Thursday, April 14, 2011

ቡና ያለ ሀገሩ


ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝቡን ማኅበራዊ ሕይወት ካቆሙት ነገሮች አንዱ የቡናው ሥርዓት ነው፡፡ ምንም እንኳን
ቡና ጥሩ ነበር ለማግኛ ወዳጅ
ቁርሱ የሰው ሥጋ መሆኑ ነው እንጂ
የሚሉ የግድግዳ ጥቅሶች የሚነቅፉት ነገር ቢኖራቸውም ቡና ባይኖር ኖሮ ግን እናቶቻችን የመወያያ፣ የመጠያየቂያ እና ጭንቀትን የመካፈያ መንገድ አይኖራቸውም ነበር፡፡
 በዚህም የተነሣ በባሕሉ ቡና አፍልቶ የሚጠራ ይመሰገናል፣ ይወደዳል፣ ይመረቃል፡፡ አንዳንዴም መንደሩ በሙሉ በተራ ቡና ያፈላል፡፡ ቡና ድኻ እና ሀብታም አይልምና፡፡
እንዲያውም «ሴቶች ቡና ላይ ወንዶች ጠጅ ቤት ተገናኝተው የወሰኑትን ማንም አይፈታውም» ይባላል፡፡ በቀበሌ ስብሰባ፣ በቴሌቭዥን ንግግር፣ በኮንፈረንስ እና በዐውደ ጥናት የተለፈፈውን ሴቶቹ ቡና ላይ ወን ዶቹም ጠጅ ቤት ሰብሰብ ብለው «ተወው እባክህ፣ተይው እባክሽ» ከተባባሉበት ቆለፉት ማለት ነው፡፡
አንድ ወዳጄ እንዲያውም ኤይድስን ለመዋጋት ለሻማ፣ ለቲሸርት እና ለቆብ ይህንን ሁሉ ገንዘብ ከማ ዋጣት ለእናቶቻችን የቡና መጠጫ ጥቂት ቢሰጧቸው ኖሮ ከዐውደ ጥናቱ በላይ ውጤት ያለው ውይይት ይደረግ ነበር ብሎኛል፡፡
እዚህ እኔ ያለሁበት ዚምባብዌ ግን ቡና ያለ ሀገሩ መጣና ጉድ ፈላበት፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ኢትዮጵ ያዊት እናት በባልዋ ሥራ ምክንያት ሐራሬ ትመጣለች፡፡ የሐራሬ ቤቶችን ብታዩዋቸው ያስቀኗችኋል፡፡ የአንዱ ሰው ግቢ በትንሹ አምስት ካሬ ሜትር ቦታ ነው፡፡ አቤት ይሄ ግቢ እኛ ሀገር ቢገኝ ስንት ኮንዶሚኒየም ይሠራበት ነበር? አልኩና ቀናሁ፡፡ (ኦፍ ዘሪከርድ እንነጋገርና አዲስ አበባ ውስጥ ባዶ ቦታ ያለው ብቻ ሳይሆን ፀጉር አልባ የሆነ ባዶ ራስ (ራሰ በራ) ሰውም ይሠጋል አሉ፡፡ ጭንቅላቱን በሊዝ እንዳይመሩበት፡፡ እዚህ ብዙ ራሰ በራ ሐበሾች አየሁ፡፡ ፈርተው መጡ እንዴ)
ኢትዮጵያዊቷ የቤት እመቤት እዚህ ሰፊ ግቢ ውስጥ ብቻዋን ውሎ ማደር ሲሰለቻት ጊዜ እንደ ባህልዋ ቡና ማፍላት ፈለገች፡፡ ችግሩ ማን ያጣጣታል? የሚለው ነው፡፡
እዚያ ቤት የተቀጠረች አንዲት ዚምባቤያዊት ሠራተኛ አለቻት፡፡ እዚህ ሀገር የቤት ሠራተኞች ከሰኞ እስከ ዓርብ እስከ 11 ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ሰባት ሰዓት ነው የሚሠሩት እሑድ አና ቅዳሜ ከሰዓት ዕረፍት ናቸው፡፡ መኖርያቸውም ለብቻ ግቢው ውስጥ የተሠራ ቤት ነው፡፡
ያቺ ኢትዮያዊት የቤት እመቤት ሠራተኛዋ ሥራ ስትጨርስ ትጠራትና ወደ አመሻሽ ቡና ይጠጣሉ፡፡ ቅዳሜ ከሰዓትም ባለቤቷ ሳይኖር ትጠራትና አብረው ወሬ እየሰለቁ ቡና ይጠጣሉ፡፡
በወሩ መጨረሻ ለቤት ሠራተኛዋ ደመወዝዋን ለመክፈል ትጠራትና የተነጋገሩትን ደመወዝ ትከፍላታለች፡፡ ይኼኔ ሠራተኛዋ
«የሚቀር ገንዘብ አለኝ» አለች፡፡
«ምን ጠየቀች የቤት እመቤቷ፡፡
«ኦቨር ታይም የሠራሁበት»
«መቼ ምን ሠራሽ»
«በዚህ በዚህ በዚህ ቀን ካንቺ ጋር ቁጭ ብዬ ቡና የጠጣሁበት»
«እንዴ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ የጠጣሁት አንቺም ጠጥተሻልኮ»
«ቢሆንም ላንቺ ብዬ እንጂ እኔ ፈልጌ አልጠጣሁም፤ አንቺን ለማዝናናት ነው የተቀመጥኩት እንጂ እኔ ቡና ለመጠጣት መች ከሁለት ደቂቃ በላይ ይፈጅብኛል»
«ወይ አዲስ አበባ ወይ ሀገሬ ሆይ
 ቡና አጣጭ እንደ እናት ይናፍቃል ወይ»
 ሳትል አትቀርም የቤት እመቤቷ፤ ቡና አፍይ ከሚመሰገንበት ሀገር ቡና ለማጣጣት ኦቨር ታይም ወደሚከፈልበት ሀር ስትገባ፡፡ ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡ ሂሳቡን ከፈላ ቡና መጠጣቱን ተወቺው፡፡ ቡና ያለ ሀገሩ ገብቶ እንዲህ መከራውን አየላችሁ፡፡
ሐራሬ፣ ዚምባቡዌ

