በበዓሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እና በኢሜይል የተመዘገቡ ከ500 በላይ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡
በዓሉ የተጀመረው በበገና፣ መሰንቆ፣ ክራር እና ዋሽንት በተቀናበረ ጥንታዊ ዝማሬ ሲሆን በማስከተልም የአጫብር ወረብ ቀርቧል፡፡
የዕለቱ ፕሮግራም መሪዎች የሸገሩ ጋዜጠኛ አንዱዓለም እና የአዲስ አድማሷ ጽዮን አዲስ ከታተመው የዳንኤል መጽሐፍ አንዳንድ መጣጥፍ አቅርበዋል፡፡
የዕለቱን ትኩረት የወሰደውና በአቀራረቡ የተመሰገነው አምስት ባለሞያዎች ያቀረቡት ዝግጅት ነበር፡፡ የታሪክ ባለሞያው ብርሃኑ ደቦጭ፣ የአኩስም ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ መምህር ገዛኸኝ ፀ፣ የኮተቤው የሻው፣ የኅትመት እና ዌብ ጋዜጠኝነት ባለሞያው ዐሥራት ከበደ እና የኮሙኒኬሽን ባለሞያው ነጻነት ተስፋየ በዳንኤል ጽሑፎች እና ተያያ ዥ ጉዳዮች ላይ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች አቅርበው በተሳታፊዎች ለሁለት ሰዓታት ያህል ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ለአዘጋጆቹ ለዐሉላ ጥላሁን፣ ኢዮብ ሥዩም፣ መንግሥተ አብ አራንሺ፣ ዲያቆን ታደሰ እና አሸናፊ ደምሴ ከዲያቆን ዳንኤል ባለቤት ከወ/ሮ ጽላት ጌታቸው ከብር የተሠራ የቁልፍ መያዣ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዝግጅቱ የተካሄደበት የአኩስም ሆቴል ሠራተኞች ለዝግጅቱ ያላቸውን ፍቅር ለመግለጥ በራሳቸው አነሣሽነት የውኃ ዳቦ ያቀረቡ ሲሆን ይህም በተሳታፊዎቹ ዘንድ ልዩ ስሜትን ፈጥሮ ነበር፡፡
የዝግጅቱን ወጭ በመሸፈን አባ ቴዎድሮስ አካሉ ከስታቫንገር እና አባ አብርሃም ከኦስሎ ከአዘጋጅ ኮሚቴዎቹ ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡ የአዲስ ጉዳይ ዝግጅት ክፍልም በራሱ ወጭ ለበዓሉ የተዘጋጀውን ብሮሸር አሳትሞ አቅርቧል፡፡
የበዓሉ ፎቶዎች እና ፊልሞች እንዲሁም ጥናታዊ ጽሑፎቹ በተከታታይ ወደፊት ይቀርባሉ፡፡
Try to narrate all the situations in your known wonderful narration mechanism so that to know and understand what was going on
ReplyDeleteIf Ethiopia/EOC has such wonderful guys, we would be saved from aggressors like reformists.
ReplyDeleteThanks Dn.Dany for sharing ur views !!!
ReplyDeleteUr view is very very ... Important for our church, country, etc
if it translate to other language(like engilish, chinise...), it is very important for z other Contenent. God be till the End !!!
Egiziabher Yetemesegene Yihun
ReplyDeletehey dani first of all i want to say thanks for the God that he select me to participate in the ceremony and also you and all other people who participate to prepare the ceremony dani i was one of the participant. all idea that raised during the discussion time is so nice and important idea specially for you dani i hope you gate another "in side or internal view that makes you to see 360 degree so Dani i expect more thing now you are the leader for this generation please keep it up dani
ReplyDeleteI pray for you and your family Long and pease life.
thanks Dani
one of your blog follower
I was one of the participants on the anniversary.That was so wonderful and really I enjoyed it.
ReplyDeleteዳኔ...
