Monday, February 21, 2011

ከፋዘር ፓውል ቦርግ ጋርበጥንታዊው እና ቢጫማ መልክ ባለው የማልታ አውቶቡስ ተሳፍረን ወደ ቫሌታ እየሄድን ነው፡፡ የማልታ ሕንፃዎች ከአራት እና አምስት ፎቅ የማይበልጡ፣ መልካቸው ደብዛዛ ቢጫ ወይንም ቢጫማ መልክ ያለው ነው፡፡ ይህም ከተማዋን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ውበቷን እንዳታጣ አድርጎታል፡፡ የሕንፃዎቿ አሠራር ከሀገሪቱ ጥንታዊነት እና ቅርስነት ጋር የተስማማ፣ ነገር ግን ዘመናዊነቱን የጠበቀ ነው፡፡
ይህንን የማልታ የሕንፃ አደራደር ሳይ የጎንደር፣ የሐረር፣ የአኩስም እና የላሊበላ ሕንፃዎች እና ቤቶች ይታሰቡኛል፡፡ ከከተሞቹ ባህል፣ ታሪክ እና ክላሲካል የሕንፃ ጥበብ ጋር የማይሄዱ፤ ተመጣጣኝ ምግብ እንዳጣ ልጅ አንዱ ከፍ አንዱ ዝቅ ያሉ፡፡ የቀለም ኤግዚቢሽን እንዲያሳዩ የተፈረደባቸው ይመስል ዝብርቅርቃቸው የወጣ ሆነው ይታዩኛል፡፡
 ባለ ሥልጣኖቻቸው እንደሆኑ ብዙ ጊዜ ውጭ ሀገር ሄደው አይተው መጥተዋል፡፡ ዕውቀቱን ቀስመው ሊተገብሩት አልቻሉም እንጂ፡፡ እስኪ የሚሻል ከሆነ ከተሞቹን ራሳቸውን ውጭ ሀገር ወስደን እናሳያቸው፡፡
የማልታ አውቶቡስ
ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል /St. Paul’s shipwreck church/ ገብተን ከሮም የመጣውን ተረፈ አጽሙን እና ከተሠዋበት ዓምድ ላይ የተቆረጠውን ተረፈ ዓምድ ተመለከትን፡፡ ያስጎበኙን ፓውል ቦርግ የተባሉ የካቶሊክ ቄስ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን ካስጎበኙን በኋላ ከእርሳቸው ጋር ሻሂ እየጠጣን ወግ ጀመርን፡፡
እንዴት ነው የማልታ ክርስትና፣ ሰዎች እንደ ጥንቱ ቤተ ክርስቲያን ይመጣሉ ወይ? ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡
ከሌላው ቦታ እኛ ትንሽ ይሻላል፡፡ ያም ቢሆን ግን እንደ ጥንቱ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመን ሰዎች ለመዝናናት ነው ትልቁን ቦታ የሚሰጡት፡፡ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ ዓይነት እየሆኑ ነው አሉኝ፡፡
(አቡነ ሺኖዳ ትዝ አሉኝ፡፡ ክርስቲያኖችን በብዙ መንገድ ይከፍሏቸዋል CEO, SO, CO እያሉ፡፡ CEO የገና እና የትንሣኤ ክርስቲያኖችን ነው፡፡ Christmas and Easter Orthodox, SO በሰንበት ብቻ የሚመጡ ክርስቲያኖችን ሲሆን Sunday Orthodox, CO የሚሏቸው ደግሞ ለአንዳንድ ሥነ ሥርዓቶች ብቻ የሚመጡትን ነው Ceremonial OrthodoxÝÝ)
ለምን ይመስልዎታል? ስል ጠየቅኳቸው፡፡ 
