Thursday, March 10, 2011

የጥፋት ሃይማኖት

ላሰባችሁ ሁሉ
ላለፈው አንድ ሳምንት መጥፋቴ ብዙ ወዳጆቼን እንዳሳሰባቸው ከኢሜይላቸው እና ከስልካቸው ተረድቻለሁ፡፡ ስለተጨነቃችሁልኝ እግዜር ይስጥልኝ፡፡ የጠፋሁት ታምሜ ለአንድ ሳምንት ተኝቼ ስለነበረ ነው፡፡ በእናንተ ጸሎት ይሄው ደኅና ሆኛለሁ፡፡ እድሜ ይስጠን አብረን እንቀጥላለን፡፡

ሃይማኖት በጠባዩ ከፍ ያለ የሞራል ብቃትን የሚያጠይቅ ነው፡፡ በእምነቶች ታሪክ ውስጥ «ብቃት» የሚለው ቃል በተደጋጋሚ የሚነሣ እና ምእመናኑ ሁሉ የሚመኙት ነገር ነው፡፡ እነዚህ ለብቃት የደረሱ የየእምነቱ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን ከማሸነፍ አልፈው ዓለምን በፍቅር እና በደግነት ያሸነፉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም ከሰዎችም በላይ ለእንስሳቱ እንኳን ሳይቀር በመራራት ለምነዋል፣ የደግነት ሥራ ሠርተዋል፤ ከዚያም አልፎ መከራ ተቀብለዋል፡፡
ሃይማኖት ጸሎትን፣ አምልኮን፣ ደግ ሥራን እና ትምህርትን መሠረት አድርጎ የሰዎችን አስተሳሰብን እና አመለካከትን መለወጥን የሚያመለክት ኃይል ነው፡፡ በሃይማኖት ምክንያት ተደረጉ የሚባሉ ጦርነቶችን እንኳን ጠለቅ እያልን ስናያቸው ሃይማኖትን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም በፈለጉ አካላት የተደረጉ እንጂ የማይማኖቶችን ድንጋጌ ተከትለው የተደረጉ ሆነው አናገኛቸውም፡፡
አሁን አሁን በዓለማችንም ሆነ በሀገራችን ሃይማኖትን በጥፋት የማካሄድ አዝማሚያዎች እየታዩ እየተከናወኑም ነው፡፡ በመግደል፣ ቤተ አምልኮን በማቃጠል፤ ሴቶችን በመድፈር፣ በግዳጅ በማግባት፣ መብትን በመንሣት፣ በማስጨነቅ እና በሌላው ቤተ እምነት ላይ ወረራ በማካሄድ ለማሳመን መሞከር እየታየ ነው፡፡ 
ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በበሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እና በአካባቢው የነበሩ ክርስቲያኖች እምነታችንን በግድ እንጭናለን በሚሉ ጽንፈኛ «ሙስሊሞች» መታረዳቸው እንኳን ከክርስቲያኖች ከሙስሊም ወገኖች እንኳን ከባድ ተቃውሞ ቀርቦበት ነበር፡፡
ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ ከሕግም፣ ከታሪክም፣ ከዘመንም የማይማሩ ጽንፈኞች የፕሮቴስታንት አብያተ ጸሎትን እያቃጠሉ እስልምናን በግድ መቀበል አለባችሁ ማለት መጀመራቸውን እየሰማን፤ ሰምተንም እያዘንን ነው፡፡  
ይህንን የመሰለው ተግባር ማንም ፈጸመው ማንም፤ በማንም ላይ ተፈጸመ በማን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ፈጽመው ሊቀበሉት እና ዝም ሊሉት የሚገባ ግን አይደለም፡፡
ሰዎች እኛ መልካም ነው ብለን ባመንነው መንገድ እንዲጓዙ መመኘት፣ ለዚህም መትጋት፣ ማስተማር፣ በሞራል እና በበጎ ሥራ ልቆ በመገኘት መማረክ፣ ያኛው ተሳስቷል ብሎ ማሰብ እና በሠለጠነ መልኩ ስሕተት የሚባለውን መግለጥ የቀናዒ ኅሊና ባለቤት መገለጫዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን «ወደድክም ጠላህም የግድ የኔን እምነት ብቻ ትቀበላለህ፣ እምቢ ካልክ ትሞታለህ» በሚል አስተሳሰብ መሥራት ከሰውነት ተራ አውጥቶ ወደ ሰይጣንነት የሚያደርስ የሲኦል መንገድ ነው፡፡
ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከሦስት ነገሮች ሊመነጭ ይችላል፡፡
የመጀመርያው ሃሳብን ለማስረዳት እና ለማሳመን ዐቅም ሲያጥር ነው፡ አንድ ሰው፣ ቡድን፣ ተቋም ወይንም ማኅበረሰብ እርሱ በጎ ነው ብሎ የተቀበለውን አስተሳሰብ፣ አመለካከት ወይንም እምነት አስረድቶ፣ አብራርቶ እና በሚገባ አቅርቦ ማሳመን ሲያቅተው የሰነፍ ዱላውን መሠንዘር ይጀምራል፡፡
ይህ ሁኔታ አመለካከት ወይንም አስተሳሰብ እንኳን ሌላውን ሊያሳምን ይቅርና የያዘውም ሰው በሚገባ እንዳልገባው ያሳያል፡፡ እርሱም ራሱ ጭፍን ስለሆነ ወይንም ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል እልክ እንደ ሚከተለው ያመለክታል፡፡ የሃሳብ ክርክር ከተነሣ ልሸነፍ እችላለሁ፣ ሊያሳምነኝ ይችል ይሆናል ብሎ የሚሰጋ አካል ከሃሳብ ክርክር ይልቅ የመሣርያውን ክርክር ይመርጣል፡፡ ምክንያቱም የመሣርያ ክርከር ከሃሳብ ክርክር ይልቅ ቀላል ነውና፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከውጤቱ ይልቅ ድርጊቱን ብቻ በማየት የሚመጣም ነው፡ በዓለም ላይ ያሉ እምነቶች ሁሉ በአንድ ዓላማ ይስማማሉ፡፡ ሰውን ከክፉው አውጥተው ወደ በጎው ዓለም መውሰድ ዓላማቸው ነው፡፡ ይህም ማለት ዋና አጀንዳቸው ሰው ነው ማለት ነው፡፡ ታድያ ልታሳምነው እና ልታድነው የሚገባውን ሰው እንዴት ገድለህ ታሳምነዋለህ? ከገደሉ በኋላ ማሳመንስ አለ?
