Friday, March 25, 2011

ነጻነት፤ ምን?

አንዳንድ ጊዜ የአፍሪካ አሜሪካውያንን የጥንት ታሪክ ስመለከት በአንድ ነገር እኛን እወቅሳለሁ፡፡ ከነጻነታችን ያገኘነው ነገር ምንድን ነው? እያልኩ፡፡
 አባቶቻችን እና እናቶቻችን ያቆዩልን ነጻነት በአራት ፊደላት ብቻ ተገልጦ የሚያልቅ ነገር አይደለም፡፡ እጅግ ጥልቅ እና ምጡቅ ነገር ነውና፡፡
የራሳችን ፊደል አለን ስንል ፊደል የነበረን እኛ ብቻ ሆነን አይደለም፡፡ ሌሎች አፍሪካ ውያን እና ላቲን አሜሪካውያንም እንደኛ ፊደል ነበራቸው፡፡ ግን በቅኝ ገዥዎች ምክንያት ጠፋ፡፡ የራሳችን ቋንቋ አለን ስንል ቋንቋ የነበረን እኛ ብቻ ሆነን አይደለም፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ቋንቋቸው ተዳክሞ በቅኝ ገዥዎቻቸው ቋንቋ የሚናገሩ ሆነዋል፡፡
እስኪ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋዎችን እንይ፡፡ የኅብረቱ የመግባቢያ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ዐረብኛ እና ፖርቱጊዝኛ ናቸው፡፡ አንድም አፍሪካዊ ቋንቋ የለበትም፡ አፍሪካውያን በራሳችን ቋንቋ መግባባት አንችልም ማለት ነው፡፡
የራሳችን የስም አጠራር የነበረን እኛ ብቻ አልነበርንም፡፡ ሌሎች አፍሪካውያን እና ደቡብ አሜሪካውያንም ነበራቸው፡፡ ግን ጠፋባቸውና ዛሬ በፈረንጆቹ ስም ይጠራሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ሀገራቸው እንኳን በራሳቸው ቋንቋ የማይጠራ ወገኖቻችን አሉ፡፡ ካሜሮን የምትጠራው በቅኝ ገዥዋ ስም ነው፡፡ አንጎላ ዛሬም የምትጠራው በቅኝ ገዥዋ ስም ነው፡፡ ምኑ ቅጡ፡፡
ኢትዮጵያ እኮ ከምድረ አፍሪካ በኢየሩሳሌም ርስት ያላት ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ራስዋ ለራስዋ የተረጎመች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ናት፡፡ ራስዋን በራስዋ የሰበከች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ናት፡፡ ሌሎችን ነጻ ለማውጣት ኮርያ እና ኮንጎ እንደ ሀገር የዘመተች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ናት፡፡
የምትተርከው ብቻ ሳይሆን የምታሳየው ታሪክ ያላት፤ ከዓለም ድንቅ ቅርሶች መካከል የራስዋ ድርሻ ያላት ሀገር ናት፡፡
ታድያ ይህ ሁሉ ታሪክ በዕድገት እና በሥልጣኔ ካልታገዘ ከታሪክነት ወደ አፈ ታሪክነት፣ ከአፈ ታሪክነትም ወደ ተረትነት መውረዱ አይቀሬ ነው፡፡
አሁን ለኢትዮጰያውያን አንድ ነገር የሚያስፈልገን ይመስለኛል፡፡ ከመዋቅር ውጭ ማሰብ፡፡ አንዱ ትልቁ በሽታችን ባለፉት ዘመናት በመዋቅር ብቻ እንድናስብ መደረጋችን ነው፡፡ ስለ ትምህርት ትምህርት ሚኒስቴር፤ ስለ እርሻ ግብርና ሚኒስቴር፣ ስለ ንግድ ንግድ ሚኒስቴር፣ ስለ ሳይንስ የሳይንስ ሚኒስቴር፣ ስለ ታሪክ የባህል ሚኒስቴር እያልን ብቻ ነው የምናስበው፡፡
እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በግላቸው ለሀገራቸው ሲንቀሳቀሱ እንኳን እንዴት ቻልክበት? ብሎ ከማድነቅ ይልቅ «ማን ፈቅዶልህ ነው ብሎ የማስደንገጡ አባዜ አለብን፡፡ ምክንያቱም ከመዋቅር ውጭ የሚሠራ ሰው ሁሉ ያበላሸ እንጂ የሠራ ስለማ ይመስለን፡፡
የመንደርን ቆሻሻ መንደርተኛው ተሰባስቦ፣ ዘዴ ዘይዶ፣ ገንዘብ አዋጥቶ ከማጽዳት ይልቅ ወረቀት ገዝቶ፣ ደብዳቤ ጽፎ ማመልከቻ ይዞ ማዘጋጃ ቤት መሄድ የሚቀናን በመዋቅር ካልሆነ በቀር ለማሰብ ስለሚቸግረን ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ለሁሉም ነገር ኮሚቴ ማዋቀር የሚቀናን እና ካልተሰበሰብን በቀር ማቀድ፣ መሥራት እና አዲስ ሃሳብ ማመንጨት የማንችለው በግለሰብነት ምንም የሚሠራ ስለማይመስለን ነው፡፡
ሀገርን የማሳደግ ኃላፊነት የዜጋው በሙሉ ነው፡፡ ማንም ሊሰጠው ማንም ሊነሣው የማይችል፡፡ መዋቅሮች ደጋፊዎች፣ አሳላጮች እና መንገዶች እንጂ ጭንቅላቶች አይደሉም፡፡
እናም ቢሮአችንን ለማስተካከል እና ለማሻሻል እኛው በቂ ነን፣ ሠፈራችንን ለማስተካከል እኛው በቂ ነን፡፡ አዳዲስ ነገር ለመፍጠር እኛው በቂ ነን፡፡ ድህነትን ለመንቀል እኛው በቂ ነን፡፡ ስለ ሀገሬ ለማሰብ የግድ ፓርቲ፣ ማኅበር፣ ፎረም፣ ሊግ አያስፈልገኝም፡፡
መፈክር መለጠፍ፣ ቢል ቦርድ መሰቀል፣ መሪ ቃል ማስተጋባት፣ ቲሸርት መልበስ፣ ቆብ ማጥለቅ፣ ሻማ ማብራት፣ ትርዒት ማሳየት አያስፈልገንም፡፡ እኔ ራሴ በቂ ነኝ፡፡ እኔ ኃላፊነት አለብኝ፡፡ ማንም ሳይጠራኝ፡፡ ማንም ሳያሰባስበኝ እኔ ራሴ፡፡
ታድያ ነጻ ሕዝብ መሆኔ፤ ባለ ታሪክ፣ ባለ ቅርስ፣ ባለ ቋንቋ መሆኔ ልዩነቱ የት ላይ ነው፡፡ በነጻነት ማሰብ፣ በነጻነት መሥራት፣ በነጻነት መኖር፣ በነጻነት መፈላሰፍ ካልቻልኩ፡፡ ነጻነቴ ታሪክ ብቻ ነው ማለት ነው?
ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ፣ በግል እናስብ፣ በጋራ እንሥራ፣ በመዋቅር እንጠቀም፡፡ ያን ጊዜ 3000 ዘመን ነጻነታችን ትርጉም ይገባናል፡፡  

