Wednesday, March 30, 2011

ሁለቱ ሰይጣናት


ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የታሪካቸው አካል አብሯቸው የሚኖር አንድ የታሪክ ቁራጭ አለ፡፡ የሰይጣን ታሪክ፡፡ 1983 ዓም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ወደ ብላቴ የወታደራዊ ማሠልጠኛ ገብተን ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ቀድመው በነበሩት ወታደሮችም ሆነ በኋላ በመጣነው ሠልጣኞች ዘንድ አፍ ከሚያስከፍቱት ወሬዎች አንዱ ሰይጣን በማሠልጠኛው ውስጥ የሚሠራቸው አስቂኝ እና አሳዛኝ ታሪኮች ነበሩ፡፡
ወታደሮቹ «ሻምበል ደቤ» እያሉ የሚጠሩት ሰይጣን በሌሊት ፊሽካ ነፍቶ ሠልጣኞችን ይቀሰቅስና ከሰባት ኪሎ ሜትር በላይ ሲያስሮጣቸው ያድራል፡፡ ፑሽ አፕ ያሠራቸዋል፤ እንጨት ያስለቅማቸዋል፣ ተራራ ያስወጣቸዋል፤ ገደል ያስወርዳቸዋል፡፡ የዛሬው ደግሞ ምን ዓይነት ነው? እያሉ ሲመሩ ያደሩት ሠልጣኞች ሊነጋጋ ሲል ይበተናሉ፡፡
እንደ ለመዱት ወደ ቁርስ ቦታ ሲሄዱ ምግብ ቤቱ እንደ ተዘጋ ነው፡፡ ግራ ይገባቸዋል፡፡ በአካባቢውም አንድም የምግብ ቤት ሰልፈኛ እና ሠራተኛ ያጣሉ፡፡ እየተነጫነጩ ወደ ማደርያቸው ሄደው ገና ጋደም ከማለታቸው እንደ ገና ፊሽካ ይነፋል፡፡ ይሄኔ ምድር እና ሰማይ ይዞርባቸዋል፡፡ እንዴት ሁለት ጊዜ ስፖርት ያሠሩናል ብለው ይነጫነጫሉ፡፡ ወታደሮቹ በየማደርያው እየገቡ «ተነሡ እንጂ» ማለት ሲጀምሩ ተማሪዎቹ «በአንድ ቀን ሁለት ጊዜ አንሠራም» ብለው ማመፅ ይጀምራሉ፡፡
ይኼኔ ነው አሠልጣኝ ወታደሮቹ መሳቅ የሚጀምሩት «ሻምበል ደቤ ነው፤ ሻምበል ደቤ ነው» እያሉ እየሳቁ ይተዋቸዋል፡፡
ይኼ የሰይጣን ታሪክ ኢትዮጵያውያንን ተከትሏቸው ባሕር ማዶም ይዘልቃል፡፡ በባሕር ማዶ ኢትዮጰያውያን ዘንድ የሰይጣን ታሪክ በሽ በሽ ነው፡፡ በተለይም በሱዳን በኩል ሊቢያን አቋርጠው ወደ አውሮጳ የሚሻገሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን አያሌ የሰይጣን ታሪኮች አሏቸው፡፡
አንድ ጊዜ ከሊቢያ ይነሡና ወደ ሃያ የሚጠጉ ኤርትራውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሱዳናውያን እና ናይጄርያውያን ስደተኞች በአንዲት የማይካ ጀልባ ተሳፍረው ወደ ማልታ ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ ከስደተኞቹ መካከል አንዲት ፀጉርዋ የተንጨባረረ ሴት ተቀምጣለች፡፡ ዓይኗ ተጎልጉሎ ወጥቶ ድፍርስ የጎርፍ ውኃ መስሏል፡፡
