Sunday, February 13, 2011

ቀን ሲደርስ አምባ ሲፈርስ


ተክለ ጻድቅ መኩርያ በጻፉት ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ዐፄ ቴዎድሮስ አንቱ የተባሉ ጉምቱ ጉምቱ መሳፍንትን እየረቱ ከቋራ ጎንደር የደረሱበትን ምክንያት ሲገልጡት «መኳንንቱ እና መሳፍንቱ የተጠናወታቸው መጠን ያለፈ ንቀት ነው» ይላሉ፡፡
 
እነርሱ የሚያውቁት ይህ ነው የተባለ የሚጠቀስ የነጋሢ ዘር የሌለው፣ «የኮሶ ሻጭ ልጅ« ካሣ የተባለ ሽፍታ፣ አንድ አሥር ጀሌ አስከትሎ የት ይደርሳል? የሚል ንቀት ነበራቸው፡፡ ካሣ እቴጌ መነንን ድል ነሥተው እንኳን መሳፍንቱን ሊያስደነግጣቸው አልቻለም፡፡ ለውጡን ከጎንደር፣ ከመቀሌ እና ከጎጃም አብያተ መንግሥታት ነበር የሚጠብቁት፡፡ እነ ደጃች ውቤ፣ እነ ራስ ዐሊ፣ እነ ደጃች ጎሹ፣ እነ ደጃች ክንፉ፣ እነ ደጃች ወንድ ይራድ፣ አንዳቸው ሌላቸውን እንጂ ካሣን ለአልጋው አይጠረጥሩም ነበር፡፡
 ሁሉም ምክንያታቸውን በአንድ ቃል ነበር የሚገልጡት «ይህ የኮሶ ሻጭ ልጅ የት ይደርሳል እያሉ፡፡ ከጎንደሯ ንግሥት ከእቴጌ መነን መኳንንት አንዱ የነበረው ደጃች ወንድይራድ «ይህን የኮሶ ሻጭ ልጅ አንገቱን እንደ ሙጭልጭላ አንቄ አመጣልሻለሁ» ብሎ ፎክሮ ነበር ጭልጋ ጫቆ ወረደ፡፡ ነገር ግን ያሰበው ከሽፎ በጦር ተወግቶ በካሣ እጅ ተማረከ፡፡ ካሣም «እናቴ ከገበያ ኮሶ ሳይሸጥላት የቀረ አለ፤ እህል ጠፍቷልና ይህንን ተመገብ» ብለው ደጃች ወንድይራድን የኮሶ ሻጭ ልጅ ብለው በተሳደበበት አፉ ኮሶ አጠጡት ይባላል፡፡
ፈርዖን ባሕር ውስጥ
 እቴጌ መነንም በሰኔ 1840 ዓም ካሣን ለመውጋት ሰባት ነጋሪት አገር አስከትተው ወደ ቋራ ሲጓዙ ከንቀታቸው ብዛት «ይህ ቆለኛ ወዴት አባቱ ሊገባ ነው ይሆን እያሉ የትዕቢት ቃል ተናገሩ ይባላል፡፡
ይህንን ክፉ ቃል የተናገሩትን እቴጌ መነንን ለመበቀል ካሣ ከማረኳቸው በኋላ በዋሻ ውስጥ አስገብተው ባቄላ አስፈጯቸው ይባላል፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ስለ ራሳቸው ኑሮ እና ሥልጣን ይጨነቁ ነበር እንጂ እየመጣ ያለው ነገር ሊታያቸው አልቻለም፡፡ አንድ ካሣ የሚባል ሰው ከቋራ ተነሥቶ ታሪክ እየሠራ መሆኑን ለማየት የሚችል ዓይነ ልቡና አልነበራቸውም፡፡
እንዲያውም ደጃች ጎሹ አባዲ ለሚባል ፈረንሳዊ በጻፉት ደብዳቤ «ተካሣ ጋር የተዋጋን እንደሆነ ጎንደር እገባለሁ፤ እንገናኛለን፡፡ ወደ ቆላ የሸሸ እንደሆነ ሰው ባገኝ እሰድልሃለሁ ፈረሱን» ብለው ጽፈው ነበር፡፡ ደጃች ጎሹ ካሣ እንደሚሸነፉ እንዲያውም ወደ ጫካ እንደሚሸሹ ነበር የሚያስቡት፡፡
ራስ ዐሊም ከደጃች ካሣ ጋር ታርቀው እናታቸውን እቴጌ መነንን ካስመለሱ በኋላ ካሣን ንቀው ተዋቸው፡፡ ካሣ ጎንደር ቤተ መንግሥት ደጅ ጥናት መርሯቸው ሀገራቸው ቋራ ሲሸፍቱ ቀድሞ የተሾሙበትን ርስት ደንቢያን ለደጃች ጎሹ ሰጧቸው፡፡
ሁሉም መሳፍንት እና መኳንንት የካሣን ጀግንነት እና ታሪክ ሠሪነት ለማየት የቻሉት ሊመለስ በማይችል አጋጣሚ ውስጥ ሆነው ነበር፡፡ ደጃች ጎሹ ጉር አምባ ላይ በኅዳር 19 ቀን 1845 ዓም በካሣ ሠራዊት ድል ከመሆናቸው ከቀናት በፊት
