እኔ እና ዲያቆን ምንዳዬ ብርሃኑ በኦስሎ በኩል ወደ ስታቫንገር ገብተን፣ በዚያም አንድ ሳምንት ያህል ቆይተን፣ ትናንት ደግሞ በፍራንክፈርት በኩል ወደ ማልታ ተጓዝን፡፡ የኛ መጽሐፍ ቅዱስ መላጥያ የሚላት ይህቺ ደሴት በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ፣ ከዚያም በጀልባ ሜዲትራንያን ለሚያቋርጡ ስደተኞች ወገኖቻችን መጠለያ ናት፡፡ በጣልያን እና በሊቢያ መካከል መገኘቷ ለብዙዎች እንደ መንገድ ማረፊያ አገልግላለች፡፡
መላጥያ/ማልታ/ ከሜዲትራንያን ደሴቶች መካከል ትልቁ ሲሆን በሜዲትራንያ ባሕር ማእከላዊ ቦታ ላይ ከሲሲሊ በስተ ደቡብ 96 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ጠቅላላ የደሴቱ ስፋት 246 ስ.ኪ.ሜ. ነው፡፡
ፊንቄያውያን በዘጠነኛው መ/ክ/ዘመን /ቅ.ል.ክ/ ደሴቲቱን በቅኝ ግዛት ይዘውት ነበር፡፡ በስድስተኛው መ/ክ/ዘ /ቅ.ል.ክ/ ደግሞ ኙኒኰች ያዙት፡፡ በሁለተኛው የፑኒክ ጦርነት /218 ቅ.ል.ክ/ ሮማውያን ደሴቱን ያዙ፡፡ ከዚያም ከሌሎች የአካባቢው ደሴቶች ጋር በአንድነት በሮም ንጉሥ በሚሾም ሀገረ ገዥ ትተዳደር ነበር፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ታሥሮ ወደ ሮም ሲጓዝ በቄዳ ደሴት አካባቢ መርከብ ተሰበረባቸውና ሁሉም በመላጥያ ደሴት ዐረፉ /የሐዋ.27÷39(28÷6/፡፡ ሐዋርያው ያረፈባት ቦታ በደሴቲቱ ሰሜናዊ የባሕር ወሽመጥ ከአሁኗ ቫሌታ /Valetta/ 13 ኪ.ሜ ሰሜን ምዕራብ ርቀት ላይ ተገኛለች፡፡ ወደ ደሴቲቱ የገባበት በዓል ለደሴቲቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ሆኖ በየዓመቱ ፌብርዋሪ 10 ቀን ይከበራል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስና ሌሎች ተጓዦች በደሴቲቱ ሦስት ወራት ተቀምጠዋል፡፡ በዚያ ደሴትም ከእፉኝት መርዝ ድኗል /28÷1(6/፡፡ በዚህም የተነሣ «ይህ አምላክ ነው» ብለውት ነበር /÷6/፡፡ የደሴቲቱን አለቃ የፑፕልዮስን አባት ከወባ በሽታ ፈወሰለት፤ በዚህም የተማረኩ ብዙ ሰዎች ድውያንን አመጡና ፈወሰላቸው /÷7(10/፡፡
መላጥያ በቅድመ እና ድኅረ ክርስትና ቅርሶች እና ሙዝዬሞች የተሞላች ደሴት ናት፡፡ በዚህች ደሴት ለቀጣዮቹ አሥራ አምስት ቀናት እንከርማለን፡፡ ከጉባኤዎቻችን ጎን ለጎን የምናያቸውን ትንግርቶች ከእናንተ ጋር እንካፈላለን፡፡
መልካም ቆይታ
Egziabher Agelegelotachihun yebarikelachu
ReplyDeleteSebakian ena zemarian tekenajetewe yemiyakahidut ywenigil agelegelot mieminun lemederes yeminorew
astewatso tilik endimihon yetayignal.
With regard to songs its better to adress through your preaching about the real EOTC songs. That will help to protect the "throatse" ones.
Abiot k oldenburg
uiypuiyouyfgy
ReplyDeletebegugut entebkaln memihir!!
ReplyDeleteI can't wait.
ReplyDeleteHave a good time!
ReplyDeleteTebarek Dani wedegase lemene beke atelum nebere...Mendayen selam belelen melekam koyeta!
ReplyDeleteDn.dani melkam fre yemtaferubt yehunlachue
ReplyDeleteDear brothers this is absolutely a great job which requests patience and devotion. what can i say more than may God be with you all wherever you go. i believe that one day your children will also follow your footstep in the future. May the grace of our God Jesus Christ and the intercession of his mother st.Mary keep you from all evil deeds.
ReplyDeleteAntonio----------Mekelle.
Dn daniel ena zemari Dn mendaye bezeh hulet ken west yesetachut agelglot be MALTA ejeg denk new,beterefew geze degmo kezeh bebelet endemtastemerun be EGZEABHER tesfa enadergalen,EGZEABHER amlak ye agelglot zemenachehun yarzemelen,edme ena tena ke kerew betesebochachehu ga yestelen,amanuel(abuti) ke MALTA
ReplyDeletethank you,wolde amanuel
ReplyDeleteGod bless you and your services.
ReplyDeleteይህቺን ደሴት በ1988 ነሃሴ ወር ላይ የማይት እድል አጋጥሞኛል ፡፡ ያረፍኩበት ሆቴል አካባቢም በቅዱስ ጳውሎስ ስም የተሰየመ ቤተ ክርስቴያን አይቻለሁ፡፡ በተክርስጢያኑ በ10 ክፍለ ዘመን እንደተመሰረተ ተነግሮኛል፡፡ የሀገሬው ህዝብ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነው፡፡
ReplyDeleteበዛች ትንሽ ደሴት ብዙ ቤተ ክርስቴያን ታንጾአል ፡፡ በተጨማሪም የዚች ደሴት አካል ወደ ሆነችው ጎዞ ደሴት /Gozo island/ በመንገደኛ መርከብ የመሄድ እድል አግኘቼ ነበር ፡፡ እዚህም አብያተ ክርስቲያናት በብዛት የገኛሉ፡፡