የፊቷ ቆዳ እዚህም እዚያም ተሸንትሯል፡፡ እጇን አሁንም አሁንም ታወናጭፋለች፡፡ አንዳንዴም አንገቷን ትሰብቀውና ትጮኻለች፡፡ ብዙዎቹ ስደተኞች የሴትዮዋን ጠባይ ከጭንቀት የመጣ ነው ብለው እያዘኑላት ነበር፡፡ እግር በእግር ተቆላልፈው ፊት እና ጀርባ ገጥመው ምጣድ በምታህል ጀልባ ላይ ለሚጓዙ ስደተኞች ጠባያው ቢዘበራረቅ የሚገርም ነገር የለውም፡፡
ጀልባዋ የሊቢያን ጠረፍ እየራቀች ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ገባች፡፡ ከላይ ሰማይ ከታች ባሕር ብቻ ነበር የሚታየው፡፡ የመርከቧ ካፒቴን በአንድ ቀን ሠልጥኖ በአንድ ቀን ለካፒቴንነት የበቃ ሰው ነው፡፡ አሻጋሪዎቹ ከስደተኞች መካከል ነቃ ያለ የመሰላቸውን ሰው ይጠሩና የመርከብ አነዳድ ኮርስ ለአንድ ሰዓት ይሰጡታል፡፡ ኮምፓሱን ያሥሩለትና ደኅና ያግባህ ብለው ይሸኙታል፡፡
ካፒቴን መርከቧን እየቀዘፈ በመጓዝ ላይ እያለ ሴትዮዋ ጮኸች፡፡ ድንገትም እንደ ስፕሪንግ ተስፈንጥራ ቆመች፡፡ ሁሉም ራስዋን ልትወረውር ነው ብለው በፍርሃት አዩዋት፡፡ እጇን አነሣችና ወደ አንደኛው ስደተኛ ጠቆመች፡፡ «አንተ ትሞታለህ» አለችና ጮኸች፡፡ ከዚያም ጸጥ ብላ ተቀመጠች፡፡ ጥቂት እንደ ቆየ ሳይታሰብ ልጁ ከመርከቧ ተወርውሮ ባሕር ውስጥ ሰጠመ፡፡
ሁሉም በፍርሃት ተዋጠ፡፡ የየራሱን ዕጣ ፈንታ እያሰበም በጭንቀት ሰመጠ፡፡ ምን ዓይነት ሴትዮ ናት፡፡ አንዴት እንዲህ ልትል ቻለች፡፡ ጠንቋይ ናት ማለት ነው፡፡ በዚሁ ታበቃለች ወይስ ትቀጥላለች፡፡ ማንም እርስ በርስ ባያወራም ተመሳሳይ ጭንቀት ውስጥ ነበር፡፡
ጀልባዋ ጥቂት እንደ ተጓዘች አሁንም ሴትዮዋ ተነሣች፡፡ የሁሉም ልብ እንደ በሰለ ሽሮ ዱክ ዱክ ይል ጀመር፡፡ እንደ ሐዋርያትም «እኔ እሆንን እኔ እሆንን» ማለት ጀመሩ፡፡ የሁሉም ዓይን እርሷ ላይ ተተከለ፡፡ እጇን አነሣች፡፡ ወዴት ትልከው ይሆን?
«አንተ ትሞታለህ» አለችና አንዱ ላይ ጠቆመች፡፡ አፍታ አልቆየም፤ ልጁ ዘልሎ ተነሥቶ ሜዲትራንያን ባሕር ውስጥ ገብቶ ቀረ፡፡ ሁሉም በድንጋጤና በጭንቀት ከመዋጣቸው የተነሣ ልጁን ይዘን እናስቀረው ብሎ ያሰበ እንኳን አልነበረም፡፡ ደግሞ ማን ይከተል ይሆን? የሚለው ነበር በየልቡ የሚንከባለለው፡፡
እነሆ ጥቂት ዝምታ ሆነ፡፡ ማንም ከማንም ጋር አላወራም፡፡
ሴትዮዋ ለሦስተኛ ጊዜ ተነሥታ በአንዱ ላይ ጠቆመች፡፡ ወዲያውም ሰው ዘልሎ ባሕር ውስጥ ገባ፡፡ በተለይም በጥንቆላ እና መተት አብዝተው የሚያምኑት ናይጄርያውያን ሴትዮዋን እንደ ንጉሥ አከበሯት፡፡ ከሥር ከሥሯ እያቶሰቶሱ ካዳሚዎቿ ሆኑ፡፡