20 comments:

 1. dani tergumu alegebagnem asteyayet lemestet gud eko new kkkkkk

  ReplyDelete
 2. Dani,

  It was entertaining. Tebarek!!!

  DC

  ReplyDelete
 3. Dn. Dani, it is very interesting. May God be with you all.
  «ወይ አዲስ አበባ ወይ ሀገሬ ሆይ
  ቡና አጣጭ እንደ እናት ይናፍቃል ወይ»

  Hiwot

  ReplyDelete
 4. «ወይ አዲስ አበባ ወይ ሀገሬ ሆይ ቡና አጣጭ እንደ እናት ይናፍቃል ወይ» ሳትል አትቀርም የቤት እመቤቷ፤ ቡና አፍይ ከሚመሰገንበት ሀገር ቡና ለማጣጣት ኦቨር ታይም ወደሚከፈልበት ሀር ስትገባ፡፡ ምንም ማድረግ አልቻለችም፡፡ ሂሳቡን ከፈላ ቡና መጠጣቱን ተወቺው፡፡ ቡና ያለ ሀገሩ ገብቶ እንዲህ መከራውን አየላችሁ፡፡

  የአንዱ ሀገር ባህል አንዱ ሀገር ነዉር የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ ሀገር ቤት ሴት ለሴት ወይም ወንድ ለወንድ እጅ ለእጅ ተያይዞ ወይም ተቃቅፎ መሄድ ምንም ማለት አይደለም ዘመድ ወይም የቅርብ ወዳጅ ሊሆን ይችላል ምናልናት ዛሬ ስልጣኔ መስሎን ከልተበላሸ ነገሩ ሁሉ? አሜሪካን ሀገር ግን ግብረ ሰዶም ነዉ ፡፡ ቡና ጠጡም እንዲሁ ነዉ ያለሀገሩ ……


  ወ/አማኑኤል ከሚንሶታ አሜሪካ

  ReplyDelete
 5. ቡና እየጠጣሁ ሰለሆነ ይህንን ጽሁፍ እያነበብኩ ያለሁት አቶ ቡናን አልወቅሳቸውም። ግን እውነት ቡና እንደሚነገርለት ከሌሎች ነገሮች ጋር ሲነጻጸር ያንን ያህል መጥፎ ነው ብዬ አላምንም።ለምሳሌ አንተ እንዳልከው ወንዶች ለጨዋታ ከአቶ ጠጅ ቤት ሄደው ጨዋታቸውን ያደራሉ።
  አሁን አቶ ቡና እና ጠጅ ከሁለታችሁ ማነው ጎጂ ቢባሉ ቡና ጠጅን ይረታዋል ብዬ አስባለሁ። ለምሳሌ ቡና ሲፈላ በተለይ አመት በአል ከሆነ ቤተሰብ ይሰበስባል ጨዋታውም እንደዛው። አቶ ጠጅ ግን መጀመሪያ ከቤት ያስወጣሉ ከዚያ ደግሞ ነገር ሲደራ ብዙ ሲጠጣ ህሊናን ማሳት ሲጀምሩ ሰውየውም እንደዛው ይቀየራሉ ታዲያ ሰውየው ከቤቱ ሲገባ የቤተሰቡን ሰላም ያሳጣል ቤቱን ያፈርሳል። በዚህ ብቻ አቶ ቡና ይረታሉ ።

