Tuesday, March 22, 2011

እነሆ አንድ ዓመት ሆነ


ይህ ጦማር (ብሎግ) አንድ ብሎ ከጀመረ እነሆ ዛሬ አንድ ዓመት ሆነ፡፡ march 22 ቀን 2010 ዓም በምድረ አሜሪካ ነበረ ይህ ጦማር የተፈጠረው፡፡ ከባለቤቴ ከጽሉ ጌች ጋር ከወር በፊት መከርን፡፡ ከወዳጄ ከኤፍሬም እሸቴ ጋር ቁጭ ብለን ሂደቶቹን ጨረስን፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ቁጭ ብዬ የመጀመርያዎቹን ጽሑፎች ለቀቅኩ፡፡
እነሆ እስከ ዛሬ 164 ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡ 75 ሀገሮች በላይ የሚገኙ አማርኛ አንባብያን ያነብቡታል፡፡ ከሁለት በፊት የወሩ አንባብያን ብዛት 100000 ደርሷል፡፡
ለዛሬ በዓሉን በማስመልከት ዐሉላ ጥላሁን በተባ ብዕሩ፣ ጠንከር ባለ አማርኛ የጻፈውን ላካፍላችሁ፡፡
                 
ዝክረ ‹‹የዳንኤል ዕይታዎች››
 ጥቂት ስለ ጡመራ (Blogging)
እ.አ.አ ከ1990ዎቹ አጋማሽ አንሥቶ ሉላዊውን የኮምፒዩተር ትይይዝ መሠረት አድርጎ በተስፋፋው የኢንተርኔት አብዮት አውራ ጎዳናነት ከተዘረጉት የመካነ ድር ማንሸራሸቻ መንገዶች አንዱ ‹‹Web blogging›› ወይም በአጭሩ ‹‹Blogging››  ነው፡፡
‹‹Blogging›› ግለሰቦች ወይም በአንድ የወል ፍላጎት ዙሪያ የተሰባሰቡ ቡድኖች በመዋዕለ ሕይወታቸው የታዘቧቸውን ገጠመኞች እንዲሁም በሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ዕይታ እና ትንታኔ በጽሑፍ ከሽነው፣ በድምፅ እና ምስል አሳምረው ከአስተያየት ጋራ በመቀመር ሐሳባቸውን እና ስሜታቸውን ከሚያካፍሉባቸው ኮምፒዩተር - ተከል - ፍዋት (Multimedia) አንድ ዘውግ (Online Publishing genre) ነው፡፡
‹‹Blogging›› በባጁት የብዙኀን መገናኛዎች በሚተላለፉ ዘገባዎች እና ዝግጅቶች ላይ ትችቶች፣ ሒሦች የሚቀርብበት በመሆኑ እንደ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ያገለግላል፤ ለአንዳንድ ኩባንያዎችም አዲስ የምርት እና የአገልግሎት ዐይነቶችን እና ሐሳቦችን አስመልክቶ ኢ-ወጋዊ ውይይት የሚካሄድበት መድረክ ነው፡፡ የ‹‹Blogging›› አዘጋጆች ‹‹Bloggers›› የዝግጅታቸው ውጤትም ‹‹Blog›› ይባላል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የ‹‹Blogging›› ቋንቋ በአመዛኙ እንግሊዝኛ ቢሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አማርኛ ከዚህ የመካነ ድር ቋንቋዎች ቤተኛ መሆኑ እየተለመደ መጥቷል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት የተጀመረው ደጀ ሰላም የተሰኘው ገጸ ድር ‹‹Blogging››ን «ጡመራ»  በሚለው የግእዝ ቃል ፈቶታል፡፡
በከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት ጦመረ የሚለው ግስ ደብዳቤ ጻፈ በሚል ተተርጉሟል፤ አለቃ ኪዳነ ወልድም ባለ ቅኔዎች ጦመረ - ጣፈ ብለው እንደሚገሱ ከዚህም ጦማርን እንደ ሚያወጡ በትርጉሙም መጽሐፍ፣ ደብዳቤ፣ ክታብ፤ የመልእክት እና የትእዛዝ የሰላምታ ቃል ያለበት፤ ካገር ወዳገር በፖስታ የሚላክ በሰው እጅ የሚሰደድ መሆኑን አብራርተዋል (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ ገጽ 496)፡፡
ቁም ነገሩ ከጽሕፈት እና ከመልእክት መተላለፍ ጋራ የተያያዘ በመሆኑ የመረጃ ማሠራጫ ቴክኖሎጂ ሲስፋፋ በሥነ ጽሑፋዊ የመፍጠር ፈቃድ(poetic license) ‹‹Blogging›› ጡመራ፣ ‹‹Blog›› ጦማር፣ ‹‹Bloggers›› ጦማሪያን ቢባል ጸያፍ የሚያሰኝ አይመስልም፡፡
ዳንኤል ክብረት በአማርኛ ቋንቋ የግል ወጎቻቸውን እና ጥናታዊ ዕይታዎቻቸውን፣ ማኅበራዊ ትዝብቶቻቸውን እና መንፈሳዊ ምክሮቻቸውን መጦመር ከጀመሩ ጦማርያን አንዱ ነው፡፡ ዳንኤል ‹‹ዛቲ ጦማር ትበጽሕ›› ብሎ ሥነ ጽሑፋዊ ምርቱን ‹‹ይድረስ ለኲሉ ዓለም›› ካለ አነሆ አንድ ዓመት ሊደፍን ነው - መጋቢት 13 ቀን 2003 ዓ.ም፤ ማርች 22 ቀን 2011፡፡
ጦማሪው ‹‹የዳንኤል ዕይታዎች›› በሚል በሰየመው ጦማሩ ላይ በአንድ ዓመት ውስጥ በጦመራቸው ጦማራት ስላስጨበጣቸው ቁም ነገሮች እና ተያያዥ ጉዳዮች ከጦማሩ ተደራሽ ቤተ ሰዎቹ ጋራ አንደኛ ዓመቱን ሊዘክረው ተሰናድቷል፡፡
 ለመሆኑ የጦማሩ ትኩረት እና ይዘት ምንድር ነው? የአንድ ዓመት ክንውኑ ምን ያህል ነው? ያስገኛቸው ውጤቶች እና የወደፊት ዕቅዱስ ምን ይመስላል?
ጦማሩን የመጀመር መግፍኤ
ላለፉት ዐሥራ አምስት ዓመታት በሥነ ጽሑፉ ዓለም በመቆየት 13 መጻሕፍትን በግሉ፣ 2 መጻሕፍትን ከሌሎች ጋራ ለኅትመት ያበቃው፣ በተለያዩ ዘውጎች የተቃኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ መጣጥፎችን በጋዜጦች እና መጽሔቶች ላይ ያበረከተው፣ በኅትመት ውጤቶች ማኔጅመንት የብዙኀን መገናኛ አመራር ልምድን ያዳበረው ዳንኤል ክብረት ‹‹የፊደል ባለቤት እና የዘመናት የጽሑፍ ታሪክ ያለው ሕዝብ ከሐሜት ልማድ ተላቅቆ በጉዳዮች /ሐሳቦች/ ላይ በአደባባይ የሚወያይበትን መድረክ ማመቻቸት ለዚህም ፈሩን በማሳየት አገርን በቀና ልብ ማገልገል›› ለጡመራ እንዳነሣሣው ይገልጻል፡፡