23 comments:

 1. Dn. dehan neh?

  Begil enasib begara enisira sibal algebagnim. Sew endet begara sayasib begara yiseral? Lemisale ante ena balebetih abirachu yalakedachihutin neger endet begara tiserutalachu?

  Beterefe gin Yetsihufu atekalay hasab tiru new.Lehagarachin ediget hulachinim halafinet alebin.

  Berta

  Tariku

  ReplyDelete
 2. ewnet bilehal memhir Daniel yichi hager endatadg ende eshok anko yeyazat neger andu yihe yimeslegnal tiru tizibt new!!!

  ReplyDelete
 3. egzer yistilin lib yisten betam tiru eyita newu wondmie daniel. fitsamiehin yasamirilin taito kemetifat yitebikih. Amen!!!

  ReplyDelete
 4. "ታድያ ይህ ሁሉ ታሪክ በዕድገት እና በሥልጣኔ ካልታገዘ ከታሪክነት ወደ አፈ ታሪክነት፣ ከአፈ ታሪክነትም ወደ ተረትነት መውረዱ አይቀሬ ነው፡፡" Let Us stand to change our selves and our country. may the help of God with his mother Marry Be with us. Dani God Bless you.

  ReplyDelete
 5. Dani

  This my best article. we need to work hard and contribute for our country. Just keep up writing....

  ReplyDelete
 6. yegermal! alemachen yehenenem asalefalech.

