Monday, April 11, 2011

«ቀበቶዎን ይፍቱ፣ ጫማዎን ያውለቁ»


ወደ ሐራሬ ዚምባቡዌ ለመጓዝ ዕቃዬን በጋሪ እያስገፋሁ ወደ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየገባሁ ነው፡፡ በሩን ስታልፉ የመጀመርያውን ፍተሻ ታገኙታላችሁ፡፡
አንድ ሸምገል ያሉ ቆፍጣና አባት ከአንዲት እንደ አውራ ዶሮ በንቃት ከሚራመዱ እናት ጋር ዕቃቸውን አንዲት ልጅ እየገፋችላቸው ከፊቴ ይጓዛሉ፡፡ የሰውዬው አረማመድ የወታደርን ቤት የቀመሱ መሆናቸውን ያሳብቅባቸዋል፡፡ ከቁመታቸው ዘለግ ብለው አካባቢውን ማተር ማተር ያደርጉታል፡፡ ምናልባትም ወደ አካባቢው ሲመጡ የመጀመርያቸው ሳይሆን አይቀርም፡፡
 የፍተሻው ቦታ ስንደርስ ልጂቱን ዕቃ የሚገፉ ሌሎች ሰዎች ረድተዋት ሻንጣዎቹን በተንሸራታቹ መፈተሻ ላይ ጫኑላት፡፡ ከዚያ በኋላ ሽማግሌው ሰውዬ ከፊት ቀደሙና ተፈታሾች በሚያልፉበት የብረት ሳጥን ለማለፍ ተዘጋጁ፡፡
ፈታሿ «አባቴ ቀበቶዎን ይፍቱ፣ ጫማዎንም ያውልቁ» አለቻቸው፡፡
«ምን አሉ ሽማግሌው ኮስተር ብለው፡፡
«ቀበቶዎን ይፍቱ፣ ጫማዎን ያውልቁ»
«ማን? እኔ? እኔ የሸዋ ረገድ ወንድም» ጠየቁ ሽማግሌው ከምድር እስከ ሰማይ ተራ በተራ እያዩዋት፡፡ እግራቸው ሲንቀጠቀጥ ይታየኛል፡፡
«አዎ ጌታዬ ሕግ ስለሆነ ነው» አለች ፈታሿ ደንገጥ ብላ፡፡
«ምንድነው ሕጉ? ሰውን ቀበቶ ማስፈታት፣ ጫማ ማስወለቅ ሽማግሌው በቁጣ ጠየቁ፡፡
ልጅቱ ዝም አለች፡፡
«ሸዋ ረገድ ትሙት ቀበቶማ አላወልቅም፣ ወንድ ልጅ እንዴት በአደባባይ ቀበቶ ያወልቃል፡፡ እንኳን ዛሬ በሰላሙ ጊዜ ለጣልያንም አልፈታሁ፤ እንዴት እንዴት ብትደርፍሩኝ ነው ቀበቶ ፍታ የምትሉኝ፤ ደግሞ ቀበቶ አጥብቅ የሚባልበት ዘመን አልፎ ቀበቶ ፍታ የሚባልበት ጊዜ መጣ? እዚህ የቆማችሁት ቀበቶ ለማስፈታት ነው ተንቀጠቀጡ፡፡
ልጃቸው ቀስ ብላ ጉዳዩን ልታስረዳቸው ሞከረች፡፡
«ተዪው ተዪው አልሄድም ይቅርብኝ፡፡ ይሄ አሜሪካ የሚባለው ገና ካሁኑ ቀበቶ ማስፈታት ከጀመረማ ችግር ነው፡፡ ቀበቶ ለመፍታት ነው እንዴ የምሄደው፡፡ ተዪው እመለሳለሁ ዕቃዬን መልሱ፡፡ ድሮም ጨቅጭቃችሁ ጨቅጭቃችሁ አስነሣችሁኝ እንጂ የነጭ ሀገር ሄጄ ምን ጤና ላገኝ፡፡» ወደ መጡበት በር ተመለሱ፡፡
እርሳቸው ወደ መጡበት ሲመለሱ አንድ ለግላጋ ወጣት በእድሜ ከርሱ ትንሽ ከፍ ያሉ ከሚመስሉት ወላጆቹ ጋር እየተጫወተ ወደ አውሮፕላን ጣቢያው ገባ፡፡ ሱሪው ከወገቡ ወርዶ ሊያመልጠው ደርሷል፡፡ ቀበቶ የሚባል የለውም፡፡ አዩት ሽማግሌው፡፡
