Wednesday, February 9, 2011

«ስኳሬ»፣ «ዘይቴ»


በአንድ ጨለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ቤቱ ያለው ከአንድ ሕንፃ ሥር ነው፡፡ በጣም ሰፊ እና ጨለማ ቤት ውስጥ፡፡ መጀመርያ በጨለማው ውስጥ አጮልቃ ማየት የቻለችው ስኳር ናት፡፡ ከእርሷ አጠገብ ዘይት ኩርምት ብላ ተቀምጣለች፡፡
«አንቺም እዚህ መጣሽ አለቻት ስኳር
«ባክሽ ሕዝቡን ከኑሮ እሥር ቤት እናወጣለን ብለው እኛን የጨለማ እሥር ቤት ከተቱንኮ» አለች ዘይት እየተንገጫገጨች፡፡
«በቃ እዚህ ሀገር መተዛዘን ጠፋ ማለት ነው? ሐበሻ እንደ ኬንያ እና ናይጄርያ ካልሆነ የሚያዝንለት ሊጠፋ ነው እንዴ?» አለች ስኳር እየተንሸራተተች፡፡
«እንዴት እባክሽ?» ዘይት ናት ፍንጥር ፍንጥር እያለች የምትጠይቀው፡፡
«ወርቅ ቤት ያለ ዘበኛ ያድራል፤ ሱቅ በደካማ ሽማግሌ ይጠበቃል፤ ሐበሻ ቢርበው ይለምንሻል እንጂ ገሎሽ አይሄድም፡፡ እንዲህ ኑሮ እየተወደደ ሰው የሚበላው ካጣኮ እህሉን ብቻ ሳይሆን ባለ እህሉንም መብላት ይጀምራልኮ፡፡ ለምን ጨዋነቱን ይፈታተኑታል) የቱኒዝያን ውቃቤ ለምን ይጠሩብናል እቴ» ስኳር ከማዘኗ የተነሣ ጩርር እያለች በጆንያው ቀዳዳ በኩል ፈሰሰች፡፡
«ታድያ ምን ያሳዝንሻል)»
«እንዴት አላዝን እዚህ ተቀምጬ ኤክስፓየሪ ዴቴ ሊያልፍ እኮ ነው፡፡»
«ታድያ አንቺ ምን አስቸገረሽ፤ እዚህ ሀገርኮ ብዙ ኤክስፓየሪ ዴቱ ያለፈበት ነገር አለ፤ አንቺ ብቻሽን አይደለሽ»
«አንቺ ትሆኚ እንደሆን እንጂ ሌላስ ያለፈበት የለም»
«ኧረ እባክሽ፤ ስንት መመርያ፣ ደንብ፣ አሠራር፣ አስተሳሰብ፣ ሥርዓት፣ መፈክር፣ ስያሜ ኤክስፓየርድ ካደረገ በኋላ በየቢሮው እየተሠራበት አይደል እንዴ፡፡ በንጉሡ ዘመን የነበረው፣ በደርግ ዘመን የነበረው ስንት አሠራር ምንም የመጠቀሚያው ጊዜ ቢያልፍበት ይሄው ሁሉም ይጠቀምበታል፡፡»
«ግንኮ እውነትሽን ነው፤ እኔ የምለው በካፒታሊዝም ሥርዓት መፈክር አለ እንዴ? ይኼው መንገዱ በሙሉ መፈክር ብቻ እኮ ነው፡፡ እኔን ያልገባኝ ድሮ ስንፈክር ግራ እጃችንን እናነሣ ነበር፤ ዘንድሮ የትኛውን ነው ማንሣት ያለብን?»
«አንዲት ሴትዮ ምን እንዳደረጉ ታውቂያለሽ?»
«ምን አደረጉ ባክሽ?»
«ግራ እጃቸውን እንዳያነሡ የኢሠፓ ርዝራዥ እባላለሁ ብለው ፈሩ፤ ቀኝ እጃቸውን እንዳያነሡ፤ የትም ስብሰባ ላይ ቀኛችሁን አንሡ የሚባል አልሰሙም፤ እና ቢጨንቃቸው ሁለቱንም አነሡ ይባላል፡፡»
