Monday, February 7, 2011

የ7000 ዓመት የአያቶቻችን ቤት


የምሥራቅ ኢትዮጵያ እምብርት ወደ ሆነችው ድሬዳዋ የዘለቀ ሰው እምብዛም የማይጎበኘው፤ ነዋሪዎቿም የማይናገሩለት አንድ ታሪካዊ ቅርስ አለ፡፡ ቅርሱ የሚገኘው ከድሬዳዋ ከተማ ከከተማዋ ምሥራቅ 37 ርቀት ላይ ነው፡፡ መንገዱ የክረምት ጥርጊያ መንገድ ይመስላል፡፡ ምቾት ያለው መኪና ላልያዘ ሰው ወተት ጠጥቶ በዚያ መንገድ ቢጓዝ ተንጦ ተንጦ ቅቤ ይወጣዋል፡፡
ከመንገዱ መናጥ በላይ መንገዱን አስቸጋሪ የሚያደርገው የአካባቢው ሕፃናት ትራጂዲያዊ ትርዒት ነው፡፡ ሕፃናቱ መኪና ሲያዩ ከመሸሽ ይልቅ በቀጥታ ከአራቱም አቅጣጫ ወደ መኪናው ይመጣሉ፡፡ እነዚህ ሕፃናት ወደ መኪናው የሚመጡት በሌሎች ቦታዎች እንደ ተለመደው ተከትለው ለመሮጥ ወይንም ለመንጠላጠል አይደለም፡፡ ወደ ጎማው ውስጥ በመግባት ጎማውን ለመያዝ እንጂ፡፡ ያን ጊዜ ሾፌሩ ማድረግ ያለበት መቆም ብቻ ነው፡፡ መንገዱን ረዥም የሚያደርገውም እየቆምን መጓዛችን ነው፡፡
«ለገ ኦዳ» በመባል የሚጠራው ዋሻ ሰላሣ ሜትር ያህል የጎን ስፋት፣ ሦስት ሜትር ያህል የውስጥ ጥልቀት እና 12 ሜትር ያህል ቁመት አለው፡፡ ወደ ዋሻው ስትዘልቁ ምንም ነገር አይታያችሁም፡፡ ቀስ እያላችሁ ግድግዳዎቹን ማስተዋል ስትጀምሩ ግን ጥንታዊው ሰው ለመግባቢያነት እና የራሱን ታሪክ ለመመዝገብ የሳላቸው ሥዕሎች ይታዩዋችኋል፡፡
እነዚህ ሥዕሎች በዚያ ዘመን የነበሩትን እንስሳት፣ የሰው ልጅ በዚያ ዘመን ይሠራ የነበረውን ሥራ እና የዚያ ዘመኑ ሰው ተፈጥሮን እንዴት ያይ እንደነበር የሚገልጡ ሥዕሎች አሉ፡፡
በአካባቢው መጠነኛ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች የዋሻው ውስጥ ሥዕሎች 7000 ዓመታት ዕድሜ እንዳ ላቸው ይገልጣሉ፡፡ ሥዕሎቹ የሚያሳዩትም የጥንታዊውን ሰው አኗኗር መሆኑን ያመለክታሉ፡፡
የአካባቢው ሽማግሌዎች የዋሻው አካባቢ ጥንት ከተማ እንደነበረ ይናገራሉ፡፡ በተለይም «ጎዳ እኩቴ» «ትልቅ ማሠሮ» የተሰኘው ቦታ ጥንት የኖሩ የነበሩት ሰዎች ዕቃዎች ዛሬም በቁፋሮ ወጥተው እንደ ሚታዩ ይተርካሉ፡፡ «መጋላ ጋላ» «የግመል ከተማ» በተሰኘው ቦታ ላይም የሸክላ ውጤቶች በቁፋሮ እንደ ሚወጡ ነግረውኛል፡፡
በዚሁ አካባቢ «ጎዳ ቢፍቱ» «ጎዳ ጃዋ» «ጎዳ ከተባ» የተባሉ ሌሎች እስከ ሰባት የሚደርሱ ያልተዳሰሱ ዋሻዎች አሉ፡፡ በተለይም ጎዳ ቢፍቱ የተባለው ዋሻ እስከ ሁርሶ የሚደርስ መሆኑ ይነገራል፡፡
የለገ ኦዳ ዋሻ ሥዕሎች በአደጋ ላይ ናቸው፡፡ ዋሻውን ከሰው እና ከእንስሳት ንክኪ ለመጠበቅ የተቀመጠ ምንም ዓይነት አጥር የለውም፡፡ በዚህም የተነሣ የአካባቢው አንዳንድ ሰዎች ዋሻው ውስጥ እሳት በማን ደድ ሥዕሎቹ በጢስ እንዲጠፉ እያደረጓቸው ነው፡፡ ከብቶቻቸውን የሚጠብቁት ልጆችም ግድግዳውን በመላጥ የሰባት ዓመት ታሪክ እያጠፉ ይገኛሉ፡፡
እኔ እንደተመለከትኩት ለገ ኦዳ ዋሻ ሥዕሎች እየጠፉ በመሆናቸው ያለ ኬሚካል በፎቶ ግራፍ ለማንሣት አስቸጋሪ ሆኖብኛል፡፡ የሚገርማችሁ ነገር ግን ይህንን ዋሻ ከአደጋ ለመጠበቅ በአካባቢው ዋጋ አሥር ብር ብቻ የሚያወጣ የእንጨት አጥር ማጠር በቂ ነበር፡፡
የታሪክ፣ የአርኬዎሎጂ፣ የአንትሮፖሎጂ እና የሥነ ሥዕል ባለሞያዎች ሥዕሎቹ ጠፍተው ተረት ከመሆ ናቸው በፊት በመድረስ አስፈላጊውን ጥናት ቢያካሂዱ ስለ ኢትዮጵያ እስካሁን ያላወቅናቸውን ነገሮች ይነግሩን ይሆናል፡፡

