ደኅና ሁኚ ማልታ፣ደኅና ሁኑ ወዳጆቼ |
እኔ እንዳየኋቸው ማልታዎች የሚመሰገን ብዙ ጠባይ አላቸው፡፡ ለሚሸጡላችሁ ዕቃ ታማኞች ናቸው፡፡ የሆነውን ብቻ ይነግሯችኋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ዕቃ የምትፈልግ ከሆነ ከእኔ ሱቅ ከምትገዛ ከእገሌ ሱቅ እዚህ ቦታ ብትገዛ ይሻልሃል ይላሉ ማልታውያን፡፡
እንደ ገጠር ባልቴት ወሬ የሚወድዱ ቢሆኑም ማልታውያን እህ ብለው ከሰሟቸው ምሥጢር የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ የውስጣቸውንም ሆነ የውጫቸውን ያወሯችኋል፡፡ በማልታ «አንዲት ሴት እስክታገባ፣ አንድ ወንድ ደግሞ ካገባ በኋላ ይሰቃያል« ይባላል፡፡
እንደ ገጠር ባልቴት ወሬ የሚወድዱ ቢሆኑም ማልታውያን እህ ብለው ከሰሟቸው ምሥጢር የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ የውስጣቸውንም ሆነ የውጫቸውን ያወሯችኋል፡፡ በማልታ «አንዲት ሴት እስክታገባ፣ አንድ ወንድ ደግሞ ካገባ በኋላ ይሰቃያል« ይባላል፡፡
ለማልታ ሴቶች ወንድ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ የወንዶች እጥረት አለ፡፡ እናም እስኪጋቡ ድረስ ሴቷ ወንዱን ትለማመጣለች፡፡ ሴቷ ብቻ ሳትሆን የሴቷ ቤተሰቦች ጭምር እስኪያገባት ድረስ ይከባከቡታል፡፡ ከጋብቻ በኋላ የቤቱ ንብረት እና ገንዘብ በሴቷ እጅ ይወድቃል፡፡ ወንዱ ገንዘቡን አምጥቶ ለሴቷ ያስረክብና በየጊዜው እያሰበች የምትሰጠው እርሷ ናት፡፡ ከዚያም በተራው እርሱ ማልቀስ ይጀምራል፡፡
በማልታ መንገዶች አሥር ሰው ካያችሁ ሰባቱ ሽማግሌዎች እና ባልቴቶች ናቸው፡፡ አገሪቱ የአረጋውያን ሀገር ናት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከማልታ መንገዶች በሠላሳ ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ከተሠሩ መደዳ ቤቶች በራቸውን ከፍተው ወጭና ወራጁን የሚያዩ የማልታ አረጋውያን ያጋጥሟችኋል፡፡
ለሁለት ሳምንት ያህል ስቀመጥ የፖሊስ መኪና ሳይረን እና የፖሊስ ግርግር ያላየሁባት ሀገር ማልታ ናት፡፡ ፖሊሶቹን ያየኋቸው ክብ ሠርተው ሲጫወቱ ነው፡፡ ሀገሪቱ የሰላም ሀገር ናት፡፡ መጀመርያ ከዲያቆን ምንዳዬ ጋር ወደዚህ ሀገር የመጣን ቀን ከአውሮፕላን ወርደን ሻንጣዎቻችንን በመያዝ በቀጥታ ወደ በሩ ስናመራ ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡
በአካባቢው ከየት መጣችሁ? ወዴትስ ትሄዳላችሁ? የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ውጭ ወጥተን እንኳን መውጣታችንን አላመንነውም ነበር፡፡ ለማልታዎች አገር ሰላም ነው፡፡
