ከማልታ ደሴቶች መካከል በስፋት ሁለተኛዋ ደሴት ናት ጉዞ፡፡ ከዋና ከተማው ከቫሌታ በመኪና የሰላሳ ደቂቃ ከዚያም በመርከብ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ያህል ትርቃለች፡፡ ሕዝቦቿ ሰላማውያን እና ሃይማኖተኞች ናቸው፡፡ አንዲያውም አንዳንድ መጻሕፍት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ተመልሶ ቢመጣ አንዳስተማራቸው የሚያገኛቸው የጉዞን ሰዎች ብቻ ይላሉ፡፡
የማልታ እና የጉዞ ሰዎች ልዩነታቸው ከደሴቶቹ ርቀት በላይ ነው፡፡ የማልታ ሰዎች የግሪክ እና የጣልያን ሰዎች ክፉ በሽታ ተጋብቶባቸው አንድ ነገር ሲሆኑ እግዚአብሔርን እና ድንግል ማርያምን መሳደብ ይወዳሉ፡፡ ነገር ግን 90 በመቶ የማልታ ሕዝብ ክርስቲያን ነው ይባላል፡፡
የማልታ ሽማግሌዎች የሚደግሙት ዳዊት ሳይሆን የሀገር ቤት «ዱርዬ» የሚሳደበውን የእናት እና የአባት ስድብ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ንግግራቸው ስድብ ካልጨመሩበት የተናገሩ አይመስላቸውም፡፡ የጉዞ ሰዎች ግን ከአፋቸው ክፉ አይወጣም፡፡
በሁለቱ ደሴቶች መካከል አያሌ አፍሪካውያን ስደተኞችን የበላው፣ ያሰቃየው እና ያጓጓዘው የሜዲትራንያን ባሕር ተንጣለሏል፡፡ ጠቅላላ ስፋቱ 2.5 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሆነውና አፍሪካን፣ እስያን እና አውሮፓን የሚያገናኘው ይህ ባሕር በዓለም ላይ የተከናወኑትን ዋና ዋና ጦርነቶች ከሰባት ሺ ዓመታት በላይ ያስተናገደ ባሕር ነው፡፡
ሜዲትራንያን የሚለው ቃል ከሁለት የላቲን ቃላት የተገኘ ስም ሲሆን ትርጉሙም በመሬት መሐል ያለ ውኃ ማለት ነው (from medius, "middle" and terra, "earth").
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የማልታ መንግሥት የጉዞን እና የማልታን ደሴቶች በድልድይ ለማገናኘት በጃፓን ባለሞያዎች አስጠንቶ ነበር፡፡ ጥናቱ ድልድዩ ሊገነባ እንደሚችል ቢያሳይም በገንዘብ እጥረት ሳይሳካ ቀረ፡፡ በዚህ ጊዜ የጉዞ ደሴት ነዋሪዎች ጮቤ ረገጡ ይባላል፡፡ ምክንያቱም ደሴቱ በቀላሉ የሚደረስበት ከሆነ የማልታ ሰዎች ክፉ ጠባይ ወደ እኛም ይጋባል ብለው ፈርተው ነበርና፡፡
የደሴቲቱን ገጽታ እና በውስጧ ያለውን ከ3000 ዓመት ቅልክ በፊት የተገነባውን የፊንቄያውያን መቅደስ ከፊልሙ ተመልከቱ፡፡
በጣም ደስ የምትል ሀገር ነው ያስጎበኘኅን በጣም እናመሰግናለን!! በሰላም ወደ ሀገርህ ይመልስህ፡፡
ReplyDeleteIts amazing place. may God bless you. (ሰማርያ)
ReplyDeleteማብራሪያ ብትሰጥ ጥሩ ነበር መዝሙር ቀርቶ ምክያቱም ዝም ብሎ ማየት እንጂ ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም
ReplyDeletethank u Dn.Daniel i have learned allot but our prayer for some people is also corrected!!!!!!!!
