ ፃድቅ››
  ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን እንዳንተ ዓይነት ሰው ጠፍቶ እኮ ነው በማስተማር በመወያየት ይሻላል እንጂ እንዴት በመደብደብ መንፈሣዊነት ይረጋገጣል፡፡አቡነ ተክለ ሃይማኖት በአንድ እግራቸው የጸለዩት ለበዕውቀቱም ጭምር ነዉና፡፡

  ReplyDelete
 9. አቡነ ተክለ ሃይማኖት «እግር አልባ ባለ ክንፍ» ሳይሆኑ «ክንፍ ያለው ባለ እግር ናቸው»

  ReplyDelete
 10. Thank you Dani. good to accept others freedom of expression; even when you think they stand against what you believe. I take that as the core of your article. I also want to pass my appreciation to Alula's coinage of a new word. "Civic Orthodox" I am in it.

  ReplyDelete
 11. Thanks God. Thanks D/n Daniel. This message is not for Bewuketu only but for those who wrote and talk about our orthodox church with little knowledge or wrong perception. Now a days I am thinking that the recent Ethiopian "Intellectuals" Or "Writers" are thinking that their writing/speach will not be accepted if not included Negative things about Orthodox Church.
  may the help of God Be with Us.

  ReplyDelete
 12. Yideres lebale teret teretu.
  Alemawekih ena dekamanetih Ye kidusanin tegadilo teret adirgobihalina bertiteh tseliy.

  ReplyDelete
 13. ዳኒ እግዚያብሔር ይባርክህ
  ብዙ ነገር ተምሬበታለሁ እንዳነተ አይነቶች መልሰ ሰጪ ኦርቶዶክሳዊያን ያብዛልን
  የፃድቁ ምልጃና በረከት ይደርብህ ይደርብን አሜን

  ReplyDelete
 14. selam dani
  yanesaahewn hasab aychewalew 50% ismamalew cos bewketu malet iko tera tsehafi aydelem manignawnim tsihuf ke metsafu befit silemitsifew neger mawek alebet beki information linorew yigebal yalebeleziya 3 mesmer tsihuf bicha anbibo litechina liyask memokeru yihe ke tera mehaym yemlitebkew neger new.ke metsafu befit manbeb neberebet manibeb ke metsaf yikedmalina yalebeleziya bemeselegn yemitsaf kehonema manim sew tsehafi mehon yichilal.
  lenegeru anidanid sew mitsifewn siyata yalhone neger yikebatral demos teklehaymanot be manim tejam simachew linesa aygebam.sew indet ke tej bet besebesebew information amarebign bilo yitsifal.yihe rasu ye lijun iwket yasayal ineko iskezare iyanebebe mitsif yimeslegnal lekas be sima belew new mitsifew kezam tinish miyask neger yichemrbetal aleke.
  HULUM IYETENESA YE TEJ ANGET SIYIZ BADERE IJU SILE KIDUSAN ABATOCHACHIN METSAF MAKOM ALEBACHEW BE MINIM MENGED YIHUN BE MINIM.

  ReplyDelete
 15. ኦ በጣም ጥሩና አስተማሪ ምላሽ ነዉ ዲያቆን ዳንኤል እንደዚህ ሀሳብን በሰለጠነ መንገድ መግለፅና ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሰለጠነ አካሄድ ነዉ፡፡
  ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሰብዓዊ መብት መሆኑን የተለያዩ ምሁራን ይናገራሉ እኔም የማምንበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ሰዉ ሰዉ ሆኖ ሲፈጠር በነፃነት እንዲያስብና የፈለገዉን አመለካከት እንዲይዝ እንዲሁም የያዘዉን አስተሳሰብና የሚከተለዉን አመለካከት በፈለገዉ መንገድ በነፃነት እንዲያንፀባርቅ ተደርጎ ነዉ፡፡በእርግጥ የራሱን መብት የሚያራምድ ሰዉ የሌሎችን መብት ላለመጋፋትና ሞራላቸዉን ላለመጉዳት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል፡፡
  ስለዚህ የሰዎችን ሀሳባቸዉንና አመለካከታቸዉን የመግለፅ መብትን ማክበርን መልመድ ይገባናል እላለሁ፡፡
  በተረፈ አቡነ ተክለ ሀይማኖትን በተመለከተ የሚነሱ ሀሳቦችን አስመልክቶ ያዘጋጀኸዉን ጽሁፍ ወድጄዋለሁ፡፡
  ሰብስቤ ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 16. በጣም ደስ የሚል ጽሑፍ ነው፡፡
  ሰው ለዓለም የሚጠቅም ሃሳብ ቢያስብም ቅሉ ሃሳቡን ሊያስተላልፍበት የፈለገውን መንገድ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ያው የአበውም ሆነ የእመው ብሒል ‹‹ከፍትፍቱ ፊቱ›› ስለሚል፡፡


  እኔ ግን በጣም የሚያሳስበኝ ጉዳይ በአንድ ቦንዳ የመጨፍለቃችን ነገር ነው፡፡ በአብርሃም ማስሎው <> መሠረት አንድ ሰው ከበላ ከጠጣ በአካባቢው ባሉት ነገሮች ላይ ይመራመራል፡፡ ተመራምሮም የፈለገውን ይወስዳል፣ የመረጠውንም ይከተላል፡፡ በዚህ ምርጫ ላይ ማኅበረሰቡ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡


  እንግዲህ ከዚህ ተጽዕኖ መላቀቅ የመራጩ ፋንታ ይኾናል፡፡ ሰው ላመነበት ነገር መሰዋት ስለሚኖርበት፡፡ ነገር ግን እስከመቼ ልዩነቱን በኀይል የሚሸነግል ማኅበረሰብ እሹሩሩ እያልን እንጓዝ? እስከመቼ አእምሮን በአንድ ቦንዳ የሚያሥር ሰው እንሸከም? ቆሎ እየተበላ ፊት ሊወዛ እንደሚችል እንወቅ፡፡ እንደፈርዖን የራሔልን ልጅ በጭቃ ላይ አንርገጥ፡፡ ሰዎች ያሰቡትን ነገር እንደልባቸው እንዲናገሩ እንፍቀድላቸው፡፡


  እጃቸውን አንያዝ፣ ሞራላቸውን አንንካ፣ ሃሳባቸውን አንጨፍልቅ፣ እግራቸውን አንሰር፡፡ ስለዚህ እንዲህ እላለሁ… ጉዱ ካሳ ይነሳ፣ ፊታውራሪ መሸሻ ይፈሩ፣ እውነትን የሚፈልጉ ሰዎች ይፈጠሩ፡፡ ማኅበረሰባችን በዚህ መንገድ ካልሆነ በምን ያድጋል? የሚጻፍ ታሪካችን ስለ አኩሱም፣ ላሊበላ ብቻ አይደለም፡፡ ስለጸሐፍቶቻችንም እንወቅ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ብቻ አይደሉም፡፡


  በእንተ ዳንኤል


  Source the crowd
  መጋቢት 18/03 በአክሱም ሆቴል የነበረውን መርሐ-ግብር ተካፍያለሁ፡፡ ያ ሁሉ ምስጋናና ውዳሴም ሲዥጎደጎድልህ ታዝቤያለሁ፡፡ ጆሮዬ ይሁን ወይም የጽዮን አፍ እንጃ ስብከት የጀመርክበትን 20ኛ ዓመት በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ልታከብር እንደሆነም አድምጫለሁ /ለምን እንደሆነ ባይገባኝም/፡፡ እኔ ይህ ሁሉ አይገባህም የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንተን ሳይሆን ሥራህ ብቻ ቢመሰገን በቂ ነው፡፡ አንተ ሰው ነህ፡፡ በመንፈሳዊውም ሆነ በሞራላዊው ሕግ መሠረት አንድ ሰው ሊመለከት የሚገባው ዓላማውን እንጂ ለዓላማው መሣርያ የዋለውን አይደለም፡፡


  ቅር የሚያሰኙኝን ነገሮች በዚሁ አጋጣሚ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ ዳንኤል ተተኪ ለማፍራት ጥረት ስታደርግ አላይህም፡፡ ስለእውነት ከሆነ እንደ ‹‹ነቢዩ ዳንኤል፣ ኢሳይያስ›› በሚያይህ ሕዝብ መካከል መገኘት ሸክም ነው፡፡ የቅኔ መምህር ናቸው ይባላል፡፡ ‹‹አባቴ ስንት መምህር አሎት?›› ብለው ይጠይቋቸዋል፡፡ ‹‹40›› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ጠያቂያቸውም ቀበል አድርጎ ‹‹ምን 40 ተማሪ አሎት 40 አጋንንት በሉ እንጂ›› አላቸው፡፡ ይህንን ሁሉ ሰው የሚያዳክም ሰይጣን የሚዋጋው አንተኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ለብዙ ሰው መንቀሳቀሻ ሞተር የሆንከው አንተ ነህ፡፡

  ሰው ነህና ነገ የሆነ ነገር ብትሆንስ? ብትሞትስ? Stroke ቢያጋጥምህና memory lose ብታደርግስ? አንተን እንደመጋቢ ወፍ አድርገው የሚጠብቁህ ጫጩቶች አለቁ ማለት አይደለም? ስለዚህ…እባክህ…የሆነ ተተኪ ለማፍራት ጥረት አድርግ፡፡ አንተ ብቻ ሳትሆን ጡመራቸውን የምንዘክርላቸው 10፣20፣50… ሰዎች ቢኖሩን እመርጣለሁ፡፡ አንተ ብቻህን 50 ሎሚ ሸክም ይሆንብሃል፡፡ መፍትሔው ደግሞ 49 ሰዎችን ፍጠርና ጌጥ ይሁንላችሁ፡፡


  ያንተ ትክክለኛ ወዳጅ የሚታወቀው በፈተናህ ጊዜ ነው፡፡ አሁን ሁሉም አድናቂህ ነው፡፡ አሁን ሁሉም ወዳጅህ ነው፡፡ ጸፍጸፍ ስትቆም ግን የቀኝና የግራህን ለይተህ ታውቃለህ፡፡ ስለዚህ ብዙ ሁኑ፣ ተበራከቱ፣ አምራችሁ እንያችሁ፡፡ ከዛም በኋላ የምንፈልገው ይሆንልናል፡፡ የምንመኘው ነጻነት፣ የምናፍቀው ፍቅር፣ የራቀን ትጉህነት ያለው ያንተ ጽሑፎች ላይ ሳይሆን ልባችን ውስጥ ነው፡፡ ገብረ-ሃካይ ወደ ገብረ ሄር ይለወጥ!!


  Equal attention
  ይህንን እንኳን እንዴት ብዬ እንደምገልጸው አላውቅም፡፡ ነገር ግን ዳንኤል ብዙ ጊዜ ስለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብቻ ነው ስትጽፍ የማነበው፡፡ ለምን ስለ ሶፍ ዑመር ዋሻ አልጻፍክም? ለምን በአይሻ ደወሌ ስላለችው ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ አልጻፍክም? ከብዙ ሰዎች ኮንታክት ስላለህ ይህንን ተጠቅመህ በደቡብ ኢትዮጵያ ስላሉት የሀገራችን ቅርሶች ለምን አልጻፍክም? ኢትዮጵያ ማለት ጎንደር፣ ጎጃም፣ ትግራይ ብቻ ናቸው?


  ስለዚህ aspire to explore.
  ለማንኛውም ‹‹ሰው የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ››፡፡ ሁላችንንም ለንስሐ ሞት ያብቃን፡፡ የኋላችንን እየረሳን ከፊታችን ላላው እጃችንን እንዘርጋ፡፡


  ትንሣኤ ለኢትዮጵያ!!

  ReplyDelete
 17. ጥበበ ሥላሴApril 20, 2011 at 11:43 AM

  የበዕውቀቱን እይታ ከሚወዱትና ከሚያደንቁት መሃከል አንዱ ነበርኩ፡፡ የሚሰነዝቸው ጉዳዮች በተለይ በአገር አስተዳደርና በቤተሰብ ላይ ለሁሉም ዜጋ ጠቃሚ እንደሆኑ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን በሃይማኖት ጉዳይ በተለይ በኦርቶዶክስ ቅዱሳት ላይ የሚያሳየውን ፌዞች በምን መልክ ከነጻነት ጋር ማያያዝ አይቻልም፡፡ ለምሳሌ በድምጽ ተዘጋጅቶ በሲዲ ከተለቀቀው ላይ ‹‹ ለመልአኩ ልጄን ስራ ብታስገኝለት ጥላ አውስሃለው አልኩት፡፡›› የሚል አለ፡፡ ይህ አነጋገር ለኦርቶዶክስ ምዕመናን ጆሮን ጭው የሚያደርግ የድፍረት ንግግር ነው፡፡ እንዲ በማለቱ የጨመረው ለህዘብ የሚጠቅም እውቀት ምንድን ነው? በምናከብራቸው አላገጠ እንጂ፡፡ እኛ ለመላእክት የምንሳለው ተሳስተን አይደለም፤ አምነንበት እንጂ፡፡
  እንደማስበው በዕውቀቱ ምናልባት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ ወይም ከኦርቶዶክስ ቤተሰብ ስለተገኘሁ የፈለኩትን የቤተክርስቲያን አጥር ለመነቅነቅ ባለመብት ነኝ ብሎ አስቦ ይሆናል፡፡ ግን ባለመብት መሆን የሚችለው ለእምነቱ ዶግማ ቀኖናና ስርዐት ቀናኢ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 18. very nice view danni!!thank you!!