እንደ እኔ እምነት የመጀመርያው ሰይጣን ከኛ በላይ ስለ ሠራ ይመስለኛል፡፡ ጥንት አባቶቻችን ከሰይጣን በላይ ይሠሩ ስለነበር ለእርሱ ዕድል አይሰጡትም ነበር፡፡ አሸንፈውት ነበር፡፡ ማርከው እንጂ ተማርከው አያውቁም ነበር፡፡ አሁን ግን እኛ ሰነፍን፡፡ እኛ ስንሰንፍ ደግሞ ሰይጣን በረታ፡፡ ስለዚህ የበረታው ማረከብን፡፡
ሁለተኛው ደግሞ እኛ ለአግዚአብሔር የምንመች አልሆንንም፤ ተመልከት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሆነውን፡፡ ቀደምት ክርስቲያኖች ስለ ሃይማኖት አባቶቻቸው ቅድስና እና ጥንካሬ፣ ደግነት እና ጽናት እየሰሙ ነው የኖሩት፣ በኛ ዘመን ግን ልጆች ስለ ሃይማኖት አባቶቻቸው ኃጢአት እና ስሕተት ሆኗል የሚሰሙት፡፡ በዚህ ላይ ሚዲያው ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ ሌሎች ምንም ቢያጠፉ ዝም የሚለውን ቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እንደ ትል የመሰለች ነገር ከተገኘች ግን እንደ ግመል ያገዝፋታል፡፡ ይህንን እያወቅን እኛም መታረም አልቻልንም፡፡ ሕዝቡን ከተአምራት ወደ ሐሜት ወሰድነው፡፡ ይህ ይመስለኛል ምክንያቱ፡፡
ለነገ ምን ተስፋ ይታይዎታል ታድያ?
አንድ መፍትሔ የያዘ አዲስ ትውልድ እየመጣ ነው፡፡ አዲሱ ትውልድ ከኛ በጣም ይሻላል፡፡ አንድ ኃያል Energetic የሆነ ትውልድ እየመጣ ነው፡፡ በኛ ኃጢአት የማይደናበር ትውልድ፡፡ ቁጭት እና እልህ የተሞላ ትውልድ፡፡ ዓለምን የናቀ በዓለም ያልተናቀ ትውልድ እየመጣ ነው፡፡ ይሄ ትውልድ ቤተ ክርስቲያንን የሚታደጋት ይመስለኛል፡፡ በኛ ዘንድ ክርስትና እምነት መሆኑ ቀርቶ ማኅበራዊ ፍልስፍና ሆኖ ነበር፡፡ ወንጌልን ወደ ማኅበራዊ ችግር መፍቻ መንገድ ቀይረነው ነበር፡፡ ይህ ትውልድ ግን ወደ ቀድሞ ቦታው እያመጣው ነው፡፡
ሃይማኖቱን ማወቅ ይፈልጋል፤ ታሪኩን ማወቅ ይፈልጋል፤ አባቶቹ በሚያደርጉት ነገር ይናደዳል፤ የመፍትሔ ሃሳብም ያቀርባል፡፡ አይቶ ለማረም ይፈልጋል እንጂ አይቶ አይበረግግም፡፡ እኔ ይህንን ትውልድ ያስነሣው እግዚአብሔር ይመስለኛል፡፡
ግን አሁን በዓለም አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮች ዘንድ የሚታየው ሥርዓት አልበኛነት፣ በምእመኑ ዘንድ የሚታየው ግዴለሽነት፣ ኃጢአት እንዲህ ሲነግሥ ማየት አያስፈራም?
ያስፈራል እንጂ፡፡ ይህንን ሳስብ የፖፕ ቤኔዲክት 16 ረድእ የሆነ አንድ አፍሪካዊ መነኩሴ የነገረኝ ትዝ ይለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ አንሥቼ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም ምን አለኝ፡፡ «ይህንን ዓይን ያፈጠጠ ችግር ያመጣው እግዚአብሔር ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ሊያጸዳ ነው፡፡ ከዚህ ልቅነት በኋላ መቅሰፍት አለ፡፡ እሥራኤል ሥጋ ተመኝተው የጥጋብ ልቅሶ ባለቀሱ ጊዜ እግዚአብሔር እስኪሰለቻቸው ምድሪቱን በሥጋ ሞላት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን መቅሰፍት መጣ፡፡ አሁንም ከዚህ ምድሪቱን ከሞላት ኃጢአት በኋላ መቅሰፍት የሚጠብቀን ይመስለኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ትሆናለች» ብሎኛል፡፡ እኔም ይህንን ማመን ጀምሬያለሁ፡፡ በጭራሽ ቤተ ክርስቲያንን ለኃጢአተኞች አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ነገር ግን እስኪሰለቸን ድረስ ዝም ይላል፡፡ ከዚያም ያጠራዋል፡፡
የጐዞ ደሴት ሰዎች ዕንቁላላቸዉን ሸጠው ስለ ሠሩት «የዕንቁላሉ ቤተ ክርስቲያን» ተባለ
አንዲት መርከብ በውኃ ላይ በመጓዟ እና በውኃ በመከበቧ የሚመጣባት ችግር የለም፡፡ ሌላው ቀርቶ ውኃው በመናወጹ እንኳን ችግር እንጂ አደጋ አያጋጥማትም፡፡ አደጋው የሚመጣው የባሕሩ ውኃ ወደ መርከቢቱ መግባት ከጀመረ ነው፡፡ በዓለም ላይ ልዩ ልዩ ዓይነት አስተሳሰቦች፣ እምነቶች፣ ፍልስፍናዎች፣ አካሄዶች እና አመለከከቶች መኖራቸው ምንም ችግር የለውም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በዚህ መካከል መጓዟ አደጋ ኣያመጣም፡፡ ፈተና ሊኖርባት ይችላል፤ አደጋ ግን አይኖርባትም፡፡
በሐዋርያት ሥራ ምእራፍ 27 ላይ እንደ ተገለጠው ቅዱስ ጳውሎስ የነበረባት መርከብ የተጎዳችው ማዕበሉ በመነሳቱ አይደለም፡፡ ባሕሩ እና ማዕበሉ መርከቢቷን ለአሥራ አራት ቀናት ያህል ፈትነዋታል፡፡ መርከቢቱን የጎዳት ግን ማዕበሉን መቋቋም አቅቷት ውኃው ወደ ውስጧ በመግባቱ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ የምትወድቀው እነዚህ የዓለም አስተሳሰቦች ወደ ውስጧ መግባት ከጀመሩ ነው፡፡ በውጭ እንደፈለጉ ይሁኑ፤ ይፈትኗትም፡፡ ወደ ውስጥ ግን መግባት የለባቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ ኖኅ መርከብ በእነርሱ ላይ እየተንሳፈፈች አሸንፋ መጓዝ ነው ያለባት፡፡
አባቶቻችን በደማቸው እና በአጥንታቸው፣ በጉባኤያቸው እና በመጽሐፎቻቸው፣ በጸሎቶቻቸው እና በቆራጥነታቸው ውኃው ወደ መርከቢቱ ሲከላከሉት ነበር፡፡ ዐቅሙም ነበራቸው፡፡ እኛ ግን የቻልንበት አይመስለኝም፡፡ እንዲያውም የመርከቧን አንዳንድ አካል አስወግደን ውኃው እንዲገባ በማገዝ ተባባሪ ሆነናል፡፡
ዛሬ ዛሬ ያለ ችግር የባሕሩ ውኃ ወደ መርከቧ ሲገባ እየታየ ነው፡፡ አደጋውም እርሱ ነው፡፡»
አሉና ፋዘር ፓውል ቦርግ ራሳቸውን ይዘው አንገታቸውን ደፉ፡፡ እኔም አብሬያቸው፡፡

