Wednesday, March 30, 2011

ዝክረ የዳንኤል እይታዎች

ኃይለ ገብርኤል ከአራት ኪሎ
የተከበራችሁ እኅቶችና ወንድሞች እንደምን አላችሁ? ሰላመ ልዑል እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

ሁላችሁም እንደምታውቁት መጋቢት 18 የዳንኤል እይታዎች የተጀመረበት አንደኛ ዓመት በአኽሱም ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከብሯል። በለቻለ መጠንም ዝግጅቱን በቀጥታ ለማስተላለፍ ተሞክሯል። ይሁን እንጂ በኢንተርኔት መቆራረጥና በስራ ምክንያት ፕሮገራሙን ላልተከታተላችሁት ሁሉ በዝክረ የዳንኤል እይታዎች በዓል ላይ የነበረው ዝግጅት ምን ይመስል ነበር? የሚለውንና በዝግጅቱ ላይም ያየሁትንና የታዘብኩትን እስኪ ከብዙ በጥቂቱ አጠር አድርጌ ላካፍላችሁ፡

ሁለቱ ሰይጣናት


ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የታሪካቸው አካል አብሯቸው የሚኖር አንድ የታሪክ ቁራጭ አለ፡፡ የሰይጣን ታሪክ፡፡ 1983 ዓም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ወደ ብላቴ የወታደራዊ ማሠልጠኛ ገብተን ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ቀድመው በነበሩት ወታደሮችም ሆነ በኋላ በመጣነው ሠልጣኞች ዘንድ አፍ ከሚያስከፍቱት ወሬዎች አንዱ ሰይጣን በማሠልጠኛው ውስጥ የሚሠራቸው አስቂኝ እና አሳዛኝ ታሪኮች ነበሩ፡፡

Monday, March 28, 2011

የዳንኤል እይታዎች አንደኛ ዓመት ተከበረ የዳንኤል እይታዎች የጡመራ መድረክ አንደኛ ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ በአኩስም ሆቴል አዳራሽ መጋ 18 ቀን 2003 ዓም ተከበረ፡፡

በበዓሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እና በኢሜይል የተመዘገቡ 500 በላይ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

Saturday, March 26, 2011

ያንተ እይታ


ኃይለ ገብርኤል ከአራት ኪሎ
ዺ/ን ዳንኤል ክብረት ሰላም ላንተ ይሁን።

ዲ/ን ዳንኤልየዳንኤል እይታዎች” በሚል ስያሜ የጡመራ መድረክ ከፍተህ እንደ ወንድም አሉላ አገላለፅ ‹‹ዛቲ ጦማር ትበጽሕ›› ብለህ ሥነ ጽሑፋዊ ምርትህን ‹‹ይድረስ ለኲሉ ዓለም›› ካልክ አነሆ አንድ ዓመት ሞላህ። ለባለቤትህ ለፅሉ ጌች እና ለዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ምስጋና ይድረሳቸውና በአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለህ የተከልከውና በንባብና ምርምር ያለመለምከው መልካም ተክል ፍሬው በዓለም እንዲበተንና የብዙዎችን ህይወት እንዲያጣፍጥ ሆነ። ዲ/ን ዳንኤል በዚህ የጡመራ መድረክ የምታቀርባቸውና እይታህን የሚያንፀባርቁት ስለ ሀገራችን ታሪክ፣ እምነት፣ ፖለቲካና ትውፊት የሚዳስሱት የብዕር ትሩፋቶችህ ብዙዎቻችንን ያስተማሩ፣ የመከሩና ራሳችንን ዞር ብለን እንድንፈትሽ ያደረጉ ናቸው። እንዲህ አይነቱ እይታ ሁላችንም ግንባር ላይ ካለው የስጋ እይን አይደለም። በውስጥ ካለውና በግብሩ እና በፍሬው እንጂ ፊት ለፊት በማየት ከማይታወቀው ከብሩህ ዓይነ ልቦና ነው። እግዚአብሔር አምላክ ጨምሮ፣ ጨምሮ፣ ጨምሮ ብሩህ ያድርግልህ።

አንድ ድፍን የአዝመራ ዓመት

ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር)
ካልጋሪ፤ ካናዳ 

ለመጻፍ የተነሳሁት የዳንኤል ዕይታዎች የጡመራ ገበታ አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ ነው። ይሁንና ቅድመ ከዊን ወደነበረ ጊዜ ሄጄ በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ትንሽ ልበል።

ጊዜው የዛሬ ሁለት ዓመት። ቦታው ፓሪስ ከተማ። የአውሮፓ ስብከተ ወንጌል ጉባኤ ለመሳተፍ ከየአገሩ ተሰባስበን ነበር። ወዳጆቼ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ዲያቆን ብርሃኑ አድማስም በመምህርነት ከአዲስ አበባ መጥተው ነበር። በወቅቱ ዳንኤል አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ አምደኛ ነበር። ከፓሪሱ ጉዞ ከወራት በፊት ለአጭር ጊዜ አዲስ አበባ በሄድኩበት አጋጣሚ የአምዷ ደንበኛ አንባቢ ነበርኩ። 