  ReplyDelete
 19. ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን። ባነሳሃቸው በርካታ ሃሳቦች እስማማለሁ። በዕውቀቱ ከአንተ ጽሑፍ ሊማር የሚችለው በርካታ ነገር ያለ ይመስለኛል። ይኸውም ስለአንድ ጉዳይ(በተለይም የአንድን ማህበረሰብ ማንንነት የሚነካ ከሆነ) ሂስ ለመስጠት ከመነሳት በፊት በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ይዞ መነሳት መሠረታዊ መሆኑ ነው። በዕውቀቱ ስህተት ውስጥ የገባውም ሀሳቡን በነፃነት በመግለጹ ሳይሆን የአቡነ ተክለሃይማኖትን ማንነት አዛብቶ በማቅረቡ መሆኑ ግን አሁንም ግልጽ መሆን አለበት።

  ከዳንኤል የሚቃረነው ሀሳቤ ግን የማህበረሰብን አጀንዳ ወደጎን በመተው 'የመጣልህን እንደወረደ መፃፍ' የሚባለው ፍልስፍና ሃይማኖት ላይስ ይሠራል ወይ? የሚለው ጥያቄዬ ነው። በፍልስፍናው አስፈላጊነት ላይ ለመከራከር አልሻም። የተስማማው ይከተላል ያልተስማማውም ይተወዋልና። እኔን ጨምሮ ለዘመናት በስብሐትና በበውቀቱ ሥራዎች(ጠቀሙም አልጠቀሙም፣ ለውጥ አመጡም አላመጡም) ስንስቅ የኖርነውም ከዚህ የምርጫ ነፃነታችን በመነጨ መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም እንደ አንድ በሳል ደራሲ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የሚነኩና የማይነኩ ወሰኖችን ወይም ስስ ብልቶችን ለይቶ ማወቅ ግን የመጀመሪያውና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ይመስለኛል። እንደእኔ አመለካከት በዕውቀቱ ደካማ የሥራ ባህላችንን ለማሳየት በጣም ከሚርቁት አቡነ ተክለሃይማኖት ላይ መንጠላጠል እንደማያስፈልገው ዙሪያ ጥምጥም በመጓዝ ሳይሆን በቀጥታ ሊነገረው የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል። ምክንያቱም አቀራረቡ የኢትዮጵያውያንን የሥራ ባህል ድክመት የሚያሄስ ሳይሆን ከነ ፓስተር ዳንኤል ጎራ ተሰልፎ ኦርቶዶክሳውያንን ማጣጣል ነውና።

  ስለዚህ ዲ/ን ዳንኤል በበውቀቱ ላይ አደጋ አደረሰ የተባለው ግለሰብ ድርጊቱ ትክክል ባይሆንም የበዕውቀቱ ስስ ብልትን ለይቶ ለመፃፍ ያለመቻል ድርሻም መዘንጋት የለበትም ባይ ነኝ። እንዲያውም እኔ በውቀቱን የተረዳሁት ሕዝባችንን ለማስተማር የሚያስችል ርዕስ ርዕስ እንዳለቀበትና አድማሱም እንደጠበበት ነው።

  በተረፈ ለበዕውቀቱ የሰጠኸውን የመፃፍ ፈቃድ ለእኔም አትነፍገኝም ብየ አስባለሁና ግላዊ አስያየቴን ለንባብ አብቃልኝ።

  ቢንያም
  ባህርዳር

  ReplyDelete
 20. መግቢያህ እራሱ ማንነትህን ይናገራል መቼም አታወጣውም

  መቼም አታወጣውም ምን ለማለት ይሆን? ከእናንተ ይህ ጽሁፍ ምን ማለት ነውና ነው የማይወጣው እንደውም መውጣት ያለበት ይሄ ነው እንጂ የማንነታችሁ መገለጫ የጭንቅላታችሁ ስፋት እና መድረሻ ማሳያ ስለሆነ በአንተ ቤት ሚሥጢር የጻፍክ መስሎህ ነው ግን አንተነትህን ነው ያስነበብከን ለማንኛውም የአንተን ጽሁፍ መሰል ነገር በማንበብ ላጠፋነው ግዜ ይቅርታ ልትጠይቀን ይገባል ቁም ነገር ያለው የምንጽናናበት የምንማርበትን ጊዜ ስለቀለድክበት ማስተዋልን ይስጥህ

  AD

  ReplyDelete
 21. በጣም ደስ የሚል ጽሑፍ ነው፡፡
  ሰው ለዓለም የሚጠቅም ሃሳብ ቢያስብም ቅሉ ሃሳቡን ሊያስተላልፍበት የፈለገውን መንገድ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ያው የአበውም ሆነ የእመው ብሒል ‹‹ከፍትፍቱ ፊቱ›› ስለሚል፡፡
  እኔ ግን በጣም የሚያሳስበኝ ጉዳይ በአንድ ቦንዳ የመጨፍለቃችን ነገር ነው፡፡ በአብርሃም ማስሎው <> መሠረት አንድ ሰው ከበላ ከጠጣ በአካባቢው ባሉት ነገሮች ላይ ይመራመራል፡፡ ተመራምሮም የፈለገውን ይወስዳል፣ የመረጠውንም ይከተላል፡፡ በዚህ ምርጫ ላይ ማኅበረሰቡ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡
  እንግዲህ ከዚህ ተጽዕኖ መላቀቅ የመራጩ ፋንታ ይኾናል፡፡ ሰው ላመነበት ነገር መሰዋት ስለሚኖርበት፡፡ ነገር ግን እስከመቼ ልዩነቱን በኀይል የሚሸነግል ማኅበረሰብ እሹሩሩ እያልን እንጓዝ? እስከመቼ ነው ተጽዕኖ ፈጣሪውን በተጽዕኖ ሥር የምናቆየው? እስከመቼ በአንድ ቦንዳ እንታሰር? ጮማ ብቻ አይደለም ፊት የሚያወዛው ቆሎ እየተበላም ፊት ሊወዛ እንደሚችል አንብበናል፡፡ እንደፈርዖን የራሔልን ልጅ በጭቃ ላይ አንርገጥ፡፡ ሰዎች ያሰቡትን ነገር እንደልባቸው እንዲናገሩ እንፍቀድላቸው፡፡
  እጃቸውን አንያዝ፣ ሞራላቸውን አንንካ፣ ሃሳባቸውን አንጨፍልቅ፣ እግራቸውን አንሰር፡፡ ስለዚህ እንዲህ እላለሁ… ጉዱ ካሳ ይነሳ፣ ፊታውራሪ መሸሻ ይፈሩ፣ እውነትን የሚፈልጉ ሰዎች ይፈጠሩ፡፡ ማኅበረሰባችን በዚህ መንገድ ካልሆነ በምን ያድጋል? የሚጻፍ ታሪካችን ስለ አኩሱም፣ ላሊበላ ብቻ አይደለም፡፡ ስለጸሐፍቶቻችንም እንወቅ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ብቻ አይደሉም፡፡
  በእንተ ዳንኤል
  Source the crowd
  መጋቢት 18/03 በአክሱም ሆቴል የነበረውን መርሐ-ግብር ተካፍያለሁ፡፡ ያ ሁሉ ምስጋናና ውዳሴም ሲዥጎደጎድልህ ታዝቤያለሁ፡፡ ጆሮዬ ይሁን ወይም የጽዮን አፍ እንጃ ስብከት የጀመርክበትን 20ኛ ዓመት በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ልታከብር እንደሆነም አድምጫለሁ /ለምን እንደሆነ ባይገባኝም/፡፡ እኔ ይህ ሁሉ አይገባህም የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንተን ሳይሆን ሥራህ ብቻ ቢመሰገን በቂ ነው፡፡ አንተ ሰው ነህ፡፡ በመንፈሳዊውም ሆነ በሞራላዊው ሕግ መሠረት አንድ ሰው ሊመለከት የሚገባው ዓላማውን እንጂ ለዓላማው መሣርያ የዋለውን አይደለም፡፡
  ቅር የሚያሰኙኝን ነገሮች በዚሁ አጋጣሚ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ ዳንኤል ተተኪ ለማፍራት ጥረት ስታደርግ አላይህም፡፡ ስለእውነት ከሆነ እንደ ‹‹ነቢዩ ዳንኤል፣ ኢሳይያስ›› በሚያይህ ሕዝብ መካከል መገኘት ሸክም ነው፡፡ የቅኔ መምህር ናቸው ይባላል፡፡ ‹‹አባቴ ስንት መምህር አሎት?›› ብለው ይጠይቋቸዋል፡፡ ‹‹40›› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ጠያቂያቸውም ቀበል አድርጎ ‹‹ምን 40 ተማሪ አሎት 40 አጋንንት በሉ እንጂ›› አላቸው፡፡ ይህንን ሁሉ ሰው የሚያዳክም ሰይጣን የሚዋጋው አንተኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ለብዙ ሰው መንቀሳቀሻ ሞተር የሆንከው አንተ ነህ፡፡
  ግን ሰው ነህና ነገ የሆነ ነገር ብትሆንስ? ብትሞትስ? Stroke ቢያጋጥምህና memory lose ብታደርግስ? አንተን እንደመጋቢ ወፍ አድርገው የሚጠብቁህ ጫጩቶች አለቁ ማለት አይደለም? ስለዚህ…እባክህ…የሆነ ተተኪ ለማፍራት ጥረት አድርግ፡፡ አንተ ብቻ ሳትሆን ጡመራቸውን የምንዘክርላቸው 10፣20፣50… ሰዎች ቢኖሩን እመርጣለሁ፡፡ አንተ ብቻህን 50 ሎሚ ሸክም ይሆንብሃል፡፡ መፍትሔው ደግሞ 49 ሰዎችን ፍጠርና ጌጥ ይሁንላችሁ፡፡
  ያንተ ትክክለኛ ወዳጅ የሚታወቀው በፈተናህ ጊዜ ነው፡፡ አሁን ሁሉም አድናቂህ ነው፡፡ አሁን ሁሉም ወዳጅህ ነው፡፡ ጸፍጸፍ ስትቆም ግን የቀኝና የግራህን ለይተህ ታውቃለህ፡፡ ስለዚህ ብዙ ሁኑ፣ ተበራከቱ፣ አምራችሁ እንያችሁ፡፡ ከዛም በኋላ የምንፈልገው ይሆንልናል፡፡ የምንመኘው ነጻነት፣ የምናፍቀው ፍቅር፣ የራቀን ትጉህነት ያለው ያንተ ጽሑፎች ላይ ሳይሆን ልባችን ውስጥ ነው፡፡ ገብረ-ሃካይ ወደ ገብረ ሄር ይለወጥ!!
  Equal attention
  ይህንን እንኳን እንዴት ብዬ እንደምገልጸው አላውቅም፡፡ ነገር ግን ዳንኤል ብዙ ጊዜ ስለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብቻ ነው ስትጽፍ የማነበው፡፡ ለምን ስለ ሶፍ ዑመር ዋሻ አልጻፍክም? ከብዙ ሰዎች ኮንታክት ስላለህ ይህንን ተጠቅመህ በደቡብ ኢትዮጵያ ስላሉት የሀገራችን ቅርሶች ለምን አልጻፍክም? ኢትዮጵያ ማለት ጎንደር፣ ጎጃም፣ ትግራይ ብቻ ናቸው?
  ስለዚህ aspire to explore.
  ለማንኛውም ‹‹ሰው የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ››፡፡ ሁላችንንም ለንስሐ ሞት ያብቃን፡፡ የኋላችንን እየረሳን ከፊታችን ላላው እጃችንን እንዘርጋ፡፡
  ትንሣኤ ለኢትዮጵያ!!

  ReplyDelete
 22. Yes I also agree to my friends idea; as your mentor Abune Gorgorios try to concentrate on another person who can really replace you!

  And also to be free from pride, take the lesson of Christ, go to mountains ....

  ReplyDelete
 23. Dear our brother Dn Daniel,
  Thank you very much for your work.
  Always there has to be someone to stand for our church. There have been so many icons of our church passed in this way. The explanation given is not only answer to the article written against our religion but deeply researched and precisely presented about our Ethiopian St.Teklehimanot.

  God Bless your work

  ReplyDelete
 24. ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

  ጥሩ አድርገህ ገልጠኸዋል፡፡ በእውነቱ እንደዚህ አድርገው በአፍም በመጽሐፍም ተከራክረው የሚረቱ ወንድሞችንና አባቶችን አያሳጣን መቼም ‹ሃገርን ካለ አንድ ጠባቂ አያስቀራትም › የሚባል አባባል አለ፡፡ በእውነቱ ከሆነ መናፍቃን ፈቃደኛ ሆነው በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ቢደረግ ቤ/ክ ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን በ1ኛ ደረጃ ማሰለፍ አለባት ብዬ አስባለሁ፡፡

  በእርግጥ በእውቀቱ የጻፈበትና የገለጸበት ሁኔታ በጣም አሳፋሪና እልህ ውስጥ የሚጨምር ነው፡፡ተከራክሮ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዶ የሚለው ነገር አሁን ካለው የቤ/ክ አስተዳደር ችግር አንጻር ሲታይ የሚያሲሄድ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ የበለጠ የቤተክርስቲያኗን መብት የሚጋፉ በህግም ሊያስጠይቁ የሚችሉ የመብት ረገጣዎች በገሃድ እየታለፉ አንድ ጸሐፊ ስለ አባታችን ጻድቁ ተክለሃይማኖት በማይገባ ሁኔታ ስለገለጸ ቤ/ክ ክስ ትመሰርታለች ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ቢያንስ እኮ ምላሽ መስጠትም የአባት ነበር፡፡
  ስንት ምእመን ነው ስለ ዲፕሎማሲና ስለመጻፍ መብት እውቀት ያለው፡፡ክርስቲያን ክፉን በክፉ አይመልስም በቀል የእግዚአብሔር ነው የሚለው የበለጠ ሊያስሄድና የምእመናንን ቁጣ ሊያበርድ ይችላል፡፡ በዕውቀቱም መሳሳቱን በግልጽ ማሳወቅና በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡ የመጻፍ መብቱ መነካት የለበትም ተብሎ መለሳለሱ ለሌሎች በር የሚከፍት ይመስለኛል፡፡

  ክርስቲያኖች እኮ በወሬ ወይም በአባቶቻችን ገድል ብቻ እንድንኮፈስ የሚያዝ አስተምህሮ የለንም፡፡ መቼ፣ ምን፣ ለምን መስራት እንዳለብን ጠንቅቀን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ እነ በዕውቀቱም ስማቸውን መስለው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዕውቀት አላባ ጭረት ከዶሮም ያሳንሳል፡፡

  በተለይ ‹ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት› በዲ/ን ያረጋል አበጋዝና ‹በዓላት› በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የበለጠ መረጃና እውቀት ይሰጡናል፡፡

  የተፈተነ የተረጋገጠ የተረዳና የተገለጸ እምነትና እውቀት ያድለን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 25. we saw a knowledge gap b/n U and Be-ewketu.I extend my thanks for a man who bit Be-ewketu because if he don`t bit him U didn`t write this article

  Marta

  ReplyDelete
 26. እግዚአብሔር ይስጥህ፤ ይባርክህም።
  የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በረከት እና ረድኤት አይለይህ።
  በጣም አስደሰትኸኝ። ስለዚህ አንተንም እግዚአብሔር ደስያሰኝህ እላለሁ።
  Alemu
  From Adama University

  ReplyDelete
 27. ዘቢለን ጊዮርጊስApril 20, 2011 at 6:26 PM

  ዲ ዳንዔል መልካም መልስ ነው የሰጠኽው ለእኟም ጥሩ እውቀት እንድናገኝ አድርገኽናል ቃለህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 28. Habtamu Hailemeskel

  Thanks D. Dani.

  there is no absolute freedom to write. writers should be aware of this fact. not only freedom of expression but other freedoms have their own limit too. it is wise to guard writers (who doesn't cross the red light in the laws of the country) against any kind of intervention and encumberence. However, one cannot enjoy his/her freedom of exprssion at the expense of other's freedom. This is mockery. Vividly, Bewketu's article is against our (TEKLEHAYIMANOTAWUYANS') freedom of religion. With all due respect to him, He should be tried before court so that others will take care of their articles.


  HAYIMANOTACHIN (Betekiristianachin) YEMETSAF NETSANET MELEMAMEJA AYIDELECHIM.

  ReplyDelete
 29. (የዚህን ዝርዝር የጥናት ውጤት በቅርብ ለኅትመት አበቃዋለሁ፡፡) keep it up I can't wait to see the book.

  ReplyDelete
 30. Dn. Dani, Egziabher YeTebeqeh. Yehn hilinahen yetebeQleh! Zeweter Yemetakoran Ethiopiaw YeTewahedo tebeQa neh. Berta. Egziabher kant gar new!

