Tuesday, March 1, 2011

ያሳዘነኝ ባንተ መመስገኔ


የታወቁ የቅኔ ሊቅ ናቸው፡፡ የእርሳቸውን ቅኔ ሰምቶ ለመረዳት ላቅ ያለ ዕውቀት እና አእምሮ ያስፈልጋል እየተባለ የሚነገርላቸው፡፡
ሊቁ ቅኔ አቅርበው ሲወጡ አንድ ጨዋ ዘመዳቸው ተከተላቸው፡፡ «የኔታ መቼም ዛሬ ያቀረቡት ቅኔ ልዩ ነው» አለና አድናቆቱን ገለጠላቸው፡፡ መቶ ብርም አውጥቶ ሸለማቸው፡፡ የኔታ አዘኑ፡፡
«ምነው የኔታ ለምን አዘኑ? ሽልማቱን አሳነስኩት እንዴ አላቸው
«እንዲያውም በዝቷል» አሉት የኔታ
«ታድያ ለምን ያዝናሉ
«ምንም ዘመዴ ብትሆን አንተ ቅኔዬን ሰምተህ ካደነቅከውማ ምኑን ቅኔ ሆነው፤ አልተቀኘሁም ማለት እኮ ነው፤ የነገርከኝኮ አለመቀኘቴን ነው፡፡ እኔን ያሳዘነኝ ባንተ መመስገኔ ነው» አሉት ይባላል፡፡
በእርሳቸው ማዕረግ የተካከሉ፤ ሲሆን በማዕረግም፣ በዕውቀትም፣ በትምህርትም የሚበልጧቸው ሊቃውንቱ ቢያደንቋቸው ሊቁ ደስታቸው ወሰን አልነበረውም፡፡ አድናቆታቸው ከመረዳት፣ ከመመርመር እና የሊቁን ቅኔ ልክ እና መልክ ከማወቅ የመነጨ በመሆኑ፡፡ ምንም ያልተማረው ጨዋው ሲያመሰግናቸው ግን የሰደባቸው ያህል አጥንታቸውን ዘልቆ ተሰማቸው፡፡ ዘመዴ ነው ብለው አላመሰገኑትም፡፡ አርሱ ምናልባት ዘመዱን ማድነቁ ይሆናል፡፡ ዝምድናው ለእርዳታ እንጂ ለአድናቆት አይመጥናቸውም፡፡  
ለመሆኑ ምስጋና ሁሉ ያስደስታል? ወቀሳ እና ትችትስ ሁሉ ያሳዝናል?
ባለፈው ሥርዓት እንዲህ የተባለ ገበሬ ማኅበር አባላት የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ተቃወሙ ተብሎ የሚነገር ዜና ነበር፡፡ እነዚህ ገበሬዎች በካድሬዎች የተነገራቸውን ይዘው እንጂ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ተረድተውት የወሰዱት አቋም አይመስለኝም፡፡
አንዳንድ ሰዎች ከየትም በሚቃርሙት የምስጋና ርጥባን ለራሳቸው ተገቢ ያልሆነ ቦታ ይሰጡታል፡፡ «ሩጫዬን ጨርሻለሁ ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ» ማለት ያምራቸዋል፡፡ ደረጃውን የጠበቀ፣ እርከኑን ያለፈ፣ የረቀቀ እና የመጠቀ ሥራ ሠርቻለሁ ብለው እንዲኮፈሱም ያደርጋቸዋል፡፡ ነገ የተሻለ ሥራ እንዳይሠሩ የድል ስሜት ይሰማቸዋል፡፡
አንድን የሥራ ውጤት ሕዝብ ወደደው ማለት ብቻ የትክክለኛነቱ መለኪያ ሊሆን አይችልም፡፡ ሕዝብ ብዙ ጊዜ ስሜቱን እንጂ አመክንዮውን አይገልጥም፡፡ አመክንዮውን ማግኘት የሚቻለው በጉዳዩ ከደከሙበት፣ ዕውቀት አደርጅተው ምሥጢር አደላድለው ከሚገኙ ባለሞያዎች እና ሊቃውንት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ያንን ነገር ሕዝቡ የወደደበትን ምክንያት ሊያስረዱ ሊተነትኑ የሚችሉት እና የሚገባቸውም ምሁራኑ፣ ሊቃውንቱ ናቸው፡፡