ሴትዮዋ አገልጋይ ስታገኝ ጊዜ «እገሌ ካልተጣለ በሰላም አንደርስም» ማለት ጀመረች፡፡ ናይጄርያዎቹ ደግሞ ትእዛዝዋን ለመፈጸም ይፋጠናሉ፡፡ የተባለውን ሰው የምድር ወገብ ግንድ በሚያህለው ጡንቻቸው እያነሡ ወደ ባሕር ይወረውራሉ፡፡ መጀመርያውንም ቀጫጭኖች፣ የበረሃ መንገድ ሲመታቸው ደግሞ ጠውልገው ከተስፋ ጋር የሚታገሉት ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ከናይጄርያውያኑ ይልቅ በሞት ጥላ ውስጥ ገቡ፡፡
ከሃያ ስደተኞች ስድስት ብቻ ቀሩ፡፡ ማልታ ላይ ምናልባት መርከቧ ብቻዋን ትደርስ ይሆናል፡፡
ሴትዮዋ በድንገት ተነሣችና አንዱን ዝሆን የሚያህል ናይጄርያዊ «ጣሉት» ብላ አዘዘች፡፡ እርሱም ሌሎቹም ደነገጡ፡፡ ተያዩ፡፡ ሰውየው መጀመርያ ቃዠ፡፡ በኋላ ግን ወደ ልቡ ተመለሰና የክንዱን እጅጌ ሰበሰበ፡፡ ጎንበስ አለ፡፡ ሴትዮዋን ተሸከመና ባሕር ውስጥ ጣላት፡፡ ሴትዮዋ ከባድ ጩኸት አሰማች፡፡
ተጓዦቹ እንደሚናገሩት የሴትዮዋ ድምፅ ማልታ እስኪደርሱ ድረስ ይሰማቸው ነበር፡፡
እነሆ እንዲህ ሆነው ከሃያ ስደተኞች አምስት ብቻ ማልታ ገቡ፡፡
እስኪ ደግሞ ከማልታ ወደ ኖርዌይ እንሻገር፡፡
የኖርዌይ ኢትዮጵያውያን በቀልዳቸው የሚያውቋቸው አንዲት እናት ነበሩ፡፡ እኒህ እናት ልጃቸውን ሊጠይቁ ነበር ኖርዌይ የገቡት፡፡ ልጃቸው የኖርዌይ ዜጋ ፈረንጅ ነበር ያገባችው፡፡ እርሳቸው ኖርዌይ ሲገቡ የባልየው እናትም እዚያ ቤት መጥተው ነበር፡፡ ከሁለት ዓለም የመጡ ሁለት አማቶች እዚያ ጣርያ ተገናኙ፡፡
ሰውዬው ደግ ሰው ነበር ይባላል፡፡ ጠዋት ጠዋት ይነሣና ድንች ቀቅሎ ከማባያ ጋር ለአማቱ ይዞላቸው ይመጣል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አማት ግን ነገር ዓለሙ አልጣማቸውም፡፡ «ምን ጮማ ሥጋ የያዘ ይመስል ደግሞ ለድንች ቢላዋውን እያፋጨ ይመጣል» ይሉታል፡፡
አልፎ አልፎ ለምሳ ነጭ ቂጣ ጋግሮ ከቲማቲም ጋር ብቅ ሲል «አንቺ ነይ፤ ማኛውን ጤፍ ይዞልሽ መጥቷል፡፡ አይ ማኛ አይ ማኛ» ብለው ይቀልዳሉ፡፡
እንዲህ እንዲህ እያሉ ሲቀልዱ ኖሩ፡፡
ታድያ አንድ ቀን ከአማቻቸው ጋር በአስተርጓሚ ሲነጋገሩ ዋሉ፡፡ እኒያ ኖርዌያዊት አማት በረዶ የመሰለ ጥርሳቸውን ፍጭጭ እያደርጉ በኖርዌይኛ ሲናገሩ ኢትዮጵያዊቷ አማትም እንደ ባህላቸው አንገታቸውን ሰበር እያደረጉ ወሬውን አስኮመኮሟቸው፡፡
ምንም እንኳን እንድ ባስልዮስ እና ኤፍሬም ነገር በአስተርጓሚ አልካተት ቢላቸው፣ ያንዱ ቋንቋ ለሌላው ሊገለጥላቸው አልቻለምና እኒያም በአማቻቸው እኒህም በልጃቸው አስተርጓሚነት የያገራቸውን ወግ አቀለጡት፡፡