  እኔ በራሴ የቡና ሴሪሞኒ አንዱ ትልቅ ባህላችን ነው እላልሁ። ትልቅ ትዝታን የሚጥልም ነው። በውጪው አለም ያሉ ኢትዮጵያን ለልጆቻቸው ይህንን ባህል እንዳይረሱ ቢያደርጓቸው እላልሁ። ለኔ በተለይ የቡና አፈላል ስርአቱን ሳስብ የሚመጣብኝ አመት በአሎች ላይ ቤተሰብ ተሰብስቦ ቡና ተፈልቶ ያለው ወግ ዘመድ አዝማድ ሲሰበሰብ ነጭ ልብስ ለብሰው ሁሉም ድስ ብሎአቸው በአልን ሲያሳልፉ ይህንን ትዝታ ውስጤ ጥሎብኝ አልፏል። ግን ያኔ ከስራዎች ሁሉ የምጠላው ቡና ማፍላት ነበር።
  ሁልጊዜ ቡና እንደባህላችን አፈላል ይፈላ ማለቱ በውጪ ላሉት ሀበሾች እራሱን የቻለ ስራ ነው የሚሆነው ግን ግን ቢያንስ እንኳን በአመት በአል ግዜ ባህላችንን ለልጆቻችን ለማስተላለፍ የቡና አፈላል ባህል ውጪ ያሉት ባይተዉት እላልሁ። በቡና ላይ አምልኮ ካላቸው ውጪ።

  ReplyDelete
 6. Hello Deacon Daneil
  Even if it is not my first time to visit your blog and to post comment;I want to personally appreciate your gifted approach of preaching and critical views.I met you at one of the universities when you gave preaching entitled < and you wisely relate this with a generation who did not know what Virgin Mary and the saints do for him/her.This moment lives with me always.So dear Decon Dani please say something about the current turmoil of the church.
  Be blessed
  DINGIL ATELEYEN

  ReplyDelete
 7. This is sooooooo funny Dn Daniel.

  ReplyDelete
 8. kkkkkkk betam man ende hager man ende enat tebelo yelem ***«ላንቺ ብዬ እንጂ እኔ ፈልጌ አልጠጣሁም፤ አንቺን ለማዝናናት ነው የተቀመጥኩት እንጂ እኔ ቡና ለመጠጣት መች ከሁለት ደቂቃ በላይ ይፈጅብኛል»

  ReplyDelete
 9. ርብቃ ከጀርመንApril 14, 2011 at 11:37 PM

  እንደምን ዋልክ ዲ/ዳንኤል ሁለቱም አይፈረድባቸውም ልጅቱም ሳትፈልግ ግዜዋን በመባከኑ መጠየቅ ያለባትን ነው የጠየቀችው ከዚህም ያስተማረችን ነገር ቢኖር በግዜ ላይ ያለቸውን ጠንካራአቁዋም እና በይሉኝታ የሚያልፉት ነገር እንደሌለ ነው ያለባህሉዋስ ምንታድርግ የኛዋም ወይዘሮ ብትሆን እንዳገሩዋ ባህል የለመደችውን መድረጉዋ ነው ለሁሉም ቢሆን ልክአላቸው አልተግባብቶ አለ ያገሬሰው ለሁሉም ቦታና ግዜ አለው!

  ReplyDelete
 10. Hello,

  We should encourage our tradition!! We should love our country!!TXS

  ReplyDelete
 11. Dani,

  This article told us how cultural differences matters. 15 years before I were in Germany for study purpose. During my stay I had a friend from Koln ... we were good friends. We sat down together and chat a lot. At one point of time, he asked me to go to the bar and have a drink together. I assume he invited me and agreed to go with him. We went to the bar and took several bottles of beer. Finally, the separate bill came to each of us and he paid his own drinks only. I stared at him by thinking why he paid his own bill only instead of both. Finally, I pick my wallet and paid my own. Since then, I found and understood let's have a drink doesn't mean let me buy you a drink. In the individualist and the so called "civilized" community the governing principle is enjoying together and paying alone. Hence, your article entails us to watch out when we interact with the people who have different mind setup and cultural differences.