ይህ ዓይነቱ ሰይጣናዊ ሥራ የሚሠራው የመሰላቸውን ነገር ማድረጋቸውን እንጂ የሚያመጡትን ውጤት ምንነት በማያስቡ ጨለምተኞች ነው፡፡ ጨለምተኞች ለራሳቸው ጀብዱ እንጂ ለሚያስከትሉት ውጤት አይጨነቁም፡፡ የፈለጉትን እና መልካም መስሎ የታያቸውን ማድረጋቸውን እንጂ በድርጊታቸው ምን ለውጥ እንዳመጡ ማሰብ አይፈልጉምም፤ አይችሉምም፡፡
ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ከእምነት ውስጥ «ሰውነት» ሲጎድል የሚከሰት ነው፡፡ ማንኛውም አማኝ አማኝ ከመሆኑ በፊት ሰው ነበር፡፡ ለማመን የበቃውም ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ግኡዝ ወይንም እንስሳ ቢሆን ኖሮ አያምንም ነበር፡፡ አማኝ መሆኑ ሰው በመሆኑ ሊኖሩት የሚገቡትን በጎ ነገሮች ይበልጥ ያጠናክራል፤ ሌሎች በጎ ነገሮችንም ይጨም ርባቸዋል፤ ሰው በመሆኑ የሚከሰትበትን ድካምም በእምነት ያሸንፈዋል፡፡
አማኝነት ሰው መሆንን ካጠፋ እና አውሬነትን ከተካ ግን ይህ አማኝነት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም አራዊት ሃይማኖት የላቸውም፤ ሊኖራቸውም አይችልምና፡፡ ለምሳሌ ለሰዎች ማዘን ሰው የመሆን ጠባይ ነው፡፡ ለዚህም ነው በሁሉም ዓይነት ማኅበረሰቦች ውስጥ ሰዎች ሲሞቱ በልዩ ሁኔታ የሚታዘንላቸው፡፡ ይህንን ጠባይ እምነት ያጠነክረዋል፤ በሚገባ ጎልቶ ወጥቶ ለምግባር እንዲበቃ ያደርገዋል እንጂ ሊያጠፋው አይገባም፡፡
ሰውን በመግደል፣ የሰውን ቤተ እምነት በማቃጠል፣ የሰውን ክብር በመንካት፣ መብቱን በመገደብ፣ በእምነቱ ምክንያት አድልዎ በማድረግ፣ በማስጨነቅ እና አካላዊ ጉዳት በማድረስ ለማሳመን ወይንም ለማጥፋት መጣር በምንም መልኩ የአማኝ ሰው መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ እምነት ሰውነትን አይደፈጥጥምና፡፡
አሁን አሁን እምነታቸው ሰውነታቸውን ያጠፋባቸው፤ በእምነት ኃይል ከሰውነት ወደ መልአክነት ይሸጋገራሉ ሲባሉ ጭራሽ ወደ አውሬነት የወረዱ አካላትን እያየን ነው፡፡ የአውሬን ሥራ ለመሥራት እምነት ምን ያደርጋል) እምነትኮ አውሬነትን አሸንፎ፣ ሰውነትን አልዕሎ መልአክነትን ገንዘብ ለማድረግ ነው፡፡
ሰውን በእምነቱ ምክንያት መግደል፤ ገንዘቡን መስረቅ፣ ሰውን በእምነቱ ምክንያት መጨቆን፤ ሴትን በእምነቷ ምክንያት መድፈር፤ ድኻን በእምነቱ ምክንያት አለ መርዳት፣ የሰውን ቤት በእምነቱ ምክንያት ማቃጠል እንዴት ሃይማኖት ሊሆን ይችላል? «መግደል፣ መስረቅ፣ መድፈር፣ አድልዎ፣ ማቃጠል» እነዚህን ድል መንሣት የተሣነው እምነት እንዴት እምነት ይሆናል?
ይህ ሰይጣናዊ ተግባር በማንም ተፈጸመ በማን፣ በማንም ላይ ተፈጸመ በማንም ላይ በሁሉም የሰው ዘር ሊወገዝ የሚገባው ድርጊት ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰውነትም የወረደ ድርጊት ስለሆነ፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርጊት ሰዎችን አይወክልም፣ አማኞችንማ ጭራሽ አይመለከትም፡፡ ይህ ዓይነቱን ሰይጣናዊ ሥራ እምነት አለኝ የሚል ሁሉ ሊያወግዘው፣ ሊጸየፈው እና ሊያነውረው የሚገባ ነው፡፡
ትናንት በኦርቶዶክሳውያን ላይ፣ ዛሬ ደግሞ በፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ላይ ተፈጸመ፡፡ ነገ በሌሎች ላይ ለሦስተኛ ጊዜ እስኪፈጸም መጠበቅ የለብንም፡፡ በኔ አልተፈጸመም፣ እኔንም አይመለከትም ልንልም አንችልም፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርጊት በአንድ እምነት ላይ የሚፈጸም ሳይሆን «በሰውነት» ሰው በመሆን ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ይህንን የፈጸሙት ወገኖች እንኳን ይህንኑ አስተሳሰባቸውን በአስተሳሰብ ልዕልና እንዲለውጡ እንጂ በገጀራ እንዲለውጡ ማናችንም አንፈልግም፡፡
             የድኅነት እንጂ የጥፋት ሃይማኖት ሊኖር አይችልምና፡፡

ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት
ምን አገናኛቸው?
ይቀጥላል

64 comments:

 1. menew betam tefahe eko danye
  yante woge endet endemenafkege tawkaleh

  ReplyDelete
 2. dani
  kalehiwot yasemalin yageliglot zemenihin yebarkilen.

  ReplyDelete
 3. በእርግጥም አማኝ እድዚህ አያደርግም
  የያዘውትን ሲጠራጠሩ የሌሎችን መበዝበሩ ይቁም,
  ከቻሉ እራሳቸውን ያጠንክሩ እንጂ ሌሎችን መንካት የቁሙ, መዕሀፋቸውንም ያንብቡት ,እነሱ የሚሉት ሌላ እሱ የሚለው ሌላ, መመስከር ካቃታቸው ዝመ ይበሉ ሌሎችን መሳደብ መግደል ምን ባይ ነው.............

