ወይዘሮ ሐረገ ወይን ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲህ የሚል ታሪክ ላከችልኝ፡፡

በሳምንቱ ያንን የአትክልት ቦታ በተመለከተ ባለቅኔው ማስታወቂያውን ሠርቶ በተከፈለበት ጋዜጣ ላይ እንዲህ ሲል አወጣው፡፡
«ፀሐይ በምሥራቅ ስትወጣ ብርሃንዋን ያለ ሃሳብ የምታስተኛበት፣ ማታ በምዕራብ ስትገባ ደግሞ ጨረሮቿን የምትሰበስብበት፤ ከዳር ሆነው መስኩን ሲያዩት አዳም ጥሎት የወጣውን ገነት የሚያስታውስ፤ የነፋሱን ለስላሳ ሙዚቃ ተከትለው ዛፎቹ ከወገባቸው በላይ ሲዘናፈሉ በታወቀ የሙዚቃ ባለሞያ የሚሠለጥኑ ወጣት ሙዚቀኞችን የሚመስሉበት፤ ከቀኝ በኩል መንጭቶ ወደ ግራ የሚፈስሰው ምንጭ በቢራቢሮዎች እና በንቦች ሲታጀብ ከቃና ወይን ቤት የሚፈስስ የወይን ጅረት የሚመስልበት፤ በወንዙ ላይ የሚንፈላሰሱት ዳክዬዎች እና ፔሊካኖች ቡድን እየሠሩ የሚያደርጉት ዋና መላእክት በየነገዳቸው የወረዱ የሚመስሉበት አንድ የአትክልት ቦታ ለሽያጭ ቀርቧል፡፡ በሚከተለው አድራሻ ሄዳችሁ በማየት ግዙ፡፡»
ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ ባለቤቱ ከተዋዋሉት በላይ ለባለቅኔው ብዙ ሺ ብሮች ላከለት፡፡ ባለቅኔውም በሰውዬው ደግነት ተገርሞ ተቀበለ፡፡
ከብዙ ወራት በኋላ ባለ ቅኔውና የአትክልት ቦታው ባለቤት ሻሂ ቤት ውስጥ ተገናኙ፡፡
«እንዴት ሆነልህ? የአትክልት ቦታህን ሸጥከው?» ብሎ ባለ ቅኔው ጠየቀው፡፡
«አልተሸጠም» አለና ባለቤቱ መለሰ፡፡
«መቼም ያንን የመሰለ ማስታወቂያ ሳልጨምርም ሳልቀንስም ሠርቼ ገዥዎችን መሳቡ የተረጋገጠ ነው» አለ ባለ ቅኔው፡፡
«ላለመሸጡ ዋናው ምክንያትኮ ማስታወቂያው ነው» አለው ባለቤቱ ሻሂውን ፉት ብሎ እየሳቀ፡፡
«እንዴት፤ እኮ እንዴት» ባለቅኔው እየጓጓም እየደገጠም የያዘውን የሻሂ ስኒ ቀስ ብሎ አስቀምጦ ወንበሩን ወደ ጠረጲዛው አስጠጋ፡፡
«በጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ ሳየው የተጻፈው ስለ እኔ የአትክልት ቦታ መስሎ አልታየኝም፡፡ ያንን ማስታወቂያ ይዤ እንደ ገና ወደ አትክልቱ ቦታ ሄድኩ፡፡ እየተዘዋወርኩ አንተ በጻፍከው መሠረት አየሁት፡፡ እውነትክን ነው፡፡ ምንም ኩሸትም ሆነ ድቅሸት የለውም፡፡ ራሴን ወቀስኩት፡፡ እንዴት እስከዛሬ እንደዚህ አድርጌ አላየሁትም ? ብዬ ተናደድኩ፡፡ በመጨረሻም ይህንን ዓይን የሰጠኸኝን አንተን አመስግኜ ከውለታችን በላይ ብዙ ብር ከፈልኩህ፡፡ የአትክልት ቦታውን መሸጤንም ተውኩት፡፡ ይኼው ነው ምክንያቱ» አለው ባለቤቱ፡፡
የባለቅኔውም ፊቱ በደስታ ፈካ፡፡
«በአንተ እና በእኔ መካከል ያለውን ልዩነት ዐወቅከው? ልዩነቱ ያየነው የአትክልቱ ሥፍራ አይደለም፡፡ ሁለታችንም ያየነው አንድ ዓይነት ቦታ ነው፡፡ ሁለታችንን የለያየን ነገሮችን ያየንበት መንገድ ነው፡፡ አንተ በአትክልት ሥፍራው ውስጥ ለሚገኙት ደካማ ነገሮች ብቻ ትኩረት እየሰጠህ ነበር የምታየው፡፡ እኔ ደግሞ በአትክልት ሥፍራው ውስጥ ያለውን ውበት ነው ያየሁት፡፡» አለው ባለ ቅኔው፡፡