ReplyDeleteጡመራ የጀመርክበትን አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ልዩና የተሳካ ዝግጅት ታዳሚ በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ:: አብዝተህ : አብዝተህ..ጻፍ...በስርህ ተኮልኩለን እውቀትን እንቀስማለን: ፍሬያችንንም ታያለህ::
አመሰግናለሁ...
እግዚአብሄር ብርታትን ይጨምርልህ
ዲ/ን ዳንኤል
ReplyDeleteለአንተ÷ ለባለቤትህ÷ ለልጆችህ እና ፈርጅ ብዙ አገልግሎት ለአከናወኑ ለፕሮግራሙ አዘጋጆች እንኮን ደሰ አላችሁ፡፡
እኛም የጡመራው መድረክ ተከታታዮች እና የዝግጅቱም ታዳሚዎች እንኮን ደስ ያለን፡፡
ዝግጅቱ በጣም ልዩ ነበር፡፡ እኔ በእውነቱ ኮርቸብሀለሁ÷ በዝግጅቱም በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ዳንኤል፤
1. መረሀ ግብሩ በጋራ ጸሎት አለመጀመሩ የተወሰነ ቅሪታ ፈጥሮብኛል ከዝግጅቱ ይዘት አንፃር ብንመለከተውም በጸሎት መጀመሩ የበለጠ ኃይልና ሞገስ ውበትና ድምቀት ከመሆን ባሻገር የተለየ መልዕክት አልነበረውምና!
2. የተሰጡህ አስተያየቶች ሁሉ መልካም ቢሆኑም ራስህን በነፃ ጦማሪነት ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ማስቀመጥ እንዳለብህ በተሰጠው ሀሳብ ላይ አልስማማም ምክንያቱም የአንተ ማንነት ተወደደም ተጠላም ከኦርቶዶክስ ጋራ ተዋሕዶአልና ፡፡በሌላ መልኩ ዳንኤል ‘’ብታርግ’’ እንኮን አብሮህ ‘’ያርጋል’’ እንጅ ‘’ማረግህን’’ የሚያምን ማናም የለም ስለዚህ ያለህ ይበቀሀል በያዝከው ጽና በጀመርከው ቀጥል!
እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡
God be with you!
ReplyDeletei am so interested to read the wonderfull naration ....please be fast to present it ....
hi dani i am so glad to hear this.how ever,i was expect that to follow on line but i could not get it so please posted the ceremony how looks like.i can not wait.and also is there was 10 things what we do not know before?what was that?
ReplyDeleteለሊ said ... .
ReplyDeleteሰላም ዲ/ን ዳኒ በትላንትናው በአል ተገኝቼ ነበር እጅግ ደስ ብሎኝ ነው እስከአሁን ከውስጤ አልወጣም መቼም የሚጠፋ አይደለም ! በተለይ የቤተሰቦችህ ህብረትና ፍቅር ልቤን ማርኮታል:: እግዚአብሔር ይጠቃችሁ ቀጣዩን አመት የተሰጡትን አስተያየቶች የሚረባህን በመያዝ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን እንደምታስኮመኩመን ተስፋ አደርጋለሁ:: ይሄ እንዳለ ሆኖ ከክርስትናው አለም ውጪ ላሉ ወንድሞቻችን አንድ መንገድ ብታስብ ጥሩ ነው በተረፈ በርታ እግዚአብሔር በነገሮችህ ሁሉ ይቅደምልህ
Dn Daniel,
ReplyDeleteI hope everything went so well. We were disapointed that we couldn't follow the ceremony live but hoping that we are going to watch and see pictures and vides on this blog soon. GOD BLESS!!! Atlanta.
D/n daniel thanks for all! እግዚአብሔር እረጅም የአገልግሎት ዘመን ይስጥህ፣ ብዙ ልደቶችን የምታከብርበትን ዕድሜ ይስጥህ፣ ፀጋውን ያብዛልህ እመቤታችን በምልጃዋ ትጠብቅህ አሜን፡፡
ReplyDeleteEgziabher Yimesgen
ReplyDeleteBRAVO!