እስካሁን በብዙ ሀገሮች ስዞር እንደ ማልታ ከነ ሆድ ዕቃዋ ያየኋት ሀገር የለችም፡፡ እድሜ ለአሌክስ ትእግሥት «መላ» እያለ (በማልቲዝ «ይሁን» ማለት ነው) ይዞኝ ይጓዛል፡፡ እያንዳንዷ ቀን በከንቱ አላለ ፈችም፡፡ በጠዋት ተነሥተን ለጉብኝት እንወጣለን፡፡ አንዳንዴ ምሳ እንይዛለን፤ አንዳንዴ መንገድ ላይ እንበላለን፡፡ ማታ ለጉባኤ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንገባለን፡፡ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት እዚያ ቆይተን እንደ ገና ለኮርስ ወደ ትንሿ አዳራሽ እናመራለን፡፡ እዚያ ደግሞ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል እንቀጥላለን፡፡
ከተቻለ በትዳሩ መኪና፣ ካልተቻለም በቢጫማዎቹ (ማልታዎቹ ሲያቆላምጧቸው «የማር መልክ ያላቸው» በሚሏቸው» አውቶቡሶች ወደ ቤታችን እናመራለን፡፡ ቀን ቀን ከቻሉ የአምበሴ ባለቤት እና ጓደኛዋ የሠሩትን፤ ካልቻሉ ደገሞ ትኁቷ ሊዲያ ቀነኒሳን በሚያስንቅ ፍጥነት የምታዘጋጀውን፣ ዕድለኞች ከሆንንም ትዳሩ ጎምለል እያለ ያሰናዳውን እራት እንበላለን፡፡
ከዚያ ሁለቱ ለብሰው፣ ሦስቱ ራቁታቸውን ተቀምጠው በተደረደሩት ፎቴዎች ላይ ዘና ብለን የሀገር ቤት ጨዋታ እናመጣለን፡፡ በተለይም ደግሞ ዳዊት እና አምኃ (ቬራ) ካሉ ተስፋዬ ካሣ አልሞተም ያሰኛሉ፡፡ በዚያ ላይ አማኑኤል (አቡቱ) እና ትዳሩ ሲጨመሩበት ያለነው ማልታ ላይ መሆኑን እንረሳዋለን፡፡ አሌክስ ከሥር ከሥር ይቆሰቁሳል፤ ሊዲያ ትጨምራለች፤ ቶማስ ነገር ጣል ያደርጋል፤ ታሪኩ ከመጣ ደግሞ ዙሩን ያከርረዋል (ታሪኩ እጅግ የተዋጣለት የምግብ ባለሞያ ነው፡፡ እኔ እና ከስፔን የመጣው ቤቢ አድንቀንለታል)፡፡ ከዚያም ጨዋታው የቴሌቭዥን ሾው ይመስላል፡፡
በማልታ ሐበሾች ዘንድ፣ ፍቅር ይጋገራል፤ ፍቅር ይቀርባል፤ ፍቅርም ይበላል፡፡ ዘረኛነት እና ፖለቲካዊ ልዩነት ሜዲትራንያን ባሕር ገብተዋል፡፡ ኤርትራውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ለመለየት ለየት ያለ ጥናት ይጠይቃችኋል፡፡ እነዚህም ትግርኛ እነዚያም አማርኛ ያቀላጥፋሉ፡፡
የአማርኛም ይሁን የትግርኛ መዝሙር ከተዘመረ ሁሉም በእኩልነት ይሳተፋሉ፡፡ ጉባኤውን የሚመራው ኮሚቴም ከሁለቱም የተውጣጣ ነው፡፡ «አየዋለሁ አሁን ግን አይደለም» እንዳለው በለዓም የሁለቱን ሕዝቦች የፍቅር ውሕደት እናየዋለን፤ አሁን ግን አይደለም፡፡ የታለ ድንበሩ? ሰላም አስከባሪውስ የታለ? ድንበር ጠባቂ ወታደሮችስ የታሉ? ጦርነቱስ የት ገባ? ተላላችሁ ማልታ ላይ ስትሆኑ፡፡ እዚህ ቁስል የለም፡፡ ቢኖርም የሻረ ቁስል ነው፡፡ እዚህ ልዩነት የለም፤ ቢኖርም ውብ የሆነ ልዩነት ነው፡፡
የአማርኛም ይሁን የትግርኛ መዝሙር ከተዘመረ ሁሉም በእኩልነት ይሳተፋሉ |
y¥L¬ DRDR ²æC |