ReplyDeleteThank you Dn. Daniel
ReplyDeleteI share the idea of EhteMichael
we are waiting for you to get YOUR TIMIRT. You are now our Kidus Pawlos....here every body is saying when is he coming? we heared that as you will come on the coming wendsday from my friend. Please come and ATSNANAN EGNANIM
ReplyDeleteውድ ወንድማችን ዲን ዳንኤል፡
ReplyDeleteእጅግ በጣም አመሰግናለሁ። መታደል ነው እነዲሁ ቢሮ ቁጭ ብሎ መኮምኮም። መቸም በቃኝ የለምና በርትዑ አንደበትህ ትረካ ጨምረህበት እንደገና እንማየው ተስፋ አለኝ።
ይህን ሁሉ እንደትሰራ ያነሳሳህ አምላክ ከክፉ ነገር ይጠብቅህ።
ወንደምህ
መዝሙር መግባቱ ነው እንዴ ሰዉን ሁሉ የጨነቀው..? የመጀመሪያው ቪዲዮ ላይ ምንም አልነበረም። እና ይህም ቪድዮ ማብራሪያ ቢያስፈልገው ማብራሪያ መስጠት እዳለበት እረስቶት አመስለኝም። ግን ለእኔ ሁሉም እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ አቀራረብ ነው። በቪድዮው ላይ ያለው ጽሁፍ እኮ መግለጫ ነው።የበለጠ አስፈላጊ መብራሪያ ካለው ደግሞ እርግጠኛ እኝ በሰፊው እንደሚቀርብልን አምናለሁ። እንደኔ እንደኔ መዝሙር በቪድዮው ላይ መግባቱ ልዩ ውበት ሰጥቶታል ከመጀመሪያው ቪድዮ የህንን ልዩ አድርጎታል። ( ሰማርያ )
ReplyDeleteአዬ ጉድ.... ዳንኤል አንተ ስታወራ ቪድዮ ላይ ማየት የለብንም ማለት ነው። ስላወራህ ብቻ ምን እንዳልክ ለማወቅ የሁሉም ልብ ተሰቀለ እኔ ደግሞ ምንዳዬ የዘመረውን ልመስማት ፈለኩ ፦)። አሁን ማን ይሙት ያወራው ነገር አስፈላጊ ቢሆን ንግግሩ እንዲሰማ ማድረግ እረስቶት ይመስላችኃል....? የሰዉ ጥያቄ ይገርማል። ስለ መኪናው ሹፌር ቢሆንስ ያወራው...?የግድ የተወራውን ሁሉ መስማት አለብን እንዴ ሆ ሆ...። ግን እጅግ ግሩም ግሩም ቪድዮ ነው ቦታውም ልዩ ነው። በሰላም ወደ ቤታችሁ ያግባችሁ። መቼም ገና ሌላም የምታሳየን ነገር እንደሚኖር ተስፋ አለኝ።
ReplyDeleteThanks, I liked it.U may let the text on the video stay a little longer next time.Blessings
ReplyDeleteተጉዠ ካሜራችን ዲ. ዳኒ የጉዞህን በረከት ስላካፈልከን እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ነገር ግን ገለጻው አነስተኛ በመሆኑ የራሳችንን ግምት እየሞላን እንድናይ ግድ ብሎናልና ገለጻው ትንሽ ቢታከልበት፡፡መስራት እነደማውራት ባይቀልም ቅሉ
ReplyDeleteአዜብ ዘሚኒሶታ
SELAM DANI EJEG BETAM DES EMIL GUZO NEW.YEGEL TEYAQE BAYHONEBEGN BOTOW LAY YE ETHIOPIA BETECHRISTIAN ENKESEKASE ALE WEYES BEGEL LEGUBEGNET HEDACHU NEW?
ReplyDeleteበመግለጫ የተደገፈ ቪዲዮ መልእክቱን የበለጠ ፍሬያማ ያደርገዋል ይሄንን ሁላችንም እናውቃለን። እየተቀረፀ እያለ ባይቻል ኤዲት በሚደረግበት ጊዜ ይሄ እንዲህ ነው ያ እንደዛ ቢባል ግሩም ነው /(አይ መሬት ያለ ሰው ብያለው ለራሴ)/የገንዘብም ሆነ ያንዳንድ ነገር እጥረት ይኖራል ብዬ እገምታለሁኝ ነገር ግን እኔ የምመኘው አብሮ ከዲ.ዳንኤል ጋር እየተከተለ የሚሰራ ባለሙያ ካሜራማን ቢኖርና ዲ.ዳንኤል ገለፃውን ቢሰራ፡ የካሜራማኑን ደሞዝ ቻላ እንዳትሉኝ ምኞቴ ነው ያልኩት / እንደ አንዳንድ ዶክመንተሪ ቪዲዮዎች /። እንደው አንድ ለማለት እንጂ ከምንም ስለሆነ ለዚህ ያበቃን እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ማለት ይበቃል።
ReplyDeleteDani have a nice journy
ReplyDeleteI don't need to check on wiki or any other web. When I read about Gadaffi's daughter @http://www.presstv.ir/detail/166736.html, immediately when I see Malta I visualized the country. Keep it up Daniel. I am just trying to point that your way of narration helped me to know new places and countries.
ReplyDeleteNB don't get me wrong friends, I am not trying to make people read this story.
Cheers!
እግዚአብሔር ይስጥልን::
ReplyDeleteአንዲያውም አንዳንድ መጻሕፍት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ተመልሶ ቢመጣ አንዳስተማራቸው የሚያገኛቸው የጉዞን ሰዎች ብቻ ይላሉ፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይመስገን።እግዚአብሔር ይስጥል።
ReplyDelete