«አይፈረድባቸውምኮ ዛሬ ሁሉ ቀበቶውን ፈትቷል፡፡ ጠላት ሳያስገድደው በገዛ እጁ ፈትቷል፡፡ ወገብ መታጠቅ ቀርቷል፡፡ ሱሪን ሳብ አድርገው ወገብ ላይ ሸብ አድርገው ሲታጠቁት ነው እንጂ፡፡ አይ ሸዋ ረገድ ገድሌ እንኳንም ይህንን አላየሺው፡፡ አይ ስምንተኛው ሺ፤ ሴቶቹ በልጠውን ሱሪያቸውን በቀበቶ ሲታጠቁ፣ ወንዱ ቀበቶ እየፈታ»
ይህንን ስሰማ ሰውዬው አባት አርበኛ መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ እናም አዘንኩ፡፡ እኒህ ሰውኮ ወደ ፍተሻው እንደ ቀረቡ የአርበኛነት የክብር መታቂያቸውን አሳይተው ሲሆን በልዩ ሳሎን ማለፍ ነበረባቸው፤ ካልሆነም ለእርሳቸው በሚመጥን መልኩ መስተናገድ ነበረባቸው፡፡ ይህ አውሮፕላን ጣቢያ የተገነባውኮ በእነርሱ የአርበኛነት ደም ላይ ነው፡፡
ግን አባት አርበኛ ማለት በኢትዮጵያኛ ምን ማለት ነው? ለአድዋ እና ለድል በዓል የአርበኝነት ልብስ ለብሶ፣ ሜዳልያውን ደርድሮ፣ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ አሸብርቆ አደባባይ የሚወጣ ሽማግሌ ማለት ነው) እና በቃ፡፡ ከዚያ የት ነው የሚኖሩት? መዓርጋቸው ምንድን ነው? የሚያገኙት ሀገራዊ ክብር ምንድን ነው? ለመሆኑ ስለ እነዚህ «ልዑላን ዜጎች» ተብሎ የወጣ የክብር እና የጥቅም ሕግ ይኖር ይሆን?
አሜሪካውያን ትዝ አሉኝ፡፡ ታላላቅ ዜጎች senior citizen የሚሏቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ ሀገሪቱን አገልግለው ለአረጋዊነት የበቁ ዜጎች፡፡ በየአውቶቡሱ እና ሕዝብ በሚበዛበት ቦታ ሁሉ «ለታላላቅ ዜጎች ቅድሚያ ስጡ» የሚሉ ማስታወቂያዎች አሉ፡፡ ለሕዝባዊ አገልግሎት በሚከፍሏቸው ክፍያዎች ሁሉ የነጻ ዕድል ወይንም ቅናሽ አላቸው፡፡ ምክንያቱም ሀገራቸውን አገልግለዋልና፡፡
ለመሆኑ የኛ አባት አርበኞች ቅድሚያ፣ ልዩ ጥቅም፣ ቅናሽ፣ የሚያሰጥ መታወቂያ ይኖራቸው ይሆን) በአውቶቡስ ሲሄዱ እኩል ይከፍላሉ? እኩልስ ይጋፋሉ? ቀበሌ ሲሄዱ እኩል ይቀጠራሉ? እኩልስ ይሰለፋሉ? ሐኪም ቤት ሲሄዱ እኩል ይከፍላሉ? እኩልስ ተራ ይጠብቃሉ? በፍተሻ ቦታዎችስ ክብራቸው ይጠበቃል? ለመዓርጋቸው በሚመጥን መልኩ ይስተናገዳሉ?
ለአንድ አባት አርበኛ «ቀበቶህን ፍታ» ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ለአንድ መፈተሽ ሥራው ለሆነ ሰው ግን የዕለት ቋንቋው ነው፡፡ በልጅቱ አልፈርድም፡፡ ሽምግልናቸውን እንጂ አባት አርበኛነታቸውን በምን ልታውቅ ትችላለች?
