Tuesday, February 22, 2011

ሐል ፋር የመጠለያ ጣቢያ

የመጠለያ ጣቢያው ውስጡ በኮንቴይነር እና በአረጁ ድንኳኖች የተሞላ ነው

በሱዳን በረሃ ተጉዘው የሰሐራን በረሐ እንደ ግመል ያቋርጣሉ፡፡ ረሃቡ፣ ጥማቱ በትግል እና በወኔ ይታለፋል፡፡ በየመንገዱ መኪና ሲበላሽ መቆሙ፣ ከፖሊሶች ለመደበቅ በየተራራው ሥር ከአንድ ቀን እስከ ለሁለት ሳምንት ያለ ምግብ መቀመጡ፤ በየቀኑ ብር ጨምሩ ከሚሉ አሻጋሪዎች ጋር መጨቃጨቁ ታለፍና ሊቢያ ይገባል፡፡
ከሊቢያ ፖሊሶች ተደብቆ፤ በማይታወቅ ቤት ውስጥ ከርሞ፣ በሌሊት ጀልባ ላይ ወጥቶ በሜዲትራንያን ባሕር ላይ ጉዞ ይጀመራል፡፡ በሕይወት እና በሞት መካከል እየተጓዙ፣ ከተሰበረ ኮምፓስ ጋር እየታገሉ፤ ልምድ በሌለው ካፒቴን እየተመሩ፤ በእግዚአብሔር ቸርነት ከባሕር አውሬ ተርፎ ማልታ ይገባል፡፡
እሥር ቤቱ ዙርያው በግንብ እና በሽቦ የታጠረ ነው
ማልታ ላይ ደግሞ በፖሊስ ተይዞ መጀመርያ ሐል ፋር እሥር ቤት detention center ከዓመት እና ከሁለት ዓመት በኋላ ሲወጡ ደግሞ ወደ ሐል ፋር መጠለያ የድንኳን ካምፕ ይገባል፡፡ እሥር ቤቱ ዙርያው በግንብ እና በሽቦ የታጠረ ሲሆን አንዳንዶች እየዘለሉ፣ ሌሎች ዘመናቸውን ጨርሰው ወጥተው በአሁኑ ጊዜ ምንም አበሻ በውስጡ የለበትም፡፡
የመጠለያ ጣቢያው ውስጡ በኮንቴይነር እና በአረጁ ድንኳኖች የተሞላ ነው፡፡ ኮንቴይነሮቹ በቅርብ እንደ መጡ ሰምቻለሁ፡፡ ድንኳኖቹ ግን ራሳቸው እርጅናቸውን ይመሰክራሉ፡፡ በተለይም በዚህ ያረጀ ድንኳን ውስጥ አጥንት ድረስ በሚገባውና «ያገሬ ብርድ ማረኝ» በሚያሰኘው የማልታ የክረምቱ ብርድ እንዴት ሆኖ ሊኖርበት እንደሚችል መድኃኔዓለም ይወቅ፡፡
በአሁኑ ጊዜ እዚህ መጠለያ የሚኖር አበሻ የለም፡፡ ሁሉም ጥለውት ወጥተው በየሥራቸው ተሠማርተዋል፡፡ እኔ ግን የታሪካችን አካል ነውና በቪዲዮ እና ፎቶ አስቀርቼዋለሁ፡፡
እንዲህ ተሰቃይተው እና መከራ ተቀብለው እዚህ ማልታ የደረሱት ሁሉ በአንድ ነገር ያስገርሙኛል፡፡ ሁሉም ለወላጆቻቸው እና ለእኅት ወንድሞቻቸው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ያዩትን መከራ ሳያዩ እዚያው በሀገራቸው ሊረዷቸው ደፋ ቀና ይላሉ፡፡ እንዲህ በመከራ ደርሰው ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ይልካሉ፡፡ ከዚህ በላይ ምን ደግነት አለ? የሚልኩት ገንዘብ እኮ የላብ ሳይሆን የደም ዋጋ ነው፡፡


13 comments:

 1. አባግንባር ከፍሎሪዳFebruary 22, 2011 at 4:30 AM

  ውድ ዳንኤል በጣም ኣሳጠርከው::ይህ የባህር ኃየሎቹ ዜና መሆኑ ነው፤ በቀላሉ ሲታወስና "ማሽላ ሆዷ እያረረ" በሚባለው የብሶት ትረካችንና አነጋገራችን ሲወሳ ማለት ነው:: እንጂ የእነርሱ ብሶት እና መከራስ ተነግሮ አያልቅም:: ከዚህ ሁሉ አልፈው ደግሞ ለኃይማኖት ያላቸው ቅንነትና ታዛዥነት እንዳንተ ቦታው ላይ ቆሞ ላስተዋለ ሰው እውነት ለመናገር በራሱ ከባድ የተግባር ትምህርት ነው:: ልክ ገጠራማው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምታየው ሰው ሁሉ ዝቅ ብለው ሲታዘዙልህ፤ ለሃገሩ ባዕድነት እንዳይሰማህ የሚያደርጉልህ መስተንግዶና የሚያሳዩህ ወንድማዊ ፍቅር ሁለም በልብ ላይ ተጽፎ የሚቀር ነው:: ስለዚህ እነዚህ ወገኖቻችን ቢጻፍላቸው ቢተረክላቸው ያንሳል:: የህን ያህልም ለእኛና መሰሎቻችን በማስተዋወቅህ መድኃኔዓለም ይስጥህ እያልኩ እስቲ ከእነርሱ ኋላ ሊቢያ ስለቀሩት አንዳንድ መረጃ ማግኘት ከተቻለ ጠይቃቸው፤ ምክንያቱም ዛሬ ሊቢያ " ቀን ደርሶ አምባ ሊፈርስ" ነውና::