«ይኼማ ሚክስድ ኢኮኖሚ አደረጉት ማለት ነው»
«አንቺ ግን ነጭ አልነበርሽ እንዴ? ምን ሆነሽ ነው ግን የጠቆርሽው?» አለቻት ዘይት ስኳርን፡፡
«እስኪ በናትሽ አሁን እኔና ቢራ እኩል መሠረታዊ ሸቀጦች እንባላለን፡፡» አለች ስኳር
«በእርሱ አልነበረም ግን መናደድ የነበረብሽ?»
«ታድያ በምንድን ነው?»
«ለሀብታሙ የቢራ ዋጋ ሲወጣለት ለድኻው ደግሞ የጠላ እና የጠጅ ዋጋ መውጣት ነበረበት፡፡ የዋጋ አወጣጡ ድኻውን እና ገበሬውን ማዕከል ያደረገ አይደለም፡፡»
«ባክሽ ዘንድሮ ቀን የወጣላቸው ድመቶች እና አይጦች ናቸው» አለች ስኳር
«እንዴት ባክሽ» ዘይት ተገርማ ነበር የጠየቀቻት
«ሥጋ ቤቱ ሁሉ 52 ብር ሽጥ ሲባል ጊዜ ያገጠጠውን ከብት እየገዛ ሥጋው ሁሉ ልፋጭ ሆነ አሉ፡፡ ከሚሸጠው የሚጣለው ሲበዛ ደጉ መንግሥታችን ይኼው ለድመቱ ቀን አወጣለት ብለው ድመቶች ደስ አላቸው አሉ፡፡
«ድሮምኮ ድመቶች በየመንግሥታቱ ተጎድተው አያውቁም፡፡ መለሳለሱን እና ጭራ መቁላቱን ይችሉበታል፡፡ በድሮም ዘመን ከእንስሳት ሁሉ ተለይተው ድመቶች «የድመት መሬት» የሚባል ነበራቸው፡፡ የአይጦቹ ነው የገረመኝ» ዘይት ተንቦጫቦጨች፡፡
«ለድመቶች መንግሥት ቀን ሲያወጣላቸው ለአይጦች ደግሞ ነጋዴው ቀን አወጣ ላቸው፡፡ ቀን ሲያልፍ እሸጠዋለሁ እያለ ስኳሩን፣ ዘይቱን፣ ነጭ ሽንኩርቱን፣ ሳሙናውን በየሥርቻው ሲደብቅ አይጥ ሆዬ ይዝናና ጀመራ፡፡ ምንጊዜም ቢሆንኮ እንዲህ ባለው ግርግር ተጠቃሚዎቹ አይጦች ናቸው፡፡ ንግዱ በይፋ በአደባባይ ከሆነ ለአይጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ እንዲህ ወደየሥርቻው ሲገባ ግን የአይጥ ሠርግ እና ምላሽ ነው፡፡»
«በዛኮ በዛ፤ ነጋዴውም አበዛው መንግሥትም አበዛው፤» አለች ዘይት እየተመናቀረች
«ደግሞ ምን ልታመጭ ነው» ስኳር ካለችበት ተሸራሸች፡፡
«ነጋዴውምኮ አራቱን የሂሳብ መደቦች ወደ ሁለት አወረዳቸው፡፡ መቀነስን እና ማካፈልን ትቶ መደመር እና ማባዛት ብቻ ሆነ፡፡ እሥራኤል እና ፍልስጤም ሲጣሉ ዋጋ ይጨምራል፤ ኢራን እና ኢራቅ ሲጣሉ ዋጋ ይጨምራል፤ ሰሜን እና ደቡብ ኮርያ ሲጣሉ ዋጋ ይጨምራል፡፡ የብራዚል ቡና ወደቀ ዋጋ ይጨምራል፤ የሕንድ ሩዝ ቀነሰ ዋጋ ይጨምራል፡፡ የነጋዴው መዝሙርኮ «ጨምር ጨምር አለኝ» ብቻ ሆኖ ነበር፡፡