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር አምላክ እንኪን ምሕረቱን አደረገልህ አሜን፡፡ በጣም ስትጠፋ ዝም ስትል አንዱ ነገር እንዳለ ያስታውቃል፡፡ ዋናው ምሕረት ነው፡፡ ይህንን ጥሩ የሆነ ወግ ስላቀረብክልን እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ ምክንያቱም ዝም የሚባል ነገር አይደለምና እና ነው፡፡ ነግ በእኔ ነውና ሰው እኮ ሰው ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን ያንተን ጡመራ በጉጉት እየጠበኩ ነበር
  በትትክልም እንዲህአይነት ጸያፍ የሆነ ሥራ በሀይማኖት ሽፋን ማካሄድ ሐይማኖተኞችን ወይም የእምነቱን ተከታዮች መናቅና ለሀይማኖቱ ክብር አለመስጠት ነው
  ስለዚህ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሊቃወመው የሚገባ ነገር ነው በተለይም የእምነቱ ተከታይ የሆናችሁ ያገሬሰዋች በእምነታችሁ ላይ የተቃጣ እምነታችሁን የማጉደፍ ስራ ነቅታችሁ ልትቃወሙተ ይገባል እላለሁ

  ReplyDelete
 6. Egziabhere enkuwan meheretune lakelehe.

  leakrariwoch fetari lebona yesetachew

  KHY

  ReplyDelete
 7. Danye wendeme Egziabhere cheriso yimareln!!!!!!!!!!!!!! Ayzoh!etselyalehu

  ReplyDelete
 8.    ማንኛውም አማኝ አማኝ ከመሆኑ በፊት ሰው ነበር፡፡ ለማመን የበቃውም ሰው በመሆኑ ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. የእግዚአብሔር መጎበኘት በዘመንህ ሁሉ ይሁንልህ፥ እንደ ምን ሰነበትክ?

  ሁለት ጉዳዮችን በማንሳት አሳቤን ለማካፈል እፈልጋለሁ፡፡

  አንድ፣

  የእስልምና አክራሪነት፣ እስላማዊ የአገዛዝ መዋቅር በፍጹም የማይፈለጉ አካሄዶች መሆኑን በበቂ ሁኔታ የተረዳንበት ጊዜና አቋራጭ ት/ቤት ቢኖር ሰሞነኛው የዓረቡ ዓለም የተቃውሞ ነውጦች ናቸው፡፡

  የግብጽን ብቻ በአብነት መውሰድ ቢቻል የእስላማዊ ወድማማቾች ቡድንን በፍጹም እንደማይፈልጉትና በዓይነ ቁራኛ እየተከታተሉት እንደሆነ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ምሑራን ሳይቀር የተገረሙበት መሆኑን በትንታኔያቸው መካከል ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ አክራሪነትና እስላማዊ መንግሥት የዜጎች ፍላጎት አለመሆኑም በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ የተደረገበት ነው፡፡ የኢራን መልሶ ያገረሸ ተቃውሞና እስከ ፓርላማ መዝለቁም ምሥጢሩ የሥልጣን ሹክቻ አይደለም ከላይ የተጠቀሰውን ዓይነት የአገዛዝ ሥርዓት በመጥላት እንጂ፡፡

  ጊዜው በጣም ተለውጧል፤ ቆም ብለን እናስብ፥ ምዕራባውያንም፣ ዓረባውያንም ለእኛ የሚሰጡን መጠፋፊያችንን እንጂ መበልጸጊያችንን፣ መከባበሪያችንን አይደለም፡፡ እናም የራሳችን እያረረ የሰው ለማማሰል አንሞክር፥ እነሱ እርግፍ አድርገው የተዉተን ብቻ ሳይሆን ላይነሳ እየቀበሩት ያለውን እክራሪነትና፣ የእስላማዊ መንግሥት ጽንሰ ሃሳብ እንተወው ያን ጊዜ በመንፈሳዊ ዓለም ጽድቅ፥ በምድራዊው ሕይወታችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ገነት ትሆንልናለች፡፡

  ሁለት፣

  የክርስትና መሠረታዊ አስተምህሮ የሚጠሉንን እንኳን እስከመውደድ ድረስ ግድ ይለናል፡፡ በመሠረቱ እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ክርስትና ለሰው ልጆች ሁሉ ያለአድልዎ በእኩልነት የሚጸለይበት ሃይማኖት ነው፤ የማያምኑት እንኳን ወደ ልቡናቸው ይመጡ ዘንድ ጭምር፡፡

  ከዚህ አንጻር ማንም ይሁን ማን በሃይማኖታችን የተገለጸውን ክፉ ሥራ፣ መግደልንና፣ጭካኔን መቃወም ለሰው ልጆች ሁሉ ድምጽ ማሰማትን የግድ ይለናልና፥ ኦርቶዶክሳውያን አያገባንም ሊሉ የሚችሉበት እንዳችም የሃይማኖት አስረጂ የለንምና ምን አገናኝቶን ልንል አይቻለንም፡፡ የሚጠበቅብንን መፈጸም እንጂ የሚደረግልን ከእኛ አይደለምና ስለሌላው ዝም እንበል፡፡

  ሰላም ለሁላችን ለሰላም ለአገራችን ኢትዮጵያ

  ReplyDelete
 10. Danye Min yahil endemisesitlh tawkaleh??Yeewinet yetewahido lij neh beye silemamin Lenegeru beahunu sehat I don't trust anybody anyways endamenkut yideregelig enkuan geta mareh ayzoh wendeme.

  ReplyDelete
 11. kalehiwot yasemalene menegeset smaye yawareselene!!!

  ReplyDelete
 12. GOD bless u. kalehiwot yasemalin! Egizeabhare yetifat libochin yimelis!!!!!

