Sunday, March 13, 2011

ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው?


የግሪክ፣ የካቶሊክ፣ የሶርያ፣ የሕንድ፣ የሩሲያ፣ የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትን ስንክሳሮች ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ በእነዚህ ቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ለቅድስና የበቁ አባቶች እና እናቶች ታሪክ ጾም፣ ጸሎት፣ ትምህርት፣ ሱባኤ፣ ትኅርምት፣ ተጋድሎ፣ ሰማዕትነት፣ በድፍረት መመስከር፣ ንጽሕና፣ ተባሕትዎ፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድረግ፣ ለሌሎች መሠዋት አና ሌሎችንም የእምነት እሴቶችን እናያለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡
የሂንዱይዝምን፣ የኮንፊሺየዝምን፣ የዞራስተሪዝምን እና የሌሎችንም የቀደምት ሰዎች እምነቶችንም እንይ፡፡ ጾም እና ጸሎት፣ ምናኔ እና ተጋድሎ፣ ራስን መግዛት እና ይህንን ዓለም መናቅ፣ ማስተማር እና መማር፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድርግ እና ለሌሎች መሥዋዕት መሆን የእምነቶቹ መሠረታውያን እሴቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡

እነዚህ ነገሮች እንድ ነገር ያመለክቱናል፡፡ ሃይማኖት ስሙ እና ሕግጋቱ ቢለያዩም ከመማር እና ከማስተማር፣ ለራስ የእምነቱን ሕግጋት ከመጠበቅ፣ ከውሳጣዊ ንጽሕና እና ለሌሎች በጎ ነገር ከማድረግ ጋር ፍጹም የተገናኘ መሆኑን፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሳስታለች፤ መሥመርዋን ለቅቃለች ልናስተካክላት ይገባል ብለው የሚያምኑ ሰዎች መነሣታቸውን ከልዩ ልዩ ምንጮች ስንሰማ ከረምን፡፡ እኔ በሃሳባቸው መቶ በመቶ ባልስማማም፤ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ማሰቡ ግን መብቱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የሚከራከርበትን ሃሳብ በግልጽ አውጥቶ፤ የማምነው እንደዚህ ነው ብሎ፣ የማይቀበለውን ኮንኖ በሠለጠነ መንገድ ሃሳቡን ካቀረበ ይኼ ሰው ጤነኛ ሰው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
እንዲህ ካለው ጤነኛ ሰው ጋር መከራከር፣ ሃሳቡን በሃሳብ፣ መጣፉን በመጣፍ፣ አባባሉን በአባባል፣ ነቀሳውን በነቀሳ መሟገት እና ቢቻል መግባባት ባይቻል ደግሞ ከነ ልዩነት መኖር ይቻላል፡፡
ሰሞኑን የምንሰማው ግን ከዚህ የከፋውን ነው፡፡ ይህንን ዓይነት አመለካከት የያዙ ሰዎች በመማር እና በማስተማር፣ በመከራከር እና በማስረዳት፣ በግልጽ አውጥተው በማሳየት እና በማሳመን ሳይሆን በማጭበርበር እና በስለላ፣ በማጥፋት እና በማውደም መንገድ እምነታቸውን ለማሥረጽ መሞከራቸውን አየን፡፡
 ይኼ ከጤነኛነት ያለፈ መንገድ ስለሆነ እንቃወመው ዘንድ ግድ ነው፡፡
አንድ ሰው በታቦት ክብር እና ሃይማኖታዊ ዋጋ አላምንም ብሎ የሚያምነውን ማስተማር ይችላል፡፡ ከፈቀድን እንቀበለዋለን፤ ካልፈቀድን በጨዋ ደንብ አንቀበልህም እንለዋለን፡፡ እርሱ በታቦት ሥርዓት ስላላመነ የኢትዮጰያ ቤተ ክርስቲያን ታቦታትን ለማጥፋት፣ ለማስሰረቅ፣ አስሰርቆም ለመሸጥ ከተነሣ ግን ስለ እምነትም ስለ ሀገርም፣ ስለ መብትም ብለን ሰው የተባልን ሁሉ እንቃወመዋለን፡፡
አንድ ሰው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት ላይ ጥያቄ በመጠየቁ ጠላት ነው ብለን አናምንም፡፡ ምናልባት የተለየ አመለካከት ያለው ሰው እንለዋለን እንጂ፡፡ ከራሱ እይታ እና መረጃ ተነሥቶ «ስሕተት ናቸው» ብሎ ማስተማሩንም ባንወድድለትም እናከብርለታለን፡፡ ምናልባት ማስረጃውን በማስረጃ፣ ሃሳቡን በሃሳብ እየተነተንን መልስ እንሰጠው ይሆናል፡፡ ጠላታችን ነው ብለን ግን አንነሣበትም፡፡
ከዚህ ድንበር ተሻግሮ እርሱ የማይፈልጋቸውን አዋልድ መጻሕፍት ለማቃጠል፣ ለመቆንጸል፣ ከየዕቃ ቤቱ ወጥተው ወደ ባዕድ እጅ እንዲገቡ ለማድረግ፣ ብራናውን ለማበላሸት፣ ቀለሙን ለማጥፋት፣ ዕቃ ቤታቸውን ለማቃጠል ከተነሣ ግን ይህ በእምነት ብቻ ሳይሆን በሀገርም ላይ የተነሣ የታሪክ እና የቅርስ፣ የመብት እና የጤነኛ አስተሳሰብ ጠላት ነውና እንቃወመዋለን፤ እንታገለዋለንም፡፡
ገዳማዊ ሕይወትን የተቃወሙትን ሁሉ አንጠላቸውም፤ ስላልገባቸው ነው፤ የዕውቀት ማነስ ነው ብለን እንገምታለን፤ ያለበለዚያም ደግሞ ጫፋችንን እስካልነኩን ድረስ በዚህ መንገድ ማመን መብታቸው ነው ብለን እንተዋቸዋለን፡፡ ከዚህ አልፈው ወደ ገዳማት እየገቡ ቅርስ የሚዘርፉ፣ ሴት ገዳማውያንን የሚደፍሩ፣ የተሣሣተ መረጃ በገዳማት ውስጥ የሚነዙ ከሆነ ግን እምነታችንን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ እና ሕጋዊ መብታችንን ተዳፍረዋልና እናጋልጣቸዋለን፤ በሕግ መንሽም ለፍርድ ነፋስ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፡፡
አንድ ክርስቲያን እስልምና የተሳሳተ እምነት ነው ብሎ ሊያምን ይችላል፡፡ ይህንን አመለካከቱንም ማስተማር እና የተቀበሉትን ማሳመን ይችላል፡፡ የራሱ እምነት ከእስ ልምና የተሻለ ነው የሚልበትን ምክንያት እና ማስረጃ እያቀረበ መከራከር እና መሟገት መብቱ ነው፡፡
ከዚህ አልፎ መስጊድ ውስጥ ገብቶ የጸሎት ሥርዓትን መበጥበጥ፣ የመድረሳ /ቤቶችን ማፍረስ፣ የሙስሊም ልብስ ለብሶ ተመሳስሎ በመግባት የእስልምና እምነት አማኞችን ሰላም መንሣት፣ ቁርዓን ማቃጠል፣ የእስልምናን ጥንታውያን ቅርሶች ማጥፋት፣ በእስል ምና ጉዳዮች ምክር ቤት የአሠራር ሥርዓት ውስጥ ሠርጎ የአሠራር ሥርዓቱን መበጥበጥ ከጀመረ ግን ከጤነኛ እና ከሕጋዊ መንገድ አልፏልና ከሙስሊሞቹ ጋር አንድ ሆነን እንቃወመዋለን፤ እንታገለዋለንም፡፡
ማንኛውም እምነት ሰይጣናዊነትን ይቃወማል፡፡ በራሱ በሰይጣን የሚያምን ካልሆነ በቀር፡፡ የሰይጣናዊነት ሁለቱ ዋና ዋና መገለጫዎች ደግሞ ክፋት እና ተንኮል ናቸው፡፡ በእምነት ስም ወንጀል ለመሥራት ካልታሰበ በቀር ከእምነት ጋር ክፋትን እና ተንኮልን አሥተሣሥሮ መጓዝ ወተት እና ኮምጣጤን አብሮ ከማኖር በላይ የማይቻል ነው፡፡
አሁን አሁን የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እናድሳለን ብለው በተነሡ አካላት ዘንድ የምናየው እና የምንሰማው ነገር የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በመቃወም የተነሣ ሌላ ንቅናቄ አይደለም፡፡ ክፋትን እና ተንኮልን አንግቦ የተነሣ ሰይጣናዊ ንቅናቄ እንጂ፡፡ ዓላማውም ማደስ አይደለም፡፡ ማፍረስ እንጂ፡፡
እስካሁን ድረስ በየትኛውም የእምነት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ስለላን፣ ሤራን፣ ማፍረስን፣ ስርቆትን፣ ዘረፋን እና ማታለልን የእምነቱ ማራመጃ መንገዶች ያደረገ ብቸኛ የእምነት ንቅናቄ አለ ከተባለ እርሱ ዛሬ ዛሬ የምንሰማው «የተሐድሶዎች ንቅናቀ&» ብቻ ነው፡፡