«ዊንዶ ሾፒንግ ታውቂያለሽ?»
«ይኼ በየሱቁ እየዞሩ ማማረጥ እና ዋጋ መጠየቅ ነው አይደል)»
«እዚህ ሀገርኮ የግዥ ዕቅድ ማውጣት አልተቻለም ነበር፡፡ የምትፈልጊውን ዕቃ መዝግበሽ ዋጋ አጠያይቀሽ በሚቀጥለው ቀን መግዛት አትችይምኮ»
«እንዴት?»
«አንቺ ብርሽን አዘጋጅተሽ ስትመጭ እነርሱ ዋጋ ጨምረው ይጠብቁሻል፡፡ እንኳን በማግሥቱ እዚያው ቼክ ዘርዝረሽ እስክትመጭ ዋጋው ተለውጦ ታገኚዋለሽኮ»
«እንዴ ሕዝቡኮ ከመብላት ወደ ማሽተት፣ ከማሽተት ወደ ማየት እየተሸጋገረ ነበር፡፡ በዚሁ ቢቀጥል ደግሞ ከማሽተት ወደ ማሰብ እየሄደ ነበር፡፡ የሥጋ ዘመድ እንጂ የሥጋ ደንበኛ ቀረ፤ ዐማኑኤል የሚሄደው ለአእምሮ ሕክምና እንጂ ጤፍ ለመግዛት መሆኑ ቀረ፡፡ ልብስ በሳሙና ማጠብ ቀርቶ ድሮ ሳሙና በነካው ማጠቢያ ማጠብ ተጀመረ፡፡»
«ሕዝቡምኮ ቢሆን ይህ ሁሉ ሲመጣበት ዝም ነው ያለው»
«አንድ ተረት ልንገርሽማ»
«ምን?»
«በአንድ ሀገር አንድ ጨካኝ ንጉሥ ነበረ፡፡»
«እሺ!!»
«በሕዝቡ ላይ መከራ አበዛበት፡፡ ኑሮ ተወደደ ብቻ ሳይሆን ኑሮ ራሱ ጠፋ፡፡ ያን ጊዜ በዚያ ሀገር በጸሎታቸው ሁሉን ማድረግ ወደሚችሉ ሴት ዘንድ ሕዝቡ ሄደ፡፡ ይህ ንጉሥ እንዲጠፋ ጸልዩ አላቸው፡፡ ጸለዩ፡፡ ንጉሡም ሞተ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ የመጣው ንጉሥ ደግሞ እህሉን ከገበያ አጠፋው፤ ሕዝቡ «እህል በትዝታ» የሚል ዘፈን ብቻ መዝፈን ሆነ ሥራው፡፡ አሁንም እኒያ ሴትዮ ሄዶ ጸልዩልን አለ፡፡ ጸለዩ፡፡ ንጉሡም ሞተ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ የመጣው ደግሞ እጅግ የከፋ ሆነ፡፡ ሰው ለሰው ሊባላም ደረሰ፡፡
«ሕዝቡ ወደ ሴትዮዋ ሄደና ካሁን በኋላ ለዚህ ንጉሥ እድሜ እንዲሰጠው ይጸልዩ አላቸው፡፡ ሴትዮዋ ይጸልዩ ጀመር፡፡ የንጉሡም እድሜ ረዘመ፡፡ ንጉሡ እድሜው ሲረዝም ጊዜ ምክንያቱን ማወቅ ፈለገ፡፡ እናም ሰላዮችን በሀገሩ ሁሉ ላከ፡፡ በመጨረሻ ሰላዮቹ የሴትዮዋ ጸሎት መሆኑን ዐወቁ፡፡
«ተመለሱና ለንጉሡ ነገሩት፡፡ «ላንተ ረዥም እድሜ እንዲሰጥህ የምትጸልይ ሴት አለች» አሉት፡፡ ገረመው፡፡ ገርሞትም አልቀረ አስጠራት፡፡
«ለእኔ ረዥም እድሜ እንዳገኝ ትጸልያለሽ አሉ» አላት፡፡
«አዎ እጸልያለሁ፡፡»
