Friday, February 18, 2011

የቅድስት አጋታ ካታኮምብ


እነሆ የማልታ ደሴት ጉብኝታችንን እንደ ቀጠልን ነው፡፡
ቅድስት አጋታ ካታኮምብ ንመበር ላይ የተሳሉ የርግብ ሥዕሎች፣
በመጀመርያዎቹ የክርስትና ዘመናት ክርስቲያኖች ከሮማውያን መከራ ለመደበቅ፣ ለጸሎት እና ለመቃብር ይጠቀሙባቸው የነበሩ የምድር ሥር ዋሻዎች ካታኮምቦች ተብለው ይጠራሉ፡፡
እነዚህ ካታኮምቦች በሜዲትራንያን ዙርያ ባሉ ሀገሮች በሰሜን አፍሪካ እና በአውሮፓ የተለመዱ ናቸው፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን ክርስቲያኖቹ አምልኮ የሚፈጽሙበት፣ የሚኖሩበት እና በኋላም የሚቀበሩበት ቦታ ይቸግራቸው ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ ከከተማ ውጭ እምብዛም በማይፈለግ ቦታ፣ ከምድር ሥር ዋሻዎችን በመፈልፈል ይጠቀሙ ነበር፡፡ ከእነዚህ ካታኮምቦች አንዱ በማልታ፣ ራባት ከተማ የሚገኘው የቅድስት አጋታ ካታኮምብ ነው፡፡
ጥንታውያን ክርስቲያኖች ያረፉ ክርስቲያኖችን በማሰብ ዝክር ይቀምሱበት የነበረው ሰፊ ትሪ የመሰለው ነገ
 ቅድስት አጋታ በጣልያን ሲሲሊ ደሴት የነበረች ቅድስት ናት፡፡ በንጉሥ ዳኪዮስ ዘመን (249 - 251 ዓም) ከንጉሡ እና ሊያገባት ከፈለገው ከሲሲሊ ገዥ ከኩይንታንየስ አምልጣ ወደ ማልታ መጥታ ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ ይህንን ካታኮመብ ለጸሎት ትጠቀምበት እንደ ነበር ማልታውያን ይተርካሉ፡፡
ጥንታዊ መሠዊያ
 አጋታ ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ ሲሲሊ ተመልሳ ጥር 28/29 251 ዓም በሰማዕትነት ዐርፋለች፡፡
በዚህ ቦታ ላይ የጥንታውያን ክርስቲያኖች መቃብር፣ የጸሎት መቅደስ እና ሥዕሎች ይገኛሉ፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ እና የቅድስት አጋታ ሥዕሎች፣ የክርስቲያኖችን ተስፋ ለመግለጥ የተሳሉ የር ሥዕሎች፣ በትርጓሜ መጽሐፋችን ጳልቃን የሚላቸው የፔሊካን ሥዕሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሥዕሎች ቀደምት ክርስቲያኖች ከቅዱሳን ሥዕሎች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ያሳያሉ፡፡
የቅድስት አጋታ ሥዕል
 ከሁሉም የገረመኝ በኢትዮጵያውያን ሰዓልያን ዘንድ በብዛት የሚዘወተረው እና በአውሮፓ ሥዕሎች ላይ የሌለው እመቤታችን ጌታን ስታጠባ የሚያሳየው ጥንታዊ ሥዕል ነው፡፡ የዚህ ሥዕል ጉዳይ ጠለቅ ያለ ጥናት የሚያስፈልገው ይመስለኛል፡፡
እመቤታችን ጌታን ስታጠባ የሚያሳየው ጥንታዊ ሥዕል
 ሌላው አስደናቂው ነገር ጥንታውያን ክርስቲያኖች ያረፉ ክርስቲያኖችን በማሰብ ዝክር ይቀምሱበት የነበረው ሰፊ ትሪ የመሰለው ነገር ነው፡፡ በኛ ቤተ ክርስቲያን ያለውን የተዝካር እና የዝክር ሥርዓት ጥንታዊነት ያየሁበት አጋጣሚ ነው፡፡

16 comments:

 1. ሰላም ዳኒ፡ ከጊዜ በሃላ የቅዱሳን ሥዕሎች ና ... ወደቤተክርስቲያን ሰርገው ገብተዋል ብለው ባለማወቅ የሚከሱ፤ ከዚህ ብዙ ትምህርት ይወስዳሉ ብዬ አስባለው። እኔም ተምሬአለው። እግዚሃብሄር መንገደህን ሁሉ ይባርክ።

  ReplyDelete
 2. Dn.dani kalehiwet yasemalen !

  ReplyDelete
 3. በአዋሳ ሌሎች ቤተክርስቲያኒቱን ይንዳሉ አንተና ወንድማችን ዲ. ምንዳዬ ደግሞ እኛን ታንጻላችሁ፡፡ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ብድራቱን ይክፈላችሁ፡፡ ለበለጠ መረጃ (http://www.eotc-mkidusan.org/) ይጎብኙ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 4. ETSUBE DENKE!!! "Bekeme Semayne Kemahu Re'ene"

  ReplyDelete
 5. ዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ፡ በዙ ነገር እያሳየከን ነው። መልካም ቆይታ።

  ReplyDelete
 6. Dani, wonderful visit. It will connect and make international our church's hertages through further study. You show the way for our professional researchers. Yebetekristian Amilak dikamihn waga ayasatabih.

