አበባ አየሁ ፈቃዱ - ጋና

ኬፕኮስት ዛሬ በጋና መንግስታዊ አወቃቀር ከጋና አስሩ ክልሎች አንዷ የሆነችው የሴንትራል ክልል (central region) ዋና ከተማ ነች፡፡ ይቺ ታሪካዊ ከተማ ከዋና ከተማዋ ከአክራ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
ወደዚች ታሪካዊት ከተማ የተጓዝነው ለጉብኝት ነው፡፡ የጉብኚታችን ዓላማ በሙዚየሙ ውስጥ የተቀመጠውን በታሪክ መዛግብት የተከተበውንና ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገረውን የባርነት ጠባሳ መመልከት ነው፡፡ የእኛ ጉብኝት ዓላማ በዋናነት የኬፕኮስትን ካስል ማየት ቢሆንም በአቅራቢያችን ግን አንድ ታሪካዊ ብሔራዊ ፓርክ ነበርና እግረ መንገዳችንን ወደዚያው አቀናን፡፡ ወደ ካኩም ናሽናል ብሔራዊ ፓርክ፡፡
ፓርኩ ውስጥ ዝሆን፣ አንበሳ፣ቆርኬ----የመሳሰሉ የዱር እንስሳት ቢኖርበትም እኛ የተገኘንበት ሰዓት ግን እነሱን ለማየት የሚያስችል አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ከመሬት 60 ሜትር ከፍታ ላይ እንስሳቱን ለማየት በሚያስችል ሁኔታ ከዛፍ ዛፍ ተሰናስሎ የተሰራውና ሰንሰለታማና ተወዘዋዥ የአየር ላይ መንገድ አድንቀናል፡፡ መንገዱ ሰባት ነው ከአንዱ ትልቅ ዛፍ እስከ ሌላኛው ዛፍ ያለው አንድ ተብሎ ተቆጥሮ ማለት ነው፡፡ ለሚፈራና ለሚደነግጥ ግን በሶስት ብቻ ለማለፍም የሚችልበት መንገድ እንደ ነበረው ለመገንዘብ ችለናል፡፡
በሚወዛወዘው ሰንሰለታማ የአየር ላይ መንገድ ሆነው ቁልቁል ወደ ታች ደኑን ለሚመለከት ከሰማይ ወደ ምድር ለማረፍ የሚያኮበኩብ አውሮፕላን ክንፍ ላይ ያሉ ሁሉ ሊመስሎት ይችላል፡፡ ከምድር ከፍ ብለው እየተወዛወዙ ነውና፡፡ ይህ ተወዛዋዥ ሰንሰለታማ መንገድ 350 ሜትር ርዝመት እንዳለው አስጎብኛችን ነግሮናል፡፡
ከካኩም(Kakum) ብሔራዊ ፓርክ ቀጥታ ያመራነው ወደ ካስሉ ነበር፡፡ ይህ ካስል የቀድሞ የአፍሪካ ቀኝ ገዢዎች እግሊዞች፣ ፖርቹጋሎች፣ ፈረንሳዮች--- ባሮችን እንዴት እንደሚያሰ ቃዩአቸውና እንደሚያንገላቱዋቸው የሚያሳይ የታሪክ አሻራ ያለፈበት ቦታ በተለይም በሰንሰለት እየታሰሩ ወደ መርከብ እስኪጫኑ ድረስ እንደ መጋዘን ዕቃ የሚቆዩባቸው የወንዶችና የሴቶች ባሮች፣ እንዲሁም የአመጸኞች ባሮች፣ የአራስ ሴቶች ባሮች ማቆያ ስፍራዎችን አይተናል፡፡
የባሮች ማቆያ ዋሻ መብራት የለውም፡፡ አሁን ለጉብኝት ተብሎ በተሰቀሉት መብራቶች እየታ ገዝን እንኳን ስንገባ የፍርሀት ድባብ ለቆብን ነበር፡፡ ጪራሽ ደግሞ መብራት ባይኖረው ከዚያ ተነስቶ ሲኦልን መገመት አያዳግትም፡፡ በዚያ ከዋሻው ጥልቀት የተነሳ በደበዘዘው ብርሃን ታግዘን ወደ ታች ስናማትር ከእግራችን በታችን ከዋሻው መሀል ለመሀል ቀጪን ቦይ ተመለ ከትንና አስጎብኚያችንን ጠየቅነው፡፡ ይህ ምንድን ነው?