  ReplyDelete
 2. ይህን ጽሑፍ የሚያነብ ሰው “ማዕበሉ ወደ መርከቢቷ እንዲገባ ያደረገው ማን ነው?” ከሚለው ይልቅ “ማዕበሉ ከዚህ በኋላ እንዳይገባ፣ የገባውም እንዲወጣ እኔ ምን ማድረግ አለብኝ?” ብሎ ቢያስብ መልካም ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው “ማዕበሉ የትኛውን የመርከቧን አካል ገንጥሎ ገባ? ያ የመርከቧ አካል ክፍተት እንዲፈጥር ያደረገው ምንድን ነበር?” ብሎ መጠየቅና መመርመር ችግሩ ዳግም በሌሎች የመርከቧ ክፍሎች ላይ እንዳይፈጠር ለመጠንቀቅና የጎደለውን እየሞሉ፣ የጠመመውን እያቀኑ ለመሔድ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ነገር ግን ጥፋተኛውን የመፈለግና የመቅጣት ሥራ መከወን ያለበት መጀመሪያ እየሰመጠች ያለችውን መርከብ ያለ ችግር መንሳፈፍ መቻሏን ማረጋገጥ ከተቻለ በኋላ ብቻ ነው፡፡ አጥፊውን ከመርከቧ ለማስወገድ መጀመሪያ የመርከቧ ህላዌ ወሳኝ ነው፡፡ በቅድሚያ ሁሉም የመርከቧ ተሳፋሪዎች በመደማመጥና በመተባበር ሊሠሩት የሚገባው ቀመር “መርከቢቱን እንዴት እናድናት?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ እንጂ “አጥፊውን እንዴት እንቅጣው?” ላይ ያተኮረ መሆን የለበትም፡፡ መርከቧን ካዳንንና ሕይወታችንን ካተረፍን በኋላ አጥፊውን ብንፈልግ የመርከቧ ተራዳ (mast) ላይ እንሰቅለዋለን፡፡ መርከቧ ከሰጠመች ግን እንኳን ለቅጣት የሚሆን ተራዳ ነፍስ ለማትረፊያ የሚሆን መቆሚያ ስፍራም አናገኝም፡፡ ችግር ፈጣሪውም፣ ተቆጭዎቹም ወደ ባሕሩ እንወረወራለን፡፡ የሻርክ ቀለብስ ከመሆን ማን ያድነናል?

  “እኔ ማዕበሉን ከመርከቢቷ እንዳይገባ ለመከላከል፣ የገባውን ደግሞ ለማስወጣት ምን እያደረግሁ ነው?” ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ለዚህ ጥያቄ “እየተቆጨሁ! እየተናደድሁ!” በቂ መልስ አይሆንም መቆጨት ማዕበሉን አያግደውምና፡፡ መርከቧ ለማዳንና ራሳቸውንም ለመታደግ መርከበኞች ከስሜታዊነትና ከግብታዊነት በራቀ መልኩ በመልካሙ ቀን በቃልና በተግባር ከሌሎች ሊቃነ ሐመር የተማሩትን ከሁኔታው ጋር እያስማሙና እርስ በርሳቸውም እየተስማሙ ፈጣንና ቆራጥ እርምጃ በመስጠት አፈጻጸሙ ላይ ሊተጉበት፣ ሊመሩ ይገባቸዋል፡፡ ተሳፋሪዎቿም መርከቧን ስለፈለጓቸው ብቻ ካግበሰበሷቸው ነገር ግን ለመርከቢቱ ህላዌ ከማይጠቅሙ ግሳንግስ ሸክሞች በፍጥነት ሊያቀሏትና የመርከበኞቹን ትእዛዝ በንቃትና በትሕትና እያዳመጡ፣ እየተከተሉ ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡ አይመስላችሁም?

