Thursday, February 3, 2011

የኔ የተለየ ነው


በጋብቻ ጉዳይ የተነሣውን ጉዳይ እያየሁት ነው፡፡ ችግሩ ካለመዋደድ እና ከችግር የሚመጣ ብቻ አይደለም፡፡ ስለ ጋብቻ ካለው ትምህርት እና ከሚነገረው ጭምር ነው፡፡ ጋብቻ ለምለም ገነት፣ እንከን አልባ ጉዞ፣ የሚያጓጓ ሕይወት ተደርጎ ብቻ ይነገራል፡፡
በውስጡ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች አይነገሩም፡፡ ችግሮችንም እንዴት መፍታት እንደሚቻል ትምህርት አይሰጥም፡፡
ለምሳሌ የኛን ቤት የሚመሩት አንድ ባሕታዊ ናቸው፡፡ ለምሳሌ እኒህ ባሕታዊ ሱባኤ ካዘዙ ሦስት ወር ሆኗቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት እኔና ባለቤቴ በአልጋ ከተለያየን ሦስት ወራችን ነው፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ይታይህ፡፡ በሰባቱ አጽዋማት፣ ቅዳሜ እና እሑድ፣ እሷ በምታከብራቸው አሥራ ሁለት በዓላት እንደገና ባሕታዊው በሚያዙት ሱባኤ ምክንያት እኔና ባለቤቴ አብረን ከምናድርበት እርሷ ገዳም የምትዞርበት ጊዜ ይበልጣል፡፡
እንዴት ነው ግን ሰው በየቀኑ ራእይ ያያል እንዴ፡፡ ደግሞስ ሁሉም ሱባኤ ባልና ሚስት ማለያየት ብቻ ነው እንዴ፡፡ ጓደኞቻችን መከሩን፣ የንስሐ አባታችን መከሩን፣ ወላጆቻችን መከሩን፤ እርሷ ግን ከኒያ ባሕታዊ በቀር የምትሰማው የለም፡፡
ልጆቼ እንኳን በሱባኤው ምክንያት ሥጋ እና ዕንቁላል መብላት ካቆሙ ቆዩ፡፡ ለመሆኑ አንድ ባሕታዊ በሚያዘው ሱባኤ አሥር ዓመት ያልሞላቸው ልጆች መጎዳት አለባቸው?
ልመሆኑ ባል እና ሚስት በሁሉም በዓላት እና ሱባኤዎች ሁሉ መለያየት አለባቸው? ፈተናውስ ይቻላል? እኔ በሁለት ነገር እየተፈተንኩ ነው፡፡ በአንድ በኩል ውስጤ ይፈተናል፤ በሌላ በኩል በትዳራችን ሌላ ሰው ማዘዙ ያናድደኛል፡፡ ልክ ነው ባለቤቴ ዝሙት ትፈጽማለች ብዬ አላምንም፡፡ ግን እርሷ ደንበኛውን የባል እና ሚስት ግንኙነትም ትታዋለች፡፡ ታድያ ምን ትላታለህ?
ይኼይስ ከናዝሬት

15 comments:

 1. Dn. dani! Ayadres newe!!!!! Bewnet yetemiheret etret newe. Betam yemiyasgermew gin, telat seitan hulunim tidar yemiyafersbet lehulum mela ena zede magngetu newe. Kzihe wotimed yemiyamelt man yihon??? Yale Egziaabhere erdata, ersu kemisetew tibeb wuchi mashenefis yichal yihon?????? Bizu linimekerbet yemigeba tilik reas newe. Menfesawi agelgai abatoch ena wondimoch, endihum balemuyawoch hasab situn.

  ReplyDelete
 2. Egziabher Betidarachihu yigba.
  All i want to say is that You have to talk to your wife and give her the ultimatum. You should say that you don't mind involving church fathers in the problems that you have but let's not make it too much. But i want to be honest with you some husbans are not as respectful as the wives are when it comes to church fathers. Are you one of them? Just asking. If not, your wife should listen to your concerns and you two should work this out. God Be With You!!! Atlanta.