«ከሁሉም ዘመን በባሰ ኑሮ ተወድዶ እያየሽ እንዴት ልትጸልይልኝ ቻልሽ?» አላት፡፡
«ካንተ በፊት በነበረው ንጉሥ ዘመን ኑሮው ከፋ፡፡ ጸለይንበት እና ሞተ፡፡ ከእርሱ በኋላ የመጣውም የባሰ ሆነ፡፡ ጸለይንበትና ሞተ፡፡ አንተ ከእርሱ በኋላ መጣህ፡፡ አንተም ከእነርሱ ስሕተት እና ጥፋት አልተ ማርክም፤ እንዲያውም የባስክ ሆንክ፡፡ አንተ ሞተህ ሌላ ቢመጣ ካንተ የባሰ ክፉ ይሆናል ብለን ሠጋን፡፡ ስለዚህም ላንተ እድሜ መለመን ጀመርን» አለቺው፡፡
«ለካስ ሰው ሲጠላም እድሜ ይለምናል» አለ ንጉሡ፡፡ እናም ጥፋቱን ሁሉ አርሞ ችግሩን ሁሉ አሻሻለው ይባላል፡፡
«ሕዝቡኮ መጮኽ የጀመረው የጤፍ ዋጋ እንደ ነዳጅ ዋጋ መጨመር ሲጀምር ነው፡፡ ኒውዮርክ ላይ ነዳጅ፤ አዲስ አበባ ላይ ጤፍ እኩል ይጨምራል፡፡
አንቺ አዲስ አበባ እንደ ኒውዮርክ ሆንሺ
ሥልጣኔ ሳይሆን አጨማመርሺ
እያለ ሕዝቡ ማንጎራጎር ከጀመረኮ ቆየ፡፡ ግን ምን ሆነ) ባንጎራጎረ ቁጥር ዋጋው ጨመረ፡፡ አንጎራጎረ፤ ጨመረ፡፡ አንጎራጎረ፤ ጨመረ፡፡
አልቃሽ እንኳን በዐቅሟ
ቅማንትህ ሲሞቱ ጤፍ አንድ ብር ነበር
አያትህ ሲሞቱ ጤፍ አሥር ብር ነበር
አባትህ ሲሞቱ ጤፍ መቶ ብር ነበር
አንተ ስትሞት ግን ጤፍ ብር ተሸጠ
ጎበዝ እንዳንተ ነው ችግር ያመለጠ
ብላ አልቅሳለች አሉ፡፡»
«ጤፍ ሚሊዮን ብር ሳይገባ በመሞትህ ደግ አደረግክ ማለቷ እኮ ነው፤ ሊቃውንት ናት ባክሽ»
በመጨረሻ ሕዝቡ ተስፋ ቆረጠና ተመስገን አለ፡፡ ይኼው ተመስገን ማለት ሲጀምር ዋጋው ቀነሰ፡፡»
«መንግሥትም ቢሆንኮ ዘገየ፤ ሲጮኽ፣ ሲለቀስ ዝም አለ፡፡ ልቅሶ ቤትኮ ገብተሽ ስለ ሟች ማውራት ቀርቶ ነበር፡፡ ወሬው ሁሉ ስለ ጤፍ፣ ስኳር እና ዘይት ሆኖ፡፡ ስንት ምጣድ ሞቶ፣ ስንት ድስት ሞቶ፣ ስንት የሻሂ ጀበና ሞቶ በየቤቱ ከተቀበረ በኋላ፤
ነጭ ሽንኩርት፣ ነጭ አዝሙድ፣ ነጭ ጤፍ ያላችሁ
እስኪ እንያችሁ
ከተባለ በኋላ ነውኮ ርምጃ የወሰደው፡፡»
«ቆይ ግን አሁን የኛ መጨረሻችን ምንድን ነው?» አለች ስኳር
«በጣም ውድ ትሆኚና የሰዉ ስም ትሆኛለሽ» ዘይት ከት ብላ ሳቀች፡፡ መልሳ ደግሞ ተቆጣጣሪዎች ሰምተው ከተደበቀችበት እንዳያወጧት ሠጋችና አፏን ያዘች፡፡
«ስም)»
«አዎ አበሻ አንድ ነገር በጣም ውድ ሆኖ የማያገኘው ከመሰለው ለልጁ ስም ያደርገዋል፡፡»
«የነገ ልጆቻችን ስም «ስኳሬ» «ዘይቴ» ሆነ በይኛ»
 ይህ ጽሑፍ በሮዝ  መሔጽት ላይ የወጣ ነዉ