አያችሁት ብያ ይህንን ዕብድ
አምስት ጋሞች ይዞ ጉር አምባ ሲወርድ
ያንጓብባል እንጂ መች ይዋጋል ካሣ
ወርደህ ጥመድበት በሽንብራው ማሳ
እያሉ ያዘፍኑ እንደ ነበር የቴዎድሮስን ታሪክ የጻፉት አለቃ ወልደ ማርያም ይነግሩናል፡፡ ጎሹ እንደ ፎከሩት የሽንብራ ማሳ አልነበረም የገጠማቸው፤ እንደ አንበሳ የሚደቁስ የካሣ ክንድ እንጂ፡፡ በጦርነቱ ቆስለው ወዲያው ነበር ጎሹ የሞቱት፡፡
ይህንን የሰሙት ራስ ዐሊ አሁንም ንቀት አልለቀቃቸውም፡፡ ካሣ የሚባል ጀግና ሊዋጥላቸው አልቻለም፡፡ ከእውኑ ዓለም ይልቅ የሕልሙን ዓለም መርጠው «እኔ ለካሣ ጦር አልጭንም» ብለው በሦስት መኳንንት የተመራ ጦር ጎርጎራ ሰደዱ፡፡ ሚያዝያ 5 ቀን 1853 እኤአ ይህ ጦር በካሣ ሠራዊት ድባቅ ተመታ፡፡ ራስ ዐሊም ጭንቅ ውስጥ ገቡ፡፡ «ጦር አልጭንም» ማለት ትተው ካሣን አይቀጡ ቅጣት ሊቀጡ ሰኔ 23 ቀን 1845 ዓም አንድ መቶ ጦር ይዘው ጎርጎራ ወረዱ፡፡ የካሣን ጦር በመነጥራቸው አዩና «ሠርገኛ እንዳንለው በዛ፣ ጦረኛ እንዳንለው አነሰ» ብለው ዘበቱ፡፡
አይሻል ላይ የተደረገው ውጊያ እሳት እና ጭድ ሆኖ መቶ ሺው የዐሊ ሠራዊት በካሣ እጅ ተደቆሰ፡፡ ዐሊ ያልጠረጠሩት ሆነ፣ ያልገመቱት ደረሰ፤ ሊቀበሉት ያልፈለጉትን መራራ እውነት መዋጥ ጀመሩ፡፡ በመጨረሻዋ ሰዓት «ይህ በትር የእግዚአብሔር ነው እንጂ የሰው አይደለም» ብለው ራስ ዐሊ በየጁ አልፈው ራያ ወሰን ገብተው በዚያው ሞቱ፡፡
በመጨረሻ የቀሩት ደጃዝማች ውቤ «ቀን ደርሷል አምባ ፈርሷል» ይግቡ የሚል መልእክት ከካሣ መጣላቸው፡፡ ለአንድ የኮሶ ሻጭ ልጅ መግባት መደፈር ነው፡፡ ደጃች ውቤ «ምንኛ የጠገበ ነው አያ» ብለው ጦር አስከተቱ፡፡ ካሣን ገድለው ወይንም ማርከው ደረስጌ ላይ ሲነግሡ እየታያቸው ውቤ ገሠገሡ፡፡
የካቲት 3 ቀን 1847 ዓም ደረስጌ አጠገብ በተደረገው ውጊያ ውቤ ቆስለው ተማረኩ፡፡ በቴዎድሮስ እጅም ገቡ፡፡ መሳፍንቱ ሳይጠረጥሩ ዘመነ መሳፍንት አለቀ፡፡ መሳፍንቱ ሁሉ ዘመነ መሳፍንት ማለቁን የተረዱት ሁሉም ሲቆስሉ እና ሲማረኩ ነበር፡፡
«ቀን ሲደርስ አምባ ሲፈርስ መመለሻ የለውም» እንዲሉ በናቋቸው ካሣ ሁሉም ተረትተው ታሪክ ሆነው ቀሩ፡፡
ሆስኒ ሙባረክ የዛሬ ሃያ ቀን አካባቢ ግብፃውያን ወደ ጣሂር አደባባይ ሲወጡ ከጩኸት ያለፈ ነገር ይመጣል ብለው አልጠበቁም ነበር፡፡ ብርዱ ሲለበልበው፣ ሆዱ ሲሞረሙረው ወደ ቤቱ ይገባል ብለው ሕዝቡን ንቀውት ነበር፡፡ ቀን መድረሱን አምባ መፍረሱን መጠርጠር አልቻሉም፡፡
ውኃ በመርጨት፣ አንዳንዶቹን በማሠር፣ ትዊተር እና ፌስ ቡክ በመዝጋት፣ የሳተላይት ቴሌቭዥኖችን በማስተጓጎል፣ ጋዜጠኞችን በማንገላታት፣ ደጋፊዎቻቸውን በኃይል በማሠማራት ችግሩን በቀላሉ እፈታዋለሁ ብለው ገመቱ፡፡ እልፍ ሲልም የጉልቻ መለዋወጥ የመሰለ የሥልጣን ለውጥ አምጥተው ያላችሁትን ፈጽሜያለሁ ለማለት ሞከሩ፡፡ ሕዝቡ እርሳቸውን እየተቃወመ «የካቢኔ አባላቱ ስለ በደሉት እንጂ እኔንማ ሕዝቡ ይወደኛል» ይሉ ነበር፡፡