በየቤተ ክርስቲያኑ በሚሰጠው ትምህርት «ጊዮርጊስን እንዲህ አድርገው በመንኮራኩር ፈጩት» ሲባል በእልልታ እና በጭብጨባ አገሩን የሚያናውጠው ምእመን መጀመርያውኑ እልል ለማለት ፈልጎ እንጂ ጉዳዩ እንኳን እልል ሊያሰኝ የሚያስለቅስ ነበር፡፡ ሊለቀስላቸው ሲገባ እልል የተባለላቸው፤ እልል ሊባልላቸው ሲገባም የተለቀሰላቸው ብዙ ነገሮች አሉ በሀገራችን፡፡
አትላንታ የሚገኘውን የኮካ ኮላ ሙዝየም ስትጎበኙ አንድ ነገር ትታዘባላችሁ፡፡ ለኮካ ኮላ ከመላው ዓለም የሚጎርፈውን አድናቆት ታያላችሁ፡፡ በየሃገሩ ምን እንደሚባል፣ አንዴት እንደሚወደድ፣ በታላላቅ የስፖርት መድረኮች ምን እንደሚባል ታያላችሁ፡፡ በርግጥም በመላው ዓለም የሚወደድ የሚጠጣ መጠጥ ሆኗል፡፡ ለኮካ ኮላ ግን ይህ ብቻ በቂው አይደለም፡፡ የኮካን ጣዕም የሚያጣጥሙ የታወቁ ቀማሾች አሉት፡፡ የኮካን ጣዕም ልክ እና መልክ የሚያወጡት እነርሱ ናቸው፡፡ ኮካም ደረጃውን የጠበቀ ምርት አወጣሁ የሚለው እነርሱ አጣጥመው ሲያደንቁት ነው፡፡
ጠርሙሱን፣ ቅመማውን፣ ማስታወቂያውን፣ የሕዝቡን ስሜት እና የመጠጡን ዓይነት በተመለከተ የሚያጠኑ፣ የሚወስኑ እና የሚያስፈጽሙ በብዙ የሚቆጠሩ ሞያተኞች አሉት፡፡ የኮካ ኮላ ካምፓኒ ከሚሊዮኖች በላይ የሚሰማቸው እነዚህን ነው፡፡ ሕዝብ እንዲወድደውም ያደረጉት እነርሱ ናቸው፡፡ ስኬቱን እና ድክመቱን፣ ውጤቱን እና ብክነቱን አንጥረው አብጠርጥረው የሚነግሩት እነርሱ ናቸው፡፡ መለኪያውንም የሚያውቁት እነርሱ፡፡
መመስገን መታደል ነው፡፡ በተለይም እንደኛ ሀገር ወቀሳ እንጂ ምስጋና ብርቅ በሆነበት ሀገር መመስገን መመረጥም ነው፡፡ ግን ምስጋናዎችን የምንሰማበት እና የመንተረጉምበት ደርዝ ያስፈልጋል፡፡ የሚያድን ምስጋና አለ፤የሚገል ምስጋናም አለ፡፡ የሚያቀና ምስጋና አለ፤ የሚሰብር ምስጋናም አለ፡፡ ከአፍ ልማድ የሚመጣ ምስጋና አለ፤ ከልብ የሚመነጭ ምስጋናም አለ፡፡ ሲባል ሰምቶ የሚመጣ ምስጋና አለ፤ ታስቦበት የሚወጣ ምስጋናም አለ፡፡
ያንዳንዱ ወቀሳ ቁጥሩ ከምስጋና፣ ያንዳንዱም ምስጋና ቁጥሩ ከስድብ ነው፡፡ ዐፄ ምኒሊክ ለባልቻ አባነፍሶ ጎራዴ ሸለሟቸው አሉ፡፡ ሰው ሁሉ አመሰገነ፡፡
ምኒሊክም «እንዴት ነው ሰው ምናለህ አሏቸው
«አመሰገነ» አሉ ባልቻ፡፡
«አለቃ ገብረ ሐናስ ምናለህ እርሱን አላገኘሁትም፡፡ ከሕዝቡ የተለየ ምን ይላል ብለው ነው» አሉ ባልቻ፡፡
 «ግዴለም መጀመርያ እስኪ አሳየው» አሉ ምኒሊክ፡፡
አለቃ ተፈልገው መጡ፡፡ ጎራዴውን አዩ፡፡ አገላበጡ፡፡ ባልቻ ስልብ ነበሩና አለቃ በሰም እና ወርቅ «አይ ጎራዴ፤ አይ ጎራዴ፤ እንዲህ ያል ጎራዴ» ብለው አድንቀው ለባልቻ ሰጧቸው፡፡