14 comments:

 1. +++
  Yetwededk wendmach endat alh? Le Malta gozoh yerdah Amlakachn Kiberna mesgan yegbaw aberh eganm wesedkn Qhy!

  አባቶቻቸው ቅድስና እና ጥንካሬ፣ ደግነት እና ጽናት እየሰሙ ነው የኖሩት፣ በኛ ዘመን ግን ልጆች ስለ ሃይማኖት አባቶቻቸው ኃጢአት እና ስሕተት ሆኗል የሚሰሙት፡፡ በዚህ ላይ ሚዲያው ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ ሌሎች ምንም ቢያጠፉ ዝም የሚለውን ቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እንደ ትል የመሰለች ነገር ከተገኘች ግን እንደ ግመል ያገዝ ፋታል

  Yehnen neger bezemta lenalfew aygebam bertten median metagel yasfelga andande yesewn besot qencheb eyadergu Abatochn maward enquan lealsenanew yestnawenm yawekal ena Betikristian yemister temert bet nat ena betchale meten LEBEGO ENQUAN BEHON ZEM MALETEN memar anzenga Gorebt laye yedrsew egagm lay yedersaln anzenga. Ketoronto akbari betseboch +++

  ReplyDelete
 2. Kale Hiwot Yasemalin. Dn Daniel
  What a wise father he is. This is a warning and encouragement for us all. we all should listen and do something about our church. I hope the new generation he is talking about will be fruitful and save our church from all the evils with God's help. AMEN. Dn Daniel we really thankfull for your effort. God Bless You!!! Atlanta

  ReplyDelete
 3. thanks a lot Danie it is a good and clear lesson to Kahinat, followers and m. kidusan. until when we r carrying this pop ? i think tolerating him more than this is allowing kahinat division, followers disintegration and tiredness,and allowing the water to enter in to the ship. why don't we all oppose together and overthrow him away b/c it will be difficult to fetch the water out of z ship after once inundated. " ene gena behaymanot lemadeg dik dik yemil sew seitanin liwaga or benesu wusane sikosil linur? " people also started loosing confidence on every priests and this is a danger for the country. we hav to unite and do som returning point. Egziabher hulem Yasadigih

  ReplyDelete
 4. ጤና ይስጥልኝ ዲ/ን ዳኒ!

  "አባቶቻቸው ቅድስና እና ጥንካሬ፣ ደግነት እና ጽናት እየሰሙ ነው የኖሩት፣ በኛ ዘመን ግን ልጆች ስለ ሃይማኖት አባቶቻቸው ኃጢአት እና ስሕተት ሆኗል የሚሰሙት፡፡ በዚህ ላይ ሚዲያው ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ ሌሎች ምንም ቢያጠፉ ዝም የሚለውን ቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እንደ ትል የመሰለች ነገር ከተገኘች ግን እንደ ግመል ያገዝፋታል።" እኛም አገር የቸገረን ይህ ነው።

  ሌላው፤
  "ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ የምትወድቀው እነዚህ የዓለም አስተሳሰቦች ወደ ውስጧ መግባት ከጀመሩ ነው፡፡ በውጭ እንደፈለጉ ይሁኑ፤ ይፈትኗትም፡፡ ወደ ውስጥ ግን መግባት የለባቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ ኖኅ መርከብ በእነርሱ ላይ እየተንሳፈፈች አሸንፋ መጓዝ ነው ያለባት፡፡"
  በጣም የሚገርም አባባል ነው። የሚደንቅ እውነት!!!

  ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ!!!

  ReplyDelete
 5. «..እስኪሰለቸን ዝም ያላል..» ይገርማል ...እንዴት ያለ ሀይለ ቃል ነው። አንድ በር ላይ ቆሞ የሚያንኳኳ ሰው። በር ባይከፈትለት ያ ሰውዬ ለጊዜው እንጂ የሌለው።ቤቱ ነው እዚያው ይገኛል። እውነትም ታዲያ የእዚአብሔር ዝምታ....ሥራውንያቆመ እክሲመስለን ወይም በቤቱ የሌለ እስኪመስለን ድርስ በቤቱ ላይ ጉልበተኛ፣አዛዥ ሆነን የቤተክርስቲያንን መብት ለመጠበቅ የስጋ ሀይል የምንጠቀም፣እልህ፣ስድብ፣ ጥላቻ፣ቂም፣.....ምኑ ቅጡ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ ለሚሰራው ሥራ እኛ ደግሞ ዛሬውኑ ካላስተካከልኩ ዛሬውኑ ዘርቼ ካላጨድኩ አሁኑኑ..እያልን ይምንሰራው የሀጢአት ናዳ.....ስለ እግዚአብሔር ቤት ብላችሁ ብትሳደቡ፣ብትጠላሉ፣ብትናከሱ፣ብትለያዩ ችግር የለውም የሚል ትምህርት ከየት እንደተማርን ግራ እስኪገባኝ ደረስ እየጨነቀኝ ነው። ....ሀዋርያት ቤተክርስቲያንን ሲሰሩ ተሰድበው፣ተዋርደው፣ነገር ግን በትህትና እና በፍቅር ንግግራቸው እንጂ በጉልበት አልነበረም ሰውን የማረእኩት። ሲሰደቡ በፍቅር አሸንፈው፣ሲጠሉእነሱ አፍቅረው....ብቻ የኛ እልከኝነትና ጉልበት ከየት የተማርነው እንደሆን .... ትልቅ ቁምነገር ወስጤ ቀረ....እግዚአብሔር እኪሰለቸን ይታገሳል።በእግዚአብሔር ትዕግስት የምንመለስበት የንሰሀ ልቦና ይስጠን። ይህንን ቃል እንዳሰማኸን የሕይወትን ቃል ያሰማችሁ።(ሰማርያ)

  ReplyDelete
 6. ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አላገኘሁም። ሕዝ22፥30
  ጡመራው ባልከፋ ለመርከቢቱ ግን ምን ይፈይዳል?