ትክክለኛ ነገር አለኝ፤ በያዝኩት ነገር አምንበታለሁ፤ ለያዝኩት ነገርም እከራከርበታለሁ፤ ማስረጃ እና መረጃም አለኝ፤ የኔ መንገድም የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ የሚል አካል ራሱን በይፋ ገልጦ፣ ፊት ለፊት ወጥቶ፣ ሃሳቡን አንጥፎ፣ ማስረጃውን አሰልፎ በብርሃን ይጓዛል እንጂ በጠላት ከተማ እንደ ገባ ሰላይ የድብቅ መንገድ አይጓዝም፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊም መንፈሳዊም ተቋም ናት፡፡ መብቶቿ እና ጥቅሞቿ በሕግ ልዕልና ያላቸው ናቸው፡፡ ተቋሞቿ፣ ንብረቶቿ፣ /ቤቶቿ እና ቅርሶቿን የመጠቀም፣ የመጠበቅ፣ የመከባከብ እና ለትውልድ የማስተላለፍ መብት አላት፡፡ በእነዚህ ክልሎች ገብቶ ማንም ሌላ ወገን ያልፈቀደችውን ተግባር በድብቅ እንዳይፈጽም ሕግም ሞራልም ይከለክለዋል፡፡
አሁን እያየነው ያለነው ተግባር ግን የሃይማኖት አስተምሮን ተቃውሞ ሌላ የተሻለ አስተምህሮ የማምጣት ተግባር ሳይሆን ክፋት እና ተንኮልን ገንዘብ ያደረገ የሤራ ተግባር ነው፡፡ በገዳማት ገብቶ ብራና መፋቅ፣ የአብነት /ቤቶችን መበተን፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ገብቶ በርዳታ ስም ሀብቷን መበከል፤ ቅርሶቿን መዝረፍ እና መሸጥ፣ ጥንታውያን ተቋማቷን ማውደም፤ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ንዋያተ ቅድሳትን እና መጻሕፍትን ማበላሸት በምን መመዘኛ ነው የሃይማኖት ሥራ የሚሆነው?
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጥንታዊ የክርስትና ትምህርት ጠባቂ፣ የጥንታዊ እና ታሪካዊ የክርስትና ሀብቶች ባለቤት፣ የጥንታዊ መጻሕፍት ግምጃ ቤት፣ የቀደምት ኢትዮጰያዊ ባህሎች እና ትምህርቶች መገኛ፣ የሀገራዊ የአስተምህሮ ጥበብ ማዕከል፣ የቀዳሚ ክርስቲያናዊ ዜማ መፍለቂያ፣ በብዙዎች ዘንድ የጠፉ የአበው ድርሳናት ማከማቻ፣ ልዩ ክርስቲያናዊ ማዕከል ናት፡፡
በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በሤራ የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በሦስት ነገሮች ላይ የሚሠራ ወንጀል ነው፡፡ በክርስትና ላይ፣ በሰው ልጅ ታሪክ ላይ እና በሀገር ላይ፡፡
በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ተጀምሮ ምዕራቡን ዓለም መንፈሳዊነት ወደ ተለየው ክርስትና የከተተው የተሐድሶ ነፋስ በክርስትና እና በክርስቲያናዊ ሀብቶች ላይ የማይተካ ጥፋት አድርሷል፡፡ በወቅቱ በተቀሰቀሰው ስሜታዊነት በተሞላው ነውጥ ምክንያት አያሌ ክርስቲያናዊ ትምህርቶች እና ቅርሶች ላይመለሱ ጠፍተዋል፡፡ ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላ ብዙ ሀገሮች ከቀበሩበት ሊያወጧቸው እንደ ዔሳው በዕንባ ቢፈልጓቸው ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡
በዚህ የተነሣ ታላላቅ የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ማኅበራትን አቋቁመው በሌሎች ሀገሮች ያሉ ቅርሶች ተመሳሳይ ውድመት እንዳይደርስባቸው የቻሉትን ሁሉ በፀፀት ሠርተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ከደረሰው ጥፋት በእግዚአብሔር ቸርነት ከተጠበቁት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለዚህ ነበር አያሌ ሚሲዮናውያን እና አሳሾች ቅርሶቻችንን ሲዘርፉ እና ሲተረጉሙ የኖሩት፡፡
አውሮፓውያን በክርስትና ላይ የሠሩት የማይካስ ወንጀል አምላክ የለሽ ትውልድ እንጂ ጻድቃንን አላፈራላቸውም፡፡ ይህንን ወንጀል ኢትዮጵያ ላይ ለመድገም መነሣት ክርስትናን ያለ ጥግ ማስቀረት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውርጅናሌው ክርስትና ምን እንደሚመስል በትክክል ማሳየት ከሚችሉ ጥቂት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት፡፡ ለዚህ ነው በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በክፋት የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በክርስትና ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against Christianity) ነው የምንለው፡፡
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታላላቅ ለውጦች ካመጡት ታሪኮች ዋነኛው ክርስትና ያመጣው ለውጥ ነው፡፡ ለዚህም ነው የክርስትና ታሪክ ከሰው ልጆች ታሪኮች መካከል ዋነኛው ታሪክ የሚሆነው፡፡ ክርስትና ትምህርት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብ፣ የትምህርት መንገድ፣ ርዕዮተ ዓለም፣ የሥነ መንግሥት ምንጭ፣ ፍልስፍና፣ የሥልጣኔ መዘውር፣ የዓለምን መልክዐ ምድር ቀያሪ፣ የሥነ ጽሑፍ መንገድ፣ የሥነ ሥዕል መርሕ፣ የሥነ ጥበብ ትልም፣ የሥነ ዜማ ስልት፣ የሕዝቦች መገናኛ ድልድይም ሆኗል፡፡ በመሆኑም የክርስትና ሀብቶች እና ቅርሶች የአንድ እምነት ሀብቶች እና ቅርሶች ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሀብቶች እና ቅርሶች ሆነዋል፡፡ በእነዚህ ሀብቶች እና ቅርሶች ላይ እናድሳለን በሚሉ አካላት የሚሠነዘረው ጥፋት በሰው ዘር ሀብት ላይ የሚሠነዘር ጥፋት (crime against human heritage) የሚሆነውም በዚህ የተነሣ ነው፡፡
ጥፋቱ ከዚህም አልፎ ሀገራዊ መልክም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያን አብዛኛውን ሕዝብ የምትወክል፣ አስተሳሰቡን እና ርዕዮቱን የምትቀርጽ ተቋም ናት፡፡ ታሪኳ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ባህልዋ የሀገሪቱ ባህል፣ ቅርሷ፣ የሀገሪቱ ቅርስ፣ ጥበቧ የሀገሪቱ ጥበብ፣ ዘመን መቁጠርያዋ የሀገሪቱ ዘመን መቁጠርያ ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀሪቱ አንዷ እና ዋነኛዋ መገለጫ ናት፡፡ እናም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ሀብቶች ላይ የሚሠነዘር ጥፋት ሁሉ በሀገር ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against the mother land) ነው፡፡ የሚመለከተውም የቤተ ክርስቲያኒቱን አማንያን ብቻ ሳይሆን መላውን ኢትዮጵያዊ፣ የሀገሪቱን መንግሥት እና የኢትዮጵያን ወዳጆች ሁሉ ነው፡፡
እናም ክርስትና ስለላ፣ ሤራ፣ ዝርፊያ፣ ውድመት እና ደባ አይደለምና፤ የክርስትናም መንገድ ቀና እና ግልጥ እንጂ ተንኮል እና ክፋት አይደለምና ይህንን በክርስትና ስም በክርስትና፣ በሰው ዘር ሀብት እና በሀገር ላይ የተቃጣ ወንጀል አንድ ሆነን ልንቃወ መው፣ ልናስቆመውም ይገባል፡፡
የመርከቡ ወለል በተሠራበት ቁስ አለመስማማት ይቻላል፤ የመርከቡን ወለል መነቃቀል መጀመር ግን ትርፉ ተያይዞ መስጠም ነው፡፡ 