  ReplyDelete
 13. Dani

  Enqan egziabher marreh lilijoch limisth lenag lebtetekirsian lehagrh. Andade eko kontet mefderg alben , Egziabher yimsgen,

  ReplyDelete
 14. እንኳን እግዚአብሔር ማረህ ዲ/ን ዳኒ!!! በዚህች ቀን ስንት ስራ እነደቀረ ለኛም እንደቀረብን ምስክር አይሻም፡፡

  ReplyDelete
 15. እንኩዋን እግዚአብሔር ማረህ ። መጥፋትህ አሳስቦን ነበር። እውነትም በ እምነት ሰበብ የራስን ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ መነሳት እንሰሳዊ እንጂ ምን ይባላል ? ስለ ትውልድ እናስብ እባካችሁ! በየ ፓል ቶክ ላይ ሁሉ ጦርነት ስለማንሳት ጤነጝነት አይመስልም ። ሌላው ቢቀር የአያቶቻችሁ አያቶች እምነታቸው ሌላ ነበር። ሀይማኖትም ከሆነ ምክንያታችሁ ማለት ነው ።

  ReplyDelete
 16. Kalehiwot Yasemalin - Ketayun Begugut Entebikalen

  Ameha Giyorgis
  VA

  ReplyDelete
 17. እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማርህ!!

  ሀይማኖትን ለማሳመን በየትኛውም እምነት የተጻፈ መጸሀፍ ጉልበት እና ሀይል ተጠውቀሙ የሚል እንደሌለ ሁሉም እያወቀ ግን በእኛ ግዜ እንዲህ ያለ ፀባይ በሁሉም ዘንድ መኖሩ ያስጨንቃል።

  ለሀይማኖታቸው ቆምንየሚሉ ከፊሉ ሙስሊም እንዲህ ያለ ግፍ መፈጸሙ የማያሰቅቀው የማያሳዝንው ሰው ያለ አይመስለኝም።
  በሌላ በኩል ደግሞ…….. እኛንም ሳይታወቀን ይህ ስሜት ውስጣችን ገብቶ ስር ስዶ ውስጥ ውስጡን እየቦረቦረን ነው...... ያስፈራል።

  በቤተክርስቲያናችን የሀሳብ አለመግባባት ሲኖር ግሩፐ ፈጥሮ ወገን ለይቶ አንዱ አንዱን በጥላቻ አይን እያየ ግን እግዚአብሔርን አመልካለሁ ለእግዚአብሔር ነው የቆምኩት የሚለው ክስቲያንስ ምን ሊባል ነው….?። እንደ ሌላው ገጀራ አያንሳ እንጂ ከስድብ ጅምሮ ግብግብ ፈጥሮ አጋጣሚውን ቢያገኝ ደግሞ ከቦክስ የማይመለሰው ክርስቲያን ነኝ ባይስ...? እኔ ይጨንቀኛል....።

  የፓፓስን እና የካህኑን ስልጣን በራሱ ሚዛን የሚምነዝነውስ..? የመታዘዝ ልብ የራቀንስ....? በጌታ ለእግዚአብሔር ታዘዙ ነው የተባልነው እያለ... ጥቅስ እየመዘዘ ማጠቃለያ ሀሳቡ በስድም የሚጨርሰው……..? ይህ ትውልድስ ትንሽ ሲቆይ ነገ ገጀራ ከማንሳት የሚመለስ የምስላችኋል...? ተሸንፈው ያሸነፉ ቅዱሳን አባቶች የሀይማኖት ሰዎች የነሱ ታሪክ መቼ ይሆን ትዝ የሚለን..? ስንናደድ ስድብ ከቀደመን....ስንሰደብ ዱላ ከቀደመን...የሀይማኖት አባቶች ታሪክ በንዴታችን ወቅት ትዝ ካላለን....በጉባኤ ላይ ብቻ ታሪክ የምንተረክውስ....? ይህስ ከየትኛው ይሆን የሚመደበው..?።

  ReplyDelete
 18. Dani eiziabher ymarhi.antenes aymemibin!.god bless u.

  ReplyDelete
 19. enquan mihretun aweredelih.
  Kalehiwot yasemalin

  ReplyDelete
 20. ውድ ወንድሜ ዲን ዳንኤል። እኔ ሳላውቅ አስሬ ከብሎጉ ገባ ወጣ እያለሁ ጦሜን በመሰንበቴ ምን ሆኖ ይሆን እያልሁ ነበር። ላካንስ ታመህ ነበር። ውድ ወንድሜ አንተንስ አይይብን። እግዚያብሔር ጤና እና እድሜ እንዲሰጥህ የዘወትር ልመኛችን ነው። አንተን ክፉ ነገር አይንካብን።

  በዚህ በወሳኙ ሰዓት ይዘኸው የተነሳኸው ርዕስ በጣም ብዙ ያስተምረናል። በተለይ ሐይማኖተኛ ነን ለምንል እኛ ኢትዮጵያውያን። ምን አለ ወደ ገጠሩ ወጣ ብለን የተለያየ እምነት ተከታዮች እንዴት ተከባብረው እንደሚኖሩ ብናይ። ምን አለ ከእነሱ ብንማር። የቆጠርነው ፊደል ሊያስምረን ካልቻለ በተግባር እነሱ ጋ ብዙ መማር እንችላለን እኮ።

  ReplyDelete
 21. Dn. Daniel Kale hiwot yasemalin.
  Emebet Mariam Selamta Yigebashal.
  Today is the first of the month. LEDETA. I'm so glad i heard your voice on this day because i was so worried that something bad might have happened to you since i stay home and check your blog atleast twice a day...not hearing anything from you for this long was worrisom. Thank God you felt better. Melkam tsom. Atlanta.

  ReplyDelete
 22. God Bless U Man I hope U will be Ok.....

  ReplyDelete
 23. ene gin KaleHiwot yasemalinin ayemugesa asteyayetoch ayimechugnim. enezih le esum le anibabim ayitekimum. bezih bezih mikiniat "wodijewalehu woim alwodedihutim" bihon yitekimenal. be'ergit sibiket sihone endetelemedewu KaleHiwot yasemalen Malet Tegebi newu.

  ReplyDelete
 24. Tariku Wakuma -Ke menen akababiMarch 11, 2011 at 8:13 AM

  Dn., Bemiheretu Silegobegneh Amlak Yetemesegene Yihun. Dani yanesahaw guday Yehaymanot abatoch kelib liyasibubet yemigeba ena mengistim yemayadagim ermija mewsed yalebet new. Yalebeleziya fikirachin adega wist endaygeba yasegal.

