Wednesday, March 23, 2011

"ልብ ካላስተዋለ ዓይን ብቻውን አያይም"

በፍቅር ለይኩን (ከደቡብ አፍሪካ)
 
ዲያቆን ዳንኤል! ድንቅ ትረካ! ድንቅ እይታ፣ ጥሩ አስተውሎት ነው! ...ስለ ማየት ወይም ስለ እይታዎቻችን ሳስብ ብዙ ነገር በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ፤ አላውቅም ብዙዎቻችን ከአስተዳደጋችን ይሁን ወይም ከሌላ ምክንያት በአብዛኛው ጊዜ በፊለ ፊታችን ከተሰቀለው ነጭ ሰሌዳ ዓይናችን ለማየት የሚታደለው በነጩ ሰሌዳ ላይ ያለችውን ጥቁር ነጥብ እንጂ የሰሌዳው ነጭነት ወይም ብሩህነት አይደለም፤ ሁሉን አቀፍ ድምዳሜ (hasty generalization) እንዳይመስልብኝ እንጂ ለሕይወት ያለን የጨልምተኝነት አባዜም (spirit of pessimism) ከዚሁ ከዓይናችን ወይም ከአመለካከታችን መንሸዋረር የተነሳ እንደሆነ እገምታለሁ።
ሓሳቤን የሚያጠናክርልኝ ታሪክ ልጥቀስ፦ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ህዝበ እሥራኤል 430 ዓመታት የግብጽ ባርነት በጸናች ክንድ፣ በተዘረጋች እጅ በታላቁ መላእክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደ ምድረ ርስት ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ የአባቶቻቸው አምላክ ቃል ኪዳን የገባላቸውን የከነዓንን ምድር ለመውረስ በተዘጋጁበት ጊዜ መሪያቸው ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከህዝቡ መካከል አሥራ ሁለት ሰዎችን መርጦ ለአርባ ቀን ያህል የከነዓንን ምድር ሰልለው ወሬ ይዘው ይመጡ ዘንድ ላካቸው። ምድሪቷን የሰለሉ ሰዎች ከአርባ ቀን በኍላ ተመልሰው ለሙሴና ለህዝበ እሥራኤል እንዲህ የሚል ዜና ይዘው መጡ፦

"ምድሪቷስ እንደተነገረላት ማርና ወተት የምታፈስ፣ የምድሪቷም ፍሬ የወይኑ ዘለላ ጋን ይመላ፣ የስንዴው ዛላ እፍኝ ይመላ...ግና በዛ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ረጃጅም ናቸው...እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፣ ደግሞ እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን፤" በማለት የሕዝበ እሥራኤልን ልብ አሸበሩት፣ ከዚህም የተነሳ እሥራኤላውያን በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ፣ አለቃ ሾመን ወደ ግብጽ ብንመለስ ይሻለናል በማለት ድምጻቸውን አንስተው ጮኹ 

ነገር ግን ከተላኩት ሰዎች መካከል ሁለቱ ኢያሱና ካሌብ፦ "የከነዓንን ምድር እግዚአብሔር እንደተናገረ ያወርሰናል፣ እነዛ ታላላቅና ግዙፍ ሰዎችንም እንደ እንጀራ ይሆኑልናል፣ የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ ጥላቸው ከላያቸው ተገፏል፣ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው አትፍሩአቸው" በማለት የሕዝቡን ልብ ለማጽናናት ሞከሩ በእነዚህ በሙሴ በተላኩት ሰዎች መካከል ከሁለት የተለያዩ እይታዎች የተነሳ በሕዝበ እሥራኤል መካከል ትልቅ ፍርኃትና ነውጥ ሆኗል፤ ለአስሩ ሰዎች የታያቸው የጠላቶቻቸው ግዙፍነትና አስፈሪነት፤ እንዲሁም እነሱ በእነዚህ ርጃጅም ሰዎች ፊት እንደ አንበጣ ሆነው ነው ራሳቸውን ያዩት፤ በአንጻሩ ለኢያሱና ለካሌብ ደግሞ ሰዎቹ ጥላቸው የተገፈፈ፤ ከእሥራኤል ጋር ካለው ከአባቶቻቸው የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያእቆብ አምላክ ክብርና ኃይል የተነሳ በፊታቸው ኔፍሊምና ኤናቅያውያን እንደ እንጀራ እንደሚሆኑላቸው ነበር የተገነዘቡት በኢያሱና በካሌብ ዓይን ወይም እይታ!