የመጦመርያ ጊዜ፣ የጦማሩ ትኩረት እና የጡመራው ይዘት
‹‹የዳንኤል ዕይታዎች›› ሦስተኛ ወሩን በቆጠረበት ወቅት ጦማሪው እንዳሰፈረው በየቀኑ ቢያንስ ሁለት ሰዓታትን በጡመራ ተግባር ላይ ያሳልፋል፤ በዚህም መጀመሪያ ላይ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ በኋላም ትኩረቱን በማስፋት በየሳምንቱ አራት ጊዜ እንደሚጦምር ገልጧል፡፡
 ጦማሩ «ከመንፈሳዊው ዓለም» «ጥናታዊ ጽሑፎች»«ወግ» ከቅርብ ጊዜ ወዲህም «የጉዞ ማስታወሻ»«ለቤተ መጻሕፍትዎ» እና «ልዩ ልዩ» በተሰኙ ዓምዶች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ይጦመሩበታል፡፡
ወግ - ጦማሪው ከቤተሰብ እስከ ኅብረተሰብ፣ ከመኖሪያ መንደሩ እስከ ዓለም አቀፍ በሚያካልሉ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ትዝብቱን እና ሒሱን ያንጸባርቅበታል፡፡
በወቅታዊ እና አነጋጋሪ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ዕወቀት እና መረጃ የሚያስጨብጥ ጦማር በየሳምንቱ ማክሰኞ በጥናታዊ ጽሑፍ መልክ ይጦመራል፡፡ በመላዋ ኢትዮጵያም ይሁን በባሕር ማዶ ጉዞን የኑሮው አንድ አካል ያደረገው ጦማሪው ከስጌ ማርያም እስከ ባለ ራእይዋ ግሪካዊ ደሴት ፍጥሞ ድረስ
 እንዲያም ሲል መካከለኛው ምሥራቅ እስከ ዩናይትድ ስቴትስ ኦ አሜሪካ በርካታ ግዛቶች በመዘዋወር ስላደረጋቸው ዑደቶች የከተበልን፣ ወደፊትም የመንገደኛ ዘገባውን የሚተውልን በጉዞ ማስታወሻ ነው፡፡
ጦማሩን ለመጀመር ጦማሪው ተነሣሽነት ከወሰደባቸው ምክንያቶች አንዱ የሆነውን «የአደባባይ ውይይት ባህል ለማዳበር» የንባብ ልምድ ወሳኝ በመሆኑ «ለቤተ መጻሕፍትዎ» በተሰኘው ዓምድ በየሳምንቱ ቅዳሜ የተለያዩ ጸሐፍትን ሥራዎች መዳሰስ ለተጦማሪዎች ያስተዋውቃል፡፡
ወግ - ብዙ ተከታታዮች ያሉት የጦማሩ ክፍል ሲሆን ‹‹ሰው በቁሙ ለምን ሐውልት ይሠራል?››ይምርሃነ ክርስቶስ የተሠወረ ሥልጣኔያችን፣ ለምጣዱ ሲባል፣ የኔ ጀግና፣ ባልን ማን ፈጠረው? ዝምታ ወርቅ አይደለም፣ ተሳቢ፣ ሀገር እንወዳለን፣ የዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ፣ የአንድ አባት ምክር፣ ባሕር ዛፍ፣ ቅኝ አልተገዛንም፣ አንድነት ይቅርብን፣ ማኅሌት እና መክፈልት፣ ከቺሊ ሰማይ ሥር በሚል ርእስ የተጦመሩት ጦማራት እስከ አሁን ባለመቋረጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚነበ እና አስተያየት የሚሰጥባቸውነዋል፡፡ ጦማሩ ከተጀ መረበት ከ2002 ዓ.ም መጋቢት ወር አጋማሽ እስከ ዛሬ ድረስ በሁሉም የዝግጅት መስኮች በአጠቃላይ 159 ጦማራት ተጦምረዋል፡፡
የጦማሩ ተደራሾች
ጡመራ ከመገናኛ(ሚዲያ) ባሕርይው አኳያ በሺሕ፣ እልፍ ወይም አእላፋት መካከል ታስቦ የሚደረግ አይደለም፡፡ ስቴፈን ግላንዜር የተባለ የጡመራ ሥርዐት ባለሞያ በውል እንደ ገለጸው፣ ‹‹ሚልዮኖችን ለመድረስ ከሻትህ በቴሌቪዥን ማስታወቂያ ታስነግራለህ፤ አንድ ሰው ብቻ ለማግኘት ከፈለግህ ትመይልለታለህ -ኢሜይል ትጠቀማለህ ወይም ስልክ ትደውላለህ፤ ከአምስት እስከ 500 ያሉ ሰዎችን ለማግኘት ግን ኢ- ጦማር (ጡመራ) ዐይነተኛው መገናኛ ነው፤›› ማለቱ ተዘግቧል(Encarta ® 2008).
ምስጋና እንደ ጎጉል ላሉት የኢንተርኔት አሳሾች ይሁንና ‹‹የዳንኤል ዕይታዎች››ን የመሳሰሉት መጦመሪያዎች ግን ይህን ገደብ የተሻገሩት ጡመራቸውን በወጠኑባቸው ሳምንታት ውስጥ ነበር፡፡
እስከ አሁን ባለው ሂደት ‹‹የዳንኤል እይታዎች›› በሰባቱ አህጉር በሚገኙ 75 የዓለም አገሮች ነዋሪዎች የሆኑ በሳምንት ከ25‚000 በላይ በወር ደግሞ ከ100‚ 000 በላይ አንባቢዎችን እና ተከታታዮችን ለማትረፍ ችሏል፡፡ ይህም ጦማሩ በወረቀት እየታተመ፣ ዳወንሎድ እየተደረገ በሬዲዮ፣ በኢ-ሜይል፣ በፌስቡክ፣ በፖስታ፣ በጋዜጣ እና በመጽሔት እየታተመ የሚሰራጭላቸውን ሰዎች ሳይጨምር ነው፡፡
ኢ-ጦማሩ ‹‹ትብጻሕ ለክሙ›› ከተባለላቸው እና ገጸ ድሩን ከሚከታተሉቱ አማርኛ አንባቢ ቤተ ሰዎች መካከል የኢትዮጵያ አንባብያን ቅድሚያውን ይይዛሉ፤ የአሜሪካዎቹ ይከተላሉ፤ ካናዳዎችም ከኖርዌይ ቀጥለው አራተኞች ናቸው፡፡ ከአውሮፓ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ፊንላንድ፣ ጣልያን፣ ሆላንድ፣ ቤልጅየም፣ ግሪክ እና ቱርክ በተከታታይ ያለውን ቁጥር ይዘዋል፡፡