  ReplyDelete
 31. ወንድማችን ምን እንደምል አላውቅም። እሱ በስውር ሁሉን ያድርግልህ። ለሚዲያው ቅርበት ያለን ሰዎች ለምን የማገናዘቢያ እንትናችን የወረደ እንደሆነ አይገባኝም። ብዙ አማራጮች በዙሪያችን እያሉ ነገሮችን በተለያዩ አቅጣጫ ለማየት አለመታደላችን በጣም ያሳዝናል። አንዳንዱማ ጽሑፉን ሳያነብ ሲተች ይታያል። ትችቱም ቆቅ ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ አይነት ነው። እናም በዚህ ውስጥ እያለን አንተን የመሰለ እግዚአብሔር ሰጠን። አንዲህ አይነት ሰዎችን አያሳጣን። ነቃፊም ተችም አያሳጣን።

  በውቀቱን በጽሑፎቹ እጅግ በጣም አደንቀዋለሁ። ብዙ ጊዜ ሞኝ ሁለት ጊዜ ይስቃል የሚባለው ነገር በእኔ ላይ ደርሷል። ፍሬ ነገሩን እንዴት አድርጎ ማስተላለፍ እንዳለበት ገብቶታል። የመሰለውን ይጻፍ። የጣመንን መውሰድ የመረረንን መትፋት የራሳችን ስራ ነው። አሁን ይህን ባያወጣ ንሮ እንዲህ የረብራራ ስለ አቡነ ተክለሐይማኖት መቸ አነብ ነበር። ያውም ቀልቤን ሰብስቤ። እናም በውቀቱን አመስግኘዋለሁ። በርታ የኔ ወንድም።

  በመሃል ሆናችው ያልተረዳችሁትን ለምታራግቡትም ልቦና ይስጣችሁ። የምትሰጡትን አስተያየት ወደ እኛ ከማድረሳችሁ በፊት እራሳችሁ ደግማችሁ አንብቡት። ጮርቃ የሆነ አስተሳሰባችሁን እባካችሁ---ገና ሳይበስል እጅጅ እያለን ነው።
  ይቆየን

  ReplyDelete
 32. Hey Daniel,

  I am your fan but i have always surprised when you explain the values of Orthodox. I think you are confused or try to mislead the new generation about Amara, Orthodox, and Ethiopia. Let me give you example, what do you think about "netela" or yehabesha kemis"? Is it part of Orthodox church ( we do not see it in Greece or Russia), is it Ethiopian tradition as some argue ( southerners or the somalies at least do not wear it)...so what...it is just simply one of ethiopian tribe's tradition i.e " yeamara bahil" but since it is beautiful with out any misleading the non Amharas can wear it any time

  ReplyDelete
 33. I liked it very much!

  ReplyDelete
 34. “መቼም አታወጣው!” ላልከው ወገኔ

  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ኢየሱስ ክርስቶስን የሰበኩ እውነተኛ ሃዋርያ ናቸው። የማቴዎስ ወንጌል 5፤14 “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ የምለውን ቃል የፈጸሙና “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ከተባሉት የተደመሩ ቅዱስ የጌታ አገልጋይ ናቸው።

  እኛንም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አይናችን አንድንተክል ብቻ ሳይወን ሁሉን ቻይ አዳኝ እና አምላክ እንደወነ አምነን በአፍ ሳይወን በህይወት እንድንከተለው የሰበኩ ሃዋሪያ ስለወኑ ቅዱስ መጽሃፍ እንደሚል “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።” የሚለወን ቃል ተከትለን እኛም ተቀብለነዋቸዋል።

  አንድ ግን የማልከደው ነገር አለ ይኽውም “ሰይጣንን ንጉሳቸው አድርገው ለሾሙ አንዳንድ ሰዎች” አይናቸውን ከሰይጣን ላይ አንዲያንሱ እና ጌታችን ኢየሱስን እንዲከተሉ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሁንም ያደርጋሉ። ጌታን (ለርሱ ክብር ይሁና) ብዔል ዜቡል ያሉት ያልታደሉ ወገኖች ክርስቶስ ኢየሱስን የሰበኩትን ቤተሰቦቹንማ አብዝተው እንደሚሰድባቸው ከእውነተኛው ጌታ ተረድተናል። አቡነ ተክለ ሃይማኖት “የዓለም ብርሃን ናቸው” ይህ ብርሃንነት ከጌታ የተሰጣቸው ስለወነ ፤ እንኳን ስጋ የለበሰ ሰው ይቅርና ክፉ መንፈስም ለዘመናት ታግሎ ተሸንፋል።

  ስለዚህም እባክዎትን ስድብዎትን ና የመውጊያው ብረት የሚያስብስብዎን ትግሎትን ያቁሙ።

  ከክርስቲያናዊ ፍቅር ጋር
  ለምለሙ ከካናዳ

  ReplyDelete
 35. እኔ ግን በጣም እየገረመኝ ካሉት ጉዳዮች አንዱ ፡ - ከተወሰኑ አመታት ወዲህ ማለቴ ነው፤ ለአገሪርቷ በስልጣኔ ሃላ መቅረት እራሳቸው ባለማወቅም ይውን ፤ ለዲምክራሲ ፍለጋ እንበለው ከአገርቷ ጠላቶች ጋር ተባብረው አገሪቷን ለአመታት በጦርነት ጠምደው የልጆቿን ደምና ንብረትና እንዳወደሙ እያወቁት፡ የነሱን ጥፋት ቤተክረስቲያን ላይ ማላከክ እስቲ ምንይሉታል? አውቆ የተኛን ካልወነ…

  እኔ ቤተክርስቲያንን ለአገርችን ድህነት ተጠያቂ የሚያደርጉትን በሁለት እከፍላቸዋለው፡ 1) ሀይለኛ ዝናብ በዘነበ ቁጥር ለጎርፉና ለንብረት ሁድመት ቤተከርስቲያን በአገራችን ላይ ያመጣቸው እርግማን ነው የሚሉ። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከመንቀፍ የማይመለሱ ፤ በዋናነት አላማቸው የክርሰቶስን መንጋ መስረቅ የወነ። 2) የ“Protestant work ethic” የተባለውን የሰሜን አውሮፓ ና አሜርካን ለማሞገስ የፈለቀውን ያለተፈተነ ሃሳብን የሚያራምዱ አንዳንድ ፊደል ቆጠርን የሚሉ ሰዎች ያለተገራ አስተሳሰብ ሲወን ።

  የመጀመሪያዎቹ በአማሪካ ወስጥ የተውፈጥሮ አደጋ ሲደርስ የህዝቦቹን እምነት(ሃይማኖት) ጥያቄ ወስጥ ለማስገባት ድፍረ የሌላቸው ፤ በኛ አገር ወይም በጃፓን አደጋ ሲደርስ ህዝቡን የእነሱን “ክርስትና” አይነት ተከታይ ስላልወነ ነው ብለው የሚከሱ። ወጥነት የሌለው ተራ አመልካከት አንጽባራቂዎች ናቸው። እነዚህ ወገኖች ተከታያቸውን ለማብዛት የሚከተሉት ዘዴ ፡ - ከየትም ፍጭው ዱቄቱን አምጪው ስለወነ ፡ እነሱ ዱቄት የሚሉትን ለማግኘት የማያደርጉት የለምና እየተከታተሉ መግለጥ ያሰፈልጋል።

  ሁለተኞቹ ደግሞ፦ የተፈጥሮ ሃብት እንደጉድ እያላቸው በድህነትና ፤ እርስበርስ በመጨራረስ ፤ሰላምና ዲሞክራሲ በማጣት ከእኛ አገር የባሱትን አገሮች እንደ ኮንጎ ኪንሻሳ እና ሩዋንዳ .. ለምን እነዚ አገሮች እነሱ የሚሉትን የ“Protestant work ethic” ከአሜርካ ጎን እንዳላሰለፋቸው አይነግሩንም። በነሱ ሎጂክ መሰረት እነዚያ አገሮች በርስ በርስ የተጫረሱት “Protestant ethic” በነሱ ባህል ወስጥ ስላለ ነው ማለት ይቻላልንን? እነዚህ ወገኖች ጃፓናን ሲንጋፖር ከድህነት የተላቀቁት በ“Protestant work ethic” እንድማይሉም ተስፋ አደርጋለው ምክንያቱም እነዚህ አገሮች እምነታቸው ከምራቡ አለም በጣም የተለየ ነው። እነዚም ወገኖች የቆጠሩት ፉደል biased እንደወነ እለት እለት በማስረጃ ሊገለጽላቸው ይገባል።

  From Canada

  ReplyDelete
 36. I learned more from this TOM ARE,CERTAINLY GOOD CULTURE DEVELOP IN OUR COUNTRY CONFLICT AND AGREEMENT WITH NOTION WITHOUT USING VIOLENT PHYSICAL FORCE( MEDEBADEBE)
  Egzabhere Bertatune Yestachu, Yesthe(DN.)
  Bewqetom berta, we learen from yourintial idea.

  ReplyDelete
 37. አቡነ ተክለ ሃይማኖት በአንድ እግራቸው የጸለዩት ለበዕውቀቱም ጭምር ነዉና፡፡ ይሕች ቃል ብቻ ለኔ በቂ ሆናለች፡፡

  እግዚአብሔር እንዳንተ ያለ ሰው አያሳጣን፡፡

  ReplyDelete
 38. “ ወደሞት የሚነዱትን ታደግ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን ” ምሳ.24/11
  ሰው ወደ ሞት የሚነዳው አውቆ በድፍረት ሳያውቅ በስህተት ነው•እንዲህ አይነቱን ሰው መታደግ ደግሞ ክርስቲያናዊ ተግባር ነው•ምክንያቱም ብዙዎች ወደመታረጃቸው እየሔዱ ያሉት በዚሁ መንገድ ስለሆነ ነው•ወንድማችን ዳኒ በእውቀቱንም በዚሁ በጠቢቡ ቃል እንደታደከው ተረድተናል እሱን ብቻ ሳይሆን በተነሳው ጉዳይ ላይ ሊጠፉ ያኮበኮቡትን ሁሉ በመታደግህ“አድን” የተባለውን ቃል ፈጽመሃል ለወደፊቱም በማይነጥፈውና በተባው ብእርህ የበለጠ እንደምታስነብበን እምነታችን የጸና ነው መልካም ትንሣኤ ላንተና ለመላው ቤተሰብህ•
  ቀሲስ ከፍያለውና ዲ/ን ምትኩ አ.አ.

  ReplyDelete
 39. ታዳጊው ወንድማችን በእውቀቱ በጻፈው ላይ ብዙ ስለተባለ መጨመር አልፈልግም።ልብ ያለው ልብ ይበል። ከአስተያየቶች ውስጥ ትኩረቴን የሳበው እና በከፊል የኔም አስተያየት ስለሆነው እና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሰላቀረበው ትንሽ ልበል። የጡመራህን አንደኛ ዓመት ያከበርክበት ዝግጅት ብዙም አላስደሰተኝም። ሰርተህ በቀላሉ የምትረካ አይመስለኝም ነበር።አሁን መርካት ጀመርክ? ዕቅዶችን ግባቸውን መቱ ማለት ነው? ያ ሁሉ መወድሰ ዳንኤል ሰለምን አስፈለገ? "የማንጠቅም ባሪያዎች ነን" ማለትን ትተን በሚታይ ስራችን እንዳንመካ እፈራለሁ። በመወድሰ ዳኒ ላይ ድክመቶችህ ተነግረውህ ነበር? አንተም እኮ ትዳር በተመለከተ ከዚህ በፊት ካስተማርከው ጋር የሚጣረስ የሚመስል ጽሑፍ አስነብህናል። ልብ ያለው ልብ ይበል.....

  ReplyDelete
 40. AD ግን ማንበብ ትችያለሽ በእወነት ነው የምልሽ? ያነበበው ሰው ይታዘብሻል ዝም በይ ዝም ስትይ ማንም አይገምትሽም ለራስሽ ነው።

  ReplyDelete
 41. ዲ. ዳንኤል

  ስለ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ እና ማንነት በዝርዝር ያቀረብከዉ የምርምር ጽሁፍ እጅግ በጣም ጥሩ ነዉ፡፡ መልእክቱም ሰዎች ቢያንስ ስለማያዉቁት ነገር እንዳይጽፉ፤ መጻፍ ከፈለጉ እንኩዋን በአግባቡ ሊያነቡ እና ሊጠይቁ እንደሚገባቸዉ ያስተምራል፡፡

  ከዚያ ዉጪ ግን በእዉቀቱ ስዩም ለጻፈዉ መጣጥፍ ተገቢዉን መልስ ሰጥተሃል ብየ አላምንም፡፡ እንደኔ ግምት ከበዉቀቱ ጋር ያለህ ወዳጅነት ተጽዕኖ ሳያሳድርብህ አልቀረም፡፡ ያንተን ጽሁፍ በጥሞና ያነበበ ሰዉ በዕዉቀቱ ስዩም ከታሪክ ማዛባት በቀር (እሱም ሆነ ብሎ ሳይሆን ከግንዛቤ ማጣት) ቤተክርስትያኗን እንዳላጠቃ፤ እንዳልዘለፈ ነዉ የገለጽከዉ፡፡ እንዲያዉም ይባስ ብለህ የሙገሳ ቃላትን ነዉ የደረደርክለት፡፡ የራስህን አዲስ የኦርቶዶክስ ስያሜ ፈጥረህ (የማያምን ኦርቶዶክስ) እንደምንም አጠጋግተህ አስገብተሀዋል፤ ምንም እንኳን እርሱ እኔ አለማዊ ፈላስፋ ነኝ ቢልም፡፡

  ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጻፈዉ መጣጥፍ ላይ የምታወድሰዉ ብታጣ አንባቢ ይታዘበኛል እንኳ ሳትል “በሌላ በኩል ደግሞ በዕውቀቱን አደንቀዋለሁ፡፡ ብዙ ጸሐፊዎች ከውጭ በመጣ ሃሳብ ኢትዮጵያን ማየት ሲመርጡ በሀገራዊ ተምሳሌት እና ሃሳብ ራሳችንን ለማየት መሞከሩ በዕውቀቱ ውርጅናሌውን የያዘ ጸሐፊ ነው እንድልም አድርጎኛል” በማለት ሀገራዊዉን ጻድቅ አባት ለክፉ ነገር ምሳሌ መጠቀሙን በተዘዋዋሪ እዉቅና ሰጥተህለታል፡፡

  ከዚህ ባሻገር ከእንደ አንተ አይነት ጸሀፊ የምንጠብቀዉን እና ቤተክርስቲያኒቱ ለድህነት ሳይሆን ለእድገት ያበረከተቻቸዉን አስተዋጾኦዎች በጥናት በተደገፈ መልኩ አቅርበህ የበእዉቀቱን ዋና የፍልስፍና ሀሳብ ሳትረታልን ቀርተሃል፡፡

  በመጨረሻም ሀሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ያንጸባረቅከዉ አቁዋም ፈጽሞ የማልስማማበት እና ከቤተክርስትያኔ መምህር አንደበት እንዲወጣ የማልመኘዉ አቋም ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የአንድን እምነት ትምህርት እና አማኞቹ የሚያከብራቸዉን ጻድቅ መዝለፍን ነዉ “እናም በዕወቀቱ ይጻፍ፣ የማልስማማበትንም ነገር ይጻፍ፣ እኔም የምስማማበትን እይዛለሁ፣ የማልስማማበትን እሞግታለሁ፡፡ ለበዕውቀቱ የመጻፍ ነጻነት ግን ጥብቅና እቆማሁ” በማለት የደገፍከዉ? ይህስ ህጋዊ ነዉን?

  ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ዘለፋ እና ስድብ መቼም ሆኖ አያዉቅም አይሆንምም!!!

  ከተክለሀይማኖታዊያን አንዱ

  ReplyDelete
 42. @ዝምታ---በመጀመሪያ የሚጣረዝ የሚመስል ስለ ትዳር ያስነበበንን በዝርዝር ጻፍልን። ለማደናገር አትሞክር። ወንድማችን የሚጽፋቸው ጽሑፎች--የራሱ እይታዎች መሆናቸውን አትዘንጋ። እሱ የተመለከተበት ላንተ ላይስማማህ ይችላል። የተሻለ ብለህ የምታስበውን አንተ ደግሞ አቅርብልን። የምንኖርባት አለም አሁን እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው በሐሳብ ፍጭትና እሱ በወለደው እውቀት ነው የሚል የራሴ ግንዛቤ አለኝ። ረካህ ማለት ነው ያሁሉ መወድስ የቀረበልህ ብለህ ያነሳኸው አልገባኝም። አሹልከህ ልታስገባ ያሰብኸው ነገር እንዳለ ግን ከጽሑፍህ ያሳብቅብሃል። በግልጽ ብትናገር ይሻላል። ለእኔ የሚገባኝ አንድ ሰው ወይም ድርጅት አመቱን ሙሉ ያከናወነውን በተለያዮ መንገድ ይገመግማል ያስገመግማል። ይህም ያለፉትን አይቶ ለበለጠ ለመስራት ስለሚረዳ ነው። እንዲህ አይነት ነገሮች አስፈላጊ መሆናቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም አለማዊ መጽሐፍት በስፋት ይጠቅሳሉ። እንደ እምነትህ አንዳቸውን አንብባቸው። እናም ወንድማችን ስለ ረካ ሳይሆን ያለፈበትን ለማየትና ለወደፊቱ ደግሞ ለመተለም ነው።

  እግዚአብሔር እንደ ወንድማችን ነገሮችን በተለያዩ አቅጣጫ እንድንመለከትና ለራሳችንም ለሌሎችም የምንተርፍበትን ጥበብ ያድለን።
  ከጀርመን

  ReplyDelete
 43. hi dani i really like this- በይኩኖ አምላክ እና ሥልጣን ላይ በነበረው በነአኩቶ ለአብ መካከል በሚፈጠረው ጦርነት የሀገሪቱ ልጆች ባለቁ ነበር፡፡ ዛሬ ቢሆን ይሄ ተግባር የኖቬል ሽልማት የሚያሸልም ነበር፡፡ ይህ ስምምነት በኋላ በዐፄ ይትባረክ ዘመን በመፍረስ የተከሰተውን ጦርነት ያየ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ያደንቃል እንጂ አይተችም፡፡

  ReplyDelete
 44. Dani selamun egziabher yabzalih,
  Kante yemitebek orthodoxawi milash new.
  Dgimo bewketum bitihon betinsh ewuket bizu difret atabiza,mejemeria negerochin telek bileh temelket,
  ante bizu yemiyamiru qualitwoch silaluh eneza lay berta.difiretin gin atabza

  ReplyDelete
 45. dani, i would rather thank God who give you this eye , and also the MK team who help you in any kind for today's Daniel . so in your life don't see yourself out of these( - God and MK ).
  for the personality , Knowledge , dedication to the church and 'Zina' that you now is directly or indirectly is from MK .

  my doubt comes because all the comments are Mugesa which will made you to feel that it is your job only . this feeling(' Enie negn, enie bicha negn tikikil '...) was killed what we loved , is killing and will kill others.
  as a result i don't want you to be killed by this feeling that is why i remind you .
  there are a lot to do for our church .

  i prefer if you are not post it

  Gebre
  Awassa

  ReplyDelete
 46. Dear Dn Daniel:

  I love the way u compose the facts as it needs broad and deep study to do it this way. Egziabher Yestehe. But i completely don't agree with the way u explained free way of writing. yetesafewe hasab weyime amelakakete sayihone weshete newe. Weshete demo endelebe yetsafe ayibaleme. Yaweme Abatachine laye. Generally also on ur conclusion while u wrote about Marriage and this article i saw u being veryyyyyyyyyyyyyyy liberal on some spiritual things. Abatoche endihe alenorume alastemarume demome democrat enji betam liberal(huluneme masemamate) type alneberume. i can't pinpoint the problems as such by now, but i can smell something bad.

  ReplyDelete
 47. ስለበዕውቀቱ ሥዩም የተባሉትና እኔ የተመለከትኳቸው ጥቂቶቹም ሆኑ ለዳንኤል ክብረት የተሰጡትን ጥቂት የማይባሉ አስተያየቶችን ስመለከት “አንድ ሰው አንዳች ነገር ብሎ ስለቤተክርስቲያን ስለጻፈ ወይም ስለተናገረ ቤተክርስቲያን ትዋረዳለች፡፡” የሚል እምነት ከጀርባቸው ያዘሉ ሆነው ታይተውኛል፡፡ ይህ እምነታቸውም ይመስላል ብዙዎቹን ሰዎች ስለ እምነታችን አንድም ሰው አንድንም የማንወደውን ነገር እንዲናገር ወይም እንዲጽፍ አንፈቅድም የሚል ጽንፍ እንዲይዙ ያደረጋቸው፡፡ ይህ አመለካከት ከሚከተሉት ነገሮች የሚመነጭ ይመስለኛል፡-
  በምናምነው ነገር ከልብ ካለማመን
  እውነተኞቹ አባቶቻችን የሚያምኑትን ነገር ፊትለፊት ገጥመው ይከራከሩበታል፤ ይከራከሩለታል፤ የተቀናቃኝን አፍ አስይዘው ይረቱበታል እንጂ ገና ለገና እገሌ ይህን ስለተናገረ ይገደል፤ ይሰቀል አላሉም፡፡ ይህንን የሚሉ በክርክሩ አስቀድመው ተረትተዋልና መጀመሪያ የሚያምኑትን ነገር እውነት ያምኑት እንደሆነ ራሳቸውን መጠየቅ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ እስኪ አንድ ጊዜ ራሳችንን እንጠይቅ፤ እናምናቸዋለን የምንላቸውን ነገሮች ምን ያህል እናምናቸዋለን? አንድ ሰው ተነሥቶ አንድ ነገር በተናገረ ቁጥር የምናምነው ነገር መሠረቱ እንደተነቃነቀ ወይም ጣሪያው መሸንቆር እንደጀመረ የሚሰማን ሰዎች ያለንበትን የእምነት ደረጃ መለስ ብለን ልናጤን ይገባናል- አንድን ነገር ከልብ የምናምነው ከሆነ ጠላቶች ክፉ ቢያወሩበት እንኳ ክፉ አለመሆኑን ለሌሎች የማስረዳት ግዴታው ክፉ አለመሆኑን በምናውቅ በእኛ ትከሻ ላይ ይወድቃልና፡፡ የሚያምኑት ነገር ተቀናቃኙ እንደሚለው አለመሆኑን በጥብዓተ ልብ፣ በአእምሮ፣ በማስተዋል ማስረዳት እንጂ መቆጣት የትም አያደርስም፡፡ ሰውየውን ብንችልና ብንገድለው እንኳ አንድ ጊዜ የተናገረውንና አደባባይ የወጣውን ነገር መልሶ ማስዋጥ አይቻለንም፡፡ በሌላም በኩል እኛ ሳንሰማ ሳናይ ብዙ ልንባል እንደምንችል ማስታወስም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ሐሳብን በዱላና በቁጣ ወይም በፍርድቤት ማስቆም አይቻልም፡፡ ይህን የሚያደርጉም የሰውን አእምሮ እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደገል ቀጥቅጠው ቢያዝዙ፣ ቢገዙ ደስ የሚላቸውና ያንንም ለማድረግ የሚሞክሩ አምባገነኖች ብቻ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ መቼም ተሳክቶላቸው አያውቅም፡፡ “ጠንቋይ መጋረጃ ለምን አስፈለገው?” ቢሉ አለማወቁን ሊሸፍንበት ነውና፡፡
  ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት
  ምናልባትም የብዙዎቻችን የእምነታችን ጥልቀቷ ከልጆች ብይ ማስገቢያ ጉድጓድ ያለፈ ያለመሆን ዐቢይ ምክንያት ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀታችን ይመስለኛል፡፡ ብዙዎቻችን ስለምናምናቸው ነገሮች ምን ያህል ከእንጀራ ማግኛ ወይም ከመግቢያ (ኢንትሮዳክሽን) የዘለለ ዕውቀት እንዳለን ራሳችንን ብንጠይቅ ያዋጣናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ውሸትን ውሸት ማሰኘት የሚቻለው ዕውነቱን ገልጦ ማሳየት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ እውነትን እናውቃለን የምንል ሰዎች እውነቷን ገልጠን ካላሳየናት የኛን ዕውነት ማን ያውቅልናል? ችግሩ እውነትን እንደምናውቅ ብንናገርም እውነትን ምን ያህል እንደምናውቅ ለራሳችንም እርግጠኞች አይደለንም፡፡ ስለዚህም እንዲህ የምናምነውን ነገር የሚሞግት የሚመስል ነገር ሲቀርብ ማጣፊያው ያጥረናል፡፡ ዳንኤሎች መልስ እንዲሰጡልን፣ ተቀናቃኞቻችንን “ልክ ልካቸውን ነግረው አንጀታችንን እንዲያርሱት”፣ የፈረሰውን የእምነታችንን መሠረት እንዲያጠባብቁልን እንጠብቃለን፤ ምክንያቱም የምናደርገውን ብቻ ሳይሆን የምናምነውንም አናውቅም፡፡ የተሳቢነት በሽታ፣ የጥገኝነት ሱስ ትብትብ አድርጎ ይዞናል፡፡

  በቤተክርስቲያን ላይ ማንም የፈለገውን አመለካከት ሊይዝ ይችላል፡፡ ይህ የሚያስደነግጣቸው ሰዎችም ይኖሩ ይሆናል፡፡ እነዚህ የሆነ ነገር በተነገረ ቁጥር የሚበረግጉ ሰዎች ከበረት ጠፍተው እንዳይኼዱ ለማድረግ ግን ሐሳቦችን ማፈንና መደፍጠጥ መፍትሔዎች ሊሆኑ አይችሉም፤ አይገቡምም፡፡ ይልቁንም ሰፋ ባለና ጨዋነት ባልተለየው መንገድ ሐሳብን በሐሳብ፣ ክርክርን በሰፊ ዕውቀት ላይ በተመሠረተ ክርክር መርታት የሚችል ሰብእና ባለቤት ሆኖ መገኘት ብቻ አዋጪው መንገድ ሆኖ ይታየኛል፡፡ ዳንኤል ጥሩ አድርገሃል፡፡

  ReplyDelete
 48. Dear Dn Daniel: I don't know how u see things nowadays but u r getting too liberal on many aspects. And this article happen to be one of it because:

  1. though u explained two core facts very well and beat bewketu's idea but u never emphasize on the fact that he shouldn't dare to write such things again. u were even supposed to use some haile kale. but never done. i don't even thnk u have the intenet.
  2. you appreciate his try of looking at our problems from our own point of view. Hey, do u think mentioning Abune teklehaimanot as an example for such an idea is lookin at it from ethiopians point of view? if ur answer is no then why do u appreciate the try? atleast if u appreciate it by urself u were only suposed to talk to him in person. But u gave more lines to the appreciation than pinpointing his wrong doings.
  3. U wrote a completely usless thing regarding freedom of writing. u don't even have a slightest clue about it. What is wrong regarding bewketu's article isn't about ideas(personally i do have a problem with the idea of representing ethiopians with being lazy on job)rather the problem is that he wrote false facts about our most respected spiritual father and base his ideas on that. so r u saying writing false facts on the most respected spiritual father included in freedom of writing? shame on u. I was expecting u to balance the freedom of writing with the spiritual respect we give to our father and bring some demarcation for writers. or atleast i expect u to say notin on this. but now what u said is very shameful.

  So in general don't get carried away by some narrow principles(freedom of writing, what if ppl get divorced if they can't live together.....) and write something usless and misleading in ur blog. Also try to watch out the way u do things like ur 1st year anniversary of blog, m not sure but 20th year anniversary of ur being preacher,....all these moves aren't useful in my view. Wudase kentune yegabezaluna. Yelike bertana yemitekuhene afera, endederowe zeme bele serahene sira. I m noone to comment all these on u but in my view problems got repeated and i feel responsible. anyways if possible try to get a lesson from kesis Dejene's blog_Just teaching yeabatochene temeherte through modern medium. But urs is way far from that. the approcah isn't k. medhanealm yerdane. kefetognale

  ReplyDelete
 49. ሰዉን ግን ምን ነካዉ? ቀፎዉ የተነካበት ንብ መሰለ ምናለ የዳንኤልን መልስ ብቻ ሳይሆን በዉቀቱ የፃፈዉንም ቢአነበዉ እላለሁ። ዲ.ዳንኤልን መጠየቅ የምፈልገዉ ግን በየዎሩ የምከበሩት በኣላት ስንት ናቸዉ? ሥራ ባለመሥራት ነዉ መከበር ያለባቸዉ? ነዉ እየተሰራም ቢከበሩ ልዩነት የለዉም በኣላቱስ በኛ ሃገር ብቻ ነዉ ዎይስ በሁሉም የአለም ዖርቶዶክስ አማኞች ይከበራል? ያለሥራ እንዲከበሩ የሚደረጉ የዉግዝ በዓላትንስ ማዉገዝ የሚችል ምን ዓይነት ደረጃ ላይ ያለ ሰዉ ነዉ? የሚሉትን ጥያቄዎች ነዉ ምክንያቱም ለስራ በምዘዋወርባቸዉ የገጠር ከተሞች የማያቸዉ በየቦታዉ የተለያዩ የበአል አከባበሮች ስለሚአስገረሙኝ እና መሰረቱ የግብፅ ጳጳሶች ናቸዉ የሚለዉን እንዳምን ስለሚአስገድደኝ በመረጃ የተደገፈ ነገር ካለ ለኔም ሆነ ለመሰሎቸ ትልቅ ትምህርት ነዉና ከተቻለህ አንድ ፕሮግራም ያዝልን

  ReplyDelete
 50. የሚያምኑት ኦርቶዶክሶች ኦርቶዶክስን የድኅነት/poorness vs heal/ መንገድ አድረገው የሚቀበሏት ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 51. እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰህ፡

  እግር ያለው ባለክንፍ የሚለው ጽሑፍ በእውነት ለበእውቀቱ መልስ ብቻ ሳይሆን ለኛም ትምህርት ነው፡፡ ዳሩ ግን የመጻፍ ነጻነት ማለት ምን ማለት ነው፡፡ በጻድቁ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ጽፎ በህዝብ እይታ ውስጥ ለመግባት ከሆነ በፍጹም ተሳስቷል፡፡ በእውነት ነው የምልህ እኔ የተክልዬ ባሪያ ነኝ ጽሑፉን ሳነብ ከልቤ ነው ያዘንኩት፤ ጻድቁማ ምን ያህል ያዝኑበታል፡፡ በእውነት እኔ ይህን የመጻፍ ነጻነት አለው ግን . . . . ለማለት ያስቸግራል፡፡ በአንጻሩ
  ..አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መጽሐፍ አጠበች..