ኢያሱና ካሌብ ጠላቶቻቸውን ያዩበት ዓይን ተራ ዓይን አልነበርም፤ ጠላቶቻቸውን ያዩበት እይታም አስሩ አብረዋቸው ከተላኩት እይታ በእጅጉ የተለየ መንፈሳዊ ዓይን ነበር፤ እነዛን ረጃጅምና አስፈሪ ሰዎች አይተው ወኔ የከዳቸው አስሩ ሰላዮች ራሳቸውን በእነሱ ፊት እንደ አንበጣ አድርገው ነበር ያዩት፤ ከዛም አልፎ ፍርሃታቸውንና ድንጋጤያቸውን ለሕዝበ እሥራኤል ጭምር በማሻገር የሕዝቡን ልብ አራዱት

ለእነዚህ ሰዎች ትላንት በሙሴ በትር የኤርትራ ባህር ተከፍሎ የተሻገሩበት፣ የግብጻውያን ፈረሰኞችና ሰረገሎች የኤርትራ ባህር ለዘላለም ታሪክ የሆኑበት የህያው አምላካቸው ክንድ ዛሬ በእነሱ ዓይን እንደምንም ተቆጥሮ ልባቸውና ዓይናቸው ከእግዚአብሔር ተነስቶ ስለ ጠላቶቻቸው ግዙፍነትና ኃይለኝነት በማውራት ራሳቸው ፈርተው ሌሎችም ጭምር እንዲፈሩ፣ ራሳቸው ተሸንፈው ሌሎችም እንዲሸነፉ፣ እነሱ ወኔ ከድቷቸው ሌሎችም ወኔ ቢስ እንዲሆኑ በማድረግ በክፉና በሽንፈት ወሬ የሕዝባቸውን ልብ ፈቱት... "ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው" እንዲሉ አባቶቻችን ይህን ወሬ የሰሙ ሕዝበ እሥራኤል አለቃ ሹመን ወደ ግብጽ እንመለስ በማለት እንደገና ወደ ባርነት እነደገና ወደ መገዛት ወደ ሞት ሀገርእምባቸውን በእጃቸው እፍኝ ወደ ሚሰፈሩበት የምሬት ሕይወት ሊመለሱ ምክክር ጀመሩ።

ዛሬም ተስፋ፣ ራእይ፣ ፍቅርና እምነት በጎደለው ልባቸው በሚያዩትና በሚሰሙት ነገር ራሳቸው ተሸብረው ሌሎችን የሚያሸብሩ ከከበባቸው ጨለማና ከተጋረጠባቸው ተራራ ባሻገር አስደናቂ ብርሃንና ደልዳላ ሜዳ መኖሩን በማይረዱ፤ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ ኤልሻዳይ መሆኑን በዘነጉልክ ህዝበ እሥራኤልን እንዳሸበሩት ያሉ እይታቸው የተንሸዋረረ ከእግዚአብሔር ይልቅ በሚታዩ ግዙፍ መሰል ነገሮች ላይ ዓይናቸውን ያደረጉ ሰዎች ዛሬም በዘመናችን በቤተ ክርስቲያናችን፣ በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ተቋሞቻችን ውስጥ በብዛት አሉ። 

ግና በኢያሱና በካሌብ ዓይን/እይታ የእስራኤል አምላክ ዛሬም ክንደ ብርቱ እንደሆነ፣ ትናት የኤርትራን ባህር ከፍሎ ያሻገራቸው የአባቶቻቸው አምላክ፣ አርባ ዘመን ሙሉ ቀን በደመና ዓምድ፣ ሌሊት በእሳት ዓምድ የመራቸውን፣ እንዳይርባቸው ከሰማይ መና እያወረደ የመገባቸውን፣ እንዳይጠማቸው ከዓለት ውኃ እያፈለቀ ያጠጣቸውን አምላክ ትልቅነት ዘንግተው እንደ አስሩ ጓደኞቻቸው ራሳቸውን እንደ አንበጣ ሳይሆን እንደ ታላቅ የእግዚአብሔ ሰራዊት በመቁጠር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አትፍሩ አትደንግጡ በማለት ልባቸውን አበረቱ፣ መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚንግረንም ያችን የተስፋ ምድር ለማየት የታደሉት ከግብጽ ባርነት ከወጡ 600 000 የእሥራኤል ህዝብ መካከል ኢያሱና ካሌብ ብቻ ናቸው። በበረሃ ጉዞአቸው የእግዚአብሔርን ታላላቅ ታምራትና ድንቅ ማየት የተሳናቸው ሁሉ ከተንሸዋረረ እይታቸው ጋር የበረሃ ሲሳይ ሆነው ነው የቀሩት።