ከአፍሪካ ናይጄሪያ፣ ኬንያ (ካኩማ የስደተኞች ካምፕን ጨምሮ)፣ ሱዳን፣ ዑጋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ብሩንዲ፣ አንጎላ እና ኤርትራ ብዙ አንባብያንን አበርክተዋል፡፡ ከመካከ ለኛው ምሥራቅ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ የመን፣ ባሕሬን፣ ኳታር እና ሊባኖስ፤ ከእስያም ሕንድ፣ ታይዋን፣ ማሌዥያ½ ኢንዶኔዥያ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮርያ ከፍተኛ አንባ ብያን የሚገኙባቸው ናቸው፡፡ ከላቲን አሜሪካ ደግሞ ዶሚኒካን ሪፓብሊክ እና ኢኳዶር ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከኦሺኒያ አገሮችም አውስትራልያ እና ኒውዝላንድ ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡
ከእኒህም መካከል ጦማሩ በኤርትራ ለሚገኙ አንባብያን፣ በዑዲ ዓረቢያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ በፀረ ሽብር ዘመቻው ለተሰማሩ የአሜሪካ ጦር ራዊት አባሎች የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መድረሱ፣ እነርሱ የሚሰጡት አስተያየት የጦማ ሪውን ልብ በሐሤት ይሞላዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን yl#M tBlW b¸gmt$ÆcW እንደ ሰሎሞን ደሴቶች፣ በርማ፣ ቺሊ፣ ሞንጎልያ፣ ፔሩ እና ፊሊፕንስ ባሉት አገሮች ባፈራቸው አድማሳዊ አንባቢዎቹ ደግሞ ይደነቃል፡፡
የጦማሩ ፍሬዎች
የ‹‹ዳንኤል ዕይታዎች›› በሚያነሣቸው ጉዳዮች ዙሪያ በሀገር ውስጥ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በውጭም በናይጄሪያ እና በሎንዶን የውይይት ክበቦች ተከፍተዋል፡፡ በትዳራቸው በገባው ነፋስ ለመለያየት የደረሱ ባል እና ሚስት ዕርቀ ሰላም አውርደው ቤታቸውን ከማፍረስ አድነዋል፡፡ «መረ» ቅሉ አገናኘ፣ አንድ አደረገ፣ አጣመረ ማለትም አይዶል!!
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለፒ.ኤች.ዲ ጥናት የወጠኑበትን ርእሰ ጉዳይ ለሀገር በሚጠ ቅምበት አገባብ የቀየሩ እና ያሻሻሉ ተመራማሪዎችም እንዳሉ ታውቋል፡፡ ‹‹ሻካራ እጆች›› የሚለውን ጦማር ካነበበ በኋላ ወዳስቀየማቸው ወላጅ እናቱ ተመልሶ የእጃቸውን መዳፍ አገላብጦ የተመለከተው ልጅ ወደ ልቡ ተመልሶ ይቅርታ መጠየቁን በጸጸት ተናግሯል፡፡
በጦማሪው የጉዞ ማስታወሻ ለተግባራዊ ርምጃ መነሣሣት የተፈጠረባቸው አጋጣሚዎችም ታይተዋል፡፡ ለአብነት ያህል በሰሜን ጎንደር ዞን ስለምትገኘው ታሪካዊቷ ደስጌ ማርያም በአራት ተከታታይ ክፍል ባቀረበው የጉዞ ማስታወሻው የዞኑ አስተዳደር የቅርስ ማስቀመጫ ዚየም ለማስገንባት፣ በካናዳ የሚገኙ በጎ አድራጊዎችም ቅርስ በጧፍ መብራት ለሚጎበኝባት ለጎንደር ቁስቋም ማርያም ጄኔሬተር ለመግዛት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በአዘዞ የጠፉትን ቅርሶች በተመለከተ የሚመለተው የክልሉ መንግሥት አካል ትኩረት ሰጥቶ ጉዳዩን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡
በመጪው ጊዜ
ከጡመራ መድረክ ፈጣንነት፣ አካላይነት እና አካታችነት አኳያ በአንድ ዓመት ውስጥ ከደቃይቅ ጀምሮ ባሉት የጊዜ መለኪያዎች ብዙ ለመከወን እንደሚቻል እሙን ነው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ በአመዛኙ በፊደላት ተቀናብሮ በጽሑፍ የሚቀርበውን ጡመራ በድምፅ ቀምሮ በምጥን ሬዲዮ(ዲዮ)፣ በቪዲዮ አሳምሮ በዩ-ቲዩብ ለማቅረብ የፕሮግራም ቀረጻ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
ምስል እና ድምፅ ለመጫን ያለውን የትይይዝ(Network) ቅልጥፍና ተግዳሮት በመቋቋም በጽሑፍ የሚቀርበውን ጦማር ተቀምጦ ለማንበብ ጊዜ ለሚያራቸው እና ማየት ለተሣናቸው ወገኖች ምቹ የክትትል እና ተሳትፎ ዕድል ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
‹‹የዳንኤል ዕይታዎች›› አንደኛ ዓመት
ጦማሩን ‹‹ከሚተርፋቸው እንደሚሰጡት ባለጸጎች ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ምጽዋቷ በክርስቶስ ከተመሰገነላት መበለት እንደ አንዱ በመቁጠር የሚጽናናው›› ጦማሪው ዳንኤል ክብረት በቀጣይ ያለፈውን በመገምገም ለመጪው በሰፊው ለመሥራት አቅጣጫ የሚይዝበትን የውይይት መድረክ በሀገር ውስጥ በአዲስ አበባ፣ በውጭም በአሜሪካ - ዋሽንግተን ዲሲ አዘጋጅቷል፡፡ ይኸውም ጡመራው የተጀመረበት አንደኛ ዓመት የሚከበርበት ይሆናል፡፡
የጦማሩን ትኩረት፣ ይዘት እና አቀራረብ የተመለከቱ äÃêE ሒሳዊ የፓናል ውይይቶችበታዋቂ ሰዎች የሚቀርቡ የጽሑፍ ንባቦች፣ እንዲሁም ሀገርኛ ዘይቤ የያዙ የዜማ ዝግጅቶች የዝክረ ጦማሩ ዋነኛ መሰናዶዎች ይሆናሉ፡፡
ዝግጅቱ በጦማሩ ላይ በወጣው ማስታወቂያ መሠረት እስከ የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል የተመዘገቡ ተከታታዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት መጋቢት.18 ቀን 2003 ዓ.ም በአኩስም ሆቴል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