  ይቆየን

  ReplyDelete
 52. this is form positive thinker!!!
  it is good writing!!!
  kibrealem

  ReplyDelete
 53. Many has been said about Daniel's current form. I conqure the fear. Wudase beztual. His 1st year anniversary was celebrated far from an Orthodox culture. He was being praised and praised. even someone suggested to publish his story now. Is that what our fathers used to do?

  At the end of the programe, he have even been putting his signature for his fans. This needs a very very cautious watch. Dany..... becareful. You are being washed by "liberal chrsitianity" as you preached it yourself.

  Ene Begashawuns yetelanachew lezihu ayidel?

  ReplyDelete
 54. " Dear Dn Daniel: I don't know how u see things nowadays but u r getting too liberal on many aspects."

  i support this idea especially pls focus on creating other daniel's i read that you are impressed by gash Girma who teach 10 --ppl but fruit full i expect this .

  Pls Don't start the wrong way , the wrong way is accepting what the people around you like celebrating yr 2o yrs preaching .... one yr blog ,,,,,, Look Dn. Daniel Abun Powulose do u think they were as what they are now ? absolutely no . ahun gin kine kaltekegnehilachew yamachewl

  yegemerachew gin endih alneberm , so please be wize don't accept any thing which leads you to the wrong direction . pleaseeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeee

  ReplyDelete
 55. Hello Daniel.

  I agree with your articles claims in general. I also appreciate the effort you put to make all those statements so the vague can be crystal clear.

  But, as far as Bewuketu is concerned, he has the sole right to say whatever he feels is worth saying. I feel, as we need to have a democratic system of government, we as well need a democratic religious thinking.

  It's never in any christian book that anyone writing what he feels about a religion should be hated and/or hurt. Everyone has the freedom of expressing anything he feels.

  In general, we should not hate those who try to write anything that opposes, ridicules, or insults whatever we believe in, though we may not like them.

  There were lots of articles, books, journals etc. written mocking and insulting Ethiopian Orthodox. Why is it different with Bewuketu that we hated and hurt him that much?? That is an important question we have to ask ourselves.

  Finally, please remember that I am an Orthodox Christian so understand that it's not because I am from another religion that I am putting this argument against Daniel's.

  Thank you,

  Netsanet

  ReplyDelete
 56. ስለ በዓል የጠየቅኸው ስምየለሽ (አኖኒመስ) ለማጠቃለያና ለወቀሳ ከመጣደፍ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ የጻፈውን “በዓላት” የተሰኘ መጽሐፍ አንብብ፡፡ የሚጠቅም ነገር ታገኝበታለህ ብዬ አምናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 57. ዲ/ዳኒ በአንተ እውቀት ሁሌም እደነቃለው፡፡ እንዲ በሙሉ እውቀት እውነታን የሚያስጨብጥ ሰው ያብዛልን፡፡ የተክልዬ በረከት ይደርብ ይደርብን፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 58. Once again I agree Daniel did the great thing. If he denounces Beewqetu - what will happen to him? I do not know.

  For your judgement I cut and paste what I consider the major problems in his article.
  የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ነጥሎ መተንተን ይቻል ይኾናል የእኔ እና የአንተ ማኅበረሰብ ግን የቄሳር እና የእግዚአብሔር ጥምር መንግሥት ውጤት ነው አንዱን ካንዱ ነጥሎ መመልከት ብዙ አይሳካም በዚያው እንቀጥል የኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ እና ባሕል ባንድ ገጹ ስናየው ሃይማኖታዊ ነው ግን ሃይማኖታዊ ባህል ይዘው በምድር የተሳካላቸው ማኅበረሰቦች አይጠፉም የእኛ ከሃይማኖታዊነትም የባሰ ነው ምናልባት ተክለሃይማኖታዊ ነው የሚለው የተሻለ ይገልጸዋል::

  እንግዲህ በሰማዩ ላይ አለቅጥ ሲያተኩር ምድሩን የሚከዳ ምድሩም የምትከዳው ማኅበረሰብ ተክለሃይማኖታዊ ይባላል።
  If Daniel agrees I can paste Beewqetu's article which I got it from Cyber Ethiopia.

  ReplyDelete
 59. Daniel,
  This is a very BOLD move that (for some reasons) I expected from you.

  I really appreciate what you did. We strongly need Be'ewqetu and YOU, man. We don't want to see white blank pages.
  I was discussing with some freinds, about your silence on the past editon of Rose / Addis Guday.

  Thanks any ways,
  Meron from Lebu hills

  ReplyDelete
 60. dani lante kale hiywot yasemalen bedmea betsega yetebekeh esti lehulachenem egziyabehair asteway lebonan yesten enea eskemigebagne deres manem mebtu enditebekelet yefelegal yemikedmew gin yelalochem mebet mebet bemakeber new manem manenem eskalneka deres manem lay cheger yemifeter aymeselegnem BEWKETU ergetegna negne yehenen tsehufem hone asteyayet tanebewaleh ahunes yaleh asteyayet menden new lela lenegereh yemefelegew neger anadandea mebete new bemalet alasfelagi waga yaskefelal (AZEB MESFIN ledetuan sitakeber TEDDY JA YASTESERYALEN azefenaw neber alu tagayoch maguremrem sigemeru tenesta ewnet yehen kumta alebesenem woye ahun selekeyernew leneresaw yegebal woye setel hulum zem alu ayenageruat neger AZEB natena hulum belbu gen yeTEDDY AFRON meche ena endet endemibekel eyaseb AZEBEM beleh natena men endasebu bemeredat TEEDIN lebechaw terta egnas eneredahalen gen andand tebaboch yehen selemayerdu arfeh betkemet yeshalehal alechew yehew ersum kalefew temero ja yasteseryal silut ebakechu ayer lewsedebet tewugne malet jemerual selezih BEWKETU beleh kesew yemaral (saykefel yalewaga) mogne genen simekerut embi belo benetsa endememar keflo yemaratal selezeh yalefe alfual neger hulu lebego new beleh endih aynetun sehetet atedgem kehzeb tetalto wedet yekedal

  ReplyDelete
 61. Dani, it is better to leave the concept of freedom of writing to the legal professionals. no one can be left free if his writings infringe others' freedom. He clearly insults the Saint that OUR CHURCH using false facts. It is against laws of the country. He and the Magazine will get the punishment if they continue insulting us.

  In this respect you are too liberal.

  ReplyDelete
 62. Part 1
  እግር ዐልባው ባለ ክንፍ
  በእውቀቱ ስዩም

  አንድ ባልንጀራዬ በኢ -ሜይል በጻፈልኝ መልእክት ላይ ሰሞኑን በእምነታችን ዙርያ ማጉረምረሜ እንዳልተዋጠለት ጠቅሶ እሱን ትተህ በአስተዳደሩ ላይ ብታተኩር ወንድ ትባል ነበር በማለት ምክሩን ለገሰኝ :: አልተገናኘንም ወንድሜ እኔ ዐምዱን ያስከፈትሁት ባሕታዊውን ታሪካችንን በዓለማዊው መነጽር ለማየት እና ለመተርጎም አስቤ ነው እምነት እና አስተዳደር ተነጣጥለው በሚቆሙበት ማኅበረሰብ ውስጥ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ነጥሎ መተንተን ይቻል ይኾናል የእኔ እና የአንተ ማኅበረሰብ ግን የቄሳር እና የእግዚአብሔር ጥምር መንግሥት ውጤት ነው አንዱን ካንዱ ነጥሎ መመልከት ብዙ አይሳካም በዚያው እንቀጥል
  የኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ እና ባሕል ባንድ ገጹ ስናየው ሃይማኖታዊ ነው ግን ሃይማኖታዊ ባህል ይዘው በምድር የተሳካላቸው ማኅበረሰቦች አይጠፉም የእኛ ከሃይማኖታዊነትም የባሰ ነው ምናልባት ተክለሃይማኖታዊ ነው የሚለው የተሻለ ይገልጸዋል በገድላቸው እንደሰማነው አቡነ ተክለሃይማኖት ብዙ ዓመታት ቆመው በመጸለያቸው እግራቸው ተሰበረ ፈጣሪም በገድላቸው ጽናት ተደስቶ ደርዘን ሙሉ ክንፍ ሸለማቸው ታሪኩ ተፈጽሟል ወይስ የደብተራ ፈጠራ ነው የሚለው እዚህ ገጽ ላይ አያሳስበኝም ግን በግሌ ሚዛን ስገመግመው ለፃድቁ የቀረበላቸው ካሳ የሚበጃቸው አልመሰለኝም በምድር ተወስኖ ለሚኖር ሰው ለእግር እጦት ክንፍ ማካካሻ አይደለም። እግሩን ላጣ ሰው ፈጣን እና ብርቱ እግር ቢተካለት የበለጠ ይጠቅመዋል አባታችን ጸሎታቸው እና ድካማቸው ከምድር ጋራ የሚያቆራኛቸውን ሕዋስ አሳጣቸው የሰማዩን አስተዋጽኦዋቸውን የሰማዩ ጌታ ይገምግመው። በምድር ኀያላን መካከል በሚደረግ ሩጫ ግን እንደማይሳካላቸው ርግጠኛ ነኝ የጥንቱ ባለቅኔ ይኼ የገባው ይመስለኛል ጻድቁን በማስመልከት እንዲህ ብሎ ጻፈ
  . . .በገቢረ ፀሎት አዘረፈ
  ብሂሎ አውርድ በተሰቀለ ክንፈ
  ዘአኀዘ ሰኮና ገደፈ
  (ትርጉም )
  ፀሎትን ያዘወተረ (አብዝቶ የተማለለ )
  የተሰቀለ ክንፍ አወርዳለሁ ብሎ
  የያዘውን ተረከዝ ጣለ
  ባለቅኔው ፃድቁ የተሰቀለ ክንፍ ማውረዳቸውን እንኳ ርግጠኛ አይደለም የተሰቀለ ክንፍ አወርዳለሁ ብሎ” የሚለው መስመር ጥርጣሬን ይገልጣል። ተረከዛቸውን ለመጣላቸው ግን ርግጠኛ ነው።
  እንግዲህ በሰማዩ ላይ አለቅጥ ሲያተኩር ምድሩን የሚከዳ ምድሩም የምትከዳው ማኅበረሰብ ተክለሃይማኖታዊ ይባላል።
  ኅሩይ ወልደሥላሴ የተባሉ የቀዳማዊ ኀይለሥላሴ ባለሥልጣን በ 1910 ዓ .ም “የልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ” የሚል መጽሐፍ ጽፈው አሳትመዋል። መጽሐፉን የጻፉት በቀጥታ ለልጃቸው፤ በእጅ ዙር ደግሞ ልጃቸው አባል ለኾነበት ትውልድ ምክር እንዲኾን ነው። መጽሐፉ በተደጋጋሚ ታትሞ ተነቧል። በመጽሐፉ ውስጥ ከተመዘገቡት ምክሮች አንዱ “ልጄ ኾይ ሐሳብህም ሁሉ ከሞት በኋላ በወዲያኛው ዓለም ስለሚኾነው ስለ ነፍስህ ነገር ይኹን እንጂ በዚህ ዓለም በስጋህ ስለሚኾነው ነገር እጅግ አትጨነቅ” ይላል።
  ምክሩ የወጣው ከባሕታዊ አንደበት ቢኾን አይገርምም። መካሪው ግን አገር አስተዳዳሪ ባለሥልጣን ነው። የምክሩ ዓላማ ትውልዱ አገሩን ጥሎ እንዲመንን ለማድረግ ይኾን ? “በዚህ ዓለም በስጋህ ስለሚኾነው አትጨነቅ” ማለት “ልጄ ኾይ ጀዝባ ኹን፣ ቦዘኔ ኹን፣ ደደብ ኹን” ብሎ ከመምከር ጋራ በይዘት አንድ ነው። ልዩነቱ የመጀመርያው መንፈሳዊ አቀራረብ መያዙ ነው። ደግነቱ ልጅየው ፈቃደሥላሴ የአባቱን ምክር አልተቀበለም። ለስጋው ተጨንቆ ተምሮ አገሩ በፋሽስት ጣልያን ስትወረር ከውጭ ተመልሶ ለአገሩ ደረሰላት፣ ተዋጋላት፣ ሞተላት፤ ታሪክ ሠሪዎች ሰዎች እንጂ መላእክት አለመኾናቸውን አሳያት።
  የኅሩይ ምክር ይቀጥላል፤
  “ልጄ ኾይ ወደ ፊት እንዲህ ያለ መከራ ያገኘኛል ብለህ አትጨነቅ፤ ነገር ግን የሚኾነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና ያለ እርሱ ፈቃድ የሚመጣው አያገኝህም። የውስጥን የሚያውቅ እግዚአብሔር ካልፈረደብህ ንብረትህ እየሰፋ ጠላትህ እየጠፋ ይሄዳል እንጂ ምንም ክፉ ነገር አይመጣብህምና አትጨነቅ . . . በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመጣውን መከራ በጉልበቴ ወይም በእውቀቴ አስቀረዋለሁ ብሎ መጣጣር በመከራ ላይ መከራ ለመጨመር እንጂ ሌላ ትርፍ አይገኝበትም።”
  To be continued

  ReplyDelete
 63. Part 2
  አስቡት፤ የሰውን ጥረት በሙሉ ዋጋ የሚያሳጣ ምክር ነው። ሰው ነገ ወረርሽኝ ይመጣብኛል ብሎ ሲጨነቅ ክትባትን ይፈለስፋል። ድርቅ ያጠቃኛል ብሎ ሲጨነቅ ዛፍ ይተክላል፣ ወንዞችን ይንከባከባል። ጦር ይመጣብኛል ብሎ ሲጨነቅ አዳዲስ መሣርያዎችን ይፈለስፋል፣ ጠንካራ ኾኖ በተጠንቀቅ ይጠብቃል። የመሬት መንቀጥቀጥ ያጠቃኛል ብሎ ሲጨነቅ አደጋው ከመምጣቱ በፊት ጥቆማ የሚያቀርብ መሣርያ ይፈጥራል። ሥልጣኔ የጭንቀት ፍሬ ነው። ሰዎች በጉልበታቸውም ኾነ በእውቀታቸው መከራን ማስቀረት እንኳ ባይችሉ የመከራን ጉልበት መቀነስ እንደሚችሉ በታሪክ ዐይተናል። የእኛ ተክለሃይማኖታውያን የሚያቀርቡልን ግን “እሱ ካመጣው አይቀርልህም” የሚል ማዘናጊያ ነው። ለነገሩ አባቶቻችን በክንፍ ከወፎች ጋራ እንጂ በምድር ከሰዎች ጋራ ስላልኖሩ የምድሩን ጠባይ ሊያውቁት አይችሉም። ተዘናግተው አስቀደሙን።