ይህ ቀጪን ቦይ እነዚያ ባሮች አንዴ ከገቡ እንደ መጋዘን ዕቃ የሚወጡት መርከብ ሲመጣ ለመጫን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ለሽንት ውጪ አይወጡም፡፡ እዚያው ይሸናሉ፡፡ መሀል ባለው ቦይ ሽንታቸው ይወርዳል፡፡ ምግብና የፀሐይ ብርሃን መቀበያ ሶስት ሜትር ከፍታ ላይ ወዳለው መስኮት በእጁ እያሳየ በዚያ ይቀበላሉ አለን፡፡
ከካስሉ በስተቀኝ ወዳለው ሌላ ሙዚየም ይዞን ሄደ፡፡ እዚያ ውስጥ ባሮች የሚታሰሩበት ከብረት የተሰሩ የእጅ፣ የእግርና የአንገት ሰንሰለቶችን ተመለከትን፡፡ በተለይ የእጅ ሰንሰለት ተብሎ የተሰቀለው ረጂምና በእጅጉ የተሰናሰለ ነበርና ለምን እንዲህ ረዘመ ብለን ጠየቅን፡፡ አስጎብኛችን መለሰ፡- ባሮቹ በተለይም ወንዶቹ በአንድና ወጥ በሆነ እርስ በእርሱ በተሰናሰለ ሰንሰለት ነው የሚታሰሩት፡፡ ይህ ደግሞ የሚደረገው አንድ እንዳይጠፉ፣ ሁለትም ከዋሻው በወጡበት ሁኔታ ለመጫን እንዲያመቻቸው ነው አለን፡፡

እኛም ወደ ዚህ ግዙፍ በር መግባት ፈራን፡፡ እኛም አንመለስ ይሆን? አስጎብኛችን ግን ቀለደና አሳቀን፡፡ አይዞአችሁ ትመሰሳላችሁ ብሎ ወደ ውቅያኖሱ ወስዶ እንዴት ወደ መርከቡ እንደ ሚጫኑ ተረከልን፡፡
የካስሉ ስፋት የቦታው ቆይታና ታሪካዊነት በተለይም ለምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች ለአይቮሪኮስት፣ለቤኒን፣ ለቻድ፣ ሴራሊዮን-----የመሳሰሉ ሀገሮች ሁሉ በባሪያ ንግድ ሂደት ውስጥ ጋናን እንደ ማዕከልነት ተጠቅመውባት እንደ ነበር መገመት አያደግትም፡፡ ምክንያቱም ሌሎቹ የተጠቀሱት የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች እንደዚህ ሰፊና ታሪካዊነት ያለው ካስልና የባሪያ ማቆያ ስፍራ የላቸውምና፡፡
ከዋሻው የመጨረሻና ሰፊ ክፍል ውስጥ ስንደርስ ከዋሻው ጥግ ብዙ አዳዲስ ጉንጉን አበባዎችን አየንና አንድ ሴራሊዮናዊ ጠየቀ፡፡ አስጎብኛችንም «ይህ ጉንጉን አበባ በዚያን ጊዜ በባርነት ሄደው ያልተመለሱ በመከራና በችግር ጊዜያቸውን ያሳለፉ የእነዚያ አባቶች ልጆቻቸው(ዲያስጶራዎች) አባትና እናቶቻቸውን ሊያስቡ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እየመጡ በየጊዜው የሚያስቀምጡላቸው መታሰቢያ ነው፡፡» አከለና «ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በሩ ላይ ዛሬ ከጀርባው «ዶር ኦፍ ሪተርን» ብለው ጽፈውበታል፡፡ እነሱ በነጻነት ተመልሰውበታልና» አለን፡፡
ሌላው ከካስሉ ስንወጣ የትኩረታችንን አቅጣጫ ስቦት የነበረው በከስሉ መግቢያ በር ላይ ተጽፎ የነበረው የእብነ በረድ ጽሁፍ ነበር፡፡ ጽሁፉ «ኢተርናል ላይፍ (Eternal life)» ይላል፡፡ ይህ ጽሁፍ የአሜሪካኑ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋናን ከባለቤታቸው ከሚቼል ኦባማና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በጎበኙበት ወቅት ስለነዚያ በግፍ ስለተሸጡ ባሮች ለነፍሳቸው የዘላለም ዕረፍት የተመኙበትና ለመታሰቢያ ያስቀመጡት ነበር፡፡
እውነት እነዚያ ባሮች፣ በ ዶር ኦፍ ኖ ሪተርን በአስከፊ ሁኔታ እንደ እንስሳ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በኩል የተሸጡ ነፍሳት፣ ጊዜ ጊዜን ወልዶ ታሪክ ተቀይሮ፣ ጥቁሩ ባራክ ኦባማ የዓለም ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካን መርቶ ቢያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን?
ኬፕኮስት የማይሽር ጠባሳ፣ የጥቁር አፍሪካ አስከፊ ገጽታ፣ ባርነት ክፉ ነው፡፡ እነዚያ በጨለማው ዘመን የነበሩ የጨለማው ነጮች ግፍ ሰርተዋል፡፡ ቀጥቅጠው ገዝተው ሽጠዋል፡፡ ወይ ኢትዮጲያ? ወይ አድዋ? ለካስ ሚስጢሩ ብዙ ነው፡፡ በዚያ የጉብኚት ቅጽበት በአዕምሮዋችን ይመላለስ የነበረው የእጂጋየው ሺባባው(ጂጂ) ስንኝ ነበር
ትናገር አድዋ ትመስክር ሀገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
አስጎብኛችን የጉብኚታችን መጨረሻ ወደሆነው አንድ ጠባብ ክፍል ይዞን ገባ፡፡ ክፍሉ ጠባብ ከመሆኑ በተጨማሪ ጣራው የቁመታችንን ያህል ብቻ ነበር ከፍ የሚለው፡፡ በዚያ ላይ ስፋት ስለሌለው ሁላችንንም ለመያዝ አቅቷት ተጨናንቃ ነበር፡፡ ወለሉ ትኩስ ደም የመሰለ ቀይ ነው፡፡ ለምን እንዲህ ቀይ ሆነ? አንዱ ጠየቀ፡፡ አስጎብኛችንም ቀጠለ «ይህ ክፍል ከባሮች መካከል አንገዛም የሚሉ የሚገደሉበት ነው፡፡ እዚሁ ይገደላሉ፡፡ እዚሁ ደማቸው ይፈሳል፡፡ ስለዚህ እነሱን ለማሰብ ነው ወለሉ ቀይ ደም የመሰለው፡፡ ክፍሉ መብራት ስለሌለው በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይሰማን የነበረው የአስጎብኛችን ድምጽ ብቻ ነበር፡፡
አሁን የጉብኚታችን መጨረሻ ስለሆነ ሁላችሁም እጂ ለእጂ ተያያዝን፡፡ «በግፍ ለሞቱት ለእነዚያ ነፍሳት ለአምስት ደቂቃ እንጸልያለን» አለን፡፡ ሁሉም ጸጥ፡፡ በእውነት አምላክ ጸሎታ ችንን ሰምቶ እነዚያን በምድር ያልደላቸውን በምድር የዋሻ ጨለማ ሲኦል የሆነባቸውን ነፍሳት አሳርፎ ከሰማዩ ድቅድቅ ጨለማ ያሳርፍልን፡፡
እናቱ ሱሪ ለባሽ የሆነችበት ትውልድ የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ ለማለት ይቸገራልና ይህ የባርነት ጠባሳ ያልነካትን ብቸኛ ጥቁር አፍሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያን ለማመስገን በድፍን አፍሪካ ፊት ቀና ብለን እንድንሄድ ያደረጉንን የአባቶቻችንን ክብር ለመናገር ለሚቸገሩ ነጮችና ጥቁሮች ሁሉ ጠባሳው ህያው የኢትዮጵያ ምስክር የአድዋ ነጸብራቅ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ፍቅሩ ኪዳኔ በፒያሳ ልጅ መጽሐፉ እንደ ነገረን ጋና ነጻነቷን ስትቀዳጂና ነጻ ስትወጣ የመጀመሪያው የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሚ ንክሩማ የስራቸው መጀመሪያ የባርነት ጠባሳ ያልነካት የነጻነት ሀገር ኢትዮጵያን መጎብኘት ያደረጉት፡፡
ምነው ታዲያ ዛሬ ይቺ የጀግና ሀገር ድህነት ከፋሽስት ኢጣሊያ ይልቅ በረታባት? እርግጥ ነው እርግጥ ነው ለማሸነፍና የአሸናፊነትን ታሪክ ለመጻፍ የጀግና ልጅ ጀግና ያስፈልጋል፡፡ እጁን ከመስጠት ሞትን የሚመርጥ የቴዎድሮስ ልጅና ትውልድ ያስፈልጋል፡፡ እስቲ ለማንኛውም ወገን እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛልና በርትተን ከድህነት ጋር እንዋጋ፡፡ እየሰራን እልፍ እንበል፡፡ ከፊት እልፍ አለና፡፡
ምነው ታዲያ ዛሬ ይቺ የጀግና ሀገር ድህነት ከፋሽስት ኢጣሊያ ይልቅ በረታባት? እርግጥ ነው እርግጥ ነው ለማሸነፍና የአሸናፊነትን ታሪክ ለመጻፍ የጀግና ልጅ ጀግና ያስፈልጋል፡፡እየሰራን እልፍ እንበል፡፡ Wow! Dani i brows your blog may be 3 times a day longing your amazing and intellectual views. thanks so much.
ReplyDelete'K menfesawiw Alem Nafeken'
ውድ ወንድሜ ዲን ዳንኤል
ReplyDeleteፎንቱን ከፍ አርገው። አይኔን ተወው--
God Bless you Abebayehu!!!
ReplyDeleteThis is what every body needs to remember.
+++
ReplyDeleteእንደው በውነት እግዚአብሔር ይስጥልኝ:: እንጃ ብቻ ውስጤ ደስ አለው::
እንጠብቃለን:: በርታ!
እርግጥ ነው እርግጥ ነው ለማሸነፍና የአሸናፊነትን ታሪክ ለመጻፍ የጀግና ልጅ ጀግና ያስፈልጋል፡፡ እጁን ከመስጠት ሞትን የሚመርጥ የቴዎድሮስ ልጅና ትውልድ ያስፈልጋል፡፡ እስቲ ለማንኛውም ወገን እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛልና በርትተን ከድህነት ጋር እንዋጋ፡፡ እየሰራን እልፍ እንበል፡፡ ከፊት እልፍ አለና፡፡
ReplyDeleteእስቲ ለማንኛውም ወገን እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛልና በርትተን ከድህነት ጋር እንዋጋ፡፡ እየሰራን እልፍ እንበል፡፡ ከፊት እልፍ አለና፡፡
ReplyDeleteYealemegezatin tikim yeminayew endezih ayinetun asekaki neger sinanebina sinisema new. Thank you for sharing this to us!
Oh! min aynet simet yifetral!!! betikuroch lay yetefetsemew gif(ijjig asazagn, aslekash,....enja!), zarem yaltadeluna yihen gif merredat yalchalu afrikawuyan meriwoch yihen gif berasachew hizb lay iyyefetsemu barinetun ketilewbetal(hasabin benetsanet alemeglet, be netsanet alemederajet, benetsanet alemesrat ,...wannaw yesewnetachin akal behonew be "A'IMIRO" lay yetaweje barinet new. Sile ADWA sasib ye abbatochachinina ye innatochachin tegadlo, Sile Ethiopia YE KIDDUSAN TSELOT inna YE EGZI'ABHEER IKID BE ETHIOPIA,...ijjig idenekalehu. ye ahunochu , BETELEY ye HAYMANOT, INNA YE HAGER MERIWOCHACHIN ASTESASEBIM yigermal! እስቲ ለማንኛውም ወገን እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛልና በርትተን ከድህነት ጋር እንዋጋ፡፡ እየሰራን እልፍ እንበል፡፡ ከፊት እልፍ አለና፡፡ ...Dn Daniel, EGZI'ABHEER YABERTAH!
ReplyDelete'DOOR OF NO RETURN'- NOW BECOMES 'DOOR OF RETURN'
ReplyDeleteWATCH THE VIDEO CLIP BELOW
http://www.youtube.com/watch?v=mX3AVaZB9Rg
KALE HIWOT YASEMALIN DN. DANIEL
yasazinal tarikacew. igna Ethiopiawiyan Iwunetim ye Dingil Mariam ye Asrat Lejoci nen. yihen hulu alayenim. Ye Dingil Mariam Lej Yikber Yimesgen!!!
ReplyDeletewud wendime D.n Daniel Ijocih Yibareku!!!