62 comments:

 1. Enquan le 1gna amet aderesen.
  yewyiyit medrekochu lemin bewichi hagerim aysfafum.Be bizu chigroch yetetebetebu astesaseboch alu ean.
  Getachew

  ReplyDelete
 2. ለዳንኤል ዕይታዎች መልካም ልደት ብያለሁ:: "ተሳቢ" በሚል ርዕስ የቀረብው ጦማርህ የኔ አንደኛ ምርጫየ ነው:: (My favorite blog).

  ዳንኤል : እንኳን ደስ አለህ:: በጣም ደስ የሚል ሥራ ነው እየሰራህ ያለኽው:: በርታ ቀጥልበት: ለዚህም አምላክ ካንተ ጋር ይሁን::

  ዐሉላ ጥላሁን ላንተም ጭምር ምስጋና ይድረስህ:: "አንድ ሰው ብቻ ለማግኘት ከፈለግህ ትመይልለታለህ -ኢሜይል ትጠቀማለህ፤ ወይም ስልክ ትደውላለህ" "ትመይልለታለህ" ተመችታኛልች:: አንዳንድ የቴክሎኖጂ ቃላት በአማርኛዊ ዘይቤ ሲባሉ ደስ ይላል::

  ReplyDelete
 3. እንኳን ለአንደኛ ዓመት አደረሰህ፡፡
  በመጪው ዓመትም ከዚህ የበለጠ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
  እኔ የምለው ግን ለበዓሉ ታዳሚ ለመሆን ግድ ከየካቲት በፊት መመዝገብ ያስፈልጋል፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች መምጣት ፈልገዋል እንዲሁም ይመጣሉ ይመልሷቸዋ እንጂ አንተ ምን ትላለህ፡፡

  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 4. Temelkach
  dany ! enquan aderseh, aderesen egzeabher yasebkewn yasfetsmeh.bezu ye emnet ena amelekaket mezabatochen eyekerfek new. amelekaket 'ATTITUDE' mekeyer new yetmehert hulu fetena yebalal ena, yibel...yibel... yemeyasegn naw.tenkirelen egnam susegna honenal by the way poletikegnochachen eyanebebut yehon ?!.....