  ReplyDelete
 7. its all amazingly correct.if only Europe had understood this during the middle ages where all kind of changes in the church started appearing along side the renaissance.artists sculpt and paint a naked body on the streets and then use their art in the church for the body of saints.now when a believer goes to the church,is he going to pray in front of a saint's paint or admire the secular art of it?so with out even realizing,the believer is surrounded by water sinking him to the ocean.in our church we don't have sculpture or a realistic image of saints.which,aside from the dogmatic point of view,is good for a believer's spirituality,in a sense it helps to block away a secular art(the water) from sinking in.our church has an art that does not affect spirituality which is accredited to our church fathers or is a work of God that kept us in a better spirituality when the rest of Europe was sinking down.
  now in our time,recording technology, modern musical instrument and the idea that "the church is hindrance to civilization",etc are making way to for the water to sink in.one such sign is the debate over our church songs.

  ReplyDelete
 8. ቃለህይወት ያሰማልን! መቼም ታላቁ አቢይ ጾማችን እየመጣ አይደል እንደ አቡነ ሺኖዳ አባባል CEO, SO, CO ከመባል ወጥተን ወደቤታችን እንመለስ፡፡ እስቲ አባቶቻንን ቁጭ ብሎ ከመዉቀስ እኛም ሄደን በድለናል ንስሓ ይስጡኝ፤ ያስተምሩኝ እንበል:: የዳኒ እንግዳ የሆኑት አባት ‹እኛ ለእግዚአብሔር የምንመች አልሆንንም› እንዳሉት ሰዉ ሁሉ መጃመሪያ እራሱን ነዉ መመርመር ያለበት፡፡ እስቲ በዚህ ጾማችን ‹ቀደምት ክርስቲያኖች ስለ ሃይማኖት አባቶቻቸው ቅድስና እና ጥንካሬ፣ ደግነት እና ጽናት እየሰሙ ነው የኖሩት› እንደተባለዉ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ስለአባቶቻችን በመስማት እኛ መሪያችንን እናስተካክል ቅዱሳን ኮምፓሳችን ናቸዉና ወደ ትክክለኛዉ ትራክ እንግባ ታላቁ አባት አቡነ ሽኖዳ ሌላም የሚሉት አላቸዉ “በዐቢይ ጾም ሕይወቱን ያልቀየረ ክርስቲያን በሌሎች አጽዋማት እንዴት ይቀየራል?” እኔ፤ አንተ አንቺ ወደ ህይወት ጎዳና ስንመለስ ዉሃዉ (ሐሰተኛዉ) መግቢያ ያጣል፡፡ አለበለዚያ እኛም የመርከቧን አንዳንድ አካል አስወግደን ውኃው እንዲገባ በማገዝ ተባባሪ ሆነናል፡፡ ዛሬ ዛሬ ያለ ችግር የባሕሩ ውኃ ወደ መርከቧ ሲገባ እየታየ ነው፡፡ አደጋውም እርሱ ነው፡፡»