ባልቻም ለምኒሊክ «ገብረ ሐና እኮ አደነቀ» አሏቸው፡፡
«ምን ብሎ አደነቀ»
«አይ ጎራዴ እንዲህ ያል ጎራዴ ታይቶ አይታወቅም ብሎ አደነቀ» አሏቸው፡፡
ምኒሊክም «ከዚህ በላይማ ምን ብሎ ሊወቅስህ ነው፤ ምስጋናኮ አይደለም ባልቻ» ብለው ነገሯቸው፡፡ ባልቻ ገብረ ሐናን እገላለሁ ብለው በስንት አማላጅ ታረቁ ይባላል፡፡ የሚያስለቅስ ምስጋና የሚያስደስትም ወቀሳ አለ፡፡
ታዋቂው፣ ዝነኛው፣ አንደኛው፣ ታላቁ፣ ሊቁ፣ ጀግናው፣ የሚሉት ቃላት የገደሏቸውን ባለ ስም ሰዎች ያህል ጥይት የጨረሰ አይመስለኝም፡፡ ሲጨበጨብላቸው፣ ሲዘመርላቸው፣ መወድስ ሲቀርብላቸው፣ ሰው ከመቀመጫው ሲነሣላቸው፣ እነርሱ ካልመሩን ሞተን እንገኛለን ሲላቸው ያንን ነገር የሥራቸው ደረጃ ማረጋገጫ አድርገው በመውሰዳቸው ተሰብረው የቀሩ ብዙ ናቸው፡፡
ለመሆኑ ታዋቂ ናቸው ያለው ማን ነው? መለኪያውስ ምንድን ነው? ስንት ሰው ሲያውቅ ነው ታዋቂ የሚባለው? የት የት ቦታስ ሲታወቁ ነው ታዋቂነት የሚስማማው? አንድን ሰው ዝነኛው ለማለት መሥፈርቱ ምንድን ነው? ይህንን ስምስ መስጠት የሚ?ችሉት እነማን ናቸው? አንድ ቀልድ ሞቶ ተሟሙቶ ያወራ ሁሉ ኮሜዲያን፣ አንድ ፊልም ውስጥ አስተናጋጅ ሆኖ ለሦስት ሰከንድ የታየ ሁሉ አርቲስት፤ ሁለት ስንኝ የጻፈ ሁሉ ባለ ቅኔ፤ ግማሽ ገጽ የጻፈ ሁሉ ደራሲ፣ እቴ ደማምዬ ያለ ሁሉ ድምፃዊ፣ ሁለት ቤት የሠራ ሁሉ ኢንቬስተር፣ አሥራ ሁለተኛ ክፍል የጨረሰ ሁሉ ምሁር፣ እየተባለ በሚጠራበት ሀገር ይህንን ተቀብሎ መደሰት መኮፈስ ይገባል?
ዐፄ ቴዎድሮስ የደብረ ታቦርን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በአማረ ሁኔታ ሠርተው ጨረሱ፡፡ በዙርያቸው ያለው ሰው ሁሉ አደነቀላቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በጣም ጠባብ መሆኑን ለመናገር የደፈረ እንኳን አልነበረም፡፡ እርሳቸውም በዚህ በጣም ተደሰቱ፡፡
በኋላ ግን እነ ገብርዬ «ይህንን መቅደስ አለቃ ገብረ ሐና አይተው ካላደነቁት ሊደሰቱ አይገባዎትም» አሏቸው ይባላል፡፡
  ወዲያው አለቃ ገብረ ሐና ተጠርተው መጡ፡፡ መቅደሱን አዩ፡፡ ዞሩ ገመገሙ፤ውስጥ ገብተውም ወጡ፡፡ ከዚያ ዐፄ ቴዎድሮስ ጠየቋቸው
«እንዴት ነው መቅደሱ አሏቸው፡፡
አለቃም «ለሁለት ቄስ እና ለሦስት ዲያቆን ይበቃል» ብለው ቤተ መቅደሱ ጠባብ መሆኑን ነገሯቸው፡፡