«ልክ ነህ» አለ ባለ አትክልቱ፡፡ «እኔ ወንዙን አይቼዋለሁ፤ ነገር ግን የዳክዬዎቹን እና የፔሊካኖቹን ትርዒት አላየሁትም፡፡ ዛፎቹን አይቻቸዋለሁ፤ ከንፋሱ ጋር ተዋሕደው የፈጠሩትን ውዝዋዜ ግን አላየሁትም፡፡ ለብዙ ቀናት በአትክልት ቦታው ላይ ሆኜ ፀሐይ መቶኛል፡፡ ለመጠለል ዛፎቹ ሥር እገባ ነበር እንጂ እንደ አንተ ግን የጨረሩን አመጣጥ አላየሁትም፡፡ እኔ ያየሁት ለአትክልቱ የማወጣውን የጥበቃ፣ የአትክልተኛ እና የኪራይ ገንዘብ ብቻ ነው፡፡
«ለኔ ያ ቦታ የአትክልት ቦታ ብቻ ነበረ፡፡ ለአንተ ግን የሕይወት እና የውበት ቦታም ጭምር ሆነ፡፡ እኔ የወዳደቁትን የረገፉ ቅጠሎች ስመለከት አንተ ግን የተንሳፈፉትን ሕይወት ያላቸው ቅጠሎች አሳየኸኝ፡፡ እኔ በደረቁ ዛፎች ስበሳጭ፤ አንተ ግን ከደረቅ ዛፍ ላይ ውበት አመነጨኽ፡፡
«እኔ ወንዙ በአትክልት ቦታው መካከል ሲያልፍ ግራ ቀኝ የፈጠረውን ረግረግ እና ጭቃ እንጂ በአወራረዱ ላይ ያለውን ውበት ለማየት አልታደልኩም፡፡ እኔ በየጊዜው እያደገ ካላጨድከኝ የሚለው ሣር አስመረረኝ፡፡ አንተ ግን ሣሩ እንደ ደብተራ ጎንበስ ቀና እያለ ሲዘምም አየኸው፡፡ አዲስ ነገር አላመጣኸም፤ አዲስ ዓይን እንጂ፡፡» አለው ባለ አትክልቱ የሻሂውን ጭላጭ አንጠፋጥፎ ሌላ ለማዘዝ አሻግሮ እያየ፡፡
«ድሮምኮ በዓለም ላይ አዲስ ዓይን እንጂ አዲስ ነገር የለም» አለ ባለ ቅኔው በጣቱ ጠረጲዛው ላይ እየጻፈ፡፡
«ዓይን አይደል የለየን» ባለ አትክልቱ ሣቀ፡፡
«እርሱ ብቻ አይደለም» አለ ደግሞ ባለ ቅኔው በሁለት መዳፉ አገጩን ደግፎ፡፡

«ይተንተንልኝ» አለ ባለ አትክልቱ ተጨማሪውን ሻሂ እያዘዘ፡፡ ባለ ቅኔውም ደገመ፡፡
«አንድን ነገር በፍቅር ላይ ሆነህ እና በጥላቻ ላይ ሆነህ፤ በደስታ ላይ ሆነህ እና በኀዘን ላይ ሆነህ፤ በብርሃን ላይ ቆመህ እና ጨለማ ላይ ቆመህ ስታየው የሚኖርህ ሥዕል ይለያያል፡፡ ውበት ያለውኮ በምታየው ነገር ላይ አይደለም፤ ዓይንህ ላይ ነው፡፡ ልቡናህ ውስጥ ነው፡፡»
«አንድ ነገር አስታወስከኝ» አለ ባለ አትክልቱ፡፡
«አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ እኔ ከሥራ ቦታዬ ወደ ቤቴ ስገባ እርሱን ወደ ውጭ ሲወጣ አገኘዋለሁ፡፡ ነገሩ ሲደጋገምብኝ ጊዜ አንድ ቀን ጠየቅኩት፡፡ ሁሌ ማታ ማታ ከሥራ ወደ ቤት ሳይሆን ከሥራ ወደ መሸታ ቤት ለምን ትሄዳለህ? አልኩት፡፡ ቤቴ አስጠላኝ አለኝ፡፡ በሦስተኛው ቀን አብረን ቤቱ ሄድን፡፡
«የወርቅ ፍልቃቂ የመሰሉ ልጆች አሉት፡፡ ባለቤቱ ትኁት እና ባለሞያ ናት፡፡ የቤት አያያዝዋ ቤቱን ቤተ መንግሥት አስመስሎታል፡፡ የዕቃዎቹ አደራደር ሊቃውንተ የተጠበቡበት እንጂ ብቻዋን ያደረገቸው አይመስልም፡፡ ያቀረበችልን ምግብ ሳትበላው በአቀራረቡ ብቻ ትጠግባለህ፡፡