ለእርሳቸው ቀበቶ ዝናር የታጠቁበት፣ ሽጉጥ የሻጡበት፣ በረሃብ ጊዜ አንጀት ያሠሩበት፣ ወገብ ሸብ ያደረጉበት ነው፡፡ ትዝ የሚላቸው ለሀገራቸው የከፈሉት መሥዋዕትነት ነው፡፡
የታለ ዝናርህ የተንዠረገገው
የታለ ቀበቶህ ወገብክን ያሠረው
የታለ ጎፈሬህ ችቦ የመሰለው
አርበኛ ነኝ ስትል ልቤን ቃር ቃር አለው
ያለችው ዘፋኝ የዛሬውን ባየቺው፡፡
ያኔ በዱር በገደሉ እየተዋደቁ ጠላት ሲያርበደብዱ፤ አንድ የጣልያን ሶላቶ ወይንም አንድ ሀገሩን የከዳ ባንዳ ሲማርኩ መጀመርያ ቀበቶውን አስወልቀው ትጥቅ አስፈትተው ነበር የሚነዱት፡፡ ዛሬ ዘመን ተቀይሮ የስንቱን ቀበቶ ያስወለቁትን ጀግና የሚያው ቃቸው ቀርቶ ቀበቶ ፍቱ ሲባሉ ምን ያድርጉ?
ለዚህች ሀገር ያገለገሉ መምህራን፣ ምሁራን፣ ሳይንቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ነጋዴዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ አርቲስቶች፣ ሾፌሮች፣ ሐኪሞች፣ ደራስያን፣ ለአገልግሎታቸው ሌሎች ዜጎች ምንድን ነው የሚከፍሏቸው? !ሞቱ ሞቱ ብለን ዜና ከመሥራት አልፈን መቼ ነው እንዲህ ያሉትን ዜጎች በሕይወት እያሉ አመስግነን የምንሸልማቸው? በእኔ ዕድሜ እንኳን ስንት የሽልማት ድርጅት ተፈጥሮ ፈረሰ፡፡
እንግሊዞች ለሀገራቸው ያገለገሉ ልዑላን ዜጎችን በንግሥቲቱ እጅ «ሰር» የሚል መዓርግ አሰጥተው ልዩ የከበሬታ ሥፍራ ያጎናጽፏቸዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ «የጌቶች ምክር ቤት» House of Lords እንዲህ ባሉ ልዑላን ዜጎች የተሞላ ነው፡፡ ሀገራቸውን ያውቃሉ፣ አገልግለዋል፣ ለሀገራቸው ያስባሉ፣ የተሻለ ልምድ እና ዕውቀት አላቸው ብለው በማሰብ ነው ቦታውን የሚሰጧቸው፡፡
እኛስ ከፖለቲካዊ ወገንተኛነት፣ ከዘር ቁራኛነት፣ ከዘመን ልምሾ፣ ከትውልድ ቁርሾ የጸዳ ተቋም ቢኖረን ምናለ፡፡ ለሀገራቸው የሠሩትን፣ ላቅ ያለ አስተዋጽዖ ያደረጉትን፣ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያሰኙትን፣ ከራሳቸው አልፈው ለሁላችን የሚተርፍ ነገር ያበረከቱትን የትውልድ ባለውለታዎች የምናከብርበት፡፡ የምናመሰግንበት፡፡ ለሥራቸው ዕውቅና የምንሰጥበት፡፡
