Tuesday, April 5, 2011

ኮኮነት


ከአዲስ አበባ ወደ ሐራሬ እየተጓዝኩ ነው፡፡ ከጎኔ አንደ ደቡብ አፍሪካዊ ተቀምጧል፡፡ እርሱ ከአዲስ አበባ ወደ ሉሳካ በሐራሬ በኩል የሚጓዝ ነው፡፡ ሲያነበብበው የነበረውን መጽሔት ተዋስኩትና ማገላበጥ ጀመርኩ፡፡
አያሌ ማስታወቂያዎች ቀልብ በሚስቡ መንገድ ተደርድረዋል፡፡ መቼም ደቡብ አፍሪካውያን ማስታወቂያ መሥራት ያውቁበታል አልኩ በልቤ፡፡ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ኬፕታውንን ስጎበኝ ያየሁትን የቮዳፎን ካምፓኒ ማስታወቂያ አስታወሰኝ፡፡ በተራራማዋ የኬፕታውን ከተማ ሐል የቴሌፎን ካምፓኒው ቮዳፎን ‘’this is cape town, where the clouds cover the mountains, and we cover the rest’’ ይል ነበር ማስታወቂያው፡፡ «እነሆ ኬፕታውን፣ ተራሮቿን ደመናዎች ይሸፍኗታል፤ እኛ ደግሞ ሌላውን እንሸፍናለን» እንደ ማለት፡፡
 ቮዳ ፎን አዲስ አበባ ላይ ቢሆን ኖሮ የሚሰቅለውን ማስታወቂያ አስቤ ለብቻዬ ሳቅሁ፡፡ «የቴሌኮ ሙኒኬሽን አገልግሎት ለሁሉም በማዳረስ የኢትዮጵያን ሕዳሴ እናበሥራለን» ነበር የሚለው፡፡ ለምንድን ነው? ቢሉ መፈከር እንጂ ማስታወቅ አንችልበትምና፡፡ ድሮስ ስንፈክር ስናቅራራ አይደል የኖርነው፡፡ «አስታወቁ» ብለን ዜና እንሠራለን እንጂ መቼ አስታውቀን እናውቃለን? «ድርጅታችን ካለፈው ዓመት ይበልጥ እመርታ አሳይቷል» ብሎ መግለጫ የሰጠን ድርጅት «ባለፈው ዓመት ስንት ነበራችሁ? ዘንድሮስ ምን ያህል ጨመራችሁ ብለው ይጠይቁታል እንጂ ያላስታወቀውን «አስታወቀ» ብለው እንዴት ዜና ይሠሩለታል? አንዳች ነገር ሳያስታውቁ «አስታወቁ» ተብሎ ዜና የሚነገርባት ሀገር ስሟ ማነው?
ይሄንን ሁሉ እያሰብኩ ወደ መጽሔቱ ሆድ ስዘልቅ እያዘንኩ መጣሁ፡፡ የማያቸው ድርጅቶች ሁሉ የእንግ ሊዝ ወይንም የአሜሪካ እንጂ የደቡብ አፍሪካ አልመስልህ አሉ፡፡ስማቸው ሁሉ ፈረንጅ ፈረንጅ ሸተተኝ፡፡
ወደዚያ የደቡብ አፍሪካ ወዳጄ ጠጋ ብዬ «ምነው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አፍሪካዊ ስም የለም እንዴ አልኩት እንደ መሳቅ ብዬ፡፡
«ምን ይደረግ ኮኮነቶች ናቸው እንዲህ የሚያደርጉት» አለኝ ራሱን እየነቀነቀ በቁጭት፡፡
«ኮኮነቶች?!» አልኩ ለራሴ፡፡ እኔ ኮኮነትን የማውቀው በዘርነቱ ነው፡፡ የማወቅ ጉጉቴ ጨመረ፡፡
«ምን ማለትህ ነው ኮኮነቶች ስትል» አልኩት መጓጓቴ እንዳይታወቅብኝ ዘና ብዬ፡፡
«እኛ ውጫቸው አፍሪካዊ ሆኖ ውስጣቸው ፈረንጅ የሆኑትን ሰዎች ኮኮነት እንላቸዋለን፡፡ ኮኮነት ላዩ ጥቁር ወይንም ቡናማ ነው፡፡ ውስጡ ግን ነጭ ነው፡፡ እነዚህም ሰዎች መልካቸው ብቻ ነው አፍሪካዊ፡፡ ሌላው ነገራቸው ሁሉ ፈረንጅ ነው፡፡ የሚያስቡት እንደ ፈረንጅ፣ የሚዘፍኑት እንደ ፈረንጅ፣ የሚለብሱት እንደ ፈረንጅ፣ የሚጠሩት እንደ ፈረንጅ፣ በዓል የሚያከብሩት እንደ ፈረንጅ፣ መሆን የሚፈልጉት ፈረንጅ፣ ሁሉ ነገራቸው ፈረንጅ ነው፡፡»
«ምናልባት ዘመናዊነትን ፈልገው ከሆነስ? መቼም ፈረንጆቹ የተሻለ ሥልጣኔ እና የአኗኗር ሥርዓት አላቸው»
«አየህ መፈርነጅ እና መዘመን ይለያያሉ፡፡ መዘመን ማለት ከማንም ካንተ ከሚበልጥ ሰው የዕድገቱን እና የሥልጣኔውን መንገድ ማወቅ እና መከተል ማለት ነው፡፡ መፈርነጅ ግን ሌላ ነው፡፡ መፈርነጅ ማለት ቢጠቅምም ባይጠቅምም፣ ቢኖርህም ባይኖርህም፣ ካንተ ጋር ቢስማማም ባይስማማም የፈረንጅ የሆነውን ሁሉ መውደድ እና መከተል ማለት ነው፡፡
«እይ እስኪ የኛ ሰዎች የወንድ ለወንድ እና የሴት ለሴት ጋብቻን እንደ መብት የሚያዩት ሥልጣኔ ነው ብለው ይመስልሃል? ለአፍሪካስ ምን የሚፈይድላት ነገር አለ? እነዚህ አፍሪካውያን ወገኖቻችን ይህንን ነገር የሚከተሉት መፈርነጅ ስለሚፈልጉ ብቻ ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ለስም የሚሆን ነገር ጠፍቶ ነው /ቤቶቻችን፣ ምግብ ቤቶቻችን፣ መደብሮቻችን፣ ልጆቻችን፣ በፈረንጆቹ ስም የሚጠሩት? ይህን በማድረግ ምን ዕድገት ይመጣል? ይህንን ዘመናዊነት ትለዋለህ? ይህኮ መፈርነጅ ነው፡፡ኮኮነትነት ነው»
ይኼኔ ወደ አገሬ በሃሳብ በረርኩ፡፡ ኒውዮርክ ካፌ፣ ዴንቨር ሬስቶራንት፣ ሲያትል ፀጉር ቤት፣ አትላንታ ጠጅ ቤት፣ ሎንደን ካፌ፣ ፓሪስ ጫት ቤት፣ ፍራንክፈርት /ቤት፣ ኦሐዮ ጫማ ቤት፣ ኦክስፎርድ ዐጸደ ሕፃናት፣ ክሊንተን ቡቲክ፣ ሎስ አንጀለስ የድለላ ሥራ፣ ዋሽንግተን ሆቴል፣ ቡሽ አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ፣ ሆላንድ የመኪና መሸጫ፣ ቤልጅየም ሙዚቃ ቤት፣ ጣልያን ስቴሽነሪ፣ እያሉ የሰየሙት ወገኖቼ ታወሱኝ፡፡ ለካስ ኮኮነት እኛም ሀገር አለ፡፡