  ReplyDelete
 5. Wudasse wwek Mahibere SelamMarch 22, 2011 at 11:21 AM

  እንኳን አደረሰን ፡፡

  ምስጋና ይድረሰው ለዚህ ያደረሰን
  ወቅቱን አፈራርቆ ሻማ ያስለኮሰን፡፡

  ትምህርት እንድንገበይ ፍሬ እንድናፈራ
  ለሃገር ለወገን በጎ እንድንሰራ
  ዓለምአቀፋዊ ዕውቀት እንዲኖረን
  በእርጋታ እንድንጓዝ ግራ ቀኙን አይተን
  መክራናለችና ወጣቷ ጦማርህ
  ለወደፊት ደግሞ ፈጣሪ ያበርታህ፡፡

  እኔ በበኩሌ ብዙ ተምሬአለሁ
  ዕውቀትና ጥበብ ቃሉን ገብይቻለሁ
  ፍቅር አንድነትን ፅናት አይቻለሁ
  በዓይነ ልቦና ውጭም ተጉዣለሁ
  ስለሃይማኖቴ ብዙ አውቄአለሁ
  በተለይ ለምግባር ስንቅ ሰንቄአለሁ
  እንደአቅሜ ደግሞ ሃሳብ ገልጫለሁ
  በግጥም ውዳሴ ትንሽ ሞክሬለሁ፡፡

  የዕውቀቱ ባህር ገና አልተጨለፈም
  ማወቅ ያለብንም ገና አልተነካም
  ትደግልን ደግሞ አንተንም ያበርታህ
  እድሜውን ጤናውን ጥበቡን ያድልህ
  ሁለቱን ለማብራት ለዓመቱ ያድርስህ፡፡

  ReplyDelete
 6. After all this block has a capability to change the attitude, perception, ideology, spirituality and political aspect of the daily living style of human being that must be followed in accordance with rational rather than emotion. Really, Dn. Daniel you were born to write and share your invaluable ideas with your colleagues. I knew you before 12 years ago as a teenager, and you are a person whom I really appreciate him in my life. Thanks to his name now as a young adult I’m able to give my compliment on the blogger the one who has a special place in the core of my heart. I have learnt a lot of things from you via this blog that even words are extremely weak to evoke my internal feelings. Lastly, I dare to say that you are the living legend to (giving a future direction, corrective and constructive ideas for the wrong deed and striving for a better Socio-Economic and political development) our spiritual and political leaders if they have a softest heart how to lead the sheep and citizen respectively. May the peace of God be with you all the time and bless your families. HAPPY BIRTHDAY TO OUR BLOG!!!

  Antonio Mulatu,Mekelle.

  ReplyDelete
 7. እንኳን አደረሳችሁ
  ጅምሮ በጎ ነው መጨረሻውን ያሳምርላችሁ

  ReplyDelete
 8. I'm happy to be the part of this blogger I hope it will be strengthen in the future.

  ReplyDelete
 9. እጅግ ማራኪ ጽሑፍ ነው ወንድሜ አሉላ። እግዚአብሄር የበለጠ እንድትሰሩ ይርዳችሁ። የቁርጥ ቀን የ ኢትዮጵያ ልጆች፤ ወንድሞቼ።

  ReplyDelete
 10. ዳንኤል : እንኳን ደስ አለህ:: በጣም ደስ የሚል ሥራ ነው እየሰራህ ያለኽው:: በርታ ቀጥልበት: ለዚህም አምላክ ካንተ ጋር ይሁን::እድሜውን ጤናውን ጥበቡን ያድልህ
  ሁለቱን ለማብራት ለዓመቱ ያድርስህ፡፡

  ReplyDelete
 11. Congratulations Dany. Your blog has been a constant source of motivation and selfcritique for me and my family. May God give you more and more wisdom. In fact, this is a prayer for us readers, as you always try to share us what you think is good to us your countrymen. Thanks a lot Dany. Many thanks also to Tsilu and the kids who sacrifices their precious time for this blessed cause.

  A Family from Germany

  ReplyDelete
 12. እንኳን አደረሰህ ዳኒዬ ፣ረጅም እድሜ ይስጥህ ፣ያሰብከውን ያሳካልህ ፣በቀጣይም ብዙ ነገር እንደምታበረከት ከእግዚያብሄር ጋር ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ?

  ReplyDelete
 13. Congrats to Dn Daniel and all participants. I appreciate how every body is waiting for new things to be posted on the scheduled dates. Dear Alula your views are so nice, but you hesitated to forward a critics.

  Anyway the work is so precious Dani. I know your wife has a lot to do along with your works. She shall be granted appreciation too.

  Do not forget to check yourself not to be like the doctor who condemns smoking while he had the cigarette in his mouth. ELSE YOU ARE DOING FANTASTIC.

  I do expect the results of the celebrations in some way to be posted.

  ReplyDelete
 14. Dear Dn Daniel

  Even though the road is course, you are doing your citizenship responsibility. Let us keep our country by droping small stone every corner. When God allows we will build our country by this stone. Dane you are dropping many stone... Let God bless you family and services.

  I have two recommendations
  1. If possible please arrange online system to participate on the Annul annversery. We can do this in paltalk.
  2. For me comparing the importance of the issue raised, 25,000 visitors are very small.we need to plan to address many people. I think in Ethiopia the internet coverage reached 1.25%( more than 1 million people). Let us target some numbers.