14 comments:

 1. Dn Daniel, Egziabher yistilin.
  7000 years? Unbeleivable. It looks like this going to change our 3000 years Ethiopian history. What can we do to save it? let's discuss that and find a solution. It was also really funny when the guide shows you a picture and says that it was a colt. I loughed so hard so i just want to share. GOD BLESS!!! Atlanta

  ReplyDelete
 2. የጉዞ ማስታወሻዎችህ የጡመራህ ዋነኛ መገለጫዎች በመሆናቸው ሁሌም በትኩረት አነባቸዋለሁ፡፡ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ከሚቀርቡት ለየት የሚያደርጋቸው ደግሞ አራትዮሽ (4D) ይዘት ስላላቸው ነው፡፡ ጸሑፍ፣ምስል፣ፊልምና፣ምናብ (ቢያንስ የእኔ)የሚዋሃዱበት በመሆኑ፡፡ በዚህኛውም ሆነ ፎቶግራፍ በለጠፍክባቸው የጉዞ ማስታወሻዎችህ ላይ የተገነዘብኩትን ጉድለቶች አንድ ሁለት ልበልና አስተያየቴን ልስጥ፡፡
  ተጓዥ እንደመሆንህ እንደ ብዕርህ ሁሉ የፎቶና የፊልም መሣሪያዎችህ ከፍ ያለ የጥራት ደረጃን እንዲይዙ ቢደረጉ ጥሩ ነው፡፡
  1. High Resolution/HD የሚባሉት ዓይነት ቢሆኑ ጥርት ያለ ምስል ለማግኘት ይቻላል፡፡
  2. የቪዲዮ ካሜራ አቀራረጹ በጉዞ ወቅት መንገራገጭ የበዛበት ከመሆኑም በላይ በዋሻው ውስጥም የማያቋርጥ ንቅናቄ ነበረው፡፡ እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴ፣ ብዥታን ይፈጥራል (blurred, defocused and shak)፣ትኩረትን ይቀንሳል፣መልእክት የማስተላለፍ አቅም ያጥረዋል፡፡ እነዚህ ጉድለቶች ትንፋሽን በመቆጠጠርና(ፎቶ ለማንሳት) በዋናነት መቋሚያ (Tripod) በመጠቀም የሚወገዱ ስለሚሆኑ ወደፊት የተሻለ 4D እጠብቃለሁ፡፡
  መልካም ጉዞ ለማሰስ ወይም ወዳ’ዲስ

  ReplyDelete
 3. በጣም አሪፍ መረጃ ነው:: ይህን ሃብት እንዳይባክን ምን ማድረግ እንችላለን? ምናልባት የገቢ ማሰባሰቢያ ባንተ አደራጅነት ማድረግ እንችል ይሆን? .... የተለያየ ዋጋ ያላቸው ትኬቶች አዘጋጅቶ መሽጥም ራሱ 10,000 ብር ማስገኘት አያቅተውም - ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው እንዲሉ:: ባለፀጎቻችንንም ብንጠይቅ ይቺን ታክልሻ አይከብዳቸውም:: መንግስት መቼም አይታጠር አይልም - ቢታጠር ያገሬው ነዋሪ የሚጎልበት ነገር ይኖር ይሆን? የሆነ ሃሳብ ካለህ እኔን በbefeqe@yahoo.com ታገኘኛለህ::

  ReplyDelete
 4. የ7000 ዓመት የአያቶቻችን ቤት ....
  Well, What is the standard to measure the age of the cave paints? It makes some confusion when I compare the year against the human existance on earth. If we follow the Anthorpoligist theory then we may accept the figure b/c they claim that man has been existing on earth before millions years ago .But as religeous person it is difficult to believe the estimated figure.