እዚህ የሚሰሙ ፊልሞች አሉ፡፡ ትራዤዲ፣ ኮሜዲ፣ ዶክመንታሪ፣ በያይነቱ ፊልም አለ፡፡ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሜዲትራንያ የተከናወኑ የሀገር ልጅን ታሪክ የያዙ ፊልሞች፡፡ ይተርኩላችኋል፡፡ መከራውን ወደ ሳቅ፣ ስቃዩንም ወደ ቀልድ ለውጠው ያቀርቡላችኋል፡፡ ቀስ እያልኩ የማካፍላችሁ ብዙ ታሪኮች አሉኝ፡፡
ማልታን ተሰናብቼያት እየወጣሁ ነው፡፡ ትዝታዋ መቼም አይለቀኝም፡፡ አዲስ አበባን እንኳን የማልታን ያህል የማውቃት አይመስለኝም፡፡ ሽሮ መልክ ያላቸው ሕንፃዎቿ፤ እዚህም እዚያም እንደ ከዋክብት ብቅ የሚሉት አብያተ ክርስቲያናቷ፡፡ በሚገባ የተዘጋጁት ሙዝየሞቿ፡፡ ተጎብኝተው የማያልቁት መዳረሻዎቿ፤ «ቬራ ተኝቶ በድምፃቸው ስንት ቁጥር አውቶቡስ እንደሆኑ ይለያቸዋል» እያለ መብራህቱ የሚቀልድባቸው አውቶቡሶቿ፡፡ እንደ ተሰለፈ ወታደር በንቃት የተደረደሩት የመንገድ ዳር ዛፎቿ፤ «ኦልራይት» እያሉ የሚተላላፉት መንገደኞቿ፤ ዙርያዋን የከበባት የሜዲትራንያን ባሕር፤ ከዘመነ ፊንቄያውያን እስከ አውሮፓ ኅብረት የሚደርሰው ታሪኳ፤ የማይረሱ ናቸው፡፡
ደኅና ሁን |
አንድ ቀን ደግሜ እንደምመጣ፣ ያለበለዚያም ደግሞ በሚሄዱበት ሀገር እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይህንን ጉዞዬን ያመቻቹትን እና ያሳኩትን አባ ቴዎድሮስ ዘስታቫንገርን፣ አባ አብርሃም ዘኦስሎን፣ ጌታቸው ዘኦስሎን እግዜር ይስጥልኝ እላለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ ሁለት ሳምንት ሙሉ ሥራውን ትቶ አብሮኝ የከረመውን አሌክስን፣ አጅግ እጅግ አመሰግነዋለሁ፡፡ አምላክ ዋጋውን ይክፈለው፡፡
ደኅና ሁኚ ማልታ፣
ደኅና ሁኑ ወዳጆቼ
ፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ፣ ጀርመን
የተራብነውን ፍቅር ያጣነውን መተሳሰብ መደጋገፍ ያገኘህባት አገር የተባረከች ትሁን ምሣሌ የሚሆን እንዳይጠፋ
ReplyDeleteዳኒ ምን ተመኘሁ መሰለህ ምናለ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ ኢትዮጵያ በሆነ እና የሰማችሁት ያያችሁት የእግራችሁ በረከት ለሃገሬ ደርሶት በበደላችን ያጣነውን የተነጠቅነውን ፍቅር ሰላም አንድነት የማንነት ክብር ቤተ ክርስትያን በልብሳችን ሳይሆን በውስጣችን ደምቃ የምትኖርበት በሆነልን አልኩ ግን አይቀርም አንድ ቀን ጉልበታችን ሳይሆን ልባችን በፈጣሪያችን ፊት በወደቀ በተንበረከከ ጊዜ
በሰላም ግቡ
ከአቡዳቢ
Welcome! We wish you a nice stay. Your journey was interesting in Malta, in Germany.... I am not sure...anyway try to make your heart strong.