  ReplyDelete
 9. ሰላም ዲን ዳንኤል፡-ከ`ፋዘር´ ጋር ያደረከው ቃለምልልስና የሰሞኑ ጉብኝቶችህ ብዙ ነገሮችን አስተማረኝ ነገሮችንም ወደ እኛው እምጥቼ እንዳያቸው ረዳኝ። ይህ ሁሉ ባንተ ነውና እግዚአብሔር የልፋትህን ዋጋ ይክፈልህ።
  የ `ፋዘር´ የወደፊት እይታ መልካም ነው። አሁን በተግባር አውሮፓ ላይ የማየው ግን የሳቸው ሃሳብ ምኞት ይመስለኛል። ከመቶ አመት በፊት የሉተር አስተሳሰብ እየጠነከረ ሲመጣ፤ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት በተለይ በጀርመን ያሉ ሉተራውያን የቤተ ክርስቲያኒቱን ምዕመናን ወደ አዳራሽ ጠራረገው ሲወስዱባቸው እንደ አማራጭ ወስደውት የነበረው ይህ በብዛት በተከሰተበት አካባቢ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሉተራውያን ገብተው ስብከት እንዲሰጡ መፍቀድ ነበር። ሲፈቅዱላቸውም የሚፈልጉትን የሐይማኖት አመለካከት ማራመድ እንደሚችሉ ነገር ግን ቤተክርሲያኒቱ ውስጥ ያሉ ስዕላትን እንዳይነኩ በውስጥ ገብተው ብቻ አገልግሎታቸውን እዲፈጽሙ የሚል ነበር። ይህ የማመቻመች ስራ መጨረሻ ላይ የተምታታበት ትውልድ እንዲፈጠር አደረገ። አሁን ያለው ትውልድ በተለይ ወጣቱ `ፋዘር´ እንሚሉት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚባል መኖሩን የሚጠራጠርና በራሱ ዛቢያ የሚሽከረከር ነው። በዚሁ በጀርመን አገር አሁን ያሉት የካቶሊክ ዋናው ፓፕ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉበት የነበረ ካቴደራል በአቅራቢያው ላለ የዩኒቨርሰቲ የመመረቂያ ጊዜ አዳራሽ ና የኤግዚብሽን ማዕከል ሆኖ ነው የሚያገለግለው። ይህ ነገር በጣም ብዙ ስለሚገርመኝ አንዱን አብሮኝ የሚማር ጀርመናዊ ጓደኛየን አንድ ጥያቄ ጠየቅሁት። ለምን እግዚዘብሔር የለም ትላለህ የሚል ጥያቄ ነበር። እሱ የመለሰልኝ መልስ እንደኛ እንደ ጀርመናውያን ለእግዚአብሔር የተገዛ ትውልድ በምዕራቡ አለም አልነበረም። ነገር ግን በሁለተኛው አለም ጦርነት ጀርመን ድምጥማጧ ስጠፋ ዝም አለ። እውነት ቢኖር ንሮ ይህ አያደርግም ነበር። የጠፋችውንም አገር እንደገና የገነቧት ቤተሰቦቻችን ሌት ተቀን ሰርተው ነው። እናም እኔ የማምነው በአምላክ ሳይሆን በስራ ነው የሚል መልስ ነው። ቤተሰቦቸም ያስተማሩኝ ስለ ጠንክሮ መስራትና ራስን ስለ መቻል እንጂ ስለ ጽድቅና ኩነኔ አይደለም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ።
  ይህ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትምህርት ይመስለኛል። ካቶሊኮች ከመቶ አመት በፊት በሰሩት ስህተት አሁን የተምታታበትና እግዚአብሔርን ሊቀበል ያልቻለ ትውልድ እንዲፈጠር ያደረጉ ይመስለኛል። አሁንም እኛ ከ100 ዓመት በፊት እንደተፈጠረው በተለያየ ጥቅም ምዕመናኑን ወደ አዳራሽ የምንነዳ ለመጭው ትውልድ ዋና ተጠያቂዎች ነን። እስኪ ወደ ራሳችን እንመለስ እውነት አላማችን ሰማያዊት እየሩሳሌም ከሆነች በብዙ ማህበራዊ ችግሮች ቋፍ ላይ ያለውን ሕዝባችንን አናምታታው። ወደ ውስጥ ፍላጎታችን አምላካችንን አምጥተን እንደ አይሁዳዊያን አንዘባበትበት። የሐዋሪያት አስተምህሮ ይህን አይደለም የሚነግረን። ጊዜያዊ ለሆነው ምድራዊ ጥቅማችን ብለን በራሳችንና በሌሎች ጥፋትን አንስራ። የሰይጣን ስራ ካሸነፈን ተምበርክከን አምላካችንን እንለምነው:፡ እስከ ትዕቢታችን ገብተን መቅደሱን አንበጥብጠው። ሕጉን መጠበቅ ካቃቀተንና ካልሆነልን ከውጭ እናልቅስ ጊዜው ሲደርስ እርሱ ይጠራናልና። በተለይ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የሌሎቹ ጉዳይ ማስፈጸሚያ አንሁን። ይህን ካላደረግን አሁን እነዳሉት የምዕራብ አለማት ክርስቲያኖች ተቅበዝባዥ እንዳንሆን አሰጋለሁ።
  አምላካችን ከእንዲህ ያለ ጥፋት ለመውጣት ልጆቹን በዚህ ዘመን ስለላስነሳልን ክብር ምስጋና ይግባው።

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንኤል እንደምን ከርመሃል?!