መጽሀፍ ቅዱስ በራእይ መጽሀፍ ውስጥ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ዮሐንስ በኩል ለሎዶቅያ / መልአክ በተጻፈው መልእክት እንዲህ የሚል ሀይለ ቃል ይገኛል፦

"... ሀብታም ነኝና ባለጠጋም ሆኛለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለሆንህ፣ ጎስቋላ ምስኪን ድሃም 'እውርም' የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፣ ባለጠጋ እንድትሆን ... 'እንድታይም' 'ዓይኖችህን' የምትኳለውን ኩል ከእኔ እንድትገዛ እመክርሃለሁ...."
                                                                  
ራእይ ፫፥፲_፲፰

ዛሬም ብዙዎቻችን በክርስትና ሕይወታችንም ሆነ ለአጠቃላይ የሕይወት ምልከታችን ወይም ሕይወትን ለምንመዝንባት ዓይናችን... በትክክል ሰለራሳችንም ሆነ ስለሌሎች የጠራ እይታ ይኖረን ዘንድ... የክርስትና ሕይወታችንን ጅማሬና ፍጻሜ አጥርተን ማየት እንችል ዘንድለዓይኖቻችን ጥራት፣ ለተንሸዋረረ እይታችን መድሃኒት/ፈውስ የሚሆነንን ኩል ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ዘንድ እንገዛ ዘንድ ያስፈልገናል።
 
ብዙዎቻችን ራሳችንን፣ ቤተሰባችንን፣ የትዳር አጋሮቻችንን፣ የመስሪያ ቤት አለቆቻችንን፣ ሀገራችንን፣ ህዝባችንን፣ ሕይወታችንን፣ ክርስትናችንን...ወዘተ የምናይበት ዓይን/እይታ ይለውጥ ዘንድ የሚያስፈልገው ይመስለኛል፤ የዲያቆን ዳኒኤልም ጽሁፍ ጭብጥ ይሄ ይመስለኛል፣ ለተስተካከለ እይታ የልብ ለውጥ ያስፈልገናል፣ "ልብ ካላስተዋለ ዓይን ብቻውን አያይም" የሚለው የአባቶቻችን ተረት ለነገሮች/ለሕይወት ያለንን እይታ የሚወስነው በዓይናችን የምናየው ብቻ ሳይሆን በልባችን ምናስተውለው የተነሳ መሆኑ ልብ ልንለው ይገባል። ወንድማችን ንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን!13 comments:

 1. egiziyabehir yakibrelin tsegawin yabizalin

  ReplyDelete
 2. Well said befikir leyikun "ልብ ካላስተዋለ ዓይን ብቻውን አያይም" የሚለው የአባቶቻችን ተረት ለነገሮች/ለሕይወት ያለንን እይታ የሚወስነው በዓይናችን የምናየው ብቻ ሳይሆን በልባችን ከምናስተውለው የተነሳ መሆኑ ልብ ልንለው ይገባል።

  ReplyDelete
 3. አንድ ታዳሚ የዳንኦልን ዓይን መልእክቱን ወድዶት አቀራረቡ ግን የተጋነነ እንደሆነ ጠቆም አድርጎ ነበር፡፡

  አሁን ደግሞ፥ ወድማችን ዳንኤል ምናባዊ ምስልን በሚፈጥር የትረካ ስልት ያቀረበልንን የአስተውሎት ጉዳይ በላመውና በጣመው እውተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አንተ ደገምክልን፡፡ የዳንኤል አቀራረብ የተጋነነ ከመሰለ፥ የኢያሱና የካሌብ አሕዛብን ገለባ አድርጎ መመልከትማ ይበልጡኑ ግነት ያየለበት ሊባል ነው፡፡

  አይደለም፡፡ በእነዚህ ሁለት ጽሁፎች እንኳን የማስተዋል ደረጃችን ልዩነት በግልጽ የታየ ይመስለኛል፡፡ ነገሮችን የምንመዝንበት ዓይነ ለቡና እኮ ነው ማስተዋል የሚባለው፡፡ ይህ ደግሞ ለሁሉም እኩል የሚሰጥ አይደለምና ለእኛ ያልገለጠልን ለሌላው አይገለጥለትም ወይም ግንነት ሊሆን ይችላል ማለት አይሆንም

  መልካም ተሳትፎ

  ReplyDelete
 4. በእምነት የምናይበትን የሀይማኖት አይን አይንሳን!