መሸና የተለመደው «ማኛ» ቀረበ፡፡ እርሳቸውም የአድአ ነጭ ጤፍ ውል እያለባቸው ጎራረሱት፡፡ የመኝታ ሰዓት ሲደርስ ኖርዌያዊቱ አማት ወደ አልጋቸው በጊዜ ገቡ፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ግን የሀገራቸው ትዝታ እየመጣባቸው እንቅልፍ አልወስዳቸው አለና ሲገላበጡ አመሹ፡፡
እኩለ ሌሊት ሲደርስ ነጠላ ጫማቸውን አጥልቀው ወደ ባኞ ቤት መጡ፡፡ የባኞ ቤት ጣጣቸውን ጨርሰው ወደ መኝታቸው ሲመለሱ እንደ ልማዳቸው አንገታቸውን አቀርቅረው ነበር፡፡
መሐል መንገድ ላይ የሌላ ሰው የእግር ኮቴ ሰሙና ቀና አሉ፡፡ አፍ ሲከፈት ጥርስ የሌለው ድድ ብቅ አለ፡፡ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ» ብለው አማተቡና ጮኹ፡፡
ሰይጣን አማቻቸውን መስሎ ከፊታቸው መጣና ወደ ባኞ ቤት ገባ፡፡ ቁርጥ የልጃቸውን አማት የምትመስል ባልቴት፡፡ ሰይጣን ጥርስ አለው፣ ያውም ግጥጥ ያለ ሲባል ነበር የሚያውቁት፡፡ የፈረንጅ ሰይጣን ግን ድድ እንጂ ጥርስ የለውም፡፡ ደግሞ አፉን ሲከፍተው ሲያስፈራ፡፡ ዋሻ ይመስላል፡፡ አቤት ስንት ክንድ ይሆን?
እየጮኹ እና እየተንቀጠቀጡ ሮጠው መኝታ ቤታቸው ገብተው ዘጉት፡፡ ልጃቸው እና ባልዋ እየተሯሯጡ ጩኸቱን ወደሰሙበት አቅጣጫ መጡ፡፡ እናት ቤታቸውን ዘግተው «አበስኩ ገበርኩ፣ አበስኩ ገበርኩ» ይላሉ፡፡ ልጂቱ «እማዬ ምን ሆነሽ ነው፤ እስኪ ክፈችው» ትላለች፡፡ እናት ግን ምንም ዓይነት ድምፅ ማመን አልቻሉም፡፡ ዘግተው ዝም አሉ፡፡
በስንት መከራ በራቸውን ከፈቱ፡፡ ልጃቸው ደንግጣ ገብታ እናቷን አቀፈችና «ምን ሆንሽ ምን ሆንሽ» አለቻቸው፡፡
«ሰይጣን ሰይጣን አማትሽን ተመስሎ ሊተናኮለኝ፣ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ» አሁንም አሁንም ያማትባሉ፡፡
«የታለ፣ የታለ» አለች ልጃቸው፡፡ እርሷም ሰይጣን ለማየት ጓጉታ፡፡
«ባኞ ቤት ገብቶልሻል»
ልጃቸው ወደ ባኞ ቤት ስትሄድ አማቷ ከባኞ ቤት ወጥተው ወደ ክፍላቸው ሲገቡ አየች፡፡ ባኞ ቤት ስትገባ ማንም የለም፡፡
«እንዴ እማዬ የባለቤቴ እናት ናቸውኮ፤ ሌላ ነገር የለም» አለች ተመልሳ፡፡
«ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የናንተ ሀገር ሰይጣን ጥርስ የሌለው ባዶ ድድ ነው፤ አይቼዋለሁ፣ አፉን ሲከፍት አይቼዋለሁ»
«እንዴ እማዬ ጥርሳቸውን አስቀምጠውት ነውኮ»
«ደግሞ እንዴት አርገው ነው ጥርሳቸውን የሚያስቀምጡት»
«አርተፊሻል ነው፤ ማታ ማታ ያስቀምጡታል»
«አበስኩ ገበርኩ፤ እኔ፣ ቀን ሌላ ማታ ሌላ የሚሆን ሰው አይቼ አላውቅም፡፡ ይኼ አገሩ ራሱ የሰይጣን ሀገር ነው፡፡ ሰው እንዴት ቀን እና ሌሊት ይቀያየራል»
«እዚህማ አልኖርም» ብለው እንዳማተቡ ሀገራቸው ገቡ፡፡
ሐራሬ፣ ዚምባብዌ
 