  ReplyDelete
 3. Spritual fathers advise should be respectd. But i donot think this "bahetawe" is our church father. Our true church fathers are those whose advise is peacefull and easy. This "bahtawe" might have some hiden agenda. sorry to say but better to keep her apart from him.

  may God safe your marriage

  ReplyDelete
 4. dear brother
  I prefer if you keep your name hidden. this is your privacy and no need to make it public with your name.

  and I agree with the advise forwarded above
  may God keep your marriage

  ReplyDelete
 5. "ጋብቻ ቅዱስ ነው መኝታውም ንጽሁ"...."የተቀደሰ መኝታ "ይህን ቅዱስ ቃል ሰዎች እንዴት እንደሚያዩዩት ንዳንዴ ግራ ይገባኛል።ጋብቻ ደካማ ለሆነው ስጋችን አጋዥ ሆኖ ወደ ፅድቅ የሚያደርሰን መንገድ እንጂ።በራሱ ጋብቻ ፈተና ወይም ከጽድቅ የምንወጣበት እንዲሆን አልነበረም።ትዳር ያለው ሰው በምኞት እንዲቃጠል አልነበረም ጋብቻ የተመሰረተው። ወንድሜ ወንጌል ያላዘዘንን እያደረግን በራሳችን ላይ መከራ የምናመጣ ከሆነ ፈተና ሲገጥመን እግዜር ምን አረኩት ማለት አይቻልም። ባለቤትህ ወንጌል ከሚያዘው ውጪ ከእግዚአብሔር ቃል ባልሆነ በባህታዊ ምክር እምትመራ ከሆነ ይህ ጥሩ አደለም። አንዳንዴ ሰዎች ባላገባሁ እያሉ የሚመረሩት ወይም ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል መኖር የሚፈሩት መታሰር ሰለሚመስላቸው ነው። መታሰር የሚመስላቸው ነው።እግዚአብሔር ካዘዘው ውጪ በራሳችን በንሸከማቸው ሸክሞች የእግዚአብሔርን ህግ ከባድ እናረገዋለን። እርሷ ከባህታዊው ካልተላቀቀች ወደፊት የባሰ መከራ እንዳያገኝህ እፈራለሁ ለራሳቸው ጥቅምሲሉ እግዚአብሔር ካዘዘው ውጪ ባህታዊ በመምሰል ለራሳቸው ጥቅም ይሚኖሩ አስመሳዮች ባህታዊያን አሉ እውነተኞች ባህታዊያን ግን እንዲህ አይድሉም። ስለዚህ ትዳርህን ለማዳን በጣም ትልቅ ጥረት ብታረግ ጥሩ ይመስለኛል። ትዳር ማለት ደስ የምንሰኝበት ተነጋግረን የምንስማማበት ምንም ያለእግባባት ቢመጣ በመጨረሻ ግን ወድ መስማማት ይምንደርስበት ካልሆነ ያለመግባባት እየሰፋ ሲመጣ መለያየት ይመጣል። ካሁኑ ልዩነቱን ለማጥበብ ጥረት አድርግ። እግዚአብሔር ይርዳህ። ‹ሚሚ›

  ReplyDelete
 6. አይይ.. ምን ይደረጋል? መንፈሳዊ ሲኮን ስለ ስጋ ማሰብ ሀጢአት ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ትዳርን ባልመሰርተ ነበር።ብዙ መንፈሳዊ ነኝ ባዮች ጾታን በተመለከተ ማሰብ፣ መማር፣ ሀጢአት የሚመስላቸው አሉ።ትዳር ወስጥም ሲገቡ ነጻ ሆነው መኖር የማይችሉ ብዙ ናቸው። እግዚአብሔር እኮ ጥብብ እና አእምሮ የሰጠን እንድናስብበት እንጂ። ሰዎች እንደፈለጉ እንዲመሩን አይደለም። እንዳንተ ትዳራቸው ፆታዊ ግንኙነትን በተመለከተ ብዙ ፈተና ብዙ ናቸው። በዛ ምክንያት ትዳራቸው የሚፈርስም አሉ።ችግራቸውን ለመናገር ያፍራሉ ይፈራሉ። ከዛ ይለያያሉ። ምክንያቱም እንዴት ብለው ያወሩታል ለነሱ ጾታዊ ግንኙነት ሀጢአት ነው።?።እሷን ከባህታዊው ካልለየሀት መፍትሔው ቅርብ አይሆንም።ወይ መመንኮስ አለበለዚያ ትዳርን በስረአት መያዝ መንከባከብ።

  ReplyDelete
 7. wendime beewunete asitemari nawu hiwotehe gine ena endamimesilagne tidare memesirete yeemiyasifaligawu wanawu kumi nagire besiga fetote lalemafitene nawu ,tadiya yihane yahile gize kebalabetehe gare kalitadeseitike ateyayaki yimasilagnale,beta kiresitiyanachine yemitimarabete yerasuwa dogima ena kinona alate,ename ena esekimawukawu direse ke abiye tsome ena filseta bisetaqere balina misete aliga yilau yimil hige menorune alasitawusem silazihe yenabise abatihen mekire meqabale yishalihale mikiniyatume bahitaweyan yete endaminoru yitawekale enasu alemine titawu niqawu nawu gedame yegabute mini alibatem bealamawewu wusite yaliwune fetena layiradute yichilalu silazihe ketalalaqe abatoch gare giltse wuyeyete yasifelgale bayi nagne