  EthiopFuter

  Melakam Addis Amet

  ReplyDelete
 15. መልካም ልደት!!! ውድ ዲ.ን ዳኒ ላንተ፤ለውድ ባለቤትህ፤እና ለዚህች ተወዳጅ ብሎግ ተሳታፊዎች በሙሉ እንኳን አደረሰን። ሥራዎችህ በየቤቱ ተፅዕኖ መፍጠር ችለዋል።እግዚአብሔር ያበርታህ።

  ReplyDelete
 16. Dear Dan may God bless you all with your life. I thankyou what you have wrote to us with the help & wisdom of God. Your views changes my attitude & my friends attitude too. I hope you will write us more views & i am ready to share your views to my friends. I am happy, my friends & the who reads your views too. God bless you & your family

  ReplyDelete
 17. +++
  Be Kirstos ejeg yetweddk wendmachn እንኳን ለአንደኛ ዓመት አደረሰህ፡፡አደረሰን:: Thanks to the Almighty God for all his blessing & using you>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> even we are far from you distance make not apart us as christian we are always with you !!!! Congrats for your body also share all your good idea! With Christ love & respect Ketoronto akbari betseboch

  ReplyDelete
 18. ከኃያሲ ወደራሲ፣ከዘመናዊ ወመንፈሳዊ፣ ወንድማችን በማይነጥፍ ብዕራ ለአንድ አመት ሳይሰለችን፤ ደግሞ ቀጣይ ምን ይጽፍልን ይሆን? ብለን አቆብቁበን የምንከታተልበት ቀልብ አግኝተን ለአንድ ዓመት እድሜና ጤና ሰጥቶ ለዚህ ላደረሰን ለመድኃኔዓለም ምስጋና ድረሰው።እሱ ይክፈለው እንጂ እኛ ለምሰጋና ቋንቋ የለንም።እስቲ የተደከመበትን ለፍሬ ይበልልን።
  ለልብነ ወለአእይንቲነ ሲሳይነ ዘለለ ዕለትነ የሆነችልን ጦማር ትመንደግልን ዕለታዊ ያድርግልን በብዙኀ ልሳን ወበበብዙኅ ኅብረ ነገር በብዙኅ ተደራሲ የጡመራዎች ቁንጮ ያድርግልን። እንደነዐሉላ ያሉ ወንድሞች ሱታፌ ቢያደርጉበት እኛ በትጋት ብናነበው ምንቀረ?
  ከማሁ ያስተጋብዓነ በደብረ ጽዮን ቅድስት

  ReplyDelete
 19. መልካም ልደት!!! እንኳን ለአንደኛ ዓመት አደረሰህ፡፡አደረሰን:: ሥራዎችህ በየቤቱ ተፅዕኖ መፍጠር ችለዋል።እግዚአብሔር ያበርታህ። መጨረሻውን ያሳምርልህ።

  ReplyDelete
 20. HAPPY BIRTH DAY!!!
  Dn. Daniel Enkuan Adereseh! Aderesen!
  Huletegnawanim SHAMA lemabrat Egziabher yadrsih! Yadirsen Amen.

  ReplyDelete
 21. እንኳን ለአንደኛ ዓመት አደረሰህ፡፡ thank you dani. keep it up!!!God bless you.

  ReplyDelete
 22. enekuwaan adersehe enaneme enekuewan adersene

  ReplyDelete
 23. +++


  እንዲሁም ሀገርኛ ዘይቤ የያዙ የዜማ ዝግጅቶች ?

  ReplyDelete
 24. when and where will be the washington event?

  ReplyDelete
 25. ዳንኤል : እንኳን ለአንደኛ ዓመት አደረሰህ፡፡አደረሰን በጣም ደስ የሚል ሥራ ነው እየሰራህ ያለኽው:: በርታ ቀጥልበት: ለዚህም አምላክ ካንተ ጋር ይሁን::እድሜውን ጤናውን ጥበቡን ያድልህ ፣ ያሰብከውን ያሳካልህ ለዓመቱ ያድርስህ፡፡
  Hailemeskel
  z Maputo-Moz

  ReplyDelete
 26. እንኳን አደረሰህ።፡ ቀጣዪንም አመት አብዝተህ የምትሰራበትን ፀጋ እግዚአብሔር ያብዛልህ!!

  ReplyDelete
 27. ዲ/ን ዳንኤል መልካም ልደት! ጥረትህ መሬት አልወደቀም። በጦማርህ ምክንያት የባሕርይ ለውጥ ያመጡትን ወገኖች ዜና ሳነብ ምን ያህል ውስጤን እንደነካው ለመግለጽ ይከብደኛል። እንክብካቤ ሊደረግላቸው የሚገቡ ቅርሶቻችን በአንተ ጡመራ አስታዋሽ አግኝተው ግለሰቦችና የክልሎቹ አስተዳደሮች አፋጣኝ ርብርብ ሲያደርጉ ሲስተዋል፣ ከዚህ በላይ የሚያስደስት ነገር ምን አለ! ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት! በዚህች በሳለፍናት አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ታላቅ የዜግነትህን ግዳጅ ተወጥተሃል። እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክልህ። ለኛም እግዚአብሔር አምላክ ዓይነ ህሊናችንን እና ዓይነ ልቡናችንን አብርቶ የድርሻችንን እንድንወጣ ይርዳን።

  ReplyDelete
 28. Dear Daniel, I frequently visit your block as source of positive learning and enjoyment when I feel tired physically and spiritually. I hope you will continue strengthening our spirit in the future as well.
  Melkam Addis Amet!

  ReplyDelete
 29. ተስፋብርሃንMarch 22, 2011 at 10:37 PM

  ዳኒ እንኳን ለአንደኛ ዓመት የጡመራ መድረካችን አደረሰን። ቀጣዩንም ዓመት ከዚህ የበለጠ እንድታስተምረን ቸሩ ፈጣሪ ብርታቱንና ጥበቡን አብዝቶ ይስጥልን። ቤተሰብህንም ይጠብቅልህ።

  ReplyDelete
 30. እንኳን አደረሰን ዲያቆን በዚሁ በርታ ግን ለምን በድቁና መዓረግህ አትጠቀምም? የትዳሯን ጽሁፍን /ማጠቃለያዋን/ አልወደድኳትም፡፡
  መልካም አንደኛ አመት