63 comments:

 1. "....የመርከቡ ወለል በተሠራበት ቁስ አለመስማማት ይቻላል፤ የመርከቡን ወለል መነቃቀል መጀመር ግን ትርፉ ተያይዞ መስጠም ነው፡፡..." ትክክል. !!!

  ReplyDelete
 2. Kale hiwot yasemalin Dn. Daniel.
  I feel like we are in a war. A battle to preserve our beloved church and country from the evil envaders. By any means necessary, we have to fight the enemies of our church. I have a feeling that this the work of those who can't accept the existence of Tewahido in an African country. So please Dn Daniel if you have any idea what we should do for a new movement? we can eat only once a day instead of three and help this cause by our money. GOD PROTECT OUR CHURCH!!! Atlanta.

  ReplyDelete
 3. Dani, Kale Hiwot Yasemalen .

  ReplyDelete
 4. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን። አኛ ባለማወቅ ከአጥፍዎች hጋር አንዳንተባበር ይቺን ቤተክርስቲያን ከተሃድሶዎች ለመታደግ የሚደክሙትን በመርዳት ሃይማኖታችንን አና ታሪካችንን ለማስጠበቅ አና ከበረከቱም ለመካፈል አንድንችል ለዚ ተግባር የሚሰሩ ሰዎችን ወይም መሃበራት ካሉ አነሱን የምንረዳበትን መንገድ ካለ ቢጠቁሙን አላለሁ።

  ReplyDelete
 5. +++
  እ/ር ይስጥልን ጥሩ ጥቆማ ነው ልብ ላለው::

  በርታ

  ReplyDelete
 6. እስካሁን ድረስ በየትኛውም የእምነት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ስለላን፣ ሤራን፣ ማፍረስን፣ ስርቆትን፣ ዘረፋን እና ማታለልን የእምነቱ ማራመጃ መንገዶች ያደረገ ብቸኛ የእምነት ንቅናቄ አለ ከተባለ እርሱ ዛሬ ዛሬ የምንሰማው «የተሐድሶዎች ንቅናቀ&» ብቻ ነው፡፡

  የመርከቡ ወለል በተሠራበት ቁስ አለመስማማት ይቻላል፤ የመርከቡን ወለል መነቃቀል መጀመር ግን ትርፉ ተያይዞ መስጠም ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጽርፈትና የጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱት በዋናነት የራሳቸው ማንነት የጠፋባቸው ምዕራባውያን(ሉተራውያን) ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ከመቶ ዓመታት በላይ በራሳቸው ጥረትና ስልት የወጡትን ያህል ወርደዋል፤ የወረዱትንም ያህል ወጥተዋል፤ ነገር ግን የተመኙትንና የፈለጉት በእጃቸው ማድረግ አልቻሉምና ሌላ ስልት ሌላ ስትራቴጂ መቀየስ ግድ ነው፡፡ ይህ ስትራቴጂ ደግሞ ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር ሻማና ክር ሆኖ በመመሳሰል እንዲቀረጽ የተደረገ በመሆኑ ብዙዎቻችን የተሃድሶአውያን ተላላኪነት በፍጹም ሊገባን አልቻለም፡፡

  ተሃድሶ የፕሮቴስታንቱ ዓለም ተላላኪ መሆኑ ግልጥ ያለ ነገር ነው፡፡ ማስረገጫው ደግሞ በዚሁ አዚም የተማረኩ ወገኖች ይኸው ቡድን በሚያደረግው የጸሎትና የዝማሬ ዝግጅት ላይ ሲገኙ የገጠማቸው ፕሮቴስታንታዊ ሥርዓት ነው፡፡

  በመሠረቱ ማንም ሃሳቡን ማራመድ ይችላል፤ የፈለገውን ማመንም እንዲሁ፤ ዓለማመንም የራሱ መብት ነው፡፡ በእኛ ቅኝት ዝፈኑ ማለት ግን በእኔ ሳንባ ተንፍሱ፣ በእኔም አፍ ተናገሩ ማለትን ግን የትኛውም የሰው ልጅ ሊቀበለው የማይችል ጉዳይ ነው፡፡

  ልጅ የቤተሰቡ ነገር ካልተመቸው ወጥቶ በራሱ መንገድ ራሱን መምራት የሚጠበቅ ነው፤ የቤተክርስቲያን ነገር በልበ ደንዳናነቱ አልዋጥለት ያለውም እንዲሁ፡፡ ልጅ ነውና ይመከራል፣ ይዘከራል፣ የሚጠቅመው ይነገረዋል፣ እኔ ነኝ የማውቀው ካለ መንገዱ ሰፊ ነው መጓዝ ይችላል፡፡

  የተሃድሶአውያን መሠረታዊ ችግር ሁለት ነው፥ በእኔ እምነት፥

  አንደኛ
  ግብዝነት፥ እንደ ፈሪሳዊ፡፡ በእውቀት የደረጀን፣ ለወንጌል አገልግሎት ቀሚስ የታጠቅን፣ የበሰበሰ የአስተዳደር ሥርዓትን መቀየር የምንችል ምሩቃን፣ ልሂቃን ብሎ መኮፈስ፡፡ በመሠረቱ ክርስትና በእውቀት ሳይሆን በልጅነት፣ በጸጋ፣ በሰማዕትነት፣በየዋህነት የሚወረስ መንግሥት ነው፡፡ ሊቀ ሐዋርያ ቅዳስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ የቁልቁሊት ተሰቅሎ ያገኘው መንግሥት ነው፣ የሐዋርያት መሪ የነበረውም በትምህርቱም ልሂቅነት አይደለም፡፡ አስተውሉ!!!