አሁን እነዚህ ወገኖቻችን ትንቧለል ሻሂ ቤት፣ መንዲ ምግብ ቤት፣ ገደል ግቡ ጠጅ ቤት፣ አያሌው አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ፣ ከርክሜ ፀጉር ቤት፣ የነገዋ ኢትዮጰያ /ቤት፣ ሰላም ዐጸደ ሕፃናት፣ ዳንዲ ቦሩ /ቤት፣ ዘናጩ ቡቲክ፣ አዲስ አበባ የምግብ አዳራሽ፣ አድዋ የመኪና መሸጫ፣ ካራማራ ሙዚቃ ቤት፣ ብራና የጽሕፈት መሣርያዎች መሸጫ፣ ታማኙ የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ እያሉ ከሰየሙት ሰዎች ይልቅ ሠልጥነዋል ማለት ነው? ወይስ ፈርንጀዋል?
ኒኒ፣ ጂጂ፣ ጲጲ፣ ቲቲ፣ ኪኪ፣ ቢቢ፣ ፊፊ፣ ኤፍ፣ ዜድ፣ እየተባሉ የሚጠሩትስ እናኑ፣ ትዕግሥት፣ እጅጋየሁ፣ መገርሳ፣ ትርሐስ፣ ኦጂሎ፣ ኪሾ፣ ከሚባሉት ስሞች በላይ ዘምነዋል ማለት ነው? አሁን የእነዚህ ሰዎች ሥራ ኢትዮጵያን እያዘመናት ነው እያፈረነጃት? አንዳንዶችማ እነርሱ ፈርንጀው ውሻዎቻቸውንም አፈርንጀዋቸዋል፡፡
ከሐበሻ ገና የፈረንጅ ክሪስማስ ማክበር የሚቀናቸው፣ ከሐበሻ አቆጣጠር የፈረንጅ ካላንደር የሚመቻቸው፣ «እንትናዬ ድረስ» «የፈጣሪ ያለህ» ከማለት ይልቅ « ማይጋድ» ሲሉ የዘመኑ የሚመስላቸው፡፡ «ኢየሱስ» ብለው ከሚጠሩ «ጂሰስ» «እግዜር ይስጥልኝ» ከሚሉ «thank you´ ቢሉ የሚቀናቸው ኮኮነቶች መጡብኝ፡፡
የገና ዕለት ዳቦ የማይደፉ፣ ነገር ግን ከቀረችን 3% ዛፍ ቆርጠው የገና ዛፍ የሚሠሩ፤
«የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው፣
በእንግሊዝ አናግሪያቸው» እያሉ የሚዘፍኑ፤ ሀገር ቤት ተቀምጠው «ልጄኮ ኦሮምኛ አይችልም፣ እንግሊዝኛ ብቻ ነው የሚናገረው» ብለው በድፍረት ሲናገሩ ኀፍረት የማይሰማቸው፤
የጋዜጣቸው ስም፣ የመጽሔታቸው ስም፣ የኤፍ ኤማቸው ስም፣ የሬድዮ ፕሮግራማቸው ስም፣ የሙዚቃ አልበማቸው ስም፣ የፊልማቸው ስም፣ የቆርቆሯቸው ስም፣ የቢራቸው ስም፣ የደብተራቸው ስም፣ የማስተ ካቸው ስም፣ የከረሚላቸው ስም፣ በፈረንጅኛ ካልሆነ የማይረኩት የኛዎቹ ኮኮነቶች ታወሱኝ፡፡
መፈርነጅ ካልሆነ በቀር አሁን በምን መለኪያ ነው «ባለ ሥልጣን» ከሚለው ይልቅ «ኤጀንሲ» «የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን» ከሚለው ይልቅ «ኢትዮ ቴሌኮም» መሠልጠን የሚሆነው? ከኢትዮጵያ ጋራዎች ኩልል ብሎ የሚወርደውን ውኃ እያሸጉ «ብራቦ» «ፋንታስቲክ» «አኳ ምናምን» «ሎው ላንድ ዋተር» እያሉ ውኃው ሰምቶት የማያውቀውን ስም የሚያወጡትን ኮኮነቶች አድባሯስ ምን ትላቸዋለች?
እንጂ አሁን ማን ይሙት «ደብር» ከሚለው ይልቅ «ካቴድራል» የሚለው በምን በልጦ ነው ያለ ቦታው ድንቅር ብሎ መከራ የሚያየው፡፡ አድባራቱ ሁሉ ካቴድራል ለመባል መከራ የሚያዩት የፈረነጁ መስሏቸው እንጂ ዘመናዊነት ቢያምራቸውማ የገንዘብ አያያዛቸውን፣ የሠራተኛ አስተዳዳራቸውን፣ የንብረት አያያዛ ቸውን፣ የቅርስ አጠባባቃቸውን፣ የምእመናን አገልግሎታቸውን፣ የሰዓት አከባበራቸውን አያሻሽሉትም ነበር፡፡ አይ ኮኮነት?
«እማዬ» «አባዬ» ከሚለው ስም ይልቅ «ማዘሬ» «ፋዘሬ» በምን በልጦ ነው ያገር ቋንቋ እስኪመስል ድረስ የተዋሐደን? ኮኮነትነት ካልሆነ በቀር?
በቀደም ቤት ልከራይ አንድ ቦታ ሄድኩላችሁ፤ ከደላሎቹ ጋር ተስማምተን ባለቤቶቹን ቀጥረን አገኘናቸው፡፡ ሰውዬው በግልጽነታቸው አመሰግናቸዋለሁ፡፡
«ይቅርታ አድርጉልኝ፣ ቤቴን ለአበሻ አላከራይም» አሉን፡፡
«ለምን» አልኳቸው ገርሞኝ፡፡
«ቤቴን በደንብ የሚይዝልኝ ፈረንጅ ነው» አሉ በድፍረት፡፡
«እንዴት መያዝ እንዳለበት የሚያስቡትን ይንገሩኝና በውላችን ውስጥ እናካትተው፤ ደግሞስ ሁሉም አበሻ በሙገባ አይዝም ሁሉም ፈረንጅ በሚገባ ይይዛል ብለው እንዴት ይደመድማሉ? ለመሆኑ ስለ እኔ ቤት አያያዝ ምን ያውቃሉ ብዬ አፋጠጥኳቸው፡፡
በመጨረሻ እንዲህ አሉኝ «ለታሪኬም ቢሆን ቤቱን ለአበሻ አከራየ ሲባልና ለፈረንጅ አከራየ ሲባል ክብሩ አንድ ዓይነት አይደለም» አሉና ኮኮነቱን ከተደበቀበት አወጡት፡፡
ምን ያድርጉ «አቶ እገሌን፣ወ/ እገሊትን ተዋወቋቸው፣ ልጆቻቸው ሁሉ አሜሪካ ናቸው» ሲባልላቸው በደስታ እና በኩራት ፈገግ በሚባልባት ሀገር ቢያንስ «አቶ እገሌኮ ቤታቸውን ለፈረንጅ አከራዩት» ይባልላቸው እንጃ!!
«ሰሞኑን ጃፓኖችን አይተሃቸዋል? የጃፓን ባለ ሥልጣናት ስለ አደጋው መግለጫ ሊሰጡ ወደ መድረክ ሲወጡ መጀመርያ ለሰንደቅ ዓላማቸው ቀጥሎ ለሌሎች ከወገባቸው ዝቅ ብለው ሰላምታ ይሰጣሉ፡፡ ያን ጊዜ መግለጫ የሚሰጡት ጃፓኖች መሆናቸውን ጆሮህ ባይሰማ እንኳን ታውቃለህ፡፡ አሁን ያንን የሚያህል የኒኩሌር ተቋም እኛ ገንብተን ቢሆን ኖሮ እንደ እነርሱ «ፉኩሺማ» እንለው ነበር? ወይ ከአሜሪካ ወይም ከእንግሊዝ ስም እናስመጣለት ነበር እንጂ?
ይህንን ሲናገር የበረራ አስተናጋጇ መጣችና «ምሳ ምን ልስጣችሁ አለችን፡፡
«የጾም ምን አላችሁ?» አልኳት፡፡
«ምንም የለንም» አለች፡፡
«አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው፤ ዐቢይ ጾም የታወቀ ጾም ነው፤ ምናለ ሁለት ሦስት እንኳን የጾም ምግብ ቢይዙ? አሁን ይህንን አሠራር ምን ልበለው? ደቡብ አፍሪካዊ የተናገረኝ መጣብኝና ከአፌ መለስኩት፡፡
ሐራሬ፣ ዚምባብዌ