ጣሂር አደባባይ የወጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ለእርሳቸው መወድስ ሊያቀርብ፣ ለዋሉለት ውለታም ሊያመሰግን፣ ለአመራራቸው ያለውንም አክብሮት ሊገልጥ የወጣ መሰላቸው፡፡ ሕዝቡ ማምረሩን፣ አንጀቱ መቃጠሉን፣ ቋቅ ብሎት አንገሽግሾት መውጣቱን መገመት አልቻሉም፡፡
ሕዝቡ «ይውረዱ» ሲላቸው እርሳቸው ስለ ልጃቸው ያወራሉ፡፡ ሕዝቡ «ይውረዱ» ሲላቸው እርሳቸው ስለ መስከረም ምርጫ ይደሰኩራሉ፤ ሕዝቡ «ይውረዱ» ሲላቸው እርሳቸው በቴሌቭዥን ቀርበው ምዕራባውያንን ይሳደባሉ፤ ጋዜጠኞችን ይኮንናሉ፡፡ ሕዝቡ «ይውረዱ» እያላቸው እርሳቸው «እኔ ከወረድኩማ ግብፅ አበቃላት» ይላሉ፡፡ ቀን መድረሱን አምባ መፍረሱን ማየት አልቻሉም፡፡
እርሳቸው በጦር ኃይል ነው የመጡት፤ ራሳቸውም ወታደር ናቸው፡፡ አገዛዛቸውም ወታደራዊ ነው፡፡ ጦር የሌለው ሕዝብ አደባባይ ቢውል ቢያድር፣ ቢራብ ቢበላ፣ ቢጮኽ ቢያቅራራ፣ ዳስ ቢጥል መፈክር ቢሰቅል፤ ቢሰለፍ ቢለፈልፍ ምን ያመጣል? ደግሞ ከመቼ ወዲህ በጩኸት መንግሥት ተቀይሮ ያውቃል? ሙባረክ ያነበቡት መጽሐፍ እንዲህ አይልም፡፡
እንዲያውም በመጨረሻ «እኔኮ እወድዳችኋለሁ» ብለው የዓመቱን ታላቅ ቀልድ ቀለዱ፡፡ ምክትላቸውም ብቅ ብለው «የሳተላይት ቴሌቭዥን አትዩ፤ እነርሱ ናቸው የሚያታልሏችሁ» ብለው በአሥር ዓመታት ውስጥ ተገኝቶ የማያውቅ ምክር ሕዝቡን መከሩ፡፡
«አልወርድም» አሉ ሙባረክ፡፡ ስዕለት ያለባቸው ይመስል ከመስከረም ወዲህ ወይ ፍንክች አሉ፡፡ ሕዝቡ ደግሞ ከጣሂር አደባባይ ወይ ፍንክች አለ፡፡ የሚያዩት ነገር እውነት ሳይመስላቸው፤ የናቁት ሕዝብ እየገነገነ መምጣቱ ሳይገለጥላቸው፤ ሰባት ወር የቀረውን መስከረም ሕዝቡ አሳጠረውና ሙባረክ ወረዱ፡፡
እኔ እንጃ፤ አሁን ራሱ ሲያስቡት «በሕልሜ ነው፣ ወይስ በውኔ፣ ወይስ በቴሌቭዥን» እያሉ ሳይቃዡ አይቀሩም፡፡ ከሳምንት በፊት እንኳን½ አሁን የሆነው ነገር ሊሆን ይችላል ብለው ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ አልነበራቸውም፡፡ ጦር ጭነው ያገኙትን መንበር ጦር ያልጫነ ያስለቅቀኛል ብለው እንኳን በታሪክ በተረት አስበውት አያውቁም፡፡ ግን ሆነ፡፡ ቀን ደረሰ አምባ ፈረሰ፡፡
 መናቅን የመሰለ የመሪዎች ክፉ በሽታ የለም፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ የተናቀው ተነሥቶ መሳፍንቱን ሁሉ ነድቶ ጎንደር ቤተ መንግሥት ይገባል፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ፣ የበጎች እረኛ ሙሴ እሥራኤልን እየመራ የኤርትራን ባሕር ያሻግራል፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ አገር ያንቀጠቀጠ ፈርዖን ባሕር ውስጥ ይወድቃል፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ ትንኝ ዝሆንን፣ ቁንጫም አንበሳን ትረታለች፡፡
ቀን ሲደርስ፣ አምባ ሲፈርስ በፈቃድ ያልሆነ በግዳጅ ይሆናል፤ እንደ ደጃች ወንድይራድ ኮሶ ያስጠጣል፤ እንደ እቴጌ መነን ባቄላ ያስፈጫል፤ እንደ ሙባረክ የሠላሳ ዓመት ቤት ጥሎ ያስኬዳል፡፡
ምናለ የአፍሪካ እና የዓረቡ ዓለም መሪዎች ዛሬ እንኳን ቢነቁ፡፡ ቀን እየደረሰ አምባ እየፈረሰ እኮ ነው፡፡
ቫሌታ፤ማልታ