  ሁለተኛ፥
  ከፍጹማዊው ሕግ ይልቅ ለሰው ሠራሹ ሕግ ቅሩብ መሆናቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ከላይ የተገለጹት በሕግ ውስጥ በስውር የተቀመጡ ኢክርስቲያናዊ አሠራሮችን በመተግበር ለመፈጸም መሞከር፡፡ ተኩላ በበግ ለምድ እንዲሉ በሕግ ማዕቀፍ ስም በሰው ልጆች ላይ የተቀመጡትን አሳሪ ሕግጋትን ከዲያብሎሳዊ መንገድ ከሚከለክሉ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ይልቅ ሙጭጭ ብሎ መያዝ፡፡ አካሄዱ ሥጋዊነትን ያጋለጥ እንደሆነ እንጂ መንፈሳዊነትን የሚያውጅ አንዳች ኃይል የለውም፡፡

  ReplyDelete
 8. Kale hiwot yasemalin memher, Endih kaltenagernew aschegari new

  ReplyDelete
 9. "የመርከቡ ወለል በተሠራበት ቁስ አለመስማማት ይቻላል፤ የመርከቡን ወለል መነቃቀል መጀመር ግን ትርፉ ተያይዞ መስጠም ነው፡፡"

  እንደ የክርስትና እምነት ተከታይነቴ ያውም እንደ ኦርቶዶክስነቴ እጅግ አድርጌ ሃሳብህን እደግፈዋለሁ……ቃለ ህይወት ያሰማልን ዳኒ መልካም እይታ ነው፡፡

  Harry from Addis

  ReplyDelete
 10. ተሐድሶን-የማጋለጥ እንቅስቃሴ ለማጠናከር የተጀመረውን ትግል ድርሻችንን አንወጣ

  ReplyDelete
 11. ባላየሁበት አቅጣጫ አሳይተህኛልና እግዚአብሄር የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 12. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዳኒ የተልዕኮው አካል ካልሆነ በቀር አሁን ቤተክርስቲያንን እናድሳለን የሚሉትን አገልጋዮች የውስጥ ስውር አላማ በግልጥ የሚያሳይ ወሳኝ መልእክት ነው፡፡ እውነት እኮ ነው የመናፍቃንን እንቅስቃሴ አይታችሁ ከሆነ ስለእምነቱ በደንብ ከሚያውቁ፤ መጽሐፍትን በደንብ ከተረዱ ሰዎች ጋር በግልጥ መነጋገር አይፈልጉም ድንገት ሳያውቁት ከገጠማቸው እንኳን መውጫ መንገድ ወደ ማፈላለጉ ነው የሚሄዱት የሚታመን የሚያምኑት ምንም ነገር የላቸውምና፡፡ የዘሬዎቹም አገልጋዮች ተብዬዎች በማስመሰል፤ ውስጥ ውስጡን በመበረዝ፤በተራ ነቀፋ ይታወቃሉ ፡፡ ስለሚያስተምሩት ትምህርት ስተት ሲነቀፉ ስለገንዘብ ያነሳሉ/ጠቅላይ ምንስቴሩ እንዳሉት ግብጾች የአባይ ውሃን እንደ አደንዛዥ እጽ ይጠቀሙበታል/ በጥቅም እንደተጣሉ አስመስለው ህዝቡን ያደነዝዙበታል፤ስለትህትና እራስን ዝቅ ስለማድረግ ሲታሙ እነርሱ የወደቁበትን ዝና እና ክብር ህዝቡ እኛን ስለተቀበለ ቀንተው ነው ይላሉ ሁሌም የእውነት እና የግልጽነት ጠላት እንደሆኑ እንዳደናገሩ ከስር ከስር ግን በስውር እያወደሙ፤ የኖረ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ማፍረስ ሀዝቡን ታሪክ አልባ ቅርስ አልባ መድረግ ተግተው የሚሰሩበት ቋሚ ስራቸው ሆኖ ቀጥለዋል፡፡ ልብ በሉ ይህ በምንም መልኩ ክርስትና ሊሆን አይችልም፡፡ ልንነቃባቸው ሳያውቁ እየተከተሉ የሚያበረታቱ ቤተሰቦቻችንን ወንድም እህቶቻችንን ልነመክር የገባል ይህ ጽሑፍ በስፋት በማሰራጨትም የበኩልዎን ሀገራዊ መንፈሳዊ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል;;

  ReplyDelete
 13. Egziabhir Amlak Bitekrsityanachin yitebkiln.

  Zegi wust yetekatelewu ye'Giyorgis betekirstiyan hulim yikochegnal.

  ReplyDelete
 14. እውነት ብለሃል ዲ/ዳንኤል ፡፡ ለተሃድሶ አራማጆች የምትቆፍሩት ጉድጓድ ማን እንደሚገባበት አታውቁምና አታርቁት አደራ!!!

  ReplyDelete
 15. ለኔ ተዋህዶ ሀይማኖት በቻ ሳትሄን መለያችንም(identity) ናት፡፡ተዋህዶን አጣን ማለት ማንነታችንን አጣን ማላት፡፡ሰለሆነም በክርስቶስ ደም የተመሰረተችውን ሃይማኖት ልናጠብ ይገባናለን፡፡

  ReplyDelete
 16. ዲ. ዳንዔል እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ ቃለህይወት ያሰማልን ! ብዙሃኑ አስተየየት ሰጪ ምንተ ንግበር (እኛስ ምን እናድርግ) እያሉ ነዉ፡፡ ይህ የሀዋሪያትም ጥያቄ ነበር፡፡ እኔ በበኩሌ የምለዉ በገንዘብና በሌላዉ የሚታይ አቅማችን የምንሰራዉ ነገር እንደለ ሆኖ ትልቁ ነገር ጊዜዉን መጠቀም ነዉ፡፡
  1) በጾም በጸሎትና በስግደት ከልብ መትጋት
  2) ስለሐይማኖታችን ማለትም ስለስርዓቷ፤ስለዶግማና ቀኖና፤ የኛን ቤተክርስቲያን ከሌሎች የለያት ምን እንደሆነ መመርመር መጠየቅና ማወቅ
  3) የሚጎድለን ምን እንደሆነ ከሞላ ጎደል ይታወቃልና በንስሓ ህይወት መመላለስ
  4) በኪዳኑ በቅዳሴዉና በስብከተ ወንጌሉ (ማዋቅ አለብኝ ይገበኛል ብሎ) በትግስት ቁጭ ብሎ መማር
  5) ቢቻል በቤተክርስቲያን ካልሆነም በሲዲና በዲቪዲዎች ያም ባይሆን በመጻህፍትና በመሳሰሉት እንደመጨረሻ ምርጫ ደግሞ በኢንትርኔትና በመሳሰሉት የምናገኛቸዉን ስብከቶችና ጽሁፎችን መጠቀም መልካም ነዉ የኛ ድርሻ ይህ ይመስለኛል

  ReplyDelete
 17. to w/medehene
  put your comment in clear words or .... what do you want to say? i cant understand

  ReplyDelete
 18. ይህ ብሎግ የተጀመረበት አንደኛ ዓመት በመጭው መጋቢት ወር በአዲስ አበባ እና በዋሽንግተን ዲሲ ይከበራል፡፡
  Megabit Geba eyetebeken new

  ReplyDelete
 19. kale heyweten yasemalen wendemachen

  ReplyDelete
 20. ዳኒ

  ይህ የንስር አይን እይታህ "ይህ እኮ ልክ አይደለም : ተዋህዶአዊ መልክ ይጎድለዋል ... " እያልኩ የምብሰለሰልበትን ጉዳይ ምክንያት አጉልቶ አሳይቶኛል:: ተባረክ ::

  ReplyDelete
 21. well said Deacon Daniel.

