Sunday, February 20, 2011

የቅዱስ ጳውሎስ ተረፈ አጽም


የቅዱስ ጳውሎስ የቀኝ እጁ አጥንት በነሐስ በተሠራ የእጅ ምስል ውስጥ
ማልታ ሃይማኖታዊ በረከቶች ሁለቱ በቫሌታ የቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል /St. Paul’s Shipwreck church/ የሚገኙት ተረፈ አጽሙ እና የተሠዋበት ዓምድ ቁራጭ ናቸው፡፡
በቤተ ክርስቲያኑ በቅዱስ ዮሴፍ መቅደስ ውስጥ በመንበሩ ላይ የቅዱስ ጳውሎስ የቀኝ እጁ አጥንት በነሐስ በተሠራ የእጅ ምስል ውስጥ ይገኛል፡፡
ይህንን ተረፈ አጽም 1823 እኤአ ለማልታ ሕዝብ የሰጡት ቪንሴንዞ አሎይስዮ ቦናቪያ /Vincenzo Aloisio Bonavia/ መሆናቸውን በቤተ ክርስቲያኑ የሚገኙ መዛግብ ይገልጣሉ፡፡
ከዚህ ቦታ አለፍ ስትሉ ደግሞ ሌላ ሃይማኖታዊ በረከት ታገኛላችሁ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን አስደግፎ የተሠዋበት ዓምድ ቁራጭ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የተሠዋው በዚያን ጊዜ ከሮም ከተማ ውጭ በነበረውና ዛሬ ባለ ምንጩ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን በተሠራበት /Church of San Paolo alle tre Fontane/ ቦታ ላይ ነው፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንገቱን አስደግፎ በሠይፍ የተቆረጠበት ዓምድ ይገኛል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን አስደግፎ የተሠዋበት ዓምድ ቁራጭ
 1818 ማልታ ውስጥ ቸነፈር ተከስቶ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ የካቴድራሉ ካህናት ሕዝቡን በማገልገል ላሳዩት ትጋት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ፖፕ ጲየስ ሰባተኛ በግንቦት 1818 እኤአ ይህንን ግማደ ዓምድ ለቤተ ክርስቲያኑ ሰጥተዋል፡፡
ይህ ዓምድም ከተረፈ ዐጽሙ ጋር የቅዱስ ጳውሎስን ሰማዕትነት እየመሰከረ ይኖራል፡፡
በረከቱ በሁላችን ላይ ይደር፡፡

12 comments:

 1. Amazing story. Its really life of eternity. Dani, Amilake hawariat yitebikihe.

  ReplyDelete
 2. The Journey of MALTA it is very GOOOOOOOOOOOOOOOOOOOOD to me because for me MALTA is a very small island according to geography study in Mediterranean sea b/n north Africa and south Europe I don't now about like this a very rich in history of CHRISTIANITY.
  D/N Daniel you are open the history of Malta in a good way.
  The life of Saint Paulo for the CHRISTIAN people a very & very ....................................................
  GOD BLESS YOUR WORK PLEASE CONTINUE.

  ReplyDelete
 3. thanks to God and le dn danielim kale hiwot yasemalin.kezih belay min malet yichalal etsub dinik yehone neger negeren gin enezih betumera yewetu tsihufoch bemetsihaf bekirib ken biwetu
  enesu haymanotawi,hagerawi,na economiawi tekemeta alachewna beteley lechristianoch astemarwoch nachewna
  MAY GOD BLESS U

  ReplyDelete
 4. it is so wonderful ....