«ምኑ ነው ቤትህ ያስጠላህ? አልኩት፡፡ ያየሁትን ነገር ስነግረው ስለ እርሱ ቤት የምነግረው አይመስለውም ነበር፡፡ እርሱ ቤቱን እንጂ የቤቱን ዝርዝር አይቶት አያውቅም፡፡ ምሳ መብላቱን እንጂ አቀራረቡን፣ አወጣጡን እና አዘገጃጀቱን አድንቆት አያውቅም፡፡ መጀመርያውኑ ቤቱ ያው ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም ምንም ነገር አይታየውም፡፡ ለማየት አልተዘጋጀማ፡፡» ባለ አትክልቱ ከሻሂው ተጎነጨለት፡፡
«ለዚህኮ ነው ነገሮችን እንድንጠላ፣ እንድንንቅ፣ እንድናማርር እና እንድንሰለች፣ ከሚያደርጉን ምክንያቶች አንዱ የምናይበት አተያይ ነው የሚባለው፡፡ እኛ የሰለቸንን፣ የምናማርረውን እና ያስጠላንን ቤት ሌሎች መጥተው ሲያዩት ሰፍ ይሉለታል፡፡ ይጓጉለታል፡፡ እኛ አቃቂር የምናወጣለትን እነርሱ ቅኔ ይቀኙለታል፡፡ እኛ የምናሾፍበትን እነርሱ ውዳሴ ያዘንቡለታል፡፡ እኛ ያቅለሸለሸንን እነርሱ ይቀኑበታል፡፡ ልዩነቱ ከአስተ ያያታችን ነው፡፡
«አያሌ ባለትዳሮች ትዳራቸው እና የትዳር አጋራቸው የሚሰለቻቸው በእውነቱ ነገሩ አሰልች በመሆኑ ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ የሚያዩበት ዓይን ጉዳይ ነው፡፡ በቤታቸው ውስጥ ምንድን ነው የሚያዩት? ነው ጥያቄው፡፡ በቤቱ ውስጥ ከሚያናድደው፣ ከሚያስጠላው እና ከሚያስመርረው ነገር ይልቅ የሚያስ ደስተውን፣ የሚያረካውን እና ነፍስን በሐሴት የሚሞላውን ነገር ማየት ለምን አይጀምሩም? ሚስቴ ያው ሚስቴ ናት፤ ባሌም ያው ባሌ ነው ብለውኮ ነው የሚያስቡት፡፡
«አንዳንዶቹማ እነርሱ ያላዩትን የትዳር አጋራቸውን ውበት ሌላው ያየውና መማለል ሲጀምር ነው ያልታያቸውን ውበት ማየት የሚጀምሩት፡፡ ለካ እንዲህ ነበረ ማለት የሚጀምሩት፡፡»
«ምን እርሱ ብቻ» አሉ ባለ አትክልቱ፡፡ «አሁን ሳስበውማ በሀገር ላይ ያለው ችግርም ይኼው ነው፡፡ ለመሆኑ የት ላይ ቆመህ ነው ባህልህን፣ እምነትህን፣ ቅርስህን፣ ማንነትህን፣ ታሪክህን የምታየው? ይኼኮ ወሳኝ ነው፡፡ እስኪ ተመልከት እኛ የምንንቃቸውን፤ አይተናቸው የማናውቃቸውን፤ ከቁም ነገር ያልቆጠርናቸውን ነገሮች ሌሎች ከሩቅ መጥተው መጽሐፍ ጽፈው፣ ፊልም ሠርተው፣ ዘገባ አዘጋጅተው በሚዲያ ሲያቀርቡት እንገረማለን፡፡ እኛ ያላየነውን እኛ እነርሱ ያዩልናል፡፡ የናቅነውን ያከብሩታል፡፡ የጣል ነውን ያነሡታል፡፡
«ችግሩ እንዳልከው የጉዳዩ መኖር አለመኖር አይደለም፤ አተያያችን ነው፡፡ የዓይን ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ለታቦተ ጽዮን ከምንሰጠው ክብር በላይ እነርሱ ለአንድ የጥንት ብርጭቆ ይሰጣሉ፡፡ ለምን? እኛ ራሳችንን በንቀት አምባ ላይ ቆመን ነው የምናየው፤ እነርሱ ግን ራሳቸውን በክብር አምባ ላይ ቆመው ነው የሚያዩት፡፡