  ReplyDelete
 7. Engdih min enilalen??? Ye kidusan Amlak Kidus EGZIABHER rejim edime ke mulu tena gar yistilin. We Ethiopians are really lucky b/s God has given us you who knows what actually we need!!! If you were not there from where do we get all the information you are feeding us???? We are getting such incredible and spiritual historical issues just being at our home with out any hardship.
  God bless you!!!! Dn. Daniel

  ReplyDelete
 8. እግዚአብሔር አምላክ ሁልጊዜ ከናንተ ጋር ይሁን! አንተን እና የተዋህዶ ቆራጥ ልጆች የሠጠን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ለሁላችሁም ፀጋውን ያብዛላችሁ የአገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክ የእመቤታችን፣የመላዕክት፣ የሰማዕይታት፣ የሀዋርያት፣ የቅዱሳን፣ የፃድቃን አማላጅነታቸውና ጥበቃቸው አይለይን፡፡ አሜን!!!

  ReplyDelete
 9. ዲ/ን ዳንኤል ቃልሕይወት ያሰማልን ፤ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህን ፡፡ አሜን!!

  ReplyDelete
 10. selam lehulacheu betam yigeremal Addisu ahun ye awassan lijochen min asterahe tosachewen yizhe hed enesu yewengel gebere nachew lib yesetachew yebtekereseteyanen lijoch kemabarer kemesdeb kemekefafel egziooo

  ReplyDelete
 11. Kale hiwot yasemalin Dn Daniel.
  Will you please tell us what religion these people are practicing aroud these places you are visiting. Is it Catholicism or Greek Orthodox? God Bless you all!!! Atlanta.

  ReplyDelete
 12. ምዕራባውያን የሚመኩበትን ሥልጣኔ አንድ እፍኝ ሰጥተው የማያውቁትንና የሌሉበትን እነርሱ ግን አለንበት የሚሉትን ሃይማኖት ተብዬ በአካፋ እየዛቁ እንደ አፍዴራ ጨው ይከምሩብናል፡፡

  የሚገርመኝ አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው በተሃድሶአዊ ስብከት ሃራራ የሚያፋሽኩት ወዳጆቻቸው ኢሉሚናቲ በረቀቀ መንገድ ዲያብሎሳዊ ዓላማውን ለማግኘት ሃይማኖት የሚመስለውን ነገር ሳይቀር መጠቀሚያው እያደረገ መሆኑን አያውቁትም፡፡

  ሃይማኖትማ ይኸው፡፡ ተረት ነው ትውፊት ቅብርጥሶ እያሉ ደረቅ ውሸት በማስተጋባት ሳይሆን ያልነጠፈውን አሻራ በአፍም በመጣም እንዲሉ፤ እንዲህ ሲቀርብ ወደ ልቡና መመለስ በጥቡና ማስተዋል የሚሻል ይመስለኛል፡፡

  በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያ ጥንታዊነትም ሆነ በቀናው መንገድ ላይ ያለመካዘነፍ እየተጓዘች መሆኑን የሚያሳየው ሥዕላቱ አንዳንዶች እንደሚሉት በዘፈቀደ የተፈበረኩ አለመሆኑን ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. ቬኔሲያ ትረካን እና ሌሎች ስለ ካታኮምብ...ስለዚያ ዘመን ክርስቲያኖች የጻፍካቸውን ሥነ-ፅሁፎች(ልብወለድ) ሳነብ በምናቤ የሳክኳቸው... እነዚያ የምድር ውስጥ ዋሻዎች በደብዛዛው በህሊናዬ ሥህል ስስላቸው ነበር። ዛሬ ከቦትው ላይ ሆነህ ፡፡እውነተኛውን ስፍራ አሳየኸን። እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛላችሁ። (ሰማርያ)

  ReplyDelete
 14. kale hiwot yasemalin dn daniel beewnetu tarikihin ewek endatihon menafik yemibalew ababal zar gebagn. lekas yan hulu yetenegeren neger ewunet new?
  dany lifatih fire yemiyafera endhon eytemegnhugn yehin hulu neger hulum sew magnet laychil silemichil bekirb ken bemetshaf bitawetaw melkam new elalehu.
  GOD bless u,Ur life and work
  DINGIL KANTE GARA TIHUN

  ReplyDelete
 15. min endemele balawokem huleam gin amelakea amesegenalehu selemin bibale ye manibebe fiker endiyaderebegne seladeregegne dero maletim befit computerean yemikefetewo facebook lemetekem bicha neber balelem endeziyawo neber ahun gin mejemeriya ayemeroyeam tatocheam keteta yemiyamerut wodezihu blog newo egziabhear yesetelene tariakchenen awoken be eminet endenetsena esu yeredan kalehiwot yasemalen!!

  ReplyDelete