31 comments:

 1. Daniel,

  When the time is just,yes the mountain can move and yes power will be in the hand of the powerless.But the one thing to note is Dictators should civilize in time.In 30 years Mubarak had committed so many atrocities against his people but some how have civilized to use tear gas and water against his people and not to create a media black out.The army is civilized to believe that the people had the right to demonstrate and even though they were loyal to their military president they were more loyal to the people they serve.There are many African countries were the level of oppression has reached its climax and ጽዋውም ሞልትዋል but...but...but...

  ReplyDelete
 2. OMG!I was thinking about it. It is my first time to see this kind of strong people in my life.I am 26 years old and I grew up in a destitue family.Our negihbors were very poor than us. When we ate lunch they had no even dinner. When we ate breakfast they had no even lunch.When any kinds of holiday came in my father called all my negihbors and said,"let us share what we have in the house" such a great father I have.I didn't notice their hunger and dehydriation during those days. Now, I feel their hunger and pain. I am thousands of miles away now.I wear what I like and I eat what I want to eat. Do I feel full and warm, honestly no? Not me, my mind always recalls about my neighbors.Am I happy to live in the United Sates? Honestly no. My small home town is still full of hunger,HIV,Malaria,illiteracy,drought and death.Can I make a little difference in my home town? Of course. Is my little difference can bring a huge change? I leave this answer to my comment readers.Any ways, I am so happy for Egyptians they got rid of that devil who trapped them for 30 years. I wish I can write more.You now some times english is very hard to express my strong feelings. It is hard to find perfect word!
  Note: I am not supporter of any politcal party.

  ReplyDelete
 3. I am proud of you Dani,Ethiopians say(belte kesew mogne kerasu yemaral yelal)what our government learn from Egypt and History.Dictatorial rigem ,no matter how you slice it,will never be accepted in the eyes of the Ethiopians. Mark(Tåsen alle)

  ReplyDelete
 4. I advise the TPLF to learn lessen from Egypt. The best solution for Ethiopia is to dissolve the parliamentary and make a free election again. Then PM Melese will be written in Africa history book. If he will not do that very soon the change will come soon by itself. You cannot stop change....

  ReplyDelete
 5. Kale Hiwot yasemalin Dn Daniel.
  The video about malta has no voice. Please fix the volume? I'm very intersted hearing more about your trip to Malta. Please don't cut it short. Atlanta

  ReplyDelete
 6. Well Written and Nice Perespective.

  ReplyDelete
 7. Dear Dn.Daniel,

  We badly need you to share a lot more for many years to come in all aspect especially in our holy church.

  Ill-minded people probably interpret your commentary article in different ways although it is very right I understand that you do because the situation goes much beyond every body's expectation.