  በአገራችን የተከሰቱ መከራዎች ከተፈጥሮ የፈለቁ በመኾናቸው መድኅናቸውም ተፈጥሯዊ ነው። ረኀብን እንውሰድ፦ ረኀብ ለአገራችን አምስተኛ ወቅት ማለት ነው። ክረምት፣ ጥቢ፣ በጋ እና በልግ አራት ወቅቶች ሲኾኑ ጠኔ አምስተኛ ወቅት ኾኖ ይከተላል። ዑደቱ ሳይቋረጥ ይመላለሳል። መከራ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ የሚያምን ሕዝብ መከራን አስቀድሞ መከላከል የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጻረር ይመስለዋል። እና ባንዱ ዘመን ድርቅ ይከሰታል - ድርቁ አስቀድሞ የቀንድ ከብቱን ይፈጃል። ሰዎች ረኀብ ሲጠናባቸው ፈረስ እና አህያ መብላት ይጀምራሉ። (ከሙሴ ትዕዛዝ የጨጓራ ትዕዛዝ ያይላል ) ባስ ሲልም ልጃቸውን የሚበሉ ወላጆች ይኖራሉ። ባጤ ምንሊክ ጊዜ አንዲት እናት ልጇን ከበላች በኋላ የሚከተለውን አንጉርጉሮ አይሉት ተረብ አወረደች።
  ዳግመኛ ለመውጣት በሌላ መንገድ
  ተመልሶ ገባ ልጅ በናቱ ሆድ

  እንዲህ ዐይነቱ መረን የለቀቀ መከራ እና እልቂት ሲደጋገም መሪዎች በመጀመርያ የሚወስዱት ርምጃ የክተት ፀሎት አዋጅ ነው። ተፈጥሮ ግን ለፀሎት ደንታ የላትም። “ታግለህ ጣል አለበለዚያ የራስህ ጉዳይ” በሚለው የተፈጥሮ ሕግ ውስጥ ኪራላይሶ ቦታ የለውም። ሰዎች በመቅደሳቸው በረንዳ ላይ መረፍረፋቸውን ይቀጥላሉ። ይኼኔ እኒያ የሕዝብ አለቆች የእግዜሩን መንገድ ለጊዜው ቸል ብለው ወደ ተፈጥሮ መንገድ ይዞራሉ። በተፈጥሮ መንገድ አንበሳ ሲርበው ወደ አደን እንጂ ወደ ቤተመቅደስ አይሄድም። ሮጥ ሮጥ ብሎ ሚዳቋን ሰብሮ ይበላል። የእኛ ነገሥታትም የአንበሳውን አርአያ ተከትለው በእምነት የማይመስላቸውን ሀብታም ጎሳ ይወሩና ከብቱን ነድተው ሲሳዩን ዘርፈው ይመለሳሉ። እነርሱ ሞአ አንበሳ ሲኾኑ በርእዮተ ዓለም የማይመስላቸውን ሕዝብ ሚዳቋ እንዲኾን ይፈርዱበታል። በዚህ ዐይነት ክፉ ቀንን በዝርፊያ ሲሳይ ይሻገሩታል። ኩነኔ አይፈሩም ? የሚል ምዕመን ይኖራል።

  ችግር አቆራምዶት ሌት እና ቀን አዝኖ
  ኩነኔስ መኖር ነው ከሰው በታች ኾኖ

  የሚለው የከበደ ሚካዔል ግጥም የቀውጢ ሰዓት አቋማቸውን የሚወክል ይመስለኛል።
  የዓለም ታሪክ የሚያስተምረን፣ ለስጋቸው የሚጨነቁ ሕዝቦች በልፅገው፣ ለነፍሳቸው ብቻ የሚጨነቁ ሕዝቦችን መግዛት እንደሚችሉ ነው። የዳርዊን አገር ከአቡነ ተክለሃይማኖት አገር በላይ ተሳክቶላታል። ዋናው ነገር ጠፈሩ የምናስበውን ያህል የዋህ አለመኾኑን ማወቅ ነው። ምድሪቱ ከፀሎታችን በላይ ላባችንን ከእንባችን ይልቅ ደማችንን ትጠይቀናለች።
  Xxxxxxxx
  ፍርዱን ለአንባቢያን

  ReplyDelete
 64. ayyaanaa ze wallaggaaApril 29, 2011 at 1:27 PM

  "በዚህ ዓለም በስጋህ ስለሚኾነው አትጨነቅ” ማለት “ልጄ ኾይ ጀዝባ ኹን፣ ቦዘኔ ኹን፣ ደደብ ኹን” ብሎ ከመምከር ጋራ በይዘት አንድ ነው;
  indih aynetu yezekete astesaseb be kidusan sim bikelid min yigermal! semayina midir kemirarakut yilk yenezih sewoch astesaseb fitsum ke Fetari hasab rikualina. be midir lay laykeru, zare leminagerut kentu neger hulu nege mels mestetachew layker,... yih hulu bekidusan mekeledina Kiristianoch BEFETARI lay yalachewn imnet lemeshersher mefchercheru,... inesu min serunna new! min lewetu!le iwuket inkua anbibew meredat yetesanachew min addis neger ametu! americana awuropa yemimeretewun ye gileseb 'haymanot' masfafat sira honena sigawiwun chigir lifetalin yidadal! hilinachewun shitew hodachewn yemollu menafikanina kitregnochachew tinant, zarem, negem be kidusan lay mekeledachewn aytewum.yih gin kiristianochin yitekimal inji aygodam. lebelete memeramer, lebelete menfesawi kinat,...yanesasal. silezzih, ye diablos serawitina kitregnochu yekiddusan telatoch menafikan iferu!!!!!!!!

  ReplyDelete
 65. ዳንኤል በርታ
  በቤተክርስቲያናችን ትውፊት፣ በ አይከኖቻችን በካህናት ላይ የሚቀልዱ፣ የሚያሾፉ ሁሉ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል።

  እኛ ለቤተክርስቲያን ቀናዒ ሆነን መገኘት አለብን!!!

  mntesnot2003@gmail.com

  ReplyDelete
 66. thanks dany for giving us indepth kdge

  ReplyDelete
 67. i have get your message very useful and one input for young Ethiopian generation to see our national unity and religious facts history and i am impressed while am reading your articles.
  Thank you, we have many brothers and sisters including you ,so if we have such opportunities we can win and became in good position with our historical heroes and religion.
  Egiziabeher melikamun waga yikifelih and kidist mariam tiketelih.

  ReplyDelete
 68. ecabod.ecabod@gmail.com
  ለጸኃፊ በእውቀቱም እግዚአብሔር ይስጥህ ጦማሪ ዲ/ን ዳንኤልም እግዚአብሔር ይስጥህ ደብዳቢዎቹም ደግሞ እግዚአብሔር ይስጣችሁ ምክንያቱም አዳዲስ እውቀት እንድናውቅ ምክንያት ሆናችሁናልና ነው ፡ አሁን እስቲ በእውቀቱ ባይወቅት (ባይጽፍ) ሰዎቹ በስሜት ፍቅራቸውን(ምንም እንኳን አቡነ ተ.ሃይማኖት ባይደግፉትም) በዱላ ባልገለጹት ነበር ይሄ ባይሆን ደግሞ ወሬው እንደ ኳስ ተጋግሎ ባልሰማነው ነበር ይህ ባይሆን ደግሞ ዳንኤል ባልጻፈ ነበር ስለዚህ ሃይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ስስ ብልት ጥንቃቄ የሚሻ ቢሆንም ፤ድብድብም አስፈላጊና መፍትሄ ባይሆንም የብዕር ጸብ ግን ዕውቀት ስለሚፈነጥቅ ጣፋጭ ነውና እባካችሁ በብእራችሁ ተደባደቡበት ፤ ጣቶቻችሁም እርባና ያለው ነገር በመጻፍ ይፈርጥሙልን !!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 69. ዲ ዳንኤል ስላካፈልከን ዕውቀት በጣም አመሰግናለሁ ግን ይህንን ያህል ተጨንቀህ ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት መልስ ሰጥተህ ለመጸፍ መብት ግን ልጓም ነፈግከው የመጻፍ መብት ከሀይማኖት ጋር ምን አገናኘው አቡነ ተክለ ሀይማኖት ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ በየጊዜው ማንም እየተነሳ የተለያየ ስም ሊሰጣቸው ማነው መብት የሰጠው ስለዚህ ማስተባበል አልነበረብህም ይህ እኮ በዘመናዊ መልኩ ማስተማር ሳይሆን መደፋፈር ይባላል ስለዚህ ተደፋፋሪን ተደፋፍረሃልና የቅዱሳንን አምላክ እግዚአብሔርን ይቅር በለኝ በል ብለህ መምከር የምታውቀው የቤተክርስቲያን እውቀት ለዋዛ ፈዛዛ፣ ለጨዋታ እና ለማንጓጠጫ አታድርገው የተማርከውንና ያወከውን ተጠቀምበት ብለህ መምከር እንጂ መጻፍ መብት ነው ግን…. እያሉ ማስተባበል ከስህተተኛ ጋር መተባበር ነውና ታረም ሌባን ሌባ ካላሉት….. ነው ነገሩ ቤተክርስቲያን የቆመችው በቅዱሳን ነውና ቅዱሳን ሲዘለፉ ችላ ማለት ለቤተክርስቲያን ዘብ ቆመናል ከምንል ከዚህ ትውልድ አይጠበቅም፡፡ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎችም የምትሏቸው አንዳንድ ነገሮች ይገርማሉ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ አባት ናቸው ብላችሁ ካላመናችሁ እሺ ከዚህም በላይ ብትሉ አልገረምም ግን የስም ኦርቶዶክሳውያን ልታውቁት የሚገባ ቅዱስነት በጭንቅ የሚገኝ ነው ቅዱሳንን ማክበር የቅዱሳንን ከብር ያሰጣል መበዝለፍና የቅዱሳንን ስራ ማጣጣል ከክርስቶሳውያን ወገን መሆን ስላልሆነ ኦርቶዶክሳዊ ካልሆናችሁ አይደንቀንም ከሆናችሁ ግን ከዚህ አሳፋሪ አስተሳሰባችሁ ውጡ፡፡

  ReplyDelete
 70. D.Daniel, it is well written. I enjoyed reading it. It is my first time to read an article from your blog. Egziabher Kale Hiwot Yasemalin.

  Keep it up.

  ReplyDelete
 71. ወይ ጉድ እዚህም ተደረሰ………. ጊዜ ገና ብዙ ነገር ያሳየናል፡፡ ግን ፈራሁ፡፡ ዳኒ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 72. ዳኒ ተው የእናቴ ልጅ ! ያዝ አድርገው። ሳታስበው ብዙዎችን ጠልፎ የጣለ ጠላት ወጥመዱን እየዘረጋልህ ነውና! በእግዚአብሔር ኃይል ካልሆነ በቀር በተፈጥሮ ሕግ ወደ ላይ የወጣ ነገር ወደ ታች መውረዱ አይቀሬ ነውና ይህንን «የመጻፍ መብት» ምናምን የሚባል ተረት ተረት ተውና እንደወድድንህ እስከመጨረሻው እንድንወድህ እግዚአብሔርም የክብርን አክሊል እንዲሰጥህ ለቅዱሳን ክብር እንደመጀመሪያህ ዘብ ቁም!

  ሠናይ

  ReplyDelete
 73. ማስተዋሉን ይስጠንMay 4, 2011 at 2:45 PM

  ዳኒ፡- በድፍረትም ይሁን ባለማወቅ ወንድሜ በዕውቀቱ የጻፈውን ጽሑፍ ምክንያት አድርገህ ስለ ጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሰፋ ያለ ትምሕርት ስለሰጠኸን እግዚአብሔር አምላክ ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፡፡ ነገር ግን እንደ ክርስቲያን እግዚአብሔር ያከበራቸው ቅዱሳን ሲዘለፉና ሲሰደቡ ‹‹የመጻፍ ነጻነት›› በሚል ምክንያት መለሳለስና ‹‹መከባበር›› ትክክል አይደለም ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህን ማለቴ በዕውቀቱንና መሰሎቹን ዱላ አንስተን እንደብድብ ማለቴ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፤ ከአምላካችን ይህን አልተማርንምና፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ስህተት ወይም ጥፋት የሚሠሩ ሰዎችን በእግዚአብሔር ቃል መገሰጽና ከስህተታቸው እንዲታረሙ መምከር እንጂ ‹‹መብታቸው›› ነው ማለት ሌሎችንም ማበረታታት እንዳይሆን እፈራለሁ፡፡ ዳኒ የቀደመዉን ቁርጠኛ ማንነትህን ዘወር ብለህ ተመልከት፡ ወደተለሳለሰ አቋም ዉስጥ እንዳትገባ አስተውል፡ ሁላችንንም በእምነታችን እስከ መጨረሻው አምላካችን ያጽናን፡፡
  በዕዉቀቱና መሰሎቹ፡ ‹‹በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።›› መዝ 30፡18 የሚለውን የእግዚአብሔር ዋል አስተዉሉ፡ ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 74. እኔ የምለው እግዜሩ ከመጀመሪያውኑ ለምን እግር አልፈጠረልንም ሌላው ዳኒ አቡኑ በተቅማጥ እንደሞቱ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደርሳቸው በተቅማጥ የሚሞቱ መንግስተ ሰማያትን እንደሚወርሱ ይጠቅሳል፡፡ለመሆኑ ተቅማጥ በየትኛው መመዘኛ እንደ ክርስቶስ ደም ይቆጠራል; ለምንስ እነዚህን የገድሉን እውነታዎች ዘለልካቸው በመጽሀፍ ቅዱስ የምታምን ከሆነ ደሙ እንጂ ሌላ ነገር አልተባለ

  ReplyDelete
 75. please dawit tell the truth and know the truth!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 76. እንዴ!!! ዳንኤል??? ምንድነው ነገሩ? ቁርጠኛ አቋም የሚጠይቅ ነገር ላይ ራሳችንን መግለጽ ያለብን ይመስለኛል፡፡ አንተ ደግሞ አስተማሪያችን ነህ፡፡ እባክህን ዳንኤል ስለ እግዚአብሔር ብለህ አታሳቀን ? “ምን በቀደደው ሽንቁር….. ምን ይገባበታል” የሚባል አባባል አለ፡፡ ዳዊት የተባለ አስተያየት ሰጪ የሚለውስ ምንድነው ? በበኩሌ አንዳንዴ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ለሚሰጡ አስተያየቶችም ጣልቃ እየገባህ መልስ መስጠት ያለብህ ይመስለኛል፡፡ የቆምክለትን ዓላማ ለማሳካት ስትል እና እኛንም ግራ ከመጋባት ለመታደግ፡፡
  በመጨረሻ እግዜአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 77. A gracious reply. I am not an Orthodox myself and I may not agree with all the ideas presented here but Daniel is a very good model for how Christians should deal with ideas opposing their views.