የክብር ስማቸውን፣ የክብር ልብሳቸውን፣ የክብር ሽልማታቸውን ወስነን፡፡ ልዩ ጥቅሞቻቸውን ለይተን፡፡ በልብስ ወይንም በመታወቂያ መለያ ሰጥተን ብናከብራቸው፡፡ መቼም ሁሉም በሁሉ እኩል አይደለም፡፡ አባቶቻቸን «ከጣት ጣት ይበልጣል» ይላሉ፡፡ «ኮከብ እም ኮከብ ይኼይስ ክብሩ» እንዲል፡፡ የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ይበልጣል፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በአንድ ወቅት የገጠማቸውን እንደዚህ ተናግረው ነበር፡፡ «አንድ ቢሮ ሄድኩና ጸሐፊዋን አለቃዋን ለማነጋገር መምጣቴን ገለጥኩላት፡፡ ይጠብቁ ብላ አስቀመጠችኝ፡፡ አላወቀችኝም፡፡
«ለመሆኑ እኔን ታውቂኛለሽ አልኳት፡፡
«አላወቅኩዎትም አባቴ» አለችኝ፡፡
«ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ሲባል አልሰማሽም» አልኳት
«አልሰማሁም» አለቺኝ፡፡
ትንሽ ስለማንነቴ ዘረዘርኩላት፡፡ አንዱንም አላወቀቺውም፡፡
በመጨረሻ «ይድነቃቸው ተሰማንስ ታውቂዋለሽ» ብዬ ጠየቅኳት፡፡
«እንዴ እርሳቸውን የማያውቅማ አለ እንዴ» ብላ ነቃ አለቺ፡፡
«እኔ የእርሱ አባት ነኝ» አልኳት፡፡
ከመቀመጫዋ ተነሥታ እየዘለለች መጣች፡፡ «የይድነቃቸው ተሰማ አባት ነዎት? ይቅርታ አላወቅኩዎትም ነበር፡፡ ምናለ እንደ መጡ ቢነግሩኝ ኖሮ» አለቺና በድጋሚ ወደ አለቃዋ ቢሮ ገባች፡፡
ከዚያም በሩን ከፍታ አስገባቺኝ፡፡ ልጆቼ ድሮ የደጃዝማች ተሰማ እሸቴ ልጆች ነን ብለው ነበር የሚመኩት፡፡ ዛሬ ዘመኑ ተቀየረና፤ እኔንም የሚያውቀኝ ትውልድ አለፈና የይድነቃቸው አባት ነኝ እያልኩ በልጆቼ መመካት ጀመርኩ፡፡ ነገ ደግሞ እርሱንም እኔንም የሚያውቀን ትውልድ ሲያልፍ ተረት እንሆናለን» ነበር ያሉት፡፡
እውነታቸውን ነው፡፡ እንዴው ለመሆኑ በአድዋ እና በአምስት ዓመቱ ወረራ የተጋደሉ አርበኞች የመሠረቱት የአርበኞች ማኅበር የአድዋ እና የአምስት ዓመቱ አርበኞቻችን በዐረፍተ ሞት እየተገቱ ሲሰናበቱን ወራሹ ማነው? ወይስ ጣልያን እንደገና መጥቶ ሀገራችንን በመውረር አርበኛ እንድናፈራ ይርዳን? ከአርበኞች ማኅበር ወደ አርበኞች የሽልማት እና የክብር ተቋም የምንሸጋገረውስ መቼ ነው?
ይህንን ሁሉ ሳስብ ነበር ዕቃዬን አስጭኜ፣ በኢሚግሬሽን በር በኩል ዘልቄ፣ ሁለተኛውን ፍተሻ አልፌ አውሮፕላን ውስጥ ራሴን ያገኘሁት፡፡
አውሮፕላኑ ሊነሣ ሲል የበረራ አስተናጋጇ «አውሮፕላኑ ለመነሣት በሚያደርገው ዝግጅት ወገባችሁን እንድትታጠቁ ትመከራላችሁ» ስትል እኒያ አርበኛ ትዝ አሉኝ፡፡ ይህንን ቃል አውሮፕላን ውስጥ ሲሲሙት «ተባረኪ፣ ታጠቁ እንጂ ፍቱ ይባላል፤ ለካስ በዚህ ዘመን ቀበቶ የሚያስፈታ ብቻ ሳይሆን ቀበቶ አጥብቁ የሚልም አለ» እንደሚሉ ገመትኩ፡፡
ሐራሬ፣ ዚምባብዌ