ReplyDeleteTHANK YOU DANI
ReplyDeleteante sile malta bizu neger alik ignas sile ante min inbel be iwnet Dn be bizu botawoch yastemarachewn timihirtoch semchalew neger gin izi Malta yastemarew betam leyet yale ina hiywet ye mikeyr new sewu timihrtun betam kemewdedu yetenesa inkuwan christian muslimoch metew yetekafelubet guba'e neber.AHUNIM IZI MALTA BALUT WENDMOCH INA IHITOCH SIM IGZI'ABHER YISTILIN BILENAL.beteley yemechereshawa ken mechem anresatim minale Dn Mindaye benore iskinil dires.
Igzi'abher indante aynet agelgay yabzalin
BEHEDKBET HULU DEG DEGU YIGTEMIH
God Bless all.
ReplyDeleteየሱዳን በርሃ፣ የሊቢያ ምድረ በዳ፣ የሜዲትራንያን ባህር እነዚህ ሁሉ ተስፋ የሚያስቆርጡ ሃሞት የሚያፈስሱ ዳግሞ በሕይወት መገኘት የማይሞከርባቸው እጅግ አሰቃቂ፣አስከፊ የስደት ታሪኮች መሆቸውን በተደጋጋሚ በጋዜጣና በመጽሔት ያነበብኩ በመሆኑ ማልታውያንን በዚህ መልኩ አልሳልኳቸውም፡፡
ReplyDeleteምከረው እምቢ ካለ ... የሚለው የአበው ብሂል ዛሬም ይሰራልና እንደወርቅ ተፈትነው ያለፉት እነዚያ ኢትዮ-ማልታውያን በጣም አስደሰቱኝ፡፡ በምናብ ባህሩን ቀዘፍኩ፣ ፊንቂያውያን ትዝ አሉኝ፤ ሰሞኑን ያነበብኳቸው ዜና መዋዕልህ በዚህ ጽሑፍ በአንደዚህ ዓይነት ክስተት የሚባል ፍጻሜ መደምደሙ አስገርሞኛል፡፡ ያጣነውን ፍቅር፣ ከዘር የጸዳ ማንነትን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሁበት በመሆኑ፡፡
አቤት ደስ ሲል!
በፍቅር ቅራሪ፣ በፍቅር አተላ
ጠቁሮ በከሰለ፣ ደፍቆ በተመላ
በአሮጌ አቅማዳ፥
የምትኮፈሰው ወይን ጠጅ ልትቀዳ
አሮጌው አይችልም አዲሱን ሊሸከም
ይልቅ ቅዘፍና ወደ ማልታ ትመም፡፡
ማልታውያን፥ በጣም በጣም መስጣችሁኛል፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡
መልካም ጉዞ ለዳንኤል፡፡
dani u make me cry!!! rejeme edemiee!
ReplyDeletewow!!! Interesting May God Give You The Strength!!!Thanks For Our Fathers,Brothers and Sisters who help you out in your jouny.
ReplyDeleteThanks For sharing as allways
ቃለ ህይወትን ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፤ ዲ/ን ዳንኤል በእውነት እግዚአብሔር ይስጥልን እናመሰግናለን፡፡ ያየኸውን እንድናይ ስለምታደርገንና መልካሙን ሁሉ ስለምታደርግ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ፤ የቅድስተ ቅዱሳን የእመቤታችን አማላጅነት አይለይህ፡፡
ReplyDeleteyou our brothers! what you did is unthinkable even words are extremely weak to evoke my internal feelings. you are some but has done a lots of things that we all know only as a history. i have one wish we need to have thousands of you (Dn.Daniel and some others)who are devoted for our church. then what can i say more than may the peace and grace of GOD be unto you forever. God bless us all!