ReplyDeleteደብረ ቁስቋም
ReplyDeleteበውነት ደስ ብሎኛል ያለመታደል ፕሮግራሙን መከታተል ባልችልም ዲ ዳንኤል እንዳልከው ሁሉንም በጉጉተ እየጠበኩ ነው
መልካም የሁለተኛ ዓመት ጅማሬ ይሁን
thanks to GOd.
ReplyDeleteI LIKE THE MIXTURE OF PEOPLE FOUND IN THE ANIVERSARRY.PLEASE DO GATHER FREQUENTLY AND DISCUSS ABOUT ETHIOPIA AND EOTC.
ReplyDeleteDani, happy birth day for your blog. I would like to appreciate Axum hotel employees what they did for the aniversary of your blog.
ReplyDeleteThank you.
ምስጋና ለሉዕል እግዚአብሄር ይግባው እና በዕለቱ ተዳሚ ነበርኩ በጣም ደስ የሚል ዝግጅት እንደነበር ላልነበሩ ወዳጆቼ ያጫወትኩ ሲሆን ከዚህም ቡኃላ አጋጣሚው ሲፈቅድ የምገልፅ ይሆናል።
ReplyDeleteቀጣዩ ምስጋናዬ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሆኖ ሳለ እንዲበረታ አየጠየኩ አንባቢዎቹ በፀሎት እንዲያስቡት እጠይቃለሁ፡፡
የሚሰልሰው ምስጋና ለመንጌ (መንግሥተ አብ አራንሺ) ይሁንልኝ እና ለኮሚቴው አድናቆቴን ሳልከትብ አላልፍም።
እግዚአብሄር ያክብርልኝ።
ባያ
dani ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እነኳን አደረሰህ ለዚህ ብቸኛ ለሆንከው ኢትዮጵያዊ ሰው ሀገር ቤት ያለህ ሳትፈራና ሳታፍር ሁለት ሰይፍ የሆንክ ከቤተ ክህነቱ ቢሆን ሚዛናዊ ሁሉን አቀፍ የሆንክ ብቸኛ ሁሉን አቀፍ የሆንክ ብቸኛ ሁሉን አቀፍ የሆንክ ብቸኛ፡፡
ReplyDeleteሀ)አንዱአለም እና ጽዮን መርሃ ግብሩን በጥሩ ሁኔታ መርተውታል ምስጋና ይገባችኃል ለሁለታችሁ ብቻ፡፡
ለ)አቅራቢዎች አንዲህ በዝተው በየሙያቸው ያቀረቡት በጣም በጣም በጣም ላመሰግን እወዳለሁ ሳትፈሩ ጠቃሚ የሆነ ገምቢ ምግብ ብየዋለሁ ፡፡
ሐ)የዳኒ ብሎግ ለሌሎች ጸሀፍት miss call ብየዋለሁ እና ዳኒ በዢሕ ጻፍባት አስቲ፡፡
ቅሬታ
ዳኒ አንዱዓለም እና ጽዮን እጄን ባወጣም ዓይናቸው ዓይኔን (እጄን)ባያየኝም ለ ዳኒ ጥያቄ አለኝ
1. ዳኒ አንተ የመረጃ ቋት ካለህ በምትታመምበት ጊ ዜ ሊለቅ የሚችል ሰዎችን ብትቀጥር አሁን ያለህ ዲያሪ ነው እና ቢታሰብበት ምን ይመስልሃል፡፡
2. የፌሥ ቡክ ነገር ም ደረሰ አባክህ ወይ ተጨማሪ ኮታ ወይ ቁጥር ሁለት ብለህ ክፈትልን
3. ዳኒ ምፈሳዊ ብቻ አናድርገው እንዲያውም ብሎጉ እኮ በመንፈሳዊ ስሙ ሣይሆን ለሁሉ ተደራሽ ያደረገው ‹‹ዳኒ ብልጥ ነው›› ያለው ገዘክኝ ፀ እንዳለው ነው እና የብሎጉ ስም ዳንኤል ክብረት ቪው ነው የሚለው፡፡
4.