  ReplyDelete
 31. እንኳን አደረሰን ለዚህ ያበቃን አምላክ በቀሪውም ጊዜ እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ የከፈልከውን ዋጋ መዘርዘር ባይጠቅምም ግን አንዱን ወገን ማንሳት እፈልጋለሁ የዚህ ስራህ ዋናዋ ሞተር ባለቤትህን ምክንያቱም ቤት ማስተዳደሩ የልጆች ሃላፊነቱን በቤት ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉትን የቤተሰብ ድርሻ አንተን እንዳይገድቡህ በመትጋት ሁሉን በመሸፈን ሦስት ሁሉን እርዳታ ከቤተሰብ የሚፈልጉ ልጆች በመያዝ የራሶን ድርሻ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ፍላጎት የበኩሏን ተወጥታለችና ምስጋን ይገባታል እንዲሁም የአባትነት የፍቅር ጊዚያቸውን ለሰጡን ልጆችህ ምስጋናችን ይድረሳቸው የማያልቅበት አምላክ ቀሪውን ግዜ ባርኮ የምንማርበት የምንጽናናበት የምንባረክበት አድርጓ አንተንም አጽንቶ ለሁለተኛው ዓመት ያብቃን

  ከአቡዳቢ

  ReplyDelete
 32. ዳንኤል : እንኳን ደስ አለህ:: በጣም ደስ የሚል ሥራ ነው እየሰራህ ያለኽው:: በርታ ቀጥልበት: ለዚህም አምላክ ካንተ ጋር ይሁን::

  ReplyDelete
 33. ሰላም ዳኒ፣
  ምን አልባት አይተኸው ከሆነ አላውቅም፤ ከአሁን በፊትም አንስቼው ነበር ብትችል በመጭው ጡመራህ ላይ በየግዜው የምትሰብካቸውንም ስብከቶች አምድ ከፍተህ ብታካትትልን። እጅግ ከምትጠብቀው በላይ ለውጥ ያመጣል ብዬ አስባለሁ፤ ለብዙዎችም መጽናኛ ይሆናል፤….
  ለማንኛውም አምላከ ቅዱሳን አገልሎትህን ይባርክ፤ ከክፉ ጠብቆ ፍጻሜህን ያሳምርልህ። አሜን!
  ዳዊት

  ReplyDelete
 34. መልካም ልደት ለጡመራህ፤
  እስከ ዛሬ ከተለቀቁት ጽሑፎችህ አንድም ሳላነብ ያመለጠኝ የለም ብዙም ተምሬበታለሁ ወደፊትም እማርበታለሁ ብዙዎቹን ገልበጬ (ኮፒ አድርጌ) አስቀምጫለሁ ፤ በተቻለኝ መጠን ለሰዎችም አስተዋዉቄያለሁ ፤ እኔ ባመሰግንህ ዋጋ የለዉም እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ፤
  ዕድሜ ላንተና ለጡመራህ በኮምፒዉተር በአማረኛ መጻፍ ችያለሁ ምክንያቱም እንደ አቅሜ አስተያየት ለመስጠት ስሞክር በእንግሊዝኛ አማርኛ መጻፍ አሳፈረኝና መማር ጀመርኩ ይኸዉ ሰአት ቢወስድብኝም ስጽፍ ያረካኛል
  እግዚአብሔር እድሜና ጤናዉን ያድልህ፡፡ እድሜንና ጤናዉን ሰጥቶን ሁለተናዉን አመት ለማክበር ያብቃን፡፡
  ሰላመ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን፡፡


  ጌታቸዉ
  MN ,USA

  ReplyDelete
 35. +++
  Thank You Dani, God Bless You. I wish you All Good Success in your life and services.

  Your Brother in Christ From Canada

  +++

  ReplyDelete
 36. ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው ዕብራ 3:4
  እንኳን አደረሰን
  ውድ ዲ.ን ዳኒ እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል እንዲል መፅሀፉ እኔ በበኩሌ በዚህ ብሎግ እግዚአብሔር ቤትን ሲሰራ ሲጠብቅ አይቻለሁ ለዚህም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ
  ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ በሚለው ስብከት ሰሪውን ነው ማክበር ተብለን የለ? ለእግዚአብሔር ሀሳብ ለታዘዛችሁት
  አንተና ከምር ዘውድ ለሆነች ባለቤትህ እንዲሁም አብረውህ ለሚተጉት በሙሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ! ብዙ ተምሬያለሁና ብዙ ጊዜ ውስጤን መርምሬአለሁና
  ከዚህ በኋላም አብረን እንቀጥላለን በርታ ሊያደክሙ የሚፈልጉ ፈተናዎች ቢኖሩም ፈጣሪና እመብርሃን ያበረቱሀል ብዬ እተማመናለሁ ለቤተክርስቲያናችን አለኝታ መሳሪያ ስላረገህ ስላንተ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን
  እሁድን በናፍቆት እየጠበኩ ነው እግዚአብሔር የዚያ ሰው ይበለን
  በርታ

  ReplyDelete
 37. Dn Daniel Happy Anniversary!!!
  I agree with one person who commented about why not use your post as Deacon we prefer that better. God Bless your work for many many years to come. Emebetachin Bemiljawa atileyih. Atlanta.

  ReplyDelete
 38. Dani , how are you?፣
  " እንዲሁም ሀገርኛ ዘይቤ የያዙ የዜማ ዝግጅቶች የዝክረ ጦማሩ ዋነኛ መሰናዶዎች ይሆናሉ፡፡" said Alula at the end of the paragraph, what does it mean ? does it mean BAHLAWI ZEFEN or YE BEGENA MEZMUR? I scared. It is ABIY TSOM and you are a PREACHER. Did you remember what did you say us about LIBRALISM? Anyway I want to know about Alula's idea.
  God bless you!!! AMEN!!!