  ReplyDelete
 7. አሁን ለኢትዮጰያውያን አንድ ነገር የሚያስፈልገን ይመስለኛል፡፡ ከመዋቅር ውጭ ማሰብ፡

  ታድያ ነጻ ሕዝብ መሆኔ፤ ባለ ታሪክ፣ ባለ ቅርስ፣ ባለ ቋንቋ መሆኔ ልዩነቱ የት ላይ ነው፡፡ በነጻነት ማሰብ፣ በነጻነት መሥራት፣ በነጻነት መኖር፣ በነጻነት መፈላሰፍ ካልቻልኩ፡፡ ነጻነቴ ታሪክ ብቻ ነው ማለት ነው?
  ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ፣ በግል እናስብ፣ በጋራ እንሥራ፣ በመዋቅር እንጠቀም፡፡ ያን ጊዜ የ3000 ዘመን ነጻነታችን ትርጉም ይገባናል፡፡

  ReplyDelete
 8. ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ፣ በግል እናስብ፣ በጋራ እንሥራ፣ በመዋቅር እንጠቀም፡፡ ያን ጊዜ የ3000 ዘመን ነጻነታችን ትርጉም ይገባናል፡፡

  ReplyDelete
 9. Tebarekelege Dn Dani leke belehale!

  ReplyDelete
 10. Do You Know you are a wise person....You always see everything according to different dimensions ... You gotta it from above! May GOD Bless you!

  ReplyDelete
 11. what does it mean FREEDOM???

  ReplyDelete
 12. እጅግ ግሩም የሆነ እይታ። -ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ፣ በግል እናስብ፣ በጋራ እንሥራ፣ በመዋቅር እንጠቀም፡፡ ያን ጊዜ የ3000 ዘመን ነጻነታችን ትርጉም ይገባናል፡፡ -
  ይህ ለእኔ ጥሩ ድምዳሜ ነው። ነገር ግን ተግባራዊ ለማድረግ ይህ አይነቱ አባዜ እንዴት ሊመጣ ቻለ? ኮሜቴ ማቋቋም ለችግሮች መፈትሄ መፈለጊያ መንገድ እንዲሆን መቸ ተጀመረ? ኮሚቴ ማቋቋሙ በውኑ መፍትሔ አምጥቷል ወይስ አድበሳብሶ አልፎታል። ለምሳሌ በአንዳንድ መስሪያቤት የማየው የዛሬ 10 ዓመት አካባቢ ለነበረ ችግር በእየ ጊዜው ለችግሩ መፍትሔ ፍለጋ ኮሚቴ ሲቋቋም ነው። መቋቋሙ ባልከፋ ግን አስቂኝነቱ የዛሬ አስር አመት አካባቢ እንደ መፍትሔ ተደርጎ በቀደሙት ኮሚቴዎች የቀረበ ሃሳብ አሁንም ባዲሶቹ ኮሚቴዎች ትንሽ ለወጥጥ ተደርጎና የመፍትሔው አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ስም ዝርዝር ተቀምጦበት መውጣቱ ነው። ስለዚህ አንድ የተበላሸ ነገር አለ ማለት ነው። እናም የችግራችን መንስኤ ምን ድን ነው የሚለቀውን ማወቅ ያለብን ይመስለኛል። መንስኤውን ካወቅን መፍትሔውን ተልሞ እንዴት ትግበራ ላይ ይዋል የሚለው ቀጣይ ይሆናል። አሁን አሁን በነጻነት እንዳያስብ አመለካከቱ የተሰለበ ትውልድ እየመጣ ይመስለኛል። በድሃ ሃገራት ችግሩ የከፋ ነው። ያኔ ሰውየውን ወስደው መስራት የሚገባውን ነገር (ፋብሪካ ውስጥም ሆነ ቤት ውስት)ስልጠና ሰጠው ባደባባይ ይሸጡት ነበር። አሁን ግን አቅጣጫቸውን ቀይረው የመጡ ይመስለኛል። የእነሱን ሃሳብ ትክክል ነው ብሎ እንዲቀበል የራሱን ማንነት በራሱ ወይም አጠገቡ ባለው እንዲንኳሰስና እንዲጠላ ማድረግ። ለዚህ አይደል ኢትዮጵያ ሰው ሆኖ ከመፈጠር አሜሪካ----- የሚል ደፍሮ ተናጋሪ የጠፋ ትውልድ ለማየት የበቃነው። እያንዳንዱ አሁንም ከዚህ አባዜ የወጣ አይመስለኝም። ነጻነትን በተንሸዋረረ አይን እንዲያያት ራሳቸው በፈጠሩአቸው ፊልሞችና ቴክኖሎጂዎች ይሰበካል። እናም ሂዶ ጉልበት አደር ለመሆን ዘወትር ያልማል። እኔ በራሴ ልዩ ሆኜ የተፈጠርሁ ሰው ነኝ የሚለው አመለካከት ኮስሶ ይታያል። እንዴት ወደ ውስጣችን አስበን ታምራዊ የሆነ ስራ እንስራ የሚለውን አሁንም በማይነጥፈው ብዕርህ ብትመነጋግለው እንዴት ደስ ባለኝ!!!!
  ለራሱ ትልቅ ክብር የሚሰጥ ወኔ የተላበሰ ሰው ለመሆን ያብቃኝ!!!