36 comments:

 1. temelkach

  negeru ahunem "alsheshum zewor.." new dany!yehotel megib,yetezegaju lebsocch, chama etc chemere engy alkenesem. lenegeru yekntotun enqua entewewalen. "nuary" yechenek bezuwoch "anuanuary" nen.
  ewnet aygermem ? techekaken eko ! benegerachin lay and asazagn neger lingereh, bahir dar new alu yand habtam teff leffech wofcho bet neber, andua chiger yestenabachew setyo teffun ansetew asfechitew yewosdalu.teffu teffa tebillo sefeleg asfechita setyowa setwosed endayu bemiliket yenageralu,kebet bale teff sedersu doketun eyaboku kita lelijoch segagru yederesal. baleteffum azno alkeso teffunem tewolachew lela 1000 birr chemiro kezeh behuala endemeredachew kal geba alu.egzeabher yekfelewu wogen ahun eko asafaree "silent hunger" lay nen be and cherk tetklelen wode afer yeminigeba sewoch metezazen tewn !

  ReplyDelete
 2. ዳኒ፤ ይገርምሀል የዘየድኩት ዘዴ፤ ከቻልክና ካገኜሀቸው ለስኳርና ዘይት ንገርልኝ እኔም ምኔ ሞኝ ነኝ ለወደፊት ለሚመጣው ትውልድ ዝናውን ለመንገር እና ለማሳየት እንዲመቸኝ ብየ ምን የመሰለ ጮማ አዘጋጅቼ ምን የመሰለ የጤፍ እንጀራ አስጋግሬ ፎቶውን ለማስቀረት ችያለሁ፡፡
  ለመሆኑ ‹‹የቱኒዝያን ውቃቤ ለምን ይጠሩብናል እቴ» አለች ስኳር .....፡፡›› ነው ያልከው ይገርማል የራሳችን ውቃቤ/ወኔ/ጀግንነት በእነ እራስ አሉላ÷ በእነ አፄ ቴዎድሮስ÷ በምዬ ምንሊክ እንዲሁም በሌሎቹም በሌሎቹም ዘመን ተሟጧ አልቆ ምን ዘመድ ምን አቻ ባልንጀራ አገኝ ብሎ ወደእኛ ይመጣል?

  ReplyDelete
 3. Dear sir
  I tried to smile but I couldn`t.It is about my every day pain.
  Worku

  ReplyDelete
 4. danyeyeye men lebelehe

  ReplyDelete
 5. It is a post addressing the current burning issue. merchants, government, all peoples, we should takecare of eachother. Might we saw a time when buyers will recommend salers to increase prise, because of overcaring salers?