35 comments:

 1. Minew decoan daneil, bekumachew hawilt eyaseran aydel-ende?

  ReplyDelete
 2. +++

  ደግሞ ቀበቶ አጥብቅ የሚባልበት ዘመን አልፎ ቀበቶ ፍታ የሚባልበት ጊዜ መጣ?
  በርታልን እንጠብቅህአለን::

  ReplyDelete
 3. ልጆቼ ድሮ የደጃዝማች ተሰማ እሸቴ ልጆች ነን ብለው ነበር የሚመኩት፡፡ ዛሬ ዘመኑ ተቀየረና፤ እኔንም የሚያውቀኝ ትውልድ አለፈና የይድነቃቸው አባት ነኝ እያልኩ በልጆቼ መመካት ጀመርኩ፡፡ ነገ ደግሞ እርሱንም እኔንም የሚያውቀን ትውልድ ሲያልፍ ተረት እንሆናለን» ነበር ያሉት፡፡

  የባሰ አታምጣ ማለት አሁን ነዉ፡፡

  ወልደአማኑኤል ከሚኒሶታ አሜሪካ

  ReplyDelete
 4. Le Ahunu Tiwld bzu yastemrenal.Negerochin ''Makabed'' eyale eyalefe negeroch kebdewbet lekere. Abatochachn yeminegrun neger hulu Denb ena srat yabezu ende ''aradoch'' ababal ''Akabedu'' eyaln norn ahun lay honen snayew yalgeban egna honen keren.
  Thank you Dani.
  Getachew

  ReplyDelete
 5. grum tshuf. min ayinet tiwld nen gn biye erasen teyekut kezam berase azenku,aferku!

  ReplyDelete
 6. <<..አይ ስምንተኛው ሺ፤ ሴቶቹ በልጠውን ሱሪያቸውን በቀበቶ ሲታጠቁ፣ ወንዱ ቀበቶ እየፈታ»
  ይሔስ እውነት ነው። ድሮ ድሮ ሴቶች እንብርታቸውን እያሳዩ እየተባለ ሲወቀስ አሁን የወንዱ ብሶ ቁጭ አለ። ሱሪው ተንጠልጥሎ ካሁን ካሁን የሚወልቅ የሚመስለው እና የውስጥ ሱሪው ሙሉ ለሙሉ የሚታይ የዚህ አይነት አለባበስ ሰለባ የሆኑ በ norths America አሜሪካ ያሉ ስንቶች ናቸው? የነጮቹ እንደዛ መሆን አይገርመኝም።የኢትዮጵያዊው እንጂ።

  እኚህ አባት አሜሪካ የገቡ እለትማ ምን ሊሉ ነው ቀበቶውን ፈቶ.. በየ ሁለት እርምጃው በአንድ እጁ ሱሪው ከፍ እያረገ የሚሄደውን የሀገረቸውን ዜጋ ሲያዩ..?

  ReplyDelete
 7. "fitegnoch hualegnoch hualegnoch fitegnoch" yilal metafu

  ReplyDelete
 8. Thank you Dn. Daniel,

  I always think about the upcoming generation not walking in the path of our fathers(paying respect to elders). I blamed parents mostly for this loss, but your article made me think that policy makers are equally responsible for this.

  Policy makers should Integrate benefits for the elderly in their budget year/plan(Medical benefits, transportation benefit, service priority and more others). This will strike the why? in the mind of the young, who would then realize the elderly deserve such benefits and their due respect.