ምስጋና
ኦ ዳኒ ሰላም ለባለቤትህ ሁሉን ከፍላ አንተን ለዚህ ያበቃችህ(ሻካራ እጅ ባንተ እይታ) ይገባታል ምስጋና
ኦ ዳኒ ሰላም ለማንበብ ላልደከሙ ለዓይኖችህ ምስጋና ይገባቸዋል
ኦ ዳኒ ሰላም ለመጻፍ ለማይደክሙት እጆችህ ምስጋና ይገባቸዋል
ኦ ዳኒ ሰላም ለመጓዝ ለመይደክሙት እግሮችህ ምስጋና ይገባቸዋል
ኦ ዳኒ ሰላም ለአእምሮህ ማስታወስን ላልዘነጉት ምስጋና ይገባቸዋል
ኦ ዳኒ ሰላም ከውጭ ስትመጣ መጽሐፍ ለመሸከም ላልዛሉት መታክፍቶችህ ምስጋና ይገባቸዋል
ኦ ዳኒ ሰላም ሰዎችን በማዳመጥ ምስጋና ለተቸራቸው ጆሮዎችህ (አዳመጥከኝ ያለችህ ፈረንጅ የተናገረችው በማስታወስ) ምስጋና ይገባቸዋል
ኦ ዳኒ ሰላም ይሁኝልሕ ለዒሕ ጨጓራ በሽታህ ብዙም ባለማደናቀፉ ምስጋና ይገባቸዋል
.
.
.
.
.
ሀብታሙ ጉ. ነኝ
ምስጋና ለእግዚአብሄር ይግባው እና የአንድኛ ዓመት ዝክሩ ላይ ታደምኩ። ከምናገራው በላይ የሚገርም ነበር። ለቅርብ ወዳጆቼ ዕለቱ እንዴት እንደነበር አጫወትኩ እንዲሁም ወደፊት አጋጣሚዎች ሲፈቅዱ እያስታወስኩ የማጫውት እና የምገልፅ ይሆናል።
ReplyDeleteሲቀጥል ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የከበረ ምስጋናዬን፣ አድናቆቴን እያቀረብኩ ብርታትን የሚሰጥ እግዚአብሄር ይስጥህ እላለሁ። እንዲሰጥህም በፀሎቴ አስባለሁ።
ሲሰልስ ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት አድናቆቴን ሳልከትብ አላልፍም። ለመንጌ (መንግሥተ አብ አራንሺ)እግዚአብሄር ያክብርልኝ።
ባያ
EGZIABHER YIMESGEN ,THANKYOU DN DANIEL. SO SPECIAL AND SUPPER MAN FOR OUR COUNTRY AND OUR CHURCH.
ReplyDeleteTESFAYE
I know your views are constructive and may contribute to our society. But I feel things are too much exaggerated here. There are many people who created websites (blogs) to disseminate their view. What makes yours so special to be celebrated to this extent? More over, isn't the celebration publicizing you not the work? ke kentu wudase gar endet tastarikaleh malete newu.
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል
ReplyDeleteየአንደኛ ዓመት የእይታ ፍሬህን ለማየት አበቃህ።
ስላበረከትከው አስተዋጽኦና ስለ መልእክትህ ብዙም
ማለት የሚያስፈልገኝ አይመስልኝም። ሥራህ ራሱ
ምስክር ነውና።
ተከታዩ ዓመት መልካም የሥራ ወቅት እንዲሆንልህ
እመኛለሁ።
እግዚአብሄር አንተንና ቤተሰብህን ይባርክ።
ረድኤተ አግዚአብሄር አይለየን።
I PARTICIPATE THE PROGRAM,IT IS WONDERFUL. I APPRECIATE THE PERSON WHO SELECT THE GUYS THAT PRESENT THEIR PAPER ON "DANIELS VIEW".