  Yanurilin,

  ReplyDelete
 25. በእስልምና ስም የተሰራ ፀያፍ ተግባር ነው
  እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው

  ReplyDelete
 26. By the way, How can their god likes human blood? Is that may be blood donation for their god. Or do they like killing people? Is that their doctrine or hobby? I don't know. I know their vision to making Islam international religious making sharia the world constitution.

  ReplyDelete
 27. Hello dani enkuan Egziabher mareh.

  ReplyDelete
 28. መጥፋትህ አሳስቦን ነበር እንኳን እግዚአብሔር ማረህና መጣህልን፡፡
  “…አሁን አሁን እምነታቸው ሰውነታቸውን ያጠፋባቸው፤ በእምነት ኃይል ከሰውነት ወደ መልአክነት ይሸጋገራሉ ሲባሉ ጭራሽ ወደ አውሬነት የወረዱ አካላትን እያየን ነው፡፡ የአውሬን ሥራ ለመሥራት እምነት ምን ያደርጋል) እምነትኮ አውሬነትን አሸንፎ፣ ሰውነትን አልዕሎ መልአክነትን ገንዘብ ለማድረግ ነው….”
  ክርስትና የፍቅር ሐይማኖት ነዉ፡፡ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ዉደድ፤ ፍቅርን የማያዉቅ እግዚአብሔርን አያዉቅም ተብሎ የለ፡፡ የህግ ሁሉ ማሰሪያ ደግሞ ፍቅር ነዉ አንተ እንዳልከዉ ሰዉን ወደ መልዓክነት የሚያሸጋግረዉ ከሁሉም በለይ ፍቅር ነዉ፡፡ ያለፍቅር ሐይማኖት ምንድነዉ? የሐይማኖቶች ሁሉ ግብ መሆን ያለበት ገነት/መንግስተ ሰማየት አይደለ እንዴ? ለምን ፍጹም ምድራዊ ይኮናል? ሰዉ ደግሞ ለራሱም ሆነ ለሌላዉ ወንድሙ መመኘት ያለበት ይህንኑ ሰማያዊ ህይወት ነዉ፡፡ ታዲያ ከገደለዉ እንዴት ያንን ሰዉ ማፍቀር ይችላል? መግደልስ እንዴት የሀይማኖት መርሆ ሊሆን ይችላል? ያዉም ኢትዮጲያዊ ላይ!!!! በፍቅር የተቀበላቸዉን፤ ነቢያቸዉ አትንኳቸዉ ያለዉን? አረ ግድየላችሁም ከአዉሬነት መልዓክነት ይሻላል !!!

  ReplyDelete
 29. Hi Dani endet neh ahun teshaleh

  ReplyDelete
 30. እንኳን ተሻለህ: እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን::

  "የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው። ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።" የሉቃስ ወንጌል 6:28-30 የፍቅር መጽሐፍ ይህንን ያስተምራል:: እራሴን ጨምሮ ይህንን ለማድረግ ይከብዳል:: ነገር ግን እንዴት መልካም ላሳዩን መልካም ማሳየት ይክበደን:: ይሄም ይቅርና : መልካም ማሳየቱ ይቅርና ለምን ዝም አይሉም?????? ሁሉን ቻይ : አከናዋኝ አምላክ አንተው ልቦና ስጣቸው:: በዚህ ችግር ለወደቁ ወገኖቻችንም ብርታቱን ይስጥልን:: አሜን

  ReplyDelete
 31. Oh Dani enikuan Mihretun lakelih.
  Hulim atitfabin
  10Q

  ReplyDelete
 32. መጥፋትህ አሳስቦን ነበር እንኳን እግዚአብሔር ማረህና መጣህልን፡፡
  “…አሁን አሁን እምነታቸው ሰውነታቸውን ያጠፋባቸው፤ በእምነት ኃይል ከሰውነት ወደ መልአክነት ይሸጋገራሉ ሲባሉ ጭራሽ ወደ አውሬነት የወረዱ አካላትን እያየን ነው፡፡ የአውሬን ሥራ ለመሥራት እምነት ምን ያደርጋል) እምነትኮ አውሬነትን አሸንፎ፣ ሰውነትን አልዕሎ መልአክነትን ገንዘብ ለማድረግ ነው….”
  ክርስትና የፍቅር ሐይማኖት ነዉ፡፡ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ዉደድ፤ ፍቅርን የማያዉቅ እግዚአብሔርን አያዉቅም ተብሎ የለ፡፡ የህግ ሁሉ ማሰሪያ ደግሞ ፍቅር ነዉ አንተ እንዳልከዉ ሰዉን ወደ መልዓክነት የሚያሸጋግረዉ ከሁሉም በለይ ፍቅር ነዉ፡፡ ያለፍቅር ሐይማኖት ምንድነዉ? የሐይማኖቶች ሁሉ ግብ መሆን ያለበት ገነት/መንግስተ ሰማየት አይደለ እንዴ? ለምን ፍጹም ምድራዊ ይኮናል? ሰዉ ደግሞ ለራሱም ሆነ ለሌላዉ ወንድሙ መመኘት ያለበት ይህንኑ ሰማያዊ ህይወት ነዉ፡፡ ታዲያ ከገደለዉ እንዴት ያንን ሰዉ ማፍቀር ይችላል? መግደልስ እንዴት የሀይማኖት መርሆ ሊሆን ይችላል? ያዉም ኢትዮጲያዊ ላይ!!!! በፍቅር የተቀበላቸዉን፤ ነቢያቸዉ አትንኳቸዉ ያለዉን? አረ ግድየላችሁም ከአዉሬነት መልዓክነት ይሻላል !!!

  ReplyDelete
 33. Dani Wendemachin amlake kidusan Yimesgen enkuan bemeheretu Gobegnelin .Fetsemom yimareh wendeme.

  Awon Ewunet belehal sewu sewu bemehonu newu wedemnet Yametawu enam Lesewu degmo maseb yemnet Megeleecha newu Yihen dergit lemifetsemut Aemlak yesewunet Aemrowachewun yimeleselachewu Keezih befitem eyetefetseme newu Zarem tefetsemual Negem yiketelal belen becha zim malet yelebenem hulachinim yerasachin guday selehonne min endeminaderg baygebagnim gin yehone neger madreg endaleben meweyayet yasfelegal.