  My suggestion to you to be very conscious you whenever you write about this issues.

  ReplyDelete
 8. አባግንባር ከፍሎሪዳFebruary 14, 2011 at 8:54 AM

  አዎ እውነት ነው ቀን ሲደርስ፤ አምባ ሲፈርስ የተናቀው አጥሩን መነቅነቁ አይቀርም:: የዘመኑ አጥር ግን ከመነቃነቅም አልፎ መፍረስ ጀምሮአል:: መፍረሱ ብቻ አይደለም አፈራረሱና አፍራሹ ቃታ ሳይስብ፤ ጎራዴውን ከአፎቱ ሳይመዝ ያለተኩስና ያለደም መሆኑ ሁሉም አጥር ንጉስን መከላከል አለመቻሉ አስገራሚው ትዕይንት ነው::

  የሚገርመው ቀድሞም “እግዚአብሔርን አላውቅም እስራኤልን አልለቅም” ያለው ፈርጣማው ፈረኦን፤ አሁን ደግሞ ለምዕራባዊያንም አልታዘዝም ስልጣኔንም አልለቅም ያሉት አዛውንቱ ሙባራክ ሁለቱም የግብጽ ነገስታት መሆናችው ነው:: ቀዳማይ እና ደሃራይ ነገሰታት:: ማን ይሆን ደግሞ ቀጣዩ ንጉስ? የእርሱስ አመራር ምን ይመስል ይሆን? “ወንበሩስ” ይቀይራው ይሆን?

  አንዳንድ ተምሳለቶችን በጣህር እና በመስቀል አደባባ ማስተዋላችን ብዙኃኑ የዚህ ጡመራ መድረክ አንባቢዎች የሚጋሩት ሃሳብ ይመስለኛል:: ሁለቱም አደባባዮች በሁለቱ ሃገራት ዋና ከተሞች ዉስጥ መገኘታቸው፤ ነጻነት ፈላጊዎች ቅረታቸውን የሚያሰሙበት፤ የሚስማሙም ሆነ የማይስማሙ አካላት የሚጋፈጡበት፤ የነጻነት መግለጫ ታላቅ የታሪክ አውድ መሆናቸው ተምሳሌታቸውን ያሳያል። ሁለቱም የአባይ ተፋሰስ ራስጌና ግርጌ ይዘው መገኘታችው ከዚህ ወንዝ የጠጣ ሁሉ ለለውጥ የማይተኙ “የአባይ ልጆች” ብሶት መግለጫ የምድር አካላት መሆናቸው ሌላኛው ምስጢራዊ ትስስሮሽ ይመስለኛል:: መሬት ለአራሹ ያለው የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የዚያን ጊዜ ወጣት ያሰበውን ግብ ቢመታም በወቅቱ ለነበረው ወታደር ሀገርቷን እንዳስረከበ ሁሉ ዛሬም የግብጽ ወጣት ለሃገሩ ወታደር ሃገሩን አስረክቧል:: ቀጣይ ዕጣ ፈንታው እንደ እኛው ይሆን?

  ብቻ ቀን ሲደርስ አምባዉ መፍረሱ አይቀርም::

  አባግንባር ከፍሎሪዳ

  ReplyDelete
 9. ተዉ ስማኝ አጘሬ
  የናት የወገኔ ተፈትኗል ፍቅሬ

  ReplyDelete
 10. እኔ ግን የእግዚአብሔር እጅ ያለበት መሰለኝ -------------------- ክርስቲያኖችን መከራ ሲያበዙባቸው አንድ ወቅት አቡነ ሽኖዳ
  "ይህ ለኛ ማንቂያ ነው እግዚአብሔር ወይ ወደ መልካም ነገር ይቀይረዋል ወይ ይፈርዳል " ብለው ነበር ።
  እናም በባግዳድ ወደ 60 የሚጠጋ ክርስቲያን በግብፅ ደግሞ ባንዴ እንክዋን ከ 23 በላይ ክርስቲያኖች ተገለው ነበር ።
  አሁን ግን እርስ በራሳቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ ።
  እግዚአብሔር በእውነትም ፈረደ ።