ReplyDeleteI WONDERFULLY APPRECIATE THE PRESENTER AND THE GUYS THAT PRESENT THEIR FEELING.
REALLY SURPRISING PROGRAM
GOD BLESS U GUYS
From Melaku Erjabo
ReplyDeleteIt is very good to share the any controvercial issues. so go ahead Dany.
May God be With us!
It is very intetesting we hope to read the papers peresented in the ocasion.
ReplyDeleteHappy birthday for "የዳንኤል እይታዎች". I was so anxious to participate on your program.
ReplyDeleteደረጀ ገመቹ (ዘደዘ)
ReplyDeleteየተቋሙ ግምገማ
ተቋሙ ተወያዩብኝ : ገምግሙኝ : ብርታቴን ንገሩኝ: ድክመቴን ንገሩኝ ብሎ ምሁራኑን ጠራ: የተቋሙን አባላትን ጋበዘ :: እናም የተጠሩ መጋቢት 18 እለት 2003 ዓም ተገናኙ::ይህ ተቋም ለሰራተኞች ገንዘብ ከፋይ አይደለም: ወኔን የሚያስታጥቅ እንጂ: ጊዜአዊ ዋጋን ከፋይ አይደለም ለሁልጊዜ የሚሆን ስንቅ የሚያሰንቅ እንጂ: ምድራ ዊውን ብቻ የሚያሳስብ አይደለም ሰማያዊውን ጭምር እንጂ: ወገናዊነት ሀገራዊነት መንፈሳዊነትን የሚያሰርጽ ነው እንጂ::
ተቋሙ ማነው የት ይገኛል ካላችሁኝ መጋቢት 18 እለት በተካሔደው የ1ኛ አመት ግምገማ ዝግጅት ላይ የታሪክ ምሁሩ አቶ ብርሃኑ ደቦጭ ” ተከታዮች እንዲኖሩት ፈለገም አልፈለገም ብዙ ተከታዮች አሉት እርሱ እንደ አንድ ተቋም ነው :: የ እርሱ ታሪክ ሊጻፍ ይገባል” ብለው ተናገሩ:: ለ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት::ከታሪክ ምሁሩ በመነሳት ዳኒ ላዘጋጀው የገምግሙኝ ዝግጅት ትዝብት ለመጻፍ መነሻ ነጥቤን የተቋሙ ግምገማ ማለቴ ለዚህ ነው::
ተወያዩ ብኝ ማለት ትልቅነት ነው:: ልክነትም ስህተትም ያለው ከሚሠራ ሰው ነው:: የሠራውትን እዩና ስህተቴን ከሚሻሻል ጎራ ብርታቴን በዚሁ ተጠናክረው ከሚቀጥሉት አድርጋችሁ መድቡልኝ ማለት የጠንካራ ሰው ምሳሌ ነው:: ለነገሩ የማይሠራ ሰው ሰለየትኛው ሥራው ሊጠይቅ ይችላል? ከነቢር ይልቅ ገቢር እንዲበልጥ እናውቃለንና::
የዳኒን ተወያዩብኝ ፕሮግራም ስካፈል እነዚህን ታዘብኩና ልጽፋቸው ወደድኩ:: እነዚሁላችሁ