እነ ገብርዬ አለቃ ይምጡ ያሉት በሁለት ምክንያት ነው፡፡ በአንድ በኩል አለቃ በነገሩ ላይ ዕውቀት አላቸው፡፡ ሊተቹም ሊያመሰግኑን ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አለቃ ሳይፈሩ ሳይቸሩ የመሰላቸውን እውነት ይናገራሉ፡፡ እንደ ሌሎቹ ሹመት ይቀርብኛል፣ ክብር ይጎድልብኛል፣ መከራ ይገጥመኛል፤ ንጉሥ ይጣላኛል ብለው አይፈሩም፡፡
ሲያመሰግኑም ሆነ ሲተቹ ሊሰሙ የሚገባቸው እንዲህ ያሉት ናቸው፡፡ አንደኛ በነገሩ ላይ ዕውቀቱ ችሎታው ያላቸው፤ ሁለተኛም በእውነት ያለ ጥቅም ሊናገሩ የሚችሉት፡፡
መንግሥትም ሊሰማቸው የሚገባቸው እንደ አለቃ ገብረ ሐና ያሉትን ምሁራን፣ ባለሞያዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ሰዎች ነው፡፡ በአንድ በኩል እውቀት በሌላ በኩል እውነት ያላቸውን፡፡
የሚተቸውን ሁሉ የሚያመሰግኑ፣ ጨለማውን ሁሉ ብርሃን የሚሉ፤ የጎደለውን ሞልቷል፤ የጠመመውን ቀንቷል ብለው የሚናገሩ፤ ምንም በሌለበት የሚያጨበጭቡ ሰዎች አቅጣጫ ከማዛባት ያለፈ ጥቅም የላቸውም፡፡ ወዳጅነት በማመስገን ብቻ አይለካም፡፡ ወዳጆች ማለትም የሚያመሰግኑ ማለት ብቻ አይደሉም፡፡ ሳያነጥሱ «ይማራችሁ» ሳያደናቅፋቸው «እኔን» ማለት ብቸኛው የወዳጅነት መለኪያ አይደለም፡፡
 እውነተኛ ወዳጅ ጨለማን ከብርሃን፣ ድክመትን ከብርታት፣ ፍየልን ከበግ ለይቶ ማመልከት የሚችል ነው፡፡ ወዳጅ መነጽር ነው እንደሚባለውም የሆነውን ነገር ቁልጭ አድርጎ ማሳየት የሚችልም ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባት ሰዎችን ከመገበ በኋላ ወደ ጥብርያዶስ ማዶ ሄደ፡፡ እነዚያው ሰዎች ተከትለውት መጡና «ስንፈልግህ ነበርኮ» የት ሄድክ» ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱ ግን «የምትፈልጉኝ እንጀራ ስላበላኋችሁ ነው፡፡» ብሎ እቅጩን ነው የነገራቸው፡፡ እንጀራ ስላበላናቸው፣ ሥራ እና መዓርግ ስለሰጠናቸው፣ የህልውናቸው መሠረቶች እኛ ስለሆንን ብቻ የሚያመሰግኑን መኖራቸውን አለመርሳት ደግ ነው፡፡
በተለይም የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዛሬ በዚህ ገመድ እየተጠለፉ እየወደቁብን ነው፡፡ ለፈጣሪ መቅረብ ያለበት ውዳሴ እና ቅኔ፣ መዝሙር እና ማኅሌት ለእነርሱ እየቀረበ ነው፡፡ ዙርያቸው በሚያመሰግኗቸው እና በሚያደንቋቸው ሰዎች ብቻ የተከበበ ነው፡፡ አንዳንዴም ያላደረጉትን እና ያልሆኑትን ጭምር እንደሆኑት እና እንዳደረጉት አድርገው የሚነግሯቸው ሰዎች አሉ፡፡ ሰማይን ከነግሡ ምድርን ከነ ግሣንግሡ የፈጠርከው አንተ ነህ ይሏቸዋል፡፡