«ኢትዮጵያውያን ከግብፃውያን በበለጠ የዓባይ ወንዝ ባለ ድርሻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ግብፃውያን የተጠቀሙበትን ያህል ለምን አልተጠቀሙበትም? ግብፆቹ ዓባይን በህልውና ዓይን ሲያዩት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዘፈን ዓይን አዩት፡፡ እነዚያ ብዙ ግድብ ሠሩ፤ እነዚህ ደግሞ ስለ ዓባይ ብዙ ዘፈን ዘፈኑ፡፡ ችግሩ ከዓባይ ይመስልሃል? አይደለም፡፡ ከዓይናቸው ነው፡፡»
ሁለቱም ሻሂያቸውን ጨለጡና ተያዩ፡፡ እናም አንዱ ከሌላው ላይ አይተውት የማያውቁትን መልክ አነበቡ፡፡
Thank you Dn. Daniel
ReplyDeleteAyin libonachinin yigletin
ዓይነ ልቡናዬን አብራው! ይሏል ለእንደዚህ አይደል
ReplyDelete"ዘነሳእከ በከንቱ..." ሆኖ እንጂ መርበብቱ እንዲህ ያለች ምክር ሰናይት "በከንቱ" ለማውረድ ብንጠይቀው አፍንጫህን ላስ ነበር ሚለን።ያስተማረን የመከረን የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን።ለሰማ ላሰማ ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
ReplyDeleteከንቱ=Free
መርበብ=Internet?Network?
ወረደ=Download.
Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel
ReplyDeletePlease GOD bless our already given wonderful eyes so we can appreciate and be gratefull of what we have. Emebetachin Tamalden. Atlanta.
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዳኒ በጣም ጥሩ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሥነ ጽሑፍ ነው። ቸሩ መድኃኔ ዓለም በሕይወት ላይ ሆና ሞትን የምታ ዓይንን ለሁላችን ይስጠን
ReplyDeleteተስፋብርሃን
ወይ አይን አያስነብብበኝ ነገር የለ!
ReplyDeleteበጣም ይገርማል....አይን እያለን አንዳንዴ አለማየታችን ዛሬ አስደነቀኝ.....
ReplyDeletesuch eye is a gift from God. Always looking the positive and the beautiful side. May God give us such an EYE
ReplyDeleteወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል! ድንቅ ነው። ችግሩ ያለው ዓይናችን ላይ ሳይሆን ዓለምን የምናይበት መነጽር ላይ ነው። አንዱ በንፁሕ መነጽር ያየዋል፣ ሌላው ደግሞ ባልፀዳ መነፅር። አንዱ በፍቅር ሲያይ ሌላው ደግሞ በጥላቻ። አንዱ በርኅራሄ ሲያይ ሌላው ደግሞ በጭካኔ። በውነቱ እህታችን ጥሩ ታዝባለች።
ReplyDeleteKale hiwet yasemaln D.Dani bewnet rsin asayehgn yet lay endekomkugn endastewl adrgognal tshufu,tsgawn yabzalh fetari.
ReplyDeleteEGZIABHER YISTILIGN KALEHEWET YASEMALIN D.DANIEL.