1 ግምገማው የተካሔደው ሙያዊ እውቀት ባላቸው ምሁራን ነው:: እርምትና ብርታት የሚፈልግ ሰው የሚያገኛቸው ከሙያው ባለቤት ነው::የግምገማውን ሂደትና ውጤት ያቀረቡት ሙያተኞች ለዳንኤል ትምህርት ለኔ ደግሞ ኩራት ነበሩ::ሙያተኞቹ ያለምንም ተጽኖ በነጻነት ያቀረቡት ግምገማ ከእውነት የሙያተኛ ነበሩ::
2 ዝግጅቱ ሽታው መንፈሳዊ ይዘቱ ደግሞ ባለ ፈርጀ ብዙ ጥቅም ነበር::ማሕበራዊ ጉዳዮች በማህበረሰቡ ውስጥ : ፖለቲካዊ ጉዳዮች በፖለቲከኞች መካከል: ሀገራዊ ጉዳዮችን በሀገራችን: መልካም ስብእናን በሰው ዘር መካከል እንዴትማስተማር እንደሚገባ ያሳየ ሀገራዊ ውይይት ነበር:: የሰው ልጅ በቆመበት ቦታ ሁሉ ሊሰራ ስለሚገባው ሥራ ዘርዝሮ የገለጠ ነበር: : የቅዱስ ጳውሎስን በአይሁድ መካከል እንደ አይሁድ ሆኖ በዕብራውያ ን ዘንድ እንደ ዕብራዊ ሆኖ በአሕዛብ ዘንድ እንደ አሕዛብ ሆኖ ያስተማረውን ትምህርት ያስታወሰኝ ዳኒንም ዳግማዊ ጳውሎስ ሆኖ ያገኘሁበት ነው::
3 የጡመራውን ጽሁፎች ኋያልነት የተናገረ ነበር::ግምገማውን ካቀረቡት ምሁራኑ መካ ከል ከዳኒ ጋር ትውውቀ አለመኖራቸውን ሲናገሩ: ራሱ ዳኒ ደግሞ የ e-mail ምዝገባ ለዚያ ሁሉ ታዳሚ ያደረገችው በአካ ል የማያቃት አንዲት ሴት መሆኗን ሲናገር ከዳኒ ልበ ሙሉነት ከምሁራኑ ቅንነት ከሴቲቱ ታታሪነት ጀርባ የጽሑፎቹን ኋያልነት የሚሳይ ጉዳይ ሆኖ አገኘሁት:;ለዚህም የአክሱም ዩ ኒቨርሲቲ ምሁር የሆኑት ገዛኸኝ ፀ ከተቀመጡበት ተነስተው “የዳንኤል ጽሑፍ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚያተኩር ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንዲጠቅም እፈልጋለው “ በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል::
4 በዝግጅቱ መጨረሻ ላይ በእድሜ የከበሩ አባት በዝግጅቱ በመደነቅ እንዲህ አሉ::” በአዳራሹ ያለውን ወጣት ተመልክቼ እኔ በዚህ መገኘት አልነበረብኝም በእንግሊዝኛ ልበለው” አሉና “ I am missfit ” ብለው ተናገሩ::የአዛውንቱ ንግግር ወጣቱ ምንያህል መስራት እንደሚችል በውስጡ የታመቀ ችሎታ ያለው ከዚህ ወጣት ጋር አብሮ መቀመጥ ያለበት የእውቀት ሰው መሆን እንዳለበት ያመላከተ ነበር:: ትክክል ብለዋል:: እኔ ግን ውስጤ አንድ ነገር አሰላሰለ::በወጣትነቴ እምቅ እውቀት ያለ መሆኑ ቢነገረኝም ለወገኔ የሚበጅ ዳኒ በተጋድሎ እያደረገ ካለው አይነት መአድ ለሀገሬ ለሃይማኖቴ አላደረኩምና እኔም እንደ አዛውንቱ “ I am missfit ” አልኩኝ:: እናንተስ ምን አላችሁ?