እውን እነዚህ ሰዎች የሚያመሰግኗቸው መመስገን ስላለባቸው ነው? ወይስ ከምስጋናው ፍርፋሪ ለራሳቸው ለማትረፍ? ራሳቸው አመስጋኞቹስ ቢሆኑ በሚናገሩት ነገር ያምኑበታል ወይስ እንጀራ ለመጋገር ያህል ነው የተናገሩት? ብለው እያሰቡ አይደለም የሚሰሟቸው፡፡ «በአፋቸው የሚያመሰግኑ፣ በልባቸው ግን የሚረግሙዋቸው» ብዙዎች መሆናቸውንም ዘንግተውታል፡፡
በምስጋና ብቻ አይደለም በትችት እና በወቀሳም እንደዚሁ ነው፡፡
ለመሆኑ ሰዎች በተናገሩት ሁሉ መናደድ አለብን? ወቀሳው ሁሉ ወቀሳ፣ ከሰሳውም ሁሉ ከሰሳ ነው? ማን ሲናገረው ነው መልስ እና ማብራርያ መስጠት ያለብን? ከየትስ ሲመነጭ ነው አጥንታችን ድረስ ዘልቆ ሊሰማን የሚገባው? ይህንን ባለማስተዋል ብዙዎች ቅስማቸው ይሰበራል፡፡ ተባልን፣ አሉን፣ እያሉ ልባቸው ይደማል፡፡
ምናልባት አንዳንድ ወቀሳዎች ሥራው ትክክል አለመሆኑን ሳይሆን ስለ ሥራው ገና ብዙ መናገር እንዳለብን ያመለክቱ ይሆናል፡፡ ዐፄ ምኒሊክ የወረቀት ገንዘብን ሲያስተዋውቁ ብዙዎቹን መኳንንት እና መሳፍንት ጨምሮ ሕዝቡ አልተቀበላቸውም፡፡ ዐዋጁ ታውጆ እንኳን ቢሆን በጠገራ ብር የሚገበያየው ሰው ይበዛ ነበር፡፡ እንዲያውም «በአዲሱ የምኒሊክ ብር ነው ወይስ በቀድሞው ብር ነው» እየተባለ መገበያየት ሁሉ ተጀምሮ ነበር፡፡
ይህ ግን የወረቀት ገንዘብ ትክክል አለመሆኑን የሚያሳይ አልነበረም፡፡ ስለ ወረቀት ገንዘብ ጥቅም እና ዋጋ ለሕዝቡ ገና ብዙ ገለጣ እንደሚያስፈልግ፣ ገና ብዙ ሥራ እንደሚቀር፣ የአመለካከቱን ለውጥ ለማምጣት ብዙ መሠራት እንዳለበት የሚያሳይ ነበር፡፡ የወረቀት ገንዘብ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ጥቅም እና ጉዳት መተንተን የምሁራኑ ድርሻ ነበር፡፡ ማስረዳትም እንዲሁ፡፡
እና ተተቸ ማለት አይጠቅምም ማለት አይደለም፡፡ ማነው የተቸው? ገብቶት ነው ወይ የተቸው? ብሎ መጠየቅም ይገባል፡፡ ሰው ሰደበን ብለው የሚያዝኑ፣ ታማን ብለው የሚቆስሉ፣ ተወቀስን ብለው የሚሰማቸው ሰዎች አሉ፡፡ መጀመርያ ነገር እነዚህ ሁሉ በራሳቸው ምንም ማለት ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ትችቱም፣ ወቀሳውም፣ ሐሜቱም መሠረት አለው ወይ? በዕውቀት ላይ የተመረኮዘ ነው ወይ? ከሚገባው ሰው የመጣ ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡
ሆድ ስለባሰው፣ ምቀኝነት ስለተጠናወተው፣ ጥቅም ስለቀረበት፣ ሹመት ስለሄደበት፣ ስለተበለጠ፣ ስለተለወጠ፣ የሚናገረውን ሰው፤ ዐውቆት ገብቶት ከሚናገረው መለየት ብልህነት ነው፡፡ የጥላቻ ወቀሳ እና የእበላ ባይነት ምስጋና ያው ናቸው፡፡ ጥቅም ቀርቶበት የሚሳደብ እና እጠቀማለሁ ብሎ የሚያወድስ አንድ ናቸው፡፡ የሁለቱም መሠረት አመክንዮ ሳይሆን ስሜት ነውና፡፡
ስታቫንገር፣ ኖርዌይ

© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ .የተወሰነ የግ. በሚታተመው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም።

26 comments:

 1. This is what most of us are lucking and should take in to consideration. unfortunately we have no culture of appreciating others. true appreciation!!! many mouths are open for discouraging or commenting. (based on Rigt or wrong backgroung )

  ሰው ሰደበን ብለው የሚያዝኑ፣ ታማን ብለው የሚቆስሉ፣ ተወቀስን ብለው የሚሰማቸው ሰዎች አሉ፡፡ መጀመርያ ነገር እነዚህ ሁሉ በራሳቸው ምንም ማለት ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ትችቱም፣ ወቀሳውም፣ ሐሜቱም መሠረት አለው ወይ? በዕውቀት ላይ የተመረኮዘ ነው ወይ? ከሚገባው ሰው የመጣ ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡

  kalehiwot yasemalin

  ReplyDelete
 2. ዲ/ን ዳንኤል! ቃለ ሕይወት ያሰማልን! እንዲህ አንጀታችንን አርስልን እንጂ። አገራችንን ወደኋላ ካስቀሯት ችግሮች አንዱ ከንቱ ውዳሴ ነው። ለእውነት ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ሰዎች በሚሰጧቸው አስተያየት ራሳቸውን የኮፈሱ፤ ሀገርን፣ ሕዝብንና ቤተ ክርስትያን የበደሉ ባለሥልጣናትና አባቶች የትየለሌ ናቸው። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጣቸው!

  ReplyDelete
 3. ይኼን ነገር በቅጡ የሚያጠና አካል ባለመቋቋሙ በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው የሞራልና ቁሳዊ ኪሣራ በሥፍር ይህን ያህል ይሆናል ብሎ መገመት እንኳ አይቻልም፡፡

  ከድሮ እስከ ዘንድሮ እንኳን ባይሆን የመንግሥቱ ኢትዮጵያ የውድቀት ምክንያት የጥላቻ ወቀሳና የእበላ ባይነት ምስጋና ናቸው፡፡ ይህ በቤተ መንግሥቱ የነበረው ልምድ እንደ አተት ተሠራጭቶ ቤተ እምነቶችን ገረፍ ከማድረጉም በላይ ሰባኪና ዘማሪ ከእኛ ወዲያ ላሳር ብለው የተነሱት ለያዥ ለገራዥ አስቸጋሪ እንዲሆኑ ያደረገው ሳይመረምሩ ያለእውቀት በደመነፍስ ምስጋና ስለተዥጎደጎደ ነው፡፡

  የኢሕአዴግም የከፋ ድክመቱ ይኸው ነው፡፡ የእባላ ባዮች ምስጋና ኪሱን ሲሞላው እንደ ጣና የተትረፈረፈለት እየመሰለው መሸወዱ፡፡

  ወደማኅበረሰቡ በአስደንጋጭ ሁኔታ መዛመቱን ለመረዳት ፌስቡክ ከበቂ በላይ ያስረዳል፡፡ በአልበም አደራደር ቅድሚያ የማይሰጠው የፎቶ ስታይል፣ የአለባበስ፣ ወዘተ ... ሥርዓት ሳይቀር ነፍስ ነው፣ ላቨሊ (sweet, lovely) ነው፣ እየተባለ የእበላ ባይነት ምስጋና ሰዉን ሁሉ እየቀረጠፈው ነው፡፡