27 comments:

 1. ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የታሪካቸው አካል አብሯቸው የሚኖር አንድ የታሪክ ቁራጭ አለ፡፡ የሰይጣን ታሪክ


  «አበስኩ ገበርኩ፤ እኔ፣ ቀን ሌላ ማታ ሌላ የሚሆን ሰው አይቼ አላውቅም፡፡ ይኼ አገሩ ራሱ የሰይጣን ሀገር ነው፡፡ ሰው እንዴት ቀን እና ሌሊት ይቀያየራል»

  ReplyDelete
 2. This is sad and so funny.

  ReplyDelete
 3. ለምን ይሆን መሸትሸት ሲል ነገሮቹ ወደ ሌላ የሚቀያየሩ? ከአስተዳደጋችን ውስጥ የትኛው ይትብሃል ይሆን አይምሮአችን ውስጥ የሰለብን?

  ReplyDelete
 4. Sewu endet ken ena mata yikeyayeral. Thanks Dn.Dani
  GOD Be with U!

  ReplyDelete
 5. waw endet yale neger new ? betam yegeremal degemom yseyetan neger sinesa betam yasferal ? endesew aseneseto sport siyasera hooooo !!!!!!!

  kezim belay degemo ye habescha amach ersun kofeso egun tatebo sikerebelet ena sibela engi ege astatebo siyakerb yalayute enate degmo (ሰውዬው ደግ ሰው ነበር ይባላል፡፡ ጠዋት ጠዋት ይነሣና ድንች ቀቅሎ ከማባያ ጋር ለአማቱ ይዞላቸው ይመጣል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አማት ግን ነገር ዓለሙ አልጣማቸውም፡፡ «ምን ጮማ ሥጋ የያዘ ይመስል ደግሞ ለድንች ቢላዋውን እያፋጨ ይመጣል» ይሉታል፡፡ kkkkk aye ye bahel leyunet hone new engi endezih yalewn neber liyamesegenut yemigeba yeneber Dani EGZIABHER YSETELEN melekam tehuf new !!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. Dani,

  You are really funny.

  ReplyDelete
 7. Yehasabu meleekt algebagnim !!!

  ReplyDelete
 8. wow danie it is fantastic

  ReplyDelete
 9. It is so funy ! DN Daniel may God bless you.Dhugaa isaanit biyyichi biyya qalanii hinyaanne biyya qananihinqabnne,biyya ilmoon saree koortu biyyailmoon nama joortu,biyya hantuuta nyaatan biyya abjuun maraatan mitiree?.

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንኤል የዛሬውንስ እኔም እየፈራሁ ነው አንብቤ የጨረስኩት በጣም ያስፈራራል፡፡ የሰይጣን ነገር መቸም አያስደስትም ምክንያቱም ከጥንትም ጠላታችን ስለሆነ፡፡ ልዑል እግዚአብሔር አንተንም እኛንም ከሰይጣን ተንኮል ይጠብቀን፡፡ የፃድቃን ሰማዕታት ፀሎት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 11. በጣም የሚገርም ነው፡፡ ምክንያቱም አእምሮን ዝም ብሎ ማዘጋዸት ይከብዳል፡፡ ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ትልቅ ነገር ነው የተማርኩበት፡፡ አንዴም እስቃለሁ፤ አንዴም አያዱርስ እላለሁ፡፡ በአጠቃላይ ጥሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ቃለ ሕይወት ያሰማንል አሜን፡፡

  ReplyDelete
 12. እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ፤ ሰው ደግሞ ሰይጣንን ፈጠረ ይባላል፡፡ እናም የሴትዋ እይታ ነበር አማቷን ሰይጣን ያስመሰላት፡፡ አሰልጣኙ የብላቴው ጀኔራልም እድሜ ቢሰጠው ኑሮ የውስጥ ጠላት/ሌላ ሰይጣን /ይጠፋ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 13. betam yigermal. tadiya sew ende ageru bibalis?
  dani berta!!!