  If the elderly are not remembered through social benefits the government provides, they will stay disrespected and we may carry their curse all along. Parents, you are still responsible for a mannered up-bringing of your children who are likely to become future leaders.

  GOD be with you D. Daniel.

  ReplyDelete
 9. kibir Lemigebaw kibir enesit!!!!

  ReplyDelete
 10. Dani,

  It is a very wonderful premises that tells us to recognize the contribution of our respected fathers and mothers.Your analysis and intervention underscore the value of passed ancestors who paid a lot to give us the actual identity we had today. I trust, we will have your deep insight on other issues.

  Abebe M. Beyene

  ReplyDelete
 11. Dani, It is nice view. Thank you!

  ReplyDelete
 12. :):):):) "አውሮፕላኑ ሊነሣ ሲል የበረራ አስተናጋጇ «አውሮፕላኑ ለመነሣት በሚያደርገው ዝግጅት ወገባችሁን እንድትታጠቁ ትመከራላችሁ» ስትል እኒያ አርበኛ ትዝ አሉኝ፡፡ ይህንን ቃል አውሮፕላን ውስጥ ሲሲሙት «ተባረኪ፣ ታጠቁ እንጂ ፍቱ ይባላል፤ ለካስ በዚህ ዘመን ቀበቶ የሚያስፈታ ብቻ ሳይሆን ቀበቶ አጥብቁ የሚልም አለ» እንደሚሉ ገመትኩ፡፡"

  Interesting finishing!!!

  ReplyDelete
 13. ዛሬ ዘመኑ ተቀየረና፤ እኔንም የሚያውቀኝ ትውልድ አለፈና የይድነቃቸው አባት ነኝ እያልኩ በልጆቼ መመካት ጀመርኩ፡፡ ነገ ደግሞ እርሱንም እኔንም የሚያውቀን ትውልድ ሲያልፍ ተረት እንሆናለን» ነበር ያሉት፡፡
  ewnt kawerann yeh neger bergit eyehone yalena yemihon new....wey semachewen beferenjinga mekeyer yinureben enja...
  masafer hulu jemroal...esti ye debter/exercise book/lay enkuan eyawetu biyastemrun.
  and thank you diakon.

  ReplyDelete
 14. ይመቻል!!!!!!!!!!!!
  ባጣም ጥሩ ነው!! ፅሑፉ አስተማሪ፣ አነቃቂ እና ለበለጡ ስራዎች የሚያነሳሳ እንዲሁም ጎዶሏችንን በግልፅ ያስቀመጠ ነው። ዲ/ን ዳንኤል ተባረክ። ረዥም እድሜን ከሙለሉ ጤና ጋር ይስጥህ።

  ReplyDelete
 15. some of the law needs ecomcal devlopment to apply anyways I do like the way u see things

  ReplyDelete
 16. really, it is good idea! thanks Dn. Dani

  ReplyDelete
 17. ሀገራችን በጣም በጣም ብዙ ነገር ይቀራታል፡፡ እሱን ማሰብ ተስፋ ያስቆርጣል፡

  ReplyDelete
 18. D/N Daniel the way you observe things is so pleasant .I used to get frustrated when the security guard order me to take off my shoe and my belt .but We have to accept .u know security is just for all of us .However for some reasons or for some VIP PPL should get more privileges.
  Sami Neda From Abware