  ReplyDelete
 11. luul egziabhere yakbirih. yitabikih

  ReplyDelete
 12. luul egziabhere yiberkih

  ReplyDelete
 13. ቀን ሊደርስ አምባ ሊፈርስ የሚችለው እኮ …
  ግብጾች ሙባረክን የምር መፋለም የጀመሩት ከዛሬ 16ዓመት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ እነዚህ ዜጎች የብዙኃን ፓርቲ ሥርዓት ጥያቄን በማንሳት ተፋልመዋል፣ የሥራ አጥነት ፈተናን አንስተው ተፋልመዋል፣ የተንሰራፋውን ምዝበራ አንስተው መንግሥቱን ተፋልመዋል፡፡ ይህ መንግሥት እስከ እዚያች ቀን ድረስ ንቅንቅ አላለም፡፡ ለምን ብለን ስንጠይቅ ዋነኛው መልሱ ጊዜው አልደረሰምና የሚለውን ስናገኝ እነዚያ ለአሥራዎች ዓመታት የተደረጉት ጥረቶችም የሁሉም ዜጎች ይሁንታን ያላገኙ ከመሆኑም በላይ የእንቅስቃሴው መሪዎች ዜጎቹን ይሁንታ በቀላሉ ማግኘት ባለመቻሉም ነበር፡፡ በዚያ ላይ የመንግሥቱ የጸጥታና የደኅንነት መዋቅር ከሚሊዮን በላይ ነጭ ለባሽ አሰማርቶ እያንዳንዷን ጥረት ሁሉ በእንጭጭ ያመክናት ስለነበር ነው፡፡ የእነ ጌቶቹም (አሜሪካ) አስተዋጽኦ ሳይረሳ ማለት ነው፡፡
  ይህን ካነሳሁ አይቀር ሰሞኑን በጀርመን የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በዋሽንግተንም ጥር 30 ቀን 2003 የተደረገ ሲሆን ነገርየው
  የቱኒዚያ ምች የፈረዖን ስጥመት፣
  ሽቅብ ገንፍልና ኢትዮጵያንም ጎብኛት ፡፡ ዓይነት መሆኑ ነበር፡፡

  አንድ ጓደኛዬ ነገረኝ የመንግሥቱ ዘመን አባባል ትዝ አለኝ፡፡ ወታደሩ ሻዕቢያን በላናት ሰለቀጥናት ዓይነት ዜማ ሁሌም እያሰማ ከሥልጠና ወደ ካምፕ ይገባል፡፡ በዚህ ነጠላ ዜማ የተሰላቹ አዛውንት “ጦርነት አስመራ ፉከራ መንጠራ” ማለታቸውን ነግሮኝ አስገርሞኝ ነበር፡፡ ችግር ያለ ኢትዮጵያ፣ የጉዳዩ ባለቤት ያለ ኢትዮጵያ፤ ሻማ የሚበራው፣ ሰንደቅ ዓላማ የሚጠለቀው፣ መጣንብህ የሚለፈፈው ዲሲ፡፡

  በእርግጥ ኢትዮጵያም ለውጥ የሚያስፈልጋት አገር መሆኗን ከቱኒዚያና ከግብጽ ሳይሆን ከምርጫ 97 የታወቀ ነው፡፡ ችግሩ የመንግሥት ነው ወይ? የሚለውን ስናነሳ ግን በፍጹም፤ መንግሥት ምን አደረገ? አፍሪካ አገራችን ናት በደንብ እንወቃት የሕይወት ዘመን አገልግሎት ሽልማት ብቻ ሳይሆን (የሽልማት ድርጅትን ያስታውሷል)የሕይወት ዘመን አገዛዝም ሳይጻፍ በሕገ ልቡና የሚተገበርባት ናት፡፡ ታዲያ መንግሥት አልወርድም፣ አልከሰስም ቢል ምን ያስደንቃል? አፄ ኃይለሥላሴም፣ መንግሥቱም ያደረጉት ይህንኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ የሕይወት ዘመን መሪዎች የተጠናወቷት በጻፈችው ሕግ ሳይሆን በዘይቤ (norm) የምትኖ ር አገር ነች፡፡ ለምሳሌ የብሮድካስቲንግ አዋጅ አላት፤ ግን ዛሬም ኢቲቪ የስዕለት ልጇ ነው፡፡ የምርጫ ሕግ አላት፤ ግን የፓርቲዎች የሥነ ምግባር ደንብ የሚገዛት አገር ናት፡፡ የነጻ ገበያ አራማጅ ናት፤ ግን ደግሞ በሌለ አቅርቦትና አገልግሎት ላይ ዋጋ የምትተምንም አገር ናት፡፡ ፓርላሜንታዊ አሠራርን የምትቀበል የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት አራማጅ ናት፤ ግን ደግሞ 99.9 በመቶ በአንድ ግንባር የምትመራ አገር ነች፡፡ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንንና እንባ ጠባቂ ተቋምን በአዋጅ አቋቁማለች፣ ግን ደግሞ ምርጫ 97 ያመጣውን እልቂት ቢያንስ ያልተመጣጠነ ኃይል መጠቀምን አበክሮ ተናግሮ መገሰጽ ያልቻለ ተቋም ያለባት አገር ነች፡፡ ታዲያ ኢትዮጵያ በጻፈችው ሕግ ተመርታ አታውቅም፤ ይሄን እያዩ እያስተዋሉ ትክክል አይደለም ማለት ምን ማለት ነው?
  ቀን ሊደርስ አምባ ሊፈርስ የሚችለው እኮ ለለውጥ በመትጋት ነው፡፡ ጥያቄው የጽናት ነው፣ የመቼት ነው፡፡ ምናልባት አንድ በማኔጅመንት ትምህርት ውስጥ ያገኘሁት ቃለ ኃይል አለ ምዕራባውያኑ በደንብ የሚጠቀሙበት there is nothing powerful than an idea whose time reach የሚል “ቦ ጊዜ ለኩሉ” የሚለው አጭር ግን ርቱዕ ቃል አይገልጠው ይሆን?
  እናም ያደመጥኩትን ቀልድ ጀባ ልበላ፤ አፄ ኃይለሥላሴ እረኛ ምን አለ እያሉ የሕዝብን ስሜት ያዳምጡ ነበር ይባላል፡፡ ዛሬ ደግሞ መረጃ የሚቀዳው ከካድሬ ሆድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሕዝብ ስሜትን አይገልጥም ይልቅ አዲስ አበባ እንደ እረኛው ካፌ ገብቶ “አንድ ሙባረክ ቡና” በማለት ያዝዛል፤ ግራ ለገባት አስተናጋጅ “እንደወረደ ማለት ነው” ብሎ ይተረጉማል፡፡ ይህ ቀሽት የሆነ የሕዝብ አስተያየት(opinion poll) መግለጫ ሳይሆን ይቀራል?