  ኧረ የማይገባ ምስጋና ቀርቶ የሚገባውም ቢሆን ሰዎችን ለትምክህት በማይዳርግ መንገድ ይሰጥ፤ ጥቂት አደሮች እንጠቀማለን ብለን ኢትዮጵያን ያህል አገር፣ ኢትዮጵያዊነትን ያህል ሕዝብ አንፍጅ፡፡

  ReplyDelete
 4. ዲ.ዳንኤል፡- ተባረክ ተምሬበታለሁ።'ምስጋና' ሁሉ ምስጋና አለመሆኑን፡ ትችት ሁሉ ነቀፋ አለመሆኑን ተረድቼበታለሁ!!!!!!!!!!!!!!!1

  ReplyDelete
 5. wow

  I took for myself 75% of the advise. Thank you Dani, please go ahead, we need you for this generation...

  But Dan, after this article, I will take care even when I comment for you...

  ReplyDelete
 6. "ጥቅም ቀርቶበት የሚሳደብ እና እጠቀማለሁ ብሎ የሚያወድስ አንድ ናቸው፡፡ የሁለቱም መሠረት አመክንዮ ሳይሆን ስሜት ነውና፡፡" Great concluding remark Dani, Thanks for the article.

  ReplyDelete
 7. I think that is the base of our life. In the poorest country in the world! If I don't appreciate someone who gave me a job or work, how can I push this life?

  ReplyDelete
 8. Dani, what can I say about this article? Just u said it more than enough but do you think that the aforementioned people will take in to account if they are told so? I doubt, because they have ears only to hear what they need not what they are. Dani, especially this "ekekegn likekih" style of business is widely spreading in our church. every decision is made in line with benefits to be earned on individual or group bases. I personally fear that we are on the way of losing those who stand for truth and speaks about it.

  Let GOD give all of us to stand for truth and to be responsible for what we are doing.

  ReplyDelete
 9. ዳኒ ግሩም ብለሀል። ላመሰግንህ ግን ፈራሁ

  ReplyDelete
 10. Many thanks Dn Daniel!!! This is what most of us lack. I have got a lot from this article. May God help me to use this in my day to day life. Thank u again.

  ReplyDelete
 11. I really afraid to comment in anyways, for the mere reason that I perceive myself as the "Relative" mentioned in this article. But one thing is true, truly impressive thought, able to speak your mind. God Bless your work. Please keep on doing this work as it has significant impact in shaping the generation in the right direction.

  ReplyDelete
 12. ተስፋብርሃንMarch 3, 2011 at 6:03 PM

  በጣም ተገቢና ሁሉንም የሚያስተምር ነው። ውድ ወንድሜ ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  በምክሩ ተጠቃሚዎች ያድርገን። ከፍቅረ ከንቱ ውዳሴ ይጠብቀን። አሜን።

  ReplyDelete
 13. I do not understand the real objective of this article. It seems like the writer felt rejection from followers or his intention is to ironically say that individuals who earned popularity are bad. I said so because I do not see any indication of criticizing cheep popularity or similar mistakes of preachers. I mean the article could have been ok if it clearly mentioned its objective and intention.
  However, obviously the writers command of language and expression power is vivid and colorful ingredients in the article.

  ReplyDelete
 14. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ.ዳንኤል MK has insulted by many protesters and compared with them by the syound as per the problem in hawasa.ይሀስ ምን ይባላል?
  GOD bless ethiopia

  ReplyDelete
 15. አንድን የሥራ ውጤት ሕዝብ ወደደው ማለት ብቻ የትክክለኛነቱ መለኪያ ሊሆን አይችልም፡፡ ሕዝብ ብዙ ጊዜ ስሜቱን እንጂ አመክንዮውን አይገልጥም፡፡ አመክንዮውን ማግኘት የሚቻለው በጉዳዩ ከደከሙበት፣ ዕውቀት አደርጅተው ምሥጢር አደላድለው ከሚገኙ ባለሞያዎች እና ሊቃውንት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ያንን ነገር ሕዝቡ የወደደበትን ምክንያት ሊያስረዱ ሊተነትኑ የሚችሉት እና የሚገባቸውም ምሁራኑ፣ ሊቃውንቱ ናቸው፡፡

  aren't u a bit harsh on the society,specially with:ሕዝብ ብዙ ጊዜ ስሜቱን እንጂ አመክንዮውን አይገልጥም.the history of Rwanda,the genocide,supports ur idea.but if this is the case what is democracy,rule of the people by the people,i mean is it a false definition?
  i think to lead the people in the right direction there must be a culture in a certain society,to listen to its elders and learned individuals so that there will be a place for አመክንዮ not ስሜት.the every day life of the people should be guided by reason which could exist if morality and ethics has a place over the majority of the people.if this is the case ur generalization would be wrong and hopefully democracy is a well defined fact.unless otherwise we,the people,have no hope and our fate lies on lucky or rather daring individuals who get to rule us.