  ReplyDelete
 22. i wish other people who doesn't have access to internet could listen this voice of yours.

  ReplyDelete
 23. Thanks Dn.Daniel.
  An excellent insight to an urgent issue!!!

  ReplyDelete
 24. "የሂንዱይዝምን፣ የኮንፊሺየዝምን፣ የዞራስተሪዝምን እና የሌሎችንም የቀደምት ሰዎች እምነቶችንም እንይ፡፡ ጾም እና ጸሎት፣ ምናኔ እና ተጋድሎ፣ ራስን መግዛት እና ይህንን ዓለም መናቅ፣ ማስተማር እና መማር፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድርግ እና ለሌሎች መሥዋዕት መሆን የእምነቶቹ መሠረታውያን እሴቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡"

  ከላይ የተዘረዘሩት እምነቶች ከክርስትና ወይም ከቅድስና ጋራ ፍፁም አይገናኙም፡፡የሰይጣን አምልኮዎች ስለሆኑ ለክርስትና ምሳሌዎች አድርገን መጠቀም የለብንም፡፡"በቅድስና መንገዳቸው" የሚለው አባባል ለነሱ መጠቀስ የለበትም፡፡ቅድስና የእግዚአብሔር እንጂ የሰይጣን ስላልሆነ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. MAHIBERE KRSTIYAN:- AND NEGER EKO METERGOM YALEBET ENDEYE AGBABU NEW ENJI BETREW KETAYEMA TENEGAGIRO MEDEMAMETIM AYNORM. SILEZIH KETSIHUFU ALAMA ANTSAR ENYEW.

   Delete
 25. እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድማችን ዕድሜ ይስጥልን

  ReplyDelete
 26. Alem from KentuckyMarch 15, 2011 at 7:54 AM

  I have two points for those guys who want to reform the church:

  1. first of all please read about the church history and what happen to Luther's reform movement.( read critically not for sake of reading)
  2. If you really believe that EOTC needs reform why don't you leave the church and form your own org. Just leave us alone and in modern terms respect our right to believe in " old teachings"

  ReplyDelete
 27. Protesnats are the one work in darkness to destroy our church. I used to take (partcipate) courses given by pro-Proestant groups(who are traind and funded by Protestant). The used to tell us how the ምዕራቡ ዓለም ክርስትና is great. Now I am living there, I have seen by my eyes how Protesnats (pro-Proestant ) are lied. They have the intention of deceiving in our people.

  However, who takes drug? who abuse alcohol? who is atheist? Are not this the fruits Protestant teaching? Why they not clean that? Why they have came in to our church to deceive the true beleivers?

  ReplyDelete
 28. ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ ቃለህይወት ያሰማልን ! የውስጤን ብሶት ነው የነገርከኝ። ይህችን ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ለመጠበቅ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ። ዲ/ን ዳንኤል ከተቻለ የዚህ ብሎግ 1 አመት ሲዘከር በዚህ ጉዳይ ላይ ብንወያይ በጣም ደስ ይለኛል አንተ ያሰብከውን መረሃ ግብር ካልበጠበጠ።

  ReplyDelete
 29. በማነጻጸር የሚገለጡ ነገሮች ጥንቃቄ ቢደረግባቸው።ምክንያቱም ጡመራህን የሚያነበውን ኦረቶዶክሳዊ አማኝ እንዳያደናግር(እዳያጠራጥር)

  ReplyDelete
 30. አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልን
  የቀናውንም መንፈስ በውስጣችን አድስ። መዝ 50፤10
  ስለ ሀይማኖታችን በጸሎት እንበርታ
  ፍቅርተ ማርያም
  ከሳርቤት

  ReplyDelete
 31. ፍቅርተ ማርያምMarch 15, 2011 at 10:20 AM

  አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልን
  የቀናውንም መንፈስ በውስጣችን አድስ። መዝ 50፤10
  ስለ አንዲቷ ሀይማኖታችን በጸሎት እንበርታ
  ፍቅርተ ማርያም
  ከሳርቤት

  ReplyDelete
 32. መርከቤ ንጉሴ /ከአዲስ አበባ/March 15, 2011 at 11:01 AM

  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ።አሜን!!

  እነዚህ ቤተ-ክርስቲያንን እናድሳለን ብለው የተነሱት ሰዎች የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ከመሆናቸውም በላይ ለርካሽ ጥቅም የተገዙና ሕሊናቸውን የሸጡ ናቸው። ያውም በቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ሳይታወቅ ሥርዓትና ደንቡን ባልጠበቀ ዝማሬ፣ ስብከት፣ ፅሑፍና የመሳሰሉትን እግዝአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን ጥቅምን ለማግበስበስ በድፍረት የሚነግዱ። ነገዱ አተረፉ ይህም አልበቃ ብሏቸው እነሱም መናፍቅ ሆነው ከመናፍቃን ጋር በማይረባና በጊዜያዊ ጥቅም ተሳስረው በተለያየ ሁኔታ ሲበጠብጡን ኖሩ። በእርግጥ እያጠቁን ያሉት ከፍተኛ እምነት ተጥሎባቸው ወሳኝ ቦታ ላይ የተቀመጡና ለርካሽ ጥቅም ብለው ሕሊናቸውን የሸጡ ሰዎች ናቸው። በአጠቃላይ ከአስመሳይና ግዴለሽ አገልጋዮች ባሻገር የቁጥጥሩ መላላትና ርምጃ አለመኖር መናፍቃኑ በቤታችን እንደልባቸው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የሚመለከተው ክፍል ችላ ቢላቸውም እንደተነቃባቸው እያወቁ ለምን ይሆን ቤታችንን የሙጥኝ ማለታቸው? የሚመለከተው ክፍል ዝም ካለን ምዕመናኑ ምንም አያመጣም ብለው አስበውት ይሆን? ነው ከገዛቸው ድርጅት ጋር የብዙ አመታት የኮንተራት ውል አላቸው? ስማቸው የተጠቀሱት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም በበአላትና በሐይማኖታችን ያልተፈቀዱ ነገሮችን ከማከናወን አልፈው እኮ የሚያስገባቸው ጠፋ እንጂ መቋሚያ፣ፀናፅን፣ ከበሮአችንንና ሌላም የሰረቁን እንሶ በገና፣ማሲንቆና የመሳሰለትን ለቤተ-ክርስቲያናችን፣ ለእምነታችን፣ መሳጭና ውበት የሆኑትን አስጥለው እንደነሱ ጨፋሪ ካደረጉን በኃላ ለመውረስ ፒያኖና ኦርጋን ይዘን ቤተ ክርስቲያን ካልገባን የሚሉ አሉ። ለዚህ ሁኔታ መጠናከር ደግሞ በእደማርያም እጅጉ ረታ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። http://www.ethiopianorthodox.org/ ይህ ድረ-ገፅ በእደማርያም እጅጉ ረታ የሚያዘጋጁት ነው። እዚህ ድረ-ገፅ ላይ የሳምንቱ ምርጥ መዝሙር እየተባለ የሚደመጠው በኦርጋን በኚሁ ሰው የተቀናበረ የቤታችን መዝሙር ነው። አብዛኛው ፅሑፋቸውና ሌላው ነገር ስለ ኦርጋን ነው። በተለያየ አድራሻ ከኚህ ሰው ጋር ቅሬታና ጥያቄዬን በማቅረብ ለመፃፃፍ ሞክሬያለሁ። ነገር ግን የሚመልሱልኝ መልስ በቂ ያልሆነና የማይገባኝ ነው። ዳኒ እባክህ የምትመልስልኝ ከሆነ ይህ ድረ-ገፅ እኛን ኦርቶዶክሳውያንን የወከለ ነው? በእደማርያም እጅጉ ረታ የሚባሉትስ ሰው ማናቸው?