  ReplyDelete
 14. Selam Lehulachehu Yehunena, Let me say one story which my friend told me. In his birth place no one knows about God & every body believes in witch doctor,even his grand mom is also believed in devil's. He himself see a devil fighting with his neighbour & that man dies after a week. He told me that no one call the name of God that is why the devil civilized on them. Finally somebody comes with the name of God & they are full of peace at the moment. But you know we the christians when we call the name of God & the saints the devil's will leave that place immediately. We are truely tell the name of God is a medicine for everything.

  Glory to God. I hate devil's because they always interferes in our life & they don't make us to feel good.

  ReplyDelete
 15. Dani betam new yemiyaskew ken mulu eyasebkut sisk new yewalkut. andande endezi zena argen enji.

  ReplyDelete
 16. It's simply an example of a delusion. In Belati camp case, soldiers might get some form of punishment if they failed to show up for morning excises. It created in them great stress and fear which awoke them in middle of the night. I don't think devil awake people for excises. In second case, the boat travelers might be under great fear and stress for lot of reasons. As a result nobody bother to challenge the lady. If she had some kind of power, she didn't allow to threw her out to sea. The third story is really funny. It's common in most culture to blame devil when people do strange things out of fear and stress.

  ReplyDelete
 17. ወይ ዳኒ ዛሬ በሳቅ ገደልከኝ። አይኖቼ ተክዬ በቀኝ እጄ ጣቶች መጠቅለያውን(scroll bar) እየደነቆልኩ ሳነብ፤ በምስል ከሳች ሥነጽሑፋዊ ገለጻህ በግራእጄን አፌን ይዤ ከመደመም በስተቀር መደነቄን ለመግለጽ ቋንቋም የለኝ።
  ጭብጡን ለኛው ተውክልን?ይሁን ልማር ላለ ሰው ከቁራስ ይማር የለ(ሚበቃውን ለቅሞ አመስግኖ ከሚበረው)
  እንዲህ እንዲህ እያልን ሁለተኛ አመት ጉዞን ...።

  ReplyDelete
 18. ምንም እንኳን ወንድማችን ዳንኤልን ሁላችንም ብናውቀውም ምሥጋናው ግን የበዛ ይምስለኛል። እስኪ አሁን ድግሞ ወደሥራው ይመለስ ዘንድ እንተወው.... ብዙ ምሥጋና ጥሩ አይደለምና

  ReplyDelete
 19. This peice is funny but important.
  Dani, you went to Zimbabwe???
  wa, take care ! you are now with our 'sewye' who is considered as 'tiliku SEITAN' by our people. Lehagerih Meqabir yabikah belew.

  ReplyDelete
 20. Thank you for sharing.

  Its true "አበስኩ ገበርኩ፤ እኔ፣ ቀን ሌላ ማታ ሌላ የሚሆን ሰው አይቼ አላውቅም፡፡ ይኼ አገሩ ራሱ የሰይጣን ሀገር ነው፡፡ ሰው እንዴት ቀን እና ሌሊት ይቀያየራል" What we are looking the patriariche(leader) of EOC what he was doing on the church Ken sewu fit sikerbu Papas kesewu fit zor silu degmo yemiserut lela newu .

  I have learned alot.