  ReplyDelete
 34. dane egzeabher enkan marhe

  ReplyDelete
 35. dani EGZABHER MEHRATUN YLAKLHEH YEMBETA LEG MENEM ATHONEM MARYAM ALHEEN

  ReplyDelete
 36. እኔ ግን ዝም እላለሁ፤ ካንተ ስሰማ ውስጤ ወደራሴ እንድመለከት፣ እንዳስተውል ፣ ልዩነቴን እንዳጤን ያደርገኛል፡፡
  ይሕ ሁሉ የተባለውን ሁሌም የማስበው ቢሆንም ይህን ያህል አብራርቶ በምክንያት እና በታሪክ አስደግፎ ማቅረብ አልችልምና ዝም ብየ አነበብኩ፡፡እውነት ያለሰውነት እምነትም ሆነ ኃይማኖት የለም ፤እንደሰውስ ማን አለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ፡፡
  አንኳን ምህረቱን ሰጠህ ወደ ጡመራህ ተመለስክ፡፡ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 37. እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማርህ!!

  ሀይማኖትን ለማሳመን በየትኛውም እምነት የተጻፈ መጸሀፍ ጉልበት እና ሀይል ተጠውቀሙ የሚል እንደሌለ ሁሉም እያወቀ ግን በእኛ ግዜ እንዲህ ያለ ፀባይ በሙስሊም ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘንድ መኖሩ ያስጨንቃል።

  ብዙሀኑ ለሀይማኖት ቆምኩ የሚለው ሳይታወቀው ይህ በሽታ ውስጥ ውስጡን እየቦረቦረው ነው…........እንደ ሌላው ገጀራ አያንሳ እንጂ ከስድብ ጅምሮ ግብግብ ፈጥሮ አጋጣሚውን ቢያገኝ ደግሞ ከቦክስ የማይመለሰውም ክርስቲያን እኮ አለ….ይህስ ከየትኛው ይሆን የሚመደበው..?።

  ReplyDelete
 38. Barreeffamaa Obbo Kibrat dubbisee jira. Garuu maal godha barreeffamichi qorannoo fi qo'annoo malee jibbaa amantaa Islaamaa qabu irraa kan ka'ee olola kanaan dura amantaan ortodoksi afuufaa turte ammas irra deebi'ee afuufaa jira. Mee uf duuba gargalii seenaa amantaa keetii ilaali. Amantaan ortodoksii ummata keenyaa fi ummata kibbaa humnaan gara amantaa ortodoksiitti jijjiiraa turuun isaa ifa. Hoo wabii barbaaddes kitaabban 'qeesootni' keessan barreessaa turan ilaaluu ni dandeetta. Amantaan ortodoks yoomiyyuu amantaa ummata Oromoo fi ummata kibbaa ta'ee hin jiru. Mitis. Kana beekuuf immoo barreeffama 'Mariyam Yetayat Ra'ey' dubbisi. Dubbistee hubatuu yoo kan dandeettuu.

  ReplyDelete
 39. kalehiwot yasemalene menegeset smaye yawareselene

  ReplyDelete
 40. ቃለ ህይወት ያሰማልን ፡፡እንኳን እግዚአብሔር ማረህ፡፡

  እኔ በጣም የሚገርመኝ የወንጀለኞቹ ሳይሆን በወንጀሉ ጉዳይ ጥያቄ ሲጠየቁ ምላሽ የሚሰጡት የሃይማኖት አባቶች ነገር ነው፡፡ ደፍረው የማያወግዙት ለምንድን ነው? ርግጠኛ አይደለሁም ፣ ማስረጃ አላገኘንም ፣ እያጣራን ነው … የሚሉ ምላሾች ነው የሚሰጡት፡፡
  መንግስትስ ምን እየጠበቀ ነው? በእርግጥ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ላይ ርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ ግን ለምን ግልጽ አያደርገውም ፤ ለምንስ የማያዳግም ርምጃ አይወስድም፡፡ ብዙ ሙስሊሞች የስልጣን ወንበር ላይ በመቀመጣቸው መንግስት ደፍሮ ለመናገር የፈራ ይመስላል፡፡

  ለማንኛውም ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ እንደሚጠፉ የምንረዳበትን ልቡና ለሁላችንም ያድለን፡፡

  በጃፓን የተከሰተው አደጋ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ በየሃገሩ የሚደርሰው አደጋና የጦርነቱና የረብሻው መብዛት የመጨረሻው ዘመን ለመሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ጃፓኖች በሃጢአታቸው ይህ መጣባቸው ማለት አይቻልም ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ፡፡›› ይላል ሉቃ.13፥5

  እድሜ ለንስሐ ይስጠን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 41. እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን ያንተን ጡመራ በጉጉት እየጠበኩ ነበር
  በትትክልም እንዲህአይነት ጸያፍ የሆነ ሥራ በሀይማኖት ሽፋን ማካሄድ ሐይማኖተኞችን ወይም የእምነቱን ተከታዮች መናቅና ለሀይማኖቱ ክብር አለመስጠት ነው
  ስለዚህ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሊቃወመው የሚገባ ነገር ነው በተለይም የእምነቱ ተከታይ የሆናችሁ ያገሬሰዋች በእምነታችሁ ላይ የተቃጣ እምነታችሁን የማጉደፍ ስራ ነቅታችሁ ልትቃወሙተ ይገባል እላለሁ ሀብታሙ ከ ባሀር ዳር ፖሊ

  ReplyDelete
 42. አሜን እግዚያብሄር ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ያገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን አሜን!!!