  እግዝአብሔር አምላክ አስተዋይ ሕሊና ይስጠን።አሜን!!
  መርከቤ ንጉሴ /ከአዲስ አበባ/

  ReplyDelete
 33. to Anonymous
  endilemalet felige new
  leteadiso aramajoch ተዋህዶን ለማጥፋት የምታጠምዱት ወጥመድ ለራሳችሁ የመጥፊያ ወጥመድ መሆኑን እወቁ!!አይጥ ለሞቷ .....

  ReplyDelete
 34. የመረከቡ ወለል በተሰራበት ቁስ አለመስማማት ይቻላል መርከቡን ግን መነቃቀል ተያይዞ መስጠም ነው ፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዕድሜህን ያርዝው

  ReplyDelete
 35. Dn Dani Kale hiwot yasemalin!!!

  Ante W/medhin yetebalk asteyayet sechi min lemalet felegeh newu????? ለተሃድሶ አራማጆች የምትቆፍሩት ጉድጓድ ማን እንደሚገባበት አታውቁምና አታርቁት አደራ!!!

  ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር yemisera hulu endigebabet reko yikofer enji min malet newu manim bihon yihen kaderege Kemimen anseto eske patriarich balewu yebetecherstiyan yeminetu teketay wust betecherstiyanen lematfat lemades ketenesa yigba lemin manim ayhonem Ariyosim eko kedegagochu abatoch wegen nebere bohala befelsifenawu newu yetewegezewu selezih Riko yikofer simeker sinegerewu yalsema lemin manem ayhonim aykereletim!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 36. እግዚያብሔር የልፋትህን ዋጋ ይስጥህ። ጀሮ ያለው ይስማ ነው። ምንም ይሁን ምን ከእኛ ጋ ያለው እግዚአብሔር ነው። ቤቱን ሲፈነጩበት ዝም አይልም። ውስጠ ማንነታቸውን ተንትኖ ባደባባይ እርቃናቸውን የሚያስቀረውን ያመጣል። የክርስትና ታሪክ ይህን ይነግረናል። ሁሉ ነገር ካለ እኔ ላሳር እያለ እንደ ፈረስ ከቦታ ቦታ እየዘለለ ያን ምስኪን ወገኔን ለማወናበድ የተነሳው ተረፈ ይሁዳ የትም አይደርስ። ክርስትና በተግባር የምትታይ ሕይወት እንጂ ያፍ ሽንገላ አይደለችም። እርግጠኛ ነኝ ማንም አማኝ ነኝ ባይና በእየ ሰፈሩ የሰውን መንፈስ እየረበሸ ያሉ ቡድኖች ይህን ጽሑፍ እስከ አስተያየቶቹ ያነቧቸዋል። ስለዚህ እባካችሁ ለጽድቅ አድርጉት። ምን አልባት ገንዘብ እንደሆን ያሰከራችሁ እሱን ለማግኘት በጣም ብዙ ክፍት የስራ ቦታ አለ። ከእግዚያብሔር ሳትጣሉ ሕዝቡንም ሳትረብሹ ኢትዮጵያ ሊያሰራ የሚችል ብዙ የስራ ዘርፍ አላት። ከእናንተ የሚጠበቀው ወደ ስራው ለመግባት የሚያስችላችሁን እውቀት መገብየት ነው። ነገር ግን የሌሎችን ድብቅ አላማ ለማራመድ ሆን ብላችሁ እየሰራችሁት ከሆነ ይህ የተበላ እቁብ ነው። መረጃ በሰከንድ በተለያዩ ቦታዎች የሚዳረስበት 21ኛው ክፍለዘመን መሆናችንን አትዘንጉ። ምን አላባት ይህን በስለላ መልክ ውስጥ ለውስጥ እንሰራዋለን ብላችሁ ብትነሱ በተጠናከረ መልኩ የተመዘገበ ማንነታችሁ እንዲጋለጥ ነው የሚያደርጋችሁ። እውነት እውነት ናት። እውነትን ማንም ሸፍኗት አያውቅም። ምን አልባት ሊያዘገያት ይችል ይሆናል። ስለዚህ ምንም ጊዜ ሳታባክኑ ማንነታችሁን ለዩ። ሚናችሁን ስትለዩ ግን መንፈራገጡ የበለጠ መላላጥ እንዳያመጣ ተተንቀቁ። እኛ ነን የቤተክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪዎች ብላችሁ ባደባባይ ብትወጡ የሌባ አይነ ደረቅ ልብ ያደርቅ የሚለው ነው የሚሆንባችሁ። ተዋርዳችሁ ወደ ነበራችሁበት ትመለሳላችሁ።
  ሌላው ከዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ሳትውቁት የገባችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ተሎ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ። ጊዜውም አብይ ፆም ስለሆነ ንሳሃ ግቡበት።
  በጋራ ሆነን ባላጋራችን ዲያቢሎስን ድል እናድርግ።
  እግዚአብሔር ልዩ ሶስትነቱን በማመን እሰከ መጨረሻይቱ ህቅታ በቤቱ ለመኖር ያብቃን።

  ReplyDelete
 37. I have questions for the religious fathers who allowed these people "to serve in/for the church" and also for the entire church member.
  1. Why they allowed to violate church dogma/Kenona?
  2. Don't they understand that this "reformist" are manipulating their politeness(yilugneta)?
  3. How do we know even the religious leaders are not Tehadiso- because sometimes they ignore tangible facts about anti-religious attitudes and actions?
  Why peoples who has been prevented from teaching in the church due to their evil inclination permitted again?
  5. Some even afraid that there is financial marriage between church detractors and "church leaders. True...? God knows
  But God will help the true children of church to be the winner. But lets pray.