  ReplyDelete
 3. Thank you, even if it is one of sad stories we need to keep it as it is part of our history in the future. ኢትዮጵያዊ ያልግባበት የዓለም ክፍል የለም የሚባለው ብዙ ጊዜ ግራ ይገባኝ ነበር:: በደሴትም: ሰው ይኖርበታል ተብሎ በማይጠበቅ ቦታ ሁሉ አለን:: የፈጠርከውን ህዝብ የማትረሳ አምላክ ስደታችን ተመልከት:: እንደ እስራኤልም መልሰን::

  ReplyDelete
 4. ዳኒ አተራረኩ አጭርና ግልጽ ነው፡፡ የጉዞ ማስታወሻ እንዲህ ሲሆን በጣም ያምራል፡፡

  ReplyDelete
 5. እንጨት ለቅማ….ወጥታ ወርዳ ያሳደገችን እናት መከራዋን ጭንቀትዋን ያልተረዳ በወጣትነት እድሜው አይዞሽ አለሁልሽ ያላለ። ቀኑደርሶ በስደት በመከራ ሲጓዝ ምነው እናቴ ያኔ ይህንን ህሊናዬን ባገኘው ኖሮ እንዴት አድርጌ በረዳሁሽ እንዲት አድርጌ አባቴን አይዞህ ባልኩት። እያለ ለሚወቅሰው ህሊናው እፎይ እንዲያሰኝለት …ያገኛትን ጉርስ ከፍሎ ለቤተሰቡ ሲልክ ምን ይደንቅ።

  ግን በዚህ ሁሉ ወስት ደግሞ ስደተኛው ወደስህተት የሚሄዱት ወንድም እህቶቹን መታደግ አለበት እሱ ባለፈበት። ሀላፊነት በጎደለው መንገድ የተጓዘበትን ጊዜ ወንድም እህቶቹ መድገም የለባቸውና።

  እኔ ሀገርቤት የሄድኩ ጊዜ የታዘብኩት ነገር ነው። በስደት ሀገር ለፍተው ግረው የሚልኩት ገንዘብ የት እንደሚውል እንኳን ግድ የማይላቸው ግን ሰላም ለማግኘት እህት ወንድሞቻቸውን ደስ ለማሰኘት ሲልኩ እነዚያ ግን ብሩ ከየት እንደመጣ ያማያስተውሉት ጓደኞቻቸውን ሁሉ ትልልቅ ሆቴሎች ጋባዥ እና አዝናኝ እነሱ ሆነው። ወንድሜ ልኮ ነው እህቴ ልካልኝ ነው ብሉ ጠጡ አይዞአችሁ ሲሉ።

  እውነት ነው ለፍተው ያላገኙት ገንዘብ እንደ ቅጠል ነው። ምናለ የገንዘቡን ምንጭ ቢያቁት አልኩ። ግን ሳያቁትም ቀርተው አደለም ስላላዩት አይገባቸውም። በመከራ ያለፈው ወገን አሁንም መከራውን አልጨረሰም ወይ ለራሱ አልሆነ ወይ ቁስሉን አልጠገነ። ይህ አለመባረክ ልበለው ወይስ…?። እነሱ ያንን መከራ እንዳያዩ የሚልከው ገንዘብ መች ስራ ላይ ዋለለት እንዳውም መጥፊያቸው የሚሆን ስንቶች ናቸው….?።
  (ሰማርያ)

  ReplyDelete
 6. When and where is going to be the end of sidet? Who can exactly predict the future Ethiopia? I asked myself trillion times about my purpose of life. I couldn’t find any aspect and any satisfaction by living abroad. O God, please make the time short to bring us together! God bless Ethiopia. We are so isolated. We are as scattered as viruses as YOU see. We are dying everywhere and please see us.

  ReplyDelete
 7. please dani do something about your picture.I have read many things on the internet and it is not my problem.

  ReplyDelete
 8. dani egzeabiher yibarkih
  lesirawochih hulu kalat silemiyatirugn new

  ReplyDelete
 9. what is wrong with his picture man?. and what do u want him to do about his picture? you must be kidding.

  ReplyDelete
 10. hi dereje wendme ye igi'abher slm le ante yihun yesetehewn asteyayet anebebkut gin dn daniel iko meche merzem meche mater indalebet yakal bezi lay dn daniel tsihufun babeza kutir igna kesu bizu kumneger inagegnalen so dn daniel berta wendmachin.
  ye amlakachin chernetu ina mihretu ke ante yihun

  ReplyDelete
 11. Ye Igi'abher seam le ante yihun Dn ye tsihuf akerarbih betam des yilal beteley ye malta guzoh yetemecheh new mimeslew.
  gin Dn iskahun sile malta bizu ina des milu beteley sile haymanotachin ina tarikawi merejawoch bizu neger astemarken gin Dani malta sialu ye orthodox lijoch minim yalken neger yelem.tebke neber b/c silenesu yesemahut neger iwnet mehonun lemawek iwnet kehone gin igzi'abhern ameseginewalew mikniyatum yegnan huneta sasbew yangebegibegnal christinachin ye manim mesalekiya be honebet gize.
  wede indeih aynet bota hedeh ye igzi'abhern chernet silasayeehen inesun demo silatsinanahachew Igzi'abher betesebihn yibark.
  KE MILANO

  ReplyDelete
 12. where is the pic?

  ReplyDelete