  ReplyDelete
 43. ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል እንኳን እግዚአብሔር ማረህ አሁንም ጨርሶ ይማርህ አሜን፡፡ ዳንኤል የፃፍከው ነገር ትክክል ነው፡፡ ለኛም ልቦን ይስጠን ለነገሮች የምንሰጠው ፖዘቲቭና ኔጋቲቭ ትርጉም ስለሆነ እግዚአብሔር መልካሙን እንድናስብ ይርዳን፡፡ አንተንም እኛንም የእመብርሃን አማላጅነት የፃድቃን ሰማዕታት ተራዳዒነት አይለየን፡፡

  ReplyDelete
 44. @malkaa,
  Akka nama yaada isaa qorannoo fi qo'annoo irratti hundaa'ee dhiyeessu wahi barreffamini kun 'qorannoo fi qo'annoo malee jibba...' jette afuufte. Keessa dabartee amantaan Ortodoxii ummata Oromoofi Kibbaatii ammantaa hin ta'u jette. Kana jechuu keetiifuu raga lafa hin keenye.Ati silaa "Raiye Mariyaam" dubbisteertayyu kan nammarra dhageeche malee? Baay'ee nama gaddisiista. Namas saalfachiista... odoo hin barreessin duratti sirritti dubbisi.
  umhahamu@yahoo.com

  ReplyDelete
 45. To melkaa,
  I read your comment. try to understand what wanted to be said, if old kings of Ethiopia and persons has done this that is totally mistake and sin, no one should be forced to change his religion. You know what Our lord Jesus Christ was doing; to do sth good to them He was asking for their will,... "DO YOU WANT TO FOLLOW ME, TO GET CURED, DO YOU WANT TO ....?" that is what Christianity go after. After all to Kill, no need to have religion. In addition don't try make yourself as representative of Oromo or southern peoples. I think you didn't tried to read and understand what was happened at this areas in the last millenniums.

  ReplyDelete
 46. @malkaa
  nagaan waaqayyoo lafa jirtutti siif haa ta'u!!
  yaadini atti barreessitte xiqoo dhugaa irra waan fagaatte bakka natti fakaateef..mee seenna beektu keessa amantiin "orthodooksii" eeboo fi gaachana baatte uumaatta oromoo ykn kibbaa isa kamiin ajeeste ykn doorsistee gara amantaa kanaatti fidde??? yoo barbaadde amantee yoo barbaadde dhiisuun durumaa kaasse mirga keetti..sirni dura ture uumata oromoo irratti dhiibba uuma tureerra jechuu ni dandeessa.kana jechuun garuu barumsi orthodoksii kana jechuu miti..yeroo hundaa jaalala,tokkumaa, walqixumaa,qulqulumaan kara waaqayyoo kan ibsittu dha.atis yaada kee jibba qofaan osoo hin taanne qo'annoo fi qorannoon osoo dhi'eessitte bayeessa...hin irraanfattin uumatinni oromoo 45% oli amantaa kana jala akka jiru beeku qabda.(resent data of Ethiopian statistics agency)

  araarri haadha keenya Mariyaamii nu faanna haa ta'u!!!!

  ReplyDelete
 47. እንደምን ከረምክ ዲ/ዳንኤል እኔ ባንተላይ ምን መጨመር እችላለሁ እንዲሁ ቸሩአምላካችን ባገልግሎት አበርትቶ በሐይማኖት አጽንቶ በውቀት አጎልብቶ በእድሜ ጸጋ አትረፍርፎ ያኑርልን ከማለት በቀር
  ቸሩአምላካችን የሰማነውን(ያነበብነውን) በስራለመተርጎም ያብቃን
  አሜን

  ReplyDelete
 48. መምህር ዳንኤል የእውነት ምስክር ነህ።
  ሙሉ ጤና እና ረጅም ዕድሜ ያድልህ።

  ReplyDelete
 49. ayyaanaa ze wollegaMarch 16, 2011 at 2:51 PM

  MALKAADHAAF!
  yaa Malkaa, nama gaddisiifta! mee waa'ee amantaa dhiisiitii akkanumaan sammuu Uumaan siif kenneen yaadi.
  1. amantaan lammii tokkoof ykn isa biraaf moo dhala namaa maraaf? ati amantaan Ortodoksii lammii kanaaf(sanaaf) jechuun kee akka ati waa'ee amantaa waa tokkollee hin beekne ragaa gahaa dha. amantaan Ortodoksii fayyina dhala namaa maraaf Jecha Isa du'e, du'aa ka'ees isa gara Samiitti ol ba'e, jaalala, tokkumma fi nageenya lallabdi malee akka "amantaa" isa waraanaan hundeeffamee dhiiga hin dhangalaaftu. dhugaan malees akka ati jettu ragaa sobaan hin barsiiftu.
  2. Waaqayyo dhala namaa uume, kan sooru, waa hunda kan godhuuf; yommuu dhiigni dhala namaa dhangala'u ni gammada moo warra dhiiga dhangalaasan irratti murteessa jettee yaaddaa? amantaa ajjeesi, qali,...jedhu barachaa turte yoo ta'e jechu kun siif fudhatamuu dhiisuu danda'a. garuu namichi amantaa ajjeesi, waraani,... jedhu hundeesse osoo hin dhalatiin dura namootni turan illee Uumaan waan ofiisaa jaallatu sammuu isaanii keessa kaa'ee isaan uumeera. namichi amantaa kee hundeesse kana si keessaa haquuf danda'eera yoo ta'e isa sababa godhattee murtoo Uumaa isa booda dhufurraa ooluuf akka hin dandeenye garuu qalbeeffadhu. Uumaan osoo barbaadee dirqisiisee dhalli namaa akka isatti amanu gochuu waan dadhabu sitti fakkaataa? Inni jaalalaan malee DIRQAMAAN HIN AMANSIISU. manni amantaa ORTODOKSIIS akka warra hin barannee fi barachuu hin barbaannee amantaa lammii ykn qomoo waliin wal hin qabsiiftu, akka warra seexananaaf bulaniis dhiiga qulqulluu dhala namaa dhangalaaftee dirqamaan hin amansiiftu. Namni Amantaa dhugaa barbaade, sammuu isaa qulqullummaan eeggatee, dhugaa barbaaduun ishee argata malee soba dhugaa fakkeessuun, qomootti amanuun, ajjeesuu fi kkfn gongumaa amantaa dhugaan hin argantu! warri ajjeesan, warri soban,... biyya lafaa kanarratti yeroo gabaabaaf dhala namaa dhiphisu, ofii isaanii garuu barabaraan harka abbaa isaanii daabiloositi dhiphatu. jaallannus jibbinus kun hin oolu!

  ReplyDelete
 50. ዲ/ን ዳንኤል እግዚያብሄር ጨርሶ ይማርህ . ቃለ ህይወትን ያሰማልን. ያገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን አሜን!
  [dereje]

  ReplyDelete
 51. ዲ/ን ዳንኤል እግዚያብሄር ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ያገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን አሜን!
  what would be next? can you predict?