  ReplyDelete
 13. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel
  Lezih hulu medihanialem kegn gar yihun. AMEN!!!

  ReplyDelete
 14. የራስ ባህል የራስ ቋንቋ የሚያኮራን ህዝብ ብንሆን ኖር ከኢትዮጵያ ውጪ ያለው ህዝብ ብቻ ብቂ ነበር በባህላችን እና በቋንቋችንን ለመኩራት እና ለማስተዋውቅ። ግን በብዙ ሚልዮን የሚቆጠረው በተለያየ አለም ላይ የተበተነው ይህ ህዝብ በውጪው አለም ላይ የራሳችንን ጥለን በነሱ ነገሮች ስንዋጥ። የሚያስፈራው ነገ ላይ ሀገራችን ስንመለስ ቋንቋውን የማያቅ ብዙ ትውልድ ፈጥረን ታሪክ አበላሽተን መመለሳችን ነው። በራስ ነገር ከመኩራት በንጮች ባህል መዋጣችን ልጁ የራሱን ቋንቋ ከሚያስተምረው ቋንቋውን እንዲጥል ማረጉ...ልጁ የራሱን በአል ከሚያከብርለት የነጮቹን ሲያከብርለት...የልጁን ስም ሲያውጣ ለነጮቹ የሚመች የነሱን ስም ሲያወጣለት ነገ ይህ ልጅ እንዴት ሆኖ በ ሀገሩ ባህል እና ቋንቋ ሊኮራ ይችላል?.።እያንዳንዱ ሰው በራሱ በሆነው ቋንቋ እና ባህል ካልተመካ መቼም ይሄ ለውጥ ሊመጣ አይችልም።

  ReplyDelete
 15. ማን ያዘዋል።March 25, 2011 at 9:50 PM

  ትላንትና መዋቅር እያልክ ትሰብክ ነበረ ዛሬ ደግሞ ተቃራኒውን እንዴት ነው?ጎበዝ የምትገለባበጠው። ወይስ ምን አይነት ለለእኮ ነው ከበስተጀርባህ ያለህ?
  ራስህን መርምር። ትላንት ምን ትል ነበረ። ዛሬስ በህብረ በማኅበር መስራትን ለመተቸት
  ምን አነሳሳህ?

  ReplyDelete
 16. Our generation past that history and noboday pay any attention to it. If you talk about such things you are "huwalaqer" and .... In a country like ours first of all the leaders must understand the meening of freedom and apply it properly on others. They wiped out from the brain of young generation with their toxices. It is shame now if I give my Son a name "Kebede or Bekele Manyazewal".

  Manyazewal! It is better to ask you why you didn't like the article. He didn't say "Mewaqir Ayasfeligim". His point as he clearly put, is the value of freedom. Why do you want to comment on such a way? Freedom is the best thing what God given for all of us.

  ReplyDelete
 17. dear dn. the issue you raised is very valuable, but i have a different openion as i discussed below

  collective thinking, discussion, and working in association will not degrade the value of freedom. The important thing is the result out of collective or individual performances. According to bible, being in group is highly supported due to several reasons. The disciples were also ordered by Our saviour Jessus christ to be in group of two when he send them for delivering service.

  this is not to exclude performing privately, but in my openion to be in collection/association is better than private performance. Otherwise, even if to do two good things it requires to sequence them through discussion. and this can only be possible through through discussion and understanding in collection.

  Abiot k oldenburg

  ReplyDelete
 18. @ማን ያዘዋል፡ ጸሃፊው ለማስተላለፍ የፈለገው- እኔ እንደተርዳውት፡፡ እንደተሳቢ ዝንብለን አንሳብ ለማለት የመስልኛል።፡ከተሳሳትኩ እታረማለው። "ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ፣ በግል እናስብ፣ በጋራ እንሥራ"

  With Love from Canada

  ReplyDelete
 19. mwkir aynur sayhone hulgize keskash anfeleg lemalet new dn daniel yetnagerkew.berokerasi anabeza new wegene.aymerochen bezu mesrat sichel mwkir aytebek new gobez. Negeru bebahelachen becha sayhone bhelwenachnem lay cheger eyfetere new. Kalhiwot yasemalen.

  ReplyDelete
 20. Is it to mean individual is an end by itself?