  ReplyDelete
 8. አንደምን አለህ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የዘወትር ሠላምታዬ ይድረስህ።

  ያአነሳሀው ርዕስ በጣም ወሳኝና የብዙዎቻችንን ቤት የሚዳስስ ነው፡፡ በመሆኑም እጅግ አድርጌ ላመሰግንህ እወዳለሁ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ እድሜና ጸጋውን ሁሉ ያብዛልህ፡፡

  1. ሌላው በአንድ ወንድሜ እንደተጠቀሰው በቤተስብ ምጣኔ ዙሪያም መነጋገር አለብን ብየ አምናለሁ፤ የልጅ አወላለድ የመራራቅ ክፍተትና ብዛትን በተመለከተ የብዙዎቻችንን ትዳር÷ ምጣኔ ሀብት÷ ክርስትናና ማኅበራዊ ሕይወት እየፈተነበት ያለ ትልቅ ጉዳይ ነውና፡፡
  2. አሁን በአነሳሀው ርዕስና በቀረቡት የወገኖቻችን ገጠመኞች እንዲሁም ወደፊት በምናነሳቸው መሰል ርዕሶች ላይ የሚመለከታቸው (በቤተክርስቲያንም በዓለሙ ጥበብም ያሉ) ባለሙያዎችን አስተያየት በመጠየቅ እንዲካተት ብታደርግ ዝግጅቱ የበለጠ አሳታፊ መልሱም/አስተያቱም በጥበብ የታሸ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በዙዎቻችን አንተ ተብለን ተጠይቀን ማንነታችን በታወቀ መልኩ መልስ/አስተያየት ካልሰጠን በቀር በእንዲህ መሰሉ የጋራ መድረክ ለመሳተፍ ገና ልምዱ ይቀረናልና በዚህ ረገድ ሥራ/ድካም እየጨመርኩብህ እንደሆነ ቢገባኝም የአንተን አሳለጭነት(ፋስሊቴተርነት) ይጠይቃል፤ ሌሎቻችንም በዚህም ረገድ የችልንውን እናድርግ፡፡

  በሌላ አስተያየት፡- ‹‹የኛን ቤት የሚመሩት አንድ ባሕታዊ ናቸው፡፡ ለምሳሌ እኒህ ባሕታዊ ሱባኤ ካዘዙ ሦስት ወር ሆኗቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት እኔና ባለቤቴ በአልጋ ከተለያየን ሦስት ወራችን ነው፡፡›› የሉት ተሳታፊ ላይ ያየሁትን÷የማውቀውን እና በጣም ያሳዘነኝን ታሪክ ለመጨመር ነው የባሰም አለና፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤ በደብረ ታቦር ከተማ (ደቡብ ጎንደር) አንድ ‹‹ባህታዊ›› በሰጠው ትዕዛዝ በገዳማት ያሉ መነኮሳት እየተራቡ ይህ ንብረት ለእናንተ ምናችሁ ነው የተባለች እማወራ የቤት እቃዋን ሁሉ ሽጣ አራት ሕፃናት ልጆቾን ያለቤት እቃ/ያለጥሪት አስቀርታለች፡፡ በዚህ ያላበቀው የ‹‹ባህታዊው›› ‹‹አባተዊ›› ምክር አንቺ የዚህ ዓለም ሰው አይደለሽም ትዳር ለአንች ተገቢም ቦታሽ አይደለም ተገልጦልኛል ተብላ ባለቤትዋን÷አራት ልጆቾን እና ቤትዋን ትታ ገዳም ገብታለች፡፡ ከብዙ ድካም ÷ ፍለጋና ቀናትም በሁዋላ ባለቤትዋ ቢያንስ ቢያንስ በቅርብ ሁና ሕፃናት ልጆቾዋ ሲናፍቁብኝ እያመጣሁ እንዲያዋት ብሎ ለምኖ አምጥቶ፤ እርሱ ሕፃናት ያሳድጋል፤እርስዋ ደብረታቦር ኢየሱስ ‹‹መንኩሳ›› ተቀምጣለች፡፡
  ለመሆኑ ይህ ይገነባሉ የተባሉ አባት ተብየዎች እየናዱ÷ ያሰራሉ የተባሉት እያፈረሱ የሚኖሩት እና ቤተክርስቲያናችንስ በጥባጩንም ተበጥባጩንም በጉያዋ እንዳቀፈች እና እንደማታውቅ በመምሰል በእንዲህ ዓይነት መንገድ በሕሊና ታስረው መግባት ወደሌለባቸው ሕይወት እየተወረወሩ ያሉትን ወገኖች እየተቀበለች የምታስተናግደው እስከመቼ ድረስ ነው÷ የጥፋቱ ሰለባዎች የወደፊት እጣፈንታስ÷ በዚህ ዙሪያስ የእኛ ድርሻ ምን ሊሆን ይችላል፡፡