  ReplyDelete
 14. ኧረ ቀልድ ሃ ሃ ሃ ሃ "አንድ ሙባራክ ቡና" እኔም ጠጣሁት:: ዳኒ እንደው የጡመራ ገጽህን ሌላ መድረክ እንዳላደርገው ፈራሁ እንጂ ሆድ ይፍጀው ያልኩት ብዙ ነገር ነበረኝ:: ይሄ ከላይ ኣስተያየት የጻፈልህ ሰው ስለ ዲሲ እና ስለ ጀርመን ዘገባ ሲያነሳ ኣንድ ነገር ትዝ ኣለኝ:: ኣንድ ውጪ የሚኖር ጓደኛዬ ያወጋኝን ልንገርህማ፤

  ያኔ ጃንሆይን ተቃውመው የወጡ ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚቃወሙ ሳይ ድንቅ ይለኛል፤ እነርሱ እዚያው እንዳሉ ጃንሆይ ወረዱ: እንግዲህ ለኢትዮጵያ ኣስበው ቢሆን ኖሮ ያኔ መመለስ ነበረባቸው::ምንም ንቅንቅ ሳይሉ ቀጠሉና ደርግን ደግሞ መቃወም ጀመሩ፤ ቀን ሲደርስ እግዚኣብሔርም ሲፈርድ ደርግም ወረደ:: እነዚህ ሰዎች ግን ኣሁንም እዚያው ናቸው:: ቀጠሉና ጀመሩ ደግሞ እህአደግ ላይ፤ የሚገርመው ያን ኣንበሳ ያለበትን ባንዲራ ይዘው መውጣታቸው::እንዲያውም አንዳንዴ የሚገርመው እኮ ተቃዋሚ ሆኖ ወደ ሃገር መመለስ ጭራሽ የገዢው ድርጅት ኣካል ተድርጎ መፈረጅ የተለመደ ነገር ሆነ ጎበዝ:: ኣሁን ኣሁንማ ተቃውሞው የሚመስለው ክሃገሪቷ መውጫ እና ጥገኝነት መጠየቂያ (ኬዝ)ማመቻቺያ ሆኗል:: ስለዚህ ከላይ ያለው ወዳጄ እንዳለው ዲሲ ላይ ሻማ ማብራትና ነጩ ቤት ፊትለፊት መፎከር ወይም ጀርመን ላይ ባንዲራ ማውለብለብ " ፍየል ቦሌ ቅዝምዝም ጉለሌ" ዓይነት ነው::

  ReplyDelete
 15. Mother of God virgin mary said "birtuwochin ke zufanachew awaredachew yetewaredutinm kef kef aderegachew" with out adoubt it is a fantastic word that can describe the above article. Good view.