5 የቤተሰቦቹ ከጎኑ መቆምና ትልቅ አላፊነታቸውን መወጣት ሌላኛው ትዝብቴ ነው:: የዘመኑ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የዲጂታል ካሜራና ቪዲዮ ካሜራ ለስራው መጥቀሙን አውቃ ስጦታ ለባሏ የሰጠችው : ለዝግጅቱ መቃናት ደፋ ቀና ላሉት ወንድሞች ሽልማት ስታበረክት : ለባሏም በርታ ጽሑፍህን ለሚሹ ሁሉ ተግተህ ጻፍላቸው እኔም ከጎንህ ነኝ ብላ የአበባ እቅፍ ስታበረክትለት እንግዳ በመጣ ጊዜ አብርሃም ሙክቱን ሊያርድ ሲጣደፍ ወደ ጓዳ ገብታ ምጣድ ጥዳ የሚበላውን ለማዘጋጀት የምትቻኮለውን ሳራ ያየሁበት ዝግጅት ነበር:; ለካ ዛሬም ሳራ አለች : ለካ ጳውሎስን ልትረዳ ልድያ አለች : ለካ ጳውሎስን ልትረዳ ጠርሲዳም አለች:: ልቤ መረቃት ::ይህን ትጋትሽን እጥፍ ያድርግልሽ : ዳኒም እጥፍ ይጽፋልና::
ይህን ታዘብኩ:: በገዛሁት ጠጠሮቹ መጽሐፍ ላይ ዳንኤልን አስፈርሜ ወጣው:: ማምሻውን ዝግጅቱን ሳሰላስል አመሸው::በማግስቱ ይህን ጻፍ ብሎ እንቅልፌ ጠፋ:; እናም ተጻፈ::
እግዚአብሔር ለቀጣዩ አመት በሰላም ያድርሰን::
Baga gammadde barsisaa Daaniel Kibret.waaqayyo maatiikee hundumaa eegee surraa isaa siif habaa'isu.eebbaaf jaalal akkasumas dhugaa amantiif dhaabachu qulquluu qabsuurota amanti sif haba'su.inkuwan dagimawiyan lijoochii andenga yelidet be'al aderesehi. k.mn
ReplyDeleteወንድሜ ዲን ዳንኤል እንኳን አንደኛ አመቱን ለማክበር እግዚአብሔር በሰላም አደረሰህ።
ReplyDeleteይቺ ቀን እኛ በተለይ ውጭ ላለነው ኢትዮጵያውያን ልዩ ነው። ኢትዮጵያዊ ዘይቤውን ሳይለቅ በሁለንተናው ሙሉና ጣፋጭ የሆነ ማዕድ መመገብ የጀመርባት ቀን። አሁን የሚኖርበት አለም ካደገበት ባህል ጋ ሲጋጭበት አይምሮውን ያስጨነቀውንና የማመቻመቻ መስመር ብሎ እሱ ጠፍቶ እኛን ሊያጠፋን ከተለያየ አቅጣጫ ከሚወረወረው የጥፋት መርዝ እንድንላቀቅና እራሳችንን እንድንፈትሽ ኢትዮጵያዊ ፈዋሽ ክኒን መዋጥ የጀመርንባት ቀን። ይህማ አይቻልም ብለን ተስፋ ቆርጠን ያገኘናትን ስራና ምግብ ይዘን ስንኳትን ሰተት ብሎ ከቤታችን መጦ በዚህም ሞክረው የማይቻል የሚመስለውን አለዝበው ሰርተውና መስክረው ካለፉት ጠንካራ አባቶች እኮ ነው የተወለድከው እያለ የሚያጽናና መካሪ ያገኘንባት ቀን። ምኑ ተዘርዝሮ ያልቃል። እንዲያው በጥቅሉ የጀመርኸውን ሰውን ወደ አይነ ልቦናው የመመለስ ተግባርህን እግዚያብሔር እስከ መጨረሻው እንድትከውን ይረዳህ። ድንግል ማርያም ጥላ ከለላ ትሁንህ።
ወንድምህ ከጀርመን
ዳኒ ምስጋና ለእግዚአብሄር እግዚአብሔር እረጅም የአገልግሎት ዘመን ይስጥህ
ReplyDeleteበተዘጋጀው ልዩዝግጅት ታዳሚ በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ
ReplyDeleteI have read all and every thing written on the anniversary and i am very happy. thanks to our God for the givenness of Dn. Daniel and the like!!!!!!
ReplyDeleteDn Daniel, I am really satisfied, when I read your all articles. Oh God thanks very much!!! I am a blessed person. God bless you.
ReplyDelete