  ReplyDelete
 5. Dn Daniel
  Its really interesting. May I suggest something which is not actually relevant to this post. If you get a chance it will be Good if you made studies about "orthodox christinaty in SNNP". Because the protestants are teaching these peoples saying EOTC belongs to northern part of Ethiopia. so pls take this in to account and let us read such history.
  Abiot ,oldenburg

  ReplyDelete
 6. i dont think it is important in defining our ethiopia.

  ReplyDelete
 7. Dear anonymous above, if you add 5500 years before Christ birth and 2003 years after Christ birth, I think it will be more than 7000. So don't get confused. Just believe.

  ReplyDelete
 8. Dn. Daniel, I wish "God will goes in-front of all your activities specially in the case of journey".

  ReplyDelete
 9. ጎዳ ኦኮቴ በኦሮምኛ (gooda Okkote) ትልቅ ማሰሮ ሳይሆን ማሰሮ ሜዳ በሚል ቢታረም፡፡ መጋላ ጋላ አሁንም በኦሮምኛ መጋላ (magaalaa) ከተማ ማለት ሲሆን ጋላ(ላልቶ ይነበባል) (gaala) ግመል ማለት ነው፡፡ አንድ ላይ ሲነበቡ የግመል ከተማ ይሰኛል፡፡ በአከባቢው በስፋት በሥራ እና በምግብነት አገልግሎት ከሚሰጡት ግመሎች የተነሳ ስያሜውን እነዳገኘ እገምታለሁ፡፡

  ReplyDelete
 10. Legeoda is not known before, even in Dire Dawa, it was launched during the Ethiopian Millanium. as one guys said the year(7000) is not well studied it is an estimation. to preserve this place i think it is not the problem of money rather it is the problem of commitment and lack of interest of the cultur and turisum bureau of the Dire Dawa region. they make it a one time work.
  from Dire Dawa

  ReplyDelete
 11. Dear anonymous above, if you add 5500 years before Christ birth and 2003 years after Christ birth, I think it will be more than 7000. So don't get confused. Just believe.
  ይህ ዋሻ የተሰራው የኖህ መርከብ ከመሰራቱ በፊተ ነውን? ከሆነስ እንዲት ሶዎቹ ወደዘህ ቦታ ሊመጡ እንደቻሉ ሊገባኝ አልቻለም ።
  ፍጥረት እንደገና መባዛት የጀመረው በኖህ መርከብ ውስጥ በተሳፈሩ ፍጥረታትና ሰዎች ይመስለኛል ። ይህ ደግሞ አዳም ከሞተ በሁአላ ነው የትፋት ውሃ የመጣው (7503-930) ስለዚህ የዋሻው እድሜ ላይ አጠራጥሮኛል ። ዝም ብለህ እመን ያልከው ወንድሜ እባክህ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ብትሰጠኝ?

  ReplyDelete
 12. ውድ ዲ/ን ዳንኤል - እዚሁ ድሬ ዳዋ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሄን የመሰለ ታሪክ ማወቅ ባለመቻሌ በራሴ እንዳፍር አድርገኸኛል፡፡ ለማንኛውም በቀረበው ፅሁፍ በጣሙን ረክቻለሁ፡፡ እግዚያብሔር ይባርክህ፤ እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባር!!

  ReplyDelete
 13. may be they are fossils....have you ever thought aboit this also????

  ReplyDelete
 14. ውድ ወንዲሜ ዳንኤል
  እስከዛሬ አልፎ አልፎ በቤተክርስቲናችን ዙሪ የምታስነብባቸውን መልእክቶችህን እና የተወሠነም ቢሆን እንዲሁም ወጎችህን አንብ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ የጉዞ ማስተዋሻዎችህን ሳነብ በጣም ተመቹኝ፡፡የምትገረም ምረጥ ታታሪ ኢትዮጵያዊነትህ ይቀጠል!

  ReplyDelete