  ReplyDelete
 21. ሰላም ዳኒ፡

  እውነትህን ነው "ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ" ለምሳሌ የእኔን ተምክሮ ልጥቀስ፦ አገራችን ያላት የውሃ ሃብት ሌሎች አገርች እንዳላቸው ነዳጅ እና የማእድን ሃብት ነው። ሌሎች አገሮች የተፈጥሮ ሓብታቸውን ሽጠው ለህዝባቸው ህክምና፤ትምህርት... እንደሚያማሉ ሁሉ። እኛም እንደአገሮቹ ውሃችንን የመሸጥ መብት አለን፤ ብዬ የሌሎችን አገሮችን ምሳሌ፦ እንደ ሌሴቶ ፤ ማሌዥያ እና እንደቱርክ ያሉ አገራት የወንዛቸውን ውሃ ለመሸጥ የሚያደርጉትን እንቅሰቃሴ መበግለጽ። ለተለያዪ የአገርችን እንባሲዎች በመረጃ በማስደገፍ ጽፌ ነበር።

  የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትራችን ውሃን ለግብጽ ለመሸጥ አናስምብ ብለው ስለነበር። ከአንዱ ወጌኔ እሁን አገራችን በአባይ ወሃ ላይ የያዘችው እቋም (equitable-share) ትክክል ነው ብሎ መለሰልኝ። የእኛን ውሃ ገዥ አፈላልገን መሸጥ አልበን ስንል የሚቅወሙን፤ የኛ የተፈጥሮ ሃብት ሲዎን equitable-share እያሉ የሚያቅራሩ ፤ በሌሎች አገሮች የተፍጥሮ ሀብት ላይ ግን ይንን ሃሳባቸውን ማይደግሙ ወጌኖች ከመዋቅር አሰተሳሰብ ሲወጡ ማየት ይናፍቀኛል።(በዚላይ ሳልጥቅስ የማላልፈው በሚሰሩት ግድቦች በጣም ደስተኛ ነኝ)።

  በነገራችን ላይ Nov 03, 1927 በጊዜው የነበሩት ንጉስ ጄ ጂ ዋይት እንጅነሪንግ ከተባለ የአሚሪካ ድርጅት ጋር ድርጅቱ ግድብ በጣና ላይ እንዲሰራና ለእንግሊዝ(ለሱዳንና ግብጽ) ውሃ እየሸጠ ከትርፉ ለአገራችን እንዲያካፍል እና ከጊዜ በዋላ የግድቡን በለቤትነት ለአገራችን እንዲያስተላልፍ በጊዜው የነበርው የአገርቱ መንግስት ተስማምቶ ነበር http://news.google.ca/newspapers?id=6PIiAAAAIBAJ&sjid=nMwFAAAAIBAJ&pg=6509,196887&dq=ethiopia+nile&hl=en። እናም ከመዋቅር አስተሳሰብ እንውጣ እና እንደ ሌሴቶ (ትንሻ አገር) ዉሃ ለምን ወሃ ለሌላቸው አንሰጥም።
  በነገራችን ላይ ውሃ ከአዲስ አበባ ካይሮ ውስጥ እንደሚረክስ ያወቃሉ።

  With Love from Canada

  ReplyDelete
 22. HI folks, the only thing I know is, I am still a slave in my own country. I don't know how you guys interpret this an abstract word "Freedom." I cann't talk. I cann't write. I cann't oppose.I can't even agree.....millions of things to say. I can do all of those mentioned above if I am ready to die! For now...let us see these.

  ReplyDelete
 23. ጥቂት ለማን ያዘዋል…………………………………..
  ወንድም ማንያዘዋል በራስ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌላ ማሰብህ መልካም ነውን?
  ጥላቻ ከካንሰር በሽታ ይከፋል መገለጫው ደግሞ በዚህ ጹሁፍ ይታወቃል ይቅርታ ለድፍረቴ ለጥቂት ጊዜ በራሴ ቢደርስ ቢዬ አሰብኩ ውስጤ ተናደደ እርግጥ ነው ጸሀፊው ዲ.ዳንኤል ውዳሴ ከንቱ ስለማይፈልግ ላይከፋው ይችላል አካፋን አካፋ ማለት መገሰጽ መልካም ነውና እንደ ይሁዳ ወጪት ሰባሪ መሆን መልካም ኣይደለም ይቅርታ ግን ስሜታዊ መሆኔ ይገባኛል በፍቅር ባሽንፍህ ደስ ባለኝ ግን አልሆነም እባክህ ዲ.ዳንኤል ለሁለታችን ጸሎት አድርግልን።

  ReplyDelete