Friday, March 25, 2011

በዓሉን በቀጥታ


 
የዚህ ብሎግ አንደኛ ዓመት በዓል እሑድ መጋቢት 18 ቀን 2003 ዓም ከሰዓት በኋላ 730 ጀምሮ ይከበራል፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ቴሌ ቢቀና ዝግጅቱን በቀጥታ በዚህ ብሎግ እናስተላልፋለን፡፡ ይከታተሉ፡፡

ነጻነት፤ ምን?

አንዳንድ ጊዜ የአፍሪካ አሜሪካውያንን የጥንት ታሪክ ስመለከት በአንድ ነገር እኛን እወቅሳለሁ፡፡ ከነጻነታችን ያገኘነው ነገር ምንድን ነው? እያልኩ፡፡

Wednesday, March 23, 2011

"ልብ ካላስተዋለ ዓይን ብቻውን አያይም"

በፍቅር ለይኩን (ከደቡብ አፍሪካ)
 
ዲያቆን ዳንኤል! ድንቅ ትረካ! ድንቅ እይታ፣ ጥሩ አስተውሎት ነው! ...ስለ ማየት ወይም ስለ እይታዎቻችን ሳስብ ብዙ ነገር በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ፤ አላውቅም ብዙዎቻችን ከአስተዳደጋችን ይሁን ወይም ከሌላ ምክንያት በአብዛኛው ጊዜ በፊለ ፊታችን ከተሰቀለው ነጭ ሰሌዳ ዓይናችን ለማየት የሚታደለው በነጩ ሰሌዳ ላይ ያለችውን ጥቁር ነጥብ እንጂ የሰሌዳው ነጭነት ወይም ብሩህነት አይደለም፤ ሁሉን አቀፍ ድምዳሜ (hasty generalization) እንዳይመስልብኝ እንጂ ለሕይወት ያለን የጨልምተኝነት አባዜም (spirit of pessimism) ከዚሁ ከዓይናችን ወይም ከአመለካከታችን መንሸዋረር የተነሳ እንደሆነ እገምታለሁ።

Tuesday, March 22, 2011

እነሆ አንድ ዓመት ሆነ


ይህ ጦማር (ብሎግ) አንድ ብሎ ከጀመረ እነሆ ዛሬ አንድ ዓመት ሆነ፡፡ march 22 ቀን 2010 ዓም በምድረ አሜሪካ ነበረ ይህ ጦማር የተፈጠረው፡፡ ከባለቤቴ ከጽሉ ጌች ጋር ከወር በፊት መከርን፡፡ ከወዳጄ ከኤፍሬም እሸቴ ጋር ቁጭ ብለን ሂደቶቹን ጨረስን፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ቁጭ ብዬ የመጀመርያዎቹን ጽሑፎች ለቀቅኩ፡፡
እነሆ እስከ ዛሬ 164 ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡ 75 ሀገሮች በላይ የሚገኙ አማርኛ አንባብያን ያነብቡታል፡፡ ከሁለት በፊት የወሩ አንባብያን ብዛት 100000 ደርሷል፡፡
ለዛሬ በዓሉን በማስመልከት ዐሉላ ጥላሁን በተባ ብዕሩ፣ ጠንከር ባለ አማርኛ የጻፈውን ላካፍላችሁ፡፡
                 

Monday, March 21, 2011

ዓይን


ወይዘሮ ሐረገ ወይን ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲህ የሚል ታሪክ ላከችልኝ፡፡
አንድ የአትክልት ቦታ የነበረው ሰው ነበረ፡፡ ሰውዬው የአትክልት ቦታው አስጠላውና ለመሸጥ ፈለገ፡፡ ከዚያም ወደ አንድ የታወቀ ባለ ቅኔ ዘንደ አመራ፡፡ «የአትክልት ቦታዬን መሸጥ እፈልጋለሁ፤ ገዥዎች እንዲመጡልኝ አንተ እባክህን ማስታወቂያውን ሥራልኝ፡፡ ነገር ግን እባክህ ያለውንም አታስቀር፣ የሌለውንም አትጨምር» ብሎ ጠየቀውና በዋጋ ተስማሙ፡፡ የአትክልት ቦታው ባለቤትም ለታወቀ ጋዜጣ የማስታወቂያውን ሂሳብ ከፍሎ ሄደ፡፡ ባለቅኔውም ወደ አትክልት ቦታው ሄዶ እየተዘዋወረ ሳይቀንስም፣ ሳይጨምርም አየው፡፡