54 comments:

 1. Ye zemenu sebakian ke netela yilk ye ferenji kemis yemiatelkut coconut honu maletim ayidel?

  ReplyDelete
 2. Daniel

  Thank you, at least I feel good when I read this kind of article. One day we will come to the media all with this idea and build our country. I believe like this, Eradicating poverty is one day job, but building identity will take hundreds year.

  ReplyDelete
 3. wey dani... really immpressive and touching. But what I am saying is that how can we make change even we (the one understand the problem). You are doing your part for your motherland so please arrange some mechanism for others who understand the problem and who are ready for action.

  ReplyDelete
 4. selam dani this is good views in our country there are millions of ኮከነት starts from top level managers to childrens

  ReplyDelete
 5. መፈከር እንጂ ማስታወቅ አንችልበትምና፡፡ ድሮስ ስንፈክር ስናቅራራ አይደል የኖርነው፡፡
  የጃፓን ባለ ሥልጣናት ወደ መድረክ ሲወጡ መጀመርያ ለሰንደቅ ዓላማቸው ቀጥሎ ለሌሎች ከወገባቸው ዝቅ ብለው ሰላምታ ይሰጣሉ፡

  ReplyDelete
 6. Dani what a nice article!! yemigerm new! you've a very distinct and unique way of looking at things. keep it up! There isn't a day that i don't open this page when i use the internet! i love your articles!

  ReplyDelete
 7. Ere belewu... 'eradicating poverty is one day job...' ho..ho.. bel Abaye endaysemahe...