  ReplyDelete
 6. ወይ! እነ ስኳሬ.... አሁን እንኳን ተመስገን ማለት ነው።በግድም ቢሆን ቅነሳ ተጀምሯል። እንደነ ግብፅ ኢትዮጵያ እንዳትሆን ድንጋይ ዳቦ ይሚሆንበት ዘመን ይመጣል.. ያኔ እነ ስኳሬ ከተደበቃችሁበት ተወጣላችሁ።

  ReplyDelete
 7. የጨነቀው …. አሉ

  ሮዝ እንደስሟ፣ እንደ መልኳ፣ እንደ መዓዛዋ ናት፡፡ ሮዝን በጥልቅ ባይሆንም አንዷን አምድ ማግኘት በጣም ጥሩ ነው፡ መጽሔቷ ምን ያህል ሃሳብ የሚንሸራሸርባት፣ ግልጽ፣ ጠቃሚና ሚዛናዊ መጃዎች የሚወጡባት መሆኗን በዚህ ጽሑፍ የበለጠ ማረጋገጥ ቢቻልም ቀደም ሲል የተጻፉ ጽሑፎችህ መውጣታቸውምን ባለመዘንጋት ነው፡፡ ለማንኛውም ሮዝን ስጣራ ከተፍ አለች በጡመራ፤ ያስኬድ ይሆን?
  የችግሩ መሠረት በዋናነት በገበያ ላይ የተመሠረተ ሸማች ማኅበረሰብ መገንባት አለመቻሉ ይመስለኛል (Consumerism: the theory that an increasing consumption of goods is economically beneficial)፡፡ በአሁኑ ወቅት አደጉ የምንላቸው አገሮች የእድገታቸው ምክንያትም ይኸው ነው፡፡ ፍላጎት የሚነዳው አቅርቦት ከሌለ ነጋዴውን አውርድ ብቻ ማለት አይቻልም፡፡ ስግብግብ ነጋዴ የሚለው አገላለጽ ጥቂት የሚል ቢጨመርበት የተሻለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ነጋዴ ሁሉ አገሩን የማይወድ፣ የዜግነት ግዴታ የሌለበት ባንዳ አድርጎ መሳልም ሆነ ማቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ ስግብግብነት የአልጠግብ ባዮች ተግባር ከመሆኑም በላይ ምናልባትም ስኳሬና ዘይቴ በጨለማ ውስጥ የሚከማቹበት ምክንያት እንደ አንድ የመታገያ ስልት ተደርገውም ሊሆን ችላል፡፡

  እውነት እንነጋገር ከተባለ በመላ አገሪቱ ያሉት በአብዛኛው በአንድ ሰው የሚዘወሩ ያውም ሱቆች ናቸው፡፡ የፍጆታ አቅርቦቶችን በእንደዚህ ዓይነት ኪዮስክ ነክ አደረጃጀት እንዲቀጠሉ የሚያደርግ አሠራር ባለበት አገር በየጉራንጉሩ አነስኳሬ ቢደበቁ አይደንቅም፡፡

  ሸመታን ለማሳደግ የሚቻለው ደግሞ ወይ በገፍ መሸመት የሚያስችል ገቢ ያለው የኅብረተስብ ክፍል ሲኖር አለያም በገፍ መቅጠር የሚችል የሠራተኛ ገበያ ሲፈጠር (labor market) ነው፡፡ ሥጋ በበዓል፣ አስቤዛ በልደታ በሚል የሸመታ ሥርዓት እጥረትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን መኖርም የግድ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለት ተቃርኖዎች አንድ ላይ ሊኖሩ አይችሉምና፤ ነጋዴ እንዲበረክት፣ ሸማች እንዲያልቅ አይፈልጉም፡፡

  ReplyDelete
 8. ያ እግር የሚሰብረው ዘይት ከሆነ ከጨለማው ባይወጣ ይሻለዋል ኖሮም አልጠቀመ ብራውኑ ስኳር እንኳን ለ ዳይት ጥሩ ነው። ለነገሩ ኑሮ እራሱ ዳይት ሆኗል።

  ReplyDelete
 9. I am just wondering how far we have to go just like this? For Gods' sake!Is there anyone out there who can predict future Ethiopia?O God please don't take me to the 2nd world before I see my mother's happy face.