  ReplyDelete
 16. ጥሩ እይታ ነዉ ዳኒ ሉሁሉም ግዜ አለዉ እይታችንን በደንብ ማጥራት ተገቢ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 17. Let me give u another look.it may be good to see a bad governance thrown away.but the fact of the matter hurts,that is in the uncivilized countries change comes after violence.and us tide up with racism,jealousy,illiteracy will desperately need a hero,who could surpass the influence of globalization,to see the light and live as powerful nations like our axumite fathers.
  u know its like a common physical kind of fight between two people,the one who got lucky in punching first will have it easier than the one under attack.the civilized countries got lucky in punching first they got all kinds of advantage over us.in a greedy world where every body is striving to live in a better comfort i don't see us shining if we continue like this.the one being attacked must have some kind of unique quality to survive the fight and start punching.our religion,being uncolonized are our qualities lets use these and fight back.

  ReplyDelete
 18. Diakon Daniel! Thank you so much. It is a briliant aproach.It teaches many things for all human beings.Not only politicians but also inside our church too. You've said once: ...."there are people who,,, Egziabeherin Ye-maiferu, Se-wunim Ye-mayafiru...

  ReplyDelete
 19. Diakon Daniel! Thank you so much. It is a very briliant aproach. I am so happy to read your article. I have read it again and again. It is just the same like you once said: "...Egziabiheren Ye-maiyferu, Se-wunim Ye-mayafiru..." Tyranny is alwayes deef to listen to the other side. To my mind they have uniqe feeling against the rest of us. They see, we see too. At the same time they are 100% blind.We listen and they listen too, at the same time they have 100% deaf ears. It always visual there existe a big barrier between leaders(not only politician) and the ordinary people.

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሄር ለመሪዎቻችን አስተዋይ ልቦና ይስጣቸው፡፡

  ReplyDelete
 21. Alas! One thing we learn from history is that ....we do not learn from history.

  ReplyDelete
 22. Diaqon Daniel r u alright? i don't know the reason why u left the blog. the last blog was on February 13,2011 but today is march 13

  ReplyDelete
 23. Thank you D/n Daniel.Please go on sharing similar information.Please come on!!

  ReplyDelete
 24. Dn. Daniel , you make history , keep it up
  thank you

  ReplyDelete
 25. What an amazing history and lesson is it! May God bless ETHIOPIA!

  ReplyDelete
 26. I hope you like praising so Thank you Danie, As I told you i don't support the fame of Mad people Tewodros is mad leader, and sinner who killed him self, tell me what did he benefit from meqdela, meqdela is the battle I don't want to read about.the real tewodros was not Hero, he was made Hero by Tsegaye gebremedihen and Mengistu haile mariam. this is the truth dont destroy the country by putting wrong IDOLS in front of the youth.

  ReplyDelete
 27. I agree with that, but it is good to see the positive contribution he made, at least he unify the country by force
  Ase tewoderos is like Gadafi of Libiya and Sadam of Iraq,

  He hate Qes, both domestic and foriegn

  ReplyDelete
 28. Dear Dani Ahahaaa...ha

  still there also guys who are do not accept the current situation to be happend but there are guys who didnt accept that is done in the past.two guys above are smple example for this.who wants to say he is shifta, yekosso shach lij,gadafi,mad,,,hmm ignoring the current situation and make themselves as the only man is the behavior of dictators where as ignorant of the past situation is COMPLEX.
  due to their deep rooted complex
  they want to be fiction what you
  wrote about teodros. they want to
  assume it is a fiction of tsegaye
  G medhin, mengistu,and u(now).

  ReplyDelete
 29. I agree Atse tewodros for hero,atse yohannes for religion,atse menilik for wise leadership,,, they have contributed alot for their country .so,no more debate on that.

  ReplyDelete
 30. I hate it when ignorant people call Tewodros a mad man.He was annointed by GOD and was a man who clearly suffered for his sanity.The name Tewodros meas GOD's gift in greek.This is what we ethiopians always do we reject and abandon anything that GOD gives us.Tewodros was a self educated man, he even read Shaekspearean plays in a time when most of the world was illiterate. He had full knwoledge of some of the Greek philosophies and sure knew like his hand the Ethiopian scriptures. Fikare Eyesus states "behold, there will come a man, his name is Tewodros, and he would put chaos to order through his sword." Most of the right things Atse Minelek did was in reaction to the wrongs Tewodros made.When he heard of his death Menelik cried saying "i have lost a father and a great teacher i will go to the woods and mourn him on my own".ALEMASTEWALACHIN YASAZENAL.

  GOD bless you Daniel i hope you see my point

  ReplyDelete