  ReplyDelete
 8. የናዝሬቱ(Ze-Nazareth)April 5, 2011 at 3:43 PM

  ዘመናዊነት፣ሥልጣኔ እና ፈረንጅን መምሰል መካከል ያለውን ልዩነት እስካላወቅን ደረስ ችግሩ መቀጠሉ አይቀርም፡፡
  እኔ እንደሚመስለኝ ሌሎች አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ምክንያት የማንነት ቅውስ ውስጥ ሲገቡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዓለም ላይ ወደን እና ፈቅደን ክርስትናን በራሳችን ጥያቄ የተቀበልን ብቸኛ ሀገር የመሆናችንን ያህል ወደንና ፈቅደን ማንም ሳያስገድደን የማንነት ቀውስ ውስጥ የገባን ብቸኛ ሀገር የምንሆን ይመስለኛል፡፡
  መገናኛ ብዙኃን፣ ትምህርት ቤቶቻችን፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ወዘተ … በሙሉ ለዚህ ችግር ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ አብዛኛው ሕብረተሰብ ስለችግሩ ብዙም ግንዛቤ ያለው አይመስለኝም፡፡ እንዲያወም መልካም ያደረግ ሁሉ ነው የሚመስለው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችን እንግሊዝኛ ካልሆነ በስተቀር መናገር የሚከለከልባቸው እየሆኑ ነው፡፡
  ወርቅነሽ፣ አያንቱ፣ ቦንቱ በሚል ስም የሚጠሩ ተማሪዎች በስማቸው እስከማፈር የደረሱበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ እኔ በማስተምርበት አንድ ኮሌጅ ውስጥ በትምህርታቸው ጎበዝ የነበሩ ሁለት ሴት ተማሪዎች መመረቂያ ዓመት ላይ ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም ቀይረው ሔለን እና ሮዛ ተብለዋል፡፡ ዘመናዊ መሆናቸው ነው፡፡
  ስለዚህ የያዘን የፈረንጅነት አባዜ ሥር እየሰደደ ስከሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ሰፋ ያለ የውይይት መድረክ ብታዘጋጅ እና መሆን ያለበትንም ብታመላክተን ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
  ቸር ይግጠመን
  ዘመናዊነት፣ሥልጣኔ እና ፈረንጅን መምሰል መካከል ያለውን ልዩነት እስካላወቅን ደረስ ችግሩ መቀጠሉ አይቀርም፡፡
  እኔ እንደሚመስለኝ ሌሎች አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ምክንያት የማንነት ቅውስ ውስጥ ሲገቡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዓለም ላይ ራሳችን ወደን እና ፈቅደን ክርስትናን በራሳችን ጥያቄ የተቀበልን ብቸኛ ሀገር የመሆናችንን ያህል ወደንና ፈቅደን ማንም ሳያስገድደን የማንነት ቀውስ ውስጥ የገባን ብቸኛ ሀገር የምንሆን ይመስለኛል፡፡
  መገናኛ ብዙኃን፣ ትምህርት ቤቶቻችን፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ወዘተ … በሙሉ ለዚህ ችግር ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ አብዛኛው ሕብረተሰብ ስለችግሩ ብዙም ግንዛቤ ያለው አይመስለኝም፡፡ እንዲያወም መልካም ያደረግ ሁሉ ነው የሚመስለው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችን እንግሊዝኛ ካልሆነ በስተቀር መናገር የሚከለከልባቸው እየሆኑ ነው፡፡
  ወርቅነሽ፣ አያንቱ፣ ቦንቱ በሚል ስም የሚጠሩ ተማሪዎች በስማቸው እስከማፈር የደረሱበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ እኔ በማስተምርበት አንድ ኮሌጅ ውስጥ በትምህርታቸው ጎበዝ የነበሩ ሁለት ሴት ተማሪዎች መመረቂያ ዓመት ላይ ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም ቀይረው ሔለን እና ሮዛ ተብለዋል፡፡ ዘመናዊ መሆናቸው ነው፡፡
  ስለዚህ የያዘን የፈረንጅነት አባዜ ሥር እየሰደደ ስከሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ሰፋ ያለ የውይይት መድረክ ብታዘጋጅ እና መሆን ያለበትንም ብታመላክተን ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 9. I like this article D/n Daniel! "አሁን ማን ይሙት «ደብር» ከሚለው ይልቅ «ካቴድራል» የሚለው በምን በልጦ ነው ያለ ቦታው ድንቅር ብሎ መከራ የሚያየው" The same reasoning goes to the word "Orthodox". Ethiopian Tewahedo Church would have been enough!

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ ያልከው ሁሉ ትክክል ነው እኛ ሃበሾች የሚያኮራ ባሕል እና ቋንቋ እያለን ለምን የሰው እንደምንቀላውጥ አይገባኝም በራሳችን ማፈር የለብንም ራሳችንን ስናከብር ነው ሌሎች የኛን ባህል እና ቋንቋ የሚያከብሩልን አሁን አሁንማ ባሕላችን በዘመናዊ ነገሮች እየተዋጠ ሊጠፋ ስለሆነ ዘመነኞች ቢያስቡበት ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 11. its an idea that goes through my head a lot well we are leaving and trying our best to forget our identity we donot figure out what to take from the westerns and what to leave thats why we always look them above us. "coconut" best expression thanks.

  ReplyDelete
 12. "ለካስ ኮኮነት እኛም ሀገር አለ፡፡" ኦ ዳኒ በጣም ደስ ይላል በጣም ይገባል ያሳምናል እግዚአብሔር እንዳንተ የኛን ልብ እና አይን ያብራልን እግዚአብሔር ይስጥ ደስ ያለ በጣም ኦ

  ReplyDelete
 13. አሁን እነዚህ ወገኖቻችን ትንቧለል ሻሂ ቤት፣ መንዲ ምግብ ቤት፣ ገደል ግቡ ጠጅ ቤት፣ አያሌው አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ፣ ከርክሜ ፀጉር ቤት፣ የነገዋ ኢትዮጰያ ት/ቤት፣ ሰላም ዐጸደ ሕፃናት፣ ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት፣ ዘናጩ ቡቲክ፣ አዲስ አበባ የምግብ አዳራሽ፣ አድዋ የመኪና መሸጫ፣ ካራማራ ሙዚቃ ቤት፣ ብራና የጽሕፈት መሣርያዎች መሸጫ፣ ታማኙ የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ እያሉ ከሰየሙት ሰዎች ይልቅ ሠልጥነዋል ማለት ነው? ወይስ ፈርንጀዋል?

  ReplyDelete
 14. Thanks for your building ideas, long live to this blog!!!

  ReplyDelete
 15. D.Daniel thank you.before your article , i think about why the government name the new & great dam 'milliniam dam' . YOSEPH ZEDEBREMITMAK

  ReplyDelete
 16. "አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው፤ ዐቢይ ጾም የታወቀ ጾም ነው፤ ምናለ ሁለት ሦስት እንኳን የጾም ምግብ ቢይዙ? አሁን ይህንን አሠራር ምን ልበለው? ያ ደቡብ አፍሪካዊ የተናገረኝ መጣብኝና ከአፌ መለስኩት፡፡ " የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጾም ምግብ የለም ብሎ እኔንም ከዲሲ አዲስ አበባ በደንብ 'አጹሞኛል'።

  ReplyDelete
 17. በጣም ጥሩ መል እክት ነው ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  ከዚህ በታች ያለውን የቪድዮ ሊንክ ይክፈቱት:: በጣም ተመሳሳይ መልዕክት ያገኙበታል።
  http://www.diretube.com/bela-lebeleha/short-holiday-drama-part-1-video_de13bed14.html

  ReplyDelete
 18. ሆ ሆ ሆ ሆ...

  “ከአሜሪካ ወይም ከእንግሊዝ ስም እናስመጣለት ነበር እንጂ...” ስትል “የምለኒዬም ግድብ” የተባለው የሰሞኑ የአባይ ግድብ አሰያየም ግርም አለኝ:: ወይ አባይ ስንቱ የሀገሬ አቀንቃኝ አታሞ እየመታ እንዳልደለቀልህ አሁን ስም ላንተ ግድብ የጥፋ? ምናለ አንዱን የብርቡዋክስ አዝማሪ ቢያማክሩ?