  ReplyDelete
 19. ቃለ ህይወት ያሰማልን። እኔን የሚገርመኝና የሚያናድደኝ ግን ለኛ ለፍተው ታግለው ሞተው ያቆዩልንን ታሪክ ቅርስ አይከን ባቆዩልን አለመመስገናቸው ሳይሆን እኛ በእድገት ኋላ ቀር መሆናችንን ተጠያቂ እነሱን ማድረጋችን ነው። ዳኒ አንተ ክብር እንስጣቸው ትላለህ በሌላኛው አቅጣጫ ደግሞ ያለው ለእድገታችን አንዱ ቅኝ አለመገዛታችን ነው የሚል አለ። በዚህ አንድ የማውቀው ሰው የአርበኞች ቀን ሲከበር በቴሌቪዥን ሲያይ እነዚህ ጅሎች ያለው ትዝ ይለኛል። ዛሬ እኮ እነሱ ከዘረፋ ባቆዩን የታሪክ የሐይማኖት መጻሕፍት አጻጻፍ ዘዴ ተምረው የታሪኩንም ባለቤት አምጭውንም ሲሳደቡ ይስተዋላል። ለነዚህ ልቦና ይስጥልን እላለሁ። መንግስትም ውለታ ከፍሎ ተከፋይ ቢሆን ይሻላል። ድንቅ እይታ ነው ስራህን እግዚአብሔር ይባርክልህ።

  ReplyDelete
 20. DANI BETAM TERU NEGER NEW
  GEN YEMTANESACHEW HASABOCHEN
  LEMTEGBER YETGEMERE ALE WOY

  ReplyDelete
 21. dni sel betseb metane eotc men telalech
  ebakehen bezeh zuria safelen plssssssssssss

  ReplyDelete
 22. ርብቃ ከጀርመንApril 13, 2011 at 10:01 PM

  እናመሰግናለን ዲ/ዳንኤል ክብረት አስተማሪየሆነ ጽሁፍ ነው ማስተዋሉን አምላክ ለቸረው ከዝንባቡየ ሁነሀ የምትጠሙረውን ለመስማ(ለማንበብ) ቸኩያለሁኝ በሰላም ተመለስ ቸርይግጠምህ

  ReplyDelete
 23. ችግሩን ማወቅ ግማሽ መፍትሔ ቢሆንም ትችት ብቻ መጻፍና ትችትን መደገፍ ብቻውን መፍትሔ አይሆንም:: ከዚህ ይልቅ ፐሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ያቋቋሙት የአረጋዊያን መጦሪያ ተግባራዊ ትርጉም አለው በእኔ እይታ:: እኔም ትችት ላንተ እየጻፍኩ እንደሆነ ይታወቀኛል:: ወደ ተግባር እንግባ በሚል አንድምታ ግን መውሰድ ብትችል ደስ ይለኛል:: እንጂ የኬፕኮስትን ታሪክ እያነበብኩ ለአባቶቻችን ውለታ መክፈል የለብንም የሚል ጭፍን አስተያየት የለኝም:: ትንሽዬ ድርጅት አቋቁምና የድጋፍ ምላሹን ከሁላችንም ታገኛለህ ባይ ነኝ::

  ReplyDelete
 24. ልጅነታችን ይሁን ልባችን በዝያን ዘመን አንዲህ ይለን ነበር
  “ እንድች እንድች አይነት ጫወታ ተጫወቱ ደስ ትላለች ተደሰቱ”

  እናም እንዲህ እንዲህ እያልክ ወደ ማንነታችን መልስን፣ ከኛነትም
  ጋር አስታርቀን.

  እኔው አበጀህ ብያለሁ; - ጣመና - ድገመና...

  ፍቅር አለም ከጆበርግ

  ReplyDelete
 25. ዳኒ ስለ አድዋ ድል እና ስለ አርበኞች ቀን ሲነሳ አንዳንድ ወጣቶች የሚሉት ነገር አለ፡፡ ጣሊያን ቀኝ ገዝታን ቢሆን ኖሮ ሀገራችን በሰለጠነች ነበር፣ የሚል ስሜት አላቸው፡፡

  እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ሀሳቦች አሉን፡- አንደኛው ቀኝ አለመገዛታችን በራስ የመተማመን ስሜት እንዲኖረን፣ በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ፣ የራሳችን የሆነ ያልተበረዘ ሀይማኖት ታሪክ ባህል ቅርስ እንዲኖረን አድርጎን ነበር እላለው በፊት ያኔ ድሮ ፡፡