  ReplyDelete
 38. ቃለ ሕይወት ያሰማልን! የሰማነውን በልቡናችን ያሳድርልንና ይህንን የዲያቢሎስ ውጊያ ከጾም፣ ከጸሎት ባሻገር የቤተ ክርስትያኗ ልጆች ሁሉ በያለንበት ልንታገለው የሚገባ ጉዳይ ነው። ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የሚጽፋቸውን ነገሮች አንብቦ ከንፈር ከመምጠጥ ወይም "በርታ" እያሉ ከማበረታታት ተቆጥበን ሁላችንም የየድርሻችንን ልንሠራ ይገባናል። እሱ የድረሱልን ጥሪ እያሰማ ነው። ...የኛ መስለው ነገር ግን የኛ ያልሆኑትን "የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች" እየተከታተልን ለምእመኑ ማጋለጥ፣ አስፈላጊም ሲሆን ሕጋዊ እርምጃ ማስወሰድ ይጠበቅብናል። አለበለዚያ ሰሞኑን በግብጥ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ላይ የተፈጸመው ሕንፃ ቤተ ክርስትያንን የማፍረስ ተግባር ወደኛ የማይመጣበት ምክንያት አይታየኝም። ይህንን ይመልከቱ። http://www.youtube.com/watch?v=O4vqwk0Vb5g&feature=player_embedded
  ጎበዝ! አናንቀላፋ!

  ReplyDelete
 39. ማንበባቸው ስለማይቀር ለእነዚህ ሰዎች አንድ ነገር ልጠቁም፡-አለማዊ ትምህርት ይማሩ። ያለማዊ ትምህርትን ምንነት ሲያዩ ወደ ልቦናቸው ይመለሳሉ። ያኔ የእምነቷን ምጡቅነትና እጝዚአብሔርን ሃያልነት ያውቁታል። አሁን እዚህ ጣጣ ውስጥ የገቡበት ምክንያት የሚመስለኝ ያገኙት መንፈሳዊ እውቀት እንጅ መንፈሳዊነትን አይደለም። ለዚህም ባገኙት መንፈሳዊ እውቀት ገንዘብ መሰብሰብ ላይ እንዲጠመዱ አደረጋቸው። ይህ ደግሞ ይሁዳ የሰራውን ሊያስደግማቸው ይችላል። ጌታን እንደሸጠ እነሱም ቤተክርስቲያኒቷን ለመሸጥ መነሳት። ገንዘብ የማያደርገው የለም። የሐጢያት ምንጭ ስለሆነ አይነ ልቦናን ሊዘጋ ይችላል። እናም ጌታን የሸጠ የይሁዳ አይምሮ ዛሬም አለ። ስለዚህ መዳህኒቱ እነሱም እንዲተርፉ አለማዊ ትምህርት ይማሩ። አይኦንም ብለው መንፈሳዊ ትምህርትን ወደ አለማዊ ጎትተን እናመጣለን ቢሉ-ወዮላቸው ነው የምለው። ያ የጓዳ ሚስጥራቸው ይወጣል። እሰከ መቸስ ከመጋረጃ በስተጀርባ የበሉትን አደባባይ ላይ ያገሱብናል።
  መንፈሳዊ እውቀት ጥበብን ለማግኛ ካልሆነ ምን ይጠቅማል።

  እንድ ቦታ ያነበብኩትን ግጥም እዚህ ብለጥፈውስ። አደራ ሰረቅህ እንዳትሉኝ። እሰከ አድራሻው አስቀምጣለሁ። ብዙ ነገሮችን ስለሚነካካና ከርዕሱ ጋ ይሄዳል ብየ ስለ አሰብሁ ነው፡-

  እምነትን ፈራሁት

  እምነቱን አምኜ ቃልኪዳን አሰርኩኝ፣

  እሱን ተከትዬ ልመንን ወሰንኩኝ።

  ለዜማዉ ታምኜ እኔ ስከተለዉ ፣

  የሚሞት ለእዉነት የሚኖር ለእሴት እያልኩ ሳጀግነዉ፣

  እጥፍጥፍ ብሎ ሌላ ዜማ ይዟል፣

  ያላስተማረኝን አጉል ካባ ለበሷል።

  አስመዝዞኝ ሸበል ከንቱ ነዉ ያለዉን፣

  ሲልስ አገኘሁት መርገምት ያረገዉን።

  እምነትና ምግባር ሲለካ ሲቀመር ፣

  ስሙን ለብሷል ብዬ ልቤ ታምኖ ነበር፣

  ምግባሩን ስለካዉ ደጋግሞ ሲሰበር።

  ለካስ እሱ ኖሯል ተስላል የጎደለዉ ለወገን የማይኖር ፣

  መንፈሱን ለሃሰት ለቁስ የሚገብር።

  ማተቡ ምግባሩን ሊገዛዉ ካልቻለ፣

  የልቡስ ማህቶት መቼ በእምነት ተዋለ?

  ከእምነቱ ቀጥኖ ባህሪዉ ከሰለለ፣

  ማተብ ምን ሊሰራ ፍቅር ካላዋለ?

  እምነት ምን ሊጠቅም ባህሪንስ ካልሳለ?

  ሰዉ እየተከተልኩ ልቤን ባዶ አረኩት፣

  እራሴ ጠፍቼ እምነትን ፈራሁት።

  በጠስኩት ማተቤን ምን ሊፈይድ ብዬ ፣

  እምነቱን አይቼ ምግባር የታል ቡዬ?

  --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

  ሸንቁጥ አየለ ፤ መጋቢት/2003 ዓም አአ

  ማስታወሻነት፤ እየመሩ፣ እያስተማሩ፣ተምሳሌት ነን እያሉ ያልሆኑትን ለሚሰብኩ፣ የሚናገሩትን ባለመሆናቸዉ ለብዙዎች የልብ፣የመንፈስ ባዶነትና ስብራት መንስኤ ለሆኑ። ለትዉልድ የሞራል መላሸቅ የሰበብ ቀዳዳን ለሚዘነጥሉ ሁሉ።

  ReplyDelete
 40. dani kalehiywetyasemalin! ‹‹ለተሃድሶ አራማጆች የምትቆፍሩት ጉድጓድ ማን እንደሚገባበት አታውቁምና አታርቁት›› ይህንን ቃላት መረዳት ለቸገራቹ ተዋህዶን ለማጥፋት የምታጠምዱት ወጥመድ ለራሳችሁ የመጥፊያ ወጥመድ መሆኑን እወቁ !! yehasabu melikit endi lemalet tfeligo new

  ReplyDelete
 41. What the so called tehadisos are doing is clearly a TRESPASS. Trespass is a crime. It is well understood that these offenders do not belong to the Holy Mother Church. As the Apostle said 'they were not amongst us'.

  The mere claim that they now and then barking in any way cannot give them the status of being the Family of our Faith. Every body should be aware that they came into our territory illegally, just for looting the laities. As we all know any one has a natural right to legitimate defense against any trespass. The EOTC has a well known legal personality.
  So long as these heretics trespassed the territorial boundary we shall not keep quite. We have to defend ourselves.
  1. To let them go out
  2. To look for judgment in the court for their aggression.
  3. To defend the belief of our Forefathers
  4. To teach those who are deceived by the tehadisos and make them repent.

  Some might take it as provocative act. But in reality the provocateurs are the tehadisos, who are criminals. This people can only take lesson if and only if they are properly charged in front of court. Else they will change their mask and come again for another disturbance, as they are the sons of the night. Therefore, let's interchange informations each other. Those lawyers who are the true family of the church should get together and think how to proceed with it.

  SOON THEY MUST STOP!!!!!!!