  ReplyDelete
 9. እግዝአብሔር በትዳራችሁ ይገባ ዘንድ ፀልዩ፡፡ ለባለቤትህም ልቦና ይስጣት፡፡

  ReplyDelete
 10. Ergfe aderghe tewate

  ReplyDelete
 11. ወንድማችን ያለህበት ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ እንደ እኔ ከሆነ በትዳር ውስጥ ችግሮችን ለመፍታት ሌላ ሶስተኛ አካል ባይገባም እመርጣለሁ፡፡ እዚህ ላይ የአባቶች ምክር (የንስሐ አባት)፡ የወንድሞች የእህቶች ምክር ጸሎት አያስፈልግም ማለቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች በማያገባቸው ሁሉ ጥልቅ የሚሉ አሉ (አንዳንዶቹማ ማንም ለምክር ሳይጠይቃቸው ነው)፡፡ ሚስትህ እንደዚህ ናት እሷኮ ዝም ብላ ነው የሚሉ አሉ፡፡ አንቺ ደግሞ እሱ ጋር ለምን ትሟዘዧለሽ ይሉናል፡፡ በሚስት ወንድም ወይም እህት ስንት ትዳር ተመሰቃቅሏል፡፡ በባልም እንዲሁ፤ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡- በትዳር ውስጥ ኑሮውን የሚኖሩት እነርሱ ተጋቢዎቹ ሳሉ ለምን ሁሌም ጥልቅ እንላለን?

  ያንተ ችግር ከባሕታዊ (ሶስተኛ አካል) የመጣ መሆኑ እኔን ያሳዝነኛል፡ ቤ/ያን ፣ ወደ የእምነት አባቶች በመሄድ ሰላም እናገኛለን ብለን ስናስብ እንደዚህ አይነት ችግር ሲገጥመን ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ግራ ይገባናል፡፡

  ጥቂት ነገሮችን እዚ ላይ ማለት እፈልጋለሁ

  1) ትዳር ፈተና እንዳለሁ ሁሌም ማሰብ
  አንተም በመግቢያ ላይ እንደገለጽኸው ጋብቻ ለምለም ገነት፣ እንከን አልባ ጉዞ፣ የሚያጓጓ ሕይወት ተደርጎ ብቻ ይነገራል፡፡ ይህ ስህተት ስለሆነ በትዳር ውስጥ ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማሰብ እና በመመካከር ለመፍታት መሞከር፡፡

  2) ቤ/ያን ስለትዳር ስለ ቤተሰብ ምንነት ተጋቢዎች ከመጋባታቸው በፊት ልታስተምር ይገባታል፡፡ ከተጋቡም በኃላ በየጊዜው በምክር በመንፈሳዊ ተጋድሎ እንዲበረቱ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ቤ/ያናችን የሚጠብቅባት ሠርታለች ለማለት ትንሽም አልደፍርም፡፡ ለዚህም ነው ብዙ የክርስቲያን ጋብቻዎች በፍርድ ቤት የምንመለከተው፡፡ በቀላሉ ሊስተካከሉ የሚችሉት ሁሉ፡፡

  3) ከንስሐ አባቶች (እና “መካሪ ነኝ” ከሚሉ ሰዎች) ብዙ መገንዘብ የሚገባቸው ነገሮች ያሉ ይመስለኛል፡፡ በመጀመሪያ ተጋቢዎቹ ያሉበትን ሁኔታ፣ ቀጥሎ በትዳራቸው ውስጥ የተፈጠረውን ችግር በደንብ ማወቅ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ከሁለቱም ተጋቢዎች ወገንታዊነት ሳይፈጠር መስማት ደግሞ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ አንተ ችግር ስመጣ የሚከተለው ሃሳብ አለኝ፡-