  “እማዬ” ሰትላቸው ዕድሜዬን ማን አባክ ቁጠር አለህ ብለውህ ያበቁና “ማዘር” ይቅርታ ስትላቸው ወዲያው መለስ የሚሉትሳ?

  “ለልጆቼ ብዬ” ብለው ልጅ አሜሪካን ሃገር ሄደው የሚወልዱትንስ ምን ትላቸዋለህ? አለመታደል ሆኖባቸው እንጂ ለድንግል ማሪያም አሥራት በሆነች ቅድስት ሀገር መውለድ በስዕለትም አያገኙትም ነበረ::

  ቋንቋማ “ውጪ ሲሄዱ እንዳይቸገሩ ብዬ ነው” ብሎ እንግልዘኛ ማስተማር ከተጀመረ እኮ ቆየ? አባት ልጁን እንደፈለገው ማሳደግ መብቱ ቢሆንም ከማኅበረሰቡ እንዲያፈነግጥ አድርጎ ማሳደግ ግን በታሪክ ከማስዋቀስ አልፎ ለታዳጊው/ጊዋ ልጅ የነገ የማንነት ጥያቄ አፍ የሚያስይዝ ነው::

  «አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው፤ ዐቢይ ጾም የታወቀ ጾም ነው፤ ምናለ ሁለት ሦስት እንኳን የጾም ምግብ ቢይዙ? አሁን ይህንን አሠራር ምን ልበለው? ያ ደቡብ አፍሪካዊ የተናገረኝ መጣብኝና ከአፌ መለስኩት፡፡

  አይ ዳንኤል “ፋስትንግ ፉድ” ብትላቸው ያመጡልህ ነበረ: ችግሩ አንተ በኮከኔትኛ ማዘዝ አቅቶህ ነው:: ቂቂቂ...

  “ኒውዮርክ ካፌ፣ ዴንቨር ሬስቶራንት፣ ሲያትል ፀጉር ቤት፣ አትላንታ ጠጅ ቤት፣ ሎንደን ካፌ፣ . . . ለካስ ኮኮነት እኛም ሀገር አለ፡፡” ምን ያድርጉ ልጆቻቸው ከተጠቀሱት ሀገሮች የጥገኝነት ኑሯቸውን እየመሩ ናቸዋ? ማን ይሙት አዲስ አባባ ላይ እምድብር ምግብ ቤት፣ ከረዩ የገብያ አዳራሽ፣ አፋር የጽህፈት መሳሪያ. . . ብሎ ሰይሞ ምንም ሳይሸጥ ይዋል እንዴ?

  ሰለ ማስታወቂያው በጥቅሉ ብዙ ማለት ይቻላል:: በየተሌቪዢን መስኮቶች የሚቀርቡትን እያንዳንዱን ማስታወቂያዎች እንኳን ብንመለከት እንግሊዘኛ ካልተቀላቀለበት ምሉዕ አይደለም የተባሉ ይመስል ሕዝቡን የሚያደናግሩ ስንቱን እያስተዋልን አይደል:: በቤታቸው “mood” መፍጠራቸው ነው:: ጋዘጠኞቻችንሳ ቃለ መጠይቅ ሲያቀርቡ ግማሹን በእንግልዘኛ ሲገፉት ይውሉ የሌ? በሚያለሙትና በሚሰሩት ጥሩ ሥራ ‘እሰይ ደግ አደረጋችሁ’ እንደምንላቸው ሁሉ ሲያጠፉም ‘አጥፍታችኋል አስተካክሉ’ ብንላቸው መልካም ነው:: ሰምተው ከተገበሩት እናመሰግናቸዋለን ‘እምቢ አሻፈረኝ’ ካሉ ግን ቢያንስ ህሊናችን ነጻ ነው፤ እስኪስተካከል ግን ዝም አንበል::

  ቅርብ ጊዜ አንድ የጤና ዶ/ር “ጤናዎ በቤትዎ” በሚል የተሌቪዢን ስርጭት ላይ ስለ ጆሮ ንጽህና ሲያስረዱ ኩክ በጥጥ መጥረግ አንዳንዴ ጎጂ ሊሆን ይችላል ብለው ሙያዊ ማብራሪያ ይሰጣሉ:: አንዱ ደወለና ኩክ የምትለው “ዋክስ” ለማለት ፈልገህ ነው ወይ ይላቸዋል:: እርሱ ቋንቋውን የበለጠ አዋቂ መሆኑ ነው:: አላዋቂነቱን ግን በአደባባይ ለእኛ ነገረን እንጂ፤ የዶ/ሩ አመላለስ ግን ደስ የሚል ነበረ:: አንተ የጠየቅከኝ ስለ አማርኛ እንጂ ስለ ጤና አይደለም ነበር ያሉት:: ምንም እንኳን መሰልጠን ተገቢ እና ቋንቋን ማወቅ የሚደገፍ ቢሆንም አጠቃቀሙን አለማወቅ ግን ዝቅጠት ነው::

  ራስን ማወቅ እና ሙያን በአግባቡና በተገቢው ቦታ መጠቀም እንዳለብን ተምሬበታለሁ ይህንን ጽሁፍህን:: ኮለኔል መንግስቱን ግን ሰላም ብለህልኝ በሰላም ወደ ሃገርህ ተመለስ::

  ReplyDelete
 19. haki bhaki dn daniel

  ReplyDelete
 20. dn daniel thank you, this is exactly what is going in africa. We are still colonizing by white mind and cultures. And most of us are not pride in our identity.
  God bless u.
  Abiy

  ReplyDelete
 21. ወይ ኮኮናት!!…..በጣም የሚመስጥ ፅሁፍ ነው። እኔ ሁልጊዜ የሚገርመኝ ነገር ነበር ይህ በማንነት አለመኩራት ታዲያ ይህ ኮኮናት የልቤን ነገረልኝ።

  በስተመጨረሻ ሰለ ጾም ምግብ ያነሳኸው ደግሞ አንድ ነገር አስታወሰኝ. . . እዚህ ባለሁበት ሀገር አንዱ ሀበሻ ሪስቶራንት አለው። ልጁ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነው። በአገልግሎቱ ትልቅ ቦታ ያለው ነው። እና አንድ ጓደኛዬ መንገድ ተገናኝተን ምሳ ካልበላን አለኝ ከዛማ ተያይዘን ወደሱ ሪስቶራንት አመራን እለቱ አርብ ቀን ነበር … ምሳ ልናዝ ስንል የጾም ምግብ የለም ሲለን…ድንግጥ ነበር ያልኩት ምክንያቱም ካሉት ሪስቶራንት መርጠን ወደዛ ያመራነው። ከሌሎቹ ይልቅ እርሱ ጋር እናገኛለን ብለን ነበር። ጓደኛዬ በጣም አዝኖ እዚያ ቤተክርስቲያን ቅጥር ውስጥ ብቻ መስበክ ምን ዋጋ አለው እንዲህ አይነት ቦታ ላይ በግልጽ መስበክ ሲቻል አለ……….ግን እውነት ነው ማንነታችንን ባህላችንን ሀይማኖታችንን እንደ ተራ ነገር እንድናየው ውስጣችን የገባ አዚም አለ።