  ፋዘር ያለውን እውነታ ነግረውናል። የቤተ ክርስትያናችን ጉዳይ ስለሚያሳስበኝ "የእግዚአብሔር ዝምታ እስከ መቼ ነው?" እያልኩ ሁልጊዜ ራሴን እጠይቀዋለሁ። ለራሴ ከምሰጣቸው መልሶች የመጀመሪያው፣ ፋዘር እንዳሉት እስራኤላውያን "እግዚአብሔር ከዓለት ውኃ ማፍለቅ ይችላልን? ማዕድንስ ከሰማይ ማውረድ ይችላልን?" እያሉ ሁሉን አድራጊ፣ ፈጣሪ የሆነውን አምላክ ሲፈታተኑት፣ የመላዕክትን ምግብ ከሰማይ አውርዶላቸው፣ የሰማያት ወፎችንም አዝንቦላቸው እስኪተርፋቸው ድረስ ካጠገባቸው በኋላ መቅሰፍቱን ከሰማይ አስነስቶ አለቆቻቸውንና ካህናቱን እንደ ገደለ፣ አህዛብን ግን እንደሰበሰበ በመዝሙረ ዳዊት ላይ የተገለጸው ታሪክ በኛም ቤተ ክርስትያን ላይ ሊደግመው አስቦ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።
  በሁለተኛ ደረጃ የማስቀምጠው፣ የኛም ሆነ ከኛ በፊት የነበረው ትውልድ እግዚአብሔርን የከዳ ስለነበረ እሱን አምነን በሱ ፈቃድ እና መንገድ እስክንጓዝ፣ እጃችንን ወደሱ እስክናነሳ ድረስ ሊቀጣንም ሊሆን ይችላል እላለሁ።
  በሦስተኛ ደረጃ፣ በቤተ ክርስትያናችን ውስጥ እንደ ፓትርያርኩ ዓይነት አዋኪ ሰው ባያስቀምጥ ኖሮ ስለ ቤተ ክርስትያናችንም ሆነ ስለ ኃይማኖታችን ለማወቅ ጥረትም ሆነ ጉጉትም ሊኖረን እንደማይችል ተረድቶ ያደረገውም ሊሆን ይችላል ብዬ ራሴን አሳምነዋለሁ። ክፉ ጎረቤት ራስ ያስችላል...እንደሚባለው
  በአጠቃላይ መርከቧን፣ የኛ መስለው ነገር ግን ከኛ ያልሆኑ "የኃይማኖት" አባቶች ናቸው የሚያናውጧት። እግዚአብሔር "በቃችሁ" የሚላት ቀን እንዴት ናፈቀችኝ! እስኪ በጸሎት እንበርታ!

  ReplyDelete
 11. Dear Editor and Readers alike,

  Thanks for the info. I should have to say that there has never been a time without the True Faith (Orthodox) nor will it be. However, our Lord has said in the gospel that: 24በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም። (ሉቃስ 13:24)- “Strive to enter through the narrow door. For many, I tell you, will seek to enter and will not be able." (Luke 13:24).

  That is it!

  Tazabiw

  ReplyDelete
 12. ሃይማኖቱን ማወቅ ይፈልጋል፤ ታሪኩን ማወቅ ይፈልጋል፤ አባቶቹ በሚያደርጉት ነገር ይናደዳል፤ የመፍትሔ ሃሳብም ያቀርባል፡፡ አይቶ ለማረም ይፈልጋል እንጂ አይቶ አይበረግግም፡፡ እኔ ይህንን ትውልድ ያስነሣው እግዚአብሔር ይመስለኛል፡፡this is reality.
  Thank's D/n Dani
  Hailemeskel
  Moz-Maputo

  ReplyDelete
 13. Kale hiwot yasemaln memhr. Emnet tesfa fqr enezih sostu tsentew ynoralu fqr gn ybeltal kehulu. And i think that is where we should focus, contemplate and work at.

  ReplyDelete
 14. Yes, yemayfera ena Yemaydenegit tiwuld yasfelgal.

  ReplyDelete