  ReplyDelete
 10. +++
  ህዝባችን ሻሂ ያለ ስኳር ወጥ ያለዘይት ላለመሞት በ24ስዓት አንድ ጊዜ በመቅመስ ህይዎቱ መግፋት ከጀመረ ዘመናትን አስቆጠሮአል እኮ:: ደልቶአቸው የሚቀማጠሉም አሉ::

  እግዚአብሔር የምህረት ፊቱን ይመልስልን::

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 11. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላFebruary 10, 2011 at 8:49 AM

  ተዉ ስማኝ አጘሬ
  የናት የወገኔ ተፈትኗል ፍቅሬ

  ReplyDelete
 12. Dani you are always special man.your idea is right but my dought is that is the government of ethiopia think and work for rich peoples only it should take measure for the majority of the poorest peoples !!!

  ReplyDelete
 13. ሰሚ ያጣ ጩህት...

  በጣም የሚገርመኝ ብዙ ሰወች አድሮ መገኘትን እንደትልቅ ስኬት የመቁጠራቸው ነገር ነው::ለውጥ በሌለበት ህይውት ውስጥ : አድሮ ቃሪያ በሆነ ቀመር 'ነገን' ያለፈውን ነገር መፈወሻ መድህኒት አድርጎ በጉጉት መጠበቅ ከየዋህነት የራቀ ጅልነት ይመስለኛል::ነገ የተሻለ ቀን የሚሆነው : በዛሬ አስተሳሰባችንና አድራጎታችን ምክንያት ነው:: ዛሬ የሚመጥነን ኑሮ ኖረን ለመገኘት/ለማለፍ እና 'ነገን' የተሻለ ሆኖ ለማግኘት: ዛሬ ላይ መክፈል ያለብንን ዋጋ መክፈል ግድ ይለናል::ዋነው ነገር ዋና ማድረግ ያለብንን ነገር ዋና አድርጎ መገኘት ነው::

  ዳኒ..እግዚአብሄር እውቀትን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 14. "Eyawazu bizu" message! Nicely Written Dani, tnxs very much. I enjoyed reading it.

  ReplyDelete
 15. Dear All
  I am living abroad, I am hearing how life is difficult from my families. But I was thinking as it is normal dihnet. But now when you express it I feel bad , my heart broken. I am seeing every one gada by their comments... Oh God what can I do ?

  Melakm ken

  ReplyDelete
 16. if u write it from the heart and from the purest side of ur mind,history will remember u for it.but if u write wat the people want to hear,u may or may not be standing on the right side of the balance because people may or may not thank meles.if they do thank him history will remember more of meles than u.

  ReplyDelete
 17. weye Dani endewe men ladergehe ..........tebareke!!!

  ReplyDelete
 18. «ለሀብታሙ የቢራ ዋጋ ሲወጣለት ለድኻው ደግሞ የጠላ እና የጠጅ ዋጋ መውጣት ነበረበት፡፡ የዋጋ አወጣጡ ድኻውን እና ገበሬውን ማዕከል ያደረገ አይደለም፡፡»

  I feel the pain. I hope God will visit all especially the poor.

  I don't understand why the Ethiopian government waste the poor country resources to control bear price (የቢራ ዋጋ) other governments impose more tax to discourage people. Who knows some people(ሀብታሙ) drink ቢራ for water replacement.

  ReplyDelete
 19. what happened in egypt & tunisia must happen here..

  ReplyDelete
 20. The problem in our country is to talk instead of thinking about the solution. Unless we stop talking and teret and start thinking about our development,,,,,,how can solutions come?