  በሁለተኝነት ደረጃ አሁን ላይ ግን የሚታየን ባሕላችንም በባእዳን ባሕላት ተቀይጧል፣ ሱሪውን ዝቅ ካላደረገ እንብርት ካላሳየች የተሰለጠነ የማይመስልበት ሀገር ሆናለች፣ ቅርሳችንም በራሷ በኢትዮጵያ ልጆች እየተዘረፈ ለፈረንጅ ይሸጣል፣ የተዋጉላት የሚባሉት አባቶቻችንም ያሁሉ ጀግና አልቆ የቀሩት ጥቂት አርበኖች እንኳን ምንም አልተጠቀሙም፣ ክብሯን ያስከበሩላት ሀገር ሳታከብራቸው ጉልበታም በነበሩበት ሰአት ጀግና የሆኑላት ጉልበታቸው ሲደክም ያልደገፈቻቸው ኑሮዋቸው እጅግ የወረደ ሆኖ ሳየው ለሀገር መዋጋት የመስዋዕትነት ጥቅሙ ምንድነው እላለው፡፡ የእነሱ አልበገሬነት እነሱንም እኛንም እንደጎዳ ይታየኛል ጠላትን መከቱ እንጂ ለሀገራቸው እድገት በዙም አልሰሩም፡፡ እንዲያውም በዘር በጎሳ በመከፋፈል ባሪያና ጌታ፣ አለቃና ምንዝር እየተባባሉ የኖሩበት ዘመን ይበልጣል፡፡ ይልቁንም እነሱ የከፈቱት መንገድ ነው አሁን ኢትዮጵያ ቁርጥራጭ ወረቀት እስክትሆን ድረስ ብጭቅጭቋ የወጣው፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 26. thank you for this but think about getting foundations that serves "arbegnoch and shimagloch",we are ready and interested to help them.

  ReplyDelete
 27. ሰላመ እግዚአብሔር አይለይህ

  እንዴት ደስ የሚል አጋጣሚ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ከምዕራቡ ዓለም በመጣ ስልጣኔ በሚባል አባዜ በምንወዛገብበት ወቅት እንደነዚህ አይነት ሰዎችን በቁጥር ጥቂት ቢሆንም በአካል መገኘታቸው ትልቅ ነገር ነው፡፡

  ቸር እንሰብት

  ReplyDelete
 28. በጣም አሪፍ ፅሁፍ ነዉ

  ReplyDelete
 29. ኤርምያስ/ሳንሆዜ/April 18, 2011 at 1:02 AM

  ጥሩ እይታ ነው። አይነ ልቡናህን ያብራልህ! ደግሜም እላለሁ ያብራልህ!

  ReplyDelete
 30. እኔ እንደምረዳው የኛ ችግር ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ጠንቅቀን ባለማወቃችን በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው ሰዎች እነማን እንደነበሩ ያለማወቅና ስለታሪክ ለማወቅ ባለመፈለግም ጭምር የተፈጠረ ችግር ነው፡፡ ሌላው ችግር ትውልድን የመገንባት ኃላፊነት ያለባችውም አካላት ያለፈውን በመኮነን ላይ የተመሰረተ አመለካከትን ወደትውልድ በማስረፅ የቀደሙ ባለታሪኮች ትኩረት እንዲነፈጋቸው አስተዋፅዎ አበርክተዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 31. ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 32. ዲያቆን ሀብታሙApril 21, 2011 at 3:30 PM

  ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 33. KHY Dn Daniel

  <>...Amlak Yirdan

  ReplyDelete
 34. Dn Daniel bertalin, astemari tsihufoch nachew. Enwedhalen

  Dept of Mgt Staff; Kab Mekelle Un

  ReplyDelete
 35. As the saying goes: "GIRD UP YOUR LOIN"!!!!

  Tena Tabia folk (Kebele 03)
  Bahirdar

  ReplyDelete