ReplyDeleteእኛም አብረንህ ማልታ ከረምን እኮ....። አሁን እኔም ሆድ ባሰኝ.... ስትሰነባበት እዛ ያለው እስኪመስለኝ። መሰነባበት እንዴት ይከብዳል..?።እንግዲህ ማልታ በር ከፍታለች። ወደፊት የሚቀጥሉት ጉዞዎችህን በጉጉት ነው እምጠብቀው። በሰላም ከቤተሰብህ ይቀላቅልህ። የሰላም መንገድ ያድርግልህ። ( ሰማርያ )
ReplyDeleteእኔም እንደሰማርያ ልክ "ያብጽሐነ" ሲዘመር ያለዉ ስሜት አይነት ተሰማኝ!!! ግን ደግሞ ከእንግዲህ በሁዋላ ሁሉንም በአካል በአንድ ቦታ ማግኘት አይቻል! በሰማይ ቤት ካልሆነ በቀር፣ አምላክ በሰላም ሁላችንንም ሳያጎድል በቸርነቱ ለቤቱ ያብቃን እንጂ!!!
ReplyDeleteminaleb tinish bitikoy noro maltan wededkat beteley yezeregninetu guday zero degree lay mehonu des alegn yemaytasebew tedergo sitay des yilal beteley ke eritrean wendmochachin ga anid honew [bezi guday lay sefa argeh bititsif legnam timihrt yihonenal indet indezi lihonu indechalu beteley MILANO lalenew] igna be 1 language megbabat alichalinm.
ReplyDeleteDANI IGZIABHER ZEMENHIN YIBARK
ye igzi'abher selam le ante yihun wendmachin Dn
ReplyDeleteye malta guzoh betam arif neber minale tinish bitkoy noro lelam bizu neger tinegren neber le gizew ye amlakachin fekad yihen yahil kehone yihun bilenal
gin ine sile malta mawek mifelgew malta yalu ye huletum abatoch[kahnat]indet ina min bilew bitselyu new hizbun be 1 lib adrgew Igziabhern indiyamesegin yaderegut.yihin betemelekete legnam timihrt indihonen sefa adrigeh tsafilin beteley Milano lalenew orthodoxoch mirt astemariwochachin lihonu yichilalu.
YIHIN YEMESELE MELKAM ZENA SILASEMAHEN INA SILAKAFELKEN BEMECHERESHA KEN IGZIABHER MELKAMUN KAL YASEMAH
ye igzi'abher selam le ante yihun wendmachin Dn
ReplyDeleteye malta guzoh betam arif neber minale tinish bitkoy noro lelam bizu neger tinegren neber le gizew ye amlakachin fekad yihen yahil kehone yihun bilenal
gin ine sile malta mawek mifelgew malta yalu ye huletum abatoch[kahnat]indet ina min bilew bitselyu new hizbun be 1 lib adrgew Igziabhern indiyamesegin yaderegut.yihin betemelekete legnam timihrt indihonen sefa adrigeh tsafilin beteley Milano lalenew orthodoxoch mirt astemariwochachin lihonu yichilalu.
YIHIN YEMESELE MELKAM ZENA SILASEMAHEN INA SILAKAFELKEN BEMECHERESHA KEN IGZIABHER MELKAMUN KAL YASEMAH
February 25, 2011 6:06 PM
Word verification
Kale hiwot yasemalin Dn Daniel.
ReplyDeleteApostolic journey. You are blessed. ..to be chosen by God to do just this is a ablessing. What's next for you, Ethiopia or some other nation? we will be waiting. Emebetachin kehulachin gara tihun. AMEN!!! Atlanta
እኔም ማልታ ያለሁ መሰለኝ ፡ስለ ከተማዋ አገላለፅህ ይመስጣል።
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክህ።
ሰላም ማልታዎች፡
ReplyDeleteየኃይማኖታችሁ ፍሬ የሆነው ፍቅራችሁ እጅግ ያስደንቃል። እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር ዓላማ አለውና በርቱ… የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔርም ከናንተ ጋር ይሁን!