  ReplyDelete
 5. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ህይወትክን እና ዘመንክን ይባርክልህ! ለመስራት ያሰብከውን ሁሉ ከፍፃሜ ለማድረስ ቸርነቱ አይለይህ፡፡ በጣም ደነቀኝ! ክርስትናን እና መለያዋን ሃይማኖትን እንደ ሸቀጥ በለወጠች ምድረ አውሮፓ በዚህ መልክ ማየት! ጌታችን፣እመቤታችንና ቅዱሳን ስዕላት!!! ግን ምን አይነት ክርስትና ነው? ተዋህዶ? ከ5 እህትም አማቾች/ኦሬንታል ቤተ ክርስቲያናት የሚመሳሰል ወይስ የተለየ? ተለየስ ትክክለኛ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚያደርስ ክርስትና አስተምሮ ነውን? ታሪክ ከሰራህ አይቀር በዚሁ ብዥታችንን ብታጠፋልን ደስተኛ ነኝ! በአገልገሎትህ ሁሉ ድንግል ማርያም አትለይህ! በእውነት በጣም በዙ ስራ እንደሚጠበቅብን ስላሳየህ ለሌሎቻችን ሁሉ በዚህ ረገድ አርዕያ ሆነሀል፡፡

  ReplyDelete
 6. Kalihiwot yasimalin

  ReplyDelete
 7. ግብረ ሐዋያትን በዘመናችን የሆነ ክስተት እስኪመስለን ድረስ የቅዱሳንን ገድል እና ትሩፋት አሳያችሁን እኮ! ክርስትናን የቄጤማ መስክ ላይ የተንፈላሰሰ ጉዞ እና ከገድል እና ከትሩፋት የተነጠለ ቅምጥል ኑሮ አስመስለው ለሚሰብኩ ሃሳውያን እግዚአብሔር ያቆያቸው ህያው ምስክሮች ናቸው እና ያያችሁትን እና የሰማችሁትን ሳታልፉ አስኮምኩሙን! ዲያቆን ዳንኤል ጸጋውን አምላክ ያብዛልህ፡፡ ዲን ምንዳዬ ምነው ‹‹እየበሉ እየጠጡ ዝም…›› ሆነ ነገሩ! ወይ መዝሙርህን አሰማን አልያም ዳንኤል ያየውን እኔም አይቻለሁ እያልክ መስክር እንጂ…
  በበረከቱ ትረፍርፋችሁ

  ReplyDelete
 8. አሜን አሜን። በረከቱ በሁላችን ላይ ይደር።ለናንተም ፀጋውን ያብዛላችሁ(ሰማርያ)

  ReplyDelete
 9. ወንድማችን ዲ. ዳንኤል የብርሀነ ዐለም ቅዱስ ጳዉሎስ በረከት በላይህ ይደር፡፡ መቼስ ከዚህ የዘለለ ምን ማለት ይቻላል፡፡ አዉሮፓዉያን በተለይ ቅዱሳንን የሚያናንቁትና ኦርቶዳክሳዊት ቤተክርስቲያናችንን እናድስ ባዮቹ ምነዉ ይህ ሁሉ መልካም ነገር አልታያቸዉ አለ? ክርስትናን ከነትዉፊቱ ያስተመረችን ቅድስት ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችን ያንተን ትምህርትና መጻህፍት በናፍቆት ለማንበብ በመቻላችን የምንዳዬን መዝሙር የምንሰማ በመሆናችን ምንኛ የታደልን ነን ህዳር 12 2003 በአዲሱ ሚካኤል ያስተማርከዉ ትምህርት ታወሰኝ በቅዱሳን አጽም ላይ የተመሰረተች ቤተክርስቲያናችንን ባለቤቱ ይጠብቅልን “እናድስ” ባዮችን ደግሞ ወደልቦናቸዉ ይመልስልን፡፡ እናንተን ደግሞ ቃለህይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 10. I can't see the pictures. Please help me.

  ReplyDelete
 11. D/n Dani kale hiwot yasemalen.

  be ewenet be krestena eminet yefeterege yene kidus paulos amilak yekeber yemesegen amen !!!
  Hailemeskel
  Moz-maputo

  ReplyDelete
 12. wow wow bro thank so much i enjoy st paul story May GOD Bless u forever!!!

  ReplyDelete