  ReplyDelete
 39. ዲ/ን ዳንኤል የምትፅፋቸው ጽሁፎችና ስብከቶች ሀይማኖት ሳይለይ ቀና ልቦና ላለው ሰው በሙሉ መሰረት ናቸው ነገር ግን እነዚህን አገልግሎቶች በተለይ ስብከቶችህ በኢትዮ በአራቱም አቅጣጫ ቢሰበኩ እጅግ መልካም ነው(በተለይ በየክፍል ሀገሩ እንደነ ጋሼዎች በየሳምንቱ ለጥቅም ባይሆንም በአመት ለተወሰነ ጊዜ ተገኝተህ ብታገለግል ፍሬ እንደምታፈራ እርግጠኛ ነኝ)ስለዚህ ለሁሉም እግዚአብሔር ይርዳህ
  ከእንዳለ ክበበው ዘ አጋሮ

  ReplyDelete
 40. Egziabher yebarkeh Daniel!

  ReplyDelete
 41. ይድረስ ከልብ ለምናከብርህ ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል
  እንኳን ለአንደኛ ዓመት በሰላም አደረሰኽ/እስከቤተሰቦችህ/
  እግዚአብሔር የገልግሎት ዘመንኽን ይባርክ እኛንም ተጠቃሚዎች
  ያድርገን!
  አፀደ ማርያም እና ወልደተክለሀይማኖት ከዳላስ

  ReplyDelete
 42. enkuan aderese aderesen

  ReplyDelete
 43. The one participant his name is Getachewu said " ዕድሜ ላንተና ለጡመራህ በኮምፒዉተር በአማረኛ መጻፍ ችያለሁ" me too, I always want to write in Amharic but I don’t know why or maybe there is compatible font problem...... Say something about this pls? Any ways I wish long live for Dani and his blog . emm and also I was ask u to participate “one year Anniversary of ye’Daniel Kibret Eyitawech” but even u did not respond my e-mail. Sorry Dani. I did this for my respect of u.

  ReplyDelete
 44. ayyaanaa ze wollegaMarch 24, 2011 at 12:02 PM

  Dn. Daniel, ahunim Ye IGZI'ABHEER TSEGA YIBZALIH! be metshaf melk biweta internet lemayagegnu wendim ihitochachin inilegsalen, ignam be hulum bota initekemibetalen biyye tesfa adergalehu!

  ReplyDelete
 45. Dn. Daniel Enkuan Adereseh! Aderesen!
  I am not clear with this. Pls take care. God be with us.

  ReplyDelete
 46. congadulation dani
  from addis alex

  ReplyDelete
 47. enkuan desyalehi Dani.

  ReplyDelete
 48. May the lord guide you through many years to come. Happy Birthday to Yedani Blogg...

  ReplyDelete
 49. እይታህ እይታዬ እንዲሆን እያንዳንዱን ነገር በተለያየ እሳቤ ማየት እንድችል ቀና አሳቢ ለሀይማኖትና ለሀገር ተቆርቋሪ እንድሆን የተጠቀምክበት የጡመራ መድረክ የምስጋና ዋጋው ከፍ ያለ ነው፡፡ ለካ እንደዚህ ጠንክሮ መስመር የሚያሳይ እሱ በርትቶ ሌላውን የሚደግፍ አለ፡፡ ሻማ ሆነህ ለብዙዎቻችን እየበራህ ነገር ግን ለአንተ እየቀለጥክ መሆኑ የሰማኛል፡፡ ምክንያቱም ከተለያየ አካል የሚደርስብህ ፈተና እንደ ሻማ ለመቅለጥህ ምስክሮች ናቸው፡፡ በዚህ ደግሞ እንደማትበገር አስተምረኸናል፡፡ወላዲተአምላክ ሁሌም ትደግፍህ ታፀናህ ዘንድ የዘወትር ፀሎቴ ነው፡፡መጋቢት 18 እሁድን ግን በስስት እየጠበኳት ነው፡፡የዛ ሰው ይበለን

  ReplyDelete
 50. MELIKAM LIDET DN.DANIEL EGZIABHER YABERTAH
  tesfaye
  canada

  ReplyDelete
 51. ዳኒ እንኳን ለአንደኛ ዓመት የጡመራ መድረካችን አደረሰን:: ብዙም ተምሬበታለሁ ወደፊትም እማርበታለሁ:: ጽሁፎችህ ሀይማኖት ሳይለይ ቀና ልቦና ባለው ሰው ሁሉ ተፅዕኖ መፍጠር ችለዋል:: እግዚአብሔር አንተን አጽንቶ ለሁለተኛው ዓመት ያብቃን::

  ReplyDelete
 52. በቤተክርስቲያን ዓውደ ምህረት ብቻ ተወስኖ የምናውቀውን የውሉደ ተዋህዶ አገልግሎት አገራዊ መልክ ይዞ እና በዓለም አድማሳት ተሸግሮ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሲመክር እና ሲያጽናና ስናይ አምላካችንን አርምሞ ጽርዓት በሌለው ውዳሴ እናመሰግነዋለን!!! አቡነ ጎርጎርዮስ እውነትም ልጆች ወለዱ !

  ReplyDelete
 53. God bless you Dani. Pls continue as this way. Many thanks to Alula & other your firends who are with you.

  ReplyDelete
 54. ምን ማለት እችላለሁ?
  ብቻ በጣም ተደስቻለሁ።
  እንኳን ለጡመራው ልደት አደረሰህ።
  እግዚአብሔር ብርታቱን ያድልህ።
  Alemu
  From Adama University

  ReplyDelete
 55. God bless you Dani, and your friends,

  ReplyDelete
 56. man for Ethiopia!

  ReplyDelete
 57. Danielin yefeter Amilak Kibir misigana Yidiresew ene erasen telahu

  ReplyDelete
 58. dani i hope yuo can do more and more GOD BLESS U

  ReplyDelete