  ReplyDelete
 52. ውይ ወንድምዬ እንኳን እግዚአብሔር ማረህ የቤተ ክረስቲያናችንና የሀገራችን የስስት ልጅ እኮ ነህ፤፤

  ReplyDelete
 53. ድረጊቱን ለማንም ዘግናኝ ነው፤ነገረ ግን አጻጻፋህ ችግር አለበት
  1 እስልምና እምነት በማስገደድ እንደሌለ ያሥተምራል፤
  ታዲያ ስታስብዉ ከእምት ትእዛዝ የወጣና ያፈነገጠ አማኝ ነዉ?
  2 በጱህፉህ ከግለሠቦች ይልቅ ወደ እምነቱ አዘንብለሀል "መግደል፣ መስረቅ፣ መድፈር፣ አድልዎ፣ ማቃጠል» እነዚህን ድል መንሣት የተሣነው እምነት እንዴት እምነት ይሆናል"ማለት ምን ማለት ነዉ:እስልምና ከነዚህ ነገሮች በላይ ያለዉ እምነት ነዉ
  3 አንዳንድ ክርስቴያኖች ሆኑ ሌሎች ለእስልምና እና ለሙስሊሞች ያላቸዉ ጥላቻ በጣም የ ወረደ ሥለሆነ እንዚህን አመለካከቶች በማስታርቅ፤በመቻቻል ዙረያ ብትጽፍ መልካም ይመስለኛል:እንኳን ለ አንደኛ አመትህ አደረሠህ
  yasin from
  ADAMA UNIVERSITY

  ReplyDelete
 54. የሆነ ቡድን አባላት በሚከተሉት በድን ስም በሚፈፅሙት ተግባር የቡድኑ መሰረታዊ አስተምህሮትና አቅዋም የሚለካ ከሆነ በምድራችን ላይ አንድም ሊከተሉት ይገባ ዘንድ ብቃት የሚኖረዉ አመለካከት ባልኖረ ነበር ፡፡ ግለሰብ ሙስሊሞች የሚፈፅሙት ቆሻሻ ተግባር እስልምናን እንደ ሀይማኖት ተጠያቂ ሊየደርገዉ እንደማይችል መረዳት መቻል ቀላል ይመስለኛል ፡፡ ሌላ ዉስጣዊ ችግር ከሌለ በስተቀር !! በመካከለኛዉ ዘመን አኮ በክርስትና ስም አጅግ ዘግናኝ ወነወጀሎች ተፈፅመዋል (EUROPEAN INQUSITION) ነገር ግን የትኛዉም ማሰብ የሚችል ቡድንም ሆነ ግለሰብ ሀይማኖቱን ተጠያቂ አላደረገም ፡፡ “የጥፋት ሀይማኖት” ስትል ሃላፊነት የጎደለዉ አገላለፅን ተጠቅመሃል፡፡
  እምነትህ ይህ ከሆነ በደቡብ ክልል በቅርቡ በክርስትና እምነት ተከታዩች ስም የተፈፀመዉን መስጊዶችን የማቃጠል ድርጊት ተከትሎ “ክርስትና የትፋት ሀይማኖት ነዉ” ብለህ ማወጅ ሊኖርብህ ነዉ !! በሀገራችን በአስር ሚሊዮኖች ተከታይ ያለዉን ሀይማኖት በተንሸዋረረ አይን እየዩ አገራዊ ብልፅግናን ማሳብ ሞኝነት ነዉ ፡፡ ግማሽ
  አካሉን ሽባ የደረገ ሰዉ ያሰበበትን የግስጋሴ ጎዳና መሸምጠጥ አይቻለዉም ፡፡ አገራችን ማደግና መሰልጠን ካለባት በሁሉም አትዮጵያዉያን አንድነት ነዉ ሊሳካ የሚችለዉ ፡፡
  ይህንን ለመረዳት አንተ ይሳንሃል ብዬ አላምንም ፡፡
  ከሙስሊም አድናቂዎችህ ፣ ኤልያስ እሸቱ

  ReplyDelete
 55. hy wha's z reason behind u.think twice before u post religious issues

  ReplyDelete
 56. እኔ እንደሚመስለኝ ፀሃፊው "የደህንነት እንጂ የጥፋት ሀይማኖት ሊኖር አይችልምና" ያለው በእስልምና ስም የሚደረግ መጥፎ ስራ ሰሪዎቹን እንጂ እስልምናን አይወክልም ምክንያቱም እስልምና ሃይማኖት ነው ሃይማኖት ደግሞ ከላይ እንደተጠቀሰው "የድኅነት እንጂ የጥፋት ሃይማኖት ሊኖር አይችልምና" ለማለት እንጂ እስልምናን ለመስደብ አይደለምኘእንድያውም እስከ ዛሬ ድረስ ካየኋቸው ሃይማኖታዊ ፅሁፎች ይህ በጣም ተመችቶኛል የፀሃፊው አመለካከት ሁሉም ሰው ጋ ቢስፋፋ ሰላም በሰፈነ ነበር!!!!

  ReplyDelete
 57. የተከበርክ ወንድም ዲ/ዳንኤል

  በቅድሚያ እንኳን ለዘመነ ዮሐንስ አደረሰህ!! እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርህ!! ዘወትር ሲቆጨኝ ያለ ታሪክ ነው፡፡ ለማንኛውም ጆሮ ያለው ሁሉ እንዲሰመማ፣ ያላነበበውም እንዲያነበውና ከታሪካዊ ስህተቱም እንዲጸዳ መልዕክትህ በእጅጉኑ አስተማሪ ነውና እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡

  መልካም ጊዜም ይሁንልህ!!

  ክንፈ ገብርኤል ዘአዋሣ

  ReplyDelete
 58. yeseletene eyeta! EGZIABHER YESTELEN

  ReplyDelete
 59. I think Nietzsche explained the cause of this phenomenon in his "will to power", a fundamental instinct in all species to overpower one another. In Hyenas, this can be seen as fratricide. In humans, sibling rivalry. Perhaps we ought to use a more natural explanation for destructive human behavior.

  ReplyDelete
 60. Anonymous......
  I think Islam is not religion of tolerance, they use religion as political power maxmizing their provocation over Christian.. This is not appropriate for Christian or Islam themselves...

  ReplyDelete