ለዲ/ን ዳንኤልም ጸጋዉን ያብዛልህ፤ ከሚመጣውም ፈተና ይጠብቅህ። የሚቻል ከሆነም በየቦታው የምትሰብካቸውን ስብከቶች በጡመራህ ውስጥ አንድ አምድ ክፈትለትና ብታካፍለን ከምታስበው በላይ በብዙዎች ዘንድ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። እንዲሁም ያጽናናል…
በዚህ በኩልም ልታግዙት የምትችሉ ካላችሁ መክሊታችሁን መወጣት ነውና የበኩላችሁን አድርጉ። ለሁሉም የእመአምላክ ምልጃ አይለየን!
ዳዊት
በወንድማችን ውስጥ የምትሰራው የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ሆይ!እናመሰግንሀለን።እርዳው፡፡እኛንም በተማርነው እንድንጠቀም እርዳን።ለዘወትር..........።ማልታ በልባችን ውስጥ ታትማ ትኖራለች።
ReplyDeleteDani, may God bless you and your family. Do you you know what I observe? In such challenged situation, we Ethiopians love each other. No Ethiopians no Ertherians, no north no south and neither east or west. Look Italy, kenya, Uganda, Egypt, Juba. As your observation, and mine too we love eachother. Dani, Im surprised, do you have any information that we have been cursed in our generation? Dani, your journey help us to see ourselves. We should learn from this journey.
ReplyDeleteGOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOD
ReplyDeleteBYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYE
DANIEL KIBRET
No words to express your journey.what will be the next.God bless you & your family. Yoseph zedebremitmak
ReplyDeleteDANI IGZIABHER AGELGILOTIHN YIBARK BENEBEREN GUBA'E BE ANTE INA BE BE MINDAYE BETAM DSTEGNOCH NEBERIN KEZI BEHALAM TSELOTACHIHU AYLEYEN.
ReplyDeleteIGZIABHER KENANTE GA YIHUN
D/n Dani enante hedu ene ke maltawoch gar ekoyalehu. be blessed.
ReplyDeleteHailemeskel
Moz-maputo
come and enjoy the best worship in malta.soon or later i will go to malta
ReplyDeleteI Agree with this statment from brother Dawit.
ReplyDeleteየሚቻል ከሆነም በየቦታው የምትሰብካቸውን ስብከቶች በጡመራህ ውስጥ አንድ አምድ ክፈትለትና ብታካፍለን ከምታስበው በላይ በብዙዎች ዘንድ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። እንዲሁም ያጽናናል…
በዚህ በኩልም ልታግዙት የምትችሉ ካላችሁ መክሊታችሁን መወጣት ነውና የበኩላችሁን አድርጉ። ለሁሉም የእመአምላክ ምልጃ አይለየን!
I hope you will do this D/N Daniel sele betekirstiyanachin bizu neger memar enechilalen ebakihin sibketochun be video kediteh ezihu letifilin please please please.
Maltawoch endet yetadelachihu nachihu! Dani, minewu be frankfurt sitalif ye maltan bereket tal bitaderigibin noro. Egziabiher rejim edemen yadilih! Weladite Amilake tila kelela tihunih!
ReplyDeleteke Germen
How lucky you are!!!!!!!!!!!. Serving those who are thirsty of love,God, truth......
ReplyDeleteI wish I could just like you. free service.............................,
mekuanint
አብረን ማልታን ዞርን እናመሰግናለን
ReplyDeleteዋው ውድ ዳንኤል ለመልካሙ ስራህ እግዛብሄር አሁንም ይባርክህ
ReplyDeleteብዙ ሀበሻ ባለበትና በምቾት ባለበት ሀገር ላይ እንኳን ኤርትራና ኢትዩፕያ ኢትዩፕያውያኑም ተስማምተው መኖር ያልተቻለበት ሁኔታ አለ የነዚህ ውድ ማልታውያን ሀበሾች ፍቅር ደስ ይላል አሁንም ፍቅር ይብዛላቸው
ለምን እንደሁ እንጃ እኔም ማልታን አብሬ የተሰናበትኳት መሰለኝ ባቃት ምን ልሆን ነው ዋው
ReplyDelete