  እኒህ ባሕታዊ መልካም ነገርን ያደረጉ አይመስለኝም፡ እሷም ሙሉ በሙሉ የሰውን ምክር መቀበል ያለባት አይመስለኝም፡፡ ከሰው የምንቀበለውን ማንኛውንም ምክር በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ ልንመረምር ይገባል፡፡ እሷ ደግሞ በትዳር ውስጥ ስለሆነች ትዳሯንም ማስቀደም ይኖርባታል ባይ ነኝ፡፡ ይህንንም ያልኩበት ምክንያት አንደኛ ችግሩን ለምን እሷ ብቻዋን ለመወጣት ትሞክራለች? አንተ እኮ የትዳር አጋሯ ነህ፤ በችግር ፡ በመከራ ጊዜ ባንድነት ሆናችሁ ችግሩን መፍታት እንደምትችሉ ማመን አለባት፡፡ ከዚህ አንጻር ስመለከተው፡ በእምነት እና በንጽሕና እግዚአብሔር በየትኛውም ቦታ ከለመንነው የለመንነውን አያሳጣንም፡፡ ፆሙ ለቤታችሁ አስቸጋሪ ከሆነ በጸሎት በጋራ እግዚአብሔርን መለምን የሚቻል ይመስለኛል፡፡ እሷ ባሕታዊውንም ሆነ የንስሐ አባትን በምትገናኝበት ጊዜ አብረሃት በመሆን አለሁልሽ ይህንን በጋራ እንወጣዋለን ልትላትና ልትደግፋት ይገባል (እያደረግክ ካልሆነ)፡፡ እሷም ደግሞ ካንተ በሱባኤ ምክንያት በምትለያይበት ጊዜ በትዳሯ መካከል ችግርን እየፈጠረች መሆኑን ልትገነዘብ ወይንም ሊያስገነዝብ የሚያስፈልግ አካል መኖር ያለበት ይመስለኛል፡፡ እኒህ ባሕታዊ ደግሞ በዚህ ረገድ መልካም ሥራን ሊሰሩ ይገባ ነበር፡፡ ለምሳሌ ባለቤትሽ እንዴት ነው? በጸሎት በሃሳብ ካንቺ ጋር ነው እንዴ ብሎ መጠየቅ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አስፈላጊ ሆኖም ከተገኘ ቤተሰብህን በመጎብኘት ችግሩን መመካከር፡፡ ለቤተሰብ ፈታኝ መሆኑን የሚረዳ ሰው ቀኖናን እዛው እናንተ በምትኖሩበት ቦታ ማድረግ ከባድ አይመስለኝም፡፡ ስለ ፍትሐ ነገስት ብዙም ባለውቅም፤ በሱባኤ ጊዜ እራሱ ባልም ሆነ ሚስት በዝሙት ተፈትነው ከሌላ ጋር እንዳይወድቁ ተለያይተው ይተኙ ከነበር ባንድነት መተኛትን የሚፈቅድበት አጋጣሚ አለ፡፡

  ብዙ አሳሳች ባሕታዊያን እንደማይጠፉም ልትገነዘቡ ያስፈልጋል፡፡

  እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ በጸሎት በርታ፡ ሁልጊዜም በጋራ ተመካከሩ፡፡

  ReplyDelete
 12. Paule be bible lay yeminagerew teru merega meselegn. esum, balena mist le tselot HULETUM tesemametew ke wesib genugnenet metakeb yechelalu keza beterefe yebal gela ye mist yemist gela ye bal selehone eres beresachew AYEKELAKELU yelal. endiya kehone befetena mewedek selemimeta maletu new.
  selezih egnh "bahetawi" ke kedus metshafu yemikaren neger selalu hasabun wedek aregeh menalebat be megemeriya le balebeteh negerat embi kalech demo lemimeleketew kefel masawek malete esua letesemachew wedemetechelachew sewoch mehedu yeshalal. "bahetawiwinem" kebelay akal gar betagenagnachw teru meselegn and yehen tezaz keyet endametut beteyeku teru new yesewen tedarkemafatatachew befit.

  ReplyDelete
 13. Pleae take care. Who is that Bahitawi? Where did he live? what is he doing? You may easily judge him whether he is spritual or not from his words and actions. Don't trust all bahtawies. There are many bad incidents with bahitawies. He does't look good father. Discuss the problem with your wife. Tel also your problem to him separetly. If he don't want to understand and hear your problem, tell him not come to your house.

  ReplyDelete
 14. ya,what i will do is i will not accpet that called him self Baha'i-God knows your heart, we are weak,whatever,there is only one way it is the marriage that protect us from sin,don't accept at all,decide by your self!
  Bible said-"every one is sinner!"-so are u trying to be perfect human being,just settle the love in your family and house,then follow GOD~! God may help and Bless your family Brother!

  ReplyDelete
 15. መፍትሄው ሙስሊም መሆን ነው!!!

  ReplyDelete