  Abebe M. Beyene

  ReplyDelete
 12. Agape from home -nice view 2 different women of different culture"mejemeria gibja mehonun,bagerachin bunna teterarto indemiteta,batekalay lijituwa gize work bicha sayhon hiywot mehonun tasredalach." Chaw...

  ReplyDelete
 13. (ኦፍ ዘሪከርድ እንነጋገርና አዲስ አበባ ውስጥ ባዶ ቦታ ያለው ብቻ ሳይሆን ፀጉር አልባ የሆነ ባዶ ራስ (ራሰ በራ) ሰውም ይሠጋል አሉ፡፡ ጭንቅላቱን በሊዝ እንዳይመሩበት፡፡ እዚህ ብዙ ራሰ በራ ሐበሾች አየሁ፡፡ ፈርተው መጡ እንዴ).....so funny.....LOL....ayhonim gin ayibalim so those of u who r .... take care....

  ReplyDelete
 14. Hope this wont happen in our country who knows!!!!

  ReplyDelete
 15. Wendime Daniel

  How are u doing there? How is our ex-presedant? I hope you will visit him by any means....

  I have good news for you, You wrote about 'Coconet' at the time of 'Milinium Project' inauguration. We all be angry by the name 'Millium', I hope some of the offical read 'Coconet', they changed the name to' Talku YeEthiopia Hidase gideb', even though it is not a strong, motive, name, it is better than the previous. Who knows I may also get fasting food in Ethiopian airline next week my way to addis.

  What I want to tell you is that, do not stop writing. I believe for our country we need two development, Social Development and Scientific Development, you have started the Social one, in near future we will start the Scientific Dev. The Social Dev is the fulcrum for the Scientific Dev.
  Tsilatnina ena sostun gormsoch selam bel

  Tesfa neng ke Uk

  ReplyDelete
 16. Intersting, educative and funnt, this reminds me a book or Joke I read about Aleka Gebrehana. Thanks Dic. Daniel with Huge respect!

  God Bless you and Your Famiy! Yakoyelegn!!!

  ReplyDelete
 17. ኤርምያስ ሳንሆዜApril 17, 2011 at 11:53 PM

  ስለቡና ስትጽፍ አንድ ትዝታ አስታወስከኝ ወደ ምድረ አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት የ እግዚአብሄር ፈቃድ ሆኖ በሀገሬ ባሉት ባንዳንድ ገዳማት የመሄድ እድል ገጥሞኝ በሄድኩበት ጊዜ ስለቡና መጥፎነት አንዴ በጻድቃኔ ማርያም ገዳም የአጋንንትን ምስክርነት በጸበል ቦታ በጆሮዬ ከሰማሁ በሁዋላ ከሰላሳ አመታት በላይ ቡና በቀን ሶስት ጊዜ ስትጠጣ የነበረችውን በቡና ሱስ ምክንያት ራሷን አዙሮ የሚያስጥላትን እናቴን ያንን ቡና ሱስ ጻድቃኔ ወስጃት ማቆሟንና እኔ ደግሞ በ አሜሪካ ምድር የስታር ባከስ ስታር ቡና ጠጭ መሆኔን ምን ትለዋለህ? ምን አልባት የእርሷ ዲያቢሎስ እንደ እሪያዎቹ ወደ እኔ ተሰናብቶ ኖሮ ይሆን ነበርን? ሌላው ደግሞ በዚሁ በአሜሪካ ባንድ የትምህርት ቤቴ ክፍል ስልጠና ላይ የዘመኑ ልጆች ሀይለኝነት/ምርቃና/ ወላጆቻቸው ከሚወስዱት የተለያዩ አበረታች እጾች በመነሳት ነው ስባልና ያለ ቡና አበረታች ንጥረ ነገር/ካፊን/ መስራት አለመቻሌ አናዶኝ ቡና መጠጣት ማቆሜንስ ምን ትለዋለህ? ጠበል ሳያስቆመኝ ትምህርት ቡና ማስቆሙንስ ምን ትለዋለህ? ጠበል አጋንንትን ሲያወጣ ትምህርት አስተሳሰብ ይቀይራል መሰል።

  ReplyDelete
 18. Hahahah. This is very hilarious. May be that is why we are still poor.

  ReplyDelete
 19. «ተወው እባክህ፣ተይው እባክሽ» ከተባባሉበት ቆለፉት ማለት ነው፡፡
  really .....

  ReplyDelete
 20. those spent someone time have to think like this.

  ReplyDelete