  ReplyDelete
 21. America's Other Most Embarrassing Allies
  Maintaining good relations with autocrats is an unfortunate but often necessary component of the delicate balancing act that is U.S. foreign policy. But as Washington learned once again this week, supporting a strongman for the sake of stability can present risks of its own. Here are eight more alliances that could prove embarrassing.
  http://www.foreignpolicy.com/articles/2011/01/31/americas_other_most_embarrassing_allies?page=0,0
  Hosni Mubarak has plenty of company.

  SAUDI ARABIA

  Leader: King Abdullah

  YEMEN

  Leader: Ali Abdullah Saleh

  JORDAN

  Leader: King Abdullah II

  ETHIOPIA

  Leader: Meles Zenawi

  UGANDA

  Leader: Yoweri Museveni

  UZBEKISTAN

  Leader: Islam Karimov

  KAZAKHSTAN

  Leader: Nursultan Nazarbayev

  VIETNAM

  Leader: Nguyen Tan Dung

  ReplyDelete
 22. በመጨረሻ ሕዝቡ ተስፋ ቆረጠና ተመስገን አለ፡፡ ይኼው ተመስገን ማለት ሲጀምር ዋጋው ቀነሰ፡፡ «ለካስ ሰው ሲጠላም እድሜ ይለምናል» አለ ንጉሡ፡፡ እናም ጥፋቱን ሁሉ አርሞ ችግሩን ሁሉ አሻሻለው ይባላል፡፡ Thanks to God

  ReplyDelete
 23. ቅማንትህ ሲሞቱ ጤፍ አንድ ብር ነበር
  አያትህ ሲሞቱ ጤፍ አሥር ብር ነበር
  አባትህ ሲሞቱ ጤፍ መቶ ብር ነበር
  አንተ ስትሞት ግን ጤፍ ሺ ብር ተሸጠ
  ጎበዝ እንዳንተ ነው ችግር ያመለጠ
  D/n Dani thanks it explain the current situation of our country.
  Hailemeskel Maputo.

  ReplyDelete
 24. Dany i'm ur new fan .i like this blog .it is well written and reflect the people view.thanks and keep it up.

  ReplyDelete
 25. Thank you Dani for sharing us the issue in a nice way bringing it to our attention, though it is our daily life. But still putting the problem in beautiful language/literature is not a solution after all.
  We have to take action NOW!!!
  Above all, we have to bring the issue before God, He's got the solution for every problem.
  Let's all Pray unto God, in our own respective beliefs. Lets pray for Meles and all the other higher officials,to bless them, to soften their heart and give them the wisdom to Lead the country. 'Cause,Cursing is no good.
  May God Bless our Ethiopia!

  ReplyDelete
 26. AG:
  YOUR ARE SO DEAR DANI GOD BLESS U MORE THAN THIS!

  ReplyDelete
 27. AGE:

  YOUR ARE DEAR ALWAYS MAY GOD BLESS U MORE THAN THIS

  ReplyDelete
 28. I am always read your articles. It always touches my heart. Dani may God bless you and allow you to live long.

  From Birhanu Aberra- B/Dar

  ReplyDelete
 29. neger be misalea endilu abatochachen ewonetime bemisalea yigebale min alebatim ke nuro wodenet gar bedereke ababale bibeger noro manim baletewatelet neber eyawazu gin aworaredenewo,,,,, selehulum esu bemiheret ayenochu yimeleketen

  ReplyDelete
 30. so enjoyable and informative!!

  ReplyDelete
 31. It is so interesting because it techs the stress of all Ethiopian people .this is by itself can be an indicator to find solution.but jut like this try to put method solving.I wish all good thing for good work to u.so please go on!

  ReplyDelete
 32. ewnetehen eko new.yebase ayemta blo metseley yishalal

  ReplyDelete
 33. "Tenorena temote" alech yegna sefer kebero ewnetwan new enga noren sayon anuanuaren new yemebalew

  ReplyDelete