  የሚያይ አይን ከሌለን እንዴት ያስፈራል? በሀይማኖት በበረታን ጌዜ ብሩህ ፋና እየበረልን በእምነት የምንሮጥበት ጊዜ ብርታት እና ሙሉነት የሚሰማን ስሜታችን ..በቅዝቃዜ ተውጦ ስንደክም የምናይበ ብርሀን ሲጨልም ያንጊዜ ነው እውርነታችን።…. ጥቂት ጌዜ አለ ታዩ ኛላችሁ ጥቂት ጊዜ ደግሞ አለ አታዩኝም ያለው……” ህያው ቃል እውነት ነው ። እውርነት ይሚይዘን ግዜ ስላለ አይደል።

  በንቃት የሚያዩ ለአፍታእ ንኳን እይታቸውን ያላነሱ እንዴት የታደሉ ናቸው….ይህንን ብርታት ለማግኘት ትልቅ አባቶቻችን ተጋደሉ ተፈተኑ ብዙ መከራ አዩ ይህንን እይታ ሳይወስዳቸው አለፉ።

  በትዳር ህይወት፤ በስራ አለም፤ በ ዕለት ተዕለት የኑሮ ውጣ ውረድ እይታው ያልተወሰደበት ሰው ትልቅ የእግዚአብሔር ፀጋ ያለው ነው። በጊዜውም አለጊዜውም መፅናት የቻለው፤ ሁሌ አይራም ሰው ከሚያየው እይታ ውጪ ብዙ ነገር ስለሚያይ። ይህንን እይታ እግዚአብሔር እለት እለት አይንሳን።

  ይህ “አይን” በሜው ርዕስ ስር በተጻፈው ፅሁፍ በሙሉ ውስጣችንን እንድንፈትሽ የሚያረግ ነው። በአይናችን ላይ የተጋረደው ነገር ምን ንደሆነ እንድናይ የሚረዳ ነው። እግዚአብሔር አሁንም ጸጋውን ያብዛላችሁ። ወዴት ያየሁ እንደሆነ ለራሴ ብዝ ነገር እንዳስተውል አርጎኛል። በዙሪያች ያለውን የእግዚአብሔርን እጅ እንዳናይ ግርዶሽ የሆነብን ነገር እንድናስተውል የሚያደርግ ፅሁፍ ነው።

  ReplyDelete
 5. +++
  Dear brother Befikir, QHY!lebona yestenena yanbebnewn lemtegber yabkan betam leb yenkal! Yetweld lewet yemset melket new mastewalen kesten! +++
  Ketoronto akbari betseboch

  ReplyDelete
 6. I boldly agree what you have said.

  ReplyDelete
 7. egziabher yistilin be-ewunet lib keseten kalilemedinewu kalun memekeriachin bezitual eski enanitem yemititsifut ebakachihu tselyu semi anbabi tadami bicha sayhon seri wode tegibar lewach honenlachi endititekemu. yesemi libunam betenagariwu menfesawinet liwosen silemichil end fildfliyamu abat ende aba dmetris.

  ReplyDelete
 8. ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድም በፍቅር፡፡
  የእግዚያብሔርን ውለታ መርሳት ትልቅ በደል ነው፡፡ ዛሬ ያስነበብከን ይሄንኑ ነው። ከዚህ ጽሁፍ የወሰድኩት የእግዚያብሔርን ውለታ መርሳታችንንና ብዙዎቻችን እርሱን የምናመሰግንበት ልቦና ማጣታችንን ነው። ለሁላችንም ማስተዋል ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 9. Amen!!!በእምነት የምናይበትን የሀይማኖት አይን አይንሳን!!!

  ReplyDelete
 10. ሀበኒ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ

  ReplyDelete
 11. Thanks Kalehiwot Yasemaln.

  ReplyDelete