  ReplyDelete
 21. ኣንዳንዴ “ሳት” እያልክ እግረ መንገድህን በምታነሳቸው ነጥቦች ትንሽ ተዓቅቦ ቢኖረኝም ጽሑፎችህ ብዙ ትምህርት እንዳላቸው መስካሪ ነኝ። የዛሬው መልእኽትህ ጥርስ ቢያስከፍትም ለኔ ግን ቀልድ ሆኖ ኣልታየኝም። ባለ ቅኔ የማያስገልገው ትልቅ መልእኽት ኣለው።
  በመርከቦቹ የነበሩት ኣፍሪቃውያን በርግጥ እኛ ነን። ፈርተን ቤታችንን ዘግተን “ኣበስኩ ገበርኩ” የምንልም እኛ ነን።
  ከመጀመርያው ጀምሮ ያችን ሴት በማየት ብቻ በውሳጣዊ ኅሊናቸው ፍርሃትን ያነገሱት ሰዎች ኢምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሴትዮዋን ልዕልና ተቐበሉ። ከመርከብዋ መጣልና ሞት ላይቀርላቸው ዝም ብለው ተገዙላት (ብኅሊናም ብግብርም)። የመጀመርያው ሰው እንደሚሞት ወሬ በነዛች ግዜ ተቃዋሚና ከንቱ ነገርን የማያምን ኅሊና የሚሰጠውን ግብረ መልስ ብታገኝ ኖሮ ተከታይ ባለገኘች። ከዛም ኣልፎም ከፍቶም ኣንድ ባንድ እንዲጣሉ ትእዛዝ ስትሰጥ ነገሩ ለሁሉም በጎ ባለመሆኑ “ለምን” “ኣይሆንም” ብሎ የሚጠይቅና የሚቃወም ቢኖር ይህ ሁሉ ጣጣ ባልመጣ።
  ያ የተቃመወ ብርቱ ሰው ግን እራሱን ኣዳነ ቢዘገይም የቀሩትንም ኣዳነ። ራሱ ላይ እስኪመጣ ጠበቀ እንጂ ቀድሞ ቢሆን ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር። “ቀድሞ ነበር እንጂ..” ሳንል ወንድማችን ለችግሮቻችን መፍትሔው ኣንድ እና ኣንድ ነው እያለን ነው። የሚበጠብጠንን እየጨረሰን ያለውን “ችግራችንን” ብቆራጥነት ተነስተን ከ “መርከባችን” እንጣለው።
  በሁለተኛው ሰይጣናዊ ምሳሌው ደግሞ የበለጠ “ችግራችን” ምን እንደሚመስል ማን እንደሆነ ቍልጭ ኣድርጎ ኣሳይቶናል። በአንድ የማይጸና - ቀንና ሌሊት የሚቀያየር - እውነተኛው ማንነቱ “ሌሊት” የሚገለጥ ወዘተ ብሎ ግልጽ ኣደረገው። ኣንድ ጊዜ ኣንድ ኣባት ስለመጨረሻው ዘመን ሰዎች ጠባይ ሲናገሩ መጽሓፍ ጠቅሰው “ጠዋት የሚለውን ማታ የማይደግም” ብለው ነበርና ያንን ኣስተወስከኝ። መርከብዋ ሰላም እንድታገኝ እንዲሁም ፍርሃትን ኣርቀን በሰላም እንድናድር ያንን “ሰይጣን”.. እናርቀው ነው መልእኽትህ ብየ ተረድቸዋለው። እሰጥ ኣገባ ውስጥ ሳንገባ ስሕተት ካለ ኣርሙኝ።
  በኔ በኩል ግን ይህ ጽሑፍህ የታሪኽ ቍራጭ ሳይሆን የ ”ሰይጣን ቁራጭ” ብየዋለው። ወንድሞች እህቶች ዲያቆን ዳንኤልን ማገዝ የምንችለው በመሳቅ ሳይሆን “እሪታውን” በመስማት ነው። የመጣውን ስናደንቅ ከምንኖር መልእኽቱ ላይ ኣተኵረን እንበሳሰል።
  እግዚአብሔር ይጠብቅህ።