ReplyDelete«ችግሩ እንዳልከው የጉዳዩ መኖር አለመኖር አይደለም፤ አተያያችን ነው፡፡ የዓይን ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ለታቦተ ጽዮን ከምንሰጠው ክብር በላይ እነርሱ ለአንድ የጥንት ብርጭቆ ይሰጣሉ፡፡ ለምን? እኛ ራሳችንን በንቀት አምባ ላይ ቆመን ነው የምናየው፤ እነርሱ ግን ራሳቸውን በክብር አምባ ላይ ቆመው ነው የሚያዩት፡፡
ReplyDelete«ኢትዮጵያውያን ከግብፃውያን በበለጠ የዓባይ ወንዝ ባለ ድርሻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ግብፃውያን የተጠቀሙበትን ያህል ለምን አልተጠቀሙበትም? ግብፆቹ ዓባይን በህልውና ዓይን ሲያዩት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዘፈን ዓይን አዩት፡፡ እነዚያ ብዙ ግድብ ሠሩ፤ እነዚህ ደግሞ ስለ ዓባይ ብዙ ዘፈን ዘፈኑ፡፡ ችግሩ ከዓባይ ይመስልሃል? አይደለም፡፡ ከዓይናቸው ነው፡፡»
ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ለእኛም ዓይነልቦናችንን ያንራልን
ወ/አማኑኤል
mn,usa
Wow! My eyes!
ReplyDeleteDn. Daniel it is a really intersting all the time i can see my weakness through your mirror "emeamlak keante gar tehun" tamrat from st. Raguel wednsday gubaye
ReplyDeleteበጣም ጥሩ ነው እግዚህብሄር ይስጥልን::
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል በአንተ ላይ አድሮ ያስተማረን፣ የመከረን፣ የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ የአንተንም የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ፣ ቃለህይወትን ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፡፡ እኛንም አይነ ልቦናችንን ያብራልን፡፡ አሜን ወአሜን
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDeleteአባቶች ሲያስተምሩ
ትምህርት በ ዓይን ይገባል ይላሉ
ፍቅርም እንዲሁ-----
እንደኔ እንደኔ በዓይን ያየነውን ማስተዋል ነው ያቃተን፡፡
ዓይነልቦናችንን ያብራልን አሜን፡፡
What a wonderful 'EYE'. Egzi'abhere Yihnen yetebib Ayin yadelen.
ReplyDeleteአረጋዊ ስምኦን በመንፈስ ዐይን ቢያይ "አይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና" በማለት ወልደ አብ መሆኑን መሰከረ::ሌሎች ግን አይተው ወልደ ዬሴፍ አሉት፡፡
ReplyDeleteአይንማ ለሁሉም ተሰጥታለች፡፡ በጥበብና በመንፈስ መልከት ግን ለጥቂቶች!!
I like the idea but I think it is a little bit exaggerated. I don't think there is this kind of big difference b/n peoples who have the same cultural and societal background.I think it is a matter of our interest than our eye......it is our internality that matters.
ReplyDeleteAnd I think the story represents our culture....most of the time we don't like to give good things for others...the story tells me how we are jealousy of each other.
Wonderful story. AS the proverb says " beauty holds in the eye of the beholder"
ReplyDeleteA very nice article!Egziabher Amlak kale hiwotin yasemalin.