  አንዴ እማልረሳው አንድ ሰባኪ ስለማንነታችን ሲያስተምር “..ልጅ ሆነን ይኼ እኮ ከውጪ የመጣ ጫማ ነው፣ ልብስ ነው እየተባልን ይህንን እየሰማን ስላደግን የውጪ የውጪ ነገር እንዲህ መውደዳችን..” ያለው። እውነት አለው ኢትዮጵያ ከተሰራ ልብስ ይልቅ የውጪ ነገር አስጠሊታ ቢሆንም እሱን እንመርጣለን።

  ግን ይኼ አዚም እንዴት ይሆን የሚቆመው…?ምናልባት የኛ ትውልድ አልፎ ለልጆቻችን ስለታሪካችን እና ሰለማንነታችን እየነገርን ካሳደግናቸው የነሱ ጊዜ ትውልድ ሁሉን ይቀይረው ይሆናል።

  ReplyDelete
 22. God Bless you, Good observation.

  ReplyDelete
 23. ዳንኤል፦ ለኢትዮጵያዊነት፤ ለባህላችን፤ ለቋንቋችን፤ ለታሪካችን እንኳን እኛ አውሮፓውያኑ ክብር ይሰጡት ነበር። 40 ዓመት ባልሞላው ጊዜ የ3ሺ ዓመት ቅርስ በመዘመን ስም አመንምነን ድራሹ ሊጠፋ ነው። በጉራማይሌ ስንጥለቀለቅ፤ የገደል ማሚቶነትን የመዘመን ተቋማዊ መላ ሲሆን እየተመለከትን ዝም ማለታችን ይሄን ነገር አባብሶት ይገኛል። አንበሳና የሜዳ አህያ አብረው ቢቦርቁ ሲርበው አንበሳው ሣር አይግጥም እኮ! አጉል መፈርነጅ ለኛም እንዲሁ ከእሳት ጋር መጫወት እንዳይሆንብን።

  ReplyDelete
 24. Dear Daniel,

  I have thoroughly read your article and benefited a lot. From linguistics point of view, this is what code mixing means. It is used for self pride and pristige. Besides, it is a habit. Therefore, we Ethiopians should struggle to keep our varied heritages.
  «እማዬ»፣ «አባዬ» ከሚለው ስም ይልቅ «ማዘሬ»፣ «ፋዘሬ» በምን በልጦ ነው ያገር ቋንቋ እስኪመስል ድረስ የተዋሐደን?

  ReplyDelete
 25. Thank you. Dn.Daniel,

  Tiru Eyita new.
  Be Addis Ababa Yemigegnu Yegil Timihirit betoch Ye Coconut Fabrica eyehonu new.Timhirit bet wist agerigna kuankua sinager yetegegne hitsan yemiketabachew t/betoch alu.Welajochim yelijachew yehagerigna kuankua chilota bizum ayasegachewim. Engilizigna menager tekami bihonim gin endezina yikoteral.Yihe degmo mulu bemulu wedemefernej yemiket new.Yenezih t/betoch temariwoch yeamarigna tiyatir,yeamarigna film,libweled telatachew new.Addisu tiwilid Yemanenet adega lay yale yimesleganl.

  ReplyDelete
 26. ርእሱ ኮኮነት ብሎ ሲዸምር እንዲህ ያለ እይታ አልመሰለኝም ነበር፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ምክንያቱም እኔ ሁልጊዜ እንዲህ ያለ ስም ሳይ ምን ዓይነት ስልጣኔ ነው እል ነበር ውስጤ በጣም ያዝናል፡፡ በተጨማሪም በመላእክት በቅዳሳን ስም ሲወጣ ያለቦታው ሲሆን፣ እንዲሁም የልዸች ስም፣ የእናት የአባት ስም አባባ እማማ የሚለው ጣፋጭ ስም ሲቀር ቅር ያሰኛል፡፡ ስለዚህ ሁሉም በአገሩ ስም ቢጠቀም ደስ ያሰኛል፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 27. ከዛሬ በሁዋላ እናቴን እማዬ እንጅ 'mother' ብዬ አልጠራትም ለካ በቁሜ ፈርንጃለሁ እናቴ ማሪኝ፡

  ReplyDelete
 28. «አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው፤ ዐቢይ ጾም የታወቀ ጾም ነው፤ ምናለ ሁለት ሦስት እንኳን የጾም ምግብ ቢይዙ? አሁን ይህንን አሠራር ምን ልበለው? coconut. i face with such phenomena and i feel afraid. they forget us and serving for the foreigners and...thanks Dani.

  ReplyDelete
 29. wey dan yemecheresha bebet ena chenkelat yemikorekur ngr nuw yetsafkew des yilal Egzeyabher yestelen ! alex

  ReplyDelete
 30. Dani this indirect colonization.
  you touch all those in the wrong truck.enam hulachnem yedershchnen enewsed.be proud of ours.
  Really you are insightfull person.

  Much respect

  Abel

  ReplyDelete
 31. I love reading your articles,they are really good

  ReplyDelete
 32. Daniel
  ye liben new ye tenagerkew egiziyabher kante ga yihun lenyam lebonan yesten

  ReplyDelete
 33. «ደብር» ከሚለው ይልቅ «ካቴድራል» የሚለው በምን በልጦ ነው ያለ ቦታው ድንቅር ብሎ መከራ የሚያየው፡፡ አድባራቱ ሁሉ ካቴድራል ለመባል መከራ የሚያዩት የፈረነጁ መስሏቸው እንጂ ዘመናዊነት ቢያምራቸውማ የገንዘብ አያያዛቸውን፣ የሠራተኛ አስተዳዳራቸውን፣ የንብረት አያያዛ ቸውን፣ የቅርስ አጠባባቃቸውን፣ የምእመናን አገልግሎታቸውን፣ የሰዓት አከባበራቸውን አያሻሽሉትም ነበር፡፡ አይ ኮኮነት?