  ReplyDelete
 78. ለ"ዳዊት" ወንድሜ፦ ስለ"ተቅማጥ" ከዚህ በፊት ከወገኖችህ ብዙ ነገር ሰምቻለው፦ እኔ ግን ገድሉ በእጄ ስለሌለ ስላልነበቡት ነገር እስተያየት አልሰጥም፡

  "በመጽሀፍ ቅዱስ የምታምን ከሆነ ደሙ እንጂ ሌላ ነገር አልተባለም" ላልከው ግን እኔ የማምንበት መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ የሚሉ ብዙ ቃላት አሉት፦

  "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።"

  "ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።"

  "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።"
  "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።" ...

  From Canada

  ReplyDelete
 79. ባለጌ
  የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ካስተማሩኝ መምህራን ውስጥ በተለየ መልኩ ከማልረሳቸው መምህራን የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአዲስ ኪዳን መምህር የሆኑት ደጉዓለም ካሳ አንዱ ናቸው :: ክፍል ውስጥ ለማስተማር ቀድመው ነው የሚገኙት ማርፈድ ለተማሪም ሆነ ለአስተማሪ ተገቢ አይደለም የሚል አቋም አላቸው :: አንድ ቀን ወደ ክፍል መግባት ከሚገባቸው ሰዓት አስር ደቂቃ ዘግይተው መጡ ሁላችንም ገርሞናል... ይሁንና ማንም ያንጎራጎረ አልነበረም : ደግሞም አስር ደቂቃ ምንም አይደል:: መምህሩ ይቅርታ ጠየቁ በማስከተልም “ባለጌ” ይዞኝ ነው የዘገየሁት ቤተ ክርቲያናችን “የራሷ ባልሆኑ ባለጌዎች” ስለተሞላች ስለቤተ ክርስቲያን ስለ ወንጌል ሲነግሯቸው አይሰሙም ብለው መደበኛ ትምህርቱን ቀጠሉ ንግግራቸው ሊገባኝ ስላልቻለ ጥያቄ አለኝ አልኩ ፈሊጥ ተጠቅመው ማስተማር የዘወትር ችሎታቸው የሆነው መ/ር ደጉ መቸ ትምህርቱ ተጀመረና ጥያቄ ትላለህ አሉኝ ቤተ ክርስቲያናችን “የራሷ ባልሆኑ ባለጌዎች” ስለተሞላች ሲሉ ስለሰማሁ የራሷ የሆኑ ባለጌ ልጅዎች አሏት ወይ ለማለት ነው አልኩ ፈገግ አሉና ለመሆኑ ባለጌ ማለት ምን ማለትነው ? ብለው ተማሪዉን ጠየቁ ከጎኔ ተቀምጠው የነበሩት አንድ አባት እንዴ መምህር ባለጌማ ባለጌ ነው ሲሉ ተማሪው ሳቁን መቆጣጠር አልቻለም ነበር :: መ/ር ደጉ ሌሎቻችሁ ሞክሩ አሉ ጥሩ ሥነ ምግባር የሌለው መጥፎ ጋጠወጥ ወዘተ.....በማለት ሁሉም የእውቀቱን ሞከረ መ/ር ደጉ ግን ስለ ቋንቋ አመጣጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንሽ ካብራሩ በኋላ በቀድሞ ዘመን ይሰጥ የነበረውን ማዕረግ መነሻ አደረጉ የደብረ ሊባኖስ አስተዳዳሪ እጨጌ እንደሚባሉ የንጉሡ ባለቤት እቴጌ እንደሆኑና ለወቅቱ መንግሥት ቅርብ ነኝ የሚል ደግሞ ባለጌ እንደሚባል “ባለጌ “ማለት ባለ ጊዜ እንደሆነ ባለጊዜ /ባለጌ / እንደፈለገ እንደሚናገር ትልቁን የሚያዋርድ አቅሙን የማያውቅ እንደሆነና እጨጌ ፡እቴጌ: ባለጌ ወዘተ... ይባል እንደነበር ነገሩን :: ዛሬም ሃይማኖት የሌላቸው የሃይማኖት መሪዎች /ባለጊዜዎች /ስለቤተ ክርስቲያን ደንታ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን ወኪሎች /ባለጊዜዎች/ መብዛታቸው ለምን ይሆን ? አርባ ዓመት የቤቴ ክርስቲያን ትምህርት ተምረው በወር አርባ ብር የተነፈጋቸው ዘመናቸውን ሙሉ መምህራንን በማፍራት ያሉ የአብነት መምህራን አስታዋሽ አጥተው ምንም የቤተ ክርቲያን ትምህርት የሌላቸው ቀድሰው የማያቆርቡ የቤተ ክርስቲያኗን ቢሮ እንጅ በመቅደሱ በር የማይታዩ አስቀድሰው የማያውቁ ማስተማር የማይችሉ አንድ ቀን ተስቷቸው ጹመው የማያውቁ ፍጹም መንፈሳዊ የሚባል ነገር የማይታይባቸው ዓለማውያን /ባለጊዜዎች/ባለጌዎች/ የራሳቸውን ሥጋዊ ኑሮ መገንባት አንሷቸው ቤተ ክርስቲያኗን ለማጥፋት መሰለፍ ምን ይሉታል ? በታሪክ በባለጌ የተሰሩ በርካታ ጥፋቶች ቢኖሩም የተመዘገበ ጥቂት በጎ ነገር የለም :: ባለጌ /ባለጊዜ ለወቅቱ ባለሥልጣን ቅርብ በመሆኑ ብቻ እንደፈለገ ሊናገር ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑን ጨለማ ሊል ይችላል መልካም ስም ስለሌለው መልካም ስም ባለበት መቆም አይችልምና መልካም የሆነውን ለማጥፋት የማይፈነቅለው ደንጋይ የለም ባለጌ የተመካበትን ባለስልጣን ጭምር ያሰድባል :: እስኪ የሽማግሌ ምርቃት ብየ ልፈጽም : ከቶሎ አኩራፊ ከበሽታ ተላላፊ ከወዳጅ ሸረኛ ከጓድኛ ምቀኛ ከልጅ አመዳም ከጥጃ ቀንዳም ከቄስ ውሸታም ከዳገት ሩጫ ከአህያ ርግጫ ከባለጌ ጡጫ ይሰውረን አሜንSee More
  By: Fasil Asres
  .

  ReplyDelete
 80. ዲ/ን ዳኒ እግዚኣብሄር ያክብርልን
  ብቅዱሳን ኣባቶቻቸን ላይ የስድብ ቃል የሚሰነዝር እግዚኣብሄር የእጁን እንደሚሰጠው ኣንጠራጠርም። እግዚኣብሄር የመረጣቸውን መክሰስ እግዚኣብሄር ያጸደቀውን መኮነን የሚቻለው የለምና። ሮሜ 8፡33 ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ።

  ReplyDelete
 81. It is an excellent piece of writing which treated the issue quite broadly. Well done, Deacon!

  ReplyDelete
 82. በእውቀቱ በጣም መሰረታዊ ሃሳብ ነው ያነሳው:: እንደኔ ሃሳብ ትልቅ የመነጋገሪያ ርእስ መሆን የነበረበት ክንፍና እግር አልነበረም:: በእርግጥ እርሱም ትልቅ መነጋገሪያ ነው – ሆኖም ግን የበውቀቱ ትኩረት ያ አልነበረም:: የኛ አገር ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግርና እኛ ችግሩን የምንመለከትበት መነጽር እግር አልባ ባለክንፍ ሳይሆን እግርም ክንፍም አልባ ያስብለናል:: አመክንዮአዊነት የጎደለው ክርክር ትተን እውነትን መጋፈጥ መጀመር አለብን:: የማይጨበጥ ታሪክ እያወራን በችግር ቀንበር ውስጥ እየማቀቅንና በእርጥባን መኖር ይበቃናል:: በ እውቀቱ የጠቀሰው ባለቅኔ ምናልባት ከዘመናት በፊት ነው ያንን የተናገረው እኛ ዛሬ በሃሳብ መሞገት ሲያቅተን ለጡጫ እንጋበዛለን:: በቃን ከእንቅልፍ እንንቃ:: ተረት ተረት እናቁም::

  ReplyDelete
 83. ማስተዋል በሌላ መንገድ መቃኘትን ሊሻ ይችላል:: ነገር ግን የብዙሀኑን እምነት ወይንም ባህል መሰረት አድርጎ ኪነ ጥበብን ለማሳደግ በሚል አንድምታ ባህልን ወይንም እምነትን መንቋሸሽ ግን አለማስተዋል ነው:: በውነቱ በእውቀቱ በዚህ ጊዜ እንዲህ አይነት ፅሁፍ መፃፉ፤ የሚየያዳምጠውን ሰውና የራሱን ስራ እያስተዋለ ይሰራል ለማለት ይከብደኛል፤ የስነ ፅሁፍ ባህላችንንም አስፓልት ማሻገሩንም እጠራጠራለሁ:: ባፃፃፍም በይዘቱም አሉታዊ ተፅእኖ የሚያመጣ፤ አላዋቂውን ምእመን ገደል የሚያስገባ ፣ መናፍቃንን የሚያበረታተታ ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ ተጨማሪ ስራ የሚያበዛ::

  ነገ ደግሞ በስነ ፅሁፍ ስም ከዚህ የበለጠ ጉድ እናይ ይሆናል:: ለማንኛውም ለሁላችን ማስተዋሉን ይስጠን::

  ReplyDelete
 84. ዳኒ እግዚአብሄር ይባርክህ አባአቶች ስምተው ዝም ሲሉ አንተ መናገርህ ! አምላከ ቅዱሳአ ጸጋውን ያብዛልክ ውዳአሴ ከንቱ አያርግብህ

  ReplyDelete
 85. ወንድማችን ኮራሁብህ ይሂነዉ መልስ ጌታይጠብቅህ

  ReplyDelete
 86. ፡የጻድቁ፡አባታችን፡የተክለሀይማኖት፡አምላክ፡እግዚአብሔር1ይጠብቅህ፡ያገልግሎት፡ዘመንህን፡ያስፋልህ፡ቃለዕይወት፡ያሰማልን።

  ReplyDelete
 87. No, Birhanu Tesfaye Said...

  May GOD keep all of us. both Dn. Daniel and Bewketu are my precious people. But when I heard 'such' thing from Bewketu, I felt a black whole on my heart. Now, My other Precious, Dn. Daniel, felt that whole on my heart. Thank you GOD.

  What is more pleasant than seeing two precious ppl love each other... especially in Ethiopia

  ReplyDelete
 88. Kale Hiwote Yasemalin!
  Ameha Giyorgis
  DC Area

  ReplyDelete
 89. i am really happy with yoour answer.
  God bless you
  duskem from Mak entertainment

  ReplyDelete
 90. I will pray and work and then pray; and remember Ethiopia, you (Dn Daniel) and Bewketu on my prayer. Egziabher Ethiopian Yibark!

  ReplyDelete
 91. ሰው ሀሳብ አያምጣ ማለት አይደለም ሀሳቡ ግን አግባብ ባለው መንገድ መሆን አለበት እንጅ፡፡በእውቀቱ ይሄን ባይጽፍ ኖሮ የአቡነ ተክለ ኃይማኖትን ታሪክ ከዚህ በፊት የማያውቅ ሰው አሁንም አያውቅም ነበረ፤ለእኔና እኔን መሰሎች ስለዚህ መጻፉ አግባብ ነው ባይ ነኝ፡፡አንተም የሰጠኸው ምላሽ ለእርሱ ከበቂ በለይ ነው ለሌሎችም ቢሆን ጥሩ ነው እናም እንደ በእውቀቱ ያሉትን ተቺዎች ያብዛልን ቤት ለቤት ከሚያነሾካሹኩ ይልቅ ምክንያቱም ብዙ የማናውቀውን ወይም የምንጠራጠርበትን ነገር እንድናውቅ ግልፅ ያደርገልናል፡፡አንተ እንዳልከው የእነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እነዲሁም ሌሎች አባቶች የፃፉአቸው መጻህፍት አይደሉም እንዴ ሁሌ ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡት በእርግጥ መፅሃፍ ቅዱስ እንዳለ ሆኖ፡፡እነዲህ አይነቱ ትችት ይቀጥል፡፡እግዚአብሔር ኢትዩጵያን ይባርክ፡፡
  አሜን!
  ሰው ሀሳብ አያምጣ ማለት አይደለም ሀሳቡ ግን አግባብ ባለው መንገድ መሆን አለበት እንጅ፡፡በእውቀቱ ይሄን ባይጽፍ ኖሮ የአቡነ ተክለ ኃይማኖትን ታሪክ ከዚህ በፊት የማያውቅ ሰው አሁንም አያውቅም ነበረ፤አኔንና እኔን መሰሎች ስለዚህ መጻፉ አግባብ ነው ባይ ነኝ፡፡አንተም የሰጠኸው ምላሽ ለእርሱ ከበቂ በለይ ነው ለሌሎችም ቢሆን ጥሩ ነው እናም እንደ በእውቀቱ ያሉትን ተቺዎች ያብዛልን ቤት ለቤት ከሚያነሾካሹኩ ይልቅ ምክንያቱም ብዙ የማናውቀውን ወይም የምንጠራጠርበትን ነገር ግልፅ ያደርገልናል፡፡አንተ እንዳልከው የእነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እነዲሁም ሌሎች አባቶች የፃፉአቸው መጻህፍት አይደሉም እንዴ ሁሌ ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡት በእርግጥ መፅሃፍ ቅዱስ እንዳለ ሆኖ፡፡እነዲህ አይነቱ ትችት ይቀጥል፡፡እግዚአብሔር ኢትዩጵያን ይባርክ፡፡
  አሜን!

  ReplyDelete
 92. It seems that--at least for me, Both Daniel and Bewketu are right. In my way of thinking, Schrödinger's cat theory can be applied here. Differently expressed, one of them can be True at the same time even if they have had different opinions. So, if God gave us the freedom to write and argue, then nobody can take out that either through sword or fire. After all, freedom is a default setting on the entire DNA of mankind!

  Tena Tabia Folk
  From Bahirdar

  ReplyDelete
 93. @Tena , Different opinions like this one will never be the same. It may be work for modern physics and it will be easy if we refer our bible. The answer of Daniel is with love, so that people like Beawketu will understand and correct themselves. Otherwise if we always respond ignorance of others with hate, things will get uncontrolled.

  N.W

  ReplyDelete
 94. ግን በእውቀቱ ስለዚህ ጉዳይ ለመፃፍ ምን አነሳሳው? መከበር በከንፈር ብለዋል አባቶች ሲተርቱ፣ አድናቂህ ብሆንም እንኳን በሃይማኖት ውስጥ ባትገባ ካልጠፋ የሚፃፍ ስለ ተክልዬ? እግዚኣብሄር የመረጣቸውን መክሰስ እግዚኣብሄር ያጸደቀውን መኮነን የሚቻለው የለምና። በርግጥ ሰዎች ስለሆንን እንሳሳታለን ለሌላ ግዜ ለበውቀና ለመሰሎቹ ትምህርት ነው እና መወቃቀሱ መልካም ነው እላለሁ፡፡ በርግጥ የአንድ ሰው ነፃነቱ ቢጠበቅም ከበእውቀቱ ይህንን አንጠብቅም፡፡ እና የኛ መምህራኖች ሳይሆኑ የሚያጠፉት ዕኛ ተማሪዎች(ምእመናን) በጣም ከፈጣሪ በላይ ከምንማረው ቃል በላይ አግዝፈን የምናየውና የምንከተለው እነሱን ስለሆነ ውድቀታቸውና ስህተታቸው ይፈጥናል እንደ በጋ ሻው

  ReplyDelete
 95. ende daniel kibret yalu sewoch sileseten Egziabher yimesgen!