  ReplyDelete
 16. ከዚህ በፊት ለ1ኛ ዓመት ዝግጅት እንድንመዘገብ የኢ-ሜይል አድራሻ ሰጥታችሁ በዚያ አድራሻ ልከን ነበር እስከ አሁን ምላሽ አላገኘንም ፡፡ምላሽ አግኝተው ደግሞ የመግቢያ ኮድ ያልተላከላቸው እንዳሉ ሰምቻለሁ ፡፡
  በተቻለ መጠን በወቅቱ ምላሽ መስጠት ብትችሉ፡፡

  ReplyDelete
 17. ሰባኪና ዘማሪ ከእኛ ወዲያ ላሳር ብለው የተነሱት ለያዥ ለገራዥ አስቸጋሪ እንዲሆኑ ያደረገው ሳይመረምሩ ያለእውቀት በደመነፍስ ምስጋና ስለተዥጎደጎደ ነው፡፡

  ReplyDelete
 18. Wat is wrong on ur pic? say some thing pls?

  ReplyDelete
 19. Dear daniel,
  I have no words to express the significance of this message especially in these days. These days, fellow ethiopian orthodox people have been wrongly led by few preachers and spiritual singers who claim they are famous and are the only ones standing for our church while doing their best to prove mahebere kidusan wrong and trouble maker.

  As you nicely put it, memebers of mahebere kidusan should not get offended; they should analyze who is criticizing and how far are the critics true.

  Equally important, mahebere kidusan should strengthen its effort to make people know what is mahebere kidusan, what are its accomplishments so far, and what are its missions and goals, ets....

  Only time (God) will tell us who is honestly standing for EOC and who is the trouble maker. Till then, may God bless you all.

  ReplyDelete
 20. Dear daniel

  I highly value this message especially in recent times when fellow EOC people are misled by few preachers and "spiritual" singers who claim they are famous and the only ones standing for EOC while doing their best to prove Mahebere Kidusan wrong and trouble maker.

  Unfortunately, we fellow orthodox people are emotional and do not usually critically analyze comments we hear from few preachers and singers on mahebere kidusan. We just cheer to any emotional preacher and singer. I hope your message would mean a lot for us.

  For members of mahebere kidsuan, the message is of high significance too. They should take it easy and analyze who is making the critics and how far are the allegations true. Equally important, mahebere kidusan should strengthen its effort to make EOC people understand about the missions, goals of mahebere kidusan and the contribution it has made so far.

  Time will tell us who is standing for EOC and who is hurting our beloved church.

  May God bless Mahebere Kidusan !

  ReplyDelete
 21. የኢንትራንስ ኮድ መላኪያችሁ ጊዜ ገና ነው ወይንስ ዘለላችሁን፡፡

  ይህንን በተመለከተ ብታሳውቁን፡፡

  ReplyDelete
 22. ዝምታው ይሰበር !!!

  ReplyDelete
 23. kale hiwot yasemalin wendimachin!!! menewu beselam newu Zim alk newu yeandegna amet beal akebaberu zigejet gize asatah ? please say some thing Zim atebel tsafelin hulem tsehufehin enenafekalen.Amlake kidusn kindihin yabertaleh? kekifu hulu yisewureh.

  ReplyDelete
 24. ከማቱሳላ ያነሰ ከአብርሀም የበለጠ እድሜ ይስጥህ ብያለሁ
  ላሜዳ አ.አ

  ReplyDelete
 25. ወይ ጉድ ለማድነቅም ለካ ዕውቀት ያስፈልጋል::

  ReplyDelete