ReplyDeleteፀበልንና አጥማቂዎችን እንዲሁም መናፍስትን የሚያስወጡ አባቶችን በባለ አትክልተኛው አይን የሚያዩ ወጣት ክርስቲያኖችን እስኪ አንድ በላቸው
ReplyDeleteሰይፈ ገብርኤል
qale hiwot yasemalign
ReplyDeletemikirun teqebiyalehu
betam amesegnalehugn
መልካም ልደት ለጡመራህ ፤
ReplyDeleteአንተንም እግዚአብሔር የበለጠ ለመስራት ያብቃህ እድሜና ጤናዉን ያድልህ፡፡
ወ/አማኑኤል ከሚንሶታ አሜሪካ
ዓይናችን የሚገለጠዉ ለዘፈን፤ ለተረት ና ለፉገራ ፡ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ReplyDeleteዓይነልቦናችንን ያብራልን መልካሙን ነገር ይግለጽልን፡፡ ለስራ ያነሳሳን፡፡
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ዕደሜና ጤናዉን ያድልህ ፡፡
ወይዘሮ ሐረግ እና ዳንኤል ምስጋና ይድረሳችሁ::
ReplyDeleteግብፆቹ ዓባይን በህልውና ዓይን ሲያዩት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዘፈን ዓይን አዩት፡፡ እነዚያ ብዙ ግድብ ሠሩ፤ እነዚህ ደግሞ ስለ ዓባይ ብዙ ዘፈን ዘፈኑ፡፡ ችግሩ ከዓባይ ይመስልሃል? አይደለም፡፡ ከዓይናቸው ነው፡፡ ትክክል ብለሻል:: በህልውና አይን ማየት ካልጀመርን በስተቀር ዓባይን መጠቀም እንጀምርም:: ዓይነ ልቦናችንን ያብራልን::
ወረት ያለው አይን ላይ ነው እንዴ ዳንኤል ወይንስ ልብ ላይ ጥሩ ጽሁፍ ነው ይህ ነገር እኮ ለዘመኑ ተሀድሶዎችም ጥሩ ትምህርት ነው የቤተክርስቲያነችን በረከትዋ ሰላምዋ በእርሳ የሚገኘው ጽድቅ በዚያ የምናኛቸው ቅዱሳን አባቶቻችን ታቦቱ ጸበሉ ያሬዳዊ ዜማው........................................ ሳይሆን ትንሻ ስግደት ትንሻ መከራ ትንሻ ጾም ትንሻ ችግር ናት እናም ከዚህ ለመሸሽ የማይኮነውን ይሆናሉ ከበፊቱም አይን ላልነበራቸው አላዝንም አይይን ለቀየሩ ግን አዝናለሁ ድመት መነጽር ስታደርግ የሚታያት አይጥ ብቻ ነው አሉ
ReplyDeleteዳንኤል የጻፍከዉን ጽሁፍ አነበብኩት ጡሩ ነዉ ግን ሁልግዜ ጡሩዉን ብቻ ማየት ለለዉጥ እንድንነሳሳ አያደርግም።ማለትም ይህን አታሳጣኝ አይነት ልመና ነዉ ወደሗላ ያስቀረን የሚል እሳቤ አለና ፈረንጆቹ comfort zone is not always comfort በሚሉት አምናለሁ የተመቸን መስሎን በመጥፎ ሁኔታዉስጥ እየኖረርን ያአለን አለንና! .....
ReplyDeleteLong live to Dani’s Blog !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteYelibonan meklikam eyita yemiyatefaw bizu neger yinoral. bezihe lai tinish bibal melikam newe.
ReplyDeleteKale hiwot yasemaln.
እግዚአብሔር ይስጥልን።
ReplyDeleteቃለ ሕይወትንም ያሰማልን።
ስለነገሩ ምን ማለት ይቻላል? በጣም ይገርማል!።
አንዳንድ ጊዜ ራሳችንን ለማየት እንጀምርና አይናችን
ተመልሶ ይጠፋል። ግን ለምን ይሆን?
እስኪ ራሳችንን ማየት የጀመርንበት ዓይናችን ተመልሶ
እንዳይጠፋ እንፀልይ።
Alemu Adama University(Nazareth)
Kale hiwot yasemaln. e/r tenawn yistih
ReplyDeleteU r ßlessed.
ReplyDeleteAm here 2 ßeg God 2 ßless u More!
(AGE)
መምህር እዲህ ነው ለማለት ቃላት ያጥረኛል እግዚአብሄር አምላክ ፀጋውን ያብዛልህ የአገልግሎት ዘመንህን ይጠብቅልህ!!! በጣም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ጽሁፍ ነው ጸሁፉን ሳነበው የብዙዎቻችን እንደሚመለከት ተገነዘብኩኝ የብዙዎቻችን ችግር አንድን ነገር ስንመለከት በጥሩ ጎኑ ሳይሆን በመጠፎ ጎኑ ነው። ስለዚህ አመለካከታችን በሁለቱ በኩል ይሁን.....
ReplyDeleteበወንዱማችን ላይ አድሮ ላስተማረን እግዚአብሄር ይመስገን አሜን......
it is a good idea,thank you d.dani.
ReplyDeleteእይታውም ሆነ የጽሁፉ አቀራረብ ሳቢና በሳል ነው በእርግጥ በአቋም ደራጃ ከላይ በ@efrata የተሰጠውን comment እጋራለው
ReplyDeleteወይ እኔ... ለኔ ነው ይሔ ሁሉ።
ReplyDelete