  ReplyDelete
 96. Ende Bewketu Ayinet Mehayimochin betsihufh ashemakiln."Civic Orthodox" Right naming.GOD Bless You Dani.Long live to you.Minew kante sitota tinish Bikafilegn.Enem Lela syame Esetew neber.

  ReplyDelete
 97. D/Daniel ejig kelib yehone misganayen laqerbelih ewedalehu. Egiziabeher betsega lay tsega yabzalih. Betam dink yehone tsehuf new. endenezih yalu betam tilket yalachew kebizu matakesha yemitetsefachewlin merejawoch betetenakere melku bemetsehaf melku eyazagajeh betakerbilin lehaymanotachinim letarikim tekami newu elalehu.yihenin lemadireg Egiziabiher yirdah!

  ReplyDelete
 98. Bewketu sew yesakelet eyemeselew sew tirsun yeminekisbetin tsuhuf eyetsafe new. anid derasi ene endemimeslegn kemetsfu befit mayet yalebey yemitsefeketin maheberedeb meselegn. Bewketu gin yihe "ewket" teftot yihun awqo maheberesebu restotal. yedirset hidetum sewun masak enju lehager mebtehe lehizib yemitekim kumneger metsafun zengitota.

  ReplyDelete
 99. መልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬ ያንን የመሰለ ኮኩሐ ሃይማኖት የተሰኘ መጽሐፍ እንዲጽፉ ምክንያት የሆናቸው አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ካቶሊካዊ ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጻፈው ጽሑፍ ነው፡፡ እርሳቸው ባረፉ ጊዜ ይኼው ሰው እያለቀሰ መጣ አሉ፡፡ ዘመዶቻቸው ተናድደው «ደግሞ እንዴት ታለቅሳለህ?» ብለው ቢጠይቁት «እንኳንም ጻፍኩ፤ እኔ ባልጽፍ እኒህን የመሰሉ ሊቅ ገንዛችሁ ልትቀብሯቸው ነበርኮ፡፡ እኔ በመጻፌ እርሳቸውም ጻፉ፤ ምነዉ ደጋግሜ በጻፍኲ ኖሮ» አለ ይባላል፡፡
  It is very impressive history you quote.Melake Berehan Admassu's books reveal his great knowlege.He was one of the best scholars or 'lique'in recent times for our church.By the way you were taking about the book 'Medlote Amin'not 'Kokha Haimanot'.One of the causes to wrote 'kokha Haimanot'was the book of Zemenfes Abreha 'Tegsats ena Mekir'.
  GOD bless you.

  ReplyDelete
 100. የስድብ መብት አለንዴ ዳኒ? ልጁ የመጻፍ ነጻነት ቢኖረው የሌላውን መብት ነክቶ መሆን የለበትም። ይህ በግልጽ ሊነገረው ይገባል። የሱ ሀሳብ ከነፓስተሮች ስብከት በምን ተለይቶ ነው ዕውቅና ሊሰጠው የሚገባ። በእንጭጩ ካልተገታ ሃይማኖታችን ያልተማሩ ጸሐፊዎች መዘባበቻ መሆኟ ይቀጥላል። ሊያስከብሩ ይገቡ የነበሩ አባቶች ግንባር ቀደም ባይሆኑም ምእመኑ ግን ሃይማኖቱን በሚችለው ሁሉ የማስከበር መብትም ግዴታም አደራም አለበት እላለሁ።

  ReplyDelete
 101. daney God bless you...........pls whould you tell me about others holy ethiopian fathers..ehh thanks!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 102. HI Daniel,

  I read your piece all the way through, it is nice one. I have one question though: At one point, you mentioned that Tekle Haimanot is given a wing because he lost his foot while praying and at another point, you said that he was given wing before losing his foot. For me it sounds a paradox.

  ReplyDelete
 103. ዮስያስ ተፈራ
  ሰላም ላንተ ይሁን
  ዲያቆን ዳንኤል በመጀመሪያ ላንተ ያለኚን አደናቆትና አክብሮት ልገልፅልቅ አፈልጋለው:: በመቀጠል በዚሀ ባነበብኩት ጽሑፊክ ተገርምያለው ያቀረብከውም ማሰረጃ ደስ የሚል አና አስተማሪም ጭምር ነው:: የአባታቸነ አቡነ ትከለሃይማኖት ማንነት በሚገባ ተንትነክ አስቅምተከዋለ:: በመሆኑም አዚህ ጋር በውቀቱን ብቻ ሳይሆን ሌላ ጭፍንተኛ አሰተሳሰብ ያላቸውንም የሚያስተምር ነው ባይ ነኝ:: አኔ የበውቀቱ ሰዩም አድናቂና የስራው ወዳጅ ነኝ: እዛጋር ያቀረበው ጽሑፍ በኒ ውድቅ ቢሆንም ሌላ ስራወቹ ከኔጋር ሁሊም አብረው ይኖራሉ ሌላው ነገር ከንደዚህ ከተሳሳተ እሳቤ አሱም እንደሚመለሰ አልጠራጠርም:: ብዙ ስላስተማርከን እናመሰግናለን ::
  ዳንአል አሁንም እግዚአብሔር ድብቁን ዕይታክን ያብዛልክ::

  ReplyDelete
 104. በጣም ተምሬበታለሁ እግዚአብሄር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል
  ጥዑመልሳን ዘምድረከብድ

  ReplyDelete
 105. Daniel tesfaye
  from ledeta sunday school A.A
  Diakon Arter daniel kibret thank you for your
  writing this postive answer.i see your different Type of text in different time all are very important to all christian follower and any body who is posetiv thinker.

  ReplyDelete
 106. አቡነ ተክለ ሃይማኖት «እግር አልባ ባለ ክንፍ» ሳይሆኑ «ክንፍ ያለው ባለ እግር ናቸው»

  ReplyDelete
 107. fore Daneal i appreciate u. fore Beweketu be care full.

  ReplyDelete
 108. Dn daniel, may god bless you. I hope the likes of bewketu can learn a lot from the article and the comments made.

  ReplyDelete
 109. Dear Daniel

  would you mind clearing out the controversy, written on the ELEVENTH paragraph under title "ABUNE TEKLEHAIMANOT MANE NACHEWE ?" and SECOND paragraph under title "EGIRENA KINFE" ?

  Both paragraphs talk about on how the holy father came to loose his leg differently.

  Hope you understand the relevance of this matter and and polish the information you passed once again.

  regards,

  ReplyDelete
 110. "...አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሦስት ሥርዓተ ትምህርቶች በተቃኘው የሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት ቤት የኖሩ ናቸው፡፡ በትምህርት፣ በሥራ እና በምንኩስና፡፡ ሥራ ለዓለማውያን ብቻ ሳይሆን ለመነኮሳትም የግድ አስፈላጊ መሆኑን የተማሩም ያስተማሩም ናቸው፡፡ በተጓዙባቸው ቦታዎች ሁሉ ሦስቱንም ሲያከናውኑ ነው የኖሩት፡፡ በመጨረሻም ወደ ደብረ አስቦ ሲገቡ ገዳማዊው ሥርዓታቸው ትምህርትን፣ ምንኩስናን እና ሥራን ያዋሐደ ነበር፡፡
  እናም «ተክለ ሃይማኖታዊ» ማለት «እየሠራ የሚጸልይ፣ እጸለየ የሚሠራ» ማለት እንጂ በሰማዩ ላይ ብቻ ያለ ቅጥ እያንጋጠጡ ምድራዊ ሕይወትን መዘንጋት እና ለድህነት መዳረግ ማለት አይደለም፡፡..." !!!

  ReplyDelete
 111. D/n Daniel GOD IS GREAT Ortodox derom, zenderom, cheger getmewatal, eyegetemuat new wedefitem yegetmuatal yehonal''GOD KNOWS'',kezh yekefa cheger endaygetmenem YEKEDUSAN ( ABUNE TEKLE HAYMANOT....) telot, melga ena bereket ayleyen ''GOD IS GREAT''

  ReplyDelete
 112. Dear D/n Daniel,
  Kindly note that I have seen this article for the second times and I have got many things, really this is good writing. But please be wise! wise! and wise!
  Keep it up

  ReplyDelete
 113. yeteret metsehafun tetachuh, wanawe mtsehaf lay tekuret aderegu... metsehaf yetechekemech aheya athunu.......
  ......."እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ............

  ReplyDelete
 114. ቃለህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
 115. Dn. Daniel
  I heard about Bewketu article and what happen to him he get what he deserve not mean bit by others but this kinds knowledge form u we get a lot from u thank u .u mention an example if people write (wrong) God raise like to correct them .enquan tsafic Bewketu.
  Do u read 444 fiction what do u feel/understand?

  ReplyDelete
 116. lesson number one ,when one gets the opportunity to be a figure in a society he should think twice .but i do not know why most do not at all .

  ReplyDelete
 117. am very very happy to read these because for a long time this has been my top question. "tekelehaymnotawinet" this phrase was used by many individuals whom doesn't follow our religion & i say the answer provided here will defiantly give them the idea of what profit meant to us "orthodoxes"

  ReplyDelete
 118. why is it allways we wont belive what we want? any one can say anything unless he didnt do things which heart peopel. i like ur idea and i want to listen the respond of bewketu as wel. peace

  ReplyDelete
 119. Agendaw beta astemeri silehone ketlubet.kaltefeche essat afetermna .giffabet egziabher kante gare yihun d/n daniel

  ReplyDelete
 120. i used to be a strong advocate of the Ethiopian orthodox church as a consensus builder forthe modern ethiopia polity.i am passionate about its history and tradition.
  1. coming to its dogma ,doctrines and religious systems -fasting,kidassie timket, kirbuan etc. i believe it is rather the most biblical and the most godlyway if it is properly understood what it entails.in this regard ,i would like you to preach in a way that is understandable to a 'miemen' or if not possible why is that ? why is for example the orthodox teachers do not tell the 'miemen' about mistere silassie and others in a plain langauge .in this regard i strongly believe that what the teachers know and what the miemen is being told has great difference. are you hiding the key of knowledge like the pharasies ? please i want to hear from you about these things .

  2. having read gadils of dekike estifanos recently ,these days i have become rather suspicious about the ethiopia orthodox church history that is why i said 'i used to' in above.waht is your view on this 14 th century ethiopia orthodox event. some people claim that the EOC TRADITION has become more europinaized from the 14 th century onwarsd. what is your view on this .
  my email- haftamu2012@yahoo.com
  thank you very much for your high moral ground and for your good articles.

  ReplyDelete
 121. ይህን የመሰለ ውብ ትንታኔ እጅግ ዘግይቼ በማንበቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ!..እስካሁን በውቀቱን ይቅር አላልኩትን ነበር፤ እነሆ አሁን ይቅር አልኩት!

  ReplyDelete
 122. እባከህ ዳንኤል!ጥሩ የመፃፍ ችሎታ ቢኖርህም እንኳ ጥሩ ስለፃፍክ እውነታውን ያንተ ጥሩ የመፃፍ ችሎታ አይቀይረውም።።እውነታውም የእነ አቡነ ተክለኃይማኖት የእውነት ታሪክ ሳይሆን የደብተራ(ዎች) ፈጠራ መሆኑ ነው፡፡ሰይጣን የክርስቶስ ወንጌል እንዲሸፈን፣እንዲቀበር የፈጠራቸው ምርጥ ዶሴዎች ናቸው (እነ ገድለ-ተክለኃይማኖት)!!ግን ክርስቶስ ምንግዜም አቸናፊ ነው፡፡ወንጌሉም አሁን እያየነው እንዳለነው የበለጠ ተቀባይ እየሆነ መሄዱ አይቀርም፡፡ተረታ ተረቶቹም ተራኪዎቹም አያቸንፉም፡፡

  ReplyDelete
 123. Dear Dn Daniel.

  I have got a simple but very important question. Why did Our Lord Jesus Christ died and resurrected? . . .you don't have to reply to the question . . .just try to understand the essence and significance of the Death and the Resurrection personally to you. . .if you do, I assure you that you will never be the same and be freed from the world of fables. I also invite most of you who posted comments here to do the same.

  GOD BLESS U ALL

  ReplyDelete
 124. wed memher daniel :-le bal ewketu tiru ewket selestehw egzihaber amlak yibarkh tebarek anbbew betam tenadje neber gen yanten mels say weste betam tedestal ahunem egzihaber chemro yibarkh selamun hulu emegnlhalew.

  ReplyDelete
 125. egzihabher yestelengn yalawekuten asawekegn astemarekegn
  egzihabher ewketehen ena edmehen yabezaleh

  ReplyDelete
 126. Decon Daniel,
  It is a wonderful write up. Thank you very much for your effort and civilized response. This will give all not only Bewuketu a very useful lesson about "Abune Tekelhaimanot". God bless you. I know Bewuketu's ambition and intention to address his concern about the backward growth of our people and country as a whole. I know him very well that he has no intention of rising against "Orthodox". In God's will I will try to write article about his paper soon.
  Bewuketu read DN. Daniel's response for your benefit and I will talk to you soon.

  Abebaw

  ReplyDelete
 127. MEMHRACN DANIEL KBERT KALEHIWT YASEMALEN .... U R LOOK LIE OUR FOR FATHER APOLOGETIC ...BE EWKETU .. KE TSAFEW ... SENFE ENDHON ...WSUN SEW ENDHON ... BUZU YE MAYAKEW NGER ENDALEW ... LEZIHU LEMAWEKE ENDITGA YERDAWAL BEY ASBALEHUNG ....

  ReplyDelete
 128. i liked the article but why dont you say somehing about the real issue that bewketu tried to raise or as you said"«ማኔያዊ» bemilew lay.

  ReplyDelete
 129. Betegiorgis@gmail.comAugust 16, 2014 at 7:34 PM

  እግዚአብሄር ይጠብቅልን ወንድማችን ዳቆን ዳንኤል ለእኛም የጻድቁ ምልጃና በረከት ይርዳን ማሥተዋሉን ያድለን

  ReplyDelete
 130. እኔ እንኳን አስተያየት ለመስጠት ሳይሆን ጥያቄ ልጠይቅ ነው። በተለያዩ የውጭ አገር ፀሐፊዎች ዘንድ የጠለምትን ይሁዲዎች (ፈላሾች) ወደ ኦርቶዶግስ ክርስትና እንዳስገቡ ተተርኳል። ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት እንደተረኩት ከሆነ ደግሞ በደቡብ፣ በሸዋ፣ በወሎና በደብረዳሞ እንደተማሩና እንደሰበኩነው። በጠለምት ውስጥ ያደረጉት እንቅስቃሴ የሚታወቅ ከሆነ ቢብራራ መልካም ነው። ምክንይሳቱም ታሪክ እንዳይዛባ መጠንቀቅ ይኖርብናል።

  ReplyDelete