  ReplyDelete
 34. D/Danie,
  I think it is the argent issue which really needs a solution. I remember Dr. Liykune was begging people to change “Blue Nile...” to Ghion or Abye. I would recommend this book for all your blog readers. The title of the book is

  "በሃይማኖት ካባ......ደባ" By Dr.Liykune Birhanue. Thanks

  ReplyDelete
 35. አፍሪካ ውስጥ ለስም የሚሆን ነገር ጠፍቶ ነው ት/ቤቶቻችን፣ ምግብ ቤቶቻችን፣ መደብሮቻችን፣ ልጆቻችን፣ በፈረንጆቹ ስም የሚጠሩት? ይህን በማድረግ ምን ዕድገት ይመጣል? ይህንን ዘመናዊነት ትለዋለህ? ይህኮ መፈርነጅ ነው፡፡ኮኮነትነት ነው»

  ReplyDelete
 36. «አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው፤ ዐቢይ ጾም የታወቀ ጾም ነው፤ ምናለ ሁለት ሦስት እንኳን የጾም ምግብ ቢይዙ?

  ReplyDelete
 37. ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎApril 7, 2011 at 9:48 AM

  ዲያቆን ዳንኤል ጥሩ አድርገህ ታዝበኸዋል። ግን ማን ይሆን ለዚህ ዓይነቱ ክስተት (ኮኮነትነት)ተጠያቂው? ኃላፊነቱን ሊወስድ የሚገባው የትኛው አካል ይሆን??? ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ተቋማት፣ መንግስት. . .እንደ እኔ አመለካከት ከእያንዳንዱ ግለሰብ ጀምሮ ሁሉም የየራሱ ድርሻ አለው።

  ReplyDelete
 38. ዲ/ን ዳንኤል ያልከው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ከውጭው ዓለም መውሰድ ያለብን የሚጠቅመንን ስልጣኔ ብቻ መርጠን ነው እንጂ ማንነታችንን፣ ባሕላችንን እና ቋንቋችንን የሚያሳጣን መሆን የለበትም፡፡ ሌላው ደግሞ የኢዮጵያ አየር መንገድ ነገር እኔም በጣም ይገርመኛል አየር መንገዱ እንዴት የጾም አንድ አይነት ምግብ እንኳን አያዘጋጅም ይሄ ራሱ ማንነትን መርሳት ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 39. Ethiopia it self is changing to "kokonat"

  ReplyDelete
 40. Dn. Daniel,

  Ayeh, bezih zemen and yalechin neger maninetachin neberech. Be'lieloch alemegezatachin yetekemen neger maninetachinin ena yalenin neger makoyet neber. Ahun gin, endemtayew new.

  Enies baygermih, yesim awotatachin( le lijochachin) sayker yanadidegnal. Metsaf Kidus lay silale bicha yelijie meteriya aladergewum. Eneziya simoch siwotu eko bewoktu yeneberewun hunet lemastawos new. Semonun hulum sew siet lijun Solyana malet azewutrual. Enie gin alismamam, ena min tilalachihu? Ethiopiawi sim hunetun yastawose bihon emertalehu.

  Egziabhier yistilign
  Bemelkam sirah ketilbet

  ReplyDelete
 41. It's great article. It made me to look myself again and again. I also blamed myself for some circumstances in the past.

  Keep writing Daniel such kind of articles. I wish if you can arrange conference or debating forums once in a year to address problem of identity crisis with in this generation.

  GOD bless you!

  ReplyDelete
 42. ምናልባት እንዲሁ በግምቴ (በሰገላዊ ጥናት ወይም በፍልስፍና ሳይሆን) ከአርባ ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ስደተኛ (በዘመኑ ዘይቤ diaspora ብለውናል) ኢትዮጵያውያን ልገልጽ የምፈልገውን ስሜት አይገባቸው ይሆን? የሚለው ጥያቄ በአዕምሮዬ ሲመላለስ ከቆየ ብዙ ዘመናት አልፈዋል። ይሄ ጥያቄ ግን እኔ ራሴ አርባ ዓመት ዕድሜዬን እስካለፍኩ ድረስ በአእምሮዬ አልተነሳም። አንተ በዚህ ‘ኮኮነት’ ባልከው ጽሑፍህ ላይ የኔን ስሜት በትክክል ስላስተጋባህልኝ እግዚአብሔር ይባርክህ።

  “ከሐበሻ ገና የፈረንጅ ክሪስማስ ማክበር የሚቀናቸው፣ ከሐበሻ አቆጣጠር የፈረንጅ ካላንደር የሚመቻቸው፣ «እንትናዬ ድረስ»፣ «የፈጣሪ ያለህ» ከማለት ይልቅ «ኦ ማይጋድ» ሲሉ የዘመኑ የሚመስላቸው፡፡ «ኢየሱስ» ብለው ከሚጠሩ «ጂሰስ»፣ «እግዜር ይስጥልኝ» ከሚሉ «thank you´ ቢሉ የሚቀናቸው ኮኮነቶች መጡብኝ፡፡
  የገና ዕለት ዳቦ የማይደፉ፣ ነገር ግን ከቀረችን ከ3% ዛፍ ቆርጠው የገና ዛፍ የሚሠሩ፤ …” እኔ ደግሞ አንድ ልጨምርበትና የወጥቶ-እብስ መሣፈሪያ ላይ ማቆሚያ/መሣፈሪያ ብሎ በቋንቋችን ከመጻፍ ይልቅ ከነአካቴው በሮማዊኛ፣ በትላልቁ BUS STOP ብሎ መጻፍስ ምን ይባላል። የሚጻፍለትስ ወጥቶ-እብስ ተሳፋሪ እንግሊዝኛ ካልቻለ መሳፈር አይችልም ማለት ነው?