  ReplyDelete
 42. Daniel,

  the shape of the article is nice and readable. I cant even a single evidence for all conclusions you made to the whole article except blaming the refromist here and there and now and then.
  this is not really import except the aesthetic value the note.
  It will be worthy to moention your idea to tlerate and appreciate differences

  Okay let assume, all your conclusion are true, why dont you show the other side of the coin. that mean what the extremist doing against the reformist. As you have the right to be exteremist, the next person even your neibour to be moderate or reformist.

  try to make your article well balanced.

  ReplyDelete
 43. who is going to approve? that is so funny/

  ReplyDelete
 44. አውሮፓውያን በክርስትና ላይ የሠሩት የማይካስ ወንጀል አምላክ የለሽ ትውልድ እንጂ ጻድቃንን አላፈራላቸውም!

  ReplyDelete
 45. ቤተ ክርስቲያንን የሲኦል ጀጆች አያናውጻትም ፡፡

  ReplyDelete
 46. ዲ/ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ
  አውሮፓውያን በክርስትና ላይ የሠሩት የማይካስ ወንጀል አምላክ የለሽ ትውልድ እንጂ ጻድቃንን አላፈራላቸውም!
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዕድሜህን ያርዝው
  Hailemeskel ZMaputo

  ReplyDelete
 47. Yih Tsehufina asteyayetochu Segawineti /tilacha,gichitini na wokesa (blame)/ lay yemiyatekuru inji minime menfesawinet(fikir, mastemare, memeles) yelelachew nachew

  ReplyDelete
 48. A very nice comparative article for those who want to run after the truth,kale hiwot yasemah!our ears are obliged to hear many hard,satanic and inethical deeds by those groups the so called tehadeso ,simply speaking their acts against the church is an indication of the end of an era and they are path preparers of the blasphemic and millitant beast that is cited in the bible.If öne compare their deeds with this beast it is one and the same,they open their blasphemic mouths against our lord,holy savior,almighty God Jesus Christe,his tabernacle,his saints and his church as he will do when he casts out of sea.Revelation 13:5 so what is the difference between the beast and tehadeso (reformists) ?

  ReplyDelete
 49. thnx,Dani but we need more,we are in need of blessing and facts.May God send his holy sprite to us and them....pray for them.

  ReplyDelete
 50. i am not sure who these people are but please let us not judge without reason and let us see it carefully god will reveal everything.

  ReplyDelete
 51. Habtamu Nigussie from AbnetJuly 16, 2011 at 8:26 PM

  Dn.Daniel please try more for orthodox church.GOD helps you forever.

  ReplyDelete
 52. God bless you Diakon Daniel k.

  ReplyDelete
 53. i solely agree with this

  ReplyDelete
 54. ያማል በእውነት ያማል ለአይምሮዬ ትልቅ ዱላ………ውስጤ አዘነ…..ለምን በእምነታችን እንደሚመጡ ግርም አለኝ……ቆይ ግን ምን አለ ሚናቸውን ቢለዩ…….እውነት ምናለበት እግዚአብሔርን ቢፈሩ…..

  ReplyDelete
 55. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማናወፅ የሚጥሩትን ልቦና ይስጣቸው፡፡

  ReplyDelete
 56. እግዚአብሔር ይስጥልን ዳኒ! እኔ የማስበው እነዚህ ቤተክርስቲያንን ለማፈራረስ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ምንአልባት በራሳቸው እይታ ጥሩ ነገር እየሰሩ መስሏቸው ከሆነ እስቲ ቆም ብለው ያስቡ ፡፡ በእውነት እየሰራሁት ያለው ትክክል ነው ወይ ብለው ራሳቸውን ይጠይቁ ምንአልባት እነደ ጳውሎስ በቀናኢነት ተነስተው ከሆነ እስቲ ይህን የተጻፈውን የዳንኤልን ጽሁፍ በማስተዋል ያንብቡ ፡፡ እግዚአብሔር ልቡና ይስጣቸው! ካልሆነ ቤተክርስቲያንን፣ ሀገርን፣ እንዲሁም ማንነትን ለመጠበቅ ማንም ትክክል የሚያስብ ጭንቅላት ያለው ሰው አይምራቸውም ከዚህ በኋላ ለራሳቸው ያስቡ፡፡
  አብነት ከሆሳዕና

  ReplyDelete
 57. ዲ/ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ:!
  እናም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ሀብቶች ላይ የሚሠነዘር ጥፋት ሁሉ በሀገር ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against the mother land) ነው፡፡ የሚመለከተውም የቤተ ክርስቲያኒቱን አማንያን ብቻ ሳይሆን መላውን ኢትዮጵያዊ፣ የሀገሪቱን መንግሥት እና የኢትዮጵያን ወዳጆች ሁሉ ነው፡፡
  እናም ክርስትና ስለላ፣ ሤራ፣ ዝርፊያ፣ ውድመት እና ደባ አይደለምና፤ የክርስትናም መንገድ ቀና እና ግልጥ እንጂ ተንኮል እና ክፋት አይደለምና ይህንን በክርስትና ስም በክርስትና፣ በሰው ዘር ሀብት እና በሀገር ላይ የተቃጣ ወንጀል አንድ ሆነን ልንቃወ መው፣ ልናስቆመውም ይገባል፡፡
  የመርከቡ ወለል በተሠራበት ቁስ አለመስማማት ይቻላል፤ የመርከቡን ወለል መነቃቀል መጀመር ግን ትርፉ ተያይዞ መስጠም ነው፡፡

  ReplyDelete
 58. ዲ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተ ይሁን
  አንድ ሰው ልብስህ (ሰውነትህ) ቆሻሻ አለበት ብሎ ቢነግርህ ፣ ያንን ሰው መልሰህ ትሰድበዋለህ ወይስ ልብስህን(ሰውነትህን) አጥበህ ትነጻለህ፡፡ ወንድሜ በቅንነት ከተመለከትነው የተሃድዎች ጥያቄ ተገቢ እና ሀይማኖታችንን ለማንጻት መልካም አጋጣሚ ይመስለኛል ፡፡ እነርሱ በእናንተ እምነት ውስጥ ስህተት አለበት ካሉ እኛ ስህተታችንን ፈልገን ማረም ነው እንጂ መናፍቅ ብለን መሳደብ ተገቢ አይደለም፡፡ ስህተታችንን ሲነግሩን መልሳችን መናፍቅ ከሆነ፣ ልጆቻችንን ሲነጥቁብን አሁንም መናፍቅ ካልን ነገ ቤተ መቅደሱን ወርሰው ላለመውሰዳቸው ምን ማረጋገጫ አለን? ወንድሞቼ እነርሱን መሳደብ ትተን እራሳችንን እንመልከት (ልብሳችንን እንጠብ)

  ReplyDelete
 59. ‹‹ለተሃድሶ አራማጆች የምትቆፍሩት ጉድጓድ ማን እንደሚገባበት አታውቁምና አታርቁት››
  ያገሬ ሰው ፉከራና ቀረርቶ ይወዳል፡፡ እስከዛሬ ወደ ጉድጋዱ እየገባ ያለው ማን ይመስልሃል? ፕሮቴስታንት ወይስ ኦርቶዶክስ?
  ሞኝ አማራ

  ReplyDelete
 60. ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀሪቱ አንዷ እና ዋነኛዋ መገለጫ ናት፡፡ምንም ጥያቄ የለውም!!!

  ReplyDelete
 61. ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀሪቱ አንዷ እና ዋነኛዋ መገለጫ ናት፡፡

  ReplyDelete