  ReplyDelete
 22. ሴይጣን በእውነት አለ? አንድ ጊዜ የገጠመኝን ልንገራቹ። አንድ ቀን ከተማ ኳስ ለማየት አምሽቼ /ቤታችን ከከተማው ትንሽ ወጣ ይላል/በግምት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ይሆናል ወደ ስሄድ አንድ የሰፈሬን ልጅ አገኛለሁ፤ የሄ የሰፈሬ ልጅ አምሽቶ ወደሰፈር በመግባት የሚየታወቅ ልጅ ነውና ስንገናኝ ዛሬ እንዴት በግዜ ገባ እያልኩ እያሰብኩ እያለ አረ ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል እያለ አላስኬድ አለኝ እኔ ደግሞ እኩለ ሌሊት የምትገባው ሰውዮ ዛሬ ምን ሆነህ ነው በሦስት ሰዓት የምትፈራው እያልኩ እየቀለድኩበት ሰፈር አካባቢ ስንደርስ ልጁ እንዲህ እያለ መጮህ ጀመረ፤ ገደሉኝ ሦስት ናቸው፣ በውስጤ አሸዋ ጨመሩብኝ፣ አረደበደቡኝ በማለት ሲጮህ ለኔ የሚታየኝም ሰውም ሆነ የሚጨምሩበት አሸዋ አልታየኝም ከዚያም የሰፈር ሰው የልጁን ድምጽ ሰምተው እየተሯሯጡ ሲመጡ ልጁ አጠገቤ ቆሞ እየተንቀጠቀጠ ያገኙታል። ምንሆነህ ነው ብለው ሲጠይቁት ከላይ የጠቀስኩላቸሁን ንግግር ደገመላቸው። ተሯርጠው ከመጡት ውስጥ በድሜ የገፉ ነበሩና ጉዳዩ ሻምበል ደቤ ነው ብለው ልጁን ወደ ቤቱ ወሰዱት ያልጅ ታድያ ለብዙ ጊዜ ታሞ በስንት ጠበል መሰላቹ የዳነው። እና እኔም ሴጣንን በአካል ባለየውም የሰራውን አስተውያለው። እግዚአብሔር ቸርነትና የቅዱሳኑ ተራዳኢነት ባይኖር ይሄ ትውልድ በዚህ ስንፍናው ሴጣንን በምን ጽናቱ ይችለው ነበር? የእግዚአብሔር ቸርንት፣የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ፈጣን ተራዳኢነትና የቅዱሳን ጸሎት አይለየን። አሜን

  ReplyDelete
 23. በጣም ደስ የሚሉ እናት ናቸው። እየሳቅኩ ነው የሳቸውን ያነበብኩት።

  ReplyDelete
 24. ወንድሜ ናግራን ፡- እርግጠኛ ሆኜ የምነግር የዳንኤልን ማንነትና ጽሁፎቹን አልተረዳሀቸውም፡፡ አንድ እውነት ልንገር ዲ/ዳንኤል በስብከቱም ላይ ይሁን በማንኛውም የጽሁፍም፤ የቃልም አስተያየቱ ላይ በግልጽነት፣ በታማኝነት፣ ጎዶሎነት በሌለው እውቀት፣ በድፍረት፣ በብስለት፣ የሚሰብክ የሚጽፍ ሰውነው፡፡ አንድን እውነት ለማሳወቅ ወደግራም ወደቀንም አይልም፤ እርሱ ካመነበት ፊት ለፊት ያደርገዋል ይናገረዋል፡፡ መጀመሪያ ግን ለሚጽፈውም ለሚናገረውም በእርግጠኝነት አውቆ ተረድቶ አንብቦ ነው አንተ እንደምታስበው እንቆቅልሻዊ ሰው አይደለም፡፡

  አንተ ጽሁፉን እንደምትፈልገው አንብበ እንደምትፈልገው ተፈጎምከው፡፡ ዲ/ዳንኤል ታሪክንም ሰይጣንንም ለይቶ በደንብ ያውቃቸዋል፡፡

  ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክ፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 25. Seblewengel,Addis ababaApril 6, 2011 at 2:38 PM

  Thanks dani this is real history we all see day to day in our life kine ena mata yeteliyayen nane ,kine biro senihone endegna tihute yelam dege sewu akibare betachine singeba gine lebete sirategnachine yeminasayate bahire seyitanawe nawu endihum lebalachine and also lelijochachine mecha yihone kineme hona mata sewu yeminihonawu ?endesewu noren endesewu yeminalifawu fetare yiredane.

  ReplyDelete
 26. waw endet yale neger new ? betam yegeremal degemom yseyetan neger sinesa betam yasferal ?

  ReplyDelete