  ባዕዳዊ ባህላት የራስችንን ሥርዓት ሲበክሉት፤ መሪዎቻችን ግንባር-ቀደም እየሆኑ የገደል ማሚቶነትን የመዘመን ተቋማዊ መላ ሲያደርጉት እየተመለከትን (አንዳንዳችንም በቁጭት ቆሽታችን እያረረ) ዝም ማለታችን ይሄን ነገር አባብሶት ይገኛል።

  ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎ "..ግን ማን ይሆን ለዚህ ዓይነቱ ክስተት (ኮኮነትነት)ተጠያቂው? ኃላፊነቱን ሊወስድ የሚገባው የትኛው አካል ይሆን??? ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ተቋማት፣ መንግስት. . .እንደ እኔ አመለካከት ከእያንዳንዱ ግለሰብ ጀምሮ ሁሉም የየራሱ ድርሻ አለው።" ብሎ በትክክል ገምግሞታል።

  የአንተም ድርሰት የስህተታችንን ዕርማት ጎዳና የሚያስጀምረን ስለሆነ ከላይ እንደተገለጸው
  አጉል መፈርነጅ በእሳት መጫወት እንዳይሆንብን እያንዳንዳችን በአስቸኳይ ኃላፊነቱን ወስደን መጀመሪያ እራሳችንን ከ'ኮኮነት' ግድፈት በመጠበቅ፤ በሌሎች ወገኖቻችንም ወንጀሉን ስንገነዘብ ከማረም፤ ከመገሰጽ ወደኋላ አንበል።

  አመሰግናለሁ
  ሰይፈ ገብርኤል

  ReplyDelete
 43. መፈርነጅ ካልሆነ በቀር አሁን በምን መለኪያ ነው «ባለ ሥልጣን» ከሚለው ይልቅ «ኤጀንሲ»፤ «የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን» ከሚለው ይልቅ «ኢትዮ ቴሌኮም» መሠልጠን የሚሆነው? ከኢትዮጵያ ጋራዎች ኩልል ብሎ የሚወርደውን ውኃ እያሸጉ «ብራቦ»፣ «ፋንታስቲክ» «አኳ ምናምን»፣ «ሎው ላንድ ዋተር» እያሉ ውኃው ሰምቶት የማያውቀውን ስም የሚያወጡትን ኮኮነቶች አድባሯስ ምን ትላቸዋለች?This is indirect colonization we have to see ourselves

  ReplyDelete
 44. You know the middle class in Africa is a white people in a black mask. The way we learn, the way we think, and even our perception are formed and nurtured by the west. Truly speaking, the beautiful people in Africa are not yet born. I agree with you, our typical identity is eroded by the dominance of the west. When we see the discourses on development I want to raise three experiences on emulation.The first experience is Japan; they are developed by copying the western model and by maintaining their own cultural values and assets. The second experience is Turkey; they developed by copying the west and by losing their own culture. The third experience is Africa as a continent; we are not developed and yet we are not maintained our cultural assets rather we are pretending to be like the west. For this reason, your intervention and usual way looking things from other angle are highly informative.

  Abebe M. Beyene

  ReplyDelete
 45. አይ ዲ.ዳንኤል እንደኔው ገጥሞሃል።አየር መንገዳችንም እኮ ፈርንጀዋል።በሁዳዴ ጾም ጊዜ የጾም ምግብ አስቀድማችሁ ማዘዝ ነበረባችሁ ብላ እንደደረቅሁ ገባሁ።ግን እስከ 9 ሰዓት ከምግብም መጾሜ እንዳይርበኝ ጠቀመኝ።

  ReplyDelete
 46. ኤርምያስ/ሳንሆዜ/April 18, 2011 at 1:57 AM

  ኢትዮጵያዊነቴን ከአሜሪካ ኗሪነትና ዜግነት ጋር እንዴት አስተባብሬ ማየት እንዳለብኝ አይኔን ከፍተህልኛል። እግዜር ይስጥልኝ!

  ReplyDelete
 47. «የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው፣
  በእንግሊዝ አናግሪያቸው» እያሉ የሚዘፍኑ፤ ሀገር ቤት ተቀምጠው «ልጄኮ ኦሮምኛ አይችልም፣ እንግሊዝኛ ብቻ ነው የሚናገረው» ብለው በድፍረት ሲናገሩ ኀፍረት የማይሰማቸው............

  ፤መፈርነጅ ካልሆነ በቀር አሁን በምን መለኪያ ነው «ባለ ሥልጣን» ከሚለው ይልቅ «ኤጀንሲ»፤ «የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን» ከሚለው ይልቅ «ኢትዮ ቴሌኮም» መሠልጠን የሚሆነው? ከኢትዮጵያ ጋራዎች ኩልል ብሎ የሚወርደውን ውኃ እያሸጉ «ብራቦ»፣ «ፋንታስቲክ» «አኳ ምናምን»፣ «ሎው ላንድ ዋተር» እያሉ ውኃው ሰምቶት የማያውቀውን ስም የሚያወጡትን ኮኮነቶች አድባሯስ ምን ትላቸዋለች?
  Hailemeskel- zmaputo

  ReplyDelete
 48. Danny Enem coconut endehonku eyetesemagn asteyayet mestet gin felegku andu coconat yemiasbilegn yihew min yemesele yeamarigna fidel eyalen becomputer metsaf gin alchalkum. Yih yehonew degmo beyetignawim college (be ene zemen malete new) computer temarn enji yeamarigna fidel altemarnim. Beergit yeras tiret yiteyiqal.

  Ethiopian airlince flight lay yetsom lemazez - vegeterian negn malet alebih- mefernej betam neber yemiakoslew. Bezih Kenyan Airwaysn salamesegin alalfim. Beferenjochu February 26 beelete Erob ke Addis Abeba we de kenya tegugze neber. Ticket office yetsom migib azigze neber - ethiopiawi ticket officer sileneberech bizum altechegerkum neber. Bereraw lay gin astenagajochu kenyawiyan sihonubign migib laynor yichilal biye asibe neber fera teba eyalku migib siyasmeritugn - fasting alkuachew. Betam yedenekegn gin tiezaze tekemto neber enam temegebku beergit andand "ethiopiawi yalhonu yegon yetsom migboch biagatimugnim".

  Beterefe Ethiopiawiw tele ye ethiopia yesilk agelgilot sechi dirigit hono sale ethio - telecom mebal alneberebetim. Gin bizum yalaschenekegn dirom telecommunication (tele) neber endiawim ahun yishalal bians astedadariwochu ferenjoch honewalina.

  Bezih agatami ye abay gidib (Millinium gidib) ahun ye Hidase Gideb libal endehone chimchimta ale - lezihim yih tsihuf ena kesir yetesetut asteyayetoch astewatsio saynorachew ayiqerim.

  Keante bizu entebikalen Egziabher Yibarkih.

  ReplyDelete
 49. betham tikikil new.

  ReplyDelete
 50. ወዴት እየሄድ ነው?ማንነቱን በመሸጥ ላይ ያለ ትውልድ ነው።

  ReplyDelete
 51. Government role is important... we can just require our schools to use local name, local calendar ... like how our courts and our parlament do. Otherwise, I have concrete evidences in my own house that